Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
رفتن به کانال در Telegram
نمایش بیشتر
2 356
مشترکین
+2424 ساعت
+987 روز
+37730 روز
آرشیو پست ها
ወጣቶችን በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ የሚፈጠሩ በርካታ እድሎችን ተጠቃሚ በማድረግ ስራ አጥነትን ለመቅረፍ በሚደረገው ርብርብ የወላጆች እና የአካባቢው ማህበረሰብ ሚና የላቀ መሆኑ ተገለፀ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለሚገኙ የወላጅ ኮሚቴዎች እንዲሁም በየወረዳው ለተመረጡ የመንደር ኮሚቴዎች በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ::
የግንዛቤ መስጫ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የስራና ክህሎት ቢሮ ም/ሀላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ስተላፉት በመልዕክታቸው በተለምዶ ያደጉ እያልን የምጠራቸው ሀገራት ዛሬ ለደረሱበት እድገት መነሻ የሆናቸው በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ላይ ያሳደሩት እምነትና ዘርፉ ላይ በሰሩት ጠንካራ ስራ መሆኑን ጠቅሰው ወጣቱን በዚህ ረገድ ግንዛቤው ተፈጥሮለት የክህሎት ስልጠናዎች ላይ እንዲሰማራ እንዲሁም እንዱስትሪውን እንዲያንቀሳቅስ የማድረጉ ተግባርና ሀላፊነት ከወላጆች ጀምሮ የሁላችንም ድርሻ ነውም ብለዋል::
ወጣቶች አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ለማስቻል እና እየተፈጠሩ ያሉ እጅግ በርካታ እድሎችን ተጠቃሚ ለመሆን የመጀመርያ መግቢያ በሩ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እንደሆነ የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ አክለውም ወጣቶች ወደ ዘርፉን በሚፈለገው መጠን እንዳይቀላቀሉ ቴክንክና ሙያ ላይ በተለምዶ ያልተገባ ስም ተልጥፏል ያሉ ሲሆን እንደ ኮሌጅ ይህንን አመለካከት ለመቅረፍ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንዳሉ ገልፀው ወላጆችን ጨምሮ ህብረተሰቡ ውስጥ ተሰሚነት ያላችሁ ሰዎች በተገኘው አጋጣሚ ለወጣቶች ግንዛቤ የመፍጠሩን ስራ ላይ መረባረብ ያስፈልጋልም ብለዋል::
በመድረኩ የተሻሻለውን የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲ ሰነድ ለተሳታፊዎች ያቀረቡት የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ም/ዲን አቶ ኤሊያስ አህመድ ሲሆኑ ባቀረቡት ሰነድም የቴክኒክና ሙያ እስፈላጊነት ጨምሮ ነባሩ ፖሊሲ ላይ የታዩ ክፍተቶች እንዲሁም የፖሊሲውን መሻሻል አስፈላጊነትን በዝርዝር ለመድረኩ ተሳቲፊዎች አቅርበዋል::
የEASE ፕሮጀክት ከአለም ባንክ ጋር የ5 አመት ፕሮጀክት እንዳለው የገለፁት ደግሞ የEASE ፕሮጀክት ዋና ኮርድኔተር ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ አያይዘውም ኮሌጁ መሰል ፕሮጀክቶችን በማፈላለግ አስፈላጊ የሚባለውን ሁሉ የሚያሟላው በከተማችን ያሉ ወጣቶችን አሰልጥኖ ከስራ ጋር ለማስተሳሰር እንደሆነም ጠቅሰው ወጣቶችን ወደዚህ እንዲመጡ ማበረታታት ያስፈልጋልም ብለዋል::
በመጨረሻም ከመድረኩ የተነሱ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ በተሳታፊዎች በርካታ ሀሳቦች ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ በቅንጅት በሚሰሩ ተግባራት ላይ ከመግባባት በመድረስ መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 5/2017 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ ለሚካሄደው የክህሎት ውድድር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
ኮሌጁ በ2017 ዓ.ም "ብሩህ አዕምሮዎች ፣በክህሎት የበቁ ዜጎች!" በሚል መሪ ሀሳብ ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አጠናቆ ከመጋቢት 9 2017 ዓ.ም ጀምሮ ውድድሩ እንደሚካሄድ የገለፁት የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ ውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎችን ከመለየት አንስቶ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በሟሟላት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መከናወናቸውንም ገልፀዋል::
በዘንድሮ ውድድር ኮሌጁን እንዲሁም ከተማ አስተዳደሩን በሀገር አቀፍ ውድድር ላይ የሚወክሉ አሰልጣኞች፣ሰልጣኞች እንዲሁም ኢንተርፕራይዞችን አወዳድሮ ለመለየት በኮሌጅ ደረጃ ከመጋቢት 9 ጀምሮ የሚደረግ ሲሆን ውድድሩም በ7 የሙያ ዘርፎች ተወዳዳሪዎችን እንደሚያሳትፍ ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
መጋቢት 4/2017 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚሰራውን ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በማጠናከር በማርያም ሰፈር እና በመድሀንያለም አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ ለሚገኙ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘርፉን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ::
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ ተማሪዎች ስለ ዘርፉ ተገቢውን ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከማደረግ አኳያና እንደ ሀገር ከተያዘው የትኩረት አቅጣጫም አንፃር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ለወጣቱ በተለይም ከዚህ በኃላ ወደዘርፉ ለሚቀላቀሉ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ብዙ መልካም እድሎችን የያዘ ዘርፍ መሆኑን በዝርዝር ማብራሪያ በመስጠት ሰፋ ያለ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መስራት ተችሏል::
የግንዛቤ ማስጨበጫውን ለተማሪዎች የሰጡት የኮሌጁ ዲኖች እንዲሁም የዲፓርትመንት ተጠሪዎች ሲሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋም ከመቀላቀላቸው አስቀድሞ ከወዲሁ በአስተሳሰብም ሆነ ለዘርፉ ባላቸው አረዳድ ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያደርጋቸውን ምክረ ሀሳብና በኮሌጁ ያለውን ተሞክሮ ለተማሪዎች አካፍለዋል::
በቀጣይም የፈጠራ አቅም ያላቸውን ተማሪዎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክህሎቶቻቸውን እንዲያዳብሩ የሚረዳቸውን የቴክኒክና ሙያ (STEM) ክበብ በየትምህርት ቤቶቹ በመቋቋም ላይ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን ይህም የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ቀደም ብለው ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር ትስስር እንዲፈጥሩና በሲስተም ውስጥ እንዲያልፉ እድል እንደሚፈጥርላቸውም ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
መጋቢት 4/2017 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት የስርዓተ-ፆታ እና አካታችነትን ለማሳደግ በተዘጋጀው ጥናት ላይ ከፑል አመራር አባላትና ሴት አሰልጣኝ መምህራን ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ::
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ባስተላለፉት መልዕክት በቅድሚያ በአለም አቅፍ ደረጃ ለ114ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ ለሚከበረው የሴቶች ቀን(March 8) እንኳን አደረሳችሁ ያሉ ሲሆኑ በዚህ ቀን ስርዓተ-ፆታን በኮሌጃችን ለማዳበር በተዘጋጀ ጥናት ላይ ውይይት ማድረጋችን ቀኑን ልዩ ያደርገዋልም ብለዋል::
የኮሌጁ ዲን አክለውም በተቋማችን በስርዓተ-ፆታ እና በአካታችነት በርካታ ፍላጎቶች መኖራቸውን አስታውሰው ከዚህ ቀደም የተወሰኑ ስራዎች ቢሰሩም በሚነሱት ፍላጎቶች ልክ በአግባቡ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ እንዳልነበሩ ጠቅሰው በዚህም በስርዓተ ፆታ እና አካታችነት ላይ መስራት በሚገባን መጠን ለመንቀሳቀስ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት አድርጎ መነሻ የሚሆን መመሪያ ማዘጋጀት አስፈልጏልም ብለዋል::
በተጨማሪም በሁለቱ ጉዳዮች ላይ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ለማድረግ በተመረጡ ቡድኖች አማካኝነት ጥናቱ ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰው በዛሬው እለትም የጥናት ቡድኑ የደረሰበት በመድረኩ አቅርቦ በቀረበው ጥናት ላይ አስተያየት እንዲሰጥበትና መካተት የሚገባቸውን ጉዳዮች ማካተት እንዲቻል የተዘጋጀ መድረክም ነው ብለዋል::
የስርዓተ ፆታ እና እካታችነትን ለማሳደግ በEASE ፕሮጀክት በቀጣይ 5አመት ውስጥ ለሚኖረው ትግበራ መነሻ ሚሆነውን መመሪያ ለማዘጋጀት የተደረገውን የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት አዘጋጆቹ የደረሱበትን ለተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን በቅድሚያ በአካታችነት ላይ የተደረገውን የፍላጎት ዳሰሳ በአሰልጣኝ መምህር ዮናስ ሙሉጌታ ለተሳታፊዎች ቀርቦ በጥናቱ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ እንደ ተቋም የተለዩ ክፍተቶችን በዝርዝር አመላክቷል::
ቀጥሎም በስርዓተ-ፆታ ላይ የተዘጋጀውን የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በወ/ሮ ራሄል እሸቱ እና ኢንጂነር ህይወት እሸቱ አማካኝነት ለመድረኩ ተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በቀረበው ጥናትም በስራ እካባቢ ለሴቶች የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች የማሟላት ክፍተት፣ ስርዓተ ፆታ ላይ በቂ ግንዛቤ ለኮሌጁ ሰራተኞች አለመፍጠር፣ ሴቶችን የማበረታታትና ወደ አመራርነት እንዲመጡ ተገቢውን ድጋፍ ያለማድረግ እንዲሁም የማማከር አገልግሎት ሚያገኙበት አግባብ ያለመኖሩ የሚሉት በጥናቱ ከተገለፁት ውስጥ ተጠቃሽ ነጥቦችም ነበሩ::
በመጨረሻም በቀረቡት ጥናቶች መነሻነት ከተሳታፊዎ በርከት ያሉ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት የተደረገበት ሲሆን ጥናቱንም ለማዳበር ተጨማሪ ግብአቶች የተገኙበት መድረክም ነበር::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
የካቲት 29/2017 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ዋና ስራ ሂደት በተቋሙ ከሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ::
የውይይት መድረኩ የመሩት የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ም/ዲን አቶ ኤሊያስ አህመድ በንግግራቸው እንደግለፁት በአካዳሚክ ካላንደሩ መሰረት የትምህርትና ስልጠናው የመጀመሪያ ተርም ተጠናቆ ሁለተኛውን ተርም ምንጀምርበት ወቅት ላይ እንደመሆናችን የነበሩ ክፍተቶችን በሚገባ ለይቶ መፍትሄ ለማበጀትና በሁለተኛው ተርም ላይ በድጋሚ እንዳይስተዋሉ ለማድረግ ይህ የውይይት መድረክ አስፈልጎናልም ብለዋል::
ም/ዲኑ አክለውም ቀደም ብለው ከአካዳሚክ አባላት ጋር ተመሳሳይ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውሰው ከዛ በተገኘው ግብዓት መነሻነት እንዲሁም ከአሰልጣኝ መምህሩ የሚነሱ ሀሳቦችንም ጨምሮ በመወያየትና መፍትሄዎችንም በማስቀመጥ ለሁለተኛው ተርም በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም ገልፀዋል::
በመድረኩ ተሳታፊ ከነበሩት አሰልጣኝ መምህራንም የትምህርትና ስልጠና ሂደቱን አስመልክቶ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በዝርዝር ያስቀመጡ ሲሆን ከተነሱት ሀሳቦች ውስጥም የትምህርትና ስልጠና ማቴሪያል ውስንነት፣ ከትብብር ስልጠና ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እንዲሁም በምሽት ስልጠና ላይ ያልተመጣጠነ የመምህራን ክፍያ ችግርን ጨምሮ ትምህርትና ስልጠናውን ውጤታማ እንዳይሆን መንስኤ ናቸው ያሏቸውን በርካታ ክፍተቶችን በመጥቀስና አያይዘውም የመፍትሄ ሀሳብ ይሆናሉ ያሏቸውንም በመድረኩ አቅርበዋል::
በመጨረሻም አጠቃላይ ከመድረኩ በተነሱ ሀሳቦች ላይ ውይይት በማድረግ እንዲሁም ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸው መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
የካቲት 28/2017 ዓ.ም
