fa
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

رفتن به کانال در Telegram

EEP Communication

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام EEP Communication

کانال EEP Communication (@eepcommuication) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 15 692 مشترک است و جایگاه 8 014 را در دسته فناوری و برنامه‌ها و رتبه 2 155 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 15 692 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 30 اوت, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 145 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 2 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 31.28% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 16.96% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 909 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 2 661 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 10 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
EEP Communication

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 31 اوت, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته فناوری و برنامه‌ها تبدیل کرده‌اند.

15 692
مشترکین
+224 ساعت
+187 روز
+14530 روز
آرشیو پست ها
ሪጅኑ ተጨማሪ ትራንስፎርመሮችን በመትከል አቅም የማሳደግ ሥራ ላይ ዕቅድ ይዟል …….///…….. በደቡብ 1 ሪጅን በየጊዜው እያደገ ለሚሄደው የኃይል ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት በይርጋለም ቁጥር 2፣ በሐ
+3
ሪጅኑ ተጨማሪ ትራንስፎርመሮችን በመትከል አቅም የማሳደግ ሥራ ላይ ዕቅድ ይዟል …….///…….. በደቡብ 1 ሪጅን በየጊዜው እያደገ ለሚሄደው የኃይል ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት በይርጋለም ቁጥር 2፣ በሐዋሳ ቁጥር 2 እና በዲላ ማከፋፈያ ጣቢያዎች የትራንስፎርመሮችን አቅም ለማሳደግ ዕቅድ መያዙን በሪጅን የማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽንና ጥገና ቢሮ ሥራ አስኪያጅ ገለፁ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ ያለው አማረ እንደተናገሩት የሐዋሳ ቁጥር 1 እና የዲላ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ከተሞቹ አሁን ለደረሱበት ዕድገት ሚናቸው የጎላ ነው። ይሁንና በአሁኑ ወቅት የሐዋሳ ቁጥር 1 ማከፋፈያ ጣቢያን ጨምሮ በሪጅኑ የሚገኙ አብዛኛዎቹ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ጭነታቸው ከ90 በመቶ በላይ በመድረሱ የሚቀርቡ ተጨማሪ የኃይል ፍላጎቶችን በአግባቡ ማስተናገድ የማይችሉበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነው ብለዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ሪጅኑ-ተጨማሪ-ትራንስፎርመሮችን-በመትከ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም

ትናንት ማምሻውን በተፈፀመ ስርቆት አንድ ታወር ሲወድቅ በሀዋሳ ከተማ በከፊል ኃይል ተቋርጧል …….///……. ከይርጋለም ቁጥር 2 - ሐዋሳ ቁጥር 2 በተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመበት ስርቆት ምክንያት አንድ ታወር መውደቁን የደቡብ 1 ሪጅን አስታወቀ። በሪጂኑ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ኦፕሬሽንና ጥገና ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞሲሳ ገልቻ እንደገለፁት ስርቆቱ የማስተላለፊያ መስመሩ በሚያልፍበት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ቱላ ክፍለ ከተማ ጨፌ በሚባል ቀበሌ በሚገኝ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የተፈፀመው ነው። የማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶው በተፈፀመበት ስርቆት ምክንያት በትላንትናው ዕለት ከምሽቱ 12:00 አካባቢ መውደቁን አቶ ሞሲሳ ተናግረዋል። የተፈፀመው ስርቆት ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ብረቶቹን መልሶ ለመጠቀም እንኳ አስቸጋሪ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ እንደ ሥራ አስጂያጁ ገለፃ በስርቆቱ ምክንያት የሐዋሳ ቁጥር 2 ማከፋፈያ ጣቢያ ከይርጋለም ቁጥር 2 ማከፋፈያ ጣቢያ የሚያገኘው ኃይል የተቋረጠ ሲሆን የጣቢያው ኃይል የመስጠት አቅም በከፊል ቀንሷል፡፡ የወደቀውን ምሰሶውን ወደነበረበት ለመመለስ ሥራዎች መጀመራቸውንም የገለፁት አቶ ሞሲሳ የማስተላለፊያ መስመሩ ዳግም ኃይል ማስተላለፍ እስኪጀምር ድረስ በከፊል ኃይል የተቋረጠባቸው ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+6

ከፕሮጀክቱ የእውቀትና ቴክኖሎጅ ሽግግር ተገኝቷል ……….///……. የደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል ከሆነው የወላይታ ሶዶ ቁጥር 2 -አርባ ምንጭ ቁጥር 2- አርባ ምንጭ ቁጥር 1 የኃይል ማስ
+8
ከፕሮጀክቱ የእውቀትና ቴክኖሎጅ ሽግግር ተገኝቷል ……….///……. የደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል ከሆነው የወላይታ ሶዶ ቁጥር 2 -አርባ ምንጭ ቁጥር 2- አርባ ምንጭ ቁጥር 1 የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ የግንባታ ሥራ የእውቀትና የቴክኖሎጅ ሽግግር ማግኘታቸውን በፕሮጀክቱ ሥራ ላይ የተሳተፉ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተናገሩ። በደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራ ተቋራጭ የምዕራፍ አንድ የሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ከበደ እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከሚኖረው ሀገራዊና አካባቢያዊ ፍይዳ ባሻገር በግንባታ ሂደት ላይ እያለ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም የእውቀትና ቴክኖሎጅ ሽግግር እንድኖር በማድረግ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ከፕሮጀክቱ-የእውቀትና-ቴክኖሎጅ-ሽግግር&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም

የሐዋሳ ቁጥር 1 ማከፋፈያ ጣቢያ የከተማዋን 90 በመቶ የኃይል አቅርቦት እየሸፈነ ነው ……..///…….. የሐዋሳ ቁጥር 1 ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ 90 በመቶ የሚሆነ
+5
የሐዋሳ ቁጥር 1 ማከፋፈያ ጣቢያ የከተማዋን 90 በመቶ የኃይል አቅርቦት እየሸፈነ ነው ……..///…….. የሐዋሳ ቁጥር 1 ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ 90 በመቶ የሚሆነውን የከተማዋን የኃይል አቅርቦት እየሸፈነ መሆኑን የጣቢያው ኃላፊ አቶ ታከለ ተፈሪ ተናገሩ። አቶ ታከለ እንደተናገሩት ማከፋፈያ ጣቢያው አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ከ1980 ዓ.ም ጀምሮ የሐዋሳ ቁጥር 2 ማከፋፈያ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት እስከጀመረበት 2011 ዓ.ም ድረስ ለሐዋሳ ከተማና በዙሪያው ለሚገኙ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ሲያቀርብ ቆይቷል። ይሁንና የቁጥር 2 ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ሥራ ከገባ በኋላ ደንበኞችን በማዛወር ኢንዱስትሪዎችን ጨምሮ የተወሰኑ የከተማዋ ደንበኞች ከቁጥር ሁለት ኃይል እንዲያገኙ የተደረገ በመሆኑ በጣቢያው ላይ የነበረውን ጫና በማቃለል በኩል ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የሐዋሳ-ቁጥር-1-ማከፋፈያ-ጣቢያ-የከተማዋን-90&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም

“ሴቶች የኢነርጂ ሽግግር ተቀባዮች ብቻ ሳይሆኑ ወደፊት የሚመሩ መሐንዲሶች እና ውሳኔ ሰጪዎች ናቸው” - ኢንጂነር የምስራች ወርቁ ….….///……... ሴቶች የኢነርጂ ሽግግር ተቀባዮች ብቻ ሳይሆኑ መ
+7
“ሴቶች የኢነርጂ ሽግግር ተቀባዮች ብቻ ሳይሆኑ ወደፊት የሚመሩ መሐንዲሶች እና ውሳኔ ሰጪዎች ናቸው” - ኢንጂነር የምስራች ወርቁ ….….///……... ሴቶች የኢነርጂ ሽግግር ተቀባዮች ብቻ ሳይሆኑ መሪዎች፣ መሐንዲሶች፣ ፈጣሪዎች እና ውሳኔ ሰጪዎች መሆናቸውን በኢትዮጵያ የሴቶች ኢነርጂ ማህበር አምባሳደር (Ethiopian Women in Energy - EWiEn) ኢንጂነር የምስራች ወርቁ ገለጹ፡፡ ኢንጂነሯ ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶች የኢትዮጵያን ኢነርጂ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በመቅረጽ ረገድ የሚጫወቱት ሚና የላቀ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ የሀገራችን የለውጥ ማዕከልና የማዕዘን ድንጋይ በመሆኑ በዚህ የለውጥ ሂደት ውስጥ ሴቶችን ማሳተፍ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ ያግዛል ብለዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ሴቶች-የኢነርጂ-ሽግግር-ተቀባዮች-ብቻ-ሳ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም

"የሥርዓተ ጾታ እኩልነት መከበር የሀገራችን ዕድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ አቅም ይፈጥራል" - አቶ ሙላት ገዛኽኝ …….///…... የሥርዓተ ጾታ እኩልነት መከበር ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዕድገትና ብ
+9
"የሥርዓተ ጾታ እኩልነት መከበር የሀገራችን ዕድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ አቅም ይፈጥራል" - አቶ ሙላት ገዛኽኝ …….///…... የሥርዓተ ጾታ እኩልነት መከበር ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዕድገትና ብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን (ማርች 8) "50 ዓመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ!” በሚል መሪ ቃል በተቋሙ ተከብሯል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ገዛኽኝ በዓሉን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሲከበር በኢትዮጵያ ብሎም በዓለም ዙሪያ ያሉ ሴቶች ለመብቶቻቸው በፅናት ታግለው ያስመዘገቧቸው ስኬቶች አብረው ይታሰባሉ፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የሥርዓተ-ጾታ-እኩልነት-መከበር-የሀገራች&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም

ሴቶች ወደ ኃላፊነት እንዲመጡ ለማስቻል የማብቃትና የመደገፍ ሥራ ሊሰራ ይገባል …..…///……. ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን (ማርች 8) "50ኛ ዓመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ"
+9
ሴቶች ወደ ኃላፊነት እንዲመጡ ለማስቻል የማብቃትና የመደገፍ ሥራ ሊሰራ ይገባል …..…///……. ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን (ማርች 8) "50ኛ ዓመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሃሳብ በአዳማ አንድ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተከብሯል። በዓሉ የሴቶችን መብት ለማስከበር፣ የእኩልነት ድምፅን ለማጎልበት እና ሴቶች ለሀገር ብልጽግና የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት ያለመ ነው። በበዓሉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች 3 ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ጥሩ ወርቅ ሽፈራው ሴቶች ወደ ኃላፊነት እንዲመጡ ለማድረግ ማብቃትና መደገፍ ያስፈልጋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ሴቶች-ወደ-ኃላፊነት-እንዲመጡ-ለማስቻል-የ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም

የተቋሙ ሥጋቶችን ቀድሞ በመለየት ፈጣን ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል …..…///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሥጋቶችን ቀድሞ በመለየት ፈጣን ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ በተቋሙ
+7
የተቋሙ ሥጋቶችን ቀድሞ በመለየት ፈጣን ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል …..…///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሥጋቶችን ቀድሞ በመለየት ፈጣን ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ በተቋሙ የኢትዮ ፓወር አካዳሚ የአመራር ልማት ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ተናኘ መኮንን አስታወቁ፡፡ ሥራ አስኪያጇ በተቋሙ ከተለያዩ ዘርፎች ለተውጣጡ የሥራ መሪዎች በስጋት አስተዳደር ዙሪያ የተዘጋጀውን ስልጠና ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት በግንባታ እና ኦፕሬሽን ላይ ባሉ የማመንጫ፣ ማከፋፈያ ጣቢያዎችና የማስተላለፊያ መስመሮች እንዲሁም በተቋሙ ሁሉም ዘርፎች ስጋቶችን በጥንቃቄ በመለየት ችግር ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ ምላሽ መስጠት ይገባል፡፡ የተቋሙ የሥራ ባህሪ ከስጋት ጋር የተገናኘ መሆኑን የጠቀሱት ወ/ሮ ተናኘ የሚሰጠው ስልጠና ስጋቶችን በመቀነስ እንደተቋም ሊደርስ የሚችል አደጋን ለመከላከል ያስችላል ብለዋል፡፡ በተለያዩ ዘርፎች የሚሰጡ ሥልጠናዎች የተቋሙን ስትራቴጅካዊ ግቦች በማሳካት በኩል ለውጥ እንዲያመጡ በተለይ የሥራ ኃላፊዎች ሥልጠናዎችን ወደ ተግባር መቀየር እንዳለባቸው ሥራ አስኪያጇ አሳስበዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 01 ቀን 2018 ዓ.ም

የመኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካው በአካባቢው ዘመናዊ ግብርና እንዲስፋፋ ዕድል ይፈጥራል ………///……… የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለወላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ጣቢያ ግንባታ የግጦሽ መሬታቸውን በካሳ ለለቀቁ
+8
የመኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካው በአካባቢው ዘመናዊ ግብርና እንዲስፋፋ ዕድል ይፈጥራል ………///……… የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለወላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ጣቢያ ግንባታ የግጦሽ መሬታቸውን በካሳ ለለቀቁ ነዋሪዎች መልሶ ማቋቋሚያ የገነባው የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በአካባቢው ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ እንዲስፋፋ እንደሚያግዝ ተገለፀ። የወላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ግርማ እንደገለፁት ጣቢያው ከተሰጠው ሀገራዊ ተልዕኮ በተጨማሪ በአካባቢው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎችን አከናውኗል። ተቋሙ ጣቢያው ሲገነባ የግጦሽ ቦታ ለተወሰደባቸው 54 የልማት ተነሽ አርሶ አደሮች ከካሳ ክፍያ በተጨማሪ በዘላቂነት ሊቋቋሙ የሚችሉበትን የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ ገንብቶ ማስረከቡን አስታውሰዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የመኖ-ማቀነባበሪያ-ፋብሪካው-በአካባቢው&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም

ከፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ......... /// ........... የሥራ መደብ መጠሪያ፦ ሞግዚት /Child Caregivers/ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www
ከፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ......... /// ........... የሥራ መደብ መጠሪያ፦ ሞግዚት /Child Caregivers/ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም

የባለሙያዎችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችል ሥልጠና እየተሰጠ ነው …….///……. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከማዕከላዊ ሪጅን 1፣ 2 እና 3 እንዲሁም ከረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫ
+7
የባለሙያዎችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችል ሥልጠና እየተሰጠ ነው …….///……. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከማዕከላዊ ሪጅን 1፣ 2 እና 3 እንዲሁም ከረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለተውጣጡ ባለሙያዎች የዲጂታል ክህሎት ማሳደጊያ ሥልጠና መስጠት ጀምሯል። የዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ተወካይ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጽዮን በቀለ እንደገለጹት ተቋሙ በተያዘው በጀት ዓመት በዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ላይ በርካታ ተግባራትን ለማከናወን አቅዶ እየሰራ ነው፡፡ እስከአሁን ወደ ሥራ የገቡትንና በቀጣይም የሚተገበሩትን ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቶች በአግባቡ ለመጠቀምና ውጤት ለማስመዝገብ በዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ዙሪያ በቂ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የባለሙያዎችን-የዲጂታል-ክህሎት-ለማሳደ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም

ፕሮጀክቱ የቱሪዝም ዘርፉን ይበልጥ ያነቃቃል .......///…….. በአርባምንጭ ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና የማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በከተ
+5
ፕሮጀክቱ የቱሪዝም ዘርፉን ይበልጥ ያነቃቃል .......///…….. በአርባምንጭ ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና የማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በከተማዋ ያለውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያነቃቃው የከተማዋ ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ኃላፊ አቶ ደስታ ደንበላ እንዳስታወቁት ከተማዋ የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በመሆኗ በግንባታ ላይ የሚገኘው የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሲጠናቀቅ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ ለቱሪዝም ዘርፉ እድገት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። በከተማዋ የቱሪዝም መዳረሻ ይሆናል ተብሎ በመገንባት ላይ ለሚገኘው የ'ገበታ ለትውልድ' ፕሮጀክት እንዲሁም ሌሎች መንግስታዊ እና የግል የቱሪዝም መዳረሻዎች በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ቁልፍ መሰረተ ልማት መሆኑን ኃላፊው አብራርተዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ፕሮጀክቱ-የቱሪዝም-ዘርፉን-ይበልጥ-ያነቃ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም

ፕሮጀክቱ በነባሩ የአርባ ምንጭ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ይቀርፋል ……..///…… የደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በአርባ ምንጭ ቁጥር 1 ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ለሚስተዋሉ የኃይል አ
+7
ፕሮጀክቱ በነባሩ የአርባ ምንጭ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ይቀርፋል ……..///…… የደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በአርባ ምንጭ ቁጥር 1 ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ለሚስተዋሉ የኃይል አቅርቦት ችግሮች መፍትሔ እንደሚሰጥ የጣቢያው ኃላፊ ተናገሩ። ኃላፊው አቶ ምንተስኖት ማሞ እንደተናገሩት የማከፋፈያ ጣቢያው ትራንስፎርመሮች ኃይል የማቅረብ አቅም ቢኖራቸውም ጣቢያው በአንድ አቅጣጫ ብቻ ኃይል የሚያገኝ በመሆኑ፣ ገቢ መስመሩ የፕሮቴክሽን ሥርዓት የሌለው እና በአካባቢው ብቸኛ የኃይል አቅራቢ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአቅርቦቱ ላይ ችግሮች ይስተዋሉ ነበር። ጣቢያው ለሚያጋጥሙት ችግሮች ከወላይታ ሶዶ ቁጥር 1 ማከፋፈያ ጣቢያ መረጃ በመቀበል እልባት ሲሰጥ እንደነበር እና ይህም ለችግሮቹ በወቅቱ መፍትሔ ለመስጠት በሚከናወነው ሥራ ላይ እንቅፋት ሲፈጥር መቆየቱን ተናግረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ፕሮጀክቱ-በነባሩ-የአርባ-ምንጭ-ማከፋፈያ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም

ማከፋፈያ ጣቢያዎቹ ለኢንቨስትመንት ፍሰት መጨመር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው …….///…….. በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኙ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች አስተማማኝ ኃይል በማቅረብ ለኢን
+7
ማከፋፈያ ጣቢያዎቹ ለኢንቨስትመንት ፍሰት መጨመር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው …….///…….. በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኙ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች አስተማማኝ ኃይል በማቅረብ ለኢንቨስትመንት መስፋፋትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን የከተማዋ ኢንቨስትመንት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ቸርነት ተስፋዬ እንደገለጹት በከተማዋ ያሉት ሁለት ማከፋፈያ ጣቢያዎች ባለሀብቶች በተለያዩ ዘርፎች በልበ ሙሉነት እንዲሰማሩ ዕድል ፈጥረዋል። በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት፣ በአምራች ኢንዱስትሪና በግብርና ዘርፎች 152 ኢንቨስትመንቶች ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፣ 41 ባለሀብቶች ደግሞ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው በግንባታ ላይ ይገኛሉ። በተጨማሪም 29 አዳዲስ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ለጽሕፈት ቤቱ መቅረባቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ማከፋፈያ-ጣቢያዎቹ-ለኢንቨስትመንት-ፍሰ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 29 ቀን 2018 ዓ.ም

ተቋሙ ኢትየጵያ በቀጣይ 10 ዓመት የሚያስፈልጋትን ኢነርጂ ታሳቢ ያደረገ ስትራቴጂ ሊኖረው ይገባል ………///………. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኢትየጵያ በቀጣይ 10 ዓመት የሚያስፈልጋት ኢነርጂ ታሳ
+6
ተቋሙ ኢትየጵያ በቀጣይ 10 ዓመት የሚያስፈልጋትን ኢነርጂ ታሳቢ ያደረገ ስትራቴጂ ሊኖረው ይገባል ………///………. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኢትየጵያ በቀጣይ 10 ዓመት የሚያስፈልጋት ኢነርጂ ታሳቢ ያደረገ ስትራቴጂ ሊቀርፅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሳሰቡ፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ዶ/ር ብሪክ ታዬ የተቋሙ የግማሽ በጀት ዓመት ግምገማ ሲጠናቀቁ በሰጡት አቅጣጫ እንዳመለከቱት የተቋሙ ስትራቴጂ ሀገሪቱ የምትፈልገውን ኢነርጂ ለያሟላ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ግልጽ ውይይት ሊደረግበት ይገባል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ተቋሙ-ኢትየጵያ-በቀጣይ-10-ዓመት-የሚያስፈል&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 7.1 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘት ችለናል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተቋሙ ወጪዎችን በመቀነስና የገቢ አማራጮቹን በማስፋት ከዚህም በላይ ትርፋማ ለመሆን መስራት ይጠበ
+9
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 7.1 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘት ችለናል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተቋሙ ወጪዎችን በመቀነስና የገቢ አማራጮቹን በማስፋት ከዚህም በላይ ትርፋማ ለመሆን መስራት ይጠበቅበታል - የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ …….///……. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከምስረታው ጀምሮ ከቆየበት ኪሳራ ወጥቶ ወደ ትርፋማነት መሸጋገሩን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ አስታወቁ፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚው የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሪፖርት ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሳይት ሲያቀርቡ እንደተናገሩት ተቋሙ በግማሽ ዓመቱ 7.1 ቢሊየን ብር ትርፍ አግኝቷል፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት የውጭ ሀገራት የኃይል ሽያጭ በሁለት እጥፍ ዕድገት ሲያሳይ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የውጭ ምንዛሪ ግኝት ደግሞ በ138 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በበጀት-ዓመቱ-ስድስት-ወራት-7-1-ቢሊየን-ብር-ት&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

የአርባ ምንጭ 2 ማከፋፈያ ጣቢያ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ……..///……. የአርባ ምንጭ ቁጥር 2 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በቅርቡ ከብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ግሪድ ጋር እንደሚገናኝ በኢ
+9
የአርባ ምንጭ 2 ማከፋፈያ ጣቢያ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ……..///……. የአርባ ምንጭ ቁጥር 2 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በቅርቡ ከብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ግሪድ ጋር እንደሚገናኝ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የምዕራፍ አንድ ሳይት ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ። ሥራ አስኪያጁ አቶ አበበ ሚጀና እንዳስታወቁት የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቱ የሲቪል ሥራ 82 ነጥብ 5 በመቶ እንዲሁም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች 90 በመቶ ተጠናቀዋል፡፡ የፕሮጀክቱ የመጀመሪያና የሁለተኛ ሙከራና ፍተሻ ሥራዎች መከናወናቸውን የገለፁት አቶ አበበ አሁን ላይ እየተከናወኑ ያሉ የማጠናቀቂያ ሙከራና ፍተሻ ሥራዎች በቅርቡ ተጠናቀው ጣቢያው ከብሔራዊ ግሪድ ጋር እንደሚገናኝም አስታውቀዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የአርባ-ምንጭ-2-ማከፋፈያ-ጣቢያ-በቅርቡ-አገ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የሥራ አመራር አባላት የህዳሴ ግድብን ጎበኙ …….///…….. በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ የተመራ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን ዛሬ ማምሻውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎበኘ፡፡ የሥራ አመራር ቡድኑ በጉብኝቱ 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ዝርመት ያለውን ባለ ኮርቻ ቅርጽ ግድብ እና 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ዝርመት ያለውን ዋናውን ግድብ ጎብኝቷል፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ እና ሌሎች የፕሮጀክቱና የኦፕሬሽን ኃላፊዎች ስለግድቡ እና ስለ ኃይል ማመንጨት ሥራዎቹ ለጎብኚዎች ገለፃ አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የሥራ አመራር አባላት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በይፋ ተመርቆ ሥራ ከጀመረ በኋላ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ነገ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን የ2018 ግማሽ በጀት ዓመት አፈፃፀም ለመገምገል ዕቅድ ይዟል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት  27 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+6