1 740
订阅者
无数据24 小时
+17 天
-630 天
帖子存档
በአስተዳደሩ በሚገኙ ሁለቱ የመንግስት ፖሊቴክኒኮች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራ ሂደቶች አዘጋጅነት ለጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ስለሚሰጠው የኢ/ኤ/ቴ/ሽ አገልግሎት ድጋፍ ላይ ያተኮረ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሄደ::
የውይይት መድረኩን የሁለቱ ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የኢ/ኤ/ቴ/ሽ አገልግሎት ስራ ሂደት ም/ ዲኖች በጋራ የመሩት ሲሆን በመድረኩም የ2016 ዓ.ም የኢ/ኤ/ቴ/ሽ አገልግሎት አፈፃፀም ላይ እንዲሁም የ2017 ዓ.ም በተሰራ የዳሰሳ ጥናት እና በቀጣይ ስለሚደረግላቸው ድጋፍ እንዲሁም የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች የሙያ ብቃት ምዘናን በተመለከተ አጠቃላይ ገለጻ በስራ ሂደቱ ባለሙያዎች የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ተችሏል፡፡
በመጨረሻም የ2016 ዓ.ም አፈፃፀምን መነሻ በማድረግና የተለዩ ችግሮችን በመለየት በ2017 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እንዲቻል ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ በመግለፅ መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል::
የኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ህዳር 10/2017 ዓ.ም
"ሀገራዊ መግባባት
ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት!"
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከበሩ።
በዓሉ በፓናል ውይይት የተከበረ ሲሆን፣ የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የሚከበር መሆኑን አውስተው፣ ሀገራዊ መግባባትን ለማጽናት ሕገ መንግሥቱን መሠረት በማድረግ ጥያቄዎችን በሰላማዊ አግባብ የሚያስተናግድ ሥርዓት መገንባትና የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ከዳር ደርሶ አንድነታችንን እንዲያጠናክር ቀዳሚ የመንግሥት ትኩረት እንደሆነ ተናግረዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 6/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የISO 9001:2015 QMS የጥራት ሥራ አመራር ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተሸላሚ::
የድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ባለቤት ሆነ።
በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኙት የመንግስት ኮሌጆች አንዱ የሆነው የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ስርዓት የጥራት ማረጋገጫ እና የብቃት መመዘኛ ISO 9001:2015 QMS አለም አቀፍ ሰርተፊኬት አገኘ።
በሰርተፊኬት ርክክብ ስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ እንዲሁም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሀርቢ ቡህ በድሬዳዋ 233 አነስተኛ ፣ 70 መካከለኛ እና 36 ከፍተኛ የኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች እንደተመዘገበ ጠቁመው የምስራቋ የኢንደስትሪ ኮሪደር እንደመሆኗ መጠን በኮሌጁ የሰለጠኑ ባለሙያዎችና ከፍተኛ የሰው ሃይል እንደሚያስፈልጋት አረጋግጠዋል።
ጥራት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራት ፤ ጥራት ባለው የትምህርት ስርዓት እና ምዘና ማለፍ ይገባል ሲሉ በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት የገለፁት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ሲሆኑ በብቃት የሰለጠነ የሰው ሃይልን በማፍራት ለኢንደስትሪው ማበርከት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።
በመድረኩ ላይ በእንግድነት የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ነቢሃ መሀመድ እንደገለፁት በሀገር አቀፍ ደረጃ እድሉን ካገኙ 20 ትቋማት መካከል 5ቱ እራሳቸውን በጥራት ደረጃ ማሳለፍ መቻላቸውንና ከእነዚህም መካከል የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንዱ መሆኑን አስታውቀዋል።
አክለውም ይህ የጥራት ማረጋገጫ ከምስራቅ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው እንደሚያደርገው ገልፀው በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ተፈላጊ ባለሙያዎችን በማሰልጠን የስራ እድልን ከመፍጠር በዘለለ ትልልቅ ድርጅቶችንና ኩባንያዎችን የሚያንቀሳቅሱ ለማድረግ መታቀዱን ጠቁመዋል።
የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬቱን ለኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ያስረከቡት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ ተቋማቸው በሀገሪቱ 9 የተደራጁ የጥራት ላቦራቶሪዎችን በማደራጀት እየፈተሸ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
በግብርና ፣ በምግብ ስርዓት ፣ በኢንደስትሪ ምርት እና በትምህርት ስልጠና የብቃት ደረጃዎችን የመለካት ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልፀው በአጠቃላይም 50 ሚሊየን ዶላር በመመደብ የጥራት ደረጃዎችን ለማሻሻልና ለመፈተሽ እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በመርሃግብሩ ማጠቃለያም ለኮሌጁ የትምህርት ስርዓትና የጥራት ደረጃ አስተዋፅኦ ላበረከቱ መምህራን የእውቅና እና ማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል።
©️ Diretv ህዳር 3/2017
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዘንድሮ አዲስ ለማሰልጠን የተቀበላቸውን ሰልጣኞች በአስተዳደሩ የሚገኙ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን አስጎበኘ::
ኮሌጁ ያዘጋጀው የጉብኝት መርሃ-ግብር በእስተዳደሩ ከሚገኙ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ጋር በመተባበር የተከናወነ ሲሆን በዚህም ሰልጣኝ ተማሪዎች ጉብኝታቸውን በኮካኮላ፣ናሽናል ሲሚንት፣ሬድዋ ሞተርስ እና ኒውዌቭ ፋብሪካዎች ላይ ተዘዋውረው እዲጎበኙ ማድረግ ተችሏል::
ሰልጣኝ ተማሪዎቹ በኢንዱስትሪ ጉብኝት ቆይታቸው በኮሌጁ ለመሰልጠን ከመረጡት የሙያ ዘርፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፉብሪካዎች ላይ ተመድበው የጎበኙ ሲሆን ይህም በኮሌጁ ቆይታቸው ስለሚሰለጥኑት የሙያ ዘርፍ የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኙም አስችሏቸዋል::
ይህን መሰል መርሃ-ግብር ሰልጣኝ ተማሪዎች በኮሌጁ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ በኃላ ያሏቸውን የስራ እድሎች ምን እንደሚመስሉ ከውዲሁ እንዲረዱና በቴ.ሙ.ስ ዘርፍ በሚኖራቸው ቆይታ መነቃቃትን እንዲፈጥርላቸው ታስቦ የተዘጋጀ የጉብኝት መርሃ-ግብር ነው::
ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም የስልጠና ዘመን አዲስ ለተቀበላቸው ሰልጣኞች የህይወት ክህሎት ስልጠና መስጠ ጀመረ::
አዲስ ገቢ ሰልጣኞቹ በቀጣዮቹ 3ቀናት የህይወት ክህሎት(Life skill )ስልጠናውን እየወሰዱ እንደሚቆዩ የተገለፀ ሲሆን ይህ ስልጠናም ሰልጣኞች የቀጣይ ህይወታቸውን በእቅድ እዲመሩ እንዲሁም ራሳቸውን ፈልገው እንዲያገኙና ሚገጥማቸውን የተለያዩ ፈተናዎች በራስ መተማመን እንዲወጡ የሚያስችላቸውን ልምድ የሚያገኙበት ስልጠና ጭምር መሆኑም ተነግሯል::
ሰልጣኞቹ ይህን ስልጠና አጠናቀው ሲጨርሱ በእስተዳደሩ የሚገኙ የተለያዩ ፋብሪካዎችንና ድርጅቶችን ተዘዋውረው የሚጎበኙ ሲሆን ይህም በተሻለ ግንዛቤና መነቃቃት መደበኛ ስልጠናቸውን እንዲጀምሩ የሚያደርጋቸውም ይሆናል::
ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም
በተመሳሳይ መልኩ ለምሽት አዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎችም የተሰጠ Orientation መድረክ በፎቶ📸
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
