WOLAYTA SODO UNIVERSITY
رفتن به کانال در Telegram
Info about wolayta sodo university Photos ,new music ,vine and different thing about the Campus@@@@@@@@@@@@@@ For junior and senior students. @veva1
نمایش بیشتر5 907
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+197 روز
+1930 روز
آرشیو پست ها
Info about wolaita sodo university
For junior and senior students
Share @wsu19be
የዩኒቨርሲቲው መምህራን ማህበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ!
በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።
በጉባኤው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት መምህር ደጉ መና በመልዕክታቸው የመምህሩ ሁለንተናዊ ጥያቄዎች የሚመለሱትና አደረጃጀቱ ጥንካሬ የሚኖረው እያንዳንዱ መምህር የነቃ ተሳትፎ ሲያደርግ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረው ሁሉም አባል በዚህ ልክ ትኩረት መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል።
በጉባኤው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር ዋና ጸሐፊ መምህር ውቤ እንግዳው የተገኙ ሲሆን በመክፈቻ ንግግራቸው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተው የማህበሩ ተቀዳሚው አጀንዳ የትምህርት ጥራት ማሻሻል በመሆኑ ይህንኑ ለማሳካት ቅድሚያ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ሌላው ጉዳይ ተከትሎ ይመጣል ብለዋል።
በጠቅላላ ጉባኤው ዓመታዊ ሪፖርትና የ2019 ዕቅድ በማህበሩ ፕሬዚዳንት; የማህበሩ አዲሱ መተዳደሪያ ደንብ በመምህር ተከተል ላበና እና የመምህራን ሙያና ሥነምግባር ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ጽሑፍ በዶ/ር ዘሩ ስዩም ቀርቧል።
በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ከተሳታፊዎች በተነሱ ጥያቄዎች አስተያየቶች ላይ ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።
በመጨረሻም በጎደሉ የማህበሩ አስፈጻሚዎች ምትክ የማሟያ ምርጫ የሚካሄድበት አቅጣጫ ተቀምጦ ጉባኤው ተጠናቋል።
@wsu19be
ማስታወቂያ
ለነባር የሳምንት መጨረሻ ተማሪዎች በሙሉ
https://t.me/WolaitaSodoUniversit/483
@wsu19be
የመምህራን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ማስታወቂያ 👇
የዩኒቨርስቲያችን መምህራን ማህበር ስብሰባ ባለፈው ማክሰኞ የነበረው በአባላቱ አለመሟላት ምክንያት ለነገ ቅዳሜ የተዛወረና ከጧቱ 2:30 ጀምሮ በካውንስል አዳራሽ ስለሚካሄድ አባላት በሙሉ እነንዲገኙ ተጋብዘዋል።
ለዝርዝር መረጃ ከሥር የተለጠፈውን ማስታወቂያ ይመልከቱ።
@wsu19be
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ 👇
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚ/ር የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የፕሬዝዳንቶች አሰያየም መመሪያ ቁጥር 1146/2018 መሠረት የፕሬዝዳንት ክፍት አመራርነት መደብ ላይ አወዳድሮ ለመመደብ የወጣ ማስታወቂያ!
ለበለጠ መረጃ ከሥር የተለጠፈውን የመስከረም 20/2019 አድስ ዘመን እትም መመልከት ይቻላል።
@wsu19be
ለአራት ተከታታይ ቀናት ስሰጥ የቆየው የመምህራን ስልጠና ተጠናቀቀ።
በማጠቃለያው መድረክ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው አ/ጉ/ም ፕሬዚዳንት አክብር ጩፎ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው ተማሪ ተኮር ሥርዓተ ትምህርት የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የሚያግዝ በመሆኑ የሥልጠናው ተሳታፊዎች ያገኙትን ዕውቀት በተግባር ለማዋልና አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት ለመተግበር ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ሰልጣኝ መምህራን በበኩላቸው ሥልጠናው በተግባራዊ ልምምዶች፣ በቡድን ውይይቶች እና በልምድ ልውውጦች የታገዘ በመሆኑ ደስቸኞች መሆናቸውን ገልጸው ያገኙትን እውቀት ለመተግበር ያላቸውን ፍላጎት እንደጨመረላቸው ተናግረዋል።
@wsu19be
ወደ ተርጫ ካምፖስ የተመደባቹ የ2ተኛ ዓመት ተማሪዎች ነገ ቅዳሜ ጥዋት 11:30 መኪና ሁለተኛ በር ላይ ሰለሚጠብቃቹ ሁላቹም በሰዓቱ እንድትገኙ እናሳስባለን::ተርጫም ያላቹ ተዘጋጅታቹ እንድትጠብቁን እናሳስባለን::
ወሶዩ
@wsu19be
