fa
Feedback
APOSTLE TIGIST MEDHIN 1000013646655 🤝እጃችንን ለበጎ ሥራ እናበርታ!!

APOSTLE TIGIST MEDHIN 1000013646655 🤝እጃችንን ለበጎ ሥራ እናበርታ!!

رفتن به کانال در Telegram

God is Good all the Time.

نمایش بیشتر
962
مشترکین
+224 ساؚت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+630 عوز
آرشیو پست ها
🌼2019 የሞገስ ዓመት ይሁንሎት!🌼 “እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።”ሐ.ሥ 2፥47 🙌ዕለት በዕለት የምስጋና 🥰በህዝብ ሁሉ ፊት የሞገስ 🥰ዕለት በዕለት የሚድኑ የሚበዙበት ዓመት ይሁን። ❤አፖስትል ቲጂ 🤝ከዓይንሀቆሬ

አስጥሎ ያልጣለን ፥ በኪዳኑ ታማኝ ዘመናችንን በመልካም የያዘ አምላካችን እግዚአብሔር ይመስገን። 5/13/2018 ዓ.ም የዕለቱ መልዕክት እነሆ፦ 🙏❤🙏 በፍለጋው ውስጥ እንኖራለን፥ የፍሬ ዘመን ይሆንልናል።🙏❤🙏 እግዚአብሔርም በጎ ነገርን ይሰጣል፥ ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች። ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፥ ፍለጋውንም በመንገድ ውስጥ ያኖራል። መዝ 85:12-13 🙏 በእግዚአብሔር በጎነት መሄድ በፍሬ መገለጥ ይሆናል። “ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ።” ሚክ 4፥2 🙏በእግዚአብሔር መንገድ ሄደው ከበጎነት የሚጎድል የለም። “የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።” 1ኛ ጴጥ 2፥21 🙏 ፍለጋውን ተከትለን በመከራ ሁሉ ድል እናደርጋለን፤ ብቻችን የማይተወን ጌታ ኃይል ይሆነናል። 🥰 በእግዚአብሔር ቃል ዘመኑን መዋጀት ይሁንልን፤ ከዓመቱ ጋር የመከራ ምዕራፋችን ይለቅ። 🙌መልካም ቀን!!

ቀኑን በቀደመው፥ ዘመኑን በዋጀው በእግዚአብሔር ቃል ተይዘናል፤ እርሱንም ይዘናል። ሁሉ የሚሆነው እንደ ቃሉ ነው። ክብር ሁሉ ለቃሉ ታማኝ ለሆነው አምላክ፥ ሰላም ለእኛ ለሰው ልጆች። 02/13/2018 ዓ.ም የዕለቱ መልእክት እነሆ፦ 🙏❤🙏 በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛችን ነው።🙏❤🙏 “በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፥ ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል።”ራእይ 7፥17 🥰 እረኛችን በጉ ነው። 🥰 የሕይወት መሪያችን ነው። 🥰 እንባን ሁሉ አባሽ ነው። 🤝ከእረኛው ጋር ነን ክፉ አይነካንም፤ እንደ ቃሉ የአልቃሾች እንባ ይታበሳል። 🙌 ተባረኩ፤ መልካም ቀን!!

❤ 2019 ዓ.ም እንዋጅ❤ የተወደዳችሁ ፥ነገ አይቀርም!! 🥰ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!!
❤ 2019 ዓ.ም እንዋጅ❤ የተወደዳችሁ ፥ነገ አይቀርም!! 🥰ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!!

🤲🤲🤲 39ኛ ቀን 🤲🤲🤲 አስጠብቆ የማይቀር፣ ተፈልጎ የማይጠፋ፣ እንደተናገረው የሚያደርግ ፤ ቃል ኪዳንን የማያጥፍ ታማኝ አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን። ከብር ሁሉ ለእርሱ ፥ ሰላምና ጸጋ ለእኛ ለሰው ልጆች ይሁን። 29/12/2019 ዓ.ም የዕለቱ መልእክት እነሆ፦ 🙏❤🙏እግዚአብሔር ጸሎትን ይሰማል!!🙏❤🙏 “ጸሎቴን ያልከለከለኝ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን።” መዝ 66፥20 🤲 እግዚአብሔር ጸሎትን፥ ይሰማል። “እግዚአብሔርም አለው፦ በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፤ ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፤ ዓይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ።”1ኛ ነገ 9፥3 🧎‍♂️ጸሎትና ልመናን ሲሰማ እንደ ፍለጋችን ያደርጋል። “ተመልሰህ የሕዝቤን አለቃ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ እነሆ፥ እፈውስሃለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ።”2ኛ ነገ 20፥5 🧎 እግዚአብሔር ጸሎትና እንባን ሲያይ፥ እንደ ፍለጋችን ይፈውሳል። “ሂድ፥ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ በዕድሜህ ላይ አሥራ አምስት ዓመት አጨምራለሁ።” ኢሳ 38፥5 🧎‍♂️እንደ ጸሎታችን፥ የተቆረጠን ይቀጥላል፤ ዕድሜ ይጨምራል። “መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።” ሉቃስ 1፥13 🧎ጸሎትና ፍርሃት አብሮ አይሄድም፥ ጸሎት ለተረሳው ጥያቄ ሁሉ መልስ ይሆናል። “ቆርኔሌዎስ ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸሎትህ ተሰማ ምጽዋትህም ታሰበ።” ሐ. ሥራ 10፥31 🧎‍♂️እግዚአብሔር ጸሎትን ለመታሰቢያ ያደርጋል፤ እግዚአብሔር ይጎበኘናል። ❤እግዚአብሔር እንባን ያያል ፣የተቆረጠን ይቀጥላል፣የተረሳን ጥያቄ ይመልሳል፣ 🧎‍♂️የቀደመውም፥ የአሁኑም ጸሎታችን🧎በእርሱ ዘንድ ይታሰባል። መልሱ ያገኘናል። 🤲🤲🤲 🧎‍♂️መልካም🧎ፆምና ጸሎት 🧎‍♂️ 🙌መልካም ቀን 🤝ሁላችሁንም ውድድድ❤❤❤

38ኛ ቀን በእርሱ የተጀመረ ነገር አይቆምም፥ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ እንደ ቃሉ ነው። ለእርሱ ክብር ይሁን ለእኛ ሠላምና ጸጋ ይብዛልን። 28/12/2018 የዕለቱ መልእክት እነሆ፦ 🙏የተከተለንን አስጠንቅቆ ያሻግረናል!!🙏 “እግዚአብሔርም ወደ ሶርያው ሰው ወደ ላባ በሌሊት ሕልም መጥቶ። ያዕቆብን በክፉ ነገር እንዳትናገረው ተጠንቀቅ አለው።”ዘፍ 31፥24 🤔 ላባ ከቤቱ ሲነሳም ሆነ ያዕቆብን ተከትሎ ድንኳን ተክሎ ሲያድር ያሰበው በፍጹም ሊሸልመው፣ ሊስመው፣በከበሮ ሊሸኘው፣ በፍቅር ሊሰናበተው አልነበረም። 👉የላባን 🤔አሳብ ያስቀየረው ሌሊት ከያዕቆብ አምላክ ከእግዚአብሔር ወደ ላባ የመጣው የእግዚአብሔር ድምጽ ነው። 🙏እግዚአብሔር በዓመቱ ፍፃሜ እንደ ቃሉ እንዲህ ያደርግልናል።🙏 👉 ሲነሱ ያሰቡብንን ክፉ አሳብ ፥ ሲደርሱን ያስቀይራል። 👉ድርጊትን ብቻ ሳይሆን ቃላቸውም ክፉ እንዳይሆንብን ያስጠነቅቅልናል። ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ። ሉቃ 22:31-32 👉 እምነታችን እንዳይጠፋ እስከ ዛሬ ተጠንቅቆልናል፥ ዛሬም ይረዳናል፤ እኛም ሌሎችን እናጽና። ❤በርግጥ ጌታን ከራሳችን በላይ እናምነዋለን። ለክፉ አሳልፎ አይሰጠንም። ያስመልጠናል፣ ያሻግረናል፥ ወደ አገራችን በሰላም እንደርሳለን። 🤗 መልካም ፆምና 🧎‍♂️ ጸሎት 🧎‍♂️ አዲስ አበባ ከኖሩ አርብ አብረን እንጸልይ!! 👨‍👩‍👧 ሁላችሁንም ❤ው❤ድ❤ድ❤ድ❤

37ኛ ቀን በእርሱ የተጀመረ ነገር አይቆምም፥ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ እንደ ቃሉ ነው። ለእርሱ ክብር ይሁን ለእኛ ሠላምና ጸጋ ይብዛልን። 27/12/2018 የዕለቱ መልእክት እነሆ፦ 🙏የተከተለንን አስጠንቅቆ ያሻግረናል!!🙏 “እግዚአብሔርም ወደ ሶርያው ሰው ወደ ላባ በሌሊት ሕልም መጥቶ። ያዕቆብን በክፉ ነገር እንዳትናገረው ተጠንቀቅ አለው።”ዘፍ 31፥24 🤔 ላባ ከቤቱ ሲነሳም ሆነ ያዕቆብን ተከትሎ ድንኳን ተክሎ ሲያድር ያሰበው በፍጹም ሊሸልመው፣ ሊስመው፣በከበሮ ሊሸኘው፣ በፍቅር ሊሰናበተው አልነበረም። 👉የላባን 🤔አሳብ ያስቀየረው ሌሊት ከያዕቆብ አምላክ ከእግዚአብሔር ወደ ላባ የመጣው የእግዚአብሔር ድምጽ ነው። 🙏እግዚአብሔር በዓመቱ ፍፃሜ እንደ ቃሉ እንዲህ ያደርግልናል።🙏 👉 ሲነሱ ያሰቡብንን ክፉ አሳብ ፥ ሲደርሱን ያስቀይራል። 👉ድርጊትን ብቻ ሳይሆን ቃላቸውም ክፉ እንዳይሆንብን ያስጠነቅቅልናል። ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ። ሉቃ 22:31-32 👉 እምነታችን እንዳይጠፋ እስከ ዛሬ ተጠንቅቆልናል፥ ዛሬም ይረዳናል፤ እኛም ሌሎችን እናጽና። ❤በርግጥ ጌታን ከራሳችን በላይ እናምነዋለን። ለክፉ አሳልፎ አይሰጠንም። ያስመልጠናል፣ ያሻግረናል፥ ወደ አገራችን በሰላም እንደርሳለን። 🤗 መልካም ፆምና 🧎‍♂️ ጸሎት 🧎‍♂️ አዲስ አበባ ከኖሩ አርብ አብረን እንጸልይ!! 👨‍👩‍👧 ሁላችሁንም ❤ው❤ድ❤ድ❤ድ❤

ዛሬ ማለዳ 1:00 ይከታተሉ፥ ይባረኩበት።
ዛሬ ማለዳ 1:00 ይከታተሉ፥ ይባረኩበት።

20ኛው ቀን ጸሎትን የሚሰማ፥ በመልስ የሚጎበኘን አምላካችን እግዚአብሔር ክብር ይሁንለት። ሰላምና ጸጋ ለእኛ ለሰው ልጆች ይብዛልን 20/12/2018 ዓ.ም የዕለቱ መልእክት እነሆ፦ “እኔ እንደ ቃልህ አድርጌልሃለሁ፤ እነሆ፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።”1ኛ ነገ 3፥12 “መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።” ሉቃስ 1፥13 👉 እንደ ሰሎሞን በትክክለኛው ሰዓት ትክክለኛ ጸሎት መጸለይ ይሁንልን። 🤲 የእኛ ጸሎት የእርሱ ደስታ ይሁን። 🧎‍♂️ጸሎታችን ሲሰማ እንደ ዘካሪያስ ባናምንም በጊዜው ይሆናል። 🤲 እግዚአብሔር በቤታችን ስያሜውን ጭምር ባገኘ በረከት ያግኘን። 🤝የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በርግጥም እንደ ቃሉ ጸሎታችንን ይመልሳል። 🧎 መልካም ፆምና ጸሎት 👨‍👩‍👧 ሁላችሁንም ውድድድ❤❤❤

28ኛ ቀን ይህ ለምን ሆነ?🤔 አይባልም። እንዴት ይሆናልም አንልም። እግዚአብሔር ሥራው ግሩም ነው፥ ከአሳባችን በላይ ነው። ሁሉን ስለሚችለው አምላካችን ክብር ይሁን። ለእኛ ለሰው ልጆች ሰላም። 18/12/2018 ዓ.ም የዕለቱ መልእክት እነሆ፦ 🙏❤🙏ጥሶ መውጣት ይሆናል!!🙏❤🙏 በመውለጃዋም ጊዜ እነሆ መንታ ልጆች በሆድዋ ነበሩ። ስትወልድም አንዱ እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም ቀይ ፈትል ወስዳ በእጁ አሰረች፦ ይህ መጀመሪያ ይወጣል አለች። እንዲህም ሆነ፤ እጁን በመለሰ ጊዜ እነሆ ወንድሙ ወጣ፤ እርስዋም፦ ለምን ጥስህ ወጣህ? አለች፤ ስሙንም ፋሬስ ብላ ጠራችው። ከእርሱም በኋላ ቀይ ፈትል በእጁ ያለበት ወንድሙ ወጣ፤ ስሙም ዛራ ተባለ። ዘፍ 38:27-30 🤲 እግዚአብሔር እንደ ቃሉና እንደ ፈቃዱ ከቀደሙት ያስቀድማችሁ። 🤔 ቃል እያላችሁ የቀደመውን፣ በር የዘጋባችሁን በችሎታው ገለል አድርጎ ያስቀድማችሁ። 👉 ይህ ዓመት ሳያልቅ ሰዎች እንዴት? ለምን? በምን መንገድ? የሚሉትን መቅድም ያድርግላችሁ። 🧎‍♂️መልካም ፆምና ጸሎት 🤲🤲🤲 👨‍👩‍👧 ሁላችሁንም ❤ው❤ድ❤ድ❤ 🙌 ተባረኩ🙌🙌🙌

25ኛው ቀን አምናችሁ የማይከዳ፣ ተጠግታችሁ የማይወጋ፣ ሁሉን የሚያስጠልል፥ ኪዳን የሚገባ ፥ለቃሉም ታማኝ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። ክብር ሁሉ ለልዑሉ አምላካችን ሰላምና ጸጋ ለእኛ ለሰው ልጆች ይብዛልን። 15/12/2018 ዓ.ም የዕለቱ መልእክት እነሆ፦ 🙏❤🙏ኢየሱስ ታማኝ ነው!!🙏❤🙏 “ከእነርሱ ጋር በዓለም ሳለሁ የሰጠኸኝን በስምህ እኔ እጠብቃቸው ነበር፤ ጠበቅኋቸውም መጽሐፉም እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።”ዮሐ 17፥12 🥰ጠብቆናል ❤ ይጠብቀናልም። 🤝መልካም 🤲ፆምና 🧎‍♂️ ጸሎት🤲

21ኛ ቀን ፆምና ጸሎት ጸሎትን የሚሰማ፥ ሰምቶ የሚመልስ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። ክብር ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ሰላምና ጸጋ ለእኛ ለሰው ልጆች ይሁን! 11/12/2018 ዓ.ም የዕለቱ መልእክት እነሆ፦ 🤲🧎🤲 በጸሎት እንትጋ እንጂ፥ይሰማናል፤ይመልስልናልም!!🤲🧎🤲 “ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ፤” ቆላ 4፥2 🤲 ከምስጋና ጋር እንጸልይ፦ ምሥጋና ለእርሱ ዘወትር ይገባዋል። 🤲 ጸሎትን በንቃት፦እርሱ እንደሚፈልገው፥ ለእርሱ ብቻ እንንቃ። 🤲 ለእርሱ እንደሚገባ መትጋት ፦ሳንታክት፣ ሳናቋርጥ እንጸልይ። 👨‍👩‍👧 ተወዳጆች 🤝በምስጋ፣ በንቃት፣ በትጋት እንጸልይ፤ ይሰማናል፥ይመልስልናልም። 🤲 መልካም 🧎‍♂️ፆምና 🧎‍♂️ጸሎት ቀን ይሁንልን!! 🤝 ሁላችሁንም 🥰ው🥰ድ🥰ድ🙌🙌🙌