es
Feedback
Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ir al canal en Telegram
1 754
Suscriptores
+124 horas
+37 días
+1130 días
Archivo de publicaciones
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ 2015 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞቹ የምስጋና እውቅና ፕርግራም አካሄደ። የድሬዳዋ አስተዳደር ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ በበጀት አመቱ የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞች የምስጋና እና የእውቅና መርሀ-ግብርም የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ተካሂዷል ። በእለቱ ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች እና በመርሀ-ግብሩ ላይም ከተጋበዙ የክብር እንግዶች በ 2015 በጀት አመት የተሻለ የስራ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ሰራተኞች የምስጋና እና የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሁም ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተቀብለዋል። በመጨረሻም የኮሌጁ ዲን ባስተላለፉት መልዕክት በ2015 በጀት አመት የተመዘገቡ ውጤቶች የሁሉም ሰራተኞች ጥረትና ድካም የተገኘ መሆኑን በመግለፅ ከእነዚህ ሰራተኞች ውስጥ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን ለይተን እውቅና ስንሰጥ ለሌላውም መነሳሳትን እንዲፈጥር በማሰብም ጭምር መሆኑን ገልፀው በቀጣይ በጀት አመትም ተቋሙ የተሻለ የስራ አፈፃፀም እንዲያስመዘግብ ሁሉም በትጋት ሊሰራ ይገባልም ብለዋል። የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መስከረም 26/1/2016 ዓ.ም

የድሬዳዋ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ያሰለጠኗቸውን ከ400 በላይ ሰልጣኞች አስመረቁ **** ሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ከደረጃ እስከ ዲግሪ መርሐ-ግብር ያሰለጠኗቸውን 420 ሰልጣኞች በዛሬው ዕለት በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አዳራሽ በጋራ አስመርቀዋል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር ሀርቢ ቡህ ትምህርት እና ስልጠና ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ እድገት ቁልፍ መሳሪያ ነው ብለዋል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና ለምታደርገው ጉዞ በሙያዊ ክህሎት እና በስነምግባር የታነፀ ተነሳሽነት የተላበሰ እና ከአዳዲስ ቴክኖሎጂ እና አሰራሮች ጋር ተዎህዶ መስራት የሚችል አምራች ዜጋን በጥራት እና በብዛት በመፍጠር ረገድ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ እድገት በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልፅዋል። በመሆኑም ተማሪዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ለሀገርና ለወገን የሚጠቅም ሥራ በመስራት በሀገሪቱ የተጀመረውን የብልፅግና ጉዞ እንዲረጋገጥ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም ነው ምክትል ከንቲባ ክቡር ሀርቢ ቡህ በመልክታቸው ያሳሰቡት። የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው በአመለካከት በእውቀት እና በክህሎት እሳድገው እንዲመረቁ ላደረጉ ለኮሌጆቹ አሰልጣኝ መምህራን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። የዛሬው ምርቃት ከወትሮ ለየት የሚያደርገውም ለመጀመሪያ ጊዜ የድሬዳዋ አስተዳደር ስራ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ተጠሪ ተቋማት ከሁለቱ ኮሌጆች ጋር በቅንጅት በመስራት እንዲሁም የደረጃ ሲ እና ቢ በአንድ ላይ ማስመረቅ መቻሉ ምርቃቱን ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል። በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ከንቲባና የንግድ ኢንደስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው፣ የድሬዳዋ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም፣ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን፣ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ እና ሌሎች የፌደራልና የአስተዳደሩ ተጋባዦች ተገኝተዋል። የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መስከረም 26/2016 ዓ.ም

በዛሬው እለት የምረቃ ስነ-ስርአታችሁን የምታከናውኑ የኮሌጃችን ሰልጣኝ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ::

“በድሬዳዋ እና በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ትምህርትና ስልጠና ተከታትላችሁ ያጠናቀቃችሁ ሰልጣኝ ተማሪዎች በምትሰማሩበት በአመለካከት፣ በዕውቀት እና በክህሎት የታነጻችሁ ብቁ ዜጋ ሆናችሁ እንደ
+3
“በድሬዳዋ እና በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ትምህርትና ስልጠና ተከታትላችሁ ያጠናቀቃችሁ ሰልጣኝ ተማሪዎች በምትሰማሩበት በአመለካከት፣ በዕውቀት እና በክህሎት የታነጻችሁ ብቁ ዜጋ ሆናችሁ እንደማያችሁ ሙሉ እምነት አለኝ፤ በዚህም የሀገር እድገት ላይ የድርሻ ሚናችሁን ለተወጣችሁ አሰልጣኞች፣ የዘርፉ አመራሮች እና ባለሙያዎች በሙሉ በቢሮው ስም ምስጋናዬን እያቀረብኩ ስልጠና አጠናቃቂዎች ለተገባችሁ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ!” አቶ ሮቤል ጌታቸው የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ እንደሚታወቀው በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር ካሉት ዘርፎች አንዱ የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ስልጠና ዘርፍ እንደመሆኑ የዘርፉን ግብ እና ዓላማ፤ ለማሳካት በሚደረገው ትግል ውስጥ የማይተካ ሚና ያላቸውና ባለራዕይ የሆኑ ከዘርፉ የሚፈሩ ሰልጣኝ ተማሪዎች እንደሆኑ እሙን ነው፡፡ የድሬዳዋ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጆችም ዘርፉን በአመለካከት፣ በእውቀት እና በክህሎት የበቁ ዜጎችን በማፍራት ላይ ሲገኙ በተለይ በአሁኑ ወቅት እንደ ቢሮ በተፈጠረው ተቀራርቦ የመስራትና የመደጋገፍ ሁኔታዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድነት ሰልጣኝ ተማሪዎችን በጋራ መስከረም 26/2016 ዓ.ም በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ትልቁ አዳራሽ በድምቀት የሚያስመርቁ ይሆናል፤ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!!!

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ ይላል::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1498ኛው የመውሊድ በአል በሰላም አደረሳችሁ ይላል::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የዘንድሮ ተመራቂዎቹን መስከረም 26/01/2016 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ የሚያስመርቅ መሆኑን እየገለፅን ተመራቂ ተማሪዎች ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን::

ከሶማሌ ክልል (ጂግጂጋ) ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተውጣጣ ልኡካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ አደረገ:: በዛሬው እለት በትቋማችን የስራ ጉብኝት በማድረግ ልምድ የተለዋወጠው ልኡክ ከሶማሌ ክልል (ጂግጂጋ) ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ የስራ ክፍል እና ዲፖርትመንት ኃላፊዎችን ያካተተ ሲሆን ለልኡካን ቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ያደረጉት የኮሌጃችን ዲኖች በመቀጠልም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከምስረታው ጀምሮ አሁን እስከደረሰበት በኮሌጁ ዲን ገለፃ ተደርጎላቸዋል:: በመቀጠል ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ወርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ይህን ካዩ በኀላም ሁሉም በሚመለከታቸው ዲፓርትመንቶች እና የስራ ሂደቶች በመከፋፈል በኮሌጁ ያለውን አሰራርና ልምድ ተመልክትዋል:: በመጨረሻም ልኡካኑ ባዩት ነገር መደሰታቸውና ተቋሙ ካሰቡት በላይ ትልቅ ተቋም መሆኑን በመጠቆም ለመጡበት አላማም በርከት ያሉ ግብአቶችን እንዳገኙ በመግለፅና ለተቋሙ ምስጋናቸውን በማቅረብ በኮሌጁ የነበራቸውን ፕሮግራም አጠናቀዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መስከረም 08/1/2016 ዓ.ም

Repost from N/a
photo content
+5

Repost from N/a
photo content
+8

Repost from N/a
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ አነስተኛ ገቢ ኖሯቸው ልጆቻቸውን ለሚያስተምሩ ሰራተኞቹ ለልጆቻቸው ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሚሆን የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ:: በድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ የኮሌጁ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት ተገኝተው የትምህርት መርጃ ድጋፉን ያስረከቡ ሲሆን በርክክቡ ወቅት የኮሌጁ ዲን ባደረጉት ንግግርም "ከዚህ ቀደም እንዲህ ያሉ ድጋፎች ከተቋሙ ውጪ ብቻ ያተኮረ እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ ግን ያለው ሁኔታ በተቋሙ ውስጥ ያሉትንም መለስ ብለን እንድናይ ያስገደደ ነውም ብለዋል:: ሀላፊው በተጨማሪም ተቋሙ ሰራተኞችን በዘላቂነት ራሳቸውን ሚደጉሙበትን አሰራር ለመዘርጋት በሂደት ላይ መሆኑን ገልፀው ሰራተኛውም ለዚህ ትግበራ መሳካት የድርሻውን እንዲወጣም ጠይቀዋል:: የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድግፍ የተደረገላች የተቋሙ ሰራተኞች በበኩላቸው የኮሌጁ አመራሮችና ማኔጅመንቱ በዚህ አዲስ የትምህርት ዘመን በሚጀምርበት ወቅት ይህን አስባችሁ ድጋፍ ማድረጋችሁ ለኛ ትልቅ ትርጉም አለው በማለት ምስጋናም እቅርበዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መስከረም 05/1/2016 ዓ.ም