cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አቡ መርየም አዳማ

هدفنا الذب عن السنة..................... ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች የሚሰራጭበት ቻናል ነው። በተጨማሪም ተውሂድንና ሽርክን እንዲሁም ሱናንና ቢድአን እንዲሁም የቢድአ ሰዎችን ለሰዎች በፁሁፍና በሙሀደራ መልክ ግልፅ ማድረግ https://telegram.me/abumerymadama

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
742
مشترکین
-224 ساعت
-37 روز
+1130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

🔷 ከመልካም ነገር ምንንም አትናቅ قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم – : " لا تحقرن من المعروف شيئا " رواه مسلم 🔹 " ከመልካም ነገር ምንን በትንሽ አይን አትይ " በዚህ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ኡመታቸውን ወደ መልካም ነገር ሲያመላክቱ የመልካም ነገር ትንሽ እንደሌለው በማመላከት ነው ። ገንዘብ የማይከፈልበት መልካም ነገር ሞልቷል ። ጉልበት የማይፈልግ መልካም ነገር ሞልቷል ። ብዙ ኪታብ መቅራት የማይጠይቅ መልካም ነገር ሞልቷል ። ለወነድም ፈገግ ማለት ፣ መልካም ንግግር ፣ ከመንገድ ላይ ቆሻሻ ማስወገድ ፣ ምላስን ዚክር ማስለመድና በማንኛውም ሁኔታ ዚክር ማድረግ ፣ ቤት ስትገባ ፈገግ ብለህ ማናገር ፣ ልጆችህን መሳም ፣ ምግብ ሲበላ ባለቤትህን ማጉረስና የመሳሰሉ የመሳሰሉ በቀላሉ የሚሰሩ መልካም ነገሮች እያሉ የመልካም ስራ ድሀ መሆን የለብንም ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👉 ከተውሒድ ዳዒነት ወደ ባህል አስተዋዋቂነት ዝቅጠት በ30 የእንቅልፍ ክኒን ደንዝዘው ከሱፍይ ሙሪድ የባሱት በፊት ወደ ተውሒድ እየተጣሩ ሽርክን በዝርዝር ያስጠነቅቁ የነበሩ የነሲሓ ዱዓቶች ከዝቅታቸው የተነሳ የዳዕዋው ብርሀን ጠፍቶባቸው ወደ ባህል አስተዋዋቂነት ተሸጋግረዋል ። አምና አንዱ ዳዒያቸው በዒደል አድሓ የጉራጌን ባህል ሲያስተዋውቅ ነበር ። ዘንድሮ ደግሞ ሌላኛው የስልጤ ባህል አስተዋውቆላቸዋል ። በጣም የሚገርመው የውመንነሕር የእርድ ቀን በጉራጌም በስልጤም ከዑድሒያ እርድ ጋር በተገናኘ ሽርክ ተንሰራፍቶ ነው ያለው ። በአብዛኛው ማህበረሰቡ በሬ ወይም ወይፈን ነው የሚያርደው ። የሚታረደው ከብት ለእርድ ሲቀርብ አብዛኛው ቦታ ሁሉም ተሰብስበው ሽማግሌዎች የከብቱን ሻኛ እያሻሹ ዱዓእ ያደርጋሉ ። ዱዓኡ አላህን በመለመን ብቻ ቢሆን ኖሮ በዛ መልኩ መደረጉ ቢዳዓ ነው እንል ነበር ። ነገር ግን የሚለመነው በየአካባቢው የሚታመንበት ሸይኽ ወይም ወልይ ነው ። እንዲህ አይነት ሙንከር በስፋት በተንሰራፋበት ሀገር ላይ ነው የነሲሓ ዳዒዮች ባጀት ተመድቦላቸው ባህል የሚያስተዋዉቁት ። የዘንድሮ አስተዋዋቂ እንሰት ወደ ቆጮነት እንዴት እንደሚቀየርና አዘገጃጀቱን ነበር ያስተዋወቀላቸው ።‼ ከወረዱ አይቀር መዝቀጥ እንዲህ ነው ። ቁርኣንና ሐዲስ ለትውልድ አደርሳለሁ ወደ ተውሒድ እጣራለሁ ከሽርክ አስጠነቅቃለሁ የሚል አካል ገጠር ገብቶ ስለቆጮ አዘገጃጀት ለከተማው ማህበረሰብ በዒድ ቀን መዝናኛ ብሎ ያቀርባል ? ይህ ነው የሰለፎችን መንገድ የመተው መጨረሻው ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

Photo unavailableShow in Telegram
📢 ምዝገባ ጀምረናል 👉 እነሆ ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል ክረምቱን ልዩ በሆነ መልኩ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 9:20 ሰኣት (ቀን ሙሉ) ከሐምሌ 1 እስከ ነሃሴ 30 ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ ምዝገባ መጀመሩን በታላቅ ደስታ ይገልፃል!! የሚሰጡ የሸሪዓ ትምህርቶች 🔹ቁርኣን ከቃዒደቱ ኑራኒያ ጀምሮ 🔹ዐቂዳ (እምነት ነክ ስለ ተውሂድ…) 🔹ፊቅህ (ስለ ጡሃራ፣ ሶላት…) 🔹ሲራ   (የነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እና የሶሃቦችን ታሪክ…) 🔹ነቢያዊ ሐዲሶች… 🔹አደብ (ኢስላማዊ ስርኣት…) ✅ በፍጥነት በማስመዝገብ ልጆች በጊዜያቸው እንዲጠቀሙ ያድርጉ!! 🕰 የምዝገባ ቀን:- ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 28 ሰኣት:- በሁሉም ቀናት ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 ✅ ልብ ይበሉ! ሸሪዓን በጠበቀ መልኩ ሴቶችን በሴት ወንዶችን በወንድ ኡስታዞች እናስተምራለን 🏢 ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል አድራሻ:- አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊትለፊት ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን መንገድ ከድልዲዩ በስተቀኝ እንገኛለን 📞Tel:+251920908031 የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://t.me/DarASSunnah1444 https://t.me/DarASSunnah1444
نمایش همه...
🟢 ከሙብተዲዕ ጋር የሚቀመጥና የሚርመጠመጥን ተጠንቀቁ። 👉 ስሜት ተከታዮች እና አይሁዶች 👉 ቢድዓን አቃሎ መየትና መደመር 👉 መዳን የፈለገ ከእሳት ዳርቻ ይራቅ 👌ሙመይዓዎች በዚህ የሰለፎች አቋም ይመዘኑ 🔊አሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን 📚ከሸርህ አሱነህ ደርስ https://t.me/SHERH_ASSUNAH
نمایش همه...
شرح_شرح_السنة_للبربهاري_الشيخ_صالح_بن_فوزان_الفوزان_الدرس_22_1.mp39.05 KB
            አስደሳች ዜና بسم الله الرحمن الرحيم በመኣከላዊ ኢትዮጲያ በስልጤ ዞን በሁልባራግ ወረዳ ዋና ከተማ ኬራቴ ቀበሌ  የነበረው የኡስታዝ ኢዘዲን ስራጅ መድረሳ ከዚ በፊት ከነበረው በተሻላ መልኩ ኢንደሚቀራ ስናሳሲብ በታላቅ ደስታ ነው ። የሚቀሩ ኪታቦች ዝርዝር ኢንደሚከተለው ነው። 1 ኪታቡ  ተውሂድ የአብዲል ወሃብ 2 ኡሱሉል ኢማን የአብዲል ወሃብ 3 ኩን ሰለፊየን አለል ጃደቲ 4  ሪያዱ ሳሊሂን የነወዊ 5  ቡሉጉል መራም የብኑ ሀጀር 6  ተንቢሃት 7   ኢርሻድ የፈውዛን 8   ፈትሁል መጂድ የዱወይሺ 9  ኢጅቲማኡል ጁዩሽ የብኑል ቀይም 10  ረውደቱል አንዋር (ሲራ) ኢነዚህ የኪታብ ዝርዝሮች በቀጣይ አመት በአረቢኛ አቆጣጠር 1446 ዓ/ሒ ሙሀረም አንድ ነው ሚጀመሩት ።           ማሳሳቢያ 1 ማነኛውም ደረሳ(ተማሪ) መታወቂያ ካርድ ሰይዝ በይመጣ ተመራጭ ነው በተለይ አቂመ አዳም የደረሰ ደረሳ ።
نمایش همه...
✍በጋብቻ ዙሪያ የተደረገ ዳሰሳ 🎙 በኡስታዝ አቡ ፊርዶወስ አላህ ይጠብቃው! 🗒 ዛሬ እሁድ ምሽት ሰኔ  2016 E.C በአልፋሩቅ የሰለፍዮች መድረሳ የተደረገ ሙሐደራ ➴➘➴➘ https://t.me/alfarukmedrasa
نمایش همه...
4_6035222576152712112.mp313.55 MB
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ የዙልሂጃ ወር በማግባት እና በአረፋ ምክኒያት ተቋርጦ የነበረው የኢብኑ ተይሚያ መስጂድ ደርስ ከነገ ከሰኞ ሰኔ 17 ጀምሮ የሚቀጥል ይሆናል https://t.me/abuabdurahmen
نمایش همه...
📝Abu abdurahman«አብዱልቃዲር ኢብኑ ሐሰን»

هدفنا الذب عن السنة ይህ ቻናል የአቡ አብዱረህማን አብዱል ቃድር ሀሰን ደርሶች ሙሓደራዎች እና ጠቃሚ የሆኑ ፈዋኢዶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው ይቀላቀሉ ➘➘➘➘➘➘➘➘

https://t.me/abuabdurahmen

https://t.me/abuabdurahmen

https://t.me/abuabdurahmen

ከአሉ ተባለ ወሬ ተከልክለናልና እንጠንቀቅ!! ——— አሎባልታ ወሬ ብዙዎችን በተለያየ መንገድ አክስሯል!! አሉ ተባለ ወሬ በማህበረሰቡ ላይ ጉዳቱና መዘዙ የከፋ ስለሆነ ሸሪዓችን አጥብቆ ከልክሏል። ከወርራድ አስሰቀፊይ ተይዞ እንዲህ አለ:- ሙዓዊየህ ወደ ሙጊረህ ቢን ሹዕበህ እንዲህ በማለት ፃፈ፣ ከአላህ መልክተኛ ﷺ ከሰማሀው ምክር የሆነ ነገር ወደኔ ፃፍልኝ አለው፣ ሹዕበህ ኢብኑ ሙጊረህም እኔ ከመልክተኛው ﷺ የሚከተለውን ሲሉ ሰምቻለሁ በማለት ፃፈለት:- “አላህ ሶስት ነገሮችን ጠልቶላችኋል፣ አሉ ተባለን፣ ገንዘብን ማባከንና ጥያቄ ማብዛትን።” [ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት ሶሂህ ሀዲስ ነው።] በዚህ አሉ ተባለ ወሬ ስንቱ ሱሰኛ ሆነ?! ስንቱ ከቂርኣት (ከደርስ) ርቆ በዚህ ተጠመደ?! ያውም የበለጠ ከማበላሸት ውጭ ሊያስተካክለው በማይችለው ነገር ላይ ገብቶ ስንቱ ተጠመደ?! ስንቱ ነው በእንዲህ ያሉ ወሬዎች ተጠምዶ እውቀት ፈላጊ ምስኪኖችን ከደርስ ያቋረጠው?! ስንቱ ነው በዚህ መልኩ ለቢድዐህ ባለቤቶችና ለአስመሳዮች በር የከፈተው?! ስንቱ ነው በዚህ ተግባር ተዘፍቆ ከድሮ ጀምሮ ወደ ቡድንተኝነት (ተሀዙብ) ያመራው?! እንንቃ!! ጎበዝ ጊዜያችን አናባክን!! ወዳጅነትን አሻክረው በጀመዓ ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ሰበብ ከሚሆኑ ተግባሮች እንራቅ!! አሉ ተባለ ወሬን አጥብቀን ተጠይፈን እንራቅ!! ታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “በአሉ ተባለ ወሬ፣ ጥያቄን በማብዛትና ጊዜን በማባከን መወጠር (ቢዚ busy) መሆን በሰዎች መካከል ከተንሰራፋ በእውነቱ በሽታ ነው!! አላህን ጤነኛነትን እንጠይቀዋለ!!። ይህ ተግባር እንደ ትልቅ አንገብጋቢ ጉዳይ ይሆንበታል፣ በል እንዲያውም አንዳንዴ (በዚህ ተግባር ያልገጠመውን) ጥላትነት ለማይገባው ሁሉ ጥላትነትን ይጠቀማል፣ አለያም ደግሞ (በዚህ ተግባር ስለ ገጠመው ብቻ) ወዳጅነት የማይገባውን ወዳጅ ሊያደርግ ይችላል። ወደዚህ ደረጃ የሚደርሰው፣ ለዚህ እውቀትን ከመፈለግ አርቆ ውጥረት ውስጥ ለከተተው (ለአሉ ባልታ ወሬ) ከሰጠው ትኩረት የተነሳ ነው። እንደ ማስረጃ የሚያቀርበው ደግሞ ሀቅን መርዳት ነው የሚል ነው። እውነታው ግን እንደዛ አይደለም!። ይልቅ እውነታው ነፍስንም ሆነ ሰዎችን በማይመለከታቸው ነገር ውጥረት ውስጥ መክተት ነው!!። የሆነ ወሬ ሳትፈልገው መምጣቱ ግን ውጥረት ውስጥ ሊከትህ አይችልም፣ እንደ ወሬ ማንኛውም ሰው ዘንድ ሳይፈልገውና ለወሬው ቦታ ሰጥቶ ሳይዘጋጅለት ሊመጣው ይችላል ነገር ግን ቦታ አይሰጠውም፣ በሱ ውጥረት ውስጥ አይገባም!!። ትልቅ ትኩረት የሚሰጠውም ጉዳዩ አይሆንም!! ምክንያቱም እውቀት ከመፈለግ ያዘናገዋል፣ ነገሮችንም ያበላሽበታል፣ በማህበረሰቡም ውስጥ የቡድንተኝነትን በር ይከፍታል፣ በዚህ ሰበብም ኡመቱ ለመከፋፈል ይበቃል።” [መጅሙዕ አል-ፈታዋ 26/127] ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) በድጋሚ ተፍሲሩ ጁዝእ ዐማ ገፅ 197 ላይ እንዲህ አሉ:- “በእኛ ላይ ግዴታ የሚሆነው ፊትናዎችን ግልፅ የወጡትንም ይሁን በድብቅ የሚሰራጩትን መጠንቀቅ ነው!!፣ ሰዎችንም ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ ከሚያነሳሱ ነገሮች ሁሉ መራቅ ይጠበቅብናል፣ ሁሌም መረጋጋትን መያዝ ይጠበቅብናል፣ ከአሉ ተባለ ወሬ እና ጥያቄን ከማብዛት መራቅ ግዴታ ይሆንብናል፣ ይህ ነቢዩ ﷺ ከከለከሉት ተግባርም ነው። ስንት (በአሉ ተባለ ወሬ የምትሰራጭ) አንዲት ቃል የሰላ ሰይፍ የማይሰራውን ሰርታለች?!፣ በእኛ ላይ ግዴታ የሚሆነው የሚግባባና የሚዋደድ ማህበረሰብ እንዲሆን ከፊትና እና ፊትናን ከሚቀሰቅስ ነገር መራቅ ነው!!።” ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
نمایش همه...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

ሰለፊዮች ፈተናን ከመካከላቸው እንዴት ሊያርቁ ይችላሉ https://t.me/abuabdurahmen
نمایش همه...
4_6034860862596977459-mc.mp36.87 KB
ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:- 🔹“የዚል ሒጀህ ቀናቶች ልክ እንደ መብረቅ በፍጥነት አለፉ፣ አያሙ ተሽሪቅም ተከተለቻትና ልክ እንደ ዓይን እርግብግብታ የተቆጠሩ ደቂቃዎችን በሚመስሉ መልኩ ፈጥነው አለፉ። ልክ እንደዚሁ ነው እድሜያችን በፍጥነት የሚያበቃው፣ ሞት ድንገት ይመጣናል፣ ልክ ህይወትህ በፍጥነት ከማለፏ የተነሳ ጥፍጥናዋንና ፍጥነቷን ሁሉ እንደ ቅዠት እስክትመለከት ድረስ ይሁንብሃል፣ እንደ ዳመና በፍጥነት ታልፋለች። ብልህ የሆነ ሰው ጊዜውን አላህን በመታዘዝ፣ ወደ አላህ በሚያቃርቡ ነገሮች፣ የአላህን ፀጋ በማስታወስና እርሱንም በማመስገን የተጠቀመው ሰው ነው። አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏልና:- وَمَا بِكُم مِّن نِّعْمَةٍ فَمِنَ اللَّهِ «ማንኛውም በእናንተ ላይ ያለው ፀጋ ከአላህ ነው፡፡» አን-ነህል 53 ከፀጋዎች ሁሉ ትልቁ ፀጋ የተውሒድና የሱንና ፀጋ ነው!! በዚህ ላይ እስከ እለተ ሞት ድረስ መፅናት ነው!! በእርግጥም በሶሂህ አል-ቡኻሪይ ከዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ - ረዲየላሁ ዐንሁ - መርፉዕ የሆነ እንዲህ የሚል ሀዲስ ተዘግቧል:- “በብዙ ሰዎች ላይ ስውር የሆኑባቸው አለያም ሰዎች የዘነጓቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: እነሱም ጤናማነትና ጊዜ ናቸው።” ኢማሙ አህመድ - ረሂመሁላህ - እንዲህ ብለዋል:- “በእስልምና እና በሱና ላይ የሞተ ሰው መልካም በተባለ ነገር ሁሉ ላይ ሆኖ ነው የሞተው።” [አስ-ሰይር] : የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
نمایش همه...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.