fa
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

رفتن به کانال در Telegram

EEP Communication

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام EEP Communication

کانال EEP Communication (@eepcommuication) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 15 685 مشترک است و جایگاه 8 030 را در دسته فناوری و برنامه‌ها و رتبه 2 153 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 15 685 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 26 اوت, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 143 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 13 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 33.48% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 17.12% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 5 250 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 2 685 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 11 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
EEP Communication

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 27 اوت, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته فناوری و برنامه‌ها تبدیل کرده‌اند.

15 685
مشترکین
+1324 ساعت
+207 روز
+14330 روز
آرشیو پست ها
የወደቀው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር የኃይል ፍሰት የማመጣጠን ሥራ ይሰራል ………///…….. በለገጣፎ - ቃሊቲ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመ
+3
የወደቀው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር የኃይል ፍሰት የማመጣጠን ሥራ ይሰራል ………///…….. በለገጣፎ - ቃሊቲ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት የወደቁ 5 የብረት ምሰሶዎችን በመጠገን ዳግም አገልግሎት መስጠት እስኪጀምሩ ድረስ የኃይል ፍሰት የማመጣጠን ሥራዎች እንደሚሰሩ የትራንስሚሽን ቢዝነስ ዘርፍ አስታወቀ፡፡ በዘርፉ የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ተወካይ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ግርማ ዘለቀ እንደገለፁት የብረት ምሰሶዎቹ የወደቁት በከባድ አውሎ ንፋስ ምክንያት ቢሆንም ቀደም ሲል በምሰሶዎቹ አካላት ላይ ይፈፀም የነበረው ተደጋጋሚ የስርቆት ወንጀል ለጉዳቱ መከሰት አሉታዊ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በወደቁት የብረት ምሰሶዎች ላይ በተደረገው የቴክኒክ ፍተሻ መሰረት የተሰረቁ የምሰሶ አካላትን መልሶ ለመተካት በማሻሻያ (Modification) መልክ ይገጠሙ የነበሩት ብረቶች የምሰሶዎቹን መደበኛ ጥንካሬና የመሸከም አቅም ማምጣት አለመቻላቸው መረጋገጡን ተናግረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የወደቀው-የኃይል-ማስተላለፊያ-መስመር-ተ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም

ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ሥርዓት የመዘርጋት አስፈላጊነት! .....///..... ውሃ ለኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማት ዋነኛውና ዋናው የኃይል ምንጭ ነው። በተለይም በውሃ ኃይል ማመንጫዎች የሚመረተው እ
ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ሥርዓት የመዘርጋት አስፈላጊነት!  .....///..... ውሃ ለኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማት ዋነኛውና ዋናው የኃይል ምንጭ ነው። በተለይም በውሃ ኃይል ማመንጫዎች የሚመረተው እያንዳንዱ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የሚጀምረው ከአንዲት የውሃ ነጠብጣብ በመጠራቀም በመሆኑ የውሃ አጠቃቀምና አስተዳደር ሥርዓት በኃይል ማመንጨት ሂደት ቁልፍ ሚና አለው!   ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ለኃይል ዘርፉ ያለው ወሳኝ ፋይዳ የኃይል ብክነትን መቀነስ በወቅታዊ የአየር ንብረት መለዋወጥና ያላግባብ በሚባክን የውሃ ሀብት ምክንያት የሚፈጠርን የኤሌክትሪክ ማመንጨት አቅም መቀነስ ይከላከላል።   ዘላቂ የኃይል አቅርቦት ግድቦች ሙሉ የማመንጨት አቅማቸውን ውጤታማ በሆነ መንገድ እና ሥርዓት ባለው ሁኔታ እንዲጠቀሙ ያስችላል።   ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እያንዳንዷ የምትባክን የውሃ ነጠብጣብ በኃይል ማመንጨት ሂደት ላይ የምታሳድረው ተጽዕኖ በቀጥታ በመኖሪያ ቤቶች፣ በፋብሪካዎች፣ በንግድና በማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር ውጤታማ ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም።   ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ጥብቅ-የውሃ-አስተዳደር-ሥርዓት-የመዘርጋ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም

በሥራ ላይ ደህንነት እና ጤንነት ዙሪያ ሥልጠና እየተሰጠ ነው ……///……. በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እና ሪጅኖች ለተመደቡ የሥራ ላይ ደህንነትና ጤና አስተባባሪ መሐንዲሶች በሥራ ላይ ደህንነት ላይ
+3
በሥራ ላይ ደህንነት እና ጤንነት  ዙሪያ ሥልጠና እየተሰጠ ነው ……///……. በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እና ሪጅኖች ለተመደቡ የሥራ ላይ ደህንነትና ጤና አስተባባሪ መሐንዲሶች በሥራ ላይ ደህንነት ላይ ያተኮረ ሥልጠና መስጠት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ ላይ ደህንነትና ጤና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ሥራ አስኪያጅ አቶ ኮርሳ ተሬሳ እንደገለፁት ሥልጠናው መሐንዲሶቹ በተመደቡባቸው የሥራ ቦታዎች ላይ በሚኖራቸው የሥራ ላይ ደህንነት እና ጤንነት ክትትልና ቁጥጥር ላይ ያላቸውን የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው። ሥልጠናው ባለሙያዎቹ በሥራ ላይ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ስጋቶችን በመለየት መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማድረግ ታስቦ መዘጋጀቱን  ነው የገለፁት። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በሥራ-ላይ-ደህንነት-እና-ጤንነት-ዙሪያ-ሥ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል መቋረጥን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ዘመናዊ የአደጋ ጊዜ የብረት ምሰሶዎች 🏗   በኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ድንገተኛ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ፈጣን መልሶ ጥገና ለመስጠት የሚያስችሉ ዘመናዊ የአደጋ ጊዜ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች (Emergency Restoration Towers) በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ተደርገዋል።   ይህ ቴክኖሎጂ ምን ዓይነት ጥቅሞችን ይዞ መጥቷል?   ፈጣን መልሶ ጥገና  ቀደም ሲል በአደጋ ወቅት ከ18 እስከ 20 የሚደርሱ የእንጨት ምሶሶዎችን መትከል ይጠይቅ የነበረ ሲሆን አዲሶቹ ምሰሶዎች ግን በደጋፊ ገመዶች (Anchor Wire) በቀላሉ የሚገጣጠሙ በመሆናቸው የተቋረጠውን መስመር በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ወደ ሥራ ለማስገባት ያስችላሉ።   የኃይል ጭነት ማመጣጠን የተጨናነቁ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን አነስተኛ የኃይል ፍሰት ወደሚገኝባቸው በማዘዋወር ከአገልግሎት ውጭ የነበሩ አካባቢዎች በፍጥነት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ያደርጋል።   የሠራተኞች ደህንነትና የአሰራር ዘመናዊነት የጥገና ሠራተኞችን ለጉዳት እንዳይጋለጡ በማድረግ ደህንነታቸውን አስተማማኝ ያደርጋል።   በተግባር ምን ውጤት ተገኘ? በሞጆ አካባቢ በተደረገ ሥልጠናና ልምምድ ባለሙያዎቹ የምሰሶ ተከላ ጊዜን ከግማሽ ቀን በታች ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡ በተጨማሪም ከቢሾፍቱ ወደ ቆቃ እና ሁርሶ እንዲሁም ከገላን ወደ ሞጆ በሚሄዱ ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመሮች ላይ ተከሰተው እስከ 7 ቀናት ሊወስዱ ይችሉ የነበሩ የኃይል መቋረጦችን በእነዚህ ምሰሶዎች አማካኝነት ፈጣን መፍትሔ መስጠት ተችሏል።   በቀጣይ ምን ታስቧል? ቴክኖሎጂውን ወደ ሁሉም ሪጅኖች ለማስፋትና የጥገና ምላሽ ጊዜን ይበልጥ ለመቀነስ የሚያስችሉ ዝግጅቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content

የፕሮጀክት አስተዳደርን ማዘመን ለተቋም ዘላቂ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ አለው .....///..... የተቋሙን ስትራቴጂካዊ ግቦች በስኬት ለማሳካትም ሆነ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን፣ ዘመናዊና ጠ
+5
የፕሮጀክት አስተዳደርን ማዘመን ለተቋም ዘላቂ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ አለው  .....///..... የተቋሙን ስትራቴጂካዊ ግቦች በስኬት ለማሳካትም ሆነ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን፣ ዘመናዊና ጠንካራ የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት መሠረታዊና ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ ተጠቆመ።   የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተቀላጠፈ ደረጃውን የጠበቀና ውጤታማ የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችለውን አራተኛ ዙር የከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ሥልጠና ለፕሮጀክት ዳይሬክተሮችና ሥራ አስኪያጆች መስጠት ጀምሯል።   በዕለቱ ሥልጠናውን የሰጡት በተቋሙ የአሰላ ንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅና አሰልጣኝ ኢንጂነር ጌቱ ጌቱ ያደቴ እንደገለጹት ይህ ሥልጠና ተቋሙ በፕሮጀክት አስተዳደር ረገድ የሚያጋጥሙትን መዋቅራዊና አሰራር ነክ ፈተናዎች በዘላቂነት በመሻገር፣ ከልማዳዊ አሰራር ወደ ተመራጭና ዘመናዊ የፕሮጀክት መሪነት ሥርዓት እንዲሸጋገር አቅም ይፈጥራል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የፕሮጀክት-አስተዳደርን-ማዘመን-ለተቋም&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ .....///..... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአውቶ ሜካኒክ 1ኛ፤ አውቶ ኤሌክትሪሺያን 1ኛ እና በአውቶ ቦዲ 1ኛ የሥራ መደቦች ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መጋቢት 3
+5
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ .....///..... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአውቶ ሜካኒክ 1ኛ፤ አውቶ ኤሌክትሪሺያን 1ኛ እና በአውቶ ቦዲ 1ኛ የሥራ መደቦች ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የውጭ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል። በዚህ መሠረት ከዚህ በታች ስማችሁ የተገለፀው አመልካቾች በሙሉ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ ብረታ ብረት ፊትለፊት በሚገኘው የተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ የፅሁፍ ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል መቋረጥን ለመቀነስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ....///.... በኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ድንገተኛ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ፈጣን መልሶ ጥገና ለመስጠት የሚያስ
+4
የኃይል መቋረጥን ለመቀነስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው  ....///....   በኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ድንገተኛ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ፈጣን መልሶ ጥገና ለመስጠት የሚያስችሉ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የትራንስሚሽን ቢዝነስ ዘርፍ አስታወቀ።              በዘርፉ የቴክኒካል ድጋፍ መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አበባው ያለው እንደገለፁት በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ የተደረጉት የአደጋ ጊዜ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች (Emergency Restoration Tower) በተለያየ ምክንያት የሚወድቁ የብረት ምሰሶዎችን በአጭር ጊዜ በመተካት የኃይል መቋረጥን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ናቸው።  በተጨማሪም የብረት ምሰሶዎቹ የተጨናነቁ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን አነስተኛ የኃይል ፍሰት ወደሚገኝባቸው ለማዘዋወርና ከአገልግሎት ውጭ የነበሩትን በፍጥነት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ ሚናቸው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-መቋረጥን-ለመቀነስ-የሚያስችል-ቴ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል መሠረተ ልማት ደህንነትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል፤ ......///...... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመሠረተ ልማት ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የአሰራር ሥርዓቶች
የኃይል መሠረተ ልማት ደህንነትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል፤ ......///...... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመሠረተ ልማት ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የአሰራር ሥርዓቶች በመተግበር ለውጥ መምጣቱን የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ በጽ/ቤቱ የአስተዳደራዊ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ ግርማ ግዛቸው (ዶ/ር) እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ ለዋና ሥራ አሰፈጻሚ የሚቀርቡ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ተፈጻሚነት ለማሻሻል፣ ተቋማዊ እና የኃይል መሰረተ ልማት ደህንነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የፖሊሲ፣ ፕሮሰስና ለውጥ ማኔጅመንት ተግባራትን በማከናወን ስትራቴጅካዊ ግቦችን ለማሳካት በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል። በዚህም በበጀት ዓመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ 5 ሪጅኖች 1 ሺህ 411 የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችን በማኅበረሰቡ ለማስጠበቅ ታቅዶ በ1 ሺህ 279 ምሰሶዎች ላይ ተፈጻሚ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-መሠረተ-ልማት-ደህንነትን-ለማረጋ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የተቋሙን ጥቅምና ገጽታ የሚያስጠብቁ ሥራዎችን ተከናውነዋል ………///…….. በ2018 በጀት ዓመት ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የተቋሙን ጥቅምና ገጽታ የሚያስጠብቁ የተለያ
ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የተቋሙን ጥቅምና ገጽታ የሚያስጠብቁ ሥራዎችን ተከናውነዋል ………///…….. በ2018 በጀት ዓመት ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የተቋሙን ጥቅምና ገጽታ የሚያስጠብቁ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮምፕሊያንስና ገቨርናንስ ዘርፍ ገለጸ፡፡ የዘርፉሥራ አስፈጻሚ ተወካይ ወ/ሮ መስከረም በቀለ እንደገለጹት የተቋሙን ስትራቴጅክ ዕቅድ መሰረት በማድረግ የተቋሙን ገጽታ ከመገንባት፣ ብልሹ አሰራሮችን ከመከላከል፣ የተቋሙን ጥቅም ከማስጠበቅ፣ ግልጸኝነትንና ተጠያቂነትን ከማስፈን እንዲሁም የሴቶችን ተሳትፎ ከማሳደግ አንጻር የተለያዩ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ 10 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ መጠን ባላቸው 355 የፍትሐብሄር እና 57 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር መጠን ባላቸው 37 የሥራ ክርክር መዝገቦች ላይ ክትትል ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ብልሹ-አሰራሮችን-በመከላከል-የተቋሙን-ጥ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

በከባድ ንፋስ ምክንያት የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ወደቁ ………///…….. ከለገጣፎ - ቃሊቲ በተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ አምስት የብረት ምሰሶዎች መውደቃ
+5
በከባድ ንፋስ ምክንያት የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ወደቁ ………///…….. ከለገጣፎ - ቃሊቲ በተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ አምስት የብረት ምሰሶዎች መውደቃቸውን የማዕከላዊ 1 ሪጅን አስታወቀ። የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ገዛኸኝ እንደተናገሩት ምንም እንኳ የብረት ምሰሶዎች በከባድ ንፋስ የወደቁ ቢሆንም በምሰሶዎቹ አካላት ላይ ስርቆት መፈፀሙ ለኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎቹ መውደቅ አሉታዊ አስተዋፅኦ አድርጓል። በዚህ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተደጋጋሚ የስርቆት ወንጀል እንደሚፈፀም የገለፁት ዳይሬክተሩ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማና ከወረዳው የአስተዳደር አካላት ጋር በመነጋገር ለችግሩ እልባት መስጠት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የወደቁ የኃይል ምሰሶዎችን በአፋጣኝ በመጠገን መስመሩን ወደ አገልግሎት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን አቶ ደረጀ ተናግረዋል። አምስቱ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊት 7 ሰዓት አካባቢ መውደቃቸውንና በሰው እና በእንስሳት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱ ታውቋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

ጥራት ያለው ሪፖርት የተቋሙን ገጽታ ከመገንባት ባሻገር የሀብት አጠቃቀምን ለማሻሻል እንደሚረዳ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ተናገሩ ……///……. ጥራት ያለው ሪፖርት የተቋሙን ገጽታ ከመገንባቱ ባሻገር የ
+4
ጥራት ያለው ሪፖርት የተቋሙን ገጽታ ከመገንባት ባሻገር የሀብት አጠቃቀምን ለማሻሻል እንደሚረዳ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ተናገሩ ……///……. ጥራት ያለው ሪፖርት የተቋሙን ገጽታ ከመገንባቱ ባሻገር የሀብት አጠቃቀምን ለማሻሻል እንደሚያግዝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ተናገሩ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ በጋራ በመሆን በሪፖርት ዝግጅትና አቀራረብ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሂደዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የኢነርጂ እና ኮኔክቲቪቲ ፖርትፎሊዮ ዳይሬክተር ዶክተር ጌትነት መላክ በሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ላይ ያተኮረ የንድፈ-ሐሳብ እና ገቢራዊ ተሞክሮዎችን ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ጥራት-ያለው-ሪፖርት-የተቋሙን-ገጽታ-ከመገ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈፀመው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ …....///….…. በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ በሚገኝ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ከባድ የስርቆት ወንጀል የፈጸመውን ግለሰ
+6
በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈፀመው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ …....///….…. በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ በሚገኝ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ከባድ የስርቆት ወንጀል የፈጸመውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረዳው ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አዳነ ቡርጄ እንደገለጹት ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 አካባቢ ከወላይታ ሶዶ-ሳውላ በተዘረጋው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የስርቆት ወንጀል የፈጸመውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ተጠርጣሪው ከ7 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማት በተለያዩ ጊዜያት በባለ ሦስት እግር ባጃጅ በማጓጓዝ በቁጫ ወረዳ ጋሌ 2 ቀበሌ ልዩ ሥፍራ ሞጎላ ማዞሪያ ከሚባል አካባቢ ከደበቀበት ቦታ በሕብረተሰቡ ጥቆማ ፖሊስ ንብረቱን በቁጥጥር ሥር መዋሉን ጠቁመዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በኤሌክትሪክ-መሰረተ-ልማት-ላይ-ስርቆት-የ-3&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

ተቋሙ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከ805 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል …….////……… የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ከ805 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረ
+2
ተቋሙ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከ805 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል …….////……… የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ከ805 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የተለያዩ የማህበራዊ ኃላፊነት ተግባራትን ማከናወኑን በተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እንደገለጹት ተቋሙ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት ከሚያከናውናቸው ሥራዎች ጎን ለጎን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም በበጀት ዓመቱ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የፋይናንስ ወጪ በማድረግ ለመቄዶኒያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ማዕድ ማጋራቱን ተናግረዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ተቋሙ-ማህበራዊ-ኃላፊነቱን-ለመወጣት-ከ805-ሚ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

ግድቡ “የሚሊየኖችን ቤት ወደ ብርሃን ቀይሯል” - ሲኤንኤን ..///…. ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ “የሚሊየኖችን ቤት ወደ ብርሃን የቀየረ ግድብ ነው” ሲል ዓለም አቀፉ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲ ኤን
+1
ግድቡ “የሚሊየኖችን ቤት ወደ ብርሃን ቀይሯል” - ሲኤንኤን ..///…. ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ “የሚሊየኖችን ቤት ወደ ብርሃን የቀየረ ግድብ ነው” ሲል ዓለም አቀፉ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲ ኤን ኤን ዘገበ፡፡ በሲኤንኤን የኬንያ ዘጋቢ ቪክቶሪያ ሩባደሪ ወደ ህዳሴ በመጓዝ ባሰናዳችው ዘገባ ግድቡን ኢትዮጵያውያን ያለማንም ድጋፍ በራሳቸው አቅም ገንብተው ለውጤት ማብቃታቸውን ገልፃለች፡፡ በአፍሪካ በግዙፍነቱ ቀዳሚ የሆነው የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ከኢትዮጵያ አልፎ ለቀጣናው የኃይል አቅርቦት ትስስር ሚናው ከፍተኛ መሆኑን በፕሮግራምዋ አንስታለች፡፡ ግድቡ ለኢትዮጵያውያን ኃይል ከማቅረብ ባለፈ የቱሪስት መዳረሻ በመሆን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በመደገፍ ረገድ ትልስ ተስፋ ይዞ እንደመጣ አብራርታለች፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በዘገባው ላይ ግድቡ 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው አስረድተዋል፡፡ ግድቡ ከኢትዮጵያ አልፎ ጎረቤት ሀገራትን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይ ደግሞ ለሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ኃይል ለመሸጥ ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 145 ሜትር ከፍታ እና 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው በዓመት በአማካይ 15 ሺህ 670 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ያመነጫል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገጽ https://www.eep.com.et ሐምሌ 28

"አንድም ኪሎ ዋት ኃይል ያላግባብ እንዳይባክን ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ሥርዓት እንዘረጋለን" ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ……..///……. ከኃይል ማመንጫዎች ግድቦች የሚመነጨውን አንድም ኪሎ ዋት ኃይል
+4
"አንድም ኪሎ ዋት ኃይል ያላግባብ እንዳይባክን ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ሥርዓት እንዘረጋለን" ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ……..///……. ከኃይል ማመንጫዎች ግድቦች የሚመነጨውን አንድም ኪሎ ዋት ኃይል ያላግባብ እንዳይባክን ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ሥርዓት እንደሚዘረጋ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ገለጹ፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለተቋሙ የሥራ አመራር ቦርድ ባቀረቡት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዋና ዋና ዕቅዶች ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት ባለፈው በጀት ዓመት ተቋሙ የጀመረው የማንሰራራት ጉዞ ወደ ኋላ እንዳይመለስ አመራሩና ሠራተኛው በቅንጅት መሥራት ያስፈልጋል። የአየር ንብረት ለውጡን ተከትሎ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳይቀንስ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በስፋት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የተቋሙ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም መዘገየት ከተቋም ስኬት አልፎ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ተግዳሮት እንደሚሆን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ሁሉም ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜና የጥራት ደረጃ መጠናቀቅ እንዳለባቸውም ነው የተናገሩት፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=አንድም-ኪሎ-ዋት-ኃይል-ያላግባብ-እንዳይባ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም

“የኃይል አማራጮችን በማስፋት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የኢነርጂ አቅም መገንባት ያስፈልጋል” ኢንጂነር አይሻ መሐመድ …....///….... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተለያዩ የኃይል አማራ
+7
“የኃይል አማራጮችን በማስፋት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የኢነርጂ አቅም መገንባት ያስፈልጋል” ኢንጂነር አይሻ መሐመድ …....///….... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተለያዩ የኃይል አማራጮችን በማስፋት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የኢነርጂ አቅም መገንባት እንዳለበት የመከላከያ ሚኒስትርና የተቋሙ የሥራ አመራር ቦርድ አባል ኢንጂነር አይሻ መሐመድ አስታወቁ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ሲገመግም ኢንጂነር አይሻ እንደገለጹት ተቋሙ በጀት ዓመቱ በቁጥር ደረጃ መልካም ውጤት ያሳየ ቢሆንም በሂደቱ የታዩ ጉድለቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በዝርዝር መተንተን አስፈላጊ ነው፡፡ በቀጣይ ከአየር ንብረት ለውጡ ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ የውሃ እና የኃይል አቅርቦት እጥረቶችን እንዲሁም እየጨመረ የመጣውን ፍላጎት ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት ሊደረግ እንደሚገባ ተናግረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-አማራጮችን-በማስፋት-ለአየር-ን&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም

Le ahun new?

ተቋሙ የኃይል አቅርቦት አስተማማኝነትን ለማረጋገጥ የግሪድ ማጠናከሪያ ጥናት አከናውኗል …….///……. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ከኮፕ-32 ጋር ተያይዞ ለአዲስ
ተቋሙ የኃይል አቅርቦት አስተማማኝነትን ለማረጋገጥ የግሪድ ማጠናከሪያ ጥናት አከናውኗል …….///……. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ከኮፕ-32 ጋር ተያይዞ ለአዲስ አበባና አካባቢዋ ተጨማሪ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል የግሪድ ማጠናከሪያ ጥናት ማከናወኑን አስታወቀ፡፡ በተቋሙ የኮርፖሬት ፕላኒንግ ዘርፍ ተወካይ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ያለውአይቀር ማንደፍሮ እንደገለፁት‎ በበጀት ዓመቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን የሚጨምሩ እንዲሁም የግሪድ ሲስተም አስተማማኝነትን የሚያሻሽሉ ሦስት ፕሮጀክቶችን የቴክኒካዊ የአዋጭነት ጥናቶች ተከናውነዋል፡፡ የአራት አነስተኛ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የቅድመ አዋጭነት ጥናት 50 በመቶ ለማከናወን ታቅዶ የዕቅዱን 90 በመቶ መጠናቀቁን ተናግረዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከአምስት ዓመት በፊት ተዘጋጅቶ የነበረውን የቴክኖሎጂ ካታሎግ የመከለስ ሥራ ከዴንማርክ እና ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለሙያዎች ጋር በጥምረት መከናወኑን የጠቆሙት ሥራ አስፈጻሚው   ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ተቋሙ-የኃይል-አቅርቦት-አስተማማኝነትን&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+7