Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
رفتن به کانال در Telegram
نمایش بیشتر
2 394
مشترکین
+424 ساعت
+677 روز
+35730 روز
آرشیو پست ها
የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
በድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አዘጋጅነት ሲሰጥ የነበረውንና "ብቃት" የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር የህይወት ክህሎት ስልጠና በኮሌጃችን ወስደው ያጠናቀቁ 353 ሰልጣኞች የምርቃት መርሃግብር በዛሬው ዕለት በድምቀት ተካሂዷል፡፡
በዕለቱ በነበረው መርሃ ግብርም የኮሌጁ ዲኖች ለሰልጣኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልክ ያስተላለፉ ሲሆን ሰልጣኞች የወሰዱት ስልጠና በዚህ እንደማያበቃና በቀጣይ በተጨማሪ ስልጠናዎች ከተቋሙ ጋር ሚገናኙ መሆኑንም ገልፀዋል።
በዚህም የሰልጣኞች የምርቃት መርሃግብር ላይ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ለሰልጣኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በስልጠናው ያገኙትን እውቀት በቀጣይ በስራ ላይ ለሚኖራቸው ስልጠና እንዲጠቀሙበት በማሳሰብ የሚመጡ እና የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች በጥንካሬ በማለፍ ለራሳቸውና ለሃገራቸው የሚጠቅሙ ዜጎች እንዲሆኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው ባለፉት 10 ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና በኮሌጆቹ ውስጥ ሲሰጣቸው የቆየ ሲሆን ይህንንም ሲያጠናቅቁ በመረጡት የሙያ ዘርፍ በአስተዳደሩ በሚገኙ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ኢንደስትሪዎች ላይ የኪስ ገንዘብ እየታሰበላቸው በተግባር እየሰሩ እውቀትና ክህሎታቸውን የሚያዳብሩ እንደሚሆን ገልጸው በስልጠና ቆይታቸውም በኮሌጆቹ የህጻናት ማቆያ ቦታዎች ተዘጋጅቶላቸው የነበረ መሆኑና በዚህም የልጅ እናት የሆኑ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች ስልጠናውን ሳይስተጓጎሉ እንዲወስዱ ማቻሉን በማስታወስ ለዜጎች ሁሉን ተደራሽ የሚያደርግ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች በመሰራት ላይ ለመሆናቸው ይህ መርሃግብር ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ሰልጣኞችን በወከል ሀሳባቸውን ያጋሩት ተሳታፊዎም ባገኙት ስልጠና ትልቅ የሂወት ልምድና ዕውቀት ያገኙ መሆኑን በመግለፅ የዚህ ፕሮጀክት አካል ስለሆኑም ደስተኞች መሆናቸውን በመድረኩ ገልፀዋል።
በቢሮው የስራ ዕድል ፈጠራ እና የአንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሚን አብዱላሂ በአጠቃላይ በዚህ ዙር በሁለቱም ኮሌጆች ሰልጥነው ካጠናቀቁ ሰልጣኞች ብዛት ስድስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይም ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞችን በተመሳሳይ ተጠቃሚ የሚደረግ መሆኑን አስታውቀው ሰልጣኞቹን በማሰልጠንና ሁኔታዎችን በማመቻቸት የተሳተፉ አካላትን ሁሉ አመስግነዋል።
የኢትዮ ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 10/2015 ዓ.ም
ድሬዳዋ
#ብቃት_የወጣቶች_የስራ_ላይ_ልምምድ_ፕሮጀክት
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ "ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት" ተጠቃሚ ለመሆን በአስተዳደሩ የቀበሌ አንድ ማዕከል የተመዘገቡ ወጣቶችን በዛሬው እለት በተቋሙ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
በዛሬው እለት በኮሌጁ ስልጠናቸውን መውሰድ የጀመሩትም የ01 ቀበሌ አንድ ማዕከል፣ የ02 ቀበሌ አንድ ማዕከል(ዋናው) እና የ02 ቀበሌ ቅርንጫፍ 1(ጎሮ ) አንድ ማዕከል ናቸው።
በተጨማሪም ሰልጣኞች ስልጠና ከመጀመራችው በፊት አስፈላጊውን ኦሬንቴሽን የተሰጣቸው ሲሆን ስልጠናውን ለቀጣይ 10 ቀናት በተቋማችን እየወሰዱ የሚቆዩ ይሆናል።
እንዲሁም ህፃናት ልጆች ያላቸው ሰልጣኞች ከስልጠናቸው እንዳይስተጓጎሉ በማሰብ በተቋሙ የህፃናት ማቆያ በማዘጋጀት ሰልጣኞች ለቀጣይ 10 ቀናት ልጆቻቸውን አምጥተው እንዲያቆዩበት መቻችቷል።
#የቴክኒክና_ሙያ_ሳምንት
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከታህሳስ 18/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆየውን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የንቅናቄ ሣምንት በዛሬው እለት በደማቅ ሁኔታ አስጀምሯል።
ለአንድ ሳምንት በሚቆየው በዚህ የንቅናቄ መርሀ ግብር ላይ በኮሌጃችን የቴክኖሎጂ ፈጠራ አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት የሚካሄድም ይሆናል።
እርሶም ለአንድ ሳምንት በሚቆየው የቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ ላይ ተገኝተው በመጎብኘት ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የተሻለ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተጋብዘዋል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ታህሳስ 18/2015 ዓ.ም
ድሬዳዋ
#የምስጋና_እና_የዕውቅና_ፕሮግራም።
………………………………………………………………
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከህዳር 19-25/03/2015 ዓ.ም ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው 9ኛው የዓለም አቀፍ የኢንተርፕሩነርሺፕ ሳምንት መድረክ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደርን ወክለው የተሳተፉትና በኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተሰሩት የዳቦ ማምረቻ ማሽኖች(ሙሉ ፓኬጅ) በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ ተወዳድረው አንደኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቃቸው እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር እና የኮሌጁን በትልቅ ደረጃ ያስጠሩ በመሆኑ ቴክኖሎጂዎች ላይ ለተሳተፉትን የኮሌጁን አሰልጣኝ መምህራን የምስጋና እና ዕውቅና ፕሮግራም በዛሬው እለት ተደርጎላቸዋል።
በእውቅና መድረኩም ላይ የኮሌጁ ዲኖች የእንኳን ደስ አለን ንግግር ያደረጉ ሲሆን በመቀጠልም የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ሀላፊ የሆኑት ወይዘሮ ፈጡም ሙስጠፋ ለቴክኖሎጂው ባለቤቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልክታቸውን በማስተላለፍ የተዘጋጀውን የምስጋና ምስክር ወረቀት ከሰጡ በኋላ ለዕለቱ የተዘጋጀውን ኬክ በጋራ ቆርሰዋል።
ታህሳስ 06/2015
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮምንኬሽን
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አግልግሎት ትግበራ በአካል በመገኘት ድጋፍ ለሚያደርግላቸውን ኢንተርፕራይዞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩም ተሳታፊ ከነበሩ ኢንተርፕራይዞች በርከት ያሉ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን በቀጣይም የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፉን በተቀላጠፈ ሁኔታና በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያችል ሰፋ ያለ ውይይትም ተደርጎበታል።
ህዳር 28/2015
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮምንኬሽን
