Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
رفتن به کانال در Telegram
نمایش بیشتر
2 356
مشترکین
+2424 ساعت
+987 روز
+37730 روز
آرشیو پست ها
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት የተቋሙን የ6ወር አፈፃፀም እና የEASE ፕሮጀክትን እስካሁን ተደረሰበትን አፈፃፀም ሪፖርት ለኮሌጁ ማህበረሰብ ቀርቦ ውይይት ተካሄደ::
መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸውም እንደ ተቋም ከዚህ አመት ጀምሮ በርካታ ዘርፈብዙ ስራዎችን ለማከናወን የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅዶችን በመንደፍ ወደተግበራ መገባቱን አስታውሰው ይህ ውጤታማ እንዲሆንም የኮሌጁን ማህበረሰብ የነቃ ተሳትፎን ከመቼው ጊዜ በላይ የሚጠይቅ ወቅት በመሆኑ ሁሉም አካል በዚህ አግባብ ተነሳሽነት በማሳይት ተልኮን መፈፅም እንደሚገባም ገልፀዋል::
በእለቱ በተካሄደው መድረክ የኮሌጁን የ2017 በጀት አመት የ6ወር አፈፃፀም ያቀረቡት የኮሌጁ የእቅድና በጀት ስራ ክፍል ሀላፊ አቶ አለማየሁ ብርሃኑ ሲሆኑ በቀረበው ሪፖርትም ኮሌጁ የበጀት አመቱን ትግበራን ከጀመረበት የዝግጁነት ምዕራፍ ወቅት አንስቶ በ6ወር ውስጥ የነበረውን አጠቃላይ ንቅስቃሴ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን አክለውም ኮሌጁ እስከ በጀት አመቱ መጠናቀቂያ ድረስ ለትግበራ በእቅድ የያዛቸውን ተግባራት ለመድረኩ ተሳታፊዎች አመላክተዋል::
በመቀጠል የEASE ፕሮጀክት ወደ ትግበራ ከገባበት ጊዜ አንስቶ የተከናወኑ ስራዎችን አፈፃፀም ሪፖርት በEASE ፕሮጀክት የሞኒተሪንግና ኢቫሉዌሽን አስተባባሪ ኢንጂነር ህይወት እሸቱ አማካኝነት ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በቀረበው አፈፃፀምም የፕሮጀክቱን ባለሙያዎች ከማዋቀርና የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪንግ ቦርድ ከማቋቋም አንስቶ የፕሮጀክቱ አመራሮችንና ባለሙያዎችን በልምድ ልውውጥና ስልጠናዎች የማብቃት እንዲሁም 65 ለሚሆኑ የተቋሙ አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ መቻሉም ተገልፇል::
በተጨማሪም በቀረበው ሪፖርት በአስተዳደሩ ለሚገኙ የሚዲያ ባለሙያዎች እና የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አመራሮችና ተማሪዎች ስለ ዘርፉ ያለውን የተዛባ አመለካከት መቀየር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መካሄዱም በሪፖርቱ ከቀረቡት ነጥቦች የሚጠቀሱ ናቸው::
በመጨረሻም የEASE ፕሮጀክት የቀጣይ ስድስት ወራት እቅድ በፕሮጀክቱ አስተባባሪ ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ አማካኝነት ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በዚህም በቀጣይ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ለመፈፀም በእቅዱ ላይ የተመላከት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በተቋሙ የሪኢኖቬሽን ስራዎች ፣ የአሰልጥኞች ስልጠና፣ የኢንተርፕሩነርሺፕ ስልጠናዎች፣ የሴቶችን መደገፍና ማብቃት እንዲሁ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠዎችን ተግባራዊ ለማድረግ መያዙ ከብዙ ጥቂቱ መሆኑን በቀረበው እቅድ ተመላክቷል::
የመድረኩ ተሳታፊዎች በቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርትና የቀጣይ እቅድን መነሻ በማድረግ ለቀጣይ ትግባራት ውጤታማነት የሚረዱ ገንቢ እስተያየቶችና ምክረ ሃሳቦች በስፋት አንስተው ውይይት ተደርጎበት መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
የካቲት 1/2017 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት የመደበኛ ስራ 6ወር አፈፃፀምና የEASE ፕሮጀክት የሩብ አመት አፈጻጸምን ለኮሌጁ የቦርድ አባላት አቀረበ፡፡
የተቋሙን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የEASE ፕሮጀክት አፈጻጸም በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ለቦርዱ የቀረበ ሲሆኑ በዚህም ኮሌጁ ከዝግጅት ምእራፍ ጀምሮ በ6ወሩ ውስጥ የነበረውን የእቅድ አፈፃፀምና የተሰሩ ስራዎችን እንዲሁም የተገኙ ውጤቶችን የገለፁ ሲሆን አያይዘውም በቀጣይ በተቋሙ ሊሰሩ በእቅድ የተያዙ ስራዎችን ለቦርድ አባላት አቅርበዋል፡:
በመድረኩ የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግም የቦርድ አባላቱ ሀሳብ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በቀጣይ በሚኖረው እንቅስቃሴ ላይ ምክረ-ሃሳባቸውን አስቀምጠዋል::
በመጨረሻም የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በኮሌጁ እቅድ አፈፃፀም እንዲሁም በፕሮጀክቱ ትግበራ አፈጻጸም ላይ ማጠቃለያ እና የቀጣይ ስራ አቅጣጫና መመሪያም ሰጥተዋል፡፡
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥር 30/2017 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት የሩብ አመት አፈፃፀምና የቀጣይ ስድስት ወር እቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ::
በዛሬው እለት በተካሄደው መድረክ የEASE ፕሮጀክት ወደ ትግበራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ እስከ እሁን የነበረውን የአፈፃፅም ትግበራ እንዲሁም በፕሮጀክቱ የቀጣይ ስድስት ወራት እቅድን መነሻ በማድረግ ከፕሮጀክቱ ኢንዱስትሪ እድቫይዘሪንግ ቦርድ አባላት ጋር የውይይት መድረክ በሀረር ተካሂዷል::
መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸው እንደገልፁት ምንም እንኳን የEASE ፕሮጀክትን ወደ ትግበራ ከገባ አጭር ጊዜ ቢሆንም እስካሁን በደረስንበት አፈፃፀም መሰረት ወቅቱን ጠብቆ ከባለድርሻ አካላት ጋር መወያየት አስፈላጊ በመሆኑ ይህን መድረክ ተዘጋጅቷል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም በመድረኩ በሚቀርበው የEASE ፕሮጀክት የቀጣይ ስድስት ወር እቅድ ላይ ከኢንዱስትሪው አኳያ ማካተት ሚገባንና የተዘነጉ ጉዳዮች ካሉ ከመድረኩ በሚገኘው ግብዓት መሰረት እቅዱን ለማሻሻል ተቋማችን ዝግጁ እንደሆነም ገልፀዋል::
የኮሌጁ ዲን አክለውም ይህ ፕሮጀክት ሲነደፍ እንደ ሀገር ማስመዝገብ የተፈለገው ውጤት እንዳለ ጠቅሰው በዚህም መሰረት Result Framework በሚኒስቴር መ/ቤቱ ፀድቆ ሲመጣ በፕሮጀክቱ ትግበራ ወቅት የኛ መመዘኛ እሱ ይሆናልም ብለዋል::
በፕሮጀክቱ የእስካሁን አፈፃፀም ሪፖርት በEASE ፕሮጀክት የሞኒተሪንግና ኢቫሉዌሽን አስተባባሪ ወ/ሮ ህይወት እሸቱ አማካኝነት ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በቀረበው አፈፃፀምም የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪንግ ቦርድ ከማቋቋም ጀምሮ የፕሮጀክቱ አመራሮችንና ባለሙያዎችን በልምድ ልውውጥና ስልጠናዎች የማብቃት እንዲሁም 65 ለሚሆኑ የተቋሙ አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ መቻሉም ተገልፇል::
በተጨማሪም በቀረበው ሪፖርት በአስተዳደሩ ለሚገኙ የሚዲያ ባለሙያዎች እና የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አመራሮችና ተማሪዎች ስለ ዘርፉ ያለውን የተዛባ አመለካከት መቀየር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መካሄዱም በሪፖርቱ ከቀረቡት ነጥቦች ይገኙበታል::
በመቀጠልም የEASE ፕሮጀክት የቀጣይ ስድስት ወራት እቅድ በፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ፋሲል ማዘንጊያ አማካኝነት ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በዚህም በቀጣይ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ለመፈፀም በእቅዱ ላይ የተመላከት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በተቋሙ የሪኢኖቬሽን ስራዎች ፣ የአሰልጥኞች ስልጠና፣ የኢንተርፕሩነርሺፕ ስልጠናዎች እንዲሁ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠዎችን ተግባራዊ ለማድረግ መያዙ ከብዙ ጥቂቱ መሆኑን በቀረበው እቅድ ተመላክቷል::
የመድረኩ ተሳታፊዎች በቀረበው የፕሮጀክቱ አፈፃፀምና የቀጣይ እቅድን መነሻ በማድረግ ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት የሚረዱ ገንቢ እስተያየቶችና ምክረ ሃሳቦችን በስፋት አንስተው ውይይት የተካሄበት ሲሆን ኮሌጁን ጨምሮ የኢንዱስትሪ እድቫይዘሪንግ ቦርድ አባላትም ለቀጣይ የየድርሻቸውን አሳይመንቶችን በመውሰድ መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥር 24/2017 ዓ.ም
ሀረር
Repost from N/a

ጥር 25/2017 ዓ.ም
ሀረር
በዲጂታል ላይብረሪ አገልግሎት ዙሪያ ለኮሌጁ የቤተ-መፃህፍት ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ተጀመረ።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዲጂታል ላይብረሪ አገልግሎት ዙሪያ በኮሌጁ ለሚገኙ የቤተ-መፃህፍት ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ስራ ሂደት ሀላፊና የኮሌጁ ም/ዲን አቶ ኤሊያስ አህመድ እንደተናገሩት የዲጂታል ላይብረሪ አገልግሎት ሰልጣኝ ተማሪዎች እንዲሁም የኮሌጁ ማህበረሰብ ንባብን እንዲያዘወትሩ በማድረጉ ረገድ ለሚደረገውን ጥረት ያግዛል ያሉ ሲሆን አክለውም ስልጠናው የመፅሀፍት ውሰትንና ንባብን በማዘመን የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚረዳ ጠቁመው ሙያዊ ስልጠናው የቤተ መፃህፍት ባለሙያዎችን እውቀትና ክህሎት በማጎልበት ረገድ የጎላ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።
በአውቶማይዜሽንና ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ እየተሰጠ ያለው ይህ ስልጠና ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በመጡ አሰልጣኞች የሚሰጥ ሲሆን አላማውም የቤተ-መፃህፍት አገልግሎትን በማዘመን ተደራሽነቱን ለማስፋትና አገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ ለማድረግ ያለመ መሆኑም ተገልፇል::
ስልጠናው ለቀጣይ ቀናት እየተሰጠ የሚቆይ ሲሆን በንድፈ ሃሳብና በኮምፒውተር የታገዘ የተግባር ስልጠናንም ያካተተ መሆኑ ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥር 20/2017 ዓ.ም
+1
እንኳን አደረሳችሁ!!
ለኮሌጃችን ማህበረሰብ እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን እያልኩ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የአብሮነት እንዲሆንልን እመኛለሁ::
#መልካም_የጥምቀት_በዓል!!
አቶ ታደለ አሰፋ
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን
ከጋንቤላ አፔኖ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና ከደቡብ ምዕራብ ቴፒ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተወጣጣ ልኡካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ልምድ ልውውጥ አደረገ፡፡
ኮሌጆቹ በነበራቸው የልምድ ልውውጥ ጉብኝት መርሃ-ግብር ወቅት የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ በEASE ፕሮጀክት ያለውን የላቀ አፈፃፀም ሂደት በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በተለያዩ ተግባራት እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎችም በኮሌጁ ዲኖች አማካኝነት ሰፋ ያለ ገልፃ ተደርጎላቸዋል::
ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ ባደረጉት ምልከታና የተደረገላቸው ገለፃን መነሻ በማድረግ በተካሄደው የጋራ ውይይት ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ አስደናቂ መሆኑን ገልፀው በተለይም ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት አተገባበር ላይ እያሳየ ያለው የላቀ አፈፃፀም ለሌሎች አቻ ተቋማትም ምሳሌ መሆን የሚችልበት የአፈፃፀም ደረጃ ላይ እንደሚገኝም በውይይታቸው ወቅት አንስተዋል::
በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የትምህርትና ስልጠና ክፍሎች እንዲሁም ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን እዚህ በኮሌጁ ያገኙትን በርካታ ልምዶችንም ቀምረው በመጡባቸው ኮሌጆች ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩም ገልፀዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥር 9/2017 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኘው የስራ አመራር ኢንቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከ ኢንቲትዩቱ ጋር በመተባበር እየሰራቸው ከሚገኙ ተግባራቶች በተጨማሪ ዘላቂነት ባለው መልኩ ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወን እንዲረዳ ሁለቱ ተቋማት የመግባቢያ ስምምነቱን ተፈራርመዋል::
የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የኮሌጁ ዲን እቶ ታደለ አሰፋ እንዲሁም የስራ አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አወቀ ለገሰ ሲሆኑ ስምምነቱም በአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፣በጥናቶች እንዲሁም በማማከር ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያለመ ሲሆን በቀጣይ በመግባቢያ ስምምነቱ መሰረት ወደ ትግበራ እንደሚገባም ትግልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥር 9/2017 ዓ.ም