ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
رفتن به کانال در Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
نمایش بیشتر603
مشترکین
-324 ساعت
-87 روز
-1730 روز
آرشیو پست ها
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
በአጥቢያችን ከተከናወኑ ከከተራ እስከ ቃና ዘገሊላ የተከበሩ በዓላት ከሚዲያና ዕቅበተ እምነት ክፍል ከምስል ማህደር በጥቂቱ ይህን ይመስላል ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን አሜን!!!
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፲፫ (13) ቀን።
✝ እንኳን #ለታላቋ_ሰማዕት_ቅድስት_ዴ_ድሚያናና ከእርሷ ጋር አብረው ሰማዕትነት ለተቀበሉ #ለአርባው_ደናግል ለዕረፍቸው መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ #ሰማዕቷ_ቅድስት_ዴ_ድሚያና፦ ይኽችም ቅድስት ዴሚያና በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ የተወለድችና በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ክርስቲያኖችን በአስከፊና በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገድል በነበረው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን የነበረች በእርሱም እጅ በጭካኔ ዐሥር ጊዜ እጅግ አሠቃቂ የሆኑ መከራዎችን በመቀበል በመጨረሻም ከተከታዮቿ ከ40 ደናግል ሰማዕታት ጋር አንገቷን የተሰየፈች ታላቅ ሰማዕት ናት፡፡
✝ ኤርትራ ውስጥ ወደሚገኘው ቅድስት ዴሚያና የሴቶች ገዳም (ቤተ ደናግል) ስንሔድ መጀመሪያ ላይ ያጋጠመንና ያስገረመን ነገር መነኰሳይያቱ በጣም ወጣት ሆነው ብዛት ያላቸው መሆኑ ነው፡፡ ገዳሙ ቤተ ደናግል ነው፣ ማለትም ድንግል የሆኑ ሴቶች ብቻ የሚኖሩበት ገዳም ነው፡፡ እንግዳን ለመቀበል የነበራቸው ጉጉትና ፍቅር፣ ትሕትናቸው፣
ትጋታቸው ሁሉ እውነትም ሰማዕቷን ድንግል ዴሚያናንና አርባውን ደናግል ሰማዕታት አስመስሏቸዋል፡፡ገዳሙ ያለበት ቦታ ከተማው ላይ ከእንዳ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ብዙም ሳይርቅ ነው፣ ከአጠገቡም የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ይገኛል፡፡
✝ ገዳሙ አሁን ያለበት ቦታ በመጀመሪያ የግለሰብ ቤት እንደነበር የነገሩን መነኰሳይያቱ ናቸው፡፡ ሰማዕቷ ቅድስት ዴሚያና በቦታው ላይ ትኖር ለነበረችው አንዲት ሕዝባዊት እናት ተገልጣላት ቦታው ወደፊት ቤተ ደናግል እንደሚሆን ስለነገረቻት ያችም እናት ቤቷን ለሰማዕቷ ቤተ ክርስቲያን እንዲሆን ሰጠች፡፡ ዳግመኛም ቅድስት ዴሚያና ለአንዲት ድንግላዊት ተገልጣላት ወደ ግብጽ ሔዳ መንኵሳ እንድትመጣና ገዳሙን ገድማ ለደናግል መነኰሳይያቱ እመ ምኔት እንድትሆን ነገረቻት፡፡ በዚኽ መሠረት ነው ገዳሙ ተስፋፍቶ ቤተ ደናግል ለመሆን የበቃው፡፡ ስያሜውም በትግርኛ "ገዳም ደብረ ደናግል ሰማዕት ቅድስት ድምያና ምስ 40 ደቃ" ተባለ፡፡
✝ የሰማዕቷ የቅድስት ዴሚያና አባቷ ማርቆስ የከሃዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ሹመኛ ሆኖ በግብፅ ሁለት ግዛቶችን ያስተዳድር የነበረ ቢሆንም እርሱና ቤተሰቡ ግን ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ እናቷ ገና በልጅነቷ ስለሞተች አባቷ ቅድስት ዴሚያናን ከልጅነቷ ጀምራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድታውቅ ሃይማኖት እንድትማር አድርጎ በንጽሕና አሳደጋት፡፡
እርሷም ከልጅነቷ ጀምራ መጽሐፍ ቅዱስንና የቅዱሳንን ሕይወት እያነበበች አደገች፡፡
✝ ቅድስት ዴሚያናም 15 ዓመት በሆናት ጊዜ በከተማው የታወቀ አንድ ሰው ሊያገባት ፈለገ፣ አባቷም ይህንን ሲያማክራት እርሷ ግን "…እኔ የክርስቶስ ሰማያዊ ሙሽራ ለመሆን ራሴን ለክርስቶስ ሰጥቻለሁ" በማለት ጋብቻውን በጽኑ ተቃወመች፡፡ ከዚኽም በኋላ ከከተማ ውጭ ባለው በረሓ ውስጥ በሰሜናዊ አቅጣጫ የምትኖርበትን ቤት ይሠራላት ዘንድ አባቷን ጠይቃ ሲሠራላት ቤቱን የጸሎት ቤት አደረገችው፡፡ በኋላም ቅድስት ዴሚያና ያንን አባቷ ያሠራላትን ቤተ መንግሥት የመሰለ ቤቷን ወደ ገዳምነት ቀየረችውና ከደናግል ጓደኞቿ ጋር በአንድነት መኖር ጀመረች፡፡ እርሷም ለደናግል ጓደኞቿ ጌታችንን ስለማመን ታስተምራቸውና ታበረታቸው ነበር፡፡ እነርሱም በጾም በጸሎት፣ ቅዱሳት መጻሕፍን በማንበብ፣ የዳዊት መዝሙርን በመዘመር፣ የእጅ ሥራንም በመሥራት እየተጉ መንፈሳዊ ሕይወታቸው ሌሎቹን ደናግል እየማረከ ስለመጣ ቊጥራቸው 40 እስኪሆኑ ድረስ ተሰባሰቡ፡፡
✝ ከዚኽም በኋላ ከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በ284 ዓ.ም ከነገሠ በኋላ ክርስቲያኖችን ሁሉ ከያሉበት እያስፈለገ ይገድል አብያተ ክርስቲያናትንም ያጠፋ ጀመር፡፡ ዲዮቅልጥያኖስ ከነገሠና ከካደ በኋላ ወርቅ አቅልጦ 35 የወንድና 35 የሴት ጣዖታትን አሠርቶ ሰው በሚመላለስበት አደባባይ ላይ በማቆም ሁሉም ለጣዖታቱ እንዲሰግድ አዋጅ አስነገረ፡፡
በዘመኑም ለጣዖታቱ ያልሰገዱትንና ክርስቶስን በማመን የጸኑትን ሁሉ በዓለም ላይ ያሉ ከ470 ሺህ በላይ ክርስቲያኖችን በግፍ በሰማዕትነት አስገደለ፡፡ ቅድስት ዴሚያናም ከ40 ቅዱሳት ደናግል ጋር በምናኔ ላይ ሳለች ነው ከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በሰይጣን ታግዞ ወደ ንግሥናው ሥልጣን የመጣው፡፡ ዲዮቅልጥያኖስም በእርሱ ሹመት በግብጽ ሁለት ግዛቶችን ያስተዳድር የነበረውን የቅድስት ዴሚያናን አባት ማርቆስን ወደ አንጾኪያ አስጠርቶ አመጣውና ለጣዖታቱ እንዲሰግድ አዘዘው፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፲፩ (11) ቀን።
✝ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካችን #ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ_ለብርሃነ_ጥምቀቱ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከፋርስ አገር ሰዎች ወገን ከሆነ #ከከበረ_ቅዱስ_እንጣልዮስ በሰማዕትነት ከዐረፈ፣ #ከከበሩ_አዮስጦስና_ከፋይዮስ ዕረፍት፣ ከከበረ ተጋዳይ #ከአባ_ወቅሪስ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ በዚች ቀን #የክብር_ባለቤት_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከአጥማቂው_ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘንድ_በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ተጠመቀ። ይችም ዕለት በዮናኒ ቋንቋ ኤጲፋንያ ትባላለች ትርጓሜውም መለኮት የተገለጠበት ማለት ነው ልዩ የሆነች የሦስትነቱ ምሥጢር ገልጦባታልና አብ ከሰማይ ሁኖ የምወደው በርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት እያለ ሲመሰክር ወልድም በዮርዳኖስ ወንዝ ቁሞ ሳለ መንፈስ ቅዱስም በነጭ ርግብ አምሳል በወልድ ራስ ላይ ሲቀመጥ ይህ አጥማቂው ዮሐንስ እንደመሰከረ። እንዳህ ሲል "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ ከውኃ በወጣ ጊዜ ወዲያኑ ሰማይ ተከፈተ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በጌታችን ራስ ላይ ተቀምጠ ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ "ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ነው እርሱንም ስሙት"።
✝ በዚች ዕለት ጌታችን ራሱን ገልጦአልና ከዚህ በፊት ሠላሳ ዓመት ያህል ራሱን አልገለጠም ነበር ግን በዚች ዕለት ለእስራኤል ልጆች ራሱን ገለጠ እነሆ "የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ" ብሎ መጥምቁ ዮሐንስ እንደገለጠው የከበረ ወንጌል ምስክር ሆነ። "እኔ አላውቅውም ነበር ነገር ግን እስራኤል ያውቁት ዘንድ በውኃ ላጠምቅ ስለዚህ መጣሁ" አለ።
✝ በዚህም በዓል የእግዚአብሔር ልጅ የክርስቶስ የጌትነቱ ክብር ተገልጧል እርሱም የዓለሙን ሁሉ ኃጢአት ለማስወገድ የሚሠዋ የእግዚአብሔር አማናዊ በግ ነው። ስለዚህም ይህ በዓል በክርስቲያን ወገኖች ሁሉ ዘንድ የከበረና ከፍ ከፍ ያለ ሆነ በርሱም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ በአበረው ውኃ ይነጹበታል የተቀበሉትንም ንጹሕና ጠብቀው ቢኖሩ በውስጡ የኃጢአታቸውን ሥርየት ያገኛሉ።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ውድ የፍኖተ ብርሀን ቤተሰቦች :-
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በአለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ።
የግራር ደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የከተራ በአል በእግዚአብሔር ረዳትነት በዚህ መልኩ በምስጋና አልፏል።
📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸ከሚዲያና ዕቅበተ እምነት ክፍል የምስል ማህደር በጥቂቱ ይህን ይመስላል
📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽
🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፲ (10) ቀን።
✝ እንኳን #ለገሀድ (ጋድ) ጾመ፣ #ለከተራ_በዓልና #ለአባ_ታውብንጦ ለዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ #ከሰማዕት_ከጠምያኒ_ከኪናርያና #ከንግሥት_በጥሪቃ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #በዚች_ዕለት_ምንም_ምን_መብልን_ሳይቀምሱ #ምእመናን_ሁሉ_እስከ_ምሽት_ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ። በዚች ዕለት ምእመናን እስከ ምሽት እንደመጾሙን ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና።
✝ እኛ በዚህ በኅላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው። እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው።
✝ በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥራ ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾም ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ።
✝ በጥምቀትም ዕለት ከእኵለ ሌሊት በፊት ተነሥተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቊርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ።
✝ የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሑድ ቀን ቢሆን በሦስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነው በየሰዓቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያች ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዐሥር ነው በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም። እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲአክብሩ አዘዋል ይኸውም መድኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህ ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው።
✝ መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዓርብም ረብዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥተው ይበላሉና። እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮርዳኖስም ወንዝ እንደ ተገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
✝ #አባ_ታውብንጦስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ አባ ታኡና በሚባል በሮሜው ሊቀ ጳጳሳት ቤት አደገ እርሱም የምንኵስናን ልብስ አለበሰው። መንፈሳዊ ዕውቀትና ኃይል እንደተሰጠው አይቶ ከእስክንድርያ አገር ውጭ ስሙ ጤናዲራን በሚባል ቦታ ኤጲስቆጶስነት ሹሞ የገዳም አበ ምኔት አደረገው ከእርሱ ሥር ያሉ መነኰሳትም ሰባት መቶ ናቸው።
✝ ከዚህም በኋላ ከእርሱ ጋር ላሉ መነኰሳት አለቃ የሆነ ኤጲስቆጶስ ታውብንጦስ ከከሀዲ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ስለሆነው ሁከት በሰማ ጊዜ ሸሽቶ ወደ ደብረ ሲሐት ገዳም ሒዶ እግዚአብሔርን ከምትፈራ ከአንዲት ድንግል ዘንድ ተቀመጠ። በእርሷ ቤትም ብዙ ዘመናት ኖረ በመጀመሪያ ወደርሷ በገባ ጊዜ ግን ንጉሡን ስለ መፍራት ጣዖትን ስታመልክ አገኛትና የክብር ባለቤት ጌታችን ክርስቶስን ወደ ማመን መለሳት።
✝ ከዚያም ተርኑጥና መርኑስ ወደ ሚባሉ ገዳማት ሔደ የአብያተ ክርስቲያናትን ወሬ ይሰማ ዘንድ ፈልጎ በጾም በጸሎት ሌሊትም በመትጋት እያገለገለ በአንዲት ገዳም ውስጥ ሁለት ሦስት ቀን ተሠውሮ ያድር ነበር። የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ በላዩ እንዳደረ እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆች ተአምራቶችን እንዳደረገ ከወንበዴዎችና ከዓመፀኞች ብዙዎችን መነኰሳትን አድርጎ ለክርስቶስ ወደ መገዛት እስከ መላሳቸው ድረስ መነኰሳቱ ሁሉ መሰከሩለት።
✝ ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ የሚሞትበትን ቀን ዐወቀ ልጆቹንም የክርስቶስ በሆነች በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ አስተማራቸው ወዲያውኑ ጥር10 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ታውብጦስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር10 ስንክሳር።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፱ (9) ቀን።
✝ እንኳን ለከበሩ አባት ጌታችን በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጦ በቤታቸው ጣራ ለገባላቸው #ለአባ_አብርሃም_ግብፃዊ ዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ አባቶች #ከአባ_ጊዮርጊስ_ከአባ_ኖስሞስና ከሮሜ ሰው #ዲዮስቅርስ ዕረፍት፣ #ከአባ_ኪናፎርያ_ከበጥሪቃና_ከጥምያኒ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #አባ_አብርሃም፦ የዚህም ቅዱስ ሰው አባቱ ድኆችን የሚወዳቸውና የሚራራላቸው ነው። በዘመኑም በግብጽ አገር ታላቅ ረሀብ ሆነ እጅግ ባለጸጋ ነበርና ከደግነቱና ከታማኝነቱ ብዛት የተነሣ እርሱ በአለበት አገር ዙሪያ ያሉ አገሮች ሁሉም የምድራቸው ፍሬ በእርሱ ዘንድ አደራ ያስቀምጡ ነበር ረሀቡም በጸና ጊዜ በእርሱ ዘንድ በአደራ የተቀመጠውን እህል ሁሉንም ለድኆች ሰጠ እግዚአብሔርም ስለ ምድራቸው ፍሬ ሁሉንም ክፉ ቃልን እንዳይናገሩት አደረጋቸው። በእርሱ ዘንድ ያኖሩትን የምድራቸውን ፍሬ ሽተው ወደርሱ በሚልኩ ጊዜ ተነሥቶ ወደርሳቸው ይሔዳል እነርሱም በየራሳቸው ለያንዳንዱ የምድራቸው ፍሬ እንደደረሳቸው አድርገው ይጽፉለታል እንጂ ምንም ምን አይናገሩትም።
✝ የዚህም ቅዱስ እናት እግዚአብሔርን የምትፈራ ምእመን ናት ሰይጣንም ቀናባት በአንድ ክፉ ሰው ልቡና አድሮ በፋርስ ሰዎች ዘንድ ነገር ሠራባት እነርሱም ማርከው ወደ አገራቸው ወሰድዋት በአንዲት ሌሊትም ራዕይን አየች ያ ነገር የሠራባት ሰው በሲኦል ውስጥ በእሳት ሰንሰለት ታሥሮ "እግዚአብሔር ያደረገልሽን ተመለከትሽን ነገር የሠራብሽን ያንን ሰው ተበቅሎታልና" ይላታል እርሷ ግን "ጌታዬ ሆይ መከራና ሥቃይ በርሱ ላይ እንዲደርስ አልሻም" ትላለች ያ የሚያሳያትም "አንቺ ግን ወደ አገርሽ ተመልሰሽ በቤትሽ ትኖሪ ዘንድ አለሽ" ይላታል እንዲሁም ሆነ።
✝ ባሏም በሞተ ጊዜ አብርሃም ድኃ አደግ ሆነ እርሷም እናቱ ሚስት ልታጋባው አሰበች እርሱ ግን ይህን አልወደደም እናቱም እጅግ ደስ ተሰኘችበት። ወደ ገዳም ሒዶ ሊመነኵስ በፈለገ ጊዜ እናቱ ልትሸኘው ወጣች እጆቿንም ወደ ሰማይ አንሥታ በመጸለይ ልጇን ወደ እግዚአብሔር አደራ አስጠበቀች። "አቤቱ ጌታዬ ይህን ቊርባንን አድርገህ ተቀበለኝ" አለች።
✝ በዚያንም ጊዜ አባ አብርሃም ሔደ በአስቄጥስ በረሀ ውስጥ ተጒዞ በአባ ዮሐንስ አበ ምኔትነት ዘመን ወደ አባ መቃርስ ገዳም ደረሰ ወደርሱም ወደ አባ ዮሐንስ ገባ ተወዳጅ ልጅንም ሆነለት። በጎ ተጋድሎንም ጀመረ በአንዲት ሌሊትም ራዕይን አየ የበዓቱ ጣሪያ ተሰነጠቀ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጦ ወደርሱ ሲወርድ አየው ኪሩቤልም ያመሰግኑት ነበር እርሱም ፈርቶ ተንቀጠቀጠ ፈጥኖም ሰገደ ጌታችንም ባረከውና በታላቅ ክብር ወደ ሰማይ ዐረገ። ጌታችንም የወረደባት በቤቱ ጣሪያ የተሠነጠቀችው ምልክት ሁና እስከ ዛሬ በመታሰቢያነት አለች እርሷም ለመንፈሳዊ አባቱ ለአበ ምኔቱ አባ ዮሐንስ መኖሪያ ቅርብ ናት እርሷም በግቢግ ትባላለች። የእግዚአብሔርም መልአክ ሁል ጊዜ ይጐበኘዋል ብዙ ምሥጢራትንም ይገልጥለታል ያስገነዝበዋልም።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፰ (8) ቀን።
✝ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቀ_ነቢያት አንዱ ለሆነው #ለቅዱስ_ሚክያስ ለመታሰቢያ በዓል፣ #የአባ_መቃርስ_ቤተ_ክርስቲያን በከበረና በተመሰገነ በእስክድርያው ሊቀ ጳጳሳት #በአባ_ብንያሚን እጅ ለከበረችበትና ለእስክድርያ ሠላሳ ስምንተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ብንያሚን_ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ ፦ከእስክንድርያ ሠላሳ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_እንድራኒቆስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #ነቢዩ_ቅዱስ_ሚክያስ፦ የዚህም ነቢይ ከታናሽነቱ ጀምሮ አካሔዱ መልካም ሆነ ስለ ሥራው ማማርና ስለ ጽድቁ ሕዝቡ ሁሉ ያደንቁታል ያከበሩታል ሚክያስም ይሉታል ትርጓሜውም መልአክ ነው ማለት መልኩ እጅግ ያማረ ነውና የሚናገረውም ትንቢት እንደተናገረው ይሆናል የእግዚአብሔር መልአክም ተገልጾለት ያነጋገረው ነበር ሕዝቡ ግን ያንን መልአክ እያዩትም ድምፁን ግን ይሰማሉ ከእርሳቸውም ያደላቸው የሚያዩት አሉ በመሳፍንት መጽሐፍ እንደተጻፈ። በጎልማሳነቱም አርፎ በአባቶቹ ቦታ ተቀበረ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና እኛን በነቢዩ ቅዱስ ሚክያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ይሁን አሜን።
✝ ✝ ✝
✝ #የአባ_መቃርስ_ቤተ_ክርስቲያን_በአባ_ብንያሚን_እጅ_መክበር፦ ከዚህም በኋላ መቆቅዝ ከሚባል ዐላዊ መለካዊ በአባ ብንያሚን ላይ መከራ ደረሰበት አባ ቢንያሚንም ሸሽቶ ወደ ላይኛው ግብጽ ሔደ ዐሥር ዓመትም እስኪፈጸም በዚያ ኖረ ከዚህም በኋላ ያን ዓላዊ መቆቅዝን እግዚአብሔር አጠፋው ለአብያተ ክርስቲያን ሁሉ ጸጥታ ሰላም ሁኖ አባ ቢንያሚንም ወደ መንበረ ሢመቱ ተመለሰ የአስቆጥስ ገዳም ሽማግሎችና መምህራን ወደርሱ መጡ ወደርሳቸውም ሒዶ አዲስ ቤተ ክርስቲያን እንዲአከብርላቸው ለመኑት እርሷም የከበረ የአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ናት። በታላቅ ደስታም ተነሥቶ ከእርሳቸው ጋር ሔደ የቤተ ክርስቲያኒቱንም መባረኪያ ጸሎት ጀመረ።
✝ መሠዊያውንም በሜሮን ሊቀባ በጀመረ ጊዜ የክብር ባለቤት የጌታችን እጅ ከእርሱ ጋር ስትቀባ አየ ከታላቅ ፍርሀት የተነሣ በግምባሩ ፍግም ብሎ ወደቀ። ከኪሩቤልም አንዱ አነሣው እንዲህም አለው "ተነሣ አትፍራ ልዩ የሆነውን ሥርዓት ለዚህ ቦታ ጻፍ ይህ የእግዚአብሔር ምሥጢር የሚፈጸምበት ነውና ማንም በትዕቢት ወይም መማለጃ በመስጠት እንዳይገባ በውስጡ በሚገባ ከሚሾም በቀር የሚደፍርና በውስጡ ከንቱ ነገርን የሚናገር አይኑር የእግዚአብሔር መመስገኛ ቤቱ ነውና ይህም ሥርዓት በዚህ ቦታ እስከ ዘላለሙ የተሠራ ይሆናል። እነሆ ዘመን ይመጣል የአባቶችንም ትእዛዝና ሥርዓት ያፈርሳሉ ይህም የከበረ ቦታ እንደ መሣለቂያ ቦታ ይሆናል"።
✝ አባ ብንያሚንም "ይህች የእግዚአብሔር ቤት የሰማይ ደጅ ናት" አለ ይህንንም ከኪሩብ ጋር ሲነናገር ከቤተ ክርስቲያኒቱ በስተምሥራቅ ተመለከተ አንድ መልኩ የሚያምር ጽሕሙ የረዘመ ፊቱም እንደ መልአክ ፊት የሚያበራ ሽማግሌ አየ። ለአባ ብንያሚንም ደስ አሰኘውና በልቡ እንዲህ አለ "ከኤጲሰሰቆጶሳት አንዱ ቢሞት በርሱ ፈንታ ይህን ሽማግሌ እሾመዋለሁ"። ኪሩብም እንዲህ አለው "ብንያሚን ሆይ ይህን አባት መቃርዮስን ኤጲስቆጵስን ታደርገዋለህ?"። እርሱ "የሊቃነ ጳጳሳት አባታቸው ነውና ዛሬ ከልጆቹ ጋር ደስ ይለው ዘንድ መጥቷልና ከልጆቹም መንፈሳዊ ሹመት የሚሾም ወይም አለቃ የሚሆን አይታጣም ከገዳማቱም የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ አይታጣም"።
✝ አባ ብንያሚንም "ልጆቹ ብፁዓን ናቸው" አለ ኪሩብም እንዲህ አለ "ብፁዓንስ የሚባሉ ትእዛዞቹን ጠብቀው ፍለጋውን ቢከተሉ እነርሱ ከእርሱ ጋር አሁን በአለበት ክብር ውስጥ ይሆናሉ ትእዛዞቹን ቢተላለፋ ግን ከእርሱ ጋር ዕድል ፈንታ አይኖራቸውም"። አባ ብንያሚንም ኪሩብን እንዲህ አለው "ጌታዬ ሆይ በዚህ ነገር በልጆቼ ላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር አትናገር ነገር ግን በሰብል ውስጥ አንዲት ቅንጣት የተረፈች እንደሆነ እግዚአብሔር በውስጥዋ በረከቱን ያደርጋል። እንዲሁም የፍቅር ቅንጣት በውስጣቸው የተገኘ እንደሆነ እግዚአብሔር ከመንግሥቱ እንደማያርቃቸው እኔ አምናለሁ"።
✝ ከአረጋዊው አባ መቃርስ ርኅራኄ የተነሣ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን አደነቀ መልአኩ ኪሩብ እንዳዘዘውም ያንን ሥርዓት ጽፎ ለዘወትር መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖረው። ዕድሜው በደረሰ ጊዜ ዕረፍቱ በዚች ቀን ይሆን ዘንድ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው እንዲሁም ሆነለት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ቢንያሚን በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
✝ #አባ_እንድራኒቆስ፡- ይኽም አባት ለእስክንድርያ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሰባተኛ የሆነ ነው። ይህ አባት የሚራራ አዋቂ ሆነ እርሱ የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ተምሮአልና እርሱም ለእስክንድር ገዥ የአጎቱ ልጅ ነውና ከእርሱ በፊት የነበሩት ሊቃነጳጳሳት እንደሚያደርጉት በገዳም አልኖረም፤ ይልቁንም ስለቤቱና ስለክብሩ ታላቅነት በእስክንድርያ ባለው ቤቱ የሚኖር ሆነ፡፡ እርሱም የተሾመው ሕርቃል በነገሠ በ10 ዓመት ከእስክንድር ዘመነ መንግሥት በ933 ዓመት ነው፡፡ በሹመቱም ወራት ፀሐይን የሚያመልክ የፋርስ ንጉሥ ክስራ ተነሣና የሶርያንና የፍልስጤምን ከተሞች ወርሮ ዘረፋቸው፡፡ ወደ ግብጽም መጥቶ እስክንድድርያ ከተማ ደረሰ፡፡ በዙሪዋ በመነኮሳት የተሞሉ ሰባት መቶ ገዳማት ነበሩ፡፡ እነርሱም ገንዘብ ያላቸው በተድላ የሚኖሩ ነበሩ፡፡ ስለዚህም በእነርሱ ላይ እግዚአብሔር ሥልጣንን ሰጥቶት ገዳማቱን አፈረሰ፡፡ እነርሱንም ሸሽተው ካመለጡት በቀር ሁሉንም ገደላቸው፡፡ ገንዘባቸውንም ሁሉ ማረከ፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፯ (7) ቀን።
✝ እንኳን #ለአጋዕዝተ_ዓለም_ለቅድስት_ሥላሴ የሰናዖር (የባቢሎንን) ቋንቋቸው ለደባለቁበትና የሠሩት ግንብ ላፈረሱበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል (ታሪኩ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ዘፍ11፥1-9)፣ ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን የክርስትና ጥምቀት ላጠመቀው ለሮሜ አገር ሊቀ ጳጳስ ለከበረ አባት #ለአቡነ_ሶል_ጴጥሮስ ለዕረፍት በዓልና ለታላቁ አባት #ለቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ ለመታሰቢያው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሰሎሞን፣ #ከጎርጎርዮስ_ከማርቆስ_ከአትያኖስ_ከሉያ፣ #ከመልይን_ከሱስዮስና_ከማርትይ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #የሮሜ_አገር_ሊቀ_ጳጳስ_አባ_ሶል_ጴጥሮስ፦ ይህንንም አባት ስለ ተጋድሎው ገናናነት ስለ አገልግሎቱም ስለ ትሩፋቱ ስለ አዋቂነቱና ስለ ደግነቱ ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ መልጥያኖስ ከዐረፈ በኋላ መርጠው ሊቀ ጵጵስና በሮሜ አገር ላይ ሾሙት። በሐዋርያት አለቃ በጴጥሮስ ወንበር በተቀመጠ ጊዜ የዕሊኒ ልጅ የሆነ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው ከከሀድያን ጋር ስለሚያደርገው ጦርነት ምክንያት ገና አልተጠመቀም ነበርና የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሶ የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ሠራላቸው።
✝ የዚህም አባት ሶል ጴጥሮስ ገድሉ እጅግ ብሩህ የሆነ ነው እርሱ ሁል ጊዜ ሕዝቡን ያስተምራቸዋልና ከልቡናቸውም ከሰይጣን የሆነ ጥርጥርንና ክፉ ሐሳብን ያርቃል። ከእነርሳቸው ሥውር የሆነውንም የመጻሕፍት ምሥጢር ተርጒሞ ያስገነዘባቸው። አይሁድንና ዮናናውያንን ሁል ጊዜ ይከራከራቸው ነበር ከእርሳቸውም ብዙዎችን መልሶ ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ስሙም በምእመናን ዘንድ ፈጽሞ የሚያስፈራ ሆነ። እግዚአብሔርን ስለ ማወቅና ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ብዙ ድርሳናትን ደረሰ።
✝ በተሾመ በሰባተኛውም ዓመት ስለ አርዮስ በኒቅያ ከተማ ሃይማኖታቸው የቀና የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት የከበሩ አባቶች የአንድነት ስብሰባ ሆነ ይህም አባት ሶል ጴጥሮስ ከእርሳቸው አንዱ ነበር አርዮስንም ከተከታዮቹ ጋር ረገመው አውግዞም ለየው። በሹመቱም ዐሥራ አንድ ዓመት ኖረ መልካም ተጋድሎን ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ጥር7 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሶል ጴጥሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር7 ስንክሳር።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፮ (6) ቀን።
✝ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ_ለንዑስ_በዓል ለአንዱ #ለግዝረት_ለኢየሱስ ዓመታዊ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ በዚች ቀን #የክብር_ባለቤት_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ #በሥጋው_ወደ_ቤተ_ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጸመ ልሳነ ዕረፍት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ" ብሎ እንደተናገረ። ለብዙዎችም ጌታችን ወደ ቤተ ግዝረት እንዳልገባና እንዳልተገረዘ ይመስላቸው ነበር እነርሱ እንዳሰቡት ሁኖ ቢሆን ኑሮ አይሁድ ታላቅ ምክንያትን የሚያገኙ በሆኑ ነበር ጌታችን ግን ግዝረትን ሕግ ፈጸመ ለእኛ በግዝረት ፈንታ የክርስትና ጥምቀትን ሰጠን የፋሲካውንም ቂጣ በላ በእርሱም ፈንታ ሥጋውንና ደሙን ሰጠን።
✝ የከበረ ወንጌል "ስምንተኛው ቀን በተፈጸመ ጊዜም ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት ሳትፀንሰው መልአኩ እንዳወጣለት ስሙን ኢየሱስ አሉት" እንዳለ ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ጻድቅ አረጋዊ ዮሴፍን "እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙንም እንድንሰይመው ብልህ የሆነ ገራዥ ሰው አምጣልኝ" አለችው። ዮሴፍም ሔዶ የሚገርዝ ባለሙያ አመጣ ያ ባለሙያም ሕፃኑን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ በእናቱ በንጽሕት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ አየው "እንድገርዘው ሕፃኑን በጥንቃቆ ያዙት" አላቸው። ሕፃን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መልሶ እንዲህ አለው "ባለሙያ ገራዥ ሆይ ደሜ ሳይፈስ ትገርዘኝ ዘንድ ትችላለህን በዚያች ዕለት ካልሆነ በቀር ደሜ አይፈስምና ጐኔን በጦር ሲወጉኝ ያን ጊዜ ውኃና ደም ይፈሳል ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆች መድኃኒት ይሆናል"።
✝ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ያ ባለሙያ በሰማ ጊዜ አደነቀ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሥቶ ከሕፃኑ ጌታ እግር በታች ሰገደ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጆቹ ላይ ቀልጠው እንደ ውኃ ሆኑ የከበረች ድንግል እመቤታችን ማርያም "ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው ይህ ልጅሽ ስለርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው" አላት።
✝ ሕፃኑም ለዚያ ባለሙያ ዳግመኛ መልሶ እንዲህ አለው "እኔ ነኝ ትገዝረኛለህ ወይስ ተውክ ወይም ያባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ እኔ ላድርግ" ያም ባለሙያ "የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው?" አለው ሕፃን ጌታችንም "አብርሃም፣ይስሐቅ ያዕቆብ የሕዝቡ ሁሉ አባቶች የሆኑ ናቸው ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው" ባለሙያውም "እኔ ከአንተ ጋር እናገር ዘንድ አልችልም በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና" አለው። በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ "አባት ሆይ ለአብርሃም፣ለይስሐቅ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ" አለ። ያን ጊዜ ያለ ሰው እጅ በሕፃኑ ሥጋ ላይ ግዝረት ተገለጠች።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ዓመታዊ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ብቸኛ በሆነው በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ።
ጥር 4/ 2016 ዓ.ም (ፍ.ብ.ሚ./አዲስ አበባ)
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፭ (5) ቀን።
✝ እንኳን #ለታላቁ_አባት_ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ልደታቸው አስመልክቶ (ሳሪስ አቦ፣ፈረሳይ አቦ) የለውጥ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ #ስለ_አባታች_አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ልደት፦ ትውልድ አገራቸው ደቡባዊ ግብፅ ከቆላው ልዩ ስሙ ከንሒሳ አካባቢ ነው፡፡ አባታቸው ስም ቅዱስ ስምዖን እናታቸው ስም ቅድስት አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ወላጆቻቸው በእግዚአብሔር ፊት ደጋጎች የነበሩ ቢሆኑም አቅሌስያ መካን ሆና ልጅ በማጣቷ እያለቀሰች 30 ዘመን ኖራለች፡፡
✝ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሥዕል ካለበት ፊት ለፊት በመቆም እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣት ዘንድ አልቅሳ ስትለምን ያንጊዜ ከሥዕሉ ቃል ወጥቶ "ክቡሩ ከሰማይ ከምድር ከፍ ከፍ የሚል፣ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር በክብር የሚተካከል ክህነቱ እንደ መልከ ጼዴቅ ንጽሕናው እንደ እንደ ነቢይ ኤልያስ፣ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ የሆነ በክብር ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር የሚተካከል ልጅ ትወልጃለሽ" አሏት። ይኸውም ለአንቺ ብቻ አይደለም ለዓለሙ ሁሉ ነው እንጂ። ያን ጊዜ ከሦስቱ አንዱ ተነሥቶ በእጁ ባርኮ በሰላም ወደ ቤትሽ ግቢ አሏት"። እርሷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ገባች፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥር ፬ (4) ቀን።
✝ እንኳን #ለከበረና_ለተመሰገነ ለታላቁ #ለወንጌላዊው_ለአቡቀለምሲስ_ለቦኤኔርጌስ፣ #ለታኦሎጎስ_ለድንግላዊው_ለቊጹረ_ገጽ፣ #ለፍቊረ_እግዚእ_ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ_ለፍልሰቱ (ከሞት ለተሰወረበት) ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦# ከከበረ_ከጊዮርጊስ ከሊቀ ጳጳሳት #ከማርቴና_ከሰማዕት_ታኦድራ_ከአባ_ሊቃኖስና #ቀውስጦስ_ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #ወንጌላዊው_ቅዱስ_ዮሐንስ፦ ለዚህም ቅዱስ ወደ እስያ አገር ይሔድ ዘንድ ዕጣው በወጣ ጊዜ እጅግ አዝኖ አለቀስ እነርሱ ክፉዎች ከሀዲዎች ልባቸው የደነደነ መሆናቸውን አውቋልና ግን ጌታችን ኃይልን መጽናናትን አግኝቶ ከደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስ ጋር ወጥቶ ወደ ክፍሉ ሔደ። ወደ ኤፌሶንም ሊሔድ ወዶ በመርከብ ላይ ተሳፈረ መርከቡም ተሰበረ እየአንዳንዱ በመርከብ ስባሪ ሠሌዳ ላይ ተንጠለጠለ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስንም የባሕሩ ማዕበል ወደአንዲት ደሴት አደረው ቅዱስ ዮሐንስ ግን በባሕሩ ማዕበል መካከል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ኖረ።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
