ar
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

الذهاب إلى القناة على Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

إظهار المزيد
603
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-87 أيام
-1630 أيام
أرشيف المشاركات
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝ ✝ ጥር ፳፩ 21 ቀን። ✝ እንኳን አምላክን ለወለደች ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም ለዕረፍቷ በዓል (ለአስተርእዮ ማርያም)
+1
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ✝             ✝ ጥር ፳፩ 21 ቀን። ✝ እንኳን አምላክን ለወለደች ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም ለዕረፍቷ በዓል (ለአስተርእዮ ማርያም)፣ ለኑሲስ ኤጲስቆጶስ ለቅዱስ ባስልዮስ ወንድም ለከበረ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ዕረፍት በዓልና ለሮሜ አገር ንጉሥ ለዘይኑን ልጅ ለከበረች ለቅድስት ኢላርያ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ እመቤታችንንም ከመጥቁ ዮሐንስ ጋር በደብረ ማሕው ከተገለጠችበት፣ ከነቢዩ ከቅዱስ ኤርምያስ፣ ከዮሐንስና ከአባ እስክንድር፣ በዋሻ ከቅዱስ ኒቆላዎስና ከኤጲስቆጶስ ከአባ ፊቅጦር ከሁሉም ከመታሰቢያቸው፣ በናፍቁ ንጉሥ በመርቅያን ዘመን በሰማዕትነት ከዐረፉ ከቅዱሳን ጳውሎስና ከቀሲስ ሲላስ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                               ✝ ✝ ✝ ✝ የዕለቱ አንገርጋ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ኢኮነ ነግደ ወፈላሴ ሀገሪቶሙ ለቅዱሳን ንሕነ ሰብአ ቤቱ ለእግዚአብሔር ኲልነ አምላክ ኀደረ ውስተ ሥጋ ተዓቊረ እንዘ ኢይትጋባዕ በሙላድ ዘድንግል መናሥግተ እያርኂዎ ዘኪሩቤል ኢርእዮ"።  √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝ ✝ ጥር ፳ (20) ቀን። ✝ እንኳን ጌታችን ወንጌልን ይሰብኩ ዘንድ በሽተኞችንም ይፈውሱ ዘንድ መርጦ ወደ ዓለም ከላካቸው ቁጥሩ ከሰብዓ ሁለ
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ✝             ✝ ጥር ፳ (20) ቀን። ✝ እንኳን ጌታችን ወንጌልን ይሰብኩ ዘንድ በሽተኞችንም ይፈውሱ ዘንድ መርጦ ወደ ዓለም ከላካቸው ቁጥሩ ከሰብዓ ሁለቱ አርድእትና ከሰባቱ ዲያቆናት ለሆነ ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊው ደቀ መዝሙር ለሐዋርያው ለቅዱስ አብሮኮሮስ ለዕረፍት በዓል፣ ልጁን በስምህ የሚሰይመውን ሁሉ እኔ እባርከዋለሁ ብሎ ጌታችን ቃል ኪዳን ለገባለት በግብጽ አገር እልፈንት ከሚባል ከተማ ለከበረ ቀሲስ ለቅዱስ አክሎግ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለታላቁ ሰማዕት ለመምህናም ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበትና ተአምራቱ ለተገለጠበት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕቱ ቅዱስ ብሕኑ ከመታሰቢያው፣ ከወንጌሉ ዘወርቅ ከቅዱስ ዮሐንስም ቤተ ክርስቲያኑ ከከበረችበትና ሥጋው ወደ ሮሜ ከፈለሰችበት፣ ከአባ ኖኅ፣ ከአባ ስልዎኖስና ከአባ አብድዩ ከመታሰቢያቸው ረድኤት በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝ ✝ #ጥር ፲፱ (19) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_መድኃኒነ_እግዚእ ካመነኰሷቸው ከሳባቱ ከዋክብት አንዱ ለሆኑት ለታላቁ አ
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ✝            ✝ #ጥር  ፲፱ (19) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_መድኃኒነ_እግዚእ ካመነኰሷቸው ከሳባቱ ከዋክብት አንዱ ለሆኑት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_አፍቅረነ_እግዚእ_ዘጉጉቤን ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                                           ✝ ✝ ✝ ✝ #አቡነ_አፍቅረነ_እግዚእ_ዘጉጉቤን፦ እኚህ ጻድቅ እጅግ ከከበሩት ከሳባቱ ከዋክብት የአገራችንን ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው። ትውልዳቸው ትግራይ አክሱም ሲሆን አባታቸው ገብረ ኢየሱስ እናታቸው አፎምያ የተባሉ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው። ልደታቸው ሐምሌ19 ሲሆን ዕረፍታቸዉ ጥር19 ቀን ነዉ። በገዳማዊ ሕይወታቸዉ በእጅጉ ይታወቃሉ። በንጉሥ ዓምደ ጽዮን ዘመን የነበሩ ሲሆን ደራሲና ፈላስፋም ናቸው። ጻድቁ ደራ ፎገራ ውስጥ ባለ አራት ዓምድ አስደናቂ ገድል አላቸው። ደራ ፎገራ ተነስተው በጣና አድርገው ፈላሾችንና ቅማንቶችን በሚገባ በማስተማርና በማጥመቅ ብዙ ሐዋርያው አገልግሎት ፈጽመዋል፡፡ √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ✝ ✝ #ጥር ፲፰ (18) ቀን። ✝ እንኳን #ለፀሓየ_ልዳ_ለኮከበ_ፋርስ ለሰማዕታት አለቃ #ለቅዱስ_ጊዮርጊስ (ለዝርወተ ዐፅሙ) ዐፅሙ ተቃጠጥሎ
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ✝           ✝ #ጥር  ፲፰ (18) ቀን። ✝ እንኳን #ለፀሓየ_ልዳ_ለኮከበ_ፋርስ ለሰማዕታት አለቃ #ለቅዱስ_ጊዮርጊስ (ለዝርወተ ዐፅሙ) ዐፅሙ ተቃጠጥሎ ተደቁሶ በይድራስ ተራራ በነፋስ ከተበተነ በኋላ ከሞት ለተነሳበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና በገድል ለተጸመደ ለከበረ አባት #ለቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ_መምህሩ ቁጥሩ ከሠለስቱ ምዕት ለሆነ ለአገረ ንጺቢን ኤጲስቆጶስ #ለአባ_ያዕቆብ_ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአራት ቀኖች በኋላ ጌታች ከመቃብር ያነሳ  #ከአልዓዛር_እኅቶች_ከቅድስት_ማርያምና #ከቅድስት_ማርታ_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                       ✝ ✝ ✝ ✝ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ዝርወተ_አፅሙ፦ በዚች ቀን ሰባ ነገሥታት ማሰቃየት በሰለቻቸው ጊዜ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ መጭመቂያ ሆኖ ከተሠራ የስቃይ መሣሪያ ላይ አውጥተው ሰውነቱን እንዲሰነጥቁት ንጉሥ ዱድያኖስ አዘዘ፡፡   √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ✝              ✝ #ጥር ፲፯ (17) ቀን። ✝ እንኳን #ለለውንድዮስ_ለሮም__ንጉሥ_ልጅ ለሆኑ ለከበሩና ለተመሰገኑ ወድማማቾች #ለቅዱስ_ዱማቴዎስ ለዕረፍት በዓልና #ለቅዱስ_መክሲሞስ ለመታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። ከእነዚህ ሁለት ወድማማቾች ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                        ✝ ✝ ✝ ✝ #አባ_መክሲሞስና_አባ_ዱማቴዎስ፦ እነዚህም ቅዱሳን ለሮም ንጉሥ ለለውንድዮስ ልጆቹ ናቸው። ይህም ንጉሥ ሃይማኖቱ የቀና እግዚአብሔር የሚፈራ በእውነትም የቀና ፍርድን የሚፈርድ ነበር ስለዚህም እሊህን ሁለት ቅዱሳን እግዚአብሔር ሰጠው እነርሱም ከታናሽነታቸው ጀምሮ በንጽሕና እንደ እግዚአብሔር መላእክት ሆኑ። ✝ ትሕትናን ፈሪሀ እግዚአብሔርን በማስተማር አሳደጋቸው የሚጾሙና የሚጸልዩ በቀንና በሌሊትም የብሉይና የሐዲስ መጽሐፍቶችን የሚያነቡ ሆኑ። ከዚህም በኋላ ይህ ዓለም ይተውት ዘንድ የመላእክት ልብስ ይለብሱ ዘንድ እርሷም የከበረች የምንኵስና ልብስ ናት ከዚያም ሀሳብ መጣባቸው ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ አስራ ስምንት አባቶች ወደ ተሰበሰቡባት ወደ ኒቂያ ሔደው ይጸልዩ ዘንድ እንዲያሰናብታቸው ለአባታቸው ምክንያት አቀረቡ። ይህንም ከእርሷቸው በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው። ከብዙ አገልጋዮችና ከብዙ ሠራዊት ጋር አሰናበታቸው ከኒቅያ አገርም በደረሱ ጊዜ ከከበረ ቦታ በረከትን ተቀበሉ ሠራዊቱንም ወደ ንጉሥ አባታቸው ጌታችን ንጉሥ ሆይ "እኛ ከዚህ ጥቂት ቀን መቆየት እንሻለን" የሚል ጽሑፍ ጋር ጽፈው ላኩ። ✝ ከዚህም በኋላ ለአንድ ጻድቅ መነኰስ ኀባቸውን ገለጡ እንዲህም አሉት "ከአንተ ዘንድ የምንኵስናን ልብስ እንድንለብስ እንሻለን" እርሱም "እኔ ከንጉሥ አባታችን የተነሣ እፈራለሁ ነገር ግን ወደ ሶርያ ሒዱ ስሙ አጋብዮስ የሚባል ከዚያ ሃይማኖቱ የቀና ካህን ደግ መነኰስ አለ" አላቸው ይህንንም ሲላቸው ምክሩን ተቀብለው ወደ ሶርያ ተጒዘው ወደ ቅዱስ አባ አጋብዮስ ደርሰው ኀሳባቸውን ገለጡለት እርሱም ተቀብሎ የምንኵስና ልብስን አለበሳቸው እስከሚአርፍበት ቀን ከእርሱ ዘንድ ኖሩ። ከዕረፍቱም አስቀድሞ ያየውን ራእይ ነገራቸው ታላቁ አባ መቃርስ ወደርሱ እንደመጣና "ልጆችህ መክሲሞስና ዱማቴዎስ ለኔ ልጆቼ ይሁኑኝ ዘንድ ወደ እኔ ወደ አስቄጥስ ገዳም እንዲመጡ ከመሞቴ በፊት እዘዛቸው" አለው። ዳግመኛም እንዲህ አላቸው ልጆቹ "እኔ ይህን ሰው አባ መቃርስን በሥጋው አየው ዘንድ እመኝ ነበር እነሆ በመንፈስ አየሁት እናንተም ከሞትኩ በኋላ ወደርሱ ሒዱ"። ✝ ከዐረፈም በኋላ አልሔዱም በዚያ በሶርያ አገር ኖሩ እንጂ እግዚአብሔር ሀብተ ፈውስ ሰጥቷቸው በሽተኞችን የሚፈውሱ ሆነ ወሬያቸውም በአገሮች ሁሉ ተሰማ በባሕርና በየብስ ከሚነግዱ ነጋድያንም የመርከብ መዛነቢያዎችን መሥራት ተምረው ከድካም ወጋቸው በጥቂቱ የሚመገቡና የተረፈውን ለድኆችና ለችግረኞች የሚሰጡ ሆኑ። እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ከሚሠራቸው ድንቆች ተአምራቶች የተነሣ የቅዱሳን መክሲሞስና ዱማቴዎስን ስም መናፍስት ርኵሳን በማሰሚ ጊዜ ከሰዎች ወጥተው ይሸሻሉ ሰዎችም ያን ጊዜ በጌታ ኃይል ይድናሉ ጤነኞችም ይሆናሉ። እጅግ ታላቅ የሆነ በጐዳና አጠገብ የሚኖር ከይሲ ነበር ብዙዎች ሰዎችንም አጥፍቷል የአገር ሰዎችም ወደ ከበሩ መክሲሞስና ዱማቴዎስ መጥተው ከዚያ ከይሲ ያድኗቸው ዘንድ ለመኗቸው አባ መክሲሞስም ክርታስ አንሥቶ እንዲህ ብሎ ጻፈ "የብፁዕ መቃርዮስ አምላክ በሆነ መንፈስ ቅዱስንም በለበሰ በአባታችን በአጋብዮስ አምላክ ሕያው እግዚአብሔር አካላዊ ቃል በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደብዳቤ ከዋሻህ ደጅ ሲደርስ አንተ ወጥተህ ሙት የሰማይ ወፎችም ይብሉህ"። ✝ አንድ ሰውም ያቺን ደብዳቤ ተቀብሎ ሔደ በዚያም የዘንዶ ዋሻ ደጃፍ አኖራት በዚያንም ጊዜ ዘንዶው ወጥቶ ሞተ የሰማይ ወፎችም በሉት ሕዝቦችም ሁሉ እጅግ አደነቁ እግዚአብሔርም።እግዚአብሔርም በእነዚህ ሁለት ቅዱሳን እጆች ብዙ አስገራሚ ተአምራትን አደረገ፡፡ በአንዲትም ዕለት ከአባታቸው መኳንንቶች አንዱ ወደ ባሕር ዳርቻ ደረሰ፡፡ ከመርከቦችም በአንደኛው መርከብ ላይ መክሲሞስና ዱማቴዎስ የሚል ጽሑፍ ባየ ጊዜ የመርከቡን ሹም የጠቀው፡፡ የመርከቡ ሹምም "ማዕበል በተነሣ ጊዜ በጸሎታቸው ከመስጠም እግዚአብሔር እንዲያድነኝ የእነዚህን ሁለት ወንድማማቾች ቅዱሳን ስማቸውን በመርከቤ ላይ ጻፍኩ" አለው፡፡ መኰንኑም "መልካቸው ምን ይመስላል?" አለው፡፡ እርሱም የመልካቸውን ነገር ነገረው፡፡ መኮንኑም የንጉሡ ልጆች መሆናቸውን ዐውቆ ያንን ነጋዴ ወደ ንጉሡ ዘንድ ወሰደው፡፡ ንጉሡም የሁለቱን ቅዱሳን ነገር ነጋዴውን የጠቀው፡፡ እርሱም ስለ ቅዱሳኑ የሚያውቀውን ሁሉ የመልካቸውንም ነገር ነገረው፡፡ ንጉሡም ልጆቹ እንደሆኑ ተረዳ፡፡ ✝ ከዚህም በኋላ እናታቸውንና እኅታቸውን ወደ ልጆቹ ዘንድ ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከ፡፡ ደርሰው ባዩአቸውም ጊዜ ጮኸው አለቀሱ፡፡ እናታቸውም ቅዱሳኑን ወደ አባታቸው ዘንድ እንዲሄዱ ለመነቻቸው፡፡ ቅዱሳኑም "ራሳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፈን ሰጥተናልና ይህን ማድረግ አይቻለንም" አሏት፡፡ "ነገር ግን ወደ ቤተ መንግሥትሽ ተመለሺና ሂጂ፣ አንቺንም አባታችንንም እግዚአብሔር ከመከራ ሁሉ እንዲጠብቃችሁ እንጸልያለን" ብለው አረጋጓትና ሸኟት፡፡ እርሷም ወደ ንጉሡ ባሏ በደረሰች ጊዜ የሆነውን ነገረችው፡፡ እርሱም ለሚስቱና ለባለሟሎቹ ሁሉ "በዓለም ውስጥ ያለ ክብር ሁሉ እንደ ሕልም ኃላፊ ጠፊ ነውና ልጆቼ ግን የማያልፈውን መንግሥት መርጠዋልና ለእግዚአብሔር ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮቹ ይሆኑ ዘንድ እንተዋቸው፣ በጸሎታቸውም እኛን ይጠብቁናል" አላቸው፡፡ √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨√ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝               ✝ #ጥር ፲፭ (15) ቀን። ✝ እንኳን #ለከበረ_ሕፃን በሦስት ዓመቱ ተጋድሎውን ለፈጸመ #ለቅዱስ_ቂርቆስ_ለዕረፍቱ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ #ለቅዱስ_ቂርቆስ_ማኅበር_ለዐሥራ_አንድ_ሽህ_አራት_ሰዎች_ሰማዕትነት ለተበቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ለሐናንያ ልጅ ለዕውተኛ ነቢይ #ለቅዱስ_አብድዩ ለዕረፍት በዓል። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በሶርያ አገር ያሉ የክርስቲያን ወገኖች #ለቅዱስ_ጎርጎርዮስ የዕረፍቱን መታሰቢያ በዓል ከመያከብሩት፣ #ከጴጥሮስ_ከሶፍያ_ከአድምራና_ከይስሐቅ ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                            ✝ ✝ ✝ ✝# ሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስ፦ በዚያንም ወራት የክብር ባለቤት የሆነ ክርስቶስን በሚያምኑ የክርስቲያን ወገኖች ላይ ታላቅ መከራና ስደት ሆነ። ስሟ ኢየሉጣ የሚባል አንዲት ሴት ነበረች እርሷም ከታናሽነቷ ጀምራ ደግ ናት ስደትም እንደሆነ በሰማች ጊዜ መኰንኑን ከመፍራት የተነሣ ሕፃኗን ይዛ ከሮሜ ከተማ ተሰዳ የኪልቅያ አውራጃ ከሆነ ከጠርሴስ ደርሳ ከዚያም በአገሮች ውስጥ እየተዘዋወረች ተቀመጠች። ወደዚያች አገርም ያ ከእርሱ የሸሸችው መኰንን እለእስክድሮስ መጣ ጭፍሮቹም ክርስቲያኖችን ፈለጓቸው። ይቺንም ቅድስት ኢየሉጣን አግኝተው ያዝዋትና ወደ መኰንኑ አደረሷት የክርስቲያን ወገንም እንደሆነች ነገሩት። ✝ መኰንኑም "ሴትዮ ተናገሪ ከወዴት ሕዝብ ወገን ነሽ ነገድሽ ምንድን ነው አገርሽስ ወዴት ነው" አላት። የከበረች ኢየሉጣም እንዲህ ብላ መለሰችለት "የአንጌቤን ሰው ለሆንኩ ለእኔ ወገኖቼ ኤሳውሮሳውያን ናቸው እኔም በአንተ ምክንያት ሸሽቼ ነበር እነሆ ዛሬ ግን በእጅህ ውስጥ ነኝ" አለችው። መኰንኑም "በእጄ ውስጥ እንደተገኘሽ ታውቂያለሽን" አላት "አሁንም የሚሻልሽን ምረጪ ስምሽንም ተናገሪ እኔንም እሺ በይኝና ለአማልክት ሠዊ" የከበረች ኢየሉጣም አለችው "ለረከሱ አማልክት እኔ አልሠዋም" አለችው መኰንኑም "ስምሽን ስጪ ተናገሪ" አላት እርሷም "የኔ ስም ክርስቲያን መባል ነው" አለችው። መኰንኑም "ይህስ ስንፍና ነው የሚጠቅምሽ አይደለም እንዳትሞቺ ስምሽን ስጪ ተናገሪ" አላት። የከበረች ኢየሉጣም "የኔ ስም ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ ሞት የሚሽረው በሰዎች ዘንድ የምጠራበትን ከፈለግህ ስሜ ኢየሉጣ ነው" ብላ መለሰችለት። መኰንኑም "ጽኑ የሆኑ ሥቃዮችን በላይሽ ሳያመጡ ተነሥተሽ መሥዋዕትን ለአማልክት አቅርቢ" አላት። የከበረች ኢየሉጣም "ዕውነት ነገርን ለመሥራት የምትሻ ከሆነ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነ ሕፃን ልጅ ይፈልጉ ዘንድ ወደ አገሩ መንደር ላክ ወዳንተም ያምጡትና የምንገዛለትንና የምናመልከውን እርሱ ይነገረን" አለችው። ✝ ያን ጊዜም የሦስት ዓመት ልጅ ይፈልጉ ዘንድ መኰንኑ ወታደሮችን ላከ የአገር ሰዎችም ልጆቻቸውን ሠውረዋልና አላገኙም ከዚያም ከከተማው ቅጽር ውጭ በፀሐይ መውጫ ወዳለው በረሀ በኩል ወጡ የቅድስት ኢየሉጣንም ልጅ አገኙት ይህ ሕፃን "የስንት ዓመት ልጅ ነው" ብለው ስለርሱ ጠየቁ ሰዎችም "ይህ ሕፃን የሦስት ዓመት ሲሆን የክርስቲያናዊት መበለት ልጅ ነው" አሏቸው። ያንንም ሕፃን ይዘው ወደ መኰንኑ ወሰዱት መኰንኑም መልኩ የሚያምርና ደም ግባት ያለው እንደሆነ በአየ ጊዜ "ደስ የምትል ደስተኛ ሕፃን ሰላምታ ይገባሃል" አለው። ሕፃኑም "እኔን ደስተኛ ማለትህ መልካም ተናገርክ ላንተ ግን ደስታ የለህም እግዚአብሔር ለዝንጉዎች ደስታ የላቸውም ብሏልና ብሎ መለሰለት መኰንኑም ሕፃኑን "ሳልጠይቅህ ይህን ያህል ትመልስልኛለህን" አለው። ሕፃኑም "ገና ከዚህ የሚበዛ ነገርን እመልስልሃለሁ" አለው። ✝ መኰንኑም "ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ "ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውኃ የተገኘ ሕፃን ስሜ ክርስቲያን መባል ነው" ብሎ መለሰለት። መኰንኑም "ዳግመኛ እንዳትሞት ስምህን ንገረኝ" አለው የከበረ ሕፃንም "ስሜ ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ ሞክሼ ስም የምትሻ ከሆነ እናቴ የሰየመችኝ ቂርቆስ ነው" በማለት መለሰለት፡፡ መኰንኑም ሕፃን ቂርቆስን "እሺ በለኝና እሾምሃለሁ በብዙ ወርቅና ብርም አከብርሃለሁ" አለው። ሕፃኑም "የሰይጣ መልእክተኛ ለዕውነትም ጠላቷ የሆንክ ከእኔ ራቅ" አለው። መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ ደሙ እንደ ውኃ እስከሚፈስ ቆዳውን እንዲጨምቁትና እንዲግፉት አዘዘ። የከበረች ኢየሉጣሜ የልጅዋን ትዕግሥት በአየች ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነችው። ✝ ከዚህም በኋላ መኰንኑ "ጨውና ሰናፍጭ አምጡ አለ። የሁለቱንም አፍንጮቻቸውን ከፍተው ያንን ጨውና ሰናፍጭ እንዲጨምሩባቸው አዘዘ ያን ጊዜ ሕፃኑ "ትእዛዝህ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ሆነ ከማርና ከስኳርም ለአፌ ጣመኝ" ብሎ ጮኸ። ሁለተኛም መኰንኑ እንዲህ ብሎ አዘዘ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች አምጡ ሰባቱን በእናቱ አካላት ውስጥ ጨምሩ በሕፃኑም ሁለት ጆሮዎቹ ሁለት በዐይኖቹ ሁለት በአፉና በአፍንጫው አንድ በልቡ ጨምሩ እንዲህ ሲጨመርበት ጆሮዎቹ እንዲአሩ ዐይኖቹም ይጠፋ ዘንድ አንደበቱም ይቃጠል ዘንድ ወደ ልቡም ጽኑ ሕማም ገብቶ እርሱ ከዚህ ዓለም በሞት እንዲለይ ለእናቱም እንዲሁ አድርጉ ችንካሮችም በቅዱሳኑ በሥጋቸው ሁሉ ተጨመሩ። የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ትእዛዝ የብረቶቹ ግለት ጠፍቶ እንደ በረዶ ቀዘቀዘ ጤነኞችም ሆኑ መኰንኑም "ወደ ወህኒ ወስዳችሁ በዚያ አሥራችሁ ዝጉባቸው" አለ። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! በአጥቢያችን ከተከናወኑ ከከተራ እስከ ቃና ዘገሊላ የተከበሩ በዓላት ከሚዲያና ዕቅበተ እምነት ክፍል ከምስል ማህደር
+9
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! በአጥቢያችን ከተከናወኑ ከከተራ እስከ ቃና ዘገሊላ የተከበሩ በዓላት ከሚዲያና ዕቅበተ እምነት ክፍል ከምስል ማህደር በጥቂቱ ይህን ይመስላል ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን አሜን!!! 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝           ✝ #ጥር ፲፫ (13) ቀን። ✝ እንኳን #ለታላቋ_ሰማዕት_ቅድስት_ዴ_ድሚያናና ከእርሷ ጋር አብረው ሰማዕትነት ለተቀበሉ #ለአርባው_ደናግል ለዕረፍቸው መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ✝ #ሰማዕቷ_ቅድስት_ዴ_ድሚያና፦ ይኽችም ቅድስት ዴሚያና በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ የተወለድችና በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ክርስቲያኖችን በአስከፊና በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገድል በነበረው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን የነበረች በእርሱም እጅ በጭካኔ ዐሥር ጊዜ እጅግ አሠቃቂ የሆኑ መከራዎችን በመቀበል በመጨረሻም ከተከታዮቿ ከ40 ደናግል ሰማዕታት ጋር አንገቷን የተሰየፈች ታላቅ ሰማዕት ናት፡፡ ✝ ኤርትራ ውስጥ ወደሚገኘው ቅድስት ዴሚያና የሴቶች ገዳም (ቤተ ደናግል) ስንሔድ መጀመሪያ ላይ ያጋጠመንና ያስገረመን ነገር መነኰሳይያቱ በጣም ወጣት ሆነው ብዛት ያላቸው መሆኑ ነው፡፡ ገዳሙ ቤተ ደናግል ነው፣ ማለትም ድንግል የሆኑ ሴቶች ብቻ የሚኖሩበት ገዳም ነው፡፡ እንግዳን ለመቀበል የነበራቸው ጉጉትና ፍቅር፣ ትሕትናቸው፣ ትጋታቸው ሁሉ እውነትም ሰማዕቷን ድንግል ዴሚያናንና አርባውን ደናግል ሰማዕታት አስመስሏቸዋል፡፡ገዳሙ ያለበት ቦታ ከተማው ላይ ከእንዳ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ብዙም ሳይርቅ ነው፣ ከአጠገቡም የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ይገኛል፡፡ ✝ ገዳሙ አሁን ያለበት ቦታ በመጀመሪያ የግለሰብ ቤት እንደነበር የነገሩን መነኰሳይያቱ ናቸው፡፡ ሰማዕቷ ቅድስት ዴሚያና በቦታው ላይ ትኖር ለነበረችው አንዲት ሕዝባዊት እናት ተገልጣላት ቦታው ወደፊት ቤተ ደናግል እንደሚሆን ስለነገረቻት ያችም እናት ቤቷን ለሰማዕቷ ቤተ ክርስቲያን እንዲሆን ሰጠች፡፡ ዳግመኛም ቅድስት ዴሚያና ለአንዲት ድንግላዊት ተገልጣላት ወደ ግብጽ ሔዳ መንኵሳ እንድትመጣና ገዳሙን ገድማ ለደናግል መነኰሳይያቱ እመ ምኔት እንድትሆን ነገረቻት፡፡ በዚኽ መሠረት ነው ገዳሙ ተስፋፍቶ ቤተ ደናግል ለመሆን የበቃው፡፡ ስያሜውም በትግርኛ "ገዳም ደብረ ደናግል ሰማዕት ቅድስት ድምያና ምስ 40 ደቃ" ተባለ፡፡ ✝ የሰማዕቷ የቅድስት ዴሚያና አባቷ ማርቆስ የከሃዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ሹመኛ ሆኖ በግብፅ ሁለት ግዛቶችን ያስተዳድር የነበረ ቢሆንም እርሱና ቤተሰቡ ግን ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ እናቷ ገና በልጅነቷ ስለሞተች አባቷ ቅድስት ዴሚያናን ከልጅነቷ ጀምራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድታውቅ ሃይማኖት እንድትማር አድርጎ በንጽሕና አሳደጋት፡፡ እርሷም ከልጅነቷ ጀምራ መጽሐፍ ቅዱስንና የቅዱሳንን ሕይወት እያነበበች አደገች፡፡ ✝ ቅድስት ዴሚያናም 15 ዓመት በሆናት ጊዜ በከተማው የታወቀ አንድ ሰው ሊያገባት ፈለገ፣ አባቷም ይህንን ሲያማክራት እርሷ ግን "…እኔ የክርስቶስ ሰማያዊ ሙሽራ ለመሆን ራሴን ለክርስቶስ ሰጥቻለሁ" በማለት ጋብቻውን በጽኑ ተቃወመች፡፡ ከዚኽም በኋላ ከከተማ ውጭ ባለው በረሓ ውስጥ በሰሜናዊ አቅጣጫ የምትኖርበትን ቤት ይሠራላት ዘንድ አባቷን ጠይቃ ሲሠራላት ቤቱን የጸሎት ቤት አደረገችው፡፡ በኋላም ቅድስት ዴሚያና ያንን አባቷ ያሠራላትን ቤተ መንግሥት የመሰለ ቤቷን ወደ ገዳምነት ቀየረችውና ከደናግል ጓደኞቿ ጋር በአንድነት መኖር ጀመረች፡፡ እርሷም ለደናግል ጓደኞቿ ጌታችንን ስለማመን ታስተምራቸውና ታበረታቸው ነበር፡፡ እነርሱም በጾም በጸሎት፣ ቅዱሳት መጻሕፍን በማንበብ፣ የዳዊት መዝሙርን በመዘመር፣ የእጅ ሥራንም በመሥራት እየተጉ መንፈሳዊ ሕይወታቸው ሌሎቹን ደናግል እየማረከ ስለመጣ ቊጥራቸው 40 እስኪሆኑ ድረስ ተሰባሰቡ፡፡ ✝ ከዚኽም በኋላ ከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በ284 ዓ.ም ከነገሠ በኋላ ክርስቲያኖችን ሁሉ ከያሉበት እያስፈለገ ይገድል አብያተ ክርስቲያናትንም ያጠፋ ጀመር፡፡ ዲዮቅልጥያኖስ ከነገሠና ከካደ በኋላ ወርቅ አቅልጦ 35 የወንድና 35 የሴት ጣዖታትን አሠርቶ ሰው በሚመላለስበት አደባባይ ላይ በማቆም ሁሉም ለጣዖታቱ እንዲሰግድ አዋጅ አስነገረ፡፡ በዘመኑም ለጣዖታቱ ያልሰገዱትንና ክርስቶስን በማመን የጸኑትን ሁሉ በዓለም ላይ ያሉ ከ470 ሺህ በላይ ክርስቲያኖችን በግፍ በሰማዕትነት አስገደለ፡፡ ቅድስት ዴሚያናም ከ40 ቅዱሳት ደናግል ጋር በምናኔ ላይ ሳለች ነው ከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በሰይጣን ታግዞ ወደ ንግሥናው ሥልጣን የመጣው፡፡ ዲዮቅልጥያኖስም በእርሱ ሹመት በግብጽ ሁለት ግዛቶችን ያስተዳድር የነበረውን የቅድስት ዴሚያናን አባት ማርቆስን ወደ አንጾኪያ አስጠርቶ አመጣውና ለጣዖታቱ እንዲሰግድ አዘዘው፡፡ √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝              ✝ #ጥር ፲፩ (11) ቀን። ✝ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካችን #ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ_ለብርሃነ_ጥምቀቱ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከፋርስ አገር ሰዎች ወገን ከሆነ #ከከበረ_ቅዱስ_እንጣልዮስ በሰማዕትነት ከዐረፈ፣ #ከከበሩ_አዮስጦስና_ከፋይዮስ ዕረፍት፣ ከከበረ ተጋዳይ #ከአባ_ወቅሪስ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                       ✝ ✝ ✝ ✝ በዚች ቀን #የክብር_ባለቤት_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከአጥማቂው_ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘንድ_በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ተጠመቀ። ይችም ዕለት በዮናኒ ቋንቋ ኤጲፋንያ ትባላለች ትርጓሜውም መለኮት የተገለጠበት ማለት ነው ልዩ የሆነች የሦስትነቱ ምሥጢር ገልጦባታልና አብ ከሰማይ ሁኖ የምወደው በርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት እያለ ሲመሰክር ወልድም በዮርዳኖስ ወንዝ ቁሞ ሳለ መንፈስ ቅዱስም በነጭ ርግብ አምሳል በወልድ ራስ ላይ ሲቀመጥ ይህ አጥማቂው ዮሐንስ እንደመሰከረ። እንዳህ ሲል "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ ከውኃ በወጣ ጊዜ ወዲያኑ ሰማይ ተከፈተ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በጌታችን ራስ ላይ ተቀምጠ ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ "ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ነው እርሱንም ስሙት"። ✝ በዚች ዕለት ጌታችን ራሱን ገልጦአልና ከዚህ በፊት ሠላሳ ዓመት ያህል ራሱን አልገለጠም ነበር ግን በዚች ዕለት ለእስራኤል ልጆች ራሱን ገለጠ እነሆ "የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ" ብሎ መጥምቁ ዮሐንስ እንደገለጠው የከበረ ወንጌል ምስክር ሆነ። "እኔ አላውቅውም ነበር ነገር ግን እስራኤል ያውቁት ዘንድ በውኃ ላጠምቅ ስለዚህ መጣሁ" አለ። ✝ በዚህም በዓል የእግዚአብሔር ልጅ የክርስቶስ የጌትነቱ ክብር ተገልጧል እርሱም የዓለሙን ሁሉ ኃጢአት ለማስወገድ የሚሠዋ የእግዚአብሔር አማናዊ በግ ነው። ስለዚህም ይህ በዓል በክርስቲያን ወገኖች ሁሉ ዘንድ የከበረና ከፍ ከፍ ያለ ሆነ በርሱም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ በአበረው ውኃ ይነጹበታል የተቀበሉትንም ንጹሕና ጠብቀው ቢኖሩ በውስጡ የኃጢአታቸውን ሥርየት ያገኛሉ። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ውድ የፍኖተ
+9
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢📢 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ውድ የፍኖተ ብርሀን ቤተሰቦች :- እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በአለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ። የግራር ደብረ አባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የከተራ በአል በእግዚአብሔር ረዳትነት በዚህ መልኩ በምስጋና አልፏል። 📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸📸ከሚዲያና ዕቅበተ እምነት ክፍል የምስል ማህደር በጥቂቱ ይህን ይመስላል 📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽📽 🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥

✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝              ✝ #ጥር ፲ (10) ቀን። ✝ እንኳን #ለገሀድ (ጋድ) ጾመ፣ #ለከተራ_በዓልና #ለአባ_ታውብንጦ ለዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦  #ከሰማዕት_ከጠምያኒ_ከኪናርያና #ከንግሥት_በጥሪቃ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                          ✝ ✝ ✝ ✝ #በዚች_ዕለት_ምንም_ምን_መብልን_ሳይቀምሱ #ምእመናን_ሁሉ_እስከ_ምሽት_ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ። በዚች ዕለት ምእመናን እስከ ምሽት እንደመጾሙን ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና። ✝ እኛ በዚህ በኅላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው። እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው። ✝ በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥራ ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾም ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ። ✝ በጥምቀትም ዕለት ከእኵለ ሌሊት በፊት ተነሥተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቊርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ። ✝ የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሑድ ቀን ቢሆን በሦስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነው በየሰዓቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያች ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዐሥር ነው በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም። እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲአክብሩ አዘዋል ይኸውም መድኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህ ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው። ✝ መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዓርብም ረብዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥተው ይበላሉና። እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮርዳኖስም ወንዝ እንደ ተገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።                               ✝ ✝ ✝ ✝ #አባ_ታውብንጦስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ አባ ታኡና በሚባል በሮሜው ሊቀ ጳጳሳት ቤት አደገ እርሱም የምንኵስናን ልብስ አለበሰው። መንፈሳዊ ዕውቀትና ኃይል እንደተሰጠው አይቶ ከእስክንድርያ አገር ውጭ ስሙ ጤናዲራን በሚባል ቦታ ኤጲስቆጶስነት ሹሞ የገዳም አበ ምኔት አደረገው ከእርሱ ሥር ያሉ መነኰሳትም ሰባት መቶ ናቸው። ✝ ከዚህም በኋላ ከእርሱ ጋር ላሉ መነኰሳት አለቃ የሆነ ኤጲስቆጶስ ታውብንጦስ ከከሀዲ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ስለሆነው ሁከት በሰማ ጊዜ ሸሽቶ ወደ ደብረ ሲሐት ገዳም ሒዶ እግዚአብሔርን ከምትፈራ ከአንዲት ድንግል ዘንድ ተቀመጠ። በእርሷ ቤትም ብዙ ዘመናት ኖረ በመጀመሪያ ወደርሷ በገባ ጊዜ ግን ንጉሡን ስለ መፍራት ጣዖትን ስታመልክ አገኛትና የክብር ባለቤት ጌታችን ክርስቶስን ወደ ማመን መለሳት። ✝ ከዚያም ተርኑጥና መርኑስ ወደ ሚባሉ ገዳማት ሔደ የአብያተ ክርስቲያናትን ወሬ ይሰማ ዘንድ ፈልጎ በጾም በጸሎት ሌሊትም በመትጋት እያገለገለ በአንዲት ገዳም ውስጥ ሁለት ሦስት ቀን ተሠውሮ ያድር ነበር። የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ በላዩ እንዳደረ እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆች ተአምራቶችን እንዳደረገ ከወንበዴዎችና ከዓመፀኞች ብዙዎችን መነኰሳትን አድርጎ ለክርስቶስ ወደ መገዛት እስከ መላሳቸው ድረስ መነኰሳቱ ሁሉ መሰከሩለት። ✝ ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ የሚሞትበትን ቀን ዐወቀ ልጆቹንም የክርስቶስ በሆነች በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ አስተማራቸው ወዲያውኑ ጥር10 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ታውብጦስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር10 ስንክሳር። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨