ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)
رفتن به کانال در Telegram
🌷ይህ ቻናል የተከፈተው ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና እምነት ተከታይ ሲሆን ዋና አላማውም ምዕመናን በንስሐ ህይወት ተመላልሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት እንድወርሱ የሚያስችል ትምህርት መስጠት ነው፡፡ 🌷💚የቅዱሳን ገድላት 🌷💛ስንክሳር 🌷♥ ቅዱሳን ስዕላት መንፈሳዊ ትምህርቶችና ጽሑፎች 🎤 ስብከቶች ............ይቀርቡበታል፡፡🌎
نمایش بیشتر2 411
مشترکین
-124 ساعت
+87 روز
+930 روز
در حال بارگیری داده...
کانالهای مشابه
ابر برچسبها
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
اکتبر '26اکتبر '26
اکتبر '26
+25
در 0 کانالها
سپتامبر '26
+51
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '26
+92
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '26
+80
در 1 کانالها
Get PRO
ژوئن '26
+53
در 0 کانالها
Get PRO
مه '26
+36
در 1 کانالها
Get PRO
آوریل '26
+49
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '26
+43
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '26
+42
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '26
+37
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '25
+46
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '25
+59
در 1 کانالها
Get PRO
اکتبر '25
+37
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '25
+25
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '25
+53
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '25
+49
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '25
+34
در 0 کانالها
Get PRO
مه '25
+58
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '25
+59
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '25
+69
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '25
+62
در 1 کانالها
Get PRO
ژانویه '25
+85
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '24
+75
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '24
+56
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '24
+49
در 1 کانالها
Get PRO
سپتامبر '24
+32
در 1 کانالها
Get PRO
اوت '24
+75
در 1 کانالها
Get PRO
ژوئیه '24
+58
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '24
+53
در 0 کانالها
Get PRO
مه '24
+52
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '24
+77
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '24
+86
در 1 کانالها
Get PRO
فوریه '24
+38
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '24
+41
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '23
+57
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '23
+54
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '23
+23
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '23
+30
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '23
+46
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '23
+58
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '23
+43
در 0 کانالها
Get PRO
مه '23
+79
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '23
+31
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '23
+53
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '23
+77
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '23
+94
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '22
+96
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '22
+79
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '22
+78
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '22
+112
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '22
+111
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '22
+92
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '22
+88
در 0 کانالها
Get PRO
مه '22
+69
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '22
+109
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '22
+119
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '22
+44
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '22
+60
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '21
+35
در 0 کانالها
Get PRO
نوامبر '21
+52
در 0 کانالها
Get PRO
اکتبر '21
+52
در 0 کانالها
Get PRO
سپتامبر '21
+31
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '21
+37
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '21
+69
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '21
+57
در 0 کانالها
Get PRO
مه '21
+75
در 0 کانالها
Get PRO
آوریل '21
+125
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '21
+77
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '21
+91
در 0 کانالها
Get PRO
ژانویه '21
+78
در 0 کانالها
Get PRO
دسامبر '20
+672
در 0 کانالها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 13 اکتبر | +1 | |||
| 12 اکتبر | +1 | |||
| 11 اکتبر | +5 | |||
| 10 اکتبر | +1 | |||
| 09 اکتبر | +1 | |||
| 08 اکتبر | +7 | |||
| 07 اکتبر | +1 | |||
| 06 اکتبر | +1 | |||
| 05 اکتبر | +1 | |||
| 04 اکتبر | +1 | |||
| 03 اکتبر | 0 | |||
| 02 اکتبر | +3 | |||
| 01 اکتبر | +2 |
پستهای کانال
እነሆ በአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ፈቃድ፣ ቸርነትና ምህረት የዘመነ ሉቃስ የመጀመሪያው ወር: መስከረም ተቋጨ ። እናታችን ቅድስት ልዴታ ማርያም ወርሃ ጥቅምት በምልጃዋ ጠብቃ ታሸጋግረን 🙏
@mahiberekidusan
| 2 | #መስከረም 29
የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ዓመታዊ በዐል ነው
እናቷ አትኖስያ ትባላለች ልጅ በማጣት ለረጅም ዘመን ታዝን ታለቅስ ነበር በኃላም እግዚያብሔር ልመናዋን ሰማት ይህችን ክብርት ቅድስት ልጅንም ሰጣት፤ቅድስት አርሴማ ጥር 6 ነው የተወለደችው፤15 ዓመት ሲሆናት ሊያጋቡአት አሰቡ እርሷ ግን ይህን አልወደደችም፤ በደናግል ገዳም ገብታ በተጋድሎ መኖር ጀመረች።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ከዚህ በኃላ እንዲህ ሆነ ከሃዲው ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ ሊያገባት ወደደ ቅድስት አርሴማ ግን ከደናግሉ ጋር ሸሽታ ወደ አርማንያ ሄደች በዚያም በበርሃ ለጥቂት ቀናት ተቀመጠች በኃላ ላይ ድርጣድስ የሚባል አገር ገዢ በበርሃ እንደሚኖሩ ሰማ ወታደሮችንም ልኮ አስመጣቸው፤ የቅድስት አርሴማን መልክ በተመለከተ ጊዜ ፈዞ ደንዝዞ ቀረ የፊቷ ውበት እጹብ ድንቅ፤ ግርማዋ የሚያስደነግጥ ልብ የሚያርድ ነበርና፤ስለዚህም ሊያሰቃያት አልደፈረም በእንክብካቤ በሰገነት ላይ አኖራት፤ ሌሎቹን ግን ለጣአት እንዲሰግዱ ገረፋቸው፤ ቅድስት አርሴማ እኔንም አሰቃዩኝ እያለች አምርራ ታለቀስ ነበር። ድርጣድስ ብዙ ጊዜ ሊሸነግላት ሞከረ እርሷ ግን ትዘልፈው ጣኦታቱንም ትረግም ነበር፤ እርሷ ጸንታ ደናግሉን ታጸና ነበር ትመክራቸው ታረጋጋቸው ነበር፤ ድርጣድስ ሽንገላው እንደማያዋጠው በአወቀ ጊዜ ማሰቃየት ጀመረ፤ በመጨረሻም ከብዙ ስቃይ በኃላ መስከረም 29 ቀን አንገቷን ቆረጣት ከእረሷ ጋር 27 ሰማዕታት አብረው ተሰይፈዋል። በአገራችን በስሟ ሰሜን ወሎ ውስጥ ሲሪንቃ ቅድስት አርሴማ የሚያስገርም ገዳም አላት፤በዚህ ገዳም ሰባት ቀን ብቻ ሱባዬ የሚገባ የልቡን መሻት ትፈጽምለታለች፤በመዲናችን አዲስ አበባም የቅድስት አርሰሴማ ቤተክርስቲያኖች አሉ አንዱም አስኮ ቃሎ ተራራ ላይ የሚያስገርም ቤተክርስቲያን አላት ይህንን የቃሎ ተራራ ሲወጡ ዝቋላ አቦ ትዝ ይላል፤ መስከረም 29 በደማቁ ታቦተ ህጉ ወጥቶ ተከብሮ ይውላል። ከሰማዕቷ በረከት ያድለን። ይህም መስከረም 29 ቀን የሰማዕትነት አክሊል የተቀዳጀችበት ዕለት ነው ፡፡ ታህሳስ 6 ፍልሰተ አጽሟ ነው
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ..........
@mahiberekidusan | 407 |
| 3 | እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን / አደረሳችሁ ። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እውነትን ቀብሮ ማስቀረት እንደማይቻል ተቀብሮ ግን ሊቆይ እንደሚችል ማሳያ ነው።
#ሀገራችንን፣ ቤተክርስቲያናችንንና ህዝባችንን በብርሃነ መስቀሉ ይጠብቅልን ። የዛሬ ዓመት በሰላም ፣ በጤናና በበረከት ያድርሰን። የመስቀሉን ሙሉውን ታሪክ ከላይ ከደመራው በዓል ጋር አያይዘን ጽፈናል ያንብቡት 🙏
@mahiberekidusan | 734 |
| 4 | የቀጠለ.....👇
በዘመነ አበው መስቀል የመባረኪያ ምልክት እንደነበረ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሷል፤ ዘፍጥረት ላይ ፤ ‹‹ያዕቆብ በሚሞትበት ጊዜ የዮሴፍን ልጆች በእምነት ባረካቸው›› ‹‹ወአስተሐለፈ እዴሁ ላዕለ ርዕሰ ኤፍሬም ወምናሴ፤ እጆቹን በኤፍሬምና በምናሴ ላይ በመስቀል ምልክት አድርጎ ጭኖ ባረካቸው›› ይላል፡፡ (ዘፍ. ፵፰፥፲፩)፤ ዕብ. ፲፩፥፳፪)
ዛሬም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህኑ ቀድሶ በሚወጣበት ጊዜ በእጆቹ ይባርካል፤ ይህም የሚያሳየው ቤተ ክርስቲያን መሠረቷ ከላይ በዓለመ መላእክት ከታች ደግሞ በዘመነ አበው ያየነው መስቀል መሆኑን ነው፡፡
መስቀል በብሉይ ኪዳን እንደየሀገሩ ሁኔታ ልዩ ልዩ ተግባራት ሲፈጸምበት ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ፡- ለወንጀለኞች መቅጫነት አገልግሏል፤ ለአርማም ይጠቀሙበት ነበር፡፡
መስቀል በሐዲስ ኪዳን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ፣ ሰው ሆኖ፣ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ፣ በመስቀል ተሰቅሎ፣ ድኅነትን ለሰው ልጆች ሰጥቶ፣ በመስቀሉ ተጣልተው የነበሩ ሰባቱን መስተፃርራን (ሰውና እግዚአብሔርን መላእክትና ሰውን፣ ነፍስና ሥጋን፣ ሕዝብና አሕዛብን) አስታርቋል፡፡
#ደመራ_
ደመራ ማለት መጨመር፣መሰብሰብ፣መከመር ነው፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ደመራ የሚለውን ቃል ደመረ ከሚለው የግእዝ ቃል አውጥተው ደመራ ግእዝና አማርኛን ያስተባበረ መሆኑን ገልጸው የበዓለ መስቀል ዋዜማ እንጨቶች የሚደመሩበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የታላቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ ከቁስጥንጥንያ ተነሥታ የጌታችን መድኃኒችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች፡፡ ኢየሩሳሌም በደረሰች ጊዜ የጌታችን መስቀል ተአምራትን እንዳያደርግ አይሁድ በምቀኝነት ቀብረውት ነበርና የተቀበረበትን ቦታ የሚያሳያት አጥታ በመፈለግ ብዙ ጊዜ አሳለፈች፡፡
በኋላ ግን አንድ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊ አካባቢውን ነግሯት ደመራ አስደምራ ዕጣን አጢሳ ወደ ፈጣሪዋ ብትማፀን የዕጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ መንበረ ጸባዖት ደርሶ ተመልሶ መስቀሉ የተቀበረበትን ስፍራ አመለከታት፡፡
እርሷም በምልክቱ መሠረት ብታስቆፍር የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል አገኘች፤ ከእርሱ መስቀል ጋር ሁለት ወንበዴዎች የተሰቀሉበትን መስቀል አብራ አግኝታው ስለነበር የጌታችን መስቀል ለይታ ያወቀችበት መንገድ ግን ድውያንን በመፈወሱ፣ አንካሳ በማበርታቱ፣ ጎባጣን በማቅናቱ የዕውራንንም ዐይን በማብራቱ ነው፡፡ ስለዚህም በየዓመቱ የመስቀልን በዓል ስናከብር ደመራ የምንደምረውና የምናበራው ንግሥት ዕሌኒን አብነት በማድረግ ነው፡፡
እርስዋም መስከረም ፲፯ ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢት ፲ ቀን መስቀሉን አግኝታ አስወጥታ የቤተ ክርስቲያኑም መሠረት ወዲያው እንዲጣል አደረገች፡፡
የጌታ መስቀል ለብዙ ዓመታት በኢየሩሳሌም ከቆየ በኋላ ነገሥታት መስቀሉን ለመውሰድ ጠብ ፈጠሩ፡፡ በዚህ ጊዜ የአንጾኪያ፣ የኤፌሶን፣ የአርማንያ፣ የግሪክ፣የእስክንድርያ፣ የመሳሰሉት የሃይማኖት መሪዎች ጠቡን አበረዱት::
ከዚያም አያይዘው በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የክርስቶስን መስቀል ለዐራት ከፍለው በስምምነት ተካፍለው ከሌሎች ታሪካዊ ንዋያተ ቅድሳት ጋር በየሀገራቸው ወስደው በክብር አስቀመጡት:: የቀኝ ክንፉ የደረሰው ለአፍሪቃ ስለነበር ከታሪካዊ ንዋየ ቅድሳት ጋር በግብፅ የሚገኘው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ተረክቦ ወስዶ በክብር አስቀመጠው፡፡
ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ዳግማዊ ዳዊት የግብፅ ክርስቲያኖች በአማሌቃውያን ከሚደርስባቸው ተጽዕኖ ነጻ እንዲወጡ በማድረጋቸው የግብፅ ፓትርያርክ የከበሩ ስጦታዎችን ላኩላቸው:: ንጉሥ ዳግማዊ ዳዊት ግን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የምትፈልገው ወርቅ ሳይሆን ጌታ የተሰቀለበትን መስቀሉን እንደሆነ ገለጹላቸው::
በመሆኑም የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ግማደ መስቀሉን ከሌሎች ንዋየ ቅድሳት ጋር ለኢትዮጵያ ሰጥታለች:: ይህ ግማደ መስቀል በግሸን ማርያም ገዳም በእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ሆኖ ኢትዮጵያን እየባረከ ይገኛል::
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መስቀልን ከሐዋርያት በተማረችው መሠረት የወርና የዓመት በዓል ሠርታ ታከብረዋለች::
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@mahiberekidusan | 831 |
| 5 | እንኳን ለደመራ በዓል አደረሰን።
#የመስቀል_ደመራ_በዓል_
የመስቀል ነገር በመጀመሪያ የተገለጸው በመላእክት ዓለም ነበር፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሥነ ፍጥረትን በጻፈበት አክሲማሮስ በተባለ መጽሐፉ እግዚአብሔር መላእክትን ፈጥሮ በተሰወረባቸው ጊዜ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ አለ፡፡ ያን ጊዜ በመላእክት ዓለም ረብሻ ሆነ፤ ከፊሉ ዲያብሎስን አምኖ ከእርሱ ጋር ሆነ፤ ቅዱስ ገብርኤል ግን የፈጠረንን እስክናገኝ በያለንበት ጸንተን እንቆይ አለ፤ ቅዱስ ሚካኤልና ሌሎች መላእክትም አብረው ጸንተው ቆዩ፤ ተጠራጥውም ከሁለቱም ጎን ሳይሆኑ የቀሩ ነበሩ፡፡
ከዚያም በመላእክትና በዲያብሎስ መካከል ጦርነት ተጀመረ፤ በተዋጉ ጊዜ ዲያብሎስ ሁለት ጊዜ አሸነፋቸው፤ ሆኖም መላእክት አምላካቸውን ‹‹ፈቃድህ ነውን?›› ብለው ቢጠይቁት፤ ‹‹ፈቃዴስ አይደለም፤ ድል የምታደርጉበትን ኃይል እንድታውቁት ብዬ ነው እንጂ›› ብሎ በክንፋቸው ላይ የብርሃን መስቀል ቀረጸላቸው፤ በእጃቸው ደግሞ የብርሃን መስቀል አስያዛቸው፤ ሄደውም ዲያብሎስን ቢገጥሙት በመስቀሉ ኃይል ድል ነሥተውታል፡፡ መላእክት ሳጥናኤልን ድል ያደረጉት በመስቀል ኃይል ነው (ራዕ. ፲፪፥፯፣ መዝ. ፶፱፥፬)፡፡ | 504 |
| 6 | #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሃዱ አምላክ ዘለዓለም ሥላሴ አሜን።🙏#
መስከረም 2
#እንኳን_ለታላቁ_ነቢይና_ሰማዕት_ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ
ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነ ዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: #ቅዱስ_ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "#ዘካርያስ ካህኑና #ቅድስት_ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
¤የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
¤እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::
¤ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
¤ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል #እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
¤የአምላክ እናቱ ስትደርስና "#ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
¤ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ #ሰብአ_ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::
¤እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና #ስምዖን ወርደው ቀበሯት::
¤ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ #ድንግል_ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::
¤ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በሁዋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::
¤ከዚህ በሁዋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::
¤ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ #መንፈስ_ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::
¤ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ:: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነ ልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::
¤"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "#መጥምቀ_መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው::
¤በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6)
¤ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት #ደብረ_ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: #ቅዱሳን_ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::
¤ከዚሕ በሁዋላ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ በዚህች ቀን ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::
<<¤ አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ (የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች) ¤>>
1.ነቢይ
2.ሐዋርያ
3.ሰማዕት
4.ጻድቅ
5.ካሕን
6.ባሕታዊ/ገዳማዊ
7.መጥምቀ መለኮት
8.ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ)
9.ድንግል
10.ተንከተም (የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ)
11.ቃለ አዋዲ (አዋጅ ነጋሪ)
12.መምሕር ወመገሥጽ
13.ዘየዐቢ እምኩሉ (ከሁሉ የሚበልጥ)
=>ጌታችን #መድኃኔ_ዓለም የመጥምቁ ዮሐንስን ቃል ኪዳን አስቦ ይቅር ይበለን:: ጸጋውን: በረከቱንና ክብሩንም ያሳድርብን:: አሜን🙏🙏
ምንጭ - ዝክረ ቅዱሳን
#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ_ሀተዋህዶ_ልጆች_ሼር ያድርጉ!
💚 @mahiberekidusan 💚
💛 @mahiberekidusan 💛
❤️ @mahiberekidusan ❤️ | 862 |
| 7 | #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሃዱ አምላክ ዘለዓለም ሥላሴ አሜን።🙏#

=>ጌታችን #መድኃኔ_ዓለም የመጥምቁ ዮሐንስን ምትረት አስቦ ይቅር ይበለን:: ጸጋውን: በረከቱንና ክብሩንም ያሳድርብን:: አሜን
ምንጭ - ዝክረ ቅዱሳን
#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ_ሀተዋህዶ_ልጆች_ሼር ያድርጉ!
💚 @mahiberekidusan 💚
💛 @mahiberekidusan 💛
❤️ @mahiberekidusan ❤️ | 1 |
| 8 | بدون متن... | 1 504 |
| 9 | #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_ዘለዓለም_ሥላሴ_አሜን ።
#መስከረም_01/2019 ዓ.ም
#እንኳን_ከዘመነ_ማርቆስ_ወዴ_ዘመነ_ሉቃስ_በሰላም አደረሰን/አሸጋገረን🙏🙏🙏
ሰላም ለሀገራችን፣ ፍቅርና አንድነት ለህዝባችን፣ ለቤተክርስቲያናችን ፣ ለቤተሰቦቻን ለወገኖቻችን ሁሉ ይሁን ።
#እግዚአብሔር_የዘመናት የፍጥረታት ጌታ ሁሉንም በጊዜው ውብ አድርጎ ሰርቶታል። እኛ ሰዎች ማስታወስ ያለብን ጉዳይ ያለ አንድ ቅንጣት መልካም ስራ እግዚአብሔር በቸርነቱ እንደሚያኖረን ለንስሐ እድሜ እንደሚጨምርርልን ነው።
መዝሙረኛው ዳዊት በተሰጠው ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር መዝ 64(5)፥11 "በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፤ ምድረ በዳዎችም ጠልን ይጠግባሉ ።" በማለት ልዑለ ባህርይ አምላካችን ቅድስት ሥላሴ(እግዚአብሔር )ዘመናትን (ዓመታትን ) እንደሚያቀዳጃቸው ይናገራል ። እግዚአብሔር የምህረት ፣የይቅርታ አምላክ ስለሆነ ሳያጠፋ ጠብቆ ዘመንን ፣ ጊዜን ይሰጠናል ። 🥀🥀🎋
ስለዚህ እድሜ ሲጨመርልን ማድረግ ያለብን ነገር በንስሐ ህይዎት መመላለስ እና መንፈሳዊ ህይወትን ማሳደግና ማጎልበት፣ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያ ጦርና ጋሻ ሆነን መንፈሳዊ ትጥቅን ታጥቀን ዘብ ልንቆም፣ እናታችንን ቤተ ክርስቲያንን ልናስደስታት ይገባናል ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ቀኖች ክፉ ናቸውና ዘመኑን ዋጁት" ይላል። ዘመን የተሰጠን እኛ ልንኖርበትና ልንጠቀምበት ነው ። እናም ጊዜ ሳይጠቀምብን እኛ ተጠቅመንበት በወቅቱ ማድረግ ያለብንን ለነፍሳችን ስንቅ ወደ አግዚአብሔር የህይወት መጽሐፍ ማስቀመጥ አለብን። መጽሐፍ እንድህ ይላል ። 🌼💐🌻
እግዚአብሔር መሀሪ ነው ብለህ ኃጢአትን አትስራ፤ ቁጣና መአትም ከእርሱ ጋር አንደሆነ እወቅ ይላል ። ስለዚህ ከዘመን ወዴ ዘመን የምንሸጋገረው በእግዚአብሔር ምህረትና ይቅርታ እንጅ በስራችን አይደለም። ስለዚህ ከገባንበት የኃጢአት ፥የበደል አዘቅት ወጥተን እግዚአብሔር ደስ ልናሰኘው ይገባናል ። በቸርቱ ከአመት ወዴ አመት፣ ከጨለማ ወዴ ብርሃን ፣ ከሞት ወደ ህይወት ፣ከገሃነም እሳት ወደ መንግሰተ ሰማያት የመለሰን አምላካችን ፣ፈጣሪያችን በአራቱም ማዕዘናተ ዓለም የተመሰገነ ይሁን። 💚💛❤️
#ዘመኑን #የሰላም_የንስሐ_የጤና_የፍቅር _የትምህርት_የምህረትና የይቅርታ ያድርግልን ።💐🌼🌻
🍶መልካም አድስ ዓመት
መልካም በዓል 🐓🐏🌺🌸🍁🍎🍊🍉
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን 🙏
@mahiberekidusan💚
@mahiberekidusan💛
@mahiberekidusan❤️ | 671 |
| 10 | #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_ዘለዓለም_ሥላሴ_አሜን ።
#መስከረም_01/2019 ዓ.ም
𝐇𝐀𝐏𝐏𝐘 ETHIOPIAN 𝐍𝐄𝐖 𝐘𝐄𝐀𝐑 (2019 E.C)
#ሰላም_ጤና_ይስጥልን_ክቡራንና_ክቡራት_ውድ_የተዋሕዶ_ልጆች__መንፈሳዊ_ሰላምታችን_በያላችሁበት የዓለም ክፍል ይድረሳችሁ ።
#እንኳን_ለ2019_ዓ.ም_የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሰን። አደረሳችሁ ።
#እንኳን_ከዘመነ_ማርቆስ_ወዴ_ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገረን ።
@mahiberekidusan💚
@mahiberekidusan💛
@mahiberekidusan❤️ | 29 |
| 11 | እንኳን ለገናናው መልአክ ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሰን🙏
#ሩፋኤል ማለት «እግዚአብሔር ፈዋሽ» ነው። ማለት ነው።ሩፋኤል ማለት «ፈታሄ ማኀፀን» ማለት ነው። ሣልሳይ ሊቀ መላእክት ነው። በኃያላት ላይ የተሾመ የመላእክት አለቃ ሩፋኤል ነው። ቅዱስ ሩፋኤል «መራኄ ፍኖት» መንገድ መሪም ይባላል፡፡
ከበሩት ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ።
(ጦቢት 12 ፥13)
ሩፋኤል ግባ ግባ በቤቴ
ታስሬ እንዳልቀር ፍታኝ አባቴ
ስለ ኃጢአቴ ማልደኝ ግባ በቤቴ
ቆሽሻለሁና ግባ በቤቴ
አማላጅነትህ ግባ በቤቴ
ያስምረኛልና ግባ በቤቴ
ጠላቴ እንዲሸሸኝ ግባ በቤቴ
ሁልጊዜ ናና ግባ በቤቴ 🙌🙌🙌
#የሩፋኤል የስራ ማዕረጉ ብዙ ነው
ከሰባቱ ሊቀ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው ሩፋኤል ሰዳዲ ሰይጣን ነው። ሩፋኤል በቁስል ላይ የተሾመ መልኣክ ነው የሚፈውሰን ሩፋኤል በማህጸን ላይ የተሾመ መልአክ ነው ፈታሄ ማህጸን ነው በተለያዩ የዲያብሎስ ሴራ የራሄሎ /ሾተል /መንፈስ የተዘጉ ማህጸኖችን የሚከፍት በተለይ እርጉዝ የሆኑ ሴቶች ድርሳኑን ቢያነቡት ቢታመኑለት ሩፋኤል ታማኝ ጽንስን ሊያጨናግፍ የመጣውን እርኩስ መንፈስ በስልጣኑ እየሰረ ሲኦል ያወርዳል እንዲሁም በተጨነቅን ጊዜ ሰይጣን እንኳን ደንግጦ ከእኛ ርቆ ቢደበቅ የገባበት ቦታ ገብቶ አንጠልጥሎት ወደ ገሃነም የሚያወርድ ጠበቂያችን ነው።
1. ሩፋኤል ጽንስ ጠባቂ ነው።
2. እርኩሳን መናፍትን የሚያሰር ተዊጊ/ሰዳዲ ሰይጣን ነው።
3. በቁስል/በሽታ ላይ የተሾመ መልአክ ነው።
4. ጳጉሜ 3 የሰው ልጆችን ኃጢአት ያስተሰርያል የኀጢአት መዝገባችንን ይዞ በጌታ ፊት ይቅር በላቸው ይልልናል።
የሩፋኤል እረድኤት በረከቱ ተራዳኢነቱ ይደርብን በእውነት ይባርከንም አሜን፫♥♥♥🌹🌹🌹
@mahiberekidusan | 695 |
| 12 | "ጳጉሜ/ጳጉሜን" አሥራ ሦስተኛዋ ወር:
የኢትዮጵያን ዘመን አቆጣጠር ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ጳጉሜ የምትባል አሥራ ሦስተኛ ወር ስላለችን ነው። የቤት ኪራይና የወር ደመወዝ የማንከፍልባትና የማንቀበልባት መብራትና ውሃን ግን ከነሐሴ ወር ጋር ጨምረው የሚያስከፍሉባት ሲሻት አምስት ሲያስፈልጋት ስድስት ስትፈልግ ደግሞ ሰባት የምትሆን ወር ናት። እንዲያውም ከአስራ ሁለቱ የኢትዮጵያ ወራት ጳጉሜ በብዙ መንገድ የተለየች ናት።
ጳጉሜ የሚለው ስያሜ "ኤፓጉሜኔ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም "ጭማሪ" ማለት ነው። በግዕዝ "ወሰከ-ጨመረ" ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ተውሳክ (ተጨማሪ) ማለት ነው።
ምዕራባውያኑ ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ቀን አድርገዋታል። እኛ ግን የዓመት ተጨማሪ ወር አድርገናት እንጠቀማለን።
በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ወርኃ ጳጉሜ የዓለም ፍጻሜ መታሰቢያ ተደርጋ ትታሰባለች። ይህም ጳጉሜ ከአሮጌው ወደ አዲሱ ዓመት ከክረምት ወቅት ወደ ጸደይ መሸጋገሪያ እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊ ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደወዲያኛው መሸጋገሪያ ናትና ነው።
ጳጉሜ የክረምቱ ማብቂያ እንደሆነች ሁሉ ምጽዓትም በመጨረሻው ዘመን መከራ የሚበዛባት የዚህ ዓለም ማብቂያ ናት። ወርኃ ጳጉሜ አዲሱን አመት ለመቀበል የዝግጅት ጊዜ እንደሆነች ሁሉ ምጽዓትም:- ጻድቃን አዲሲቷን ምድር /መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ ተዘጋጅተው "ኑ የአባቴ ብሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።" የሚባሉበት ናት።
በዚህም የተነሳ ብዙ ምዕመናን በጾምና በጸሎት /በሱባኤ ያሳልፏታል። በተለይም በቅዱስ ሩፋኤል ዕለት ሰማያት የሚከፈቱበት /ርኅዎተ ሰማይ መሆኑን በማመን ምዕመናን የጸሎታቸው ማረጊያ /ማሳረጊያን ዕለት በማሰብ ከምንጊዜውም በበለጠ በእምነት ይጸልያሉ። ርኅወተ ሰማይ የስሙ ትርጉም የሰማይ መከፈት እንደማለት ሲሆን በክርስቶስ ክርስቲያን የተባሉ ሁሉ ጸሎት ልመናቸው ምልጃቸው የሚያርግበት ዕለት ነው። ቅዱሳን መላእክት የምዕመናንን ልመና መስዋዕቱን የሚያሳርጉበትና የአምላካችንን ምህረት ቸርነት ለሰው ልጆች የሚያወርዱበት ዕለት ነው። ከዚህም የተነሳ ውኆች እንደሚባረኩ በሚረዳ ጽኑ እምነት ምዕመናን ወደወንዞች በመሄድና በሚዘንበው ዝናብ ውሃ ይጠመቃሉ።
በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው ጾመ ዮዲት ነው። የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለጾመችው ነው።
ዮዲት ማናት? እንዴት ጾመችው? በመጾሟ ምን አገኘች? እኛስ ለምን እንጾማለን? ብንጾም ምን እናገኛለን? የሚለውንና ስለቅዱስ ሩፋኤል አመታዊ ክብረ በዓል ነገ ሙሉ ጽሑፉን ይጠብቁ!
ጳጉሜ ወር ነገረ ምጽአት የሚነገርባት የሚታሰብባት ናት፡፡ ጳጉሜን ወር ዮዲት ጾማ ጠላቶቿን ማጥፋት እንዳስቻላት እኛም ይህችን አምስት ቀን ጾመን ጸልየን ጠላት ዲያቢሎስን: ጠላት መለያየትን: ጠላት በሽታን: ጠላት ጥላቻን: ጠላት ጭንቀትን: ጠላት ስንፍናን: ወዘተ ማጥፋት ማሸነፍ እንችል ዘንድ እንትጋ ብዬ በልጅነት መንፈስ በክርስቶስ ፍቅር እጠይቃለሁ።ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላድቱ ድንግል አሜን፡፡
@mahiberekidusan | 814 |
| 13 | ነሐሴ ፴ /30/
በዚህች ዕለት ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ የሆነው ታላቁ ነቢይ ሚልክያስ አረፈ።
እግዚአብሔር አምላክ በነቢዩ አንደበት አድሮ እንዲህ ይለናል።
ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። ትንቢተ ሚልክያስ 3:8
እንዴት አድርጌ ነው ከ5ሺህ ብር ደሞዝ በዛ ላይ የኑሮ ውድነቱ ተጨምሮበት አስራት የማወጣው? ብላችሁ ብትጠይቁም እግዚአብሔር በነቢዩ አድሮ እንዲህ ይለናል።
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ትንቢተ ሚልክያስ 3:10
ቅዱስ ሚልክያስም በበጎ ተጋድሎው እግዚአብሔርን ከአገለገለ በኋላ በዛሬዋ ዕለት ከዚህ ዓለም በመፍለስ በሰላም አረፈ። ሚልክያስ ማለት መልዐክ አንድም የተላከ ማለት ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @mahiberekidusan 💚
💛 @mahiberekidusan 💛
❤️ @mahiberekidusan ❤️ | 722 |
| 14 | በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ዘለዓለም ሥላሴ አሜን።
#እንኳን_ለታላቁ_ቅዱስ ለአቡነ ተክለ ኃይማኖት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።🙏
#ልደት
በልቡናው መልካም መልካም መዝገበ ያስቀመጠ ሰው ከልቡናው መዝገብ አውጥቶ ዛፍ የሚናገረው ከዚያው ነውና የጻድቁ ወላጆችም በደግነት፣ በጸሎት ከልባቸው የተመኙትን ወደ እግዚአብሔር አመልክተው ተደርጎላቸዋለ። መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው። እርሱ በክህነቱ እርሷ በደግነቷ በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል።
በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል ጸጋ ዘአብን ከሞት እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል። በሁዋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል።
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታሕሳስ 24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው። በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል። ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል።
#ዕድገት/አስተዳደጋቸው
የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል። ይሕንን ስም ይዘው አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል። በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል። በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል። ዲቁናም ከወቅቱ ዻዻስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል።
#መጠራት_ወደ ቅድስና ህይወት
አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮስ ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ።
የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ። "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን። ከዚህ በሁዋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ። ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ። ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ሰዓትን አላጠፉም። ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ።
#አገልግሎት
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ። በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ። ያን ጊዜ ኢትዮዽያ 2 መልክ ነበራት።
1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል።
2ኛው. ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር።
ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ። ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል::
#ገዳማዊ_ሕይወታቸው
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል። እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል።
እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል።
በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በሁዋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል። በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል።
#ስድስት_ክንፍ
ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል። ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::
የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል። ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በሁዋላ ነው ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር።
ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም። በገሃድ:-
-በቤተ መቅደስ ብስራቱን
-በቤተ ልሔም ልደቱን
-በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
-በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
-በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር።
የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ። በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው።
#በዚያም :-
-የብርሃን ዐይን ተቀብለው
-6 ክንፍ አብቅለው
-የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
-ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
-ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
-ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
-"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል።
#ያደረጓቸው_ተአምራት
የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው።
ሙት አንስተዋል
ድውያንን ፈውሰዋል
አጋንንትን አሳደዋል
እሳትን ጨብጠዋል
በክንፍ በረዋል
ደመናን ዙፋን አድርገዋል።
ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል። በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል። በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::
#ዕረፍት
ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል።
ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል። 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል።
የጻድቁ በረከት ምልጃና ጸሎት ይደረግልን። በቃል ኪዳናቸው ለሀገራችን ሰላምን ይስጥልን።
#ለእግዚአብሔር_ምስጋና ይሁን💚💛❤️
💚 @mahiberekidusan 💚
💛 @mahiberekidusan 💛
❤️ @mahiberekidusan ❤️ | 899 |
| 15 | በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ዘለዓለም ሥላሴ አሜን።

| 16 | "…በዚህ ዓለም 64 ዓመት ኑራ ጥር 21 ቀን ያረፈችው የእመቤታችን የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉ…
"…ቅዱስ ዮሐንስን እንደምን ሆነች አሉት ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች አላቸው። ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ 2ሱባዔ ሲፈጸምም እሑድ አምጥቶ ሰጥቷቸው ቀብረዋታል። በ3ኛ ቀን ማክሰኞ “ከመ ትንሳኤ ወልዳ” እንደ ልጇ ተነሥታለች። ቅዱስ ቶማስ አልነበረም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት። ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬም ደግሞ ያንችን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁን ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ከኀዘኑ የተነሳ ሊወድቅ ወደደ። እመቤታችንም አይዞህ አትዘን እሊያ ትንሣኤዬን ዕርገቴን አላዩም አንተ አይተሃል ተነሣች ዐረገች ብለህ ንገራቸው ብላ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው። ከዚህ በኋላ ሂዶ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ? አላቸው። አግኝተን ቀበርናት አሉት። ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተዉ ይህ ነገር አይመስለኝም አላቸው። ቅዱስ ጴጥሮስም መልሶ አንተ እንጅ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራልህ ብሎ ተቆጥቶ ወደ መቃብሩ ሂዶ ቢከፍተው አጣት። ደንግጦ ቆመ ሐዋርያው ቶማስም አታምኑኝም ብየ እንጅ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች አላቸው። የያዘውንም ሰበን ሰጣቸው። ለበረከትም ተካፍለውታል።
"…በዓመቱ ሐዋርያት ቅዱስ ቶማስ ትንሣኤሽን ዕርገትሽን ዓይቶ እኛ ሳናይ ብለው ጾም ጀመሩ በ16ኛው ቀን እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ካህን፣ ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ በዚያው ላይ ቀድሶ አቁርቧቸዋል። ቤተክርስቲያንም ይህንን መታሰቢያ አድርጋ በየዓመቱ ታከብረዋለች።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@mahiberekidusan | 977 |
| 17 | #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_ዘለዓለም_ሥላሴ_አሜን።
#እንኳን_ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_ጾመ_ፍልሰታ የፍቺ በዓል ና ለእመቤታችን የትንሳኤና የዕርገት በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ!
በአጽናፈ ዓለም የምትኖሩ/የምትገኙ ውድ የክርስትና እምነት ተከታዮች የተዋህዶ ልጆች ክርስቲያናዊ ሰላምታችን በቅዱስ እግዚአብሔር ስም ይድረሳችሁ፡፡
#የእመቤታችን_ትንሣኤና_ዕርገት_
ነሐሴ 16 ቀን የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ያረገበት ዕለት ነው።
#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ_አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው፡፡
እመቤታችን እመ አምላክ በስዕለት የተወለደች ፣ በጸጋ የተሞላች፣ ባለሟልነትን የተጎናጸፈች፣አምላክን በአጭር ቁመት ፣በጠባብ ደረት የወሰነች፣የመለኮቱ እሳትነት ስጋዋን ሳያቃጥላት አምላክ ፈጣሪዋን ጸንሳ የወለደች ፣ በግብፅ በርሃ በስደት የተንከራተተች፣ በእውነቱ የህይወትን ምግብ አዝላ ስለእኛ የተራበች ፣የተጠማች፣ ከመዓር ከስኳር የሚጥም ጡቶቿን ያጠባችው ልጇ በቀራኒዮ ኮረብታ ተሰቅሎ ሲሞት መሪር እንባን ያለቀሰች፣ ለቅዱሳን ስደትን ለመባረክ ምሳሌ በመሆን የተጓዘች የተንገላታች ... ድንቅ ዘለዓለማዊ እናት ነች። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በቅዳሜ አርጋኖን ሶስቱ ያልተከፈቱ ደጆች ይልና ። ያብራራል ። አንድም በድንግልና መጽነሷን፦ ድንግልናዋን ሳይለውጠው እግዚአብሔር ወልድ በግብረ መንፈስ ቅዱስ የመጸነሱ፤ በሁለተኛ ደረጃ ክርስቶስን በምትወልድበት ጊዜ የሴቶች ልማድ ሳያገኛት በጥበበ እግዚአብሔር መውለዷ፤ በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ ከወለደችው በኋላ ማህተመ ድንግልናዋ አልተፈታም። እመቤታችን ዘላለማዊ ድንግል ናት። የስጋ ብቻ ያይደለ የሀሳብም ድንግል ናት።
አጠር ባለ አገላለጽ አምላክን ከመውለዷ በፊት፣ አምላክን በምትወልድበት ጊዜ እና አምላክን ከወለደች በኋላ ፍጹም ዘላለማዊ ድንግል መሆኗን ሊቁ ያስረዳል ። እመቤታችን ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ከዚህ አለም ድካም አርፋ ወደ ልጇ ተጠርታ ሄዳለች።
ወላድተ አምላክ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት" ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ፡፡
አይሁድም ከተማከሩ በኋላ ከመካከላቸውም ብርቱ ጉልበተኛ ሰው የሆነው #ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ሥጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ሥጋዋ ያለበትን የአልጋ ሸንኮር ሲይዝ በመልአከ እግዚአብሔር እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፤ ከዚህ የጥፋቱ ሥራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች፡፡
ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የተቀደሰ ሥጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነሱም የእመቤታችን ሥጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ፡፡
ከሁለተኛ ሱባኤ ቆይታቸው በኋላ በአሥራ አራተኛ ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌቴ ሴማኔ ቀበሯት፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› › ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት ‹‹ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ /መዝ. 131፥8/፡፡
የእመቤታችንን ቅድስት ሥጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመናሰረገላ ተጭኖ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ አገኛት። ለማረጓ ምልክት ይሆን ዘንድ ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን (የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ፡፡ ለወንድሞቹ ለቅዱሳን ሐዋርያት ያየውን ምስጢር/የተመለከተውን ድንቅ ተዓምር/የወላድተ አምላክን ዕርገት ነገራቸው፡፡
እመቤታችን ለበረከት የሰጠችውንም ሰበን አሳያቸውና አካፈላቸው ፤ ሐዋርያት ‹ ‹ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል› › ብለው በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡
በንጽህና፣ በፍጹም እምነት ፣በትኅትና የያዙት በተስፋ የጠበቁት በአንድነት ወደ እግዚአብሔር ያቀረቡት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1-16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ሥርዐት ሠራችልን፡፡
በቅዱሳን አበው በነቢያትና በሐዋርያት በቅዱሳን ሁሉ መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም በሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፤ ሆነናልም፡፡ ለቅዱሳን ሐዋርያት ትንሳኤዋን ፣ ዕርገቷን እንደገለጸችላቸው ለእኛም ምስጢርን ፣ እውቀትን ታድለን ። ትግለጽልን ። የአመት ሰው ይበለን። መልካም በዓል
ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከወላድተ አምላክ በረከት፣ረድኤት ፍቅር፣ምልጃና ጸሎት ተካፋዮች ያድርገን፡፡
አሜን!
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን🙏🙏🙏
#ለወዳጅዎ_ዘመድ_ ፣_ለተዋህዶ_ልጆች #ሼር_ያድርጉ!
💚 @mahiberekidusan 💚
💛 @mahiberekidusan 💛
❤️ @mahiberekidusan ❤ | 869 |
| 18 | የሐሙስ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
#ሼር-ያድርጉ
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan | 526 |
| 19 | #በስመ-አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
መንፈሳዊ ግጥም
#ደብረ_ታቦር
ከደብሮች ሁሉ ልቀሽ
እውነት ብርሃንን አጥልቀሽ
ተንቀሽ የነበርሽ ተራራ
አንቺ የምሥጢር ሥፍራ
የመለኮት ብርሃን በር
የሥሉስ ቅዱስ ምሥጢር
ልቆ የታየብሽ መንደር
ደብረ ታቦር!!!
ከአድማሳት ከፍ ከፍ ብሎ
የስምሽ ተረፈ ውሉ
የተዘከረው በዓለሙ
ምን ይሆን ወርቅ ሰሙ?
ምን አገኘሽ ያኔ ታቦር
እንዲያ ተከፍቶ የብርሃንሽ በር
የክብሩ ግርማ የዋጠሽ
እኮ ማን ነው የረገጠሽ?
ጌታሽ ነው አሉ ስሰማ
ከተራራሽ አናት ማማ
የብርሃን ጉንጉን ሸማ
ያጎናፀፈሽ በግርማ
ግሩም እኮ ነው!
ከተራሮች አንቺን መርጦ
ከነአባቱ ተገልጦ
ደጅሽን ሳይንቅ ማክበሩ
እንዴት እንዴት ይሆን ምሥጢሩ?
ይህንንም ደግሞ ዳዊት
ተናግሯል አሉ በትንቢት
ታቦር ወአርሞንኤም በሚል ቅኔ
በስሙ ተደሰቱ ያኔ
እያለ ዘመረ በክብር
የዚህችን ተራራ ምሥጢር
ያ ልበ አምላክ ዳዊት
የተናገረው ትንቢት
ለካ ይህ ኖሯል ግቡ
ደጅሽ በብርሃን ማበቡ
ኧረግ! አንቺስ ታድለሻል
የማይቻለውን ችለሻል
እሳተ መለኮትን ይዘሻል
ለመሆኑ እንዴት ቻልሽው ታቦር
ያን እውነተኛ ፍቅር?
ከመንበሩ የሳበው ንጉሥ
በብርሃን ሠረገላው ሲፈስ
መሠረትሽ ሳይናጋ
ባለበት ቆሞ የረጋ
ምን ይሆን ምሥጢሩ የፅናትሽ
በፊቱ ቆመሽ መታየትሽ?
ልብሱ ነጭ ሆኖ በረድ
አብም ከሰማይ ሲወርድ
ዙሪያው በክብር ደመና
ተመልቶ በብርሃን ፋና
ሙሴ ከመቃብሩ ተጠርቶ
ኤልያስ ከብሄረ ሕያዋን መጥቶ
በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው
ሲወያዩ ላስተዋለው
ምን ይመስል ይሆን ገጹ?
የብርሃን መለኮት መገለጹ
ደግሞ የሐዋርያቱ
የእነዚያ የሦስቱ
ሲጋልቡ ርደው
እንደ ቄጤማ ወርደው
ከሰሩ የተነጠፉቱ
ምንድን ይሆን ምክንያቱ?
ጴጥሮሰማ ተሽብሮ
ናላው በድንጋጤ ዞሮ
ለእያንዳንዳችሁ በጋራ
ሦስት ዳሶችን እንስራ
ብሎ በዚያች የብርሃን እልፍኝ
የዘለዓለም ደስታን ሊያገኝ
አስቦ በቅጽበት መመኘቱ
ገርሞትም አይደል ክስተቱ
የብርሃን ፀዳል ድምቀቱ?
እኮ እንደምን አይገርመው
ሙሴና ኤልያስ ቆመው
ክብሩን ሲያውጁ እያዩ
ማነው የሙሴን አምላክ ሙሴ ባዩ?
ሲል ሙሴ ባሕር ከፋዩ
የኤልያስንስ ክብር ጌታ
አውርደውት ከሰው ተርታ
ኤልያስ ባዮቹ እነማን ናቸው?
ሲል ኤልያስ ገርሟቸው
ይህን ሲሰሙ ሐዋርያቱ
በድንጋጤ ሲመቱ
ደግሞ ወርዶ አባቱ
ልጄን ስሙት በማለቱ
በፍርሃት ማዕበል ሲንገላቱ
ይህ ሁሉ ምስጢር መታየቱ
በአንቺም አይደል ታቦር
መገለጹ የሦስትነት ምስጢር
ጥንትስ ታሪክሽ ተዘክሮ
መቼ ያልቅና ተነግሮ
እንዲያው ድንቅ
እንበል እንጂ ድንቅ ድንቅ!
የብርሃንሽ ሰንደቅ
ከአድማሳት ልቆ ሲደምቅ
ክብር እንበልሽ ክብር!ክብር!
አንቺ እውነተኛ የምስጢር በር
የሥሉስ ቅዱስ ነገር
የተገለጸብሽ መንደር
ደብረ ታቦር!!!
ያበራሽ ይብራ ስሙ ይግነን
ዛሬም ለእኛ ብርሃን ይሁነን
ገኖ ያግነን በፈቃዱ
በራ ይሁንልን መንገዱ
ክብሩም ከፍ ከፍ ወደ ላይ
ከሰማየ ሰማያት በላይ
እንዲሁም በምድር በቀላይ
የአምላካችን አዶናይ
ክብርሽ ዛሬም ነገ ይነገር
መሆንሽ እውነተኛ የብርሃን በር
የሥሉስ ቅዱስ ምስጢር
የተገለጠብሽ መንደር ደብረ ታቦር!!!
ልዑል አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር በብርሃነ መለኮቱ ዘመናችንን ፣ ህይወታችንን ያብራልን። መልካም በዓል 🙏🙏🙏
ወስበሐት ለእግዚአብሔር።
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan | 934 |
| 20 | የረቡዕ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
#ሼር-ያድርጉ
@mahiberekidusan
@mahiberekiduaan | 367 |