SNE Ethiopia (ልዩ ፍላጎት)
رفتن به کانال در Telegram
This channel focuses on raising public awareness, increasing education and sharing tips about childrens with and without disabilities. For more info @Snie_bot
نمایش بیشتر523
مشترکین
+324 ساعت
+107 روز
+930 روز
در حال بارگذاری دادهها
کانالهای مشابه
ابر برچسبها
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
اکتبر '26اکتبر '26
اکتبر '26
+145
در 0 کانالها
سپتامبر '260
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '260
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '260
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '260
در 0 کانالها
Get PRO
مه '260
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '260
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '260
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '260
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '260
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '250
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '250
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '250
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '250
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '250
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '250
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '250
در 0 کانالها
Get PRO
مه '250
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '250
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '250
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '250
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '250
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '24
+16
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '24
+15
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '24
+14
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '24
+359
در 0 کانالها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 25 اکتبر | +1 | |||
| 24 اکتبر | +3 | |||
| 23 اکتبر | +2 | |||
| 22 اکتبر | +3 | |||
| 21 اکتبر | +1 | |||
| 20 اکتبر | +2 | |||
| 19 اکتبر | 0 | |||
| 18 اکتبر | 0 | |||
| 17 اکتبر | +1 | |||
| 16 اکتبر | +1 | |||
| 15 اکتبر | 0 | |||
| 14 اکتبر | +1 | |||
| 13 اکتبر | 0 | |||
| 12 اکتبر | 0 | |||
| 11 اکتبر | 0 |
پستهای کانال
| 2 | 🌙 በጨለማው ሌሊት ተስፋህን አታጥፋ!💫 ❤️
ሌሊት ሲረጋጋ፣ የነገ ጭንቀት በብዙ ሰዎች ልብ ውስጥ ይጮኻል። በተለይም ከአካል ጉዳት ጋር ለሚኖሩ ሰዎች የሕይወት ፈተናዎች ቀላል አይደሉም። ይሁን እንጂ «አካል ጉዳት የሰውን ዋጋ፣ ችሎታና ሕልም አይወስንም!»
🙏 በእግዚአብሔር ተማመን፣ በራስህ ችሎታ እመን፣ ያሉትን ዕድሎች ፈልግ። ዛሬ ያለው ዲጂታል ዓለም ለመማር፣ ክህሎት ለማዳበርና ሥራ ለመፍጠር አዳዲስ በሮችን ከፍቷል። ትንሽ ጥረትም ቢሆን የለውጥ መጀመሪያ ሊሆን ይችላል።
ማኅበረሰቡም ሊያስታውስ የሚገባው አንድ እውነት አለ፦ አካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች ርኅራኄ ብቻ ሳይሆን፣ እኩል ዕድል፣ ተደራሽ ትምህርትና የተከበረ ሥራ ያስፈልጋቸዋል።
🌹 እምነት ሰላም ይሰጣል፤ ተስፋ ያበረታታል፤ ጥረት ደግሞ ወደ ዕድል ይመራል። ተስፋህን አታጥፋ፤ ሕልምህ ዋጋ አለው!
እግዚአብሔር ለሁሉም በችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች ተስፋና መፍትሔ ይስጥ። አሜን!❤
#disability #Hope #EqualOpportunity #selfimprovement #DigitalOpportunity #supporteachotherandgrow | 105 |
| 3 | بدون متن... | 269 |
| 4 | ሴሬብራል ፓልሲ
ሴሬብራል ፓልሲ (Cerebral Palsy) በአንጎል እድገት ወቅት በሚፈጠር ጉዳት ወይም ያልተለመደ እድገት ምክንያት የሰውነት እንቅስቃሴን፣ የጡንቻዎችን ቁጥጥርና የአካል አቀማመጥን የሚነካ የነርቭ ሥርዓት ሁኔታ ነው። በእያንዳንዱ ሰው ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ የተለያየ ሲሆን አንዳንዶች በቀላል የእንቅስቃሴ ችግር ሊኖሩ ሲችሉ ሌሎች ለመራመድ፣ ለመቀመጥ፣ ለመናገር ወይም የዕለት ተዕለት ተግባራትን ለማከናወን ተጨማሪ ድጋፍ ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ስለዚህ ሁኔታውን በትክክል መረዳትና የእያንዳንዱን ሰው ፍላጎት በተናጠል ማየት አስፈላጊ ነው።
ሴሬብራል ፓልሲ የሰውን ዋጋ፣ ክብርና ችሎታ መወሰን አይችልም። ምክንያቱም ሴሬብራል ፓልሲ ያለበት ሰው የመማር፣ የማደግ፣ ሐሳቡን የመግለጽ፣ ከሌሎች ጋር የመግባባትና በማኅበረሰብ ውስጥ በንቃት የመሳተፍ ችሎታና መብት አለው። የእንቅስቃሴ ችግር መኖር የአእምሮ ችሎታ ዝቅተኛ መሆንን አያመለክትም፤ እንዲሁም ተግባቦት ላይ ችግር ቢኖርበትበም ሰውየው መረዳት አይችልም ማለት አይደለም። ስለዚህ ሰዎችን በአካል ጉዳታቸው ብቻ ከመመዘን ይልቅ በችሎታቸው፣ በፍላጎታቸውና ሊያሳኩ በሚችሉት ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባናል።
ሴሬብራል ፓልሲ ላላቸው ሕፃናት ተገቢ የትምህርት፣ የጤናና የማገገሚያ አገልግሎቶችን ማቅረብ የእድገታቸውንና የነፃነታቸውን ዕድል ያሰፋል። በትምህርት ቤት ውስጥ ተደራሽ አካባቢ፣ እንደ ፍላጎታቸው የተስተካከለ የማስተማር ዘዴ፣ የመማሪያ መርጃዎችና አስፈላጊው የግል ድጋፍ መኖር አለበት። አካቶ ትምህርት ማለት ልጆችን በአንድ ክፍል ውስጥ ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉም ልጆች እንዲማሩ፣ እንዲሳተፉና የራሳቸውን አቅም እንዲያዳብሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው። እንዲሁም የእንቅስቃሴ መርጃ መሣሪያዎችና ሌሎች የድጋፍ አገልግሎቶች ተደራሽ መሆናቸው በማኅበረሰብ ውስጥ በንቃት ለመሳተፍ ይረዳል።
እንደ ማኅበረሰብ የምንወጣው ኃላፊነት ርኅራኄ ማሳየት ብቻ አይደለም። አካል ጉዳት ያላቸውን ሰዎች የሚያገልሉ አመለካከቶችን መቀየር፣ አድሎን መቃወም፣ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ማቅረብና የመሳተፍ ዕድላቸውን ማረጋገጥ ይገባናል። ቤተሰቦች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ መንግሥትና ማኅበረሰቡ በጋራ በመሥራት አካታችና ተደራሽ የሆነ አካባቢ መፍጠር ይችላሉ።
አካል ጉዳት የሰው ልጅ ልዩነት አንዱ ክፍል ነው። ሁሉም ሰው ክብሩ ተጠብቆ፣ ችሎታው ታውቆና መብቱ ተከብሮ መኖር ይገባዋል። በአካል ጉዳት ምክንያት ማንም ከትምህርት፣ ከጤና አገልግሎትና ከማኅበራዊ ተሳትፎ መገለል የለበትም። ችሎታን እናክብር፣ እኩል ዕድል እንፍጠር፣ ማንንም ወደ ኋላ አንተው!
#CerebralPalsy #InclusiveEducation #DisabilityInclusion #learningdisabilities | 303 |
| 5 | አካል ጉዳተኛ ዜጎች ርህራሄ ብቻ ሳይሆን መረዳትንና እኩል መብትን ይፈልጋሉ።
ብዙ ሰዎች የአካል ጉዳተኞችን የዕለት ተዕለት ሕይወት፣ ተግዳሮቶቻቸውን፤ ከማህበረሰቡና ከተቋማት ጋር ሲገናኙ የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች በቀላሉ ሊረዱ አይችሉም። ምክንያቱም አካል ጉዳት በራሳቸው ላይ እስካልደረሰ ወይም በቅርብ የሚያውቁትን ሰው እስካልነካ ድረስ የእነዚህ ሰዎች ችግር የዕለት ተዕለት ጉዳያቸው ላይሆን ይችላል።
ነገር ግን አካል ጉዳት የግለሰቡ ብቻ ችግር አይደለም። ተደራሽ ያልሆነ ሕንፃ፣ የመጓጓዣ እጥረት፣ ተገቢ የሆነ የረዳት መሳሪያ አለመኖር፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎት መሰናክሎች እንዲሁም የማህበራዊ አመለካከት ችግሮች የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ሊገድቡ ይችላሉ። ስለዚህ ችግሩን በሰውየው ላይ ብቻ ከመመልከት ይልቅ በአካባቢውና በማህበረሰቡ ያሉትን መሰናክሎችም መመልከት ያስፈልጋል።
እኛም አንድ ችግር እስከራሳችን ወይም እስከቤተሰባችን ድረስ እስኪደርስ መጠበቅ የለብንም። ሌላው ሰው የሚያጋጥመው ችግር እውነተኛ እንዲሆን እኛ ራሳችን ተጋላጭ መሆን አያስፈልገንም። ሰዎች የሚነግሩንን ልምድ ማዳመጥ፣ ማመን እና መረዳት የርህራሄ እውነተኛ መገለጫ ነው።
አካል ጉዳት በማንም ሰው ላይ ሊደርስ ይችላል፤ ስለዚህ ለአካል ጉዳተኞች ድምፅ መስጠትና እኩል ዕድል መፍጠር እኛ ላይ እስኪደርስብን ድረስ የምንጠብቀው ጉዳይ ሳይሆን ዛሬ ልንከናውነው የሚገባ የሰብዓዊነት ኃላፊነት ነው። | 363 |
| 6 | ልዩ ፍላጎት ላላቸው ልጆች ልዩ ትምህርት ቤት ይሻላል ወይስ አካቶ ትምህርት?
ልዩ ፍላጎት ላለው ልጅ የትኛው የትምህርት አካባቢ ይሻላል? የሚለው ጥያቄ በልጁ የግል ፍላጎት፣ የመማር አቅም፣ የአካልና የግንዛቤ ሁኔታ እንዲሁም ትምህርት ቤቱ ሊሰጠው በሚችለው ድጋፍ ላይ ይመሰረታል። በአጠቃላይ ግን አካቶ ትምህርት (Inclusive Education) ተመራጭ ነው። አካቶ ትምህርት ልጁ ከእኩዮቹ ጋር በአንድ የትምህርት አካባቢ እንዲማር፣ እንዲጫወት፣ ጓደኝነት እንዲመሰርት እና የመግባባትና የትብብር ችሎታውን እንዲያዳብር ዕድል ይሰጠዋል። እንዲሁም ሌሎች ልጆች ልዩነትን እንዲቀበሉ፣ እንዲከባበሩ እና እንዲረዳዱ ያስተምራል።
ነገር ግን ልጁን በመደበኛ ክፍል ውስጥ ማስቀመጥ ብቻ በአካቶ ትምህርት እየተማረ ነው ማለት አይቻልም። ልጁ በክፍል ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን ተገቢ የማስተማሪያ ዘዴ፣ የግል ትምህርት ዕቅድ (IEP)፣ የመማሪያ ማስተካከያ፣ ተጨማሪ ጊዜ፣ የመግባቢያ ድጋፍ ወይም ሌሎች የሚያስፈልጉት ድጋፎች ሊቀርቡለት ይገባል። ይህ ካልተደረገ ልጁ በክፍል ውስጥ ቢገኝም ከትምህርቱ ሊገለል ይችላል።
በሌላ በኩል፣ ልዩ ትምህርት ቤት ለአንዳንድ ልጆች የበለጠ ልዩ የሆነ የትምህርት አካባቢ፣ ልዩ ባለሙያዎች እና የተለያዩ የማገዣ መሳሪያዎችን ሊያቀርብ ይችላል። ስለዚህ የልጁ ፍላጎት በአካቶ ትምህርት ቤት በበቂ ሁኔታ ሊሟላ ካልቻለ ልዩ ትምህርት ቤት ተገቢ አማራጭ ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ የተሻለው ውሳኔ ልጆችን በምድብ መከፋፈል ሳይሆን እያንዳንዱ ልጅ የሚማርበት፣ የሚሳተፍበት፣ የሚከበርበት እና አቅሙን በተሻለ ሁኔታ የሚያዳብርበትን አካባቢ መምረጥ ነው። ዋናው ግብ ልጁ የት እንደሚማር ሳይሆን የትምህርት መብቱን በእኩልነት እንዲያገኝ፣ በንቃት እንዲሳተፍ እና ከአቅሙ በሚችለው ከፍተኛ ደረጃ እንዲያድግ ማስቻል ነው። | 561 |
| 7 | የኦቲዝም ሶስቱ የድጋፍ ደረጃዎች
የኦቲዝም ስፔክትረም ልዩነቶች ከልጅ ወደ ልጅ በጣም ይለያያሉ። ስለዚህ የኦቲዝም ምርመራ ሲደረግ ልጁ ምን ያህል የድጋፍ ፍላጎት እንዳለው ለመግለጽ ሶስት የድጋፍ ደረጃዎች ይጠቀማሉ። ይህ ደረጃ የልጁን የጉብዝና ደረጃ፣ የመማር አቅም ወይም የሰውነት ችሎታ አይመዝንም፤ በዋናነት ልጁ በማህበራዊ መግባባት፣ ለለውጥ መላመድ እና ተደጋጋሚ ባህሪዎችን በመቆጣጠር ረገድ ምን ያህል ድጋፍ እንደሚፈልግ ያመለክታል።
1. የመጀመሪያ ደረጃ (Level 1) — ድጋፍ የሚያስፈልገው ኦቲዝም (Requiring Support)
በዚህ ደረጃ ያለ ልጅ ከሌሎች ጋር ግንኙነት ሲፈጥር ወይም ውይይት ሲያደርግ ከእድሜው ጋር ሲነጻጸር ችግር ሊያሳይ ይችላል። ለምሳሌ ውይይትን ራሱ መጀመር፣ የሌላውን ሰው ምላሽ መረዳት ወይም የውይይት ሂደትን መቀጠል ሊከብደው ይችላል። እንዲሁም የተለመደው የዕለት ተዕለት ሥርዓት ሲቀየር ተጨማሪ መመሪያና ድጋፍ ሊፈልግ ይችላል። ተገቢ የሆነ ድጋፍ ሲሰጠው ግን በብዙ የትምህርትና የዕለት ተዕለት ተግባራት በተሻለ ሁኔታ መሳተፍ ይችላል።
2. ሁለተኛ ደረጃ (Level 2) — ከፍተኛ ድጋፍ የሚያስፈልገው ኦቲዝም (Requiring Substantial Support)
በዚህ ደረጃ ያለ ልጅ የማህበራዊ መግባባት ችግሩ የበለጠ ግልጽ ሊሆን ይችላል። ሌሎችን ሰዎች ለመቅረብ፣ የሚፈልገውን ለመግለጽ ወይም የሌሎችን የግንኙነት ምላሽ ለመረዳት ተጨማሪ ድጋፍ ይፈልጋል። በተጨማሪም የተለመደ ሥርዓቱ ሲቀየር ወይም የሚፈልገው ነገር ሳይገኝ ሲቀር ከፍተኛ ብስጭት ሊያሳይ ይችላል። ተደጋጋሚ ባህሪዎች ወይም ጥብቅ የፍላጎት ዘይቤዎችም በመማርና በማህበራዊ ተሳትፎ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ ሊኖራቸው ይችላል።
3. ሶስተኛ ደረጃ (Level 3) — በጣም ከፍተኛ ድጋፍ የሚያስፈልገው ኦቲዝም (Requiring Very Substantial Support)
በዚህ ደረጃ ያለ ልጅ በማህበራዊ መግባባትና ሌሎች ሰዎችን በተግባር ለመገናኘት ከፍተኛ ችግር ሊያሳይ ይችላል። ፍላጎቱን፣ ፍርሃቱን ወይም የሚያስፈልገውን ነገር በቃል ወይም በሌላ የመግባቢያ ዘዴ ለማሳወቅ በጣም ተጨማሪ ድጋፍ ሊፈልግ ይችላል። የተለመደ ሥርዓት ሲቀየር መላመድ በጣም ሊከብደው ይችላል፤ ተደጋጋሚ ባህሪዎችና ጥብቅ ፍላጎቶችም በትምህርት፣ በግንኙነትና በዕለታዊ ኑሮ ላይ ከፍተኛ መሰናክል ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ ልጁ በተለያዩ የሕይወት አካባቢዎች ቀጣይነት ያለው እና ከፍተኛ የሆነ የግለሰብ ድጋፍ ሊፈልግ ይችላል።
ለማስታወስ የሚጠቅም ነጥብ፦ እነዚህ ሶስት ደረጃዎች ልጆችን “ጎበዝ” እና “ጎበዝ ያልሆኑ” ብለው አይከፋፍሉም። የሚያሳዩት የሚያስፈልገው የድጋፍ መጠን ነው። ስለዚህ በልዩ ትምህርት ውስጥ የልጁን የኦቲዝም ደረጃ ብቻ በመመልከት የትምህርት ድጋፍ መወሰን ተገቢ አይደለም። የልጁን ጥንካሬ፣ ፍላጎት፣ የመግባቢያ ችሎታ፣ የመማር ፍላጎት፣ የባህሪ ፍላጎት እና የዕለት ተዕለት ነፃነት በመመርመር የግል ድጋፍ ማዘጋጀት ይገባል። | 435 |
| 8 | بدون متن... | 346 |
| 9 | بدون متن... | 848 |
| 10 | በኦቲዝም ውስጥ የሚታይ የክህሎት መቀነስን (Regression) መረዳት
የክህሎት መቀነስ (Regression) ምንድን ነው?
Regression ወደ አማርኛችን ስንመልሰው ማሽቆልቆል/መመለስ/ወደኋላ መመለስ ማለት ሲሆን ይህም አንድ ልጅ ቀድሞ የተማራቸውንና ያዳበራቸውን ክህሎቶች መልሶ ሲያጣ ማለት ነው።
ይህም የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፦
- የንግግር መቀነስ ወይም ቃላትን መርሳት
- የአይን ንክኪ ወይም ማህበራዊ ግንኙነት መቀነስ
- የጨዋታ ወይም የዕለት ተዕለት ክህሎቶችን (እንደ ራስን መመገብ፣ መልበስ) ማጣት
- የባህሪ መለዋወጥ (ቶሎ መቆጣት) ወይም ራስን ማግለል
* ይህ ሁኔታ በድንገት ወይም በሂደት ሊከሰት ይችላል።
የክህሎት መቀነስ (Regression) ለምን ይከሰታል?
ለዚህ አንድ ወጥ የሆነ ምክንያት ባይኖርም፣ የተለመዱት መንስኤዎች የሚከተሉት ናቸው፦
- የአንጎል እድገት ለውጦች፦ የልጆች እድገት ፍጥነት የተለያየ ነው። አንዳንድ ጊዜ አንጎላቸው ራሱን መልሶ በሚያደራጅበት ወቅት በክህሎቶቻቸው ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
- ውጥረት ወይም ትልልቅ ለውጦች፦ አዳዲስ ነገሮች ለልጁ ከአቅም በላይ ሊሆኑባቸው ይችላሉ። ለምሳሌ፦ አዲስ ትምህርት ቤት፣ የመኖሪያ ቤት መቀየር፣ አዲስ ጨቅላ ህጻን ወደ ቤት ሲመጣ ወይም የለመዱት የዕለት ተዕለት ተግባር ሲቀየር።
- የመግባባት ችግር መፈጠር፦ አንድ ልጅ ፍላጎቱን መግለጽ ካልቻለ፣ ንግግርን መሞከር ሊያቆም ወይም በምትኩ በለቅሶና በንዴት ስሜቱን ሊገልጽ ይችላል።
- የጤና ወይም የስሜት ህዋሳት ችግር፦ እንደ ህመም፣ የእንቅልፍ እጦት ወይም ለከፍተኛ ድምጽና ብርሃን መጋለጥ ለክህሎት መቀነስ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ።
- ልምምድ ማነስ፦ አንድ ክህሎት በየቀኑ ካልተተገበረ ሊረሳ ይችላል።
ወላጆች እንዴት ሊረዱ ይችላሉ?
- በመረጋጋት ሁኔታውን መከታተል፦ የትኞቹ ክህሎቶች ተቀየሩ? መቼ ጀመረ? በወቅቱ ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ? የሚሉትን በማስተዋል መንስኤውን ማወቅ ይቻላል።
- ከመሰረታዊ ነገሮች መጀመር፦ ልጁ ያጣቸውን ክህሎቶች በድጋሚ በቀላል ደረጃ እናስተምረው። "ከዜሮ እየጀመርን ሳይሆን፣ የነበረውን መልሰን እየገነባን ነው" ብለን እናስብ።
- የተለመዱ ተግባራትን አለማዛባት፦ በየቀኑ ተመሳሳይ የጊዜ ሰሌዳ ይኑረን። ለውጦች ከመደረጋቸው በፊት አስቀድመን ማሳወቅ፤ ምስሎችን በመጠቀምም ነገሮችን ማስረዳት አለብን።
- የመግባቢያ መንገዶችን ማበረታታት፦ ልጁ በእጅ ምልክትም ይሁን በምስል ለመግባባት የሚያደርገውን ሙከራ ሁሉ መቀበል አለብን። ምርጫዎችን እንስጠው (ለምሳሌ፦ "ውሃ ወይስ ወተት?")።
- ጥረቱን ማድነቅ፦ ውጤቱን ብቻ ሳይሆን ሙከራውንም እናበረታታ። ለትናንሽ ስኬቶች ሽልማት እንስጥ።
- ውጥረትን መቀነስ፦ ጸጥ ያሉ ቦታዎችን እናዘጋጅለት። ለልጁ የሚረብሹትን ድምጾች ወይም ብርሃናት እናስወግድ።
- ከባለሙያዎች ጋር መሥራት፦ ከህክምና ባለሙያዎችና ከመምህራን ጋር በቅንጅት መስራት ፈጣን መሻሻል ለማምጣት ይረዳል።
ተጨማሪ እርዳታስ መቼ ያስፈልጋል?
የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ባለሙያ እናማክር፦
- የክህሎት መቀነሱ እየቀጠለ ከሄደ
- ልጁ ሙሉ በሙሉ መግባባት ካቆመ
- ድንገተኛና ከፍተኛ የባህሪ ለውጦች ከታዩ
ለወላጆች ማሳሰቢያ
- የክህሎት መቀነስ የሚያስደነግጥ ቢሆንም ተስፋ አስቆራጭ ግን አይደለም።
- ብዙ ልጆች ተገቢው ድጋፍ ከተደረገላቸው ክህሎቶቻቸውን መልሰው ያገኛሉ።
- ለዚህ ሁኔታ መከሰት ተጠያቂዎቹ እኛ አይደለንም።
- የእኛ ትዕግሥትና ድጋፍ ለልጁ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። | 851 |
| 11 | بدون متن... | 787 |
| 12 | ስለ ኦቲዝም (Autism) ማወቅ የሚገቡን ቁልፍ ነጥቦች
ኦቲዝም ምንድን ነው?
ኦቲዝም ወይም ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር (ASD) የልጆችን ማህበራዊ ግንኙነት፣ ተግባቦት (ንግግር) እንዲሁም ባህሪ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር የነርቭ እድገት ሁኔታ ነው። «ስፔክትረም» የተባለበት ምክንያት ምልክቶቹ የአንዱ ልጅ ሁኔታ ከሌላው ልጅ በጥንካሬያቸውና በዓይነታቸው ስለሚለያዩ ነው።
የኦቲዝም ቁጥር መጨመር ምክንያቶች
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በወላጆች፣ በመምህራንና በዶክተሮች ዘንድ ያለው ግንዛቤ እየጨመረ በመምጣቱ ምልክቶቹን ቀድሞ መለየት ተችሏል። ቀደም ሲል መጠነኛ ምልክት ያላቸው ልጆች ትኩረት ሳይሰጣቸው ይታለፉ ነበር፤ አሁን ግን በዘመናዊ የምርመራ ዘዴዎች ገና በለጋነታቸው መለየት ተችሏል።
መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?
ሳይንሳዊ ምርምሮች እንደሚያሳዩት ለኦቲዝም ዋነኛው መንስኤ የዘር ውርስ (Genetic factors) ነው። ከዚህ በተጨማሪ፦
- ያልተሟላ የእርግዝና ጊዜ (ከቀኑ ቀድሞ መወለድ)
- በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥሙ የጤና እክሎች
- አንዳንድ አካባቢያዊ ሁኔታዎች ለችግሩ የመጋለጥ እድልን ሊጨምሩ ይችላሉ።
የተሳሳቱ አመለካከቶች
- ኦቲዝም በወላጆች የአስተዳደግ ጉድለት የሚመጣ አይደለም።
- በክትባትና በኦቲዝም መካከል ምንም አይነት ሳይንሳዊ ግንኙነት የለም።
🚨 ወላጆች ሊያስተውሏቸው የሚገቡ የጥንቃቄ ምልክቶች
ልጅዎ የሚከተሉትን ምልክቶች ካሳየ ወደ ባለሙያ በመውሰድ ማማከር ያስፈልጋል፦
~ ስሙ ሲጠራ ምላሽ ካልሰጠ።
~ የአይን ለአይን ግንኙነት (Eye contact) ካላደረገ ወይም ግንኙነቱ ካነሰ።
~ ንግግር ላይ ከዘገየ።
~ ከሌሎች ልጆች ጋር መጫወት ወይም መቀላቀል ካልፈለገ።
~ አንድን ድርጊት ወይም እንቅስቃሴ ደጋግሞ የሚያደርግ ከሆነ።
🛠️ ቀድሞ መድረስ (Early Intervention) ያለውን ጥቅም
ኦቲዝምን ገና በልጅነት መለየትና ተገቢውን ድጋፍ መስጠት በልጁ እድገት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል። የሚከተሉት የድጋፍ ዓይነቶች ልጁ የዕለት ተዕለት ኑሮውን በብቃት እንዲመራ ይረዱታል፦
- የንግግር ህክምና (Speech Therapy)
- የባህሪ ህክምና (Behavior Therapy)
- የሙያ ህክምና (Occupational Therapy)
- ልዩ የትምህርት ድጋፍ
ለሌሎቹ ያጋሩ።
#autismawareness #autismacceptance #autismsupport #awereness #autismparenting #Ethiopia | 883 |
| 13 | بدون متن... | 594 |
| 14 | ስለ ዲስሌክሲያ (Dyslexia) ወይም የማንበብ ችግር ምን ያህል ያውቃሉ? 📚🧠
እንደ ሀገራችን ባሉ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ውስጥ ብዙ ጊዜ ልጆች ማንበብና መፃፍ ካልቻሉ «ሰነፍ ናቸው» ተብለው ይታወቃሉ። ሰዎች «ውይ! የእከሌ ልጅ እኮ ሰነፍ ነው፤ የሰው ስም እንኳን በአግባቡ ማንበብ አይችልም» በማለት ከብልህነቱ ጋር ያያይዙታል። ነገር ግን ምክንያቱ ዲክሌክሲያ (Dyslexia) ሊሆን ይችላል። ዲክሌክሲያ ከልጁ ብልህነት ወይም የማሰብ ችሎታ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ነገር ግን አእምሮ ቃላትንና ድምጾችን የሚረዳበት መንገድ ልዩ በመሆኑ ምክንያት የሚከሰት የተፈጥሮ ሁኔታ ነው።
«ሰነፍ» የሚለው ቃል ራሱን የቻለ ትንታኔ ቢፈልግም በተለምዶ አጠራር «ሰነፍ» ልጆች አብዛኛውን ጊዜ በሁሉም ነገር (በንግግር፣ በጨዋታ፣ በንባብ…) ፍላጎት ሊያጡ ይችላሉ። ዲስሌክሲያ ያለባቸው ልጆች ግን በፈጠራ፣ በሥዕል፣ በንግግር ጎበዝ ሊሆኑ ይችላሉ። ድንገት ግን ንባብና ፅሁፍ ላይ ሲደርሱ መንገዱ ይጠፋባቸዋል። ይህ የስንፍና ሳይሆን የአዕምሮ መረጃ የማቀናበር ችግር ነው።
🔍 ዲስሌክሲያ ዋና ዋና ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
የንባብ መዘግየት፡ ቃላትን ለማንበብ መቸገር ወይም ደግሞ በጣም በዝግታ ማንበብ።
የፊደላት ድምጽ ግራ መጋባት፡ የፊደላትን ቅርጽ ከድምጻቸው ጋር አዛምዶ ለመጥራት መቸገር።
የአጻጻፍ (Spelling) ችግር፡ ቃላትን በትክክል ለመጻፍ መቸገር።
የቃላት አጠቃቀም፡ የታወቁ ቃላትን እንኳ በንባብ ጊዜ ለማስታወስ መቸገር።
💡 ከዲክሌክሲያ ጋር አብረው ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮች (Comorbidities):
ዲክሌክሲያ ያለባቸው ልጆች የሚከተሉት ተደራራቢ ችግሮች ሊታዩባቸው ይችላሉ፦
ADHD፡ ትኩረትን ሰብሰብ አድርጎ የመቆየት ችግር።
ዲስካልኩሊያ (Dyscalculia)፦ የሒሳብ ስሌቶችን ለመስራት መቸገር።
ልዩ ተሰጥኦ (Giftedness)፦ ብዙ ጊዜ እነዚህ ልጆች በሥዕል፣ በፈጠራ ስራ ወይም በቴክኒክ ሙያ ረገድ በጣም ጎበዝ ናቸው።
⏰ ዲስሌክሲያ መቼ ነው የሚታወቀው?
ብዙውን ጊዜ ልጆቹ 2ኛ ወይም 3ኛ ክፍል አካባቢ ሲደርሱ በግልጽ ይታያል። ነገር ግን ከዚያ በፊትም ምልክቶች ከታዩ ቀድሞ ድጋፍ ማድረግ ለልጁ ውጤታማነት ወሳኝ ነው።
🛠️ መፍትሄው ምንድን ነው?
ዲክሌክሲያ «መድኃኒት» የለውም፣ ነገር ግን ልጁ በተገቢው መንገድ የትምህርት ድጋፍና ልምምድ ካገኘ ስኬታማ ሊሆን ይችላል።
አንዳንድ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች የተሳሳተ አሠራር አለ። ይኸውም የሙዚቃ ቴራፒ ወይም ምሥሎችን ብቻ የማየት ልምምዶች እንደ ብቸኛ መፍትሔ አድርጎ ማየት ነው። እነዚህ ልምምዶች ለልጁ የንባብ ችግር ቀጥተኛ መፍትሄ ላይሆኑ ስለሚችሉ፣ ከእነዚህ በተጨማሪም ሌሎች በሳይንሳዊ መንገድ የተረጋገጡ የንባብ ድጋፎችን (Phonics-based) መጠቀም ይመከራል።
ልጆቻችን «ሰነፍ» ከመባላቸው በፊት ችግራቸውን እንረዳላቸው! ❤️
ፅሁፋችንን በማጋራት ሁሉም ጋር እንዲደርስ ይተባበሩን።
በፌስቡክ ይከታተሉን፦ https://www.facebook.com/snieet
#dyslexia #readingproblems #specialneeds #AwarenessMatters #inclusion #Ethiopia | 649 |
| 15 | بدون متن... | 691 |
| 16 | በሕፃናት ላይ የሚታዩ ሥነልቦናዊ ችግሮች መንስኤ
በሕፃናት ላይ የሚከሰቱ ሥነልቦናዊ (የአዕምሮ ጤና ችግሮች) አብዛኛዎቹ በድንገት የሚከሰቱ አይደሉም። ይልቁንም ሥነሕይወታዊ፣ ሥነልቦናዊና ማህበራዊ ሁኔታዎች ተደማምረው ቀስ በቀስ የሚያመጡት ነው። እያንዳንዱ ሕፃን የተለያየ ባህሪ እንዳለው ሁሉ የችግሮቹም መንስኤ ሊለያይ ይችላል። ታዲያ ዋና ዋናዎቹ መንስኤዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?
ሥነሕይወታዊ (Biological)ና የዘር ውርስ፦ በቤተሰብ ውስጥ የድብርት፣ የጭንቀት፣ የአትኩሮት ማጣትና የመቅበጥበጥ ባህሪ (ADHD)፣ ኦቲዝም ወይም ሌሎች የነርቭ ሕመሞች ታሪክ ካለ ለሥነልቦናዊ ችግር የመጋለጥ ዕድሉ ሰፊ ሊሆን ይችላል።
የወላጆች አያያዝና የቤት ውስጥ ሁኔታ፦ በቤተሰብ መካከል የሚፈጠር ግጭት፣ የልጁን ፍላጎት ችላ ማለት፣ ጠንካራ ወይም ጨካኝ የቅጣት እርምጃዎች እንዲሁም ለልጆች በቂ የሆነ ስሜታዊ ድጋፍ አለመስጠት ወዘተ የችግሩ መንስዔ ሊሆኑ ይችላሉ።
አሰቃቂ ገጠመኞች (Trauma)ና ውጥረት፦ አካላዊ ወይም ስሜታዊ ጥቃት፣ በትምህርት ቤት የሚደርስ ትንኮሳ (Bullying)፣ የቅርብ ሰውን በሞት ማጣት ወይም ድንገተኛ አደጋዎች ወዘተ እንደዚሁ ተጠቃሽ መንስዔዎች ናቸው።
የትምህርት ጫና፦ በተለይም ባለንበት ዘመን ወላጆች ከልጁ አቅም በላይ የሆነ ውጤት የመጠበቅ ፍላጎት አለ። ይሄ አካሄድ ደግሞ አደገኛ ነው። በተጨማሪም ልጆች ራሳቸው በውድድር ውስጥ የመሸነፍ ፍርሃት ወይም የመማር ችግር (Learning difficulties) ውስጥ ይወድቁና ለሥነልቦናዊ እክሎች ይጋለጣሉ።
የማህበራዊ ሚዲያና የቴክኖሎጂ ተጽዕኖ፦ ከልክ በላይ ስክሪንን መመልከት (ስልክ፣ ቲቪ፣ ታብሌት) ወይም ሕፃናት ለማይገቡ ምስሎችና መረጃዎች መጋለጥ ሥነልቦናዊ እክልን ያመጣል።
አካላዊ ጤናና የአኗኗር ዘይቤ፦ ሥር የሰደደ ሕመም፣ የአስፈላጊ ንጥረ ነገር እጥረት (የምግብ እጥረት) ወይም በቂ እንቅልፍ አለማግኘት እንደዚሁ ተጋላጭ ያደርጋሉ።
በአጠቃላይ በልጆቻትን ላይ የሚከተሉት ምልክቶች ለረጅም ጊዜ ዘልቀው ከታዩ የባለሙያ ምክር ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው። እነሱም፡-
የባህሪ ለውጥ፦ ተከታታይ የሆነ የሐዘን ስሜት፣ ከፍተኛ ቁጣ ወይም ራስን ከሰዎች የማግለል ባህሪ በተከታታይ ካሳየ፤
የአካል ለውጥ፦ የእንቅልፍ መዛባት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም መጨመር ካለ፤
የትምህርት ሁኔታ፦ በትምህርት ቤት የሚታይ የውጤት ማሽቆልቆል ወይም የመማር ፍላጎት መቀነስ ካለ በትኩረት መከታተልና ባለሙያን ማማከር ያስፈልጋል።
#parenting #parentingtips #ParentingSupport #psychology #parenthood #parents #children #Psychological #Ethiopia | 876 |
| 17 | بدون متن... | 515 |
| 18 | የABA ቴራፒ (Applied Behavior Analysis)
ABA (ተግባራዊ የባህሪ ትንተና) የኦቲዝም ችግር ላለባቸው ልጆችና የተለያዩ የዕድገት ውስንነት ለሚታይባቸው ልጆች የሚሰጥ ሳይንሳዊ የድጋፍ ዘዴ ነው። ይህ የሕክምና ዘዴ ልጆች ጠቃሚ የሆኑ የሕይወት ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ እንዲሁም አስቸጋሪ የሆኑ የባህሪ ችግሮችን በአዎንታዊ ማበረታቻ (Positive Reinforcement) እንዲቀንሱ ይረዳል።
የABA ቴራፒ ዋና ዋና ጥቅሞች
የተግባቦት ክህሎትን ይጨምራል፦ ንግግርን፣ በምልክት መረዳዳትንና ፍላጎትን በግልጽ መግለጽን ለማሳደግ ይጠቅማል።
ማህበራዊ ግንኙነትን ያጠናክራል፦ ከእኩዮች ጋር አብሮ መጫወትን፣ ሰላምታ መለዋወጥንና ግለሰባዊ ድንበሮችን ማወቅን ማለማመድ ያስተምራል።
የዕለት ተዕለት የሕይወት ክህሎትን ያሻሽላል፦ ራስን መመገብ፣ የግል ንጽህና መጠበቅንና መመሪያዎችን ተከታትሎ መተግበርን ያካትታል።
ባህሪንና ስሜትን ለመቆጣጠር፦ የንዴት፣ ግልፍተኝነትና የስሜት መረበሽን (Sensory triggers) በአግባቡ ለመቆጣጠር ይረዳል።
ራስን መቻልን ያለማምዳል፦ ልጁ በራሱ እንዲተማመንና ሌሎችን ሳይጠብቅ ራሱን ማገዝ እንዲችል ያደርጋል።
እያንዳንዱ የABA መርሃ-ግብር እንደ ልጁ የግል ፍላጎትና ጥንካሬ የሚቀረጽ ሲሆን፤ አገልግሎቱም በቤት፣ በትምህርት ቤት ወይም በልዩ ማዕከላት ሊሰጥ ይችላል።
የABA ቴራፒ ውጤታማ የሚሆነው የልጁን ስብዕናና ስሜት ባከበረ መልኩ ሲተገበር ብቻ ነው። ዘመናዊው አቀራረብ ልጁን ከማስገደድ ይልቅ ፍላጎቱን ተከትሎ ማስተማር ላይ ያተኩራል። በመሆኑም በቂ ስልጠናና ርህራሄ ያለው ባለሙያ መምረጥ ለለውጡ መሰረት ነው።
ወላጆች ቴራፒ ከመጀመራቸው በፊት ሊጠይቋቸው የሚገቡ ጥያቄዎች
የአሰልጣኙ አቀራረብ የልጁን ፍላጎትና ዝንባሌ (Child-led) ያከበረ ነው?
አስቸጋሪ ባህሪያት የሚታረሙት በምን ዓይነት ዘዴ ነው?
ተቋሙ በቂና የሰለጠነ የሰው ኃይል አለው?
የልጁ ለውጥ ወይም እድገት የሚለካው በምን መስፈርት ነው?
በአጠቃላይ ABA ሕፃናት የተሻለ የሕይወት ክህሎት እንዲኖራቸው ትልቅ አስተዋጽኦ ቢኖረውም፣ የእያንዳንዱ ልጅ እድገትና ፍላጎት ግን የተለያየ ነው። ትክክለኛው ባለሙያ፣ የቤተሰብ ንቁ ተሳትፎና የቴራፒው አቀራረብ ለስኬቱ ወሳኝ ናቸው። | 546 |
| 19 | بدون متن... | 491 |
| 20 | እንዴት በአዎንታዊ መንገድ የልጆችን ፀባይ መቀየር ይቻላል?
የልጆችን ፀባይ መቀየር ትዕግስትን፣ ያላሰለሰ ክትትልንና ፍቅርን ይጠይቃል። ቤት ውስጥም ሆነ ትምህርት ቤት፣ እነዚህ ቀላል ስልቶች ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ።
ውጤታማ የሆኑ ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ፤
1. ከፀባዩ ጀርባ ያለውን ምክንያት መረዳት/Understand the Behavior
ልጁን ከመቅጣታችን በፊት ያለበትን ሁኔታ ማስተዋል ያስፈልጋል። «ልጁ ደክሞታል? ርቦታል? ወይንስ ትኩረት ይፈልጋል?» ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። ብዙ ጊዜ ልጆች መጥፎ ፀባይ የሚያሳዩት የተቸገሩበትን ነገር መግለጥ ሲፈልጉ ነው።
2. ግልጽና ቀላል ደንቦችን ማስቀመጥ/ Set Clear and Simple Expectations
አጫጭርና የማይቀያየሩ ደንቦችን መጠቀም አለብን። እነዚህንም ደንቦች ለልጆች በአወንታዊ መልኩ ማስተማር አለብን። ለምሣሌ፦
«ቤት ውስጥ ጥሩ/ አወንታዊ ቃላትን እንጠቀም።»
«እጃችን የተፈጠረው ሰው ለመርዳት እንጂ ለመምታት አይደለም።» የሚሉ ህጎችን ማውጣት።
3. ጥሩ ሲያደርጉ ማበረታታት/Reinforce Postive Behavior
ልጆችን ጥፋት ሲያጠፉ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ነገር ሲያደርጉም መመልከትና እውቅና መስጠት አለብን። ለምሣሌ፦ «መጫወቻህን ለእህትህ ስለሰጠሃት በጣም ደስ ብሎኛል!» በማለት ማወደስ አለብን።
4. ምክንያታዊ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ/ Use Fair Consequences
የምንወስዳቸው እርምጃዎች ምክንያታዊና እርጋታ ያለባቸው መሆን አለበት። አንዳንዴ በተፈጠረው ችግር ውስጥ ተውጠን ምክንያቱን ሳናጣራ አላስፈላጊ እርምጃዎችን እንወስዳለን። ልጆች ላይ መጮህ ወይም እነሱን መምታት ፍርሃትን እንጂ ትምህርት አይሰጥም።
5. ወጥ የሆነ አቋም/ Be Consistent
ለልጆች የምንሰጠው ደንብ ዛሬም ነገም ሁሌም ተመሳሳይ መሆን አለበት። በመሆኑም ወላጆች፣ መምህራንና የልጆች ተንከባካቢዎች አንድ ዓይነት ደንብ መተግበር አለባቸው።
6. ስሜታቸውን እንዲያውቁ ማስተማር/ Teach Emotional Skills
ልጆች የሚሰማቸውን ስሜት በስም እንዲጠሩት እንርዳቸው። «ተናደሻል አይደል? ይገባኛል» የሚሉ ቃላትን እንጠቀም።
ከዚያም ስሜትን የማረጋጋት ብልሃቶችን ማለማመድ
- በጥልቀት እንዲተነፍሱ ማድረግ
- እስከ 10 እንዲቆጥሩ… ማድረግ አለብን።
7. ምርጫ መስጠት/Offer Choices
ልጆች እልኸኛ እንዳይሆኑ ቀላል ምርጫዎችን ብንሰጣቸው የተሻለ ነው። «የቱን መልበስ ትፈልጋለህ? ቀዩን ሸሚዝ ወይስ ሰማያዊውን?» ማለት። እንደዚህ ያሉ ምርጫዎች ልጆችን በራሳቸው እንዲተማመኑ ይረዳል።
8. ሥዕላዊ መግለጫዎችን መጠቀም (በተለይ ልዩ ፍላጎት ላላቸው ልጆች)
ኦቲዝም፣ የአትኩሮት ማጣትና የመቅበጥበጥ ችግር (ADHD) ወይም የመማር ችግር ላለባቸው ልጆች የቀን ውሏቸውን በሥዕል መልኩ ማሳየት፥ በዕለቱ ምን እንደሚጠበቅባቸው እንዲረዱት ትልቅ እገዛ ያደርጋል።
9. መወገድ ያለባቸው የተለመዱ ስህተቶች
- ልጆች ጥፋት ሲያጠፉ ብቻ ትኩረት መስጠት፦ ልጆች ጥሩ ነገር ሲያደርጉ ትኩረት ካልሰጠናቸው፣ የእኛን ትኩረት ለማግኘት ሲሉ መጥፎ ፀባይ ሊያዳብሩ ይችላሉ። ስለዚህ በጥሩ ፀባያቸው ላይ ትኩረት እናድርግ።
- መነሻ ምክንያቶችን ችላ ማለት፦ ድካም፣ ረሃብ ወይም በአካባቢያቸው ያለው ግርግር የልጆችን ፀባይ ሊቀይሩ ይችላሉ። ከመቆጣታችን በፊት ልጁ የተራበ ወይም የደከመ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል።
- አቋም አልባ መሆን/Inconsistency፦ ዛሬ የከለከልነውን ነገር ነገ ከፈቀድን ልጁ ግራ ይጋባል። ደንቦች ሁልጊዜም ተመሳሳይ መሆን አለባቸው።
በፌስቡክ ይከታተሉን https://www.facebook.com/snieet | 863 |
