fa
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

رفتن به کانال در Telegram

EEP Communication

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام EEP Communication

کانال EEP Communication (@eepcommuication) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 15 540 مشترک است و جایگاه 8 340 را در دسته فناوری و برنامه‌ها و رتبه 2 161 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 15 540 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 28 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 1 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -4 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 24.98% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 16.34% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 3 882 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 2 539 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 8 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
EEP Communication

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 29 ژوئن, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته فناوری و برنامه‌ها تبدیل کرده‌اند.

15 540
مشترکین
-424 ساعت
-147 روز
+130 روز
آرشیو پست ها
photo content
+4

የተበጠሰው የባህር ዳር - ጋሸና - አላማጣ መስመር በእልህ አስጨራሽ ርብርብ ተጠግኗል ……..///…….. ትናንት ጉዳት ደርሶበት የተበጠሰው የባህር ዳር - ደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በከፍተኛ ርብርብ መጠገኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ፡፡ በዘርፉ የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ውበት አቤ እንዳስታወቁት ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በተከናወነው የጥገና ሥራ የተበጠሰውን መስመር መልሶ የማገናኘቱ ሥራ ማምሻውን ተጠናቋል። የባህር ዳር ወልዲያ ኮምቦልቻ የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክትን በመገንባት ላይ የሚገኘው ታታ ሊሚትድ ማሽነሪ ከማቅረብ ባለፈ ባለሙያዎቹ ከሪጅኑ የጥገና ባለሙያዎች ጋር እንዲሳተፉ ማድረጉን ተናግረዋል። ጥገናውን ተከትሎ የክልሉ መዲና ባህርዳር፣ ጎንደር እና ሌሎች ከተሞች እንዲሁም የትግራይ መዲና መቀሌና ሌሎች ከተሞች ዳግም ኃይል ማግኘታቸውን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡ ወልዲያ፣ ኮምቦልቻና በአካባቢው ያሉ ከተሞች እንዲሁም በኮምቦልቻ በኩል ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የአፋር መዲና ሠመራ እና ሌሎች ከተሞችን ለማገናኘት ጥረቱ ቀጥሏል። በጥገና ሥራው ላይ ለተሳተፉ የሪጅኑ ባለሙያዎችና ለታታ ሊሚትድ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+1

photo content

ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቻይልድ ኬር አድሚኒስትሬቲቭ አሲስታንት 1ኛ የሥራ መደብ ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ታህሳስ 15 ቀን 2016 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን አሟልታችሁ ከተመዘገባችሁ ተወዳዳሪዎች መካከል ወ/ሮ ስንታየሁ ብርሁኑ ፋንታሁን በተሰጠው የጽሁፍ እና የቃል ፈተና ብልጫ ያመጡ በመሆኑ ከየካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 (አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ ኮተቤ በሚገኘው በተቋሙ ዋና መ/ቤት የሰው ኃይል ምደባ ቢሮ በመገኘት የትምህርት ማስረጃ ዋናውን በመያዝ ቀርበው የቅጥር ሂደት እንዲፈፅሙ እናሳውቃለን፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content

ተቋሙን ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል እየተሰራ ነው- ወንድወሰን ሽፈራው ……..///…….. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተግባራዊ ማድረግ የጀመረውን የዲጂታል አሰራር ተከትሎ ሊሰነዘሩበት ከሚችሉ የሳይበር ጥቃቶች ራሱን ለመከላከል እየሰራ መሆኑን በተቋሙ የሳይበር ደህንነት ሞኒተሪንግ እና ሪሶርስ ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡ ሥራ አስኪያጁ አቶ ወንደወሰን ሽፈራው እንዳስታወቁት በተቋሙ የለሙና ተግባራዊ የተደረጉ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂና የሲስተም መሰረተ ልማቶች እየጨመሩ መምጣታቸውና የተቋሙ አሰራር ዲጂታላይዝ መደረጉ ተቋሙ ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም ተቋሙን ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በኦፕሬሽን ዘርፎች የሚተገበሩ ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት በማድረግ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡ ተቋሙን ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል የሳይበር ደህንነት የሚመራባቸው የተለያዩ ፖሊሲዎችና ማኑዋሎች ተቀርፀው ተግባራዊ መደረጋቸውን ነው አቶ ወንድወሰን የተናገሩት፡፡ እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ በራስ አቅም የሚበለጽጉም ሆነ ከውጪ የሚገዙ ሶፍትዌሮች የሚተገበሩት የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ደረጃቸው ተፈትሾ ነው፡፡ በኃይል መሰረተ ልማቱ ዘርፍ እየተስፋፋ የመጣውን የሳይበር ጥቃት ስጋት ለማስወገድ የግሪድ መሰረተ ልማቱን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ስለመሆናቸውም አቶ ወንድወሰን አንስተዋል፡፡ የሳይበር ደህንነት ቅድመ ሁኔታዎች ባልተካተቱባቸው የማከፋፈያ እና ማመንጫ ጣቢያዎች ላይ የጥቃት ተጋላጭነት ዳሰሳ በማከናወን እንዲካተቱ እየተደረገ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ አዲስ የሚገነቡ የኃይል መሰረተ ልማቶችን ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል የሚያስችሉ ሶፍትዌሮችና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ተካተውባቸው እንዲገነቡ እየተደረገ ስለመሆኑም አስረድተዋል፡፡ እስከ አሁን ባለው ሁኔታ በተቋሙ ላይ የሳይበር ጥቃት አጋጥሞ እንደማያውቅ አቶ ወንድወሰን አረጋግጠዋል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

ከባህር ዳር - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋው መስመር በመበጠሱ ኃይል ተቋርጣል ……..///…….. ከባህር ዳር - በደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመበጠሱ በአካባቢዎቹ ኃይል መቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ፡፡ በዘርፉ የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ውበት አቤ እንዳስታወቁት ዛሬ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ጀምሮ በንፋስ መውጫ አካባቢ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ አንደኛው ፌዝ በመበጠሱ ከንፋስ መስጫ - ጋሸና- አላማጣ - መሆኒ - መቀሌ የሚሄደው መስመር ኃይል ተቋርጣል፡፡ የደረሰውን ጉዳት በአፋጣኝ በመጠገን አገልግሎቱን ለመመለስ እንቅስቃሴ መጀመሩን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከደብረ ብርሃን - ሸዋሮቢት - ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በሸዋ ሮቢት ከተማ አቅራቢያ በመበጠሱ ከሸዋ ሮቢትና ከሚሴ ከተሞች በስተቀር አብዛኛዎቹ የሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መቋረጡን የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ በድሩ አህመድ አስታውቀዋል፡፡ ከኮምቦልቻ በባቲ ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የአፋር ክልል መዲና ሰመራና የተለያዩ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች እንዲሁም በወልዲያ አላማጣ መስመር ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የትግራይ ክልል መዲና መቀሌን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ከተሞች ኃይል እንደተቋረጠባቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ እንደ አቶ በድሩ ገለፃ ከትናንት በስቲያ ከሰዓት በኋላ የተበጠሰውን መስመር በመጠገን አገልግሎቱን ለማስቀጠል ጥረቶች ተጀምረዋል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

ምስል ከአርካይቭ
ምስል ከአርካይቭ

photo content
+2

በፕሮጀክቱ ለደህንነት ቅድሚያ ሰጥቶ እየተሠራ ነው ………///……. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በፕሮጀክቶች ትግበራ ወቅት ለደህንነት ቅድሚያ ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን የበቆጂ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት አስታወቀ። በፕሮጀክቱ የሥራ ደህንነት ባለሙያ የሆኑት ዮዲት ታምሩ እንደገለፁት በፕሮጀክቱ የግንባታ ሥራ የሠራተኞችን የሥራ ላይ ደህንነት ለማስጠበቅ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል፡፡ በፕሮጀክቶች ላይ የሚሳተፉ ሠራተኞች ለተለያዩ አደጋዎች ተጋላጭ በመሆናቸው ሠራተኛው ደህንነቱ ተጠብቆ እንዲሰራ ለማድረግ የተለያዩ የሥራ ላይ አደጋ መከላከል ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ እንደ ባለሙያዋ ገለፃ የሠራተኛውን ደህንነት ለማረጋገጥ በሥራ ላይ ስለሚያጋጥሙ አደጋዎች፣ በአደጋ መከላከያ መንገዶች፣ ሠራተኞች በስራ ቦታቸው ላይ ስለሚኖራቸው እንቅስቃሴ እና ከደህንነት መሳሪያዎች አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የግንዛቤ ማስጨበዎች ተሰጥተዋል፡፡ ከግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራው በተጨማሪ ተቋሙ የሥራ ላይ ደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎችን እያቀረበ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ሠራተኛው የተሠጠውን የግንዛቤ ማስጨበጫ በተግባር ላይ ማዋሉን እና በሥራ ቦታው ላይ የደህንነት መሳሪያዎቹን በአግባቡ እየተጠቀመ ስለመሆኑ የክትትል ሥራዎች እንደሚከናወኑም ባለሙያዋ ገልፀዋል፡፡ በፕሮጀክቱ የግንባታ ሥራ ላይ በአናፂነት እየሠሩ የሚገኙት አቶ ደጀኔ ጣፋ እና ሙሐመድ ጉደታ በበኩላቸው ተቋሙ የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎችን ከማቅረብ ጀምሮ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችን እየሠጣቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የሚሰጣቸውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባር ላይ በማዋል ደህንነታቸው ተጠብቆ እየሠሩ እንደሚገኙም አረጋግጠዋል፡፡ በበቆጂ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት የግንባታ ሥራ ላይ ከ150 በላይ የሚሆኑ ሰዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content

የማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ የሰረቁ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ ……..///……. ከጌዶ - ገፈርሳ በተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ ስርቆት የፈፀሙ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ፡፡ ሰለሞን ድሪባ እና ሰኚ ደረጀ የተባሉት ግለሰቦች ጥቅምት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. የስርቆት ድርጊቱን የፈጸሙት በሸገር ከተማ አስተዳደር ገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ መገልቱ በተባለ አካባቢ ነበር፡፡ ወንጀለኞቹ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ብረቶቹን ሰርቀው በመቆራረጥ በማዳበሪያ ይዘው ሲሄዱ እጅ ከፍንጅ የተያዙት በአካባቢው በጥበቃ ስራ ላይ በተሰማሩ ሚሊሻዎች ነው፡፡ ጉዳዩ የቀረበለት የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ ሰለሞን ድሪባ በአራት ዓመት ከአምስት ወር፤ 2ኛ ተከሳሽ ሰኚ ደረጄ በአምስት ዓመት እንዲቀጡ ውሳኔ ማስተላለፉን የማዕከላዊ ሪጅን 1 የማስተላለፊያ መስመር እና ኦፕቲካል ፋይበር ጥገና ሥራ አስኪያጅ ገልፀዋል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

የፕሮጀክቱን የግንባታ ሥራ እስከ ግንቦት ወር ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው ………///……… የበቆጂ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ግንባታን እስከ መጪው ግንቦት ወር ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ የሳይት አስተባባሪ ተናገሩ፡፡ አስተባባሪው አቶ እንዳልካቸው ጃንቦ እንደተናገሩት ትራንስፎርመር የማስቀመጥ፣ የመቆጣጠሪያ ክፍል ጣሪያ የኮንክሪት ሙሊት፣ የውስጥ ለውስጥና መጋቢ መንገዶች ጠረጋ፣ የጣቢያው የግቢ አጥር እና የመኖሪያ ቤቶች የመሰረት ሥራ እና 90 በመቶ የሚሆነው የሲዊችያርድ ቁፋሮ፣ የመሰረትና የብረት ተከላ ሥራዎች ተጠናቀዋል። የሲዊችያርድ የብረት ተከላ፣ የመኖሪያ ቤቶች ኮለን የማቆም እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ሥራዎችን ለማጠናቀቅ እየተሰሩ መሆኑን አቶ እንዳልካቸው ገልጸዋል፡፡ እንደ አስተባባሪው ገለፃ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን የመገጣጠም፣ የመሬት ውስጥ መስመሮችን የመዘርጋት፣ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የመኖሪያ ቤቶችና የመቆጣጠሪያ ክፍል የግድግዳ ግንባታና የማጠናቀቂያ እንዲሁም የማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ በቀጣይ የሚከናወኑ ይሆናል፡፡ የማከፋፈያ ጣቢያው የሲቪል ሥራ ከ45 በመቶ እንዲሁም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ከ5 በመቶ በላይ መከናወናቸውን የጠቆሙት አቶ እንዳልካቸው ቀሪ የፕሮጀክቱ የግንባታ ሥራዎችን እስከ ግንቦት 2016 ዓ.ም ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ የበቆጂ ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት የሳይት ሥራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ተኮላ ተሾመ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት የማከፋፈያ ጣቢያው አብዛኛዎቹ ሥራዎች መከናወናቸውንና የማስተላለፊያ መስመሩ የምሶሶ መትከያ የመሰረት ቁፋሮ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱን በተያዘው የበጀት ዓመት መጨረሻ ሥራ ለማስጀመር እየተሰራ እንደሆነ የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ በአሁኑ ወቅት የዕቃ አቅርቦትና የዲዛይን ሥራውን ጨምሮ አፈፃፀሙ 63 ነጥብ 8 በመቶ ደርሷል ብለዋል። እንደ አቶ ተኮላ ገለጻ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ሁሉም ዕቃዎች ሳይት በመድረሳቸው እና ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ ችግሮች ባለመኖራቸው ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ ማጠናቀቅ ይቻላል፡፡ የፕሮጀክቱ አማካሪና ተቆጣጣሪ መሀንዲስ አቶ ሲሳይ አዱኛ እንደተናገሩት የፕሮጀክቱ ሥራዎች በስምምነቱ ላይ በተቀመጠው መስፈርት መሠረት እንዲከናወን ቁጥጥር እየተደረገ ነው፡፡ እስከ አሁን ባለው ሁኔታ ከዕቃዎች ጥራት ጀምሮ የግንባታ ሥራዉ ጥራቱን በጠበቀ እየተከናወነ እንደሚገኝም አረጋግጠዋል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content

photo content
+9

photo content

ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሾፌር 4ኛ የሥራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም የጽሁፍ ፈተና ተፈትኛችሁ ያለፋችሁ በመንገድ ትራንስፖርት በሚፈቅደው ህግ እና ደንብ መሰረት ከ74 በላይ ውጤት ያመጣችሁ ለተግባር ፈተና ያለፋችሁ ሲሆን ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 ስማችሁ የተገለጸው አመልካቾች የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተሽከርካሪ ጥገና አስተዳደር ቢሮ የተግባር ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እሳውቃለን፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

የቦንጋ ሚዛን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በጊዜያዊነት ተጠግኗል ……..///…….. በባህር ዛፍ መውደቅ የተነሳ ለሶስት ቀናት ተቋርጦ የነበረው የቦንጋ ሚዛን ባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በጊዜያዊነት በእንጨት ምሰሶ ተተክቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች የኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ። በዘርፉ የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ሲሳይ እንደገለፁት መስመር ተሸካሚ ምሰሶው በጊዜያዊነት በመጠገኑ ኃይል ተቋርጦባቸው የነበሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ዳግም ኃይል ማግኘት ጀምረዋል። የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን የሚሸከሙ የብረት ምሰሶዎችን በእንጨት ምሰሶዎች መተካት የማይመከር ቢሆንም በጊዜያዊነት የተወሰደ መፍትሔ በመሆኑ ህብረተሰቡና የመስተዳድር አካላት ትልልቅ ዛፎችን በመስመሩ ሥር እንዳይተከሉ በማድረግ እና ለኤሌክትሪክ መሰረተልማቶች ጥበቃ በማድረግ እንዲተባበሩ ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et የካቲት 24 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+5