fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

رفتن به کانال در Telegram
2 387
مشترکین
+424 ساعت
+677 روز
+35730 روز
آرشیو پست ها
አዲስ ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ስትመጡ ማሟላት የሚጠበቅባችሁ ማስረጃዎች።

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ      በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የውስጥ ማስተግበሪያ መመሪያ አዲሱ የሰልጣኝ ተማሪዎች ውጤት አያያዝ እና አገባብ ዙሪያ ለኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ከ የካቲት 27/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ የሚያካሂድ መሆኑን እየገለፀ እርሶም ባሉት ጥቂት የምዝገባ ቀናት በአካል ተገኝተው እንዲመዘገቡ ይጋብዛል።

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች የ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ 6ወር የስራ አፈፃፀምና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያዩ።      በዕለቱ በተዘጋጀው መድረክ የኮሌጁን የመጀመርያ 6ወር የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ጠቅለል ባለ መልኩ  በኮሌጁ ዲ/ን የቀረበ ሲሆን ከሰራተኛውም በግማሽ አመቱ ተግዳሮት የነበሩና በቀጣይ ሊሻሻሉ ይገባል ባሏቸውን ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን ለመድረኩ አካፍለዋል።    በተጨማሪም በተቋሙ በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸውን የታቀዱ ተግባራትን ለኮሌጁ ማህበረሰብ የቀረቡ ሲሆን ባጠቃላይ በመድረኩ የተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ላይ በ ኮሌጁ ዲኖች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰቶባቸው ውይይቱ ፍፃሜውን አጊዥቷል። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን የካቲት 10/2015 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአስተዳደራችን ለሚገኘው የድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል የማቴሪያል ድጋፍ አደረገ።     ተቋማችን በኮሚኒቲ ሰርቪሲንግ ለሆስፒታሉ ያደረገው ድጋፍ 10 የታካሚዎች መቀመጫ ወንበሮች እና 30 የግሉኮስ መስቀያ(IV Stands) ሲሆኑ ድጋፉንም የኮሌጃችን ም/ዲን አቶ ኤልያስ አህመድ ለሆስፒታሉ ተውካዮች አስረክበውልናል።      እነዚህ የማቴሪያል ድጋፎችም በኮሌጃችን በሚገኙት የውድ ዎርክ ዲፓርትመንት፣ የማኑፋክቸሪንግ ዲፓርትመንትና ከኢ/ኤ/አ ቴክኖሎጂ ስራ ሂደት ጋር በትብብር የተመረቱ ናቸው። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ጥር 30/2015 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  "በብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት" ተጠቃሚ ለመሆን በአስተዳደሩ የቀበሌ አንድ ማዕከላት የተመዘገቡ ወጣቶችን የሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች በዛሬው እለት ስልጠና መስጠት ጀመረ።         በዛሬው ዕለት ለስልጠናው ወደ ኮሌጃችን የመጡት የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ሰልጣኞች በቅድሚያ ከሚወስዱት የህይወት ክህሎት ስልጠና አስቀድሞ ስለ ስልጠናው ሰፋ ያየ ግንዛቤ የተሰጣቸው ሲሆን ለሚቀጥሉት 10ቀናትም ስልጠናቸውን እየወሰዱ በተቋማችን የሚቆዩም ይሆናል።      በስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የስራ እድል ፈጠራ እና የቀበሌ አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሚን አብዱላሂ በዚህ ዙር ዘጠኝ መቶ ሀምሳ የሚደርሱ ሰልጣኞች ወደ ስልጠና የገቡ መሆኑን ጠቅሰው ሰልጣኞች ይህን እድል በሚገባ ተጠቅመው እራሳቸውንና አገራቸውን የሚጠቅሙ ዜጎች እንዲሆኑ አሳስበዋል። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ህዝብ ግንኙነት ጥር 16/2015 ዓ.ም ድሬዳዋ

በብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለመሆን በአስተዳደሩ የቀበሌ አንድ ማዕከላት የተመዘገባችሁ ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች ማክሰኞ ጥር 16/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:30 ስልጠና የምትጀም
በብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለመሆን በአስተዳደሩ የቀበሌ አንድ ማዕከላት የተመዘገባችሁ ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች ማክሰኞ ጥር 16/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:30 ስልጠና የምትጀምሩ ይሆናል። በዚህም 👉 በ06 ቀበሌ አንድ ማዕከል 👉 በ09 ቀበሌ አንድ ማዕከል 👉 በ07 ቀበሌ አንድ ማዕከል(100 ሰልጣኞች) የተመዘገባችሁ ወጣቶች ስልጠናችሁ በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሲሆን፤ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኬሽን። ጥር 15 2015 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ ይላል።