Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
رفتن به کانال در Telegram
نمایش بیشتر
2 370
مشترکین
+324 ساعت
+937 روز
+36430 روز
آرشیو پست ها
በጀርመን ሀገር ሚገኘው የአድራ ጀርመኒ የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስፍፃሚ ልኡካን ቡድናቸውን በመያዝ በአድራ ኢትዮጵያ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጉብኝት እካሄዱ::
አድራ ኢትዮጵያ ከአድራ ጀርመኒ ጋር በመተባበር በጀርመን መንግስት ድጋፍ የሶላር ፒቪ ዝርጋታ እና ጥገና የሚሆን ወርክሾፕ በማደራጀት እና ስልጠናውን ለመስጠት የሚያስችል አቅም በመፍጠር በአሁን ሰአት ከገጠር እና ከከተማ የተመለመሉ ሰልጣኞች 23 ከገጠር 20 ከከተማ በድምሩ 43 ሰልጣኞችን በመያዝ ስልጠናውን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠናውን በመስጠት ላይ ይገኛል::
ልኡካን ቡድኑም በቅድሚያ በአዲስ መልክ የተደራጀውን የፕሮጀክቱን ማሰልጠኛ ወርክ ሾፕ ተዝዋውረው የጎበኙ ሲሆን በዚህም ሰልጣኞቹ የመግቢያ ፈተና ወስደው በተገኘው ውጤት መሰረት የ Life Skill ስልጠና ካገኙ በኋላ መሰረታዊ የኤሌክትሪክ እና የኮምፒውተር ስልጠና በመውሰድ ላይም እንደሚገኙ ተመልተው በቀጣይም ሰልጣኞቹ ወደ ሶላር ስልጠና እንደሚያመሩ ከአስተባባሪዎች ገለፃ ተደርጎላቸዋል::
የአድራ ጀርመኒ ዋና ስራ አስፈፃሚና ልኡካቸው በኮሌጁ የተገኙት ይህንን ጨምሮ በፕሮጀክቱ የተሰሩ አጠቃላይ ስራዋችን ለመገምገም እና የግብአት ጉድለቶችን ለማሟላት የሚያስችል ሁኔታዋችን ለመፍጠር እንዲሁም ሰልጣኞች ያሉበትን ሁኔታ ለማየት ሲሆን በፕሮጀክቱ የታዩትን ተግዳሮቶች እና በቀጣይ ሊሰሩ የሚችሉ ተግባራትን ከኮሌጁ ዲኖች እና ከአሰልጣኝ መምህራኑ ጋር በጥልቅ ተወያይተዋል::
በመጨረሻም ልዑካኑ ከአድራ ሶላር core string comittee ጋር በመገናኘትና ውይይት በማድረግ ፕሮጀክቱ ያለበትን ሁኔታ በመገምገም ያሉትን ማነቆዎች በማውጣት ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ናቸው ያሏቸውን በዝርዝር ለይተው አስቅምጠዋል::
በተሰጠውም ግብረመልስ በፕሮጀክቱ አፈፃፀምና አጠቃላይ እንቅስቃሴ ልዑካን ቡድኑ በእጅጉ መደሰቱበመግለፅ ለኮሌጁ ምስጋናቸውን ይቀረቡ ሲሆን በቀጣይም የኢትዮጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በሶላር ዘርፍ በምስራቁ ክፍል center of exellence ሊሆን የሚችልበትን ሁኔታ ና አቅም ለመፍጠር ዝግጁ መሆናቸውንም ገልፀዋል::
ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ህዳር 14/2016 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች የፀረ-ሙስና ቀንን በፖናል ውይይት አከበሩ::
ዘንድሮ ‹‹ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤በህብረት እንታገል ›› በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገራችን ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ- ሙስና ቀንን እስመልክቶ የኮሌጁ ሰራተኞች እና አመራሮች በተገኙበት በፓናል ውይይት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል፡፡
በእለቱ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ እንዲሁም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸው ሙስናን ምንም ስሙን ማሰማመር እንደማያስፈልግና በትክክለኛ መገለጫው #ሌብነት ብለን ልንጠራው ይገባል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም ሙስና የጋራ ጠላታችን በመሆኑ በህብረት ሆነን የማንታገለው ከሆነ ሀገራችንን ወደ ምንመኝላት የእድገት ጎዳና እንዳትደርስ አስሮ ወደኋላ የሚይዝ ማነቆ በመሆኑና ነገ ለልጆቻችን የተሻለች ኢትዮጵያን ማስረከብ የምናልም ከሆነ ይህን ሀገር ገዳይ የሆነ ካንሰር ለመግታት የሁላችንንም ቁርጠኝነትና ሀላፊነት የሚጠይቅ መሆኑን አፅዕኖት ሰጥተው ተናግረዋል::
በመቀጠል ሙስና እንደ ሀገር በምን ያህል ደረጃ እየፈተነን እንደሚገኝ የሚያሳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ በአሰልጣኝ መምህር ፋሲል ማዘንጊያ ሰፋ ባለና ግልፅ በሆነ መልኩ ለኮሌጁ ማህበረሰብ የቀረበ ሲሆን ከተሳታፊዎችም የተለያዩ ሀሳቦችና ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ የኮሌጁ ማህበረሰብ ሙስናን ለመከላከል ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባው በመተማመን መድረኩ ፍጻሜ አግኝቷል፡፡
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ህዳር 13/2016 ዓ.ም
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2016 ዓ.ም የስልጠና ዘመን አዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ተቀብሎ ስማሰልጠን አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ሰልጣኞችን በመጠባበቅ ላይ መሆኑን እየገስፀ የቴክኒክና ሙያ መግቢያ መስፈርትን የምታሟሉ ስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ ኮሌጃችን ከታች በተዘረዘሩት የሙያ መስኮች እርሶን ስማሰልጠን በመጠባበቅ ላይ መሆኑን በደስታ እናበስራስን፡፡
