fa
Feedback
እግዚአብሔርን ማወቅ

እግዚአብሔርን ማወቅ

رفتن به کانال در Telegram

ሰላምታ በተለዋወጥን ቁጥር ይመስገን ስለምንለው አምላካችንና አባታችን እግዚአብሔር ያለንን ዕውቀት ለማዳበር የሚያግዝ ቻነል ነው፡፡

نمایش بیشتر
964
مشترکین
+124 ساعت
+67 روز
+230 روز
آرشیو پست ها
እግዚአብሔር ያየልን ነገር አለን፡፡   ..የሳኦልም አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፡- ከብላቴኖቹ አንዱን ወስደህ ተነሣ፥ አህዮችንም ለመሻት ሂድ አለው።  በተራራማው ..አገር.. አለፉ፥ አላገኙአቸውም..  ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበረውን ብላቴና፡- አባቴ ስለ አህዮች ማሰብ ትቶ ስለ እኛ እንዳይጨነቅ፥ ና፥ እንመለስ አለው። እርሱም፡- እነሆ፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በዚህች ከተማ አለ፤ እርሱም የተከበረ ሰው ነው፥ የሚናገረውም ሁሉ በእውነት ይፈጸማል፤ አሁን ወደዚያ እንሂድ፤ ምናልባት የምንሄድበትን መንገድ ይነግረናል አለው። ..ሳኦልም ብላቴናውን ፡- ና፥ እንሂድ አለውና የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ.. ገናም ሳኦል ሳይመጣ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንዲህ ብሎ ገልጦለት ነበር። ነገ በዚህች ሰዓት ..አንድ ሰው እሰድድልሃለሁ፤ ..ለሕዝቤ ለእስራኤል አለቃ ይሆን ዘንድ ትቀባዋለህ.. ሳሙኤልም ሳኦልን ባየ ጊዜ እግዚአብሔር፡- ያ የነገርሁህ ሰው እነሆ፤ እርሱም በሕዝቤ ላይ ይሠለጥናል አለው። ሳኦልም በበሩ ወደ ሳሙኤል ቀርቦ፡- የባለ ራእዩ ቤት ወዴት እንደ ሆነ፥ እባክህ፥ ንገረኝ አለው። ሳሙኤልም መልሶ ሳኦልን፡- ባለ ራእዩ እኔ ነኝ፤ ..በልብህም ያለውን ሁሉ እነግርሃለሁ፤  ከሦስት ቀንም በፊት የጠፉ አህዮችህ ተገኝተዋልና ልብህን አትጣልባቸው። የእስራኤል ምኞት ለማን ነው?  ለአንተና ለአባትህ ቤት አይደለምን? አለው ( ትነግሣለህ እያለው ነው )። ሳኦልም መልሶ፡- እኔ ከእስራኤል ነገዶች ከሚያንስ ወገን ..ወገኔስ ከ.. ወገኖች ሁሉ የሚያንስ አይደለምን? እንዲህስ ያለውን ነገር ለምን ነገርኸኝ? አለው ( 1ሳሙ  9 ) ። ሳሙኤልም የዘይቱን ብርሌ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፥ ሳመውም፥ እንዲህም አለው፡- በርስቱ ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶሃል.. ( 1ሳሙ  10 ÷ 1 ) ።   ማብራሪያ ከበላይ እንዳነበባችሁት የአባቱን  አህዮች ሊፈልግ የወጣ ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ተሹሞ  እንደ ተመለሰ አይተናል፡፡ የንጉሥ ልጅ ያልሆነ እንዴት ንግሥናን ይጠብቃል? በተለይ ደግሞ አህዮች ጠፍተውት የጠፉበት አህዮች ስላጎደሉት በአባቱ ፡- አህዮቼን ፈልግልኝ ተብሎ የተላከ ልጅ ንጉሥ ይሆናል ተብሎ እንዴት ይጠበቃል? ንጉሥ ያልሆነውም አባቱ ልጁ ንጉሥ እንደሚሆን የተነገረውን ትንቢት ሲነግረውም የሚገርም ነገር ነው፡፡ አባቱ የላከው የጠፉ አህዮችን ይዞ እንዲመጣ እንጂ ንግሥናን ይዞ ይመጣል ብሎ እንዴት ማሰብ ይችላል? .. እግዚአብሔር  ግን የአባቱን አህዮች ሊፈልግ የተላከውን ሰው ንጉሥ አድርጎ ሾመው፡፡ ሳኦል የአባቱ አህዮች መጥፋት ቢያስጨንቁት ነው የጠፉትን አህዮች ፈልግ ሲባል ፡- እሺ ብሎ ለመፈለግ የወጣው፡፡ ስለ አባቱ አህዮች እየተጨነቀ ለወጣው ሳኦል ግን እግዚአብሔር ንግሥናን አዘጋጅቶለት ነበር፡፡ እግዚአብሔርን የምትወዱ ወገኖች አግዚአብሔር ያየልን ነገር አለ፡፡ እኛ ለራሳችን ያየነው ነገር ባዶ ቢሆን አግዚአብሔር ያየልን ነገር ደግሞ አለን፡፡ የጠፉትም አህዮች ተገኙ፡፡ ደግሜ የምለው ማይት ስላልቻልን እንጂ በእግዚአብሔር ግን የታየልን ነገር አለ፡፡ በዕጣ አማካኝነት ለሚሰጥ ቤት ያልተመዘገበ ሰው ዕጣ ከመውጣቱም በፊት ወይም ዕጣ ይወጣል የተባለ ቀን ቤት ይደርሰልኛል ብሎ ተስፋ ሊያደርግ አይችልም፡፡ በእግዚአብሔር ግን እንዲህ አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን አምኖ የሚከተል ሰው እርሱ ያልታየው ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚቸረው ነገር እንዳለ መኖሩን ነው፡፡ አህያ ፈላጊ ንግሥናን ሊያስብ ከቶ አይችልም፡፡ እኛ ከእግዚአብሔር በጎ የታሰበልን ባይመስለንም ከእግዚአብሔር የታሰበልን ነገር ግን እንዳለ እንወቅ፡፡ ሲነጋ ፀሐይን ያወጣልን አምላክ ከመዛግብቱ የሚስፈልገንን ነገር ይሰጠናል፡፡ ወደ ውጪ አገር የሄደ ሰው የቤተሰቡን ችግር ስለሚያውቅ ለቤተሰቡ ብር ይልካል፡፡ ሰው እንኳን ይህን ያህል አስቦ ያደርጋል፡፡ ከሚወደን አባታችን ለኛ ለልጆቹ የሚቸረን ነገርም አለ፡፡ በእጃችን ምንም ነገር ሳይኖር ሲቀር ነው በእግዚአብሔርም ጭምር የታየልን ነገር እንደሌለን የሚመስለን፡፡ ባለንበት ዓለም የዜግነት ተብሎ እንኳን የሚከፈላቸው ሰዎች አሉ፡፡ አገሮች ይህን ያህል ለዜጎቻቸው ካሰቡ እግዚአብሔር ታዲያ ለልጆቹ ለዜጎቻቸው እንደሚያሰቡ አገሮች እንጂ ለዜጎቻቸው ዴንታ እንደሌላቸው አገሮች እንዴት ይሆናል? እግዚአብሔር ለኛ ያየልን ነገር እንዳለ ሁሌም ብናምን መልካም ነው ፡፡ ተስፋ ሳንቆርጥ በየቀኑ መጓዝ ይሆንልናል፡፡ ጽሑፌን እያነበባችሁ ጭራሽ ምንም አልዋጥ ላላችሁ፣ ሳኦልም እኮ ወገኑ ታናሽ ከተባሉት መካከል በመሆኑ፡- ትነግሣለህ ሲባል ማመን አቅቶት ነበር፤ ማመን ስላቃተው የታየለት ንግሥና ግን አልቀረበትም፡፡ ስናምን ከእግዚአብሔር ትልቅ ነገር እንደሚደረግን ቃሉ ያስተምረናል፡፡ እስከ ጭራሹ ማመን ደግሞ ሲያቅተን እግዚአብሔር ከበጎነቱ የተነሣ ማመን ያቃተንን ነገር ያደርግልናል፡፡ ከገዛ በጎነቱ ለሚያደርግልን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን ! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

ከታቀደልን ስውር ደባ እግዚአብሔር ይጠብቀናል፡፡   የሶርያም ንጉሥ ከእስራኤል ጋር ይዋጋ ነበር፤ ከባሪያዎቹም ጋር ተማክሮ፡- በዚህ ተደብቀን እንሰፍራለን አለ።  የእግዚአብሔርም ሰው፡- ሶርያውያን በዚያ ተደብቀዋልና በዚያ ስፍራ እንዳታልፍ ተጠንቀቅ ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ላከ። የእስራኤልም ንጉሥ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ነገረው ስፍራ ሰደደ፤ አንድ ጊዜም ሳይሆን፥ ሁለት ጊዜም ሳይሆን በዚያ ራሱን አዳነ።  የሶርያም ንጉሥ ልብ ስለዚህ እጅግ ታወከ፤ ባሪያዎቹንም ጠርቶ፡- ከእኛ ዘንድ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የተወዳጀ እንዳለ አትነግሩኝምን? አላቸው። ከባሪያዎቹም አንዱ፡- ጌታዬ ሆይ፥ እንዲህ እኮ አይደለም፤ ነገር ግን በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእስራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ይነግረዋል አለ ( 2ነገ 6 ÷ 8 - 12 ) ።   ማብራሪያ የሶርያ ንጉሥ የእስራኤል ንጉሥ ላይ አደጋ ሊያደርስ ከቻለም ሊገድለው ፈልጎ አደባ፡፡ የእስራኤል ንጉሥ ያልፋል ብሎ ባሰበበት ስፍራ ተደበቀ፡፡ እግዚአብሔር ለነቢዩ ለኤልሳዕ ስለ ገለጸለት ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ በዚያ ስፍራ እንዳያልፍ መልእክት ላከበት ፡፡ የእስራኤል ንጉሥ መልእክቱን ተቀብሎ ራሱን አዳነ፡፡ የሶርያ ንገሥ ከባሪያዎቹ አንዱ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የተወዳጀ ያለ መስሎት ነበር ፡፡ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የተወዳጀው እግዚአብሔር እንደ ነበር አላወቀም፡፡ የሶርያ ንጉሥ ማድባት ችሏል፤ መግደልና አደጋ ማድረስ ግን አልቻለም፡፡ ሰዎች ዕውቀታቸውን፣ ኃይላቸውን ፣ ተሰሚነታቸውን ተጠቅመው ሊጎዱን ያደቡብናል፡፡ አኛ እውቀት ፣ ኃይል ፣ ተሰሚነት ስለሌለን ሴራቸውን መመከት ያቅተናል፡፡ እግዚአብሔር ሲኖረን እውቀት ባይኖረን እውቀት ሆኖ፣ ኃይል ባይኖረን ኃያል ሆኖ ለደካሞቹ ለኛ እግዚአብሔር ይቆማል፡፡ ከሴራቸውም ያድነናል፡፡ ማለዳ ስንነሳ አንዳፍታ ስለ ውሎአችን ፣ ከአቅማችን በላይ ስለሆኑ ነገሮች አሳልፈን እንስጠው፡፡ በአንዳፍታ ውስጥ የሰጠነው እግዚአብሔር ሰዎች በስውር ደባቸው ከመከሩብን ነገር እግዚአብሔር ይጠብቀናል፡፡ አንዳንድ ሰዎች በጠላት ዲያብሎስ ተነድተው በኛ ላይ በስውር የሚያደቡ አሉ፡፡ በስውር እያደቡ ይምሰላቸው እንጂ እግዚአብሔር የሚሰሩትን በግልጽ ያየዋል፡፡  ጠብቀን ያልነው አምለክ ታማኝ ነው፡፡ ከደባቸው እንድናመልጥ ያደርጋል፡፡ በመንገድ ዳር ወፍን ለማጥመድ ያሰበ ሰው አሥር ጊዜ ወፊቱ ልትገባለትና ገመዱን ሊስብ በፈለገበት ሰዓት መንገደኞች እያለፉ ወፊቷን እንድትበር በማድረጋቸው እንደሚበሳጭ ሴረኛ ሰው አድብቶ አድብቶ ደባው ስለማይሳካለት መጨረሻው ብስጭት ነው፡፡ የሶርያም ንጉሥ መጨረሻ ተበሳጨ፡፡ ጠዋት ስንነሳ፡- ሰላም አውለኝ አምላኬ፣ ከክፉሁሉ አድነኝ ብሎ መውጣት ተገቢ ነው፡፡ ሰላም አውለኝ አምላኬ፣ ከክፉ ሁሉ አድነኝ ብሎ መውጣት ማለት የሚያደባብን ሰው ፍተሻ እንዲደረግበትና እኛን ሊጎዳበት የያዘውን ነገር በእግዚአብሔር ቁጥጥር ስል እንዲውል ማስደረግ ነው፡፡ ሊጎዳን የሚመጣውን ነገር ለእግዚአብሔር አሳልፈን በመስጠታችን እግዚአብሔር በዙሪያችን ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርግልን መንገራችን ነው፡፡ የመንግሥት ባለስልጣናት ወደ አንድ ሥፍራ ሊሄዱ ሲያስቡ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግላቸው እኛም አምላካችን ሊጎዳን ከሚያስበን ነገር እኛ ከማናውቀው እርሱ ከሚያውቀው ከክፉ ነገር ይጠብቀናል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ አሜን! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ፡፡   መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥ ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው ( 1ቆሮ 1 ÷ 22 - 24 ) ።   ማብራሪያ ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን መልእክት ሲጽፍ በዋናነት ከሚታወቁት ሕዝቦች መካከል አይሁድና የግሪክ ሰዎች ናቸው ፡፡  አይሁድ ምልክትን የሚሹ ናቸው ( ዮሐ 6 ÷ 30 ፡ 31 ) ፡፡ ሙሴ ከሰማይ መና እንዳወረደ ያውቁ ነበርና  ከሰማይ ምልክትን እንዲያሳያቸው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስንን ሲጠይቁት ፡- ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክትን ይሻል ብሎ መልሶላቸዋል ( ማቴ 16 ÷ 1 - 4 ) ። ሐዋርያው ጳወሎስም ክርስቶስን መስበክ ትቶ ምልክትን ለሚፈልጉት ለአይሁድ ምልክትን ለማሳየት አልደከመም ፡፡ የግሪክ ሰዎች ደግሞ ጥበብን የሚሹ ናቸው ፡፡ የሚፈልጉትን ጥበብ ሳይሆን ከእግዚአብሔር የሆነውን ጥበብ ይኸውም ክርስቶስን ነው የሰበከላቸው ፡፡ የተሰበከውን ክርስቶስ አይሁድ ባለማመናቸው ሲሰናከሉ ፣ ለግሪኮች ደግሞ ሞኝነት ሆነባቸው ፡፡ ላመኑት አይሁድና የግሪክ ሰዎች የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው ፡፡ ዛሬም ጳውሎስ የሰበከውን ክርስቶስን እንሰብካለን ፡፡ ላመኑት የሚያድን ጌታ ነውና ፡፡ ተሰቅሎ አድኖናልና ፡፡ የክርስትና ሃይማኖት የተሰቀለውን ክርስቶስን የምንሰብክበት ነው ፡፡ ከተሰቀለው ክርስቶስ በቀር ተሰቅሎ ያዳነን የለምና ፡፡ በተሰቀለው በክርስቶስ በቀኙና በግራው የተሰቀሉ ነበሩ ፡፡ እነርሱ ስለ ገዛ ጥፋታቸው የተሰቀሉ ናቸው ፡፡ ክፉ አድራጊዎች ነበሩና ( ሉቃ 23 ÷ 32 ፡ 33 ) ፡፡ እርሱ ግን የተሰቀለው ስለኛ በደል ነው ፡፡ ለዚህ ነው የተሰቀለውን ክርስቶስን የምንሰብከው ፡፡ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን በሐምሌ 7 ቅዳሴ ሲቀደስና ከ10 - 31 ያለው ሲነበብ  ከበላይ የጠቀስኩት ክፍል ይነበባል ( መጽሐፈ ግጻዌን ይመልከቱ ) ፡፡  ወስብሐት ለእግዚአብሔር ። አሜን ! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

ጥልን በመስቀሉ ገደለ፡፡   ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ፤ በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ። አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና ( ኤፌ 2 ÷ 11 - 18 )።   ማብራሪያ መስቀል ከሰባቱ የጌታ ንዑሳን  በዓላት አንዱ ሲሆን ክብሩ ከዓበይት በዓላት አንዱ ከሆነው ከደብረ ታቦር ያነሰ ነው፡፡ ከበላይ ባለው ኃይለ ቃል ሁለት ሕዝቦችን እናያለን፡፡ አይሁድና አሕዛብ ናቸው፡፡ አይሁድ በሥጋቸው የተገረዙ ናቸው፡፡ አይሁድ በእግዚአብሔር የተመረጡ ሕዝብ ናቸው፡፡ ከአይሁድ ውጭ ያሉ ሕዝቦች አሕዛብ ይባላሉ፡፡ አሕዛብ እግዚአብሔርን የማያምኑ ነበሩ፡፡ በሥጋቸው ያልተገረዙ ስለነበሩ በተገዙት በአይሁድ ያልተገረዙ እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ አሕዛብ የእስራኤል ዜግነት ያልነበራቸው ነበሩ፡፡ እንደ አይሁድ የተስፋ ቃል ኪዳን ያልነበራቸው ነበሩ፡፡ ተስፋም አጥተው ከእግዚአብሔር ተለይተው ይኖሩ ነበር፡፡ ተስፋ የነበራቸው አይሁድም ሆኑ ተስፋ አጥተው የነበሩት አሕዛብ በክርስቶስ ሲያምኑ በፈሰሰው ደም ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ቻሉ፡፡ ክርስቶስ ሰላም ነውና ሁለት የነበሩትን አይሁድንና አሕዛብን አንድ አደረጋቸው፡፡ ግድግዳ ሰውን እንደሚለይ አይሁድንና አሕዛብን የሚለያቸው ግድግዳ በሥጋው ማለት በሞቱ አፈረሰው፡፡ ሁለት የነበሩትን አንድ አድርጎ አዲስ ሰውን ፈጠረ፡፡ አይሁድ ክርስቶስን ሰቅለው ገድለውት ነበር፡፡ ጌታችን ደግሞ እርሱን እንደ ሰቀሉት እርሱ ደግሞ በአይሁድና በአሕዛብ የነበረውን ጠላትነትን (ጥልን ) ገደለ፡፡ በክርስቶስ ያመኑ አይሁድና አሕዛብ አንድ ሕዝብ እንጂ ሁለት ሊባሉ እንዳይቻል አድርጎ አንድ አደረጋቸው፡፡ ሁለቱን አንድ አካል አድርጎ ከእግዚአብሔር አብ ጋር አስታረቃቸው፡፡ በክርስቶስ ያመነ አይሁድ ፣ ኢትዮጵያዊ ፣ ግብፃዊ ሁሉም አንድ ናቸው እንጂ የተለያዩ አይደሉም፡፡ በክርስቶስ ሞት ያመንን ክርስቲያኖች ወደ አብ መግባት ቻልን፡፡ ወደ አብ መግባት ቻልን ማለት ወደ አብ መቅረብ መቻላችንን ለመናገር ነው፡፡ ክርስቲያኖች በከርስቶስ የምናምን ስለ ሆነን እግዚአብሔር እንደ ተቀበለንና እንደሚወደን አውቀን ስንጸልይ የሚሰማን ልጆቹ እንደ ሆንን እርግጠኝነት ሊሰማን ይገባል፡፡ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን በመስቀል ላይ ስለሞተልን በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ እንደምንችል መዘንጋት የለብንም፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

የነገ ሰው ካለን ነገም እግዚአብሔር ድንቅን ሠርቶ ያሳየናል፡፡   ኢያሱም ሕዝቡን፡- ነገ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ተቀደሱ አለ። ኢያሱም ካህናቱን፡- የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክማችሁ በሕዝቡ ፊት እለፉ ብሎ ተናገራቸው፤ የቃል ኪዳኑንም ታቦት ተሸክመው በሕዝቡ ፊት አለፉ።  እግዚአብሔርም ኢያሱን፡- ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር መሆኔን ያውቁ ዘንድ በዚህ ቀን በእስራኤል ሁሉ ዓይን ከፍ ከፍ አደርግህ ዘንድ እጀምራለሁ። አንተም የቃል ኪዳኑን ታቦት የሚሸከሙትን ካህናት፡- በዮርዳኖስ ውኃ ዳር ስትደርሱ በዮርዳኖስ ውስጥ ቁሙ ብለህ እዘዝ አለው።  ኢያሱም ለእስራኤል ልጆች፡- ..የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ አለ። ..የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ ከላይ የሚወርደው የዮርዳኖስ ውኃ ይቋረጣል፤ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል። .. እንደ መከር ወራት ሁሉ ዮርዳኖስ እጅግ ሞልቶ ነበርና ታቦት ተሸካሚዎቹ ወደ ዮርዳኖስ ሲደርሱ፥ ታቦቱንም የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች በውኃው ዳር ሲጠልቁ፥ ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ.. ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ። የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር፥ ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ እስራኤል ሁሉ በደረቅ መሬት ተሻገሩ ( ኢያሱ 3 )። እንዲህም ሆነ፤ ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ እግዚአብሔርም ኢያሱን፡- ..አሥራ ሁለት ሰዎች  ምረጥና በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ አሥራ  ሁለት ድንጋዮች አንሡ፤ ተሸክማችሁም በዚህ ሌሊት በምታድሩበት  ስፍራ አኑሩአቸው ብለህ እዘዛቸው አለው።   ..ኢያሱም ..ከእስራኤል ልጆች ያዘጋጃቸውን አሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ። ኢያሱም አላቸው፡- ከእናንተም ሰው ሁሉ ..በጫንቃው ላይ አንድ አንድ ድንጋይ ከዚያ ይሸከም። ይህም በመካከላችሁ ምልክት ይሆናል፤ ልጆቻችሁም በሚመጣው ዘመን የእነዚህ ድንጋዮች ነገር ምንድር ነው? ብለው ሲጠይቁአችሁ፥ እናንተ፡- በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት የዮርዳኖስ ውኃ ስለተቋረጠ ነው.. እነዚህም ድንጋዮች ለእስራኤል ልጆች ለዘላለም መታሰቢያ ይሆናሉ ትሉአቸዋላችሁ።  ..እግዚአብሔርም ኢያሱን እንደ ተናገረው ..ከዮርዳኖስ መካከል አሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሥተው ወደሚያድሩበት ስፍራ ወሰዱ፥ በዚያም አኖሩአቸው። ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎችን አሥራ ሁለት ድንጋዮች ተከለ.. ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል ቆመው ነበርና፤ ሕዝቡም ፈጥነው ተሻገሩ። ..እግዚአብሔርም ኢያሱን፡- የምስክሩን ታቦት የሚሸከሙትን ካህናት ከዮርዳኖስ እንዲወጡ እዘዝ ብሎ ተናገረው። ኢያሱም ካህናትን፡- ከዮርዳኖስ ውጡ ብሎ አዘዛቸው። የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ከዮርዳኖስ መካከል በወጡ ጊዜ፥ የካህናቱም እግር ጫማ ደረቅ መሬት መርገጥ በጀመረ ጊዜ፥ የዮርዳኖስ ውኃ ወደ ስፍራው ተመለሰ፥ ቀድሞም እንደ ነበረ በዳሩ ሁሉ ላይ ሄደ፡፡ ሕዝቡም ..በጌልገላ ሰፈሩ። ከዮርዳኖስም ውስጥ የወሰዱአቸውን እነዚያን አሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ኢያሱ በጌልገላ አቆማቸው። ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፡- በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ አባቶቻቸውን፡- እነዚህ ድንጋዮች  ምንድር ናቸው? ብለው ሲጠይቁ፡- ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ። እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ተሻገረ፤ እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ የኤርትራን ባሕር  ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ  እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችሁ አደረቀ። ይኸውም የእግዚአብሔር እጅ ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ፥ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ለዘላለሙ እንድትፈሩ ነው ( ኢያሱ 4 )፡፡   ማብራሪያ ታቦቱ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን  ታቦት በመባል ይጠራል፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ታቦት አሁን ካለው የተለየ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳኑን ታቦት የሚሸከሙት አራት ሰዎች ሆነው ነው፡፡ የአሁኑ ታቦት ምሥዋዕ በመባል ይጠራል፡፡ ለሥጋ ወደሙ መፈተቻነት የሚያገለግል ነው፡፡ እስራኤላውያኑ ከግብፅ ወጥተው ወደ አገራቸው በሚያደርጉት ግስጋሴ የዮርዳኖስ ወንዝ ፊታቸው ተደንቅሮ አላሳልፍ አላቸው፡፡ ታቦቱ በአንድ ሰው ብቻ ሊሸከሙት የማይቻል ነበርና ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ውስጥ ሲቆም እንደ ክምር ሆኖ ቆመ፡፡  ለእነርሱ ሲል ውኃው ሲቆም ሲያዩ ምንኛ ይደነቁ! ቆሞ አሳለፋቸው ፡፡ ሕዝቡ ተሻግረው ሲያበቁ ካህናቱ ከውኃው ወጥተው እግራቸው ደረቅ መሬት መርገጥ ሲጀምር ውኃው መልሶ መፍሰስ ጀመረ፡፡ ውኃው ቆሞ እንዳሳለፋቸው ፣ ከወጡ በኋላ ደግሞ መፍሰስ ሲጀምር መልሰው እንዴት ነው የማይደነቁት ትላላችሁ? ከወንዙም ውስጥ ያወጡአቸውን 12 ድንጋዮች ካህናቱ እግራቸው ቆሞ በነበረበት በወንዙ ውስጥም እንዲሁም ከወንዙ ውጭም ተተከሉ፡፡ የሚመጣ ትውልድ እግዚእብሔር ያደረገውን ተአምር እንዲሰማ ታስቦ ነው፡፡ እግዚእብሔር ከግብፅ ያወጣውን ሕዝብ ሊያውም እጅግ ባለመታዘዝ ያስቸገሩትን በእንዲህ መልኩ ነበር ደንቅን እያሳያቸው የመራቸው፡፡ ቸርነቱ እንዴት ብዙ ነው! ድንቅን የሚሠራ አምላክ እያለን ነገ ምን እንሆናለን? በሚል ብዙ ሰው ስለ ነገ ይጨነቃል ፡፡ የነገ ሰው ካለን ነገ የሚያስጨንቅ ቀን ሳይሆን እግዚአብሔር ድንቅን ሠርቶ የሚያሳያን ቀን ነው፡፡ ስለ ነገና ስለ ተለያዩ ነገሮች መጨነቅ ይብቃ ፡፡ ሕዝቡ ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው ውኃውን በእግራቸው ይዘው እለፉ ሲባሉ፡- ውኃው ቢመለስብንስ? ሳይሉ በእምነት እንደ ተሻገሩ በአምላካችን እንታመን እንጂ  እርሱ እኛንም ያሻግረናል፡፡ እግዚአብሔር ድንቅን ነገር የሚሠራ ድንቅ አምላክ ነው፡፡ ድንቅ ማድረግ አያልቅበትም፤ እኛ ሁሌም ታምነነውና እርሱን በመፍራት እንኑር ፡፡ እኛ ያላሰብነውንና ያልጠበቅነውን ድንቅ ነገር የሚያደርግ አምላክ ነው፡፡ ድንቅ ነገርን መሥራት ልማዱ ነው፡፡ በእግር ውኃን ያስቆመ አምላክ የኛ ነገር ታዲያ ምን ያቅተዋል? ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

የመስቀሉ ቃል ለምንድን ለኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው ።   የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና ( 1ቆሮ 1  ÷ 18 ) ።   ማብራሪያ ከበላይ ያለውን ቃል ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች የጻፈው ነው ፡፡ ቆሮንቶስ የግሪክ ከተማ ናት ፡፡ ሐዋርያው የግሪክ ከተማ በሆነች ወደ ቆሮንቶስ ሄዶ የተሰቀለውን ክርስቶስን ሰብኮአል ፡፡ ተሰቅሎ የሞተ ሰው ያድናል ብሎ መቀበል አሕዛብ ለሆኑት ለግሪክ ሰዎች ሞኝነት ነው ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ለገዛ ወገኖቹ ክርስቶስን ለሰቀሉት ለአይሁድም የተሰቀለውን ክርስቶስን ሰብኮላቸዋል ፡፡ ለአይሁድ መሰናከያ ሆነባቸው ፡፡ ጳውሎስ የተሰቀለውን ክርስቶስን ስለሚሰብክ አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር ፡፡ ሐዋርያው የምንድንና የሚጠፉ ሰዎች እንደሉ ገልጾልናል ፡፡ የግሪክ ሰዎች፣ አይሁድ እንዲሁም እንደነርሱ በመስቀል ላይ ክርሰቶስ ያደረገውን የማዳን ሥራ ያላመኑ ሁሉ የሚጠፉ ናቸው ፡፡ የሚጠፉት እግዚአብሔር እንዲጠፉ ወዶ ሳይሆን ባለማመናቸው ነው የሚጠፉት ፡፡ እግዚአብሔር ማንም እንዲጠፋ አይወድም ፡፡ እኛ ክርስቲያኖች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን በመስቀል እንደ ተሰቀለ የምናምን ስለ ሆነን የምንድን ነን እንጂ የምንጠፋ አይደለንም ፡፡ ስለ ኃጢአታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ እንደ ተሰቀለልን የምናምን ድነናል ፡፡ ቃሉም ፡- ድናችኋል ( ኤፌ 2  ÷ 5 ) ይለናል ፡፡ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን በመስቀል ላይ እንደ ተሰቀለ የምናምን ሰዎች ክርስቶስን አምነን መከተል በጀመርንበት ሰዓት ድነናል ፡፡ ዛሬም የዳንን ነን ( እየዳንን ነን ) ፡፡ ክርስቶስ ዳግም በሚመጣበት ሰዓትም በእርሱ ጸንተን እስከ ተገኘን ድረስ ከቍጣው እንድናለን ( ሮሜ 5  ÷ 9 ) በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ መዳን በሀላፊ ፣ በአሁንና በትንቢትም ጊዜያት ተጠቅሶ እናገኛለን ፡፡ ለዛሬው ስለ መዳናችን በአሁን ጊዜ በግሪኩ የሰፈረውን ሀሳብ እያነሳሁ አብራራለሁ ፡፡  በሀላፊና በትንቢት ስለ መጠቀሱ ደግሞ በቦታው ስደርስ ግሪኩ የሚለውንም እያነሳሁ የማብራራ እሆናለሁ ፡፡ ከበላይ ባሰፈርኩት ቃል ፡- ለእኛ ለምንድን የሚለው ቃል በግሪኩ ፡- ሶዞሜኖይስ ይለዋል ፡፡ ቃሉ የአሁን ጊዜን ( Present )ና የአሁን ቀጣይ ጊዜን ( Present continuous ) ያሳያል ፡፡ NIV መጽሐፍ ቅዱስን ለምትጠቀሙ ፡- to us who are being saved ( እየዳንን ላለነው ) በማለት በአሁን ቀጣይ ጊዜ ( Present continuous ) አመልካችነት እንደ ተተረጎመ ልጠቁማችሁ እወድዳለሁ ፡፡ የክርስትና ሕይወት ተሰቅሎ ያዳነን ክርስቶስን አምነን በመከተል የምንጀምረው ጉዞ ሲሆን የሚጠናቀቀው ደግሞ ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ ነው ፡፡ ባልታደሰ መታወቂያ አገልግሎት ለማግኘት ፈልጋችሁ ፡- አድሳችሁ ኑ ከተባላችሁ በኋላ አድሳችሁ ስትመጡ ፡- አልታደሰም ይሉኝ ይሆን ብላችሁ መስጋት እንደሌለባችሁ የምንድን እንደ ሆንን ( እንደ ዳንን ) ስጋት ሊገባን አይገባም ፡፡  ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችሁ እንደ ተሰቀለ የምታምኑ ኦርቶዶክሳውያን ድናችኋል ፡፡ መዳናችንን ማወቃችን ደግሞ ትልቅ ኃይል ነው ፡፡ ዛሬ ብለን በምንጠራው ቀን ሁሉ ስለ መዳናችን ስናስብ ፡- ድነን ነበር ምን ዋጋ አለው በማለት ሳይሆን “ ዛሬም የዳንን ነን ( እየዳንን ነን ) ” በማለት በድፍረት እንናገር ፡፡ አድኖን በማይተወን እስከ ሕይወታችን ፍጻሜም በሚያጸናን በክርስቶስ እንመካለን ፡፡ የመስቀሉ ቃል ማለት ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን መሰቀሉ ለኛ ለምንድን ኃይለ እግዚአብሔር ( የእግዚአብሔር ኃይል ) ነው ፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመ አሳዛኝ የዝሙት ኃጢአት ፡፡   በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና። እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ። እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን፥ መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው ( 1ቆሮ 5 ÷ 1 - 5 ) ።   ማብራሪያ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን አንድ ሰው የአባቱን ሚስት አግብቶ ይኖር ነበር ፡፡ እንጀራ እናቱን ማለት ነው ፡፡ ክርስቲያን ያልሆኑ አሕዛብ እንኳን እንደዚህ ያለ ጋብቻ አይፈጽሙም ነበር ፡፡ አይደለም በክርስቲያን ዘንድ በአሕዛብም ዘንድ አጸያፊ ነው ፡፡ ወሬው ወደ ሐዋርያው ጳውሎስ ደረሰ ፡፡ አንድ ሰው የአባቱን ሚስት አግብቶ እንደሚኖር ተነገረው ፡፡ ጳውሎስ በአካል ከእነርሱ ጋር አልነበረም ፡፡ 1ኛ ቆሮንቶስን ጽፎ የላከላቸው በዚህና በሌሎችም ምክንያቶች ነው ፡፡ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ጥፋታቸው በተሠራው ሥራ አላዘኑም ፡፡ ሰውየው ድርጊቱን ትቶ ንስሐ እንዲገባ አልመከሩም ፡፡ ንስሐ አልገባም ካለ ደግሞ ማግለል ነበረባቸው ፡፡ የአባትን ሚስት ማግባት ዝሙት እንጂ ጋብቻ አይደለም ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ይህ ሰው ከቤተ ክርስቲያን ( ከማኅበረ ምዕመናን ) እንዲወገድ አዝዞአል ፡፡ ከጉባኤ እንዲታገድ ( እንዲወገዝ ) ያደረገው ሰውየው ተጸጽቶ እንዲመለስና በፍርድ ቀን ነፍሱ እንድትድን ብሎ ነው ፡፡ ሰውየው ወዲያውኑ ቢጸጸትና ንስሐ ቢገባ ከቤተ ክርስቲያን እንዲለይ አያደርግም ነበር ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ዝሙት የተፈጸመው የክርስትና ሃይማኖት ገና 60 ዓመት ገደማ ሳይሞላው የዛሬ 1600 ዓመት ገደማ በፊት መሆኑ ነው ፡፡ ድርጊቱ ደግሞ ሐዋርያው ጳውሎስ ወንጌልን በሚሰብክበት ዘመን መሆኑ ይገርማል ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ የዝሙትን ሥራ የሠራውን ሰው አልሰደበም ፡፡ ትርፍ ቃላትም አልተናገረውም ፡፡ ያዘዘው ከቤተ ክርስቲያን እንዲለይ ነው ፡፡ በቆሮንቶስ አገር የሚኖሩ ክርስቲያን ያልሆኑ አሕዛብ በቤተ ክርስቲያን ( በክርስቲያኖች ዘንድ ) ተፈጸመ የተባለውን ዝሙት ሲሰሙ ጉድ የሚሉትን ሥራ ሰውየው ፈጽሞአል ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ገጽታ አበላሽቶአል ፡፡ በየትኛውም ዘመን እንደዚህ አሳዛኝና ሰው ሁሉ ሁሉ ጆሮ የደረሰ ኃጢአት ሲወራ ስንሰማ ያሳዝናል ፡፡ እንደዚህ ያለውን ሰው የማይጠቅም ቃል ከመናገር ብንችል ወደ ንስሐ እንዲመጣ መምከርና መጸለይ ነው ፡፡ በንስሐ ከተለመሰ በቤተ ክርስቲያን አባልነቱ ይቀጥላል ፡፡ አልመለስም ካለ ተወግዞ ይለያል ፡፡ ተወግዞ ቢለይ እንኳን ቤተ ክርስቲያን ይህ ሰው እግዚአብሔር ልቦና እንዲሰጠውና እንዲጸጸት ግን ከመጸለይ አታቋርጥም ፡፡ ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያንን ገጽታ ጭምር ያበላሸ ሰው ከሠራው ኃጢአቱ ተጸጽቶና ንስሐ ገብቶ ስናየው ደስታችን ወደር አይኖረውም ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ባሳዘነው ፈንታ መልሰን ልናዝንለትና ከጎኑ መሆናችንንም በፍቅር እንገልጽለታለን ፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን ! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

ኃጢአታችንን ከኛ የሚያርቅ ይቅር ባይ አምላክ ::   ዳዊት.. በሰገነቱ ሳለ አንዲት ሴት ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም መልከ መልካም ነበረች።  ዳዊትም ..ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፤ አንድ ሰውም፡- ይህች ..የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን? አለ። ዳዊትም ..አስመጣት፤ ..ከእርስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤትዋም ተመለሰች።  ሴቲቱም ..ወደ ዳዊትም፡- አርግዤአለሁ ብላ ላከችበት።  ዳዊትም ወደ ኢዮአብ፡-  ..ኦርዮን ስደድልኝ ብሎ ላከ። ኢዮአብም ኦርዮን ወደ ዳዊት ሰደደው። ኦርዮም ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ ዳዊት የኢዮአብንና የሕዝቡን ደኅንነት፥ ሰልፉም እንዴት እንደ ሆነ ጠየቀው።  ዳዊትም ኦርዮን፡- ወደ ቤትህ ሂድ ..አለው። ..ኦርዮ ግን ከጌታው ባሪያዎች ሁሉ ጋር በንጉሥ ቤት ደጅ ተኛ፥ ወደ ቤቱም አልወረደም። ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም ብለው ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም ኦርዮን;- አንተ ከመንገድ የመጣህ አይደለምን? ስለ ምን ወደ ቤትህ አልወረድህም? አለው። ኦርዮም ዳዊትን:- ታቦቱና እስራኤል ይሁዳም በጎጆ ተቀምጠዋል፤ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም ባሪያዎች በሰፊ ሜዳ ሰፍረዋል፤ እኔ ልበላና ልጠጣ ወይስ ከሚስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄዳለሁን? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም አለው። ዳዊትም ኦርዮን፡- ..ነገም አሰናብትሃለሁ አለው። ..ዳዊትም ጠራው፥ በፊቱም በላና ጠጣ፥ አሰከረውም፤ ነገር ግን በመሸ ጊዜ ..ከጌታው ባሪያዎች ጋር ..ተኛ፥ ወደ ቤቱም አልወረደም። በነጋም ጊዜ ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጻፈ፥ በኦርዮም እጅ ላከው። በደብዳቤውም:- ኦርዮን ጽኑ ሰልፍ ባለበት በፊተኛው ስፍራ አቁሙት፥ ተመትቶም ይሞት ዘንድ ከኋላው ሽሹ ብሎ ጻፈ።  ኢዮአብም ..ጀግኖች እንዳሉበት በሚያውቀው ስፍራ ኦርዮን አቆመው። ..ኦርዮም ደግሞ ሞተ። ..መልእክተኛውም ተነሥቶ ሄደ፥ መልእክተኛውም ዳዊትን፡- ..ኦርዮ ..ሞተ አለው። ፤ የኦርዮም ሚስት ..ለባልዋ አለቀሰች። የልቅሶዋም ወራት ሲፈጸም ዳዊት ልኮ ወደ ቤቱ አስመጣት፥ ሚስትም ሆነችው ( 2ተኛ ሳሙ ( ሳሙኤል ካልዕ) ም 11 ) ፡፡ እግዚአብሔርም ናታንን ወደ ዳዊት ላከ.. ናታንም ዳዊትን አለው፡- ..የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ..በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእግዚአብሔርን ነገር ለምን አቃለልህ? ኦርዮን በሰይፍ መትተሃል፥ ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃል.. ዳዊትም ናታንን፡- እግዚአብሔርን በድያለሁ አለው። ናታንም ዳዊትን፡- እግዚአብሔር ደግሞ ኃጢአትህን አርቆልሃል፤ አትሞትም ( 2ተኛ ሳሙ ( ሳሙኤል ካልዕ ) ም 12 ) ፡፡   ማብራሪያ ቅዱስ ዳዊት የእግዚአብሔር ሰዎች ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ዳዊት አንድ ቀን መልከ መልካም ሴት አየ፡፡ ቆንጆዋ ሴት የሰው ሚስት ነበረች፡፡ ትዳር ያለው ዳዊት በሰው ሚስት ተፈተነ፡፡ ባሏ ጦር ሜዳ ነበርና አስጠራትና ከእርሷ ጋር ተኛ ፡፡ ከተወሰነ ቀናት በኋላ እንዳረገዘች ለንጉስ ዳዊት ነገረችው፡፡ ዳዊት የፈጸመው ድርጊት እንዳይታወቅበት የሴቲቱን ባል ኦርዮን ከጦር ሜዳ አስጠራው፡፡ ወደ ሚስቱም እንዲሄድ ነገረው፡፡ ኦርዮ ግን ወገኖቹ ጦር ሜዳ መሆናቸውን አስቦ ከሚስቱ ጋር ሊተኛ አልወደደም፡፡ በነጋው ኦርዮ ወደ ሚስቱ ሄዶ እንዳልተኛ ለዳዊት ተነገረው፡፡ የዳዊት ዓላማ ግልጽ ነው፡፡ ወደ ሚስትህ ሂድ የሚለው ኦርዮ ወደ ሚስቱ ሄዶ ከተኛ የተረገዘው ከኦርዮ ለማስመሰል ነበር፡፡ ዳዊት ነገሩ እንዳይታወቅበት በሁለተኛው ቀን ኦርዮ ገብቶ ከሚስቱ ጋር እንዲተኛ አስቦ አሰከረው፡፡ ኦርዮ ግን አሁንም ከሚስቱ ጋር ሳይተኛ ቀረ፡፡ በነጋው ለዳዊት ኦርዮ ከሚስቱ ጋር እንዳልተኛ ተነገረው፡፡ ዳዊት ወደ ጦር ሜዳ ኦርዮ እንዲመለስ አዘዘው፡፡ ደብዳቤም አስይዞ ላከው፡፡ ደብዳቤው ኦርዮ ታላቅ ውጊያ ባለበት ቦታ እንዲዋጋና እንዲገደል ለጦር አዛዡ የተላከ ነበር፡፡ ኦርዮ የሞቱን ደብዳቤ ይዞ ሄደ፡፡ እንደታቀደውም ተገደለ፡፡ እግዚአብሔር ወደ ዳዊት ነቢይ ላከና ስለ ሠራው ኃጢአት ገሰጸው፡፡ ዳዊት፡- በድያለሁ በማለቱ እግዚአብሔር ይቅር አለው፡፡ በነገራችን ላይ ጠቢቡ ሰለሞን የተወለደው ከዚች ሴት ነው፡፡ ዳዊት ሁለት ትላልቅ ኃጢአቶችን ሠርቷል፡፡ 1) ዝሙት ፈጸመ ( ሊያውም ከሰው ሚስት ጋር ተኛ) 2) ኦርዮን አስገደለ ፡፡ ማስከርም በጎ ሥራ አይደለም፡፡ እነዚህ የጠቀስኳቸው ኃጢአቶች ትላልቅ ናቸው፡፡ በራሱ ሰው ብቻ መግደል  ወይም ዝሙት መፈጸም ትልቅ ኃጢአት ነው፡፡ ሁለቱን ደግሞ በአንዴ መፈጸም ከባድ ነው፡፡ እነዚህን ሁለት ከባድ ኃጢአቶች ሠርቶ ይቅር በለኝ አላለም ( ንስሐ አልገባም ) ፡፡ ምንም ኃጢአት እንዳልሠራ ሰው እጁን አጣጥፎ ነበር የተቀመጠው፡፡ እግዚአብሔር ዳዊት ከላይ የጠቀስኳቸውን ኃጢአቶች ሠርቶ፡- ይቅር በለኝ ሳይል እግዚአብሔር ትዕግሥቱን አበዛለት (አብዝቶለት ለንስሐ ግዜ ሰጠው) ፡፡ ሲነገረው ንስሐ በመግባቱ (ይቅር በለኝ በማለቱ ) ይቅርታ ተሰጠው ፡፡ ምንም ኃጢአት ብንሠራ ይቅር በለን ካልነው ይቅር የሚል አምላክ ነው፡፡ አግዚአብሔር በእውነት ቸር አምላክ ነው፡፡ ምሕረቱ ደግሞ ለዘላለም ነው፡፡ የእኛ ዕድሜ ደግሞ አጭር ናት፡፡ ምሕረቱ ለዘላለም የሆነ አምላክ በምንኖራት አጭር ዕድሜአችን ውስጥ ለምንሠራው በደል ይቅር በለን ካልነው እርሱ ይቅር ለማለት አይደክምም፡፡ እንደ ዳዊት ያሉ የእግዚአብሔር ሰዎች ከበደሉት እኛማ እንዴት አንበድለው? ትልቁ ነገር ወዲያው ይቅር በለን ማለት ነው፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ አሜን! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

እግዚአብሔር መዋረዳችንን ይመለከታል፡፡   … ለናቡቴ በሰማርያ ንጉሥ በአክዓብ ቤት አጠገብ የወይን ቦታ ነበረው። አክዓብም ናቡቴን፡- በቤቴ አቅራቢያ ነውና የአትክልት ቦታ አደርገው ዘንድ የወይን ቦታህን ስጠኝ፤ ስለ እርሱም ከእርሱ የተሻለ የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ፤ ወይም ብትወድድ ግምቱን ገንዘብ እሰጥሃለሁ ብሎ ተናገረው። ናቡቴም አክዓብን፡- የአባቶቼን ርስት እሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር ያርቅልኝ አለው።  … ናቡቴ፡- የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም ብሎ ስለ ተናገረው አክዓብ ተቈጥቶና ተናድዶ ወደ ቤቱ ገባ። በአልጋውም ላይ ተጋድሞ ፊቱን ተሸፋፈነ፥ እንጀራም አልበላም።  ሚስቱም ኤልዛቤል ወደ እርሱ መጥታ፡- ልብህ የሚያዝን እንጀራስ የማትበላ ስለምንድር ነው? አለችው። እርሱም፡- … ናቡቴን፡- የወይንህን ቦታ በገንዘብ ስጠኝ፤ ወይም ብትወድድ በፋንታው ሌላ የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ ብዬ ተናገርሁት፤ እርሱ ግን፡- የወይን ቦታዬን አልሰጥህም ብሎ ስለ መለሰልኝ ነው አላት። ሚስቱም ኤልዛቤል፡- አንተ አሁን የእስራኤልን መንግሥት ትገዛለህን? ተነሣ እንጀራም ብላ፥ ልብህም ደስ ይበላት፤ … የናቡቴን የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ አለችው። በአክዓብም ስም ደብዳቤ ጻፈች፥ በማኅተሙም አተመችው፤ በከተማው ወደ ነበሩትና ከናቡቴም ጋር ወደ ተቀመጡት ሽማግሌዎችና ከበርቴዎች ደብዳቤውን ላከች። ሁለትም ምናምንቴ ሰዎች በፊቱ አስቀምጡና፡- እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው ይመስክሩበት፤ አውጥታችሁም እስኪሞት ድረስ ውገሩት ብላ ጻፈች።  በከተማውም የተቀመጡት የከተማው ሰዎችና ሽማግሌዎች ከበርቴዎችም ኤልዛቤል እንዳዘዘቻቸውና ወደ እነርሱ በተላከው ደብዳቤ እንደ ተጻፈ እንዲሁ አደረጉ። … ወደ ኤልዛቤልም፡- ናቡቴ ተወግሮ ሞተ ብለው ላኩ። ኤልዛቤልም ናቡቴ ተወግሮ እንደ ሞተ በሰማች ጊዜ ኤልዛቤል አክዓብን፡- ናቡቴ ሞቶአል እንጂ በሕይወት አይደለምና በገንዘብ ይሰጥህ ዘንድ እንቢ ያለውን … የናቡቴን የወይን ቦታ ተነሥተህ ውረስ አለችው። አክዓብም ናቡቴ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ ይወርሰው ዘንድ ወደ … ወደ ናቡቴ ወይን ቦታ ሊወርድ ተነሣ። የእግዚአብሔርም ቃል ወደ … ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፡- ተነሥተህ በሰማርያ የሚኖረውን የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ትገናኝ ዘንድ ውረድ፤ እነሆ፥ ይወርሰው ዘንድ በወረደበት በናቡቴ የወይን ቦታ ውስጥ አለ።  አንተም፡- እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ገድለህ ወረስኸውን? ብለህ ንገረው። ደግሞም፡- እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ስፍራ የአንተን ደም ደግሞ ውሾች ይልሱታል ብለህ ንገረው።  አክዓብም ኤልያስን፡- ጠላቴ ሆይ፥ አገኘኸኝን? አለው። እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት፡- አግኝቼሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ለማድረግ ራስህን ሽጠሃልና። እነሆ፥ ክፉ ነገር አመጣብሃለሁ.. በሥራህም አስቈጥተኸኛልና፥ ..በእግዚአብሔር ፊት ክፋት ለመሥራት ራሱን እንደ ሸጠ፥ ሚስቱም ኤልዛቤል እንደ ነዳችው፥ እንደ አክዓብ ያለ ሰው አልነበረም.. ጣዖታትን በመከተል እጅግ ርኩስ ነገር ሠራ።  አክዓብም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ ገላውን ማቅ አለበሰ፥ ጾመም፥ በማቅ ላይም ተኛ፥ ቅስስ ብሎም ሄደ። ደግሞም፡- አክዓብ በፊቴ እንደ ተዋረደ አየህን?  በፊቴ የተዋረደ ስለ ሆነ በልጁ ዘመን በቤቱ ላይ ክፉ ነገር አመጣለሁ እንጂ በእርሱ ዘመን ክፉ ነገር አላመጣም የሚል የእግዚአብሔር ቃል ..ወደ ኤልያስ መጣ (1ነገ 20 ) ።   ማብራሪያ አክአብ የእስራኤል ንጉሥ ሲሆን ናቡቴን፡- የወይን እርሻህን ስጠኝ ባለው ጊዜ እምቢ ሲለው ተናድዶ ጥቅልል ብሎ በአልጋው ውስጥ በመተኛት በናቡቴ ላይ ፈጽሞ ክፉ ላለማደረግ ማሰቡ መልካም ነበር፡፡ ሚስቱ ናቡቴን አስገድላው፡- ተነሥተህ የወይኑን እርሻ ውረስ ብላ ስትነግረው፡- ጥሩ አላደረግሽም በማለት አለመተባበር ነበረበት፡፡ በተጨማሪም ጣዖታት በአገሩ ላይ እንዲመለክ በማድረጉ እግዚአብሔርን ያስቆጣ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ክፉ እንደሚያመጣበት ለአክአብ በነቢዩ ኤልያስ በኩል ተናገረው፡፡ አክአብ ክፉ እንደሚመጣበት ሲነገረው ወደ ቤቱ በታላቅ ሀዘን ሄደ ፤ ልብሱን በመቅደድ ማቅ ለብሶ በጾም ራሱን በእግዚአብሔር ፊት አዋረደ፡፡ እግዚአብሔር የአክአብን መዋረድ ስለ ተመለከተ በዘመኑ ሊያመጣ ያሰበበትን ክፉ ነገር አሳልፎለት በልጁ ዘመን እንደሚያመጣ ተናገረ፡፡ ወገኖቼ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር እንዴት ያለ መሐሪ አምላክ እንደ ሆነ እንይ፡፡ አክአብ እግዚአብሔርን እንዴት እንደ በደለ አይተናል፡፡ አክአብ የናቤቴ ደም በመፍሰሱ ያልተጸጸተ በተጨማሪም ጣዖትን በማምለክ እግዚአብሔርን ያስቆጣ ሲሆን በእግዚአብሔር ፊት ሲዋረድ ግን ቸርነቱ የበዛ አምላክ መዋረዱን ተመልክቶለታል፡፡ የምናመልከው አምላክ ከምናስበው በላይ መሐሪ አምላክ ነው፡፡ በድለነው በፍጹም ልባችን ስንጸጸት ይቅር የሚለን አምላክ ነው፡፡ ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አንበድል ፤ ከበደልነው በኋላ ደግሞ ዛሬ ነገ ሳንል ወዲያውኑ ይቅር እንዲለን እንለምነው ፤ የማይጨክን አምላክ ነውና ይቅር ይለናል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይም፡፡   እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፡- … በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ፤ በልጆቹ መካከል ንጉሥ አዘጋጅቻለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ አለው።… እሴይንና ልጆቹንም ቀደሳቸው፥ ወደ መሥዋዕቱም ጠራቸው። እንዲህም ሆነ፤ በመጡ ጊዜ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ፡- በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው አለ። እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፡- ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው። እሴይም አሚናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት አሳለፈው፤ እርሱም፡- ይህን ደግሞ እግዚአብሔር አልመረጠውም አለ። እሴይም ሣማን አሳለፈው፤ እርሱም፡- ይህን ደግሞ እግዚአብሔር አልመረጠውም አለ። እሴይም ከልጆቹ ሰባቱን በሳሙኤል ፊት አሳለፋቸው። ሳሙኤልም እሴይን፡- እግዚአብሔር እነዚህን አልመረጠም አለው። ሳሙኤልም እሴይን፡- የቀረ ሌላ ልጅ አለህን? አለው። እርሱም፡- ታናሹ ገና ቀርቶአል፤ እነሆም፥ በጎችን ይጠብቃል አለ። ሳሙኤልም እሴይን፡- እርሱ እስኪመጣ ድረስ አንረፍቅምና ልከህ አስመጣው አለው። ልኮም አስመጣው፤ እርሱም ቀይ፥ ዓይኑም የተዋበ፥ መልኩም ያማረ ነበረ። እግዚአብሔርም፡- ይህ ነውና ተነሥተህ ቅባው አለ። ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው ( 1ሳሙ 16 ፥ 1 - 13 ) ።   ማብራሪያ እሴይ የዳዊት አባት ነው፡፡ እሴይ እዚህ ግባ የማይበል ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን በልጆቹ መካከል ንጉሥ አዘጋጀ፡፡ ደካማ ብንሆንም እዚህ ግቡ የማንባል ብንሆንም በእግዚአብሔር የምንታይበት ቀን አለን፡፡ እግዚአብሔር ደስ የሚል አምላክ ነው፡፡ ሳሙኤል እግዚአብሔር እንዳለው ለእስራኤል ንጉሥ የሚሆነውን ለመቀባት እሴይን አስጠራ፡፡ እሴይ እግዚአብሔር ሊቀባው የሚፈልገውን ልጁን ትቶ ፣ ሰባቱን ልጆቹን ይዞ በሳሙኤል ፊት ቀረበ፡፡ ሳሙኤል የእሴይን በኵሩን ልጅ ተመለከተ፡፡ ቁመቱንና መልኩን አይቶ ከሌሎቹ ወንደሞቹ የተሸለ መሆኑን አሰበና ሊቀባው ተዘጋጀ፡፡ በኵሩ ኤልያብ ንጉሥ እንደሚሆን ደመደመ፡፡ ሳሙኤል የተደነቀበትን ሰው እግዚአብሔር ናቀው፡፡ ቀሪዎቹን ስድስቱንም እግዚአብሔር አልመረጣቸውም፡፡ እሴይ ይዟቸው የመጣቸው ሰባቱም ልጆች ለንግሥና በእግዚአብሔር ሳይመረጡ ቀሩ፡፡ ሳሙኤል የቀረ ልጅ እንዳለው ገመተና እሴይን፡- የቀረ ልጅ ካለ ይምጣ አለ፡፡ የቀረው ልጅ የሁሉ ታናሽ ነበር፡፡ በጎቹንም ለእሴይ የሚጠብቅለት ነበር፡፡ ልኮ አስመጣው፡፡ እግዚአብሔርም፡- ይህ ነውና ቅባው አለው፡፡ ሳሙኤልም ቀባው፡፡ እሴይ ለንግሥና የሚቀባውን ልጁን ትቶት ነበር የመጣው፡፡ የእግዚአብሔር አሠራር የሚገርም ነው፡፡ የመጀመሪያውን በኵሩን ናቀ፡፡ የመጨረሻ የሆነውንና የተተወውን ግን በኵሩ እያለ ለንግሥና እንዲቀባ አደረገው፡፡ የሁሉ መጨረሻ የነበረው ብላቴናው ዳዊት ስድስቱን ታላላቆቹንና በኵሩን ( መጀመሪያውን ) ኤልያብን ሳይቀር አስንቆ ተገኘ፡፡ ሰው እንደሚያይ ቢሆን ኖሮ ዳዊት ተትቶ በኵሩ ኤልያብ ነግሦ ነበር፡፡ አንዳንድ ሰርግ ላይ ለልጆች ቦታ የለንም ይላሉ፡፡ ታናናሾች የሆንን በእግዚአብሔር ዘንድ ቦታ እንደሌለን ብናስብም እግዚአብሔር ግን ታናናሾችንን ሊያውም ለታላቅ ነገር ያስባቸዋል፡፡ በፊቱ ምስኪኑም ተስፋ አለው፡፡ እግዚአብሔር ሰው እንደሚያይ አያይም፡፡ ሰው እንደሚያይ ቢሆን ኖሮ ዳዊት በእሴይ በአባቱና በሳሙኤል የተተወ ነበር፡፡ አባቱ ቀድሞውኑ በእግዚብሔር ይታያል ብሎ ስላላሰበ ይዞት አልሄደም፡፡ ሳሙኤል ደግሞ ከቀረቡለት የእሴይ ልጆች መካከል በኵሩን ሲያየው ቁመቱንና መልኩን አይቶ፡- እግዚአብሔር የሚቀባው ይህ ነው አለ፡፡ እግዚአብሔር ግን ነቢዩ ሳሙኤልና እሴይ እንደሚያዩ አላየም፡፡ ሁለቱም ያላዩትን ትንሹን ዳዊትን እንዲቀባና እንዲነግሥ አደረገ፡፡ አዎ ሰው ፊትን ያያል እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል፡፡ እግዚአብሔር ሰው እንደሚያይ አያይም፡፡ እሴይና ነቢዩ ሳሙኤል ከታላቁ ኤልያብ በመጀመር ወደ ታች ወረዱ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ከታናሹ ዳዊት ከታች ጀመረ፡፡ ሰው እንደሚያይ ቢሆንማ ኖሮ ብዙዎቻችን ቦታ አይኖረንም ነበር፡፡ ምስኪኑን ከጉድፍ የሚያነሣ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ በድጋሚ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie