fa
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

رفتن به کانال در Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

نمایش بیشتر
613
مشترکین
+124 ساعت
-17 روز
-1030 روز
آرشیو پست ها
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሐምሌ ፳፰ (28) ቀን። ❤ እንኳን ክርስቶስ ለሚወዱ #ለቅዱስ_እንድራኒቆስና #ሚስቱ_ቅድስት_አትናስያ_ለመታሰቢያ_በዐላቸው በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከቅዱሳን አባቶቻችን #አብርሃም_ከይስሐቅና_ከያዕቆብ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅዱስ_እንድራኒቆስና_ሚስቱ_ቅድስት_አትናስያ፦ እነርሱም ከአንጾኪያ ከተማ ነበሩ። በወርቅና በብርም የከበሩ ባለጸጎች ነበሩ ከገንዘባቸውም ለድኆችና ለችግረኞች ይሰጡ ነበር።  ❤ ከዚህም በኃላ አንድ ወንድ ልጅና አንዲት ሴት ልጅን ወለዱ ወንዱን ዮሐንስ ሴቲቱንም ማርያም ብለው ሰየሟቸው ልጆችም አደጉ እንዱራኒቅስና ሚስቱም እንግዳ በመቀበል ለድኆችና ለምስኪኖች በመመጽወት በጎ ሥራን አበዙ እነርሱም መገናኘትን ትተው ሰውነታቸውን በንጽሕና ጠበቁ።  ❤ ልጆቻቸውም ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆናቸው ጊዜ የሆድ ዝማ በሽታ ታመው በአንዲት ቀንም ሞቱ እንዲራኒቆስም አይቶ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ፊት ራሱን ጥሎ እንዲህ ብሎ አለቀሰ "ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ወጣሁ ወደ እግዚአብሔርም ራቁቴን እሔዳለሁ እርሱም ሰጠ እርሱም ወሰደ የእግዚአብሔር የጌትነቱ ስም የተባረከ ይሁን ለዘላለሙ አሜን"። እናታቸውም ለሞት እስከምትደርስ እጅግ አዘነች ልጆቿ ወደ ተቀበሩበት ወደ ዐፀደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች ከኀዘንዋም ብዛት የተነሳ አንቀላፋች በእንቅልፏም ውስጥ "በልጆችሽ ሞተ አታልቅሺ እነርሱ ግን በሰማያት ደስ እያላቸው ናቸው" እያለ በመነኰስ አምሳል ሲነግራት አየች። ይህንንም ሰምታ ሒዳ ለባሏ ነገረችው።  ❤ ከዚህም በኃላ ይህን ዓለም ይተዉ ዘንድ ተስማሙ ገንዘባቸውንም ሁሉ ምንም ሳያስቀሩ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጡ በሌሊትም ወጥተው ወደ እስክንድርያ ከተማ ደረሱ ሚስቱንም በዚያ ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በአባ ዳንኤል ዘንድ መነኰሰ። ከዚያም ተመልሶ ሚስቱ አትናስያን ወደ ሴቶች ደናግል ገዳም ወሰዳት በዚያም ተዋት።  ❤ ከዐሥራ ሁለት ዓመትም በኋላ እንድራኒቆስ ከቅዱሳት መካናት ይባረክ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ አባ ዳንኤልን ለመነው ፈቀደለትም በመድኃኒታችንም ቸርነት ሚስቱ አትናስያ በወንድ አምሳል በጉዞ ላይ ተገናኘችው ሚስቱ እንደሆነችም አለወቀም እርሷ ግን አወቀችው ነገር ግን ሚስቱ እንደሆነች አልገለጠችለትም።  ❤ ወደ ቅዱሳት መካናትም በደረሱ ጊዜ ሥራቸውን ፈጽመው ወደ አባ ዳንኤል በአንድነት ተመለሱ። አባ ዳንኤልም ሚስቱ እንደሆነች በመንፈስ ቅዱስ አውቆ እንድራኒቆስን "ባልንጀራ ካደረግኸው ከዚህ መነኰስ ጋራ በአንድ ቦታ ኑሩ እርሱ ቅዱስ ነውና" አለው። ዐሥራ ሁለት ዓመትም በአንድነት ኖሩ ማንም የአወቀ አልነበረም።  ❤ አባ ዳንኤልም ይጎበኛቸውና ስለ ነፍሳቸው ጥቅም ያስተምራቸው ነበር። ከዚህም በኃላ አትናስያ በታመመች ጊዜ ለእንድራኒቆስ "አባታችንን አባ ዳንኤልን ጥራልኝ" አለችው ሒዶም ለአባ ዳንኤል እንዲህ ብሎ ነገረው "ባልንጀራዬ ታሞ ለመሞት ተቃርቧልና ትጎበኘው ዘንድ ና"። በደረሰም ጊዜ በታላቅ ሕመም ላይ አገኛት እርሷም "ታቆርበኝ ዘንድ እሻለሁ" አለችው ያን ጊዜም ተፋጠነና ሥጋውንና ደሙን አቀበላት ከዚህም በኋላ አረፈች በሚገንዟትም ጊዜ ሴት እንደሆነች አገኙ ዳግመኛም ታሪኳንና ለባሏ ያወራቻቸውን ምልክቶች አገኙ።  ❤ እንድራኒቆስም በአነበበ ጊዜ እርሷ ሚስቱ እንደሆነች አወቀ ደንግጦም ልቡ ተሠወረ ፊቱንም እየጻፈ ጮኸ ያለቅስ ጀመረ። ከጥቂት ቀን በኋላም ታመመ አረጋውያንም መጥተው በረከቱን ተቀበሉ ሥጋውንና ደሙንም ተቀበሉ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ እንድራኒቆስ በሚስቱ አትናስያ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 28 ስንክሳር።                                            ✝ ✝ ✝                       ❤ "#ሰላም_ለእንድራኒቆስ_ለምኔተ አስቄጥስ ዘሐወጻ። እንዘ ይዘሩ ብዕሎ ዘኢኮነ ብዕለ ዐመፃ። #ወለአትናስያ_ሰላም ለነቢር ዘተባየፃ። ከመ ይእቲ ብእሲቱ እንበለ ይጠይቅ ገጻ። እስመ አዕፅምቲሃ በጽምእ ከመ ሣዕር ነቅጻ። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_28።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወአንተሰ ብእሲ ዘከመ ነፍስየ። ማእምርየ ወዐውቅየ። ዘኅቡረ አስተጠዓምከ ሊተ መባልዕተ"። መዝ 54፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ 7፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-8 እና የሐዋ ሥራ 7፥1-9። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 19፥1-13። የሚቀደሰው ቅዳሴ የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ፊሊጶስ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ አያይዘውም በዚሁ በሹመት ሽኩቻ ምክንያት ወደፊት የሚፈጠረውን ነገር በመንፈስ ቅዱስ መነፅርነት አይተውት የሚከተለውን ትንቢት ተናግረዋል፡- "እውነት እላችኋለሁ በመጨረሻው ዘመን ደጋጎች ሰዎችን ክፉዎችና ተሳዳቢዎች የሚያደርጉ፣ ሐሰተኞችና ዋዛ ፈዛዛ የሚወዱትን ደጋጎች የሚያደርጉ ሰዎች ይመጣሉ፡፡ በመጨረሻው ዘመን ኃጥአን በጻድቃን ይመሰላሉ፣ ጻድቃንን ኃጢአተኞች ያደርጓቸዋል፡፡ በዚያን ዘመን እውነተኛዎቹ መምህራን አይሾሙም፣ ኃጢአተኞች መማለጃ ሰጥተው ወሬ እያቀበሉ ይሾማሉ፣ እንደ እባብ ክፉ ነገርን ለማድረግ ፍላፃቸውን ያሾሉ ደጋግ ሰዎችን በነገር ያጠፏቸው ዘንድ በእውነት ንጹሕ የሆኑትን ሰዎች አመፅን በተመላ አንደበታቸው ሹመትን ከመውደድ የተነሣ በቅናት ያጠፏቸዋል፡፡ በዚያን ዘመን መጻሕፍትን የሚያውቁ አይሾሙም፣ ነገርን የሚያመላልሱና የአገሮችን ቋንቋ የሚያውቁ ከመኳንንትና ከነገሥታት ዘንድ ሔደው ነገርን የሚሠሩ ሰውን የሚያጣሉ በአመፅ ሹመትን የሚያገኙ ብቻቸውን ይሾማሉ እንጂ ደጋጎች አይሾሙም፡፡ በሚመረጡበትም ጊዜ ከአባታቸው ከሰይጣን ጋር ሆነው "እገሌ መጻሕፍትን ያውቃል፣ የአገሮችን ቋንቋ የሚያውቅ ይሾም" ይላሉ፡፡ ያንጊዜም አመፅ ይበዛል፣ ፍቅርም ትጎድላለች፡፡ ከእኔ በኋላ የሚሆነውን እነሆ ነገርኳችሁ ይህንንም አውቃችሁ በልቡናችሁ ያዙ"፡፡ ❤ ጌታችን ለአቡነ ፊሊጶስ የገባላቸው ልዩ ቃልኪዳን፡- "ገድልህንና ስለ እኔ የታገስከካቸውን መከራዎችህን የጻፈውን ከሁላቸው ከቅዱሳንና ከሰማዕታት ጋር በሰማያዊት ኢየሩሳሌም በወርቀ ቀለም ለዘለዓለሙ ስሙን እጽፍልሃለሁ፡፡ ሥጋህ ከተቀበረበት ቦታ ይቅርታዬንና ቸርነቴን አደርጋለሁ፡፡ መቃብርህ የበረከት ቦታ ትሆናለች"። ከአባታችን ከአቡነ ፊሊጶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!፡፡ ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሐምሌ ፳፰ (28) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ለደብረ ሊባኖስ ሦስተኛ አበምኔት (እጨጌ) #ለአቡነ_ፊሊጶስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።                                                     ✝ ✝ ✝                          ❤ #የደብረ_ሊባኖሱ_እጨጌ_አቡነ_ፊሊጶስ፡- በተወለዱ በ15 ዓመታቸው በምናኔ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገቡ፡፡ ከብዙ ጊዜ አገልግሎትም በኋላ በአቡነ ተክለሃይማኖት እጅ መንኲሰው ከእርሳቸውም ዕረፍት በኋላ ሦስተኛ አበምኔት ሆነው አገልግለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከተወለዱት የመጀመሪያ ፓትርያርክ ሆነዋል፡፡ አባታቸው ቅዱስ ተክለሃይማኖትም በመንፈቀ ኢትዮጵያ ጳጳስ ሆነው ነበር፡፡ ❤ በመጀመሪያ የአቡነ ፊሊጶስን የጽድቅ ሕይወትና ሹመታቸውን በተመለከተ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድልና በራሳቸው በአቡነ ፊሊጶስ ገድል ላይ የተጻፈውን እንመልከት፡- "ክቡር አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ከዚህ ዓለም ተለይቶ የሚሄድበት ጊዜ ሲደርስ "ከአንተ በኋላ አንተን ተክቶ በዙፋንህ የሚቀመጥ ማነው?" አሉት፡፡ እርሱም "ብዙ ዘመን አይኖርም እንጂ ኤልሳዕ በእኔ ተተክቶ ይቀመጥ" አለ፡፡ ስለ ፊሊጶስ ግን አላነሳም፣ ኤልሳዕ ካረፈ በኋላ በእርሱ ተተክቶ አባት ይሆን ዘንድ ጌታችን የተሸለመ ፊሊጶስን እንደመረጠው ስም አጠራሩ ለልጅ ልጅ ዘመን እንደሚጸና ያውቅ ነበርና ስለዚህ "አልሳዕ በእኔ ተተክቶ አባት ይሁናችሁ" አለ፡፡ ክቡር አባታችንም በታላቅ ክብር ዐረፈ፡፡ ❤ አንድ ቀን አንድ ዲያቆን ዐረፈና ሬሳውን ገንዘው አጠቡት፣ ይቀብሩትም ዘንድ አስክሬኑን ይዘው ሲሄዱ በአልጋ ላይ ሳለ አስክሬኑ ተንቀሳቀሰ፡፡ የተሸከሙትም ደንግጠው መሬት ላይ አስቀመጡትና ከመግነዙ ፈቱት፡፡ እርሱም ተነሥቶ ሦስት ጊዜ ተነፈሰ፡፡ ወንድሞችም "ምን እያልክ ነው?፣ ወዴትስ ነበርክ?" አሉት፡፡ ያ የከበረና የተመረጠ ዲያቆንም "ክቡር አባታችን ተክለሃይማኖት "ኤልሳዕ ወደኔ ይምጣ፣ ፊሊጶስ ስለ እኔ ተሹሞ በወንበሬ ይቀመጥ እርሱ ለብዙዎች አሕዛብ አባት ይሆናልና የክርስቶስንም መንጋ በጽድቅና በቅን ይጠብቃል ብሎኛል" ብሎ ይህን ተናግሮ ተመልሶ ዐረፈ፡፡ ወንድሞችም ኤልሳዕ እንደልማዱ ጎኑን ሳያሳርፍ በወንበር ላይ እንደተደገፈ በሞት ማረፉን አላወቁም ነበር"፡፡ ❤ ወደ ጻድቁ የልጅነት ገድላቸው እንመለስና አቡነ ፊሊጶስ በእግዚአብሔር ተመርጠው የመንፈስ ቅዱስም ማደሪያ ሆነዋልና ገና በሕፃንነታቸው በተወለዱባት ሰላሌ ክፍለ ሀገር ዝማ በምትባል ልዩ ቦታ ውስጥ ሰይጣን በጠንቋይ ላይ አድሮ በነደደ በእሳት ውስጥ በመግባትና የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ በአካባቢው ራሱን ያስመልክ የነበረን ሰይጣን በእሳት ውስጥ እንዳለ በስመ ሥላሴ አማትበውበት አመድ አድርገውታል፡፡ በዚህ በአቡነ ፊሊጶስ ድንቅ ተአምር የጠንቋዩ ቤተሰቦችና የአካባቢው ሰዎችም አምነው ሊጠመቁ ችለዋል፡፡ ይህንንም ያደረገው ገና ሕፃን ሳለ ነው፡፡ ❤ መልአከ እግዚአብሔር ተገልጦለት የትውልድ መንደሩን ትቶ ወደ ግራርያ ሀገር ደብረ አስቦ ሄዶ ቅዱስ ተክለሃይማኖትን እንዲያገኝ በነገረው መሠረት አንድ ቀን ያህል ተጉዞ ተክለሃይማኖትን አገኛቸውና ባርከውት ከመነኰሳት ጋር እንዲያርፍ አደረጉት፡፡ ሦስት ዓመት እነርሱን በመልካም ሥራ ፍጹም ሆኖ ሲያገለግላቸው ከቆየ በኋላ "ሁሉም በአንድነት አሁን ልብሰ ምንኵስና ይገባዋል" አሉ፡፡ ቅዱስ አባታችን ተክለሃይማኖትም የምንኵስናን ሥራ የሚያሠራ ቅድስናን ሰጠው፡፡ በሌላም ጊዜ ቅስናን ይቀበል ዘንድ ወደ ጳጳሱ ዘንድ ላኩት፡፡ አቡነ ፊሊጶስ በንጉሥ አምደ ፅዮን ዘመነ መንግሥት ሥጋቸው አልቆ አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ ሲገረፉ ደማቸው እሳት ሆኖ ገራፊዎቻቸውን ያሳደደ ቅዱስና ጻዲቅ አባት ናቸው፡፡ ❤ ንጉሥ አምደ ጽዮን በክፉ ጠንቋዮች ምክር ተታሎ "ያልወለደችህን የአባትህን ሚስት ብታገባ መንግሥትህ ትፀናለች" ብለው ክፉ ምክርን መክረውት የእንጀራ እናቱን አገባትና ንግሥት አደረጋት፡፡ አቡነ ፊሊጶስም ይህን ሲሰሙ ነቢዩ ኤልያስ ንጉሡ አክአብንና አልዛቤልን በድፍረት እንደገሠጻቸው እርሳቸውም በቀጥታ ሄደው ንጉሡን ዘልፈው ገሠጹት፡፡ ወደ ንጉሡም ከመሄዳቸውም በፊት በዚህ ምክንያት ሰማዕት እንደሚሆኑ አውቀውት ነበርና ልጆቻቸውን ተሰናብተውና የሚተካቸውን ሰው ነግረዋቸው ነው የሄዱት፡፡ ንጉሡ አምደ ጽዮንም አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ አስገረፋቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቶቻቸውም መሬት ላይ እየተቆረሰ የወደቀውን ሥጋቸውን እያነሱ ለበረከት ወሰዱት፡፡ ደማቸውም እንደ እሳት ሆኖ ገራፊዎቻቸውን ያቃጥላቸው ነበር፡፡ 300 እንስራ ውኃ አምጥተው ከደሙ በወጣው እሳት ላይ ቢያፈሱትም የውኃው ብዛት እሳቱን ማጥፋት አልቻለም፡፡ ንጉሡም በፍርሃት ከዙፋኑ ላይ ወርዶ ሸሸ፡፡ ❤ የንጉሡ ጭፍሮች ግን በጋለ ማረሻ ጀርባና ግንባራቸውን ደረታቸውንም ተኮሷቸው፡፡ ኃፍረታቸውንም እንዳይሸፍኑ እጆቻቸውን ወደ ኋላ አስረው ራቁታቸውንም በከተማው ሁሉ ሲያዞሯቸው ዋሉ፡፡ ማታም ንጉሡ "ታስረው ለኖሩ ኃይለኛ ውሾች ስጡት" ብሎ በማዘዝ ውሾቹ እንዲቦጫጭቋቸው ቢያደርጉም ውሾቹ ግን ከእግራቸው ስር ሰግደዋል፣ እርሳቸውም በእግራቸው ባረኳቸው፡፡ አማካሪዎቹም ንጉሡን "ከዚህ መነኩሴ ጋር ምን አጨቃጨቀህ በግዞት አርቀህ ስደደው ብለው" ብለው መክረውት "እስከ ቆርቆራ አገር አውጥታችሁ ወደ ትግሬ አገር ውሰዱት" ብሎ አዘዘ፡፡ እርሳቸውም ንጉሡን ከ3 ዓመት በኋላ ትሞታለህ ብለው ትንቢት ነገረውት በወታደሮች ተወሰዱ፡፡ በግርፋት ብዛት የተቆረሰ ሥጋቸው ድውያንን ይፈውስ ነበር፡፡ ደማቸውም አስረው የሚወስዷቸውን የአንዱን ወታደር አንድ ስውር ዐይኑን ፈወሰለትና ወታደሮቹም አምነው ከእርሳቸው ጋር በዚያው ተሰደው መከራን ተቀብለዋል፡፡ እሳቸው በትግራይ ታላላቅ ተአምራትን እያደረጉ ሲያስተምሩ በትንቢታቸው መሠረትም ንጉሡ ከሦስት ዓመት በኋላ ሞተና ልጁ ነገሠ፡፡ ልጁም አባታችንን ከስደት መለሳቸውና ከተክለሃይማኖት መቃብር ደብረ አስቦ ገቡ፡፡ ❤ የነገሠውንም ልጅ አንድ ክፉ ሰው "ከአንድ በላይ ማግባት ትችላለህ፣ በገና ወቅትም ረቡዕና አርብን መጾም ተገቢ አይደለም" ብሎ ስለመከረው ጳጳሱን ወደ ሀገራቸው ግብፅ እንዲሰደዱ ሲያደርግ አቡነ ፊሊጶስን ደግሞ "ረቡዕና አርብን በጠዋት ካልቀደስክ" ብሎ ወደ ደራ ተሰደው እንዲሄዱ አደረገ፡፡ አባታችን በአጠቃላይ አምስት ጊዜ ተሰደው በትግራይ፣ በደራ፣ በዝዋይ ባሕረ ደሴት፣ በዳሞት ገማስቄ እና በወለቃ በስደት ቆይተዋል፡፡ ጳጳሱን አባ ሰላማን በአቃሊት ቅበረኝ ብለዋቸው በቃሬዛ አድርጎ ከጌርጌሳ ወደ አቃሊት ወሰዷቸው፤ እዚያም ሐምሌ 28 ቀን በሰላም ዐረፉ፡፡ አጽማቸውም ከተቀበረ ከ140 ዓመት በኋላ በመጋቢት 23 ቀን ወደ ደብረ ሊባኖስ በክብር መጥቶ ዐርፏል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሰባት አክሊላት አቀዳጅቷቸዋል፡፡ ❤ ስለ አሁኑ ዘመን የአቡነ ፊሊጶስ ትንቢት!፡- በወቅቱ የነበሩት ጳጳስ አባ ያዕቆብ በብዙ ልመናና ምክር አቡነ ፊሊጶስን ጳጳሱ ራሱ የሚለብሰውን የክብር ልብስ አልብሶ በሸዋ አገር ላይ ኤጲስ ቆጶስነት ሾመው፡፡ ከተሾሙም በኋላ አቡነ ፊሊጶስን "ሌሎችን ሹምልን" የሚሉ በርካቶች ሲያስቸግሯቸው እሳቸው የሰጡት ምላሽ "በሥልጣን ፍለጋ ምክንያት ይህችን የትርህምትና የፅሙናን ቦታ (ደብረ ሊባኖስን) የጨዋታ የተድላ ቦታ እናደርጋታለን" በማለት በወቅቱ ማንንም አልሾምም ብለው ነበር፡፡

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሐምሌ ፳፯ (27) ቀን። ❤ እንኳን #ለነቢዩ_ቅዱስ_ሕዝቅኤል ለራእዩ መታሰቢያ ቀን በዐል፣ #ለአዳም_ልጅ_ለቅዱስ_ሴት ለዕረፍት በዐል፣ #ለወንጌላዊው_ለቅዱስ_ዮሐንስ በእስክንድርያ #ቤተ_ክርስቲያኑ ለከበረችበት በዐልና ተርኑጥ ከሚባል አገር ሰው ለሆነ #ለቅዱስ_አሞን ሰማዕትነት ለቀበለበት ለዕረፍቱ በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከሰማዕቱ #ቅዱስ_አሞን ጋር ሰማትነት ከተቀበለች ከድንግል #ቅድስት_ትዮጲላ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትን በረከትን ያሳትፈን።                                                      ✝ ✝ ✝ ❤ #የአዳም_ልጅ_ቅዱስ_ሴት፦ ሴትም ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖረ ሔኖስንም ወለደው። ሔኖስንም ከወለደ በኋላ ሰባት መቶ ዓመት ኖረ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። መላ እድሜውም ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት ሆነ በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_አሞን፦ ይህም ቅዱስ ተርኑጥ ከሚባል አገር ሰው የሆነ ነው። ወደ ላይኛው ግብጽ በሔደ ጊዜ የቅዱሳን ሰማዕታት ግፍ ተመለከተ ወደ እንዴናው ገዥ ወደ አርያኖስም ቀርቦ ክብር ይግባውና በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ታላቅ ስቃይ አሠቃየው ሥጋውን ሁሉ ሠነጣጠቀው እረጃጅም በሆኑ በተሳሉ በብረት ችንካሮች ቸነከሩት ጌታችንም ያጸናውና ያስታግሠው ያለ ጉዳትም በጤና ያስነሣው ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ በዚያ ያሠቃዩት ዘንድ ወደ እስክንድርያ ከተማ ሰደደው ክብር ይግባውና ጌታችንም ለእርሱ ተገልጦ መታሰቢያው ለሚያደርግ፣ ገድሉንም ለሚጽፍ ስሙንም በሕይወት መጽሐፍ እንደሚጽፍ ቃል ኪዳን ሰጠው። ይህን ቃል ኪዳን ከሰጠው በኋላ በታላቅ ክብር ወደ ሰማይ ዐረገ አባ አሞንም ፈጽሞ ደስ አለው። ❤ ከዚህም በኋላ በዚያ ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከሥቃዩ ሁሉ አዳነው ይህንንም ባዩ ጊዜ ብዙ ሕዝቦች ስለ ርሱ በጌታ አመነው በሰማዕትነት ሞቱ። ከውስጣቸው ቲዮጲላ የምትባል ድንግል ነበረች ወደ መኰንኑ ቀርባ ርሱንና የረከሱ አማልክቶቹን ረገመች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነች። በእሳት ውስጥ እንዲጥሏት አዘዘ እሳቱም አላቃጠላትም ከዚህም በኋላ ራሷን በሰይፍ ቆረጡ የሰማዕትነት አክሊል ተቀበለች። ❤ ቅዱስ አሞንንም ብዙ ከአሠቃዩት አባላዘሩንም ቆረጡ ከዚያም እራሱን በሠይፍ ይቆርጡ ዘንድ መኰንኑ አዝዞ ቆረጡት ተጋድሎውንም ፈጽሞ የሰማዕትነት አክሊልን ፈጸመ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ አሞን ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 27 ስንክሳር።                              ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለአሞን_አባላቲሁ_ዘቊስላ። በቅንዋተ ኅፂን ዲቤሁ እለ ተተክላ። እስከ አስፈዎ አምላክ ኪዳነ መሐላ። ወሰላም ዓዲ ለድንግል ቲዮጲላ። እንተ ምስሌሁ በሠይፍ መኰንን አቅተላ። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_27።                                                   ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም። ወገብረ መድኃኒተ በማእከለ ምድር። አንተ አጽናዕካ ለባሕር በኃይልከ"። መዝ 73፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 18፥20-ፍ.ም።                          ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወቅዱሰ እስራኤል ንጉሥነ። ውእቱ አሚረ ተናገርኮሙ በራእይ ለደቂቅከ። ወትቤ እሬሲ ረድኤተ በላዕለ ኃይል"። መዝ 88፥18-19። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 5፥7-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 5፥17-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 4፥10-19። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ10፥30-43። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅድስት መስቀል ክብራ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሐምሌ ፳፯ (27) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊቷ_ጻድቅ ለታላቁ ለጻድቅ ንጉሥ #ለቅዱስ_ላሊበላ_ባለቤት (ሚስት) #ለቅድስት_መስቀል_ክብራ_ለዕረፍቷ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅድስት_መስቀል_ክብራ፡- የትውልድ ሀገሯ ትግራይ ሽሬ አካባቢ ነው፡፡ ይኽችም ቅድስት የታላቁ ጻጽቅ ንጉሥ የቅዱስ ላሊበላ ባለቤት ስትሆን ሁለቱን ያጋባቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ የሚያንጻቸውውን የሕንጻ ዲዛኖችና ሌሎችንም ብዙ ምሥጢራትን ካሳየውና ወደ ምድር ከመለሰው በኃላ ድጋሚ ተገልጦለት "...እንደ አንተ የተመረጠች ናት እንደ ልብህም ትሆናለች፣ ሥራዋም ከሥራህ አያንስም እርሷ የተመረጠች የእግዚአብሔር አገልጋይ ናትና" በማለት መልአኩ የቅድስት መስቀል ክብራን ንጽሕናና ቅድስና መስክሮላታል፡፡ ❤ ቅድስት መስቀል ክብራ ከቅዱስ ላሊበላ ይትባረክን የወለደች ሲሆን በ23 ዓመት ውስጥ ቅዱስ ላሊበላ 11 እጅግ አስደናቂ የሆኑ ፍልፍል ቤተ መቅደሶቹን ከመላእክት ጋር ሲያንጽ ብታየው ልቧ በመንፈሳዊ ተመስጦ ተመልቶ እርሷም እግዚአብሔር ፈቅዶላት አስደናቂውን የአባ ሊባኖስን ቤተመቅደስ ራሷ እንዳነጸችው መጽሐፈ ገድሏና ገድለ ቅዱስ ላሊበላ ያስረዳል፡፡ ከዚህም በኋላ ቅድስት መስቀል ክብራን መንና ትግራይ ገባች። ወደ ትግራይ እየመራ የወሰዳት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ መልአኩ እርሷን በትግራይ ቅዱስ ሚካኤል እንዲጠብቃት ከተዋት በኃላ ቅዱስ ላሊበላን ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ መንግሥተ ሰማያት አውጥቶታል፡፡ ❤ ቅድስት መስቀል ክብራም በትግራይ ሆና መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃት ከሰው ተለይታ በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ በቀን እልፍ እልፍ እየሰገደች በታላቅ ተጋድሎ ስትኖር ጌታችን ተገልጦ ክብሯ ከ 36ቱ ቅዱሳት አንስት ጋር እኩል መሆኑን ነግሯታል፡፡ ይኽችም ቅድስት ብዙ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽማለች፡፡ ለምሳሌ በመስቀል ጦርነት ጊዜ እስላሞች ከባሕር ማዶ እየፈለሱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በፍቅር እየተቀበለችና እያስተናገደች ሃይማኖትንና ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች ወደ ክርስትና እንደገቡና እንዲጠመቁ አድርጋለች፡፡ ❤ ቅድስት መስቀል ክብራም በትግራይ ክልል ሽሬ አውራጃ መደባይ ታብር በተባለው ቦታ ላይ በስማ የተሰራ ትልቅ ገዳም አላት። እጅግ ውብ በሆኑ ሰንሰላታማ ትላላልቅ ድንጋዮች መካከል የሚገኝ አስደናቂና ጥንታዊ ገዳም ነው። ገዳሙ ከሽሬ ከተማ በእግር የ 7 ሰዓት መንገድ ያስኬዳል። የቅድስት መስቀል ክብራ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ እግዚአብሔር አምላክ ይማረን፡፡ ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳት በዐላት።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ እንኳን #ለዘመነ_ክረምት_አምስተኛ_ሳምንት ዕለተ እሑድ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                          ✝ ✝ ✝ ❤ #በዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ "#በሰንበት_ቦአ_ኢየሱስ ምኵራቦሙ ለአይሁድ ምህሮሙ ወይቤሎሙ አክብሩ ሰንበትየ፤ አዝ፣(በሰንበት) በሰንበት አጋንንተ አውጽአ ወበቃሉ እለ ለምጽ አንጽሐ፤ አዝ፣ በሰንበት ወረቀ ምድረ ወገብረ ፅቡረ ወበምራቁ አሕየወ ዕውረ፤ አዝ፣ (በሰንበት) #ዘይኤዝዞሙ #ለደመናት_ያውርዱ_ዝናመ ውስተ ኵሉ ምድር፤ አዝ፣ ያወርዱ ዝናም ውስተ ኵሉ ምድር ውስተ ፍና ኀበ ዘይፈቀድ መካን፤ አዝ፣ ውስተ ፍና ኀበ ይትፈቀድ መካን ከመ ኅቡረ ይትፈሣሕ ዘይዘርእ ወየዐርር፤ አዝ፣ ምድርኒ ርእየቶ ወአእኰተቶ ባሕርኒ ሰገደት ሎቱ"። ትርጉም፦ #ኢየሱስ_በሰንበት ወደ አይሁድ ምኵራብ ገባ፤ አስተማራቸው ሰንበቴን አክብሩ አላቸው በሰንበት አጋንንትን በቃሉ አወጣ፤ ለምጻሞችን አነጻ፤ በሰንበት ምራቁን ወደ ምድር እንትፍ ብሎ ጭቃ አደረገ፤ በምራቁም የዕውርን ዐይን አበራ፤ ወደ ምድር #ዝናምን_ያወርዱ_ዘንድ_ደመናት የሚያዛቸው ወደሚፈለገው ቦታ የሚመራቸው እርሱ ነው፤ የሚዘራውም የሚያጭደውም በአንድነት ይደሰታል፤ ምድርም አየችው አመሰገነችው ባሕርም ሰገደችለት። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ሐወጽካ ለምድር ወአርወይካ። ወአብዛኅኮ ለብዕላ። ፈለገ እግዚአብሔር ምሉዕ ማያተ"። መዝ 64፥9። የሚነበቡት መልዕክታት። 2ኛ ቆሮ 10፥1-ፍ.ም፣ ያዕ 3፥1-9 እና የሐዋ ሥራ 28፥17-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 8፥1-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም ዕለተ ሰንበት ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤              ❤ #ሐምሌ ፳፮ (26) ቀን። ❤ እንኳን #ለእመቤታች_ድንግል_ማርያም_እጮኛዋ (ጠባቂ) ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆን ለተገባው #ለአረጋዊው_ለጻድቁ_ለቅዱስ_ዮሴፍ_ለዕረፍት በዐል፣ #ለኢትዮጵያው_ለመጀመርያው_ሊቀ_ጳጳስ #ለአቡነ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን (ፍሬምናጦስ) ለዕረፍት በዐልና #ለእስክድርያው_ሊቀ_ጳጳስ በጉባኤ ቁስጥንጥንያ መቅዶንዮስን፣ ሰባልዮስና አቡሊናርዮስንም ተከራክሮ ለረታቸው #ለአቡነ_ጢሞቴዎስ_ለዕረፍት_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከአባ_ሮዲስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                         ✝ ✝ ✝ ❤ #የእመቤታችን_ጠባቂ ( እጮኛ) #ጻድቁ_ቅዱስ_ዮሴፍ፦ መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን ድንግል ማርያም እጮኛዋ ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆኑ የተገባው ነው። ❤ እርሱም እምቤታችንን በርሱ ዘንድ ካስጠበቋት ጀምሮ በሁሉ ነገር ያገለግላት ነበር። በመከራዋም ሁሉ አልተለያትም። በወለደችም ጊዜ በቤተ ልሔም ከርሷ ጋራ ነበረ። ወደ ግብጽም በተሰደደች ጊዜ ከእርሷ ጋራ ብዙ መከራ ደረሰበት። ከዚህም ዓለም የሚለይበት ጊዜው በደረሰ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን ጠርቶ ተሰናበታቸው እጆቹንም ዘርግቶ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሐምሌ 26 ቀን ሰጠ። የዘላለምንም ሕይወት ወረሰ። ❤ በዐረፈበትም ጊዜ ጌታችን ወደርሱ መጥቶ እጆቹን በላዩ ጫነ ለሥጋውም መፍረስና መበስበስ እንዳያገኘው ኃይልን ሰጠው በአባቱ በያዕቆብም መቃበር አኖሩት። ዕረፍቱም ክብር ይግባውና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዊ በዐሥራ ስድስት ዓመት ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ቅዱስ ዮሴፍ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን (ፍሬምናጦስ)፦ ዜናውም እንዲህ ነው ስሙ ሜሮጵዮስ የሚባል የጥበበኞች አለቃ አንድ ሰው ወደ ሕንድ አገር ሊአልፍ ወዶ ከጢሮስ አገር መጣ ከእርሱም ጋራ ከዘመዶቹ ወገን የሆኑ ሁለት ብላቴኖች ነበሩ። የአንደኛው ስሙ ፍሬምናጦስ የሁለተኛውም ኤዴስዮስ ይባላል። ሲድራኮስ የሚሉትም አሉ። በኢትዮጵያ በኩል ወዳለው ወደ አፍሪቃ ባሕር ወደብ ደረሱ ልቡ የተመኘችውን የኢትዮጵያን አገር መልካምነቷን ሁሉ ተመለከተ። ❤ ከዚህም በኃላ በድንገት ወንበዴዎች ተነሥተው በመርከብ ከአሉት ሁሉ ጋር ገደሉት እኒህ ሁለት ልጆች ግን ተረፉ። የአገሩ ሰዎችም አገኙዋቸው ወደ ንጉሥም ወስደው አንድ እጅ መነሻ አድርገው እነርሱን ሰጡት ንጉሡም ተቀበላቸው። ❤ ከጥቂት ቀኖች በኃላም ንጉሡ ኤዴስዮስን በፊቱ የሚቆም ጋሻ ዣግሬ አድርጎ ሾመው ፍሬምናጦስን ግን በገንዘቡ ሁሉ ላይ በጅሮንድ አድርጎ ሾመው ይህም ንጉሥ የአብርሀና የአጽብሐ አባታቸው ስሙ አይዛና የተባለው ነበር። እነርሱ ሕፃናት ሳሉም አረፈ። እኒህም አካለ መጠን እስከሚያደርሱ ድረስ የንጉሡን ልጆች እያሳደጉ ኖሩ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ማመንንም አስተማሩዋቸው። ❤ የንጉሡም ልጆች አድገው በነገሡ ጊዜ ኤዴስዮስ ወደ አገሩ ተመለሰ ፍሬምናጦስ ግን ወደ ግብጽ ሔደ ወደ እስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ወደ አባ አትናቴዎስም ደረሰ። የደረሰብትንም ሁሉ ነገረው። ስለ ኢትዮጵያውያንም ሃይማኖት ጳጳስ ሳይኖራቸው ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንዳመኑ ነገረው። አባ አትናቴዎስም በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ ፍሬምናጦስንም የነጻ ሕዝብ አገር ለሆነችው ለኢትዮጵያ አገር ጳጳስ ይሆን ዘንድ ግድ አለው። ጵጵስነትንም ሾመ ከታላቅ አክብሮት ጋራ ላከው በአብርሀና በአጽብሐ ዘመነ መንግሥትም ወደ ኢትዮጵያ በደረሰ ጊዜ በክብር ተቀበሉት። ❤ በኢትዮጵያም አገሮች ሁሉ የቀናች ሃይማኖትን ሰበከ አስተማረም ክብር ይግባውና ክርስቶስን የጌትነቱን ብርሀን በሁሉ አገሮች ገለጠ ስለዚህም ብርሃንን ገላጭ ሰላማ ተባለ ሁሉንም አስተካክሎ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ) ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለም አሜን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የእስክንድር_ሊቀ_ጳጳስ_አባ_ጢሞቴዎስ፦ በተሾመ ጊዜም የክርስቶስን መንጋዎች ከአርዮስ ከመቅዶንዮስና ከሰባልዮስ ተኩላዎች ጠበቀ። ይህም አባት በተሾመ በስድስተኛው ዓመት ለክርስቲያን ወገኖች ደግ የሆነ ቴዎዶስዮስ ነገሠ በዚያችም ዓመት ክብር ይግባውና መንፈስ ቅዱስን ስለ ካደው ስለ መቅዶንዮስ በቁስጥንጥንያ የተሰበሰቡ የመቶ ሃምሳ ቅዱሳን ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ተደረገ ይህም አባት ጢሞቴዎስ ሊቀ ጉባኤ ሆኖ መቅዶንዮስንና ሰባልዮስን አቡሊናርዮስንም ተከራከራቸው። ረትቶም አሳፈራቸው። እነሆ የክህደታቸውንና የክርክራቸውንም ነገር የካቲት አንድ ቀን ላይ ጽፈናል። ❤ ከዚህም በኃላ ይህ አባት በሹመቱ ዘመን አብያተ ክርስቲያናትን በማነፅና በሚገባውም ሥራ ሁሉ በእድሳታቸውም አሰበ። ለመጻተኞችም ቤቶችን ሠራላቸው። ❤ መንጋዎቹንም ሁልጊዜ ያስተምራቸው ነበር በመልካም እውቀቱና በትምህርቱ ጣዕም ሁልጊዜም በማስረዳቱ በቀናች ሃይማኖት አጸናቸው። ከአርዮስና ከመቅዶንዮስ ወገኖችም ብዙዎቹን መልሶ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሆነች የቀናች ሃይማኖት አስገባቸው። ❤ በወንጌላዊው በቅዱስ ማርቆስ መንበርም ላይ ዘጠኝ ዓመት ተኩል ኖረ ከዚያም በኋላ ሐምሌ 26 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጢሞቴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 26 ስንክሳር።                              ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለጢሞቴዎስ_ለጴጥሮስ_እኍሁ። ጳጳሰ ሀገር ዘእምቅድሜሁ። በቊስጥንጥንያ ዘኮነ ሊቀ ማኅበሮሙ ለእሊአሁ። ተክዕወ ለምእመናን እምሁከተ ዐለውት ዘሠርሑ። ሰላም ብዙኅ እስከ የኀልፍ ወርኁ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 26።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ዚአከ ውእቱ ሰማያት ወእንቲአከ ይእቲ ምድር። ዓለምኒ በምልዑ ዘአንተ ሣረርከ። ባሕረ ወመስዐ ዘአንተ ፈጠርከ። መዝ 88፥11-12 ወይም  67፥31-32። ። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 6፥1-15 ወይም ማቴ 1፥18-25።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሐምሌ ፳፮ (26) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያው_ጻድቅ የጌታችን መከራ በማሰብ ከተወለዱ ጀምሮ ተላጭተውት የማያውቁትን ፀጉራቸውን ከትልቅ ዛፍ ላይ እያሠሩ ይጸልዩ ለነበሩ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ሃሌሉያ ለዕረፍት በዐል በሰላም አደረሰን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ሃሌሉያ፦ የትውልድ ሀገራቸው ተንቤን ነው፡፡ አባታቸው ይስሐለነ እግዚእ እናታቸው ትቀድሰነ ማርያም ይባላሉ፡፡ አቡነ አቢየ እግዚእ አጎታቸው ናቸው፡፡ እናታቸው እሳቸውን ፀንሳ ሳለ ቡራኬ ለመቀበል ወደ ወንድሟ ስትሄድ አቡነ አቢየ እግዚእ መሬት ላይ ወድቀው ሰግደውላታል፡፡ ደቀ መዛሙርቶቻቸውም "ለዚህች ሴት እንዴት ሰገዱላት?" ብለው ቢጠይቋቸው አቡነ አቢየ እግዚእ ስለ አቡነ ሳሙኤል ክብርና ጽድቅ ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡ ❤ አቡነ ሳሙኤል ሲወለዱ እናታቸው ለአቡነ ዐቢየ እግዚእ ሰጠቻቸው፣ እርሳቸውም በሃይማኖት በመግባር ኮትኩተው ሁሉን አስተምረው አሳደጓቸው፡፡ አባታችን የጻድቃንና የሰማዕታትን ታሪክ እያነበቡ ያዝኑና ያለቅሱ ነበር፡፡ እንደ እነርሱ በሆንኩም እያሉ ይመኙ ነበር፡፡ አቡነ አቢየ እግዚእ ሀሳባቸውን በመንፈስ ተረድተውላቸው ነበርና መርቀው ባርከው አሰናበቷቸው፡፡ አቡነ ሳሙኤልም በሕፃንነታቸው መንነው ወደ አቡነ እንጦንዮስ ገዳም ገብተው በ14 ዓመታቸው መነኰሱ፡፡ ✝ ከየት እንደመጣ የማይታወቅና መላ አካሉ እንደበረዶ ነጭ የሆነ አንበሳ መጥቶ እየመራቸው አሁን ደብረ ሃሌሉያ እየተባለ ወደሚጠራው ገዳማቸው ሄደው በዓታቸውን አጽንተው ገዳሙን መሠረቱት፡፡ አቡነ ሳሙኤል ዘሀለሎም እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ ❤ ጻድቁ የጌታችን መከራ በማሰብ ከተወለዱ ጀምሮ ተላጭተውት የማያውቁትን ፀጉራቸውን ከትልቅ ዛፍ ላይ እያሠሩ ይጸልዩ ነበር፡፡ እንዲሁ አድርገው ዛፍ ላይ ራሳቸውን ሰቅለው 40 ቀንና 40 ሌሊት ሲጸልዩ በመጨረሻ የታሠሩበት ፀጉራቸው ተነቅሎ ከመሬት ላይ ወደቁ፡፡ ደማቸውም እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልን አስከትሎ ተገልጦላቸው እጃቸውን ይዞ አንሥቷቸዋል፡፡ "ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ?" ቢላቸው ስለ ሀገራችን ሰላም ይልቁንም በዚህ በቆረቆሩት ገዳማቸው የሚኖሩትን ልጆቻቸውን እንዲጠብቅላቸው ለመኑት፡፡ ❤ ጌታችንም በገዳማቸው ውስጥ በፍጹም ሕማም፣ ደዌና ተስቦ በሽታ እንደማይገባ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ለመንግሥተ ሰማያትም ያልታጨ ሰው በዚህ ገዳም ገብቶ አይቀበርም፡፡ ጻድቁ ከዛፉ ላይ ወድቀው ሳለ ጌታችንን እጨብጣለሁ ብለው የዘረጓት እጃቸው እያበራች ኖራለች፡፡ እንደ መብረቅም እየጮኸች ለገዳሙ እንደ ደወል ታገለግል ነበር፡፡ በመጨረሻም ሊያርፉ ሲሉ ልጆቻቸውን ሰብስበው ባርከዋቸዋል፡፡ ያ አቡነ ሳሙኤል የባረኩበት ቡራኬም በመጽሐፈ ግንዘት ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ዛሬም ድረስ ሰው ሲሞት "ቡራኬ ዘአቡነ ሳሙኤል" ብሎ ካህኑ ይደግማል፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ በከተማ አካባቢ ግን እየተደረገ አይደለም፡፡ አቡነ ሳሙኤል ብዙዎችን ያመነኰሱ ሲሆን እንደነ አቡነ ተጠምቀ መድኅን፣ አቡነ ዘኢየሱስ፣ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ያሉ ሌሎችንም በርካታ መነኰሳትን አፍርተዋል፡፡ ❤ አባታችንን ያመነኰሷቸው አባት አቡነ እንጦንዮስ ሊጠይቋቸው ወደ ደብረ ሃሌሉያ ሄደው ሲመለሱ እንዲላላካቸው አንድ ትንሽ ልጅ ትተውላቸው ተመለሱ፡፡ አቡነ ሳሙኤልም በጥበብ መንፈሳዊ ኮትኩተው አሳደጉት፡፡ ❤ አንድ ቀን ምግባቸው የሚሆን የእንጨት ፍሬዎችን ለመልቀም ከበዓታቸው ሲወጡ ልጃቸው እንዳይደክምባቸው በማሰብ በገዳማቸው ትተውት ለመሄድ አሰቡ፡፡ ብቻውን ስለሆነ አስፈሪ አራዊት እንዳያስደነግጡት በማሰብ ጉድጓድ ቆፍረው በዚያ አኑረውት ሄዱ፡፡ ርቀው ሄደው የእንጨቶችን ፍሬ ሲለቅሙ በጫካው እሳት ተስቶ ገዳማቸውንም ሙሉ በሙሉ አቃጠለው፡፡ ጻድቁ ስለ ልጃቸው ወደ ፈጣሪያቸው ጸልየው ካበቁ በኋላ ወደ ገዳማቸው ቢሄዱ የልጃቸው የራስ ፀጉር እንኳን ሳትቃጠል በሰላም አገኝተውታል፡፡ ያ ልጅም በኋላ አቡነ ገብረ መስቀል የተባለው ገድለኛ አባት ነው፡፡ ከአባታችን ከአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ሃሌሉያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።

❤ ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ ከእነርሱም አንድ ዐይኑ የታወረች አንድ ሰው ነበረ ከእርሱም በተባረከ ጊዜ ዐይኑ ድና አየች እንደ ሁለተኛዋም ሆነች ሁለተኛም ጉባጣ ሰው ወደርሱ አመጡ በውኃና በዘይትም ላይ ጸልዮ የመጻጉዑን ሥጋ አጥቦ አዳነው ዲዳውንም እንዲሁ አዳነው። ❤ ከዚህም በኋላ ባልና መካን ሚስቱ መጡ ስለ እነርሱም ይጸልይ ዘንድ ለመኑት እርሱም ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ለምኖላቸው ልጆችን ሰጣቸው ወደርሱም ልጆቻቸውን አምጥተው ባረካቸው። ከዚህም የሚበዛ ብዙ ተአምራትን አደረገ። ❤ በከሀዲው በዋሊጦስ ዘመንም የአምላክ ወዳጅ ንጉሥ ቁስጠንጢኖስ ያሠራቸውን አብያተ ክርስቲያናት ጭፍሮቹ ወደ አንጾኪያ መጥተው አፈረሱ። ከዚህም በኃላ የፋርስ ሰዎች ጦርነት ሊገጥሙት መጡ ሲጓዙም ወደ ቅዱስ ዱማድዮስ ማደሪያ ደረሱ ስለ ርሱም ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም ይወግሩት ዘንድ አዘዘ ከረድኡም ጋራ በድንጊያ ወገሩት። የጣሉባቸው ድንጋይም በበዐታቸው ላይ ታላቅ ኮረብታ ሆነ። እርሱና ረድኡም እንዲህ በሆነ ድርጊት ዐረፉ። ❤ ከአንድ ዓመትም በኃላ ለአንድ መንገደኛ ነጋዴ ሰው ገለጠለት።ገመልም ጭኖ ነበር። እርሱም ሲያልፍ ገመሉ ከምድር በታች በጉድጓድ ውስጥ ወደቀ። ሰዎችም ገመሉን ሊያወጡት በመጡ ጊዜ የቅዱስ ዱማድዮስ በዐት ተገለጠ። ቆፍረውም የቅዱስ ዱማድዮስንና የረድኡን ሥጋ በክብር አወጡ ይኸውም በዐረፈበት በሐምሌ ሃያ አምስት ቀን ነበር። ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው የእርሱን ሥጋና የረድኡን ሥጋ በውስጥዋ አኖሩ ጌታችንም ከእርሱ ብዙዎች ተአምራትን ገለጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አበከረዙን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ኵሎ ዘፈቀደ ገብረ እግዚአብሔር። በሰማይኒ ወበምድርኒ። በባሕርኒ ወበኵሉ ቀላያት"። መዝ 134፥6። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 5፥1-9።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳ_ምስባክ፦ "መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁ። አምላክ እሥራኤል ውእቱ ይሁብ ኃይለ ወጽንዐ። ወይትባረክ እግዚአብሔር"። መዝ 67፥35። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 2፥1-ፍ.ም፣ ይሁ 1፥11-17 እና የሐዋ ሥራ 26፥6-12። የሚነበበው ወንጌል ማር13፥5-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ የዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ መርቆሬዎስ የቅዳሴ ቤትና የልደት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።

                              ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅዱስ_አበከረዙን፦ ይህም ቅዱስ ባንዋን ከሚባል አገር ነው። አስቀድሞ ወንበዴ ነበር ሌሎችም ሁለት ወንበዴዎች ነበሩ ገንዘቡን ሊሰርቁ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደ አንድ መነኰስ በአንድነት ሔዱ በጸሎትም እየተጋ አገኙት ጸሎቱን ጨርሶ እስቲተኛ ድረስ ጠበቁት እርሱ ግን ከቶ አልተኛም በልቡናቸውም ፍርሀት አደረባቸውና ደነገጡ። በነጋ ጊዜም ያ ሽማግሌ መነኰስ ወደ ሽፍቶቹ ወጣ ባዩትም ጊዜ ከእግሩ በታች ሰገዱ ሰይፎቻቸውንም በፊቱ ጥለው ደቀ መዝሙሮቹ ያደርጋቸው ዘንድ ለመኑት በርሱም ዘንድ መነኰሱ። ቅዱስ አባ አበከረዙንም በሥጋውም በመንፈሱም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። አንድ አረጋዊም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰማዕት ይሆን ዘንድ እንዳለው ነገረው። ❤ ከሰባት ዓመት በኃላም ሰይጣን በክርስቲያን ወገኖች ላይ መከራን አመጣ አባ አበከረዙንም ተነሥቶ መንፈሳዊ አባቱን እጅ ነሥቶ ከእርሱም ቡራኬ ተቀብሎ ኒቅዮስ ወደሚባል አገር ሔደ ንጉሥ መክስምያኖስንም አገኘው ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰም በፊቱ ታመነ መኰንኑም በጽኑ ስቃይ አሰቃየው በብረት መጋዝም ስጋውን መገዘው ቁስሉንም በመጣጣና በጨው አሸው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ሲወስዱት አምስት ጊዜ በመርከብ ምሰሶ ላይ ሰቀሉት ገመዶችም ተበጠሱ ከማስ በተሠራ ጋን ውስጥም አድርገው በባሕር ጣሉት ከእግዚአብሔርም የተላከ መላክ ከባሕር አውጥቶ ወደ ገምኑዲ ከተመሰ እንዲሔድ አዘዘው ብንውም ወደሚባል አገር ደረሰ ስለ አባ አበከረዙንም ጠየቀ እነርሱም አላወቁትም ነበርና ከብዙ ጊዚያትም ጀምሮ ከዚህ ሔዷል ወዴት እንዳለም አናውቅም ወሬውንም አልሰማንም አሉት። ❤ አንዲት ብላቴና ግን አስተውላ አወቀችው ፈራችም ከፍርሀቷም ብዛት የተነሣ ወደቀችና እንስራዋ ተሰበረ እርሷም ሰዎች "ይህ አባ አበከረዙን ነው" አለቻቸው የአገሩ ሰዋችም ሁሉም ፈጥነው መጥተው ከእርሱ ተባረኩ ደዌ ያለባቸውም ወደርሱ ይመጡ ነበር እርሱም በዘይት ላይ ጸልዮ ሲቀባቸው ወዲያውኑ ይድኑ ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ገመኑዲ ከተማ ሔደ ከወታደሮቹም አንዱን "እኔ ክርስቲያን ነኝና በዚች ከተማ ውስጥ አሥረህ ጎትተኝ" አለው እርሱም ወደ መኰንኑ እስከሚአደርሰው እንደ አዘዘው አደረገ መኰንኑም በእንጨት ላይ ዘቅዝቆ ሰቀለው በአፍንጫውና በአፋም ብዙ ደምእየፈሰሰ ዐሥር ቀኖች ኖረ አባ አበከረዙንም የጭፍራ አለቃውን ልጅ ረገማትና ወዲያውኑ ሞተች በመቃብርም ዐሥራ ሁለት ቀኖች ኖረች። ስለ እርሷም አባ አበከረዙንን ለመኑት ክብር ይግባውና ወደጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየ ያንጊዜም ከሙታን ተለይታ ተነሥታ በሲኦል ያየችውን ሁሉ ነገረቻቸው ከጭፍሮቹ ጋር ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ ቁጥራቸውም ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት ነፍስ ነበር። ❤ ከዚህ በኋላ አባ አበከረዙንን ወደ እስክንድርያ ሰደደው በዚያም ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ዳግመኛ ወደ ገምኑዲ ላኩት በዚያም በብረት በትሮች ደብድበው የጀርባውን አጥንት ሰበሩት እርሱ ግን በፈጣሪው ኃይል ዳነ። ❤ መኰንኑም ማሰቃየት በደከመ ጊዜ ዳግመኛ ወደ እስክንድርያ ከተማ ላከው ወደ እስክንድርያም በሚያዚያ ወር በደረሰ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለትና አጽናናው ገድሉንም በዚያ እንደሚፈጽም ነገረው። ስሙን ለሚጠራ ሁሉ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ ኃጥያቱን እንደሚያስተሠርይለት ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚህም በኃላ ራሱን ቆረጡት ተጋድሎውንም ፈጽሞ የሰማዕትነትን አክሊል ተቀበለ። ❤ የእግዚአብሔር መልአክም መኑፍ ከሚባል አገር ለአንድ ቄስ ተገልጦ የቅዱስ አበከረዙን ሥጋ ያለበትን ቦታ ነገረውና እንዲወስደው አዘዘ። እርሱም ወስዶ ባማሩ ልብሶች ገነዘው የመከራውም ወራት እስከሚፈጸም በመልካም ቤት አኖረው ከዚህም በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሰርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አበከረዙን በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #ሶርያዊው_ሰማዕት_ቅዱስ_ዲማድዮስ፦ ይህም ቅዱስ በፋርስ አገር አደገ የከዋክትን ምግብን ጥበብ ተማረ ከዚህም በኋላ ክርስርስቲያን ሊሆን ወደደ ከፋርስ ሰዎችም ስሙ አጋሊዮስ የሚባል ቄስ በገበያ ውስጥ አገኘ እርሱም ወደ እግዚአብሔር የሚያደርስ ሃይማኖትን አስተማረው እጅግ ደስ ብሎት ቤተሰቦቹን ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ ያስተምራቸው ጀመረ አሳመናቸውም። ❤ ከዚህም በኋላ በሶሪያና በሮም መካከል ወዳለች አገር ሔደ በዚያም የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቆ መነኰሰ ታላቅ ተጋድሎንም መጋደል ጀመረ መነኰሳቱም ታላቅ የሆነ ተጋድሎውን በአዩ ጊዜ በእርሱ ላይ ቀንተው ከገዳም ሊያሳድዱት ወደዱ። በአወቀም ጊዜም ወጥቶ ወደ ቅዱስ ሰርጊዮስ ገዳም ሔደ በዚያም በአንድ ባህታዊ ቄስ ዘንድ ተቀመጠ ከዚህም በኋላ ዲቁና እንዲሾመውና ከእርሱ ጋር በቤተ መቅደስ ውስጥ እንዲያገለግል ቅዱስ ዲማድዮስን አስገደደው ትዛዙንም መተላለፍ ባልተቻለው ጊዜ ዲቁና ተሾመ። ❤ አረጋዊው ቄስ በመሰዊያው ላይ በሚሰየም ጊዜ በቅዳሴው እኩሌታ በምሥዋቱ ላይ ርግብ ስትወርድ ቅዱስ ዱማድዮስ ያያት ነበር እርሱም ሥጋዊት ርግብ እንደሆነች ያስብ ነበር ሽማግሌው ግን አያያትም ነበር የቅዳሴው ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ባሕታዊው ቄስ እንዲህ ብሎ ጠየቀው በቅዳሴ ጊዜ የምትደነግጥ እጅህንም ወደ መሥዋቱ የምትዘረጋው ምን ሆነህ ነው እርሱም ርግቧን እንዳያት ነገረው "ከእንግዲህ ስታያት ንገረኝ" አለው። ❤ ከዚያም በኋላ በአያት ጊዜ "አባቴ ሆይ ያቺ ርግብ መጣች" ብሎ ነገረው ሽማግሌው ግን አላያትም እጅግም አዝኖ በእግዚአብሔር ፊት ሰገደ ያቺንም ርግብ እስከሚያያት ድረስ ፈጽሞ ይጸልይና ይማልድ ነበር ያቺ ርግብ መንፈስ ቅዱስ እንደ ሆነ ያውቅ ነበርና ለዲያቆን አባ ዱማድዮስም ልቡ እንዳይታበይ አልነገረውም። ❤ ከዚህ በኃላም ሽማግሌው ቄስ ወደ ኤጲስቆጶስ ሒዶ ዱማድዮስን የቅስና መዐረግ ይሾምለት ዘንድ ለመነው ልመናውንም ተቀብሎ ያለ ውዴታው ቅስናን ሾመው። ሊቀ ጳጳሳቱም ዜናውንና ገድሉን በሰማ ጊዜ ከእርሱ ጋራ ወገኖቹን ወሰደ ከወገኖቹ ጋራም ወደርሱ ሔዶ በረከቱን ሊቀበል ወደደ። ቅዱስ ዱማድዮስ ግን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ከዚያ ተሠውሮ ሔደ ወደ ሰማዕቱ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም ደረሰ ከዚያም ወደ በረሀ ሔዶ በዚያ ሣር እየበላ ኖረ እርሱ ከከንቱ ውዳሴ ይሸሽ ነበረና። ❤ እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆችንና ተአምራቶችን ያደርግ ነበር። በአንዲት ቀንም ውኃ ሊቀዳ ወደ ወንዝ ሔደ ውኃ የሚቀዱ ሴቶችም አይተውት በመጠቃቀስ በእርሱ ላይ ተዘባበቱ በልቡም እያዘነ ውኃ ሳይቀዳ ተመለሰ ያን ጊዜም ወንዙ ደረቀ። ❤ ሰዎችም ቅዱስ ዱማድዮስ እንዳደረቀው በአወቁ ጊዜ ሴቶችና ወንዶች ሁሉ ወጥተው በብዙ ለቅሶ ለመኑት ልቅሶአቸውንም አይቶ ክብር ይግባውና ጌታችንን ለመነው የወንዙንም ውኃ እንደ ቀድሞው መለሰላቸው። ሰዎችም ሲያከብሩት በአየ ጊዜ ከዚያ መጠለያ ከሰማይ በታች ያለውን የበጋውን ቃጠሎና የክረምቱን ቅዝቃዜ ታግሦ እየተጋደለ ዓመት ሙሉ ኖረ በብዙ ድካምም አስገድደው ትንሽ ጎጆ ሠርተው በውስጧ አስገብት።

❤ ከዚህም በኋላ ቆሎንያ ወደሚባል አገር ሔዳ ሰበከች ከዚያም ወደ አገርዋ ሔዳ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማረች አባትና እናቷንም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን መለሰቻቸው። ተጋድሎዋንም ፈጽማ ሐምሌ 25 ቀን በሰላም አረፈች። የሐዋርያነት አክሊልንም ተቀበለች። ሥጋዋም በግብጽ ደቡብ ሰንጋር በሚባል አገር እስከ ዛሬ አለ። ከሥጋዋም ብዙ ድንቅና ተአምር ተገለጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ተክላ ጸሎት ይማረን በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እንዲኒና፦ ይህም ቅዱስ ባና ከሚባል አገር ነው። ጎልማሳም ነበር። ወላጆቹም ከሀገር ሽማግሌዎች የሆኑ ምዕመናን ነበሩ። ከዚህም በኋላ ይህ ቅዱስ ወደ እንዴናው ከተማ ሔደ። በመኰንኑም ፊት በመቆም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። ❤ መኰንኑም በፍላፃ ይነድፉት ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት ነገር ግን ከፍላፃዋች ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም። ከዚህም በኋላ አሥሮ ወደ እስክንድርያ ከተማ ላከው ከእርሱም ጋር ቅዱስ ቢማኮስና ሌሎች ሁለት ሰማዕታት ነበሩ። የእስክንድርያውም ገዥ አሠራቸው። ❤ ቅዱስ እንዲኒናን ግን በአፍንጫው ብዙ ዳም እስኪፈስ ድረስ ዘቅዝቆ ሰቀለው። በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም ብዙ አሠቃየው። ከማሠቃየትም በሰለቸ ጊዜ ፈርማ ወዳሚባል አገር ላከው። ❤ በዚያም በወህኒ ቤት ቅዱስ ሚናስን አገኘውና ደስ አለው። እርስ በርሳቸውም ተፅናኑ። ከዚህም በኋላ መኰንኑ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ አሠቃየው በእሳት ባጋሉትም መጋዝ ሥጋውን ሰነጥቀው። በብረት ምጣድ ውስጥም አበሰሉት ጌታችንም ያለጉዳት በጤና አስነሣው። ❤ መኰንኑም ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ከሥጋውም ታላላቅ ተአምራት ተደረጉ። ለበሽተኞችም ፈውስ ተደረገ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ እንዲኒና ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_አባ_ይስሐቅ፦ ይህም ቅዱስ ሳምሳ ከምባል አገር ነበር እሱም የአታክልት ቦታዎች ጠባቅ ነበረ ደግ የዋህና ፁሙድ አገልጋይ ነበረ ሰጋም አይበላም ነበር ወይንም አይጠጣም ነበር በየሁለት ቀን ይፆም ነበረ ቅጠልም ይበላ ነበረ ድሆችንና ችግረኞችንም ይጎበኛቸው ነበረ ከደመዙም የምተርፈውም ይሰጣቸዋል። ❤ ክብር ይግባውና ጌታችንም በራእይ ተገለጠለትና ወደ መኩንኑም ሒዶ በቅዱስ ስሙ እንዲታመን አዘዘው ከዝህም ቡኃላ ብዙ ቃል ክዳን ሰጠው ያዘጋጀለትንም የደስታ አክልሎችን ተስፍ አስደረገው። ❤ በነቃ ግዜም እጅግ ደስ አለው ተነሥቶም ከእርሱ ያለውን ገንዘብ ለድሆች ሰጠ ከዝያም በኋላ ይረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ወደ መኰንኑም ደርሶ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው በእሳትም አቃጠለው ሕዋሳቱንም ቆራርጦ ሰቀለው በመንኰራኲርም አበራየው ጌታችንም ያጸናውና ይፈውሰው ነበር ከመሠቃየቱም የተነሣ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ የሰማዕትነትንም አክልሊ በመንግስተ ሰማያት ተቀበለ። ❤ ከዚህም በኃላ ምእመናን ሰዎች ከሀገሩ ሳምሳ መጥተው ሥጋውን ወሰዱ በአማሩ ልብሶችንም ገንዘው የመከራው ዘመን እስክፈጸም ድረስ በመልካም ቦታ አኖሩት ከዚያም በኋላ ውብ የሆነች ቤተክርስትያን ሠሩለት ሥጋውን በዝያ አኖሩት ከእርሱም ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ ይስሐቅ ጸሎት ይማረን በረከት ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅድስት_ኢላርያ፦ ይች ቅድስት በድሜራ አቅራብያ ድምድል ከሚባል አገር የሆነች ነች። የዚችም ቅድስት ወላጆቿ ደጎች ምእመናን ነበሩ እርሷዋም በስጋዋና በነፍሷ የነጻች ነበረች ሁሉ ጊዜም ትጾምና ትጸልይ ነበረች። አሥራ አንድ ዓመትም በሆናት ጊዜ እርሷ ቆማ ስትጸልይ ጌታችን ታላቅ። ብርሃንን ገለጠላት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሩፋኤልም ተገልጦ እንድህ አላት "ተጋድሎ ተዘርግቶ ሳለ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ለሚጋደሉም አክልሎች ተዘጋጅተው ሳሉ አንቺ ለምን ከዚህ ተቀምጣሻል" አላት። ❤ ይህንንም በሰማች ጊዜ ደስ አላት ገንዘቧዋንም ሁሉ ለድኖችና ለችግረኞች ሰጥታ ጣው ወደ ምባል አገር ሔደች ከዝያም ስርስና ወደ ምባል አገር ሒዳ በመኰንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነች ጌታችንም ሳኑሲ ለሚባል ሰው ለዚች ቅድስት ከእርሷ የሚሆነውን ነገረው። ባያትም ጊዜ በእርሷ ደስ አለው አረጋጋት ልቧንም አጸናናት መኰንኑም ታላቅ ሥቃይን አሰቃያት ሥጋዋን ሁሉ ሠነጣጠቀ በእሳት ያጋሏቸውንም የብረት ችንካሮች በሥጋዋ ውስጥ ቸነከሩ። ❤ ከዚህም በኋላ ከአምስት መቶ ባልንጀራሞች ሰማዕታት ጋራ አሠራት በመርከቦችም ከእርሱ ጋራ ወሰዳቸው እነርሱም በመርከብ ስጓዙ አንበሪ መጥቶ ከእናቱ እቅፍ አንዱን ሕፃን ልጅ ነጥቆ ወሰደ እናቱም ከእርሱ በቀር ሌላ ስለሌላት እጅግ አዝና አለቀሰች ይች ቅድስትም አይታ ራራችላት ስለእርስዋም ጌታችንን ለመነችው ጌታችንም አንባሪውን አዘዘውና ሕፃኑን ደኅና እንደሆነ ወደ እናቱ መለሰው ምንም ጥፋት አላገኘውም። ❤ ከዚህም በኃላ ሕዋሳቷን ቆራረጡ የእጆቿንና የእግሮቿን ጥፍሮች ነቀሉ ምላሷንም ቆረጡ እግሮቿንም በብረት ችንካሮች ቸነከሩ። በብረት ዐልጋ ላይም አስተኝተው ከበታችዋ እሳትን አነደዱ። ነገር ግን ምንም ምን ጥፋት አልደረሰባትም ክብር ይግባውና ጌታችን አድኗታልና። ❤ መኰንኑም እርሷን ከማሠቃየት የተነሣ በሰለቸ ጊዜ ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ኢላርያ በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅዱሳት_ቴክላና_ሙጊ፦ እነዚህም ከእስክንድርያና ከባሕያራ አውራጃ ቀራቁስ ከሚባል መንደር የከበሩ ናቸው። እሊህም ቅዱሳት ቀራቁስ በሚባል መንደር በአንዲት እግዚአብሔርን በምትፈራ አማኒት ሴት ዘንድ አደጉ። ወደ ባሕር ዳርቻ በአለፉ ጊዜም የክርስቲያን ወገኖችን ሲአሠቃያቸው መኰንኑን አዩት። እነዚያም ደናግል ስለ ልቡ ደንዳናነት አደነቁ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠላቸው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም መከራን ለሚታገሡ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጀውን ክብራቸውን አሳያቸውና አጽናናቸው። ❤ ከዚህም በኃላ በመርከብ ተጭነው ወደ እስክንድርያ ተጓዙ። እመቤታችን ማርያምም አልቃሾች በሆኑ በሁለት ሴቶች አምሳል ከኤልሳቤጥ ጋራ ተገለጸችላቸው ከእርሳቸውም ጋራ ወደ ከተማው በደረሱ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመኰንኑ ፊት ታመኑ መኰንኑም ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸው። ❤ ከዚህም በኃላ የቅድስት ሙጊን ራስ በሰይፍ ቆረጠ ተጋድሎዋንም ፈጸመች። ቅድስት ቴክላን ግን ድሙጢ ወደሚባል አገር ላካት በዚያ ሰማዕት ሆነች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዳሳት ቴክላና ሙጊ ይማረን በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤               ❤ #ሐምሌ ፳፭ (25) ቀን። ❤ እንኳን #ለሰማዕቱ_ለቅዱስ_መርቆሬዎስ ቁጥር የሌላቸው ተአምራትንና ድንቆችን ባሳየበት በምስር አገር #ለቤተ_ክርስቲያን_ቅዳሴ_ቤቱና_ለልደቱ ዓመታዊ በዐል፣ #ለነቢዩ_ቅዱስ_ኄኖክ_ከሞት_ለተሰወረበት (ለዕርገቱ) በዐል፣ ከኒቆምድያ አገር ለሆነች ለሐዋርያዊት ለቅዱስ ጳውሎስ ረድእ #ለቅድስት_ቴክላ_ለዕረፍት_በዐል፣ ባና ከሚባል አገር ለሆነ #ለቅዱስ_እንዲኒና_ሰማዕትነት_ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዐል፣ #ለአባ_ይስሐቅ_ሰማትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ በድሜራ አቅራቢያ ድምድል ከሚባል አገር ለሆነች #ለቅድስት_ኢላርያ ሰማዕትነት ለተቀበላችበት ለዕረፍት በዓል፣ ከእስክንድርያና ከባሕያራ አውራጃ ቀራቁስ ከሚባል መንደር ለሆኑ ለከበሩ #ቅዱሳት_ቴክላና_ሙጊ ሰማዕትነት ለቀበሉበት ለዕረፍት በዓል፣ ባንዋን ከሚባል አገር ለሆነ #ለቅዱስ_አበከረዙን_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለሶርያው ሰው ለሰማዕቱ #ለቅዱስ_ዱማድዮስ_ለዕረፍት በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በፍቅር አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከስድስት_መቶ_ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው፣ አትሪብ ከሚባል አገር #ከሃያ_አምስት_ሽህ_ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና እግዚአብሔር አምላክ በረከትን ያሳትፈን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ በዚችም ዕለት የያሬድ ልጅ #ቅዱስ_ኄኖክን የመላልኤል ልጅ የቃይናን ልጅ የኄኖስ ልጅ የሴት ልጅ የአዳም ልጅ ኄኖክን መላእክት ይዘው አሳረጉት ይኸውም በመባርቅትና በነፋሳት ላይ ተጭኖ በመብረር ወደ ሰማይ ወስደው ከረቂቃን መላእክት ጋር አኖሩት የእግዚአብሔርም ትእዛዝ ጸሐፊ ተባለ። ❤ እንዲህም አለ "ከማደሪያው ከሚወጣው ከቅዱሱና ከገናናው በጸናች ኃይሉ ከሠራዊቱ ጋር በሲና ተራራ ከሚገለበጠው ጋር በመነጋገር ተመላለስኩ። ሁሉም ይፈሩ ነበር በውኃ ዳርም ሳለሁ የልመናቸውን መታሰቢያ ጻፍኩ እስከ አንጎላቸሁና ሕልም እንደሚያይ እስከምሆን ይችም በአርሞን ግራና ቀኝ ያለች አገር ናት"። በደብር ቅዱስ ለነበሩ ለኃጢአት ለሚተጉ ለሴት ልጆች ይዘልፋቸው ዘንድ ቃል እንደጠራውና እንዳሳየው ተናገረ። ❤ እንዲህ አለ "በበረድ ደንጊያ ወደ ተሠራ ታላቅ ቤት ቀረብኩ በበረድ ደንጊያ የተሠራ የዚያ ቤት ግድግዳ እንደ ሳንቃ ልዝብ ነው ከዚህ ቤት የሚበልጥም ሌላ ቤት አየሁ ደጃፉም የተከፈተ ነው በእሳት ቅጽርም የተሠራ በክብር ከሁሉ የሚበልጥ ነው። በውስጡም ከፍ ያለ የእግዚአብሔርን ዙፋን አየሁ መልኩም እንደ ውርጭ ነው አጎበሩም እንደሚያበራ ፀሐይ ነው ከዙፋኑም በታች የኪሩቤል ድምፅ ይሰማል። ዳግመኛም ወደ ሰባት ተራራዎች ደረስኩ ሦስቱ በምሥራቅ በኵል ሦስቱ በአዜብ በኵል ናቸው የመካከለኛው ግን ሰማይ ጠቀስ ነው የመላእክትም ጌታ በላዩ አለ"። ሌሎች አራት ገጾች ኪሩቤልን አየ ስለ ክርስቶስም እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "የዘመናት አለቃ ወደ ሆነው የሰው ልጅ ተጠራ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የነበረ ሆነ" ሁለተኛም "ለጻድቃን የጽድቅ በትር ለአሕዛብም ብርሃን ተስፋ ለሌላቸወሰ አለኝታ ይሆናል" አለ። ❤ በሰማይ ገጽ ስለሚመላለሱ ብርሃናት እንዲህ አለ "አንዱም አንዱ በየወገናቸው በሠለጠኑበትና በተሠየሙበት ጸንተው ይኖራሉ" ስለ ነፋሳትም መውጫዎች እንዲህ ብሎ ተናገረ "ሦስቱ በሰማይ ገጽ ሦስቱ በምድር ገጽ ሦስቱ በግራ ናቸው"። ስለ አዳምም እንዲህ አለ "እነሆ በሬ ከምድር ወጣ ፀዓዳም ሆነ" ስለ ሔዋንም "ሴት እምቦሳ ከርሱ ወጣች" አለ። ❤ ስለ ምኵራብም "ያንን አሮጌ ቤት እስከሚአሳንሰው ድረስ አየሁ አለ ምሰሶዎቹንም ከውስጡ አወጣ"። ስለ ቤተ ክርስቲያንም "ጌታ አዲስ የበጎች ቤት አምጥቶ እስቲሠራ ድረስ አየሁ ከቀድሞውም ቤት የበለጠ ነው በጎችም ሁሉ በውስጧ ይሠማራሉ" አለ። ስለ ምእመናንም "የእሊህም በጎች ፀጒራቸው ንጹሕ ነጭ ነው የተበተኑትም ከአራዊት ጋራ ይሠማራሉ ሁሉም በአንድነት ተሰብስበው ገራሞች ሁነዋልና"። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ኄኖክ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር 27 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ፦ በዚች ቀን ቁጥር የሌላቸው ተአምራትንና ድንቆችን ባሳየባት በምስር አገር የቅዱስ መርቆሬዎስ ቅዳሴ ቤተ ክርስቲያኑ ሆነ። ልደቱም በዚሁ ዕለት ነው፡፡ ታሪኩን፦ ከኅዳር 25 ይመልከቱ።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #ሐዋርያዊት_ቅድስት_ቴክላ፦ ይህችም ቅድስት አገሯ ኒቆምድያ ነው። በቅዱስ ሐዋርያ በጳውሎስ ዘመን ሐዋርያዊት ሆነች። ቅዱስ ጳውሎስም ከአንጾኪያ ከተማ በወጣ ጊዜ ወደ ኒቆምድያ ከተማ ሔደ በዚያም ስሙ ሰፋሮስ የሚባል ምእመን ሰው ነበረ ቅዱስ ጳውሎስን ወስዶ በቤቱ አኖረው ብዙ አሕዛብም የሐዋርያው የጳውሎስን ትምህርት ይሰሙ ዘንድ በእርሱ ዘንድ ይሰበሰቡ ነበር። ይህች ቅድስት ቴክላም በቤቷ መስኮት ተመለከተች የሐዋርያውንም ትምህርት ሰማች እንዲሁም ትምህርቱን እያዳመጠች ሳትበላና ሳትጠጣ ሦስት ቀኖች ቆየች ትምህርቱም በልቧ አደረ አባትና እናቷ ቤተሰቦቿ ሁሉ አዘኑ። ከምክርዋም እንድትመለስ ሐዋርያው ጳውሎስንም እንዳትከተል ለመኑዋት ነገር ግን አልሰማቻቸውም። ❤ ሁለተኛም አባቷ ወደ ንጉሡ ሒዶ ሐዋርያው ጳውሎስን ከሰሰው ንጉሡም ወደ እርሱ አስቀርቦ ስለ ሥራው ጠየቀው። ነገር ግን የሚቀጣበት ምክንያትን በላዩ አላገኘም ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስንም እንዲአሥሩት አዘዘ። ❤ ይህች ቅድስት ቴክላም ልብሶቿንና ጌጦቿን ከላይዋ አስወገደች። ወደ ቅዱስ ጳውሎስም ሒዳ ከእግሩ በታች ሰገደች በእርሱም ዘንድ እየተማረች ተቀመጠች። ወላጆቿም በፈለጓት ጊዜ አላገኟትም በሐዋርያው ቅዱሰሰ ጳውሎስ ዘንድ እርሷ እንዳለች ሰዎች ነገሩዋቸው በመኰንኑም ዘንድ ከሰሱዋት እርሱም በእሳት እንዲአቃጥሉዋት አዘዘ። እናቷም "ስለርሷ ሴቶች ሁሉ እንዲገሠጹና እንዲፈሩ አቃጥሏት" እያለች ጮኸች ብዙዎች የከበሩ ሴቶች በሐዋርያው ጳውሎስ ትምህርት አምነው ነበርና እርሷ ግን በሚአቃጥሏት ጊዜ ልቧን አጽንታ ቅዱስ ጳውሎስን ተመለከተችው። ❤ ዳግመኛም ሲጸልይ ቅዱስ ጳውሎስን አወጡት በላይዋም በመስቀል ምልክት አማተበ። ራሷንም ወደ እሳቱ ምድጃ ወረወረች። ሴቶችም ያለቅሱላት ነበር። ያን ጊዜም እግዚአብሔር ብዙ ዝናብን በረድና መብረቅን ላከ የእሳቱም ምድጃ እንደ ቀዝቃዛ ጠል ሆነ ቴክላም ሩጣ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ተሠውሮ ወደ አለበት ቦታ ደረሰች ራሷንም ላጭቶ ትከተለው ዘንድ ለመነችው እንዲሁም አደረገላት። ❤ ወደ አንጾኪያ ከተማም በሔደች ጊዜ ከመኳንንቶች አንዱ ሊአገባት ፈለገ መልኳ እጅግ ውብ ነበረና እርሷም ዘለፈችው ረገመችውም እርሱም በዚያች አገር ገዥ በሆነ በሌላ መኰንን ዘንድ ከሰሳት እርሱም ለአንበሶች እንዲጥሏት አዘዘ። በአንበሶች መካከልም ሁለት መዓልት ሁለት ሌሊት ኖረች እነዚያም አንበሶች እግርዋን ይልሱ ነበር እንጂ ምንም አልከፉባትም። ❤ ከዚህም በኋላ በሁለት በሬዎች መካከል አሥረው በከተማው ውስጥ ሁሉ አስጐተቷት። ነገር ግን ምንም ምን ክፉ ነገር በላይዋ አልደረሰም ከዚያም በኋላ ለቀቁዋት። ወደ ቅዱስ ጳውሎስም ሔደች እርሱም አረጋጋት አጽናናትም። ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድትሰብክ አዘዛት።