fa
Feedback
ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

رفتن به کانال در Telegram

Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

کانال ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 13 369 مشترک است و جایگاه 1 754 را در دسته حمل و نقل و رتبه 2 531 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 13 369 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 19 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 119 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 19 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 40.59% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 15.42% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 5 423 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 2 060 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 11 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 21 ژوئن, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته حمل و نقل تبدیل کرده‌اند.

13 369
مشترکین
+1924 ساعت
+677 روز
+11930 روز
آرشیو پست ها
photo_2021-10-21_11-41-38.jpg1.14 KB

photo_2021-10-21_11-42-04.jpg0.99 KB

photo_2021-10-21_11-42-41.jpg0.58 KB

photo_2021-10-21_11-43-31.jpg0.49 KB

የኤዶ - ሶሮፍታ - ወርቃ የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ

ዲማ ራድ ብሪጅ

የሚረዝምው የጅግጅጋ-ገለለሽ ኮንትራት ሁለት እና ሶስት የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት
+4
የሚረዝምው የጅግጅጋ-ገለለሽ ኮንትራት ሁለት እና ሶስት የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት

110 ኪሎ ሜትር የሚረዝምው የጅግጅጋ-ገለለሽ ኮንትራት ሁለት እና ሶስት የአስፋልት መንገድ ግንባታ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ባሳለፍነው በጀት አመት የተጀመረው ይህው ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት ፣ ትንንሽና መካከለኛ ማፋሰሻዎችን እንዲሁም በርካታ የስትራክቸር ስራዎችን አካቶ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ግንባታውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው ቤአይካ ጄኔራል ቢዝነስ ፒኤልሲ ነው። የግንባታዉ ሙሉ ወጪም (አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ ሃያስምንት ሚሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ አራት ሺህ ብር በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ይሆናል፡፡ አጠቃላይ ስራውን በሶስት ዓመት ተኩል ዉስጥ ለማጠናቀቅ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር የስምምነት ውል የተፈራረመው ይህ የስራ ተቋራጭ ግንባታውን ቀድሞ በመጀመር አጠቃላይ አፈጻጸሙ በአሁኑ ሰዓት 20 በመቶ ላይ ደርሷል ። የመንገዱን የማማከርና የቁጥጥር ስራ ሲ ቴክ ኢንጂነሪንግ ፒኤልሲ (C Tech Enginnering P.L.C) እየሰራ ነው። የመንገድ ፕሮጀክቱ በዞን ከተማ 21 ሜትር እና በገጠር 10 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ መስመሩ ከሚያስተናግደው የተሸከርካሪ ብዛት፣ ማህበራዊና ኢኮኖማዊ ፋይዳ አኳያ እንዲሁም ከከተማው ቀጣይ እድገት ጋር ታልሞ በአስፋልት ደረጃ እንዲገነባ እየተደረገ ነው። ግንባታው ሲጠናቀቅ የገለለሽ ፣ ደጋሃመድ እና እንሰግድ አካባቢዎችን ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ ከሚወስደው ዋና መንገድ ጋር በማስተሳሰር ከዚህ ቀደም በአካባቢው ይከሰት የነበረውን የትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ ያስችላል፡፡ ከጅግጅጋ ወደ ደነን የሚወስድ ተለዋጭ መንገድ ስለሚኖረው የአካባቢዉን ማህበረሰብ አማራጭ የትራንስፖርት ተጠቃሚ እንዲሆን ያደርገዋል። በተጨማሪም የጤና ፣ የትምህርት እና ሌሎች የማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲስፋፉ እና በአካባቢው የሚገኙ ትንንሽ ከተሞች እንዲያድጉ ከማድረግ አኳያ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነዉ፡፡ ከዚህ ቀደም ይወስድ የነበረውን የጉዞ ጊዜ በማሳጠር በቂ የሆነ የትራንስፖርት ምልልስ እንዲኖር ያደርጋል።

በመቱ-ውጠቴ አውራ መንገድ ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት ምክንያት የከባድ ተሸከርካሪዎች ጉዞን ተቋረጦ የነበረው መንገድ ተጠግኖ መደበኛ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። የመሬት መንሸራተቱ ያጋጠ
በመቱ-ውጠቴ አውራ መንገድ ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት ምክንያት የከባድ ተሸከርካሪዎች ጉዞን ተቋረጦ የነበረው መንገድ ተጠግኖ መደበኛ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። የመሬት መንሸራተቱ ያጋጠመው በትላትናው እልት ውጠቴ ቀበሌ ኦዳ ዶጊ በመባል የሚታወቅ ስፍራ ላይ ነው። ይህን ተከትሎም በኢመባ የጅማ ዲስትሪክት ያጋጠመውን የመሬት መንሸራተት በአሰቸኳይ ጥግና በራስ ሀይል በመስራት መስመሩን ክፍት ማድረግ ተችሏል። በአሁኑ ሰአትም መደበኛ የትራንስፖርት ፍሰቱ ወደ ነበረበት ሙሉ ለሙሉ ተመልሷል አካባቢው የመሬት መንሸራተት የሚከሰተበት በመሆኑ ዘላቂ መፈትሄ ለመስጠትም ጥረቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

የዶጎሎ-ከለላ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት
+4
የዶጎሎ-ከለላ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት

የዶጎሎ ከለላ
+4
የዶጎሎ ከለላ

72 ኪ. ሜትር የሚረዝመው የዶጎሎ-ከለላ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመፋጠን ላይ ነው። እስካሁን ባለው አፈጻጸምም ከ40ኪ.ሜትር በላይ አስፋልት የማንጠፍ ስራ ተከናውኗል። እንዲሁም የአፈር ሙሌትና፣ ድልዳሎ፣የውሃ መፋሰሻ ቱቦ ቀበራ እና ድልድዮች ግንባታ ፣ የሰብ ቤዝ ስራ እንዲሁም የቤዝ ኮርስ ማምረት ፣ የአቃፊ ግንብ እና ሌሎች የግንባታ ስራዎች እየተሰሩ ነው በቀጣይ ቀሪ ስራዎች በያዝነው በጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው። አንድ ቢሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሚሊየን ስምንት መቶ አርባ ስድስት ሺህ ብር ወጪ እየተደረገበት የሚገኘውን ይህን የመንገድ ፕሮጀክት የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው። ሀገር በቀሉ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ ግንባታውን እያከናወነው ሲሆን የማማከርና የቁጥር ሥራውን ደግሞ ቤዛ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ኃ/የተ/የግ/ማ እያካሄደው ይገኛል። የዶጎሎ-ከለላ የመንገድ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲሆን ካለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ አንጻር በአስፋልት ደረጃ እንዲገነባ ሆኗል። መስመሩ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን ስር የሚገኝ ሲሆን የግንባታው መጠናቀቅ በዋነኝነት የጃማ ወረዳን እና የከለላ ወረዳን ምቹ በሆነ አስፋልት መንገድ ያስተሳስራል ። ግንባታው ሲጠናቀቅ በአካባቢው የሚገኘውን ከፍተኛ የግብርና ምርቶችን ወደ ማዕከላዊ ገበያ በተሻለ ዋጋ በመሸጥ አምራች እና ሸማቹን ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል። በተለይም የአባ ጊዮርጊስ ዘ-ጋስጫ ገዳም እና የሼህ ሁሴን መስጊድ በአካባቢው ስለሚገኙ የመንገዱ መገንባት ወደ ስፍራዉ የሚደረገውን ጉዞ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች አመች ያደርገዋል፡፡ የመንገድ ፕሮጀክቱ የጎን ስፋት በወረዳ 21. ሜትር በቀበሌ 12 ሜትር እንዲሁም በገጠር የመንገድ ትከሻን ጨምሮ 8-1ዐ ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ነው የተገነባው።

የሞጆ - ሃዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነውን የሞጆ - መቂ - ባቱ መዕራፍ አንድ /92 ኪሜ /ፈጣን መንገድ ዛሬ በይፍ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። የምዕራፍ አንድ የሞጆ መቂ ባቱ መንገድ ከወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዳክተር አቢይ አህመድ መመረቁ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም የፍጥነት መንገዱንለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ በርካታ የማጠቃለያ ስራዎችን ሲከናወኑ ቆይተዋል። ከነዚህም መካከል የክፍያ ጣቢያዎች ግንባታ፣የትራፊክ ምልክቶች ተከላ ቴክኖሎጂን የማሞላት ስራዎችን ጨምሮ ሌሎች ተጓዳኘ ስራዎች ተጠናቀዋል። ይህን ተከትሎም ዛሬ በሞጆ የፈጣን መንገዱ መግቢያ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት አገልግሎት የማስጀመር መርሃ ግብር ተካሂዷል። የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ዘመናዊና ፈጣን መንገዱ አገልግሎት መጀመሩ ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ ሚናን እንደሚያበረክት ተናግረዋል። የፍጥነት መንገዱ የግብርና ምርታማነትን በመስመሩ የሚገኙትን ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለጎብኚዎች ተደራሽ በማድረግ እረገድ ዘርፈ ብዙ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል። በመንገዱ ክልል ውስጥ ያሉ ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ላሉ እና በቀጣይ ለመገንባት በታቀዱ ግዙፍ የኢንዱስትሪ እና የአግሮፕሮሰሲንግ ፓርኮች ደረጃቸውን የጠበቀ መንገዶችን በማቅረብ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በሚደረገው ጥረት የፍጥነት መንገዱ ጉልህ ሚናን ያበረክታል ያሉት ደግሞ የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ ናቸው። የሞጆ መቂ ባቱ የፍጥነት መንገድ ከነባሩ መንገድ ትይዩ በአዲስ መልክ ከእንስሳት እና ከሰዎች እንቅስቃሴ ነጻ በሆነ መልኩ የተገነባ እንደሆነም እና ከአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ በመቀጠል ለአገራችን ሁለተኛው ፍጥነት መንገድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህ መንገድ ፍጻሜውን አግኝቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ ላስቻሉ ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የምዕራፍ አንድ የሞጆ - መቂ - ባቱ የፍጥነት መንገድ በሁለት ኮንትራት የተከፈለ ሲሆን አሱም ሞጆ - መቂ 56 ኪሜ እና መቂ -ባቱ 36 ኪ.ሜ ናቸው ። ከሞጆ እስከ ባቱ በተዘረጋው 92 ኪሜ ውስጥ 6 ያህል ከነባሩ መንገድ ጋር የሚያገናኙ ማሳለጨዎች ተገንብቶለታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለእግረኛ ከመንገድ በታች እና በላይ 45 መተላለፊያ አሉት ፡፡ በአጠቃላይ ሞጆ መቂ ባቱን ጨምሮ ሃዋሳ ድረስ የሚዘልቀው 202 ኪ .ሜ የፍጥነት መንገድ የጎን ስፋቱ 32 ሜትር ነው፡፡ የመንገድ አካፋዩ በዚህ ደረጃ እንዲሰፋ የተደረገው በተቃራኒ አቅጣጫ ያለን ተሸከርካሪን በመለየት አደጋን ለማስወገድ አልያም ለመቀንስ ነው፡፡ የመንገዱ አጠቃላይ ወሰን 90 ሜትር ስፋት ያለው ነው፡፡ ይህም በቀጣይ ለሚኖረው የማስፋፋት ስራ በቂ ቦታ እንዲኖር የሚያስችል ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂን መሰረት ባደረገ መልኩ ችግኞች መተከል ተጀምረዋል፡፡ በፍጥነት መንገዱ ለመጠቀም የተቀመጠለት የፍጥነት ገደብ በሰአት ከ80 እስከ 120 ኪሜ ነው፡፡ የክፍያ መንገዶች ኢንተር ፕራይስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙስጠፍ አባሲመል በበኩላቸው ግዙፍ የሀገር ሀብት የፈሰሰበትን መሰረተ ልማት መላው የመንገዱ ተጠቃሚ በባለቤትነት እንዲንከባከበው ጠይቀዋል። የመንገዱ ተጠቃሚዎችም ከአደጋ በጸዳ መልኩ አስፈላጋውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። ይህ ፈጣን መንገድ 10 ሺ ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ከግብጽ ካይሮ ተነስቶ ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ድርስ የተዘረጋው የታላቁ የትራንስ አፍሪካን ሃይዌይ የመንገድ ትስስር አካል ነው ፡፡ የፍጥነት መንገዱ የአዲስ አበባ-ሞያሌ-ናይሮቢ-ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር አካል ሲሆን የኢትዮጵያን የወጪ ገቢ ንግድ እንቅስቃሴን በተሻለ ሁኔታ ለመጠቀም የሚያስች ነው። ቀሪ የመንገዱ ክፍል በተሻለ የግንባታ ፍጥነት ሂደት ላይ ይገኛል።

እንኳን ከዘመን ዘመን በጤና አሸጋገራችሁ! አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የፍቅር እንዲሁም የብልጽግና እንዲሁንላችሁ እንመኛለን።

በከባድ የቋጥኝ ድንጋይ መንሸራተት ምክንያት ተዘግቶ የቀየው የአዲስ አበባ ጎጃም መንገድ በከፊል ተጠግኖ ከትላንት ምሽት ጀምሮ ለትራንስፖርት ክፍት ሆኗል። መንገዱ ክፍት መሆኑን ተከትሎም ምሽቱን እን
+4
በከባድ የቋጥኝ ድንጋይ መንሸራተት ምክንያት ተዘግቶ የቀየው የአዲስ አበባ ጎጃም መንገድ በከፊል ተጠግኖ ከትላንት ምሽት ጀምሮ ለትራንስፖርት ክፍት ሆኗል። መንገዱ ክፍት መሆኑን ተከትሎም ምሽቱን እንዲሁም በአሁኑ ሰዓትም ለቀናት ቆመው የነበሩ መኪኖች መተላለፍ የቻሉ ሲሆን የነበረው መጨናነቅም ወደ መደበኛ ሁኔታው ተመልሷል። በአንድ በኩል የሚያሳልፍ አማራጭ ተለዋጭ መንገድ መሰራቱም የነበረውን የትራፊክ ክምችት እንዲቀንስ አሰተዋጾ አበርክቷል። የአባይ በረሃ አካባቢ የሚንሸራተት ጠመዝማዛና ናዳ የሚበዛበት በመሆኑ እና በዚሁ ስፍራ ከወትሮ የተለየ ግዙፍ ናዳ መከሰቱ ስራውን እጅግ ማክበዱ ይታወሳል ። ሀገራዊ ወሳኝ መተላላፊያ የሆነውን ይህን መሰመር ለመክፈት ኢመባ ቀን ከለሊት ያለሰለስ ጥረት አድርጓል። የተንሸራተተው ናዳ በበርካታ ማሽነሪዎች ብቻ መሰባበር የሚቻል በለመሆኑ ከ160በላይ የድማሚት ፍንዳታዎችን በመጠቀም ቋጥኝ ድንጋዩን በመፈረካክስ ነው መንገዱን ለትራንስፖርት ክፍት ለማድረግ የተቻለው። በስፍራው የስራውን ክብደት ሲከታተሉ የነበሩ በርካታ አሽከርካሪዎች ይህን ከባድ ስራ በቀናት ወስጥ አጠናቆ ለትራንስፖርት ክፍት በማድረጉ ለኢመባ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በቀጣይ የመንገዱን ቀሪ ክፍል ከዘጋው ቋጥኘ ድንጋይ ነጻ ለማድረግና መስመሩን ሙሉ ለሙሉ ወደ ነበረበት ለመመለስ ሲባል ፤ የትራንስፖርት ፍሰቱን ለሰዓታት በመዝጋትና በመከፈት ቀሪ ስራዎቹ እንደሚከናወኑ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ገልጾል።