Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
رفتن به کانال در Telegram
نمایش بیشتر
2 356
مشترکین
+2424 ساعت
+987 روز
+37730 روز
آرشیو پست ها
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአስተዳደሩ በሚገኘው የብስራተ ገብርኤል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት ለተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ጋር ተቀራርቦ በጋራ ለመስራት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው አለትም በብስራተ ገብርኤል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት ለተማሪዎች ግንዛቤን የመፍጠር ስራ ሰርቷል::
የግንዛቤ ማስጨበጫውን ለት/ቤቱ ተማሪዎች የሰጡት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ታደለ አሰፋ እንዲሁም የኮሌጁ የኢ/ኤ/ቴ/ሽ/አ ስራ ሂደት ሀላፊና የኮሌጁ ምክትል ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ በመድረኩም ተማሪዎቹ ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያላቸውን የተዛባ አመለካከት የሚቀርፍና የቴክኒክና ሙያ ነባራዊ ሁኔታን በግልፅ በሚያሳይ መልኩ በመተንተን ዘርፉ ለተማሪዎቹ የሚያስገኘውን ምቹ አጋጣሚ ሰፋ ባለ ማብራሪያ ገለፃ ያደረጉላቸው ሲሆን ተማሪዎች የነገ መዳረሻችውን ከዚሁ ትኩረት ሰተው በጥንቃቄ መምረጥ እንደሚገባቸውም ምክር ለግሰዋል::
እንዲሁም በአዲሱ ፖሊሲ መሰረት የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰጡ የሙያ ስልጠናዎችንም አያይዘው የሚሰለጥኑ በመሆኑ በዘርፉ የሚሰጡትን የስልጠና አይነቶች ቀድመው በግልፅ እንዲረዷቸው በማድረግ ካላቸው ዝንባሌ ጋር የሚጣጣም የስልጠና አይነትን ምርጫቸው እንዲያደርጉ የሚረዳቸውን ግንዛቤ ማግኘትም ችለዋል::
በተጨማሪም ከት/ቤቱ ጋር የጋራ ስምምነት ሰነድ በመፈራረም እንዲሁም በት/ቤቱ የቴክኒክና ሙያ ክበብ በማቋቋም ተማሪዎቹ ላይ ሰፊ የግንዛቤ ስራ እንደሚሰራ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም የቴክኖሎጂ ፈጢራ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች በመለየት ከኮሌጁ የሚያስፈልገውን ድጋፍ እንዲያገኙ የሚደረግ መሆኑም ተገልፇል::
የግንዛቤ ማስጨበጫው በት/ቤቱ ለሚገኙ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የተሰጠ ሲሆን በዚህም ለ92 ሴት እና ለ80 ወንድ በድምሩ 172 ለሚሆኑ የት/ቤቱ ተማሪዎች ስለ ዘርፉ ግንዛቤ የተፈጠረበት መድረክም ነበር::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም
በኢንዱስትሪዎች ላይ የሚታየውን የሙያ ደህንነትና ጤንነት አስተዳደር ባለሙያዎች እጥረት ለመቅረፍ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ::
በዛሬው ዕለት በአስተዳደሩ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሲሰጥ የነበረው የሙያ ደህንነትና ጤንነት አስተዳደር (OSH) ስልጠና መጠናቀቁን ተከትሎ ለሰልጣኞች የሰርተፍኬት መስጠትና የተመደቡበትን ኢንደስትሪ ዕጣ የማውጣት ፕሮግራም ተካሄደ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንደገለጹት ቢሮው በኢንዱስትሪዎች ላይ የሚታየውን የሙያ ደህንነትና ጤንነት አስተዳደር ባለሙያዎች እጥረት ለመቅረፍ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑና በዚህም የመጀመሪያ ዙር ለአርባ አምስት ቀናት በተሰጠ ስልጠና ሰላሳ አንድ ሰልጣኞችን ማሰልጠን መቻሉን ተናግረዋል::
የቢሮው ም/ኃላፊ እና የቴ/ሙ/ት/ስ ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ይህ የተሰጠው ስልጠና ኮሌጆች ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን የሰው ሃይል በማፍራቱ ረገድ በቅንጅት እየተሰሩ ከሚገኙ ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን አንስተው ሰልጣኞች በስልጠናው የቀሰሙትን በስራው አለም በተግባር ውጤት እንዲያመጡ አሳስበዋል።
የአሰሪና ሰራተኛ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሀመድ ኢብራሂም በበኩላቸው በአስተዳደሩ ከየቀበሌው የተወጣጡ ተመርቀው ስራ ለሚፈልጉ ወጣቶች የስራ ዕድል ከመፈጠሩ ጎን ለጎን የሙያ ደህንነትና ጤንነት አስተዳደር ጋር በተያያዘ በኢንዱስትሪዎች ላይ የሚታየውን ክፍተት የመሙላቱ ተግባር በተመሳሳይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በቅንጅት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስረድተዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 7/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ስራ ሂደት አዲሱን እሳቤ እና የጥራት ስራ አመራር ስርዓት መሠረት አድርጎ በተከለሰው እቅድ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ::
በመድረኩ አዲስ በተከለሰው እቅድ ዙሪያ ተሻሽለው የመጡና አዲስ በተጨመሩ የአዲሱ እሳቤዎች እና የጥራት ስራ አመራር ስርዓት መነሻ በሆነው እቅድ ላይ ለትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል::
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው በዘርፉ አዲሱ እሳቤዎች ዓላማ ከሰው ሀይልና ቴክኖሎጂ ልማት አኳያ ያሉ ተግዳሮቶችን በመፍታት የታለመውን ጥራቱን የጠበቅና የተሟላ ስልጠና መስጠት እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑም ተገልፇል::
በመድረኩ በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሳታፊዎች በቀረበው የተከለሰ እቅድ ዙሪያ ያላቸውን አስተያየትና ምክረ-ሃሳብ በማቅረብ ሰፊ ውይይትም ተደርጎበታል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ጥር 5/2017 ዓ.ም
እንኳን ለ2017 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ::
በቅድሚያ ለኮሌጃችን ሰራተኞች እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል(ገና) በሰላም አደረሳችሁ እያልኩኝ በዓሉ የሰላም፣የፍቅር፣የጤና፣የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ በዓሉን ስናከብርም የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳትና ያለንን በማካፈል በዓሉን በበጎ ተግባር ማሳለፍ ይኖርብናል እያልኩ በድጋሚ በኮሌጁ ስም እንኳን አደረሳችሁ ማለት እወዳለሁ::
#መልካም_የገና _በዓል!!
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ ዲን
አቶ ታደለ አሰፋ
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት አማካኝነት ለኮሌጁ አስተዳደር ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው የሁለተኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከድሬዳዋ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ለመስራት በገባው ውል መሰረት ለ2ኛ ዙር ለኮሌጁ የአስተዳደር ሰራተኞች ለ5 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል::
የአቅም ግንባታ ስልጠናው በEASE(Education and Skills for Employ Ability) ፕሮጀክት አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን ይህ ስልጠናም በኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞች ሲሰጥ የቆየና በአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት እና በስራ ሥነ-ምግባር ላይ ያተኮረ ስልጠናም ነበር::
የስልጠናው ዋነኛ አላማ የኮሌጁ የአስተዳደር ሰራተኞች የተለያዩ የስራ ላይ ስልጠናዎችን አግኝተው አቅማቸውን እንዲገነቡና በተመደቡበት የስራ ዘርፍ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ለተቋሙ ራዕይና ስኬት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑን የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አክለውም ለስልጠናው ውጤታማነት የድሬዳዋ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት እያደረገ ላለው ትብብርም ምስጋና አቅርበዋል።
በ2ኛ ዙር ስልጠናው ማጠቃለያ መርሀ-ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይር ሀጂኑር አንደገለፁት ቢሮው ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች እና አመራሮችን በተለያዩ ስልጠናዎች አቅማቸውን መገንባት እንደሆነ ጠቅሰው ለዚህም ኮሌጁ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ለመስራት ውል ተፈራርሞ ወደ ትግበራ በመግባቱ አመስግነው ሰልጣኞችም የወሰዳችሁት ስልጠና በስራ ገበታቸው ላይ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል::
ኮሌጁ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ሲያደግና የተሰጠውን Resource ተፈፃሚ ለማድረግ አጠቃላይ የኮሌጁን ሰራተኛ ባስተፈ መልኩ በመሆኑ በEASE ፕሮጀክትም ቅድሚያ ትኩረት የተሰጠው ተግባር የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለሰራተኛው መስጠት እንደሆነ የገለፁት የEASE ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፋሲል ማዘንጊያ አክለውም በቀጣይ በዝርዝር የተለዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በተያዘላቸው መርሃ-ግብር ለሰራተኛው የሚሰጡ ይሆናልም ብለዋል::
የማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ ስልጠናው በአግባቡ ተከታትለው ላጠናቀቁ ሰልጣኞች ከእለቱ ክብር እንግዶች የምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው ሲሆን በቀጣይ ሶስተኛ ዙር ሰልጣኞችም ስልጠናውን የሚወስዱ ይሆናል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት አማካኝነት በተቋሙ በሚከናወኑ Building & Infrastructure Renovation ስራዎች ላይ ውይይት ተካሄደ::
በመድረኩ በኮሌጁ አጠቃላይ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን 21ኛውን ክፍለ ዘመን ባማከለ መልኩ ሳቢና ለስልጠና ምቹ ከማድረግ አንፃር የሚያስፈልጉ የRenovation ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በባለሙያዎች ተለይቶ ቀርቧል::
በዚህም በቀረበው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ላይ የኮሌጁ ማኔጅመንት ጨምሮ የስልጠና ክፍል ተጠሪዎችና የኮንስትራክሽን ዲፖርትመንት አ/መምህራን ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በዚህም በጥናቱ ላይ ሊካተቱ ይገባል ያሏቸውን ነጥቦችና ማሻሻያ ያስፈልጋቸዋል ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ለጥናቱ ግብአት የሚሆኑ ሀሳቦችንም አስቀምጠዋል::
የRenovation ትግበራው የEASE ፕሮጀክት በቀጣይ 5 አመት ከሚከውናቸው ትግብራዎች አንዱ ሲሆን ፕሮጀክቱ በተቋሙ በሚኖረው ቆይታም መሰል ተግባራትን የሚያካትት መሆኑም ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም የሩብ አመት የድጋፍ፣ክትትልና ግምገማ ተካሄደ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ በሚገኙ ዋና ስራ ሂደቶችና ስራ ክፍሎች ላይ በበጀት አመቱት የሩብ አመት የድጋፍ፣ክትትልና ግምገማ መርሃ-ግብር አካሂዷል::
የድጋፍ፣ክትትልና ግምገማ መመሪያው በቼክሊስት መልክ የተዘጋጀ ሲሆን ይህን መነሻ በማድረግም በበጀት አመቱ ለዋና ስራ ሂደቶችና ስራ ክፍሎች በተሰጡ የቁልፍ ውጤት አመላካች እስትራቴጂክ ተግባራት አንፃር የተገኘውን አፈፃፀም ለመገምገም እንዲሁም በአተገባር ወቅት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ወደሌሎች ክፍሎች ለማስፋት የታለመ መሆኑ ተግልፇል::
የድጋፍ፣ክትትልና ግምገማውን የኮሌጁ ማኔጅመንትና የISO Task force በጋራ በመሆን እንዲሁም ቼክሊስቶችን በማዘጋጀት በስራ ሂደቶችና ክፍሎች በመገኘት የበጀት አመቱ የሩብ አመቱን ግምገማ ያካሄዱ ሲሆን በዚህም ከተሰጡ ዋና ቁልፍ እስትራቴጂክ ተግባራት በተጨማሪ የISO ትግበራን ከማስቀጠል አኳያ ስራ ሂደቶችና ክፍሎች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ መመልከት ተችሏል::
በተካሄደው የድጋፍ፣ክትትልና ግምገማው መሰረት በስራ ሂደቶችና ክፍሎቹ የታዩ የአፈፃፀም ውስንነቶችን እንዲሁም የተለዩ ምርጥ ተሞክሮችን በመሰብሰብ ግብረ-መልስ የተሰጠ ሲሆን በቀጣይ የድጋፍ ክትትልና ግምግማውን መነሻ በማድረግ እንደ ተቋም የተመዘገበው የአፈፃፀም ሪፖርት የሚቀርብም ይሆናል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም
