እግዚአብሔርን ማወቅ
الذهاب إلى القناة على Telegram
ሰላምታ በተለዋወጥን ቁጥር ይመስገን ስለምንለው አምላካችንና አባታችን እግዚአብሔር ያለንን ዕውቀት ለማዳበር የሚያግዝ ቻነል ነው፡፡
إظهار المزيد975
المشتركون
+124 ساعات
+57 أيام
+1630 أيام
أرشيف المشاركات
975
እግዚአብሔር አይጥልም ፡፡
ኤፍሬም ሆይ፥ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፥ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አዳማ እጥልሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዮ አደርግሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፥ ምሕረቴም ተነሣሥታለች።
እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥ በመካከልህም ቅዱሱ ነኝና የቁጣዬን መቅሠፍት አላደርግም፥ ኤፍሬምንም አጠፋ ዘንድ አልመለስም፤ በመዓትም አልመጣም ( ሆሴዕ 11 ፥ 8 ፡ 9 ) ።
ማብራሪያ
ኤፍሬም ሆይ የሚለው የእስራኤልን ሕዝብ ነው፡፡ የሰሜኑን መንግሥት ያመለክታል፡፡
አዳማና ሲባዮ ሰዶም በጠፋች ጊዜ የፈረሱ ከተሞች ናቸው፡፡
የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር አብዝቶ ቢጠራቸው አጥብቀው የራቁ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ከፊቱም ርቀው በመሄድ የሚጠላውን ጣዖት የሚያመልኩ ነበሩ፡፡ ከፊቱ በመራቃቸው የተጎዱት ራሳቸው ናቸው፡፡
በራሳቸው መንገድ ከመሄዳቸው የተነሣ ሲጎዱ የእግዚአብሔርን ርኅራኄ ከማሰብ ይልቅ ቁጣውን አግነው ሊመለከቱ ይችላሉ፡፡ ርኅራኄውን አሳንሰው ሰዶም ስትጠፋ አዳማና ሲባዮን ያጠፋውን ቁጣውን ብቻ ልብ ሊሉ ይችላሉ፡፡
እግዚአብሔር በድለውት እንደማይጥላቸው፣ እንደ አዳማና ሲባዮ እንደማያጠፋቸው ቃል ይገባላቸዋል፡፡ እኛው በድለንና በገዛ ፈቃዳችን መሄዳችን ዋጋ ስላስከፈለን ስናለቅስ መልሶ ደግሞ ያባብለናል፤ ያጽናናናል፡፡ እንደ እግዚአብሔር ያለ አምላክ ከቶ የለም፡፡
በደለኞች ስለሆንን የእግዚአብሔር ቅዱስነት ያስፈራናል፡፡ እውነት ነው እግዚአብሔር ቅዱስ ነው፡፡ በደለኛ ሆኖ ቅዱሱ ፊት መቅረብ ያስፈራል ፡፡ ይህ የሚሳየው ፈሪሀ እግዚአብሔር እንዳለን ነው፡፡ ደግሞ የምንረሳው አንድ ትልቅ ነገር አለ፡፡ የእግዚአብሔር ርኅራኄውን ነው፡፡
የጦርነት ቀጠና በሆነች አገር ውስጥ የሚኖር ሰው ከአሁን አሁን ሞትኩ እያለ ሁሌም እየተሳቀቀ ይኖራል ፡፡ ሰው የእግዚአብሔርን ርኅራኄ ካላወቀ በቤቱ የሚኖረው ኑሮ የሰቀቀን ነው፡፡ በበደለ ቁጥር ከአሁን አሁን ጠፋሁ እያለ በስጋት ይኖራል፡፡ ብንበድለውም ፡- ይቅር በለን ብለን ፊቱ ስንቀርብ ይራራልናል፡፡
እኛ ሰው በመሆናችን ብንበድልም እግዚአብሔር ሰው ስላልሆነ የርኅራኄ አምላክ በመሆኑ ይራራልናል፡፡
እንዴት እጥልሃለሁ? እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አዳማ እጥልሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዮ አደርግሃለሁ? የሚሉት ንግግሮቹ ውስጣችን ገብተው የሚቀሩ አንጂ የሚወጡ አይደሉም፡፡
በተጨማሪም ለበደለው ለእስራኤል ሕዝብ ርኅራኄ ለማድረግ ፡- ልቤ በውስጤ ተናውጣለች ( ርኅራኄን ያዘለ ቃል )፥ ምሕረቴም ተነሣሥታለች ብሎ የተናገረው ቃል ከእርሱ ጋር በምናደርገው ጉዞ ስንወድቅ የሚያነሳን የእግዚአብሔር ርኅራኄ እንዳለ ስናውቅ ትልቅ ተስፋ እንድንሰንቅና በእግዚአብሔር ቤት ለመኖር የምንፈልገውን መሻታችንን የበለጠ አስተማማኝ ያደርግልናል፡፡
ርኅራኄ ያዘሉ ቃላቱን ልብ እንበላቸው፡፡
እንዴት እጥልሃለሁ? እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ ------ እጥልሃለሁ ( እንደ አዳማ ) ? እንዴትስ እንደ ------- አደርግሃለሁ ( እንደ ሲባዮ )? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፥ ምሕረቴም ተነሣሥታለች። እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥ የቁጣዬን መቅሠፍት አላደርግም፥ በመዓትም አልመጣም።
አምላካችን ሆይ ስለ ርኄራኄህ እናመሰግንሀለን፤ አሜን!
ኤፍሬም ሆይ( እስራኤል ሆይ ) ፥ እንዴት እጥልሃለሁ ( ሆሴዕ 11 ፥ 8 ) ?
የእግዚአብሔርን ርኅራኄ አሳንሰን ቁጣውን አግነን መመልከት የለብንም፡፡ ከቁጣው ይልቅ ርኅራኄው ብዙ ነው፡፡
እግዚአብሔር ይጥለኛል ብለን ለምናስብ እንዴት እጥልሃለሁ? ብሎ እርሱ ራሱ እንደማይጥል የተናገረውን አንርሳ፡፡
ሰው ይጥላል እርሱ ግን እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁም ያለውን ከቶ መዘንጋት የለብንም፡፡ አምላክ ደግሞ አይረሳም፡፡ እንደ ሰው እያሰብነው ስለ ተቸገርን ራሱም፡- ሰው አይደለሁም በማለቱ ርኅሩኅ አምላክ መሆኑን ነግሮናል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ አሜን!
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
ወንጌል እንማር ፡፡
ክፍል 8 (፰) ፡፡
የጌታችን በዲያብሎስ መፈተን ፡፡
ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። እርሱም መልሶ፡- ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።
ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ። መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው። ኢየሱስም፡- ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው።
ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ። ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው። ያን ጊዜ ኢየሱስ፡- ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው። ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ተወው፥ እነሆም፥ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር ( ማቴ 4 ÷ 1 - 11 ) ።
ማብራሪያ
ፈታኝ የተባለው ዲያብሎስ ነው፡፡
ዲያብሎስ ለክርስቶስ፡- ድንጋዩን እንጀራ እንዲሆኑ እዘዛቸው ሲለው ጌታችን ተርቦ ነበር፡፡ ድንጋዩን ወደ እንጀራ መቀየር ይችላል፡፡ ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ ሲቀይር ወደ ፊት እናያለን፡፡ ሆኖም ለዲያብሎስ መታዘዝ ስለሌለበት ከኦሪት ዘዳግም በመጥቀስ፡- ሰው የሚኖረው በእንጀራ ብቻ አይደለም፡፡ ሰው እንጀራ እንደሚያስፈልገው ሁሉ የእግዚአብሔርም ቃል ያስፈልገዋል በማለት መለሰለት ( ዘዳ 8 ÷ 3) ፡፡ ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ሲል ጥቅሱን የጠቀሰው ተርቦ እያለ ነው፡፡
ከእግዚአብሔር ቃል ተጠቅሶለት የተሸነፈው ዲያብሎስ የሁለተኛውን ጥያቄ ጥቅስ በመጥቀስ ( የእግዚአብሔርን ቃል ተንተርሶ ) ጠየቀው ፡፡ ከመቅደስ ጫፍ ላይ ራስን ወርውር ነበር ጥያቄው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ ሆንክ አብ መላእክትን ያዝልሃል ፤ መላእክትም በእጃቸው ያነሱሃል ( መዝ 90 ÷ 11 ፡ 12 ) በሚል ላመሉ ከመዝሙረ ዳዊት ጥቅስ ጠቅሶ መሆኑ ነው፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራስን ዝም ብሎ መወርወር እግዚአብሔርን መፈታተን መሆኑን ከቃሉ ጠቅሶ መለሰለት ( ዘዳ 6 ÷ 16 )፡፡
በሦስተኛው ጥያቄ የድፍረቱ ድፍረት፡- ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህንና ይህን እሰጥሃለሁ ብሎ አረፈው፡፡ ለአንደኛውና ለሁለተኛው ጥያቄ እንደ መለሰለት ሁሉ ለሦስተኛውም ጥያቄ ከእግዚአብሔር ቃል በመጥቀስ ፡- ለአምላክህ ስገድ እርሱን ብቻ አምላክ ተብሎአል ብሎ ( ዘዳ 6 ÷ 13 ) ድል ነሳው፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ለሦስቱም ጥያቄዎች ለዲያብሎስ የመለሰለት ከኦሪት ዘዳግም ነው፡፡
ዲያብሎስ ክርስቶስን ሲፈትነው በሁለቱ ጥያቄዎች፡- የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ የሚልን ቃል ተጠቅሟል፡፡ ወልድ ( ክርስቶስ ) የአብ ልጅ በመሆኑ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ በሥጋ የተገለጠው የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ነው፡፡ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ ተብሎ ተጽፎአልና ( 1ዮሐ 3 ÷ 8 ፡ 9 ) ፡፡
ክርስቶስ ዲያብሎስን በመስቀል ላይ በማያዳግም ሁኔታ ድል ስለ ነሳልን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እኛም ድል እንነሳዋለን፡፡ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ለመስዋዕትነት እንደ ንፁህ በግ ሆኖ በቀራንዮ በመቅረብ ደሙን አፍስሶልናል፡፡ በፈሰሰው ደሙ ኃጢአታችን ተሰርዮልናል፡፡ ኃጢአት ሠርተን ደግሞ ፡- ይቅር በለን ስንለው በፈሰሰው ደሙ ከኃጢአታችን መልሶ ያነፃናል ፡፡
ዲያብሎስ ፈተና እያመጣብን በፈተናው እየጣለን መልሶ ደግሞ በመክሰስ ሰላም ሊያሳጣንና ከእግዚአብሔር ሊለየን ይፈልጋል፡፡ ስለ ኃጢአታችን በፈሰሰው በበጉ ( በክርስቶስ ) ደም ድል ልንነሳው ይገባል፡፡ ከበጉ ደም የተነሳ ድል ነሱት ይላልና ( ራዕ 12 ÷ 11 )፡፡ ዲያብሎስ ለሠራነው ኃጢአት ይቅር እንደማንባል በመክሰስ ድል ሊነሳን ይፈልጋል፡፡ የፈሰሰው የክርስቶስ ደም ደግሞ ስለ ኃጢአታችን መሆኑን ሁሌም ካስተዋልን፡- ይቅር በለን በምንለው አምላካችን ዘንድ በፈሰሰው በበጉ ( በክርስቶስ ) ደም እንደምንነጻና ይቅር እንደምንባል ስለሚገባን ለሚከሰን ክስ ቦታ አንሰጠውም፡፡ ክሱን ቦታ አለመስጠታችን ድል ነሳነው ማለት ነው፡፡ ስለ ኃጢአታችን የፈሰሰውን ደም መዘንጋት ግን ዋጋ ያስከፍላል፡፡
ዲያብሎስ ፈታኝ ነው፡፡ ፈተናም ያለ ነው ፡፡ ባንፈተን መልካም ነው፡፡ ፈተና አይኑር ማለት አንችልም፡፡ በተለያየ ምክንያት ፈተና ከመጣብን ትልቁ ነገር በፈተናው እጅ አለመስጠት ነው፡፡ ፈተናውን ሥጋችን ቢያቅተው አንኳን እምቢታችንን ( አልታዘዝልህም የሚል ቃውሞአችንን ) በውስጣችን ማሰማት ተገቢ ነው፡፡ ብንፈተንም ከፈተናው ለመውጣት የእግዚአብሔርን እርዳታ መፈለግ አስፈላጊ ነው፡፡
ፈተናው የቱንም ያህል ቢበረታብን የሚረዳን አምላካችን ክርስቶስ እንዳለ እንወቅ፡፡ በዲያብሎስ የተፈተነው ጌታችን የምንፈተነውን እኛን ይረዳናል፡፡
እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና ( ዕብ 2 ÷ 18 )። የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና የሚለው ስንፈተን እንደሚረዳን የሚያስገነዝበን ቃል ነው፡፡
ክርስቶስ ልክ የሚዋኙ ሰዎች ሲሰምጡ እንደሚያወጣ ዋናተኛ ( ሕይወት አድን ) ነው፡፡ ሕይወት አድን ውኃው ውስጥ ገብተው የሚዋኙትን በንቃት ይከታተላል፤ ሲሰምጡ ወደ ውኃው ውስጥ ዘሎ በመግባት ዋኝቶ ያወጣቸዋል፡፡ ክርስቶስም ስንፈተንና ፈተናው ሲያሰምጠን ከፈተናው የሚያወጣን ርኅሩኅ አምላክ ነው፡፡ ስንፈተን ብቻችንን እንዳልሆንንና የሚረዳን፣ ከፈተናው የሚያወጣንም አምላክ እንዳለን ማወቅ ትልቅ ሐሴትና መረጋጋት ይሰጣል፡፡
የምንፈተነው እኛ ብቻ አይደለንም፡፡ በወቅቱ አብሮአቸው የነበሩትን ሐዋርያትን ሳይቀር ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊበጥራቸው ፈልጎ ነበር፡፡
ጌታም፡- ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ ( ሉቃ 22 ÷ 31 ፡ 32 ) ።
ስምዖን የተባለው ጴጥሮስ ነው፡፡ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራቸው ቢፈልግም ስለ አንተ ጸለይኩ ( አማለድሁ ) በማለት ለጴጥሮስ መልሶለታል፡፡ ክርስቶስ በሥጋው ወራት ወደ አባቱ ይጸልይ ነበር፡፡ እዚህ ጋር እንድንማር የፈለኩት ዲያብሎስ የቱንም ያህል ፈተና በማምጣት ቢበረታብን ብርቱ የሆነው ክርስቶስ ደግሞ እንደማይተወን ለማሳየት ነው፡፡
ዲያብሎስን ለማሸነፍ ቃሉን ማወቅ ተገቢ ነውና ሁሌም ቃሉን መማራችንንና ብንችል ደግሞ በግላችን ዘወትር መጽሐፍ ቅዱስን ማንበባችንን አንተው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ አሜን!
ይቀጥላል፡፡
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
ሰዎችን የሚገድሉ እነርሱም የውርደት ሞት ይሞታሉ ፡፡
የይሩበኣል ( የጌድዮን ) ልጅ አቤሜሌክም ወደ ሴኬም ወደ እናቱ ወንድሞች ሄደ፥ ለእነርሱም ለእናቱ አባት ቤተ ሰቦችም ሁሉ፡- በሴኬም ሰዎች ሁሉ ጆሮ፡- ሰባ የሆኑት የይሩበኣል ( የጌድዮን ) ልጆች ሁሉ ቢገዙአችሁ ወይስ አንድ ሰው ቢገዛችሁ ምን ይሻላችኋል? ብላችሁ ንገሩአቸው ብዬ እለምናችኋለሁ፤ ደግሞ እኔ የአጥንታችሁ ፍላጭ የሥጋችሁ ቍራጭ እንደ ሆንሁ አስቡ ብሎ ተናገራቸው።
የእናቱም ወንድሞች ይህን ቃል ሁሉ ስለ እርሱ በሴኬም ሰዎች ሁሉ ጆሮ ተናገሩ፤ እነርሱም፡- እርሱ ወንድማችን ነው ብለው አቤሜሌክን ለመከተል ልባቸውን አዘነበሉት።
...ሰባ የሆኑትን የይሩበኣልን ልጆች ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ አረዳቸው፤ ትንሹ የይሩበኣል ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ነበርና ተረፈ። የሴኬምም ሰዎች ..አቤሜሌክን አነገሡ።
ይህንም ነገር ለኢዮአታም በነገሩት ጊዜ፥ ሄዶ በገሪዛን ተራራ ራስ ላይ ቆመ፥ ድምፁንም አንሥቶ ጮኸ፥ እንዲህም አላቸው። የሴኬም ሰዎች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲሰማችሁ ስሙኝ።
አንድ ጊዜ ዛፎች በላያቸው ንጉሥ ሊያነግሡ ሄዱ፤ ወይራውንም፡- በእኛ ላይ ንገሥ አሉት። ወይራው ግን፡- እግዚአብሔርና ሰዎች በእኔ የሚከበሩበትን ቅባቴን ትቼ በዛፎች ላይ እንድሰፍፍ ልሂድ? አላቸው።
ዛፎችም በለሱን፡- መጥተህ በላያችን ንገሥ አሉት። በለሱ ግን፡- ጣፋጭነቴንና መልካሙን ፍሬዬን ትቼ በዛፎች ላይ እንድሰፍፍ ልሂድ? አላቸው።
ዛፎችም ውይኑን፡- መጥተህ በላያችን ንገሥ አሉት። ወይኑም፡- እግዚአብሔርንና ሰውን ደስ የሚያሰኘውን የወይን ጠጄን ትቼ በዛፎች ላይ እንድሰፍፍ ልሂድ? አላቸው።
ዛፎችም ሁሉ እሾህን፡- መጥተህ በላያችን ንገሥ አሉት። እሾሁም ዛፎችን፡- በእውነት እኔን በእናንተ ላይ ታነግሡኝ እንደ ሆነ ኑ ከጥላዬ በታች ተጠጉ። እንዲሁም ባይሆን እሳት ከእሾህ ይውጣ፥ የሊባኖስንም ዝግባ ያቃጥል አላቸው።
አሁን እንግዲህ አቤሜሌክን በማንገሣችሁ እውነትንና ቅንነትን አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ ለይሩበኣልም ለቤቱም በጎ አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ ..አባቴ ስለ እናንተ ተጋድሎ ነበርና፥ ከምድያምም እጅ ሊያድናችሁ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶ ነበርና፥ እናንተም ዛሬ በአባቴ ቤት ተነሥታችኋልና፥ ሰባ የሆኑትን ልጆቹንም በአንድ ድንጋይ ላይ አርዳችኋልና፥ ወንድማችሁም ስለ ሆነ የባሪያይቱን ልጅ አቤሜሌክን በሴኬም ሰዎች ላይ አንግሣችኋልና፥
እንግዲህ ለይሩበኣልና ለቤቱ እውነትንና ቅንነትን ዛሬ አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ በአቤሜሌክ ደስ ይበላችሁ፥ እርሱ ደግሞ በእናንተ ደስ ይበለው፤ እንዲህ ባይሆን ግን ከአቤሜሌክ እሳት ይውጣ፥ የሴኬምንም ሰዎች ..ይብላ፤ ከሴኬምም ሰዎች ..እሳት ይውጣ፥ አቤሜሌክንም ይብላ። ኢዮአታምም ሸሽቶ አመለጠ፥ ወንድሙንም አቤሜሌክን ፈርቶ ..ሄደ፡፡
አቤሜሌክም በእስራኤል ላይ ሦስት ዓመት ነገሠ።
በአቤሜሌክ ላለ የመጣ የእግዚአብሔር ፍርድ ::
እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ፤ የሴኬምም ሰዎች በአቤሜሌክ ላይ ተንኰል አደረጉ። ይህም የሆነው፥ በሰባ የይሩበኣል ልጆቹ ላይ የተደረገው ዓመፅ እንዲመጣ፥ ደማቸውም በገደላቸው በወንድማቸው በአቤሜሌክ ላይ፥ ወንድሞቹንም እንዲገድል እጆቹን ባጸኑአቸው በሴኬም ሰዎች ላይ እንዲሆን ነው።
አቤሜሌክም በሴኬም ግንብ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ሆነው እንደ ተሰበሰቡ ሰማ። …ሕዝቡም ሁሉ እንዲሁ እያንዳንዳቸው የዛፉን ቅርንጫፎች ቈረጡ፥ አቤሜሌክንም ተከትለው በምሽጉ ዙሪያ አኖሩአቸው፥ ምሽጉንም በላያቸው አቃጠሉት፤ የሴኬምም ግንብ ሰዎች ሁሉ ደግሞ አንድ ሺህ የሚያህሉ ወንድና ሴት ሞቱ።
አቤሜሌክም ወደ ቴቤስ መጣ፥ ቴቤስንም ከብቦ ያዛት። በከተማይቱም ውስጥ ብርቱ ግንብ ነበረ፥ የከተማይቱም ሰዎች ሁሉ፥ ወንዱና ሴቱ ሁሉ፥ ወደዚያ ሸሹ፤ ደጁንም በኋላቸው ዘጉ፥ ወደ ግንቡም ሰገነት ላይ ወጡ። አቤሜሌክም ወደ ግንቡ ቀርቦ ይዋጋ ነበር፥ በእሳትም ሊያቃጥለው ወደ ግንቡ ደጅ ደረሰ። አንዲትም ሴት በአቤሜሌክ ራስ ላይ የወፍጮ መጅ ጣለችበት፥ አናቱንም ሰበረችው።
እርሱም ፈጥኖ ጋሻ ዣግሬውን ጠርቶ፡- እኔን ሴት ገደለችው እንዳይሉ ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ አለው፤ ጕልማሳውም ወጋው፥ ሞተም። ..እንዲሁ ሰባ ወንድሞቹን በመግደል አቤሜሌክ በአባቱ ላይ ያደረገውን ክፋት እግዚአብሔር መለሰበት። እግዚአብሔርም የሴኬምን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰባቸው፤ የይሩበኣልም ልጅ የኢዮአታም እርግማን ደረሰባቸው ( መሳ 9 ) ።
ማብራሪያ
በእናት ቢለያዩም በአባት አንድ የሆኑትን የገዛ ሰባ ወንድሞቹን አቤሜሌክ አረዳቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ የሴኬም ሰዎች የእናቱ ዘመዶች ተባባሪ ነበሩ፡፡ ከመገደል ያመለጠው ትንሹ ወንድሙ የመሰለባቸው ምሳሌ ያነገሣችሁት አቤሜሌክ እንደ እሾክ ነው ፤ አይጠቅማችሁም ለማለት ነው፡፡
ከአቤሜሌክ እሳት ይውጣ፥ የሴኬምንም ሰዎች ይብላ፤ ከሴኬምም ሰዎች እሳት ይውጣ፥ አቤሜሌክንም ይብላ እንዳለው ከሦስት ዓመት በኋላ የእግዚብሔር ፍርድ መጣ፡፡ አቤሜሌክና ያነገሡት የገዛ ዘመዶቹ የሴኬም ሰዎች እርስ በርስ ጦርነት አደረጉ፡፡ እርስ በርሳቸው መበላላት ጀመሩ፡፡ አቤሜሌክም የገዛ ዘመዶቹን የሴኬምን ሰዎች በሺህ የሚቆጠሩትን ገደለ ፡፡
ጀግና የሆነ መስሎት ሰባ ወንድሞቹን ባረዳቸው አቤሜሌክ ላይ ጀግናዋ ሴት መጅ ወርውራ አቤሜሌክን አንገቱን ሰበረችው፡፡ ሴት ገደለችው እንዳይባል አብሮ ያለውን ጋሻ ጃግሬውን ግደለኝ ብሎ ቢገድለውም ስለ አቤሜሌክ በተነሣ ቁጥር ፡- ሴት ገደለችው ተብሎ በእስራኤል መወራቱ አልቀረለትም ( 2ሳሙ 11 ÷ 21)፡፡
አቤሜሌክ በሚያሳፍር ሁኔታ ሞተ፡፡ ሰባ ወንደሞቹን በማረዱ እግዚአብሔር ተበቀለው፡፡ የሞተውም ሊያውም የውርደት ሞት ነው፡፡
በዚህ በ21ኛው መቶ ክ / ዘ ዓለም በዘመነበት ሰውን በግፍ መግደል አሳዛኝ ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን ይፈርዳል ፤ በክፉ ዲያብሎስ እየተነዱ ሰው የሚገድሉ አሟሟታቸው የውርደት ሞት ነው፡፡ ሰውን ሲገድሉና ሲያስገድሉ የነበሩ ፍጻሜአቸው አያምርም ፡፡ ክፉ ለሚያደርጉ ሁሉ ምሳሌ ሆነው በክፉ ሲነሡም ይኖራሉ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ አሜን!
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
ወንጌል እንማር ፡፡
ክፍል 7 ( ፯ ) ፡፡
ክርስቶስ በዮሐንስ መጠመቁና ትህትናው ፡፡
ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ዮሐንስ ግን፡- እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር። ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።
ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ ( ማቴ 3 ÷ 13 - 17 ) ።
ማብራሪያ
ከበላይ እንዳነበብነው ኢየሱስ ወደ ዮሐንስ መጣ እንጂ ዮሐንስ ኢየሱስ ወዳለበት ሄዶ አላጠመቀውም፡፡ አለቃ የሆነ ሰው ከበታቹ ያለውን ሰው ለሆነ ጉዳይ ቢፈልገው፡- ቤሮዬ ድረስ ሊያውም ባስቸኳይ ና ይለዋል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ዮሐንስን ያለበት ድረስ እንዲመጣ ማዘዝ ሲችል ነገር ግን በእግሮቹ ተጉዞ ዮሐንስ ወዳለበት ድረስ መጣ፡፡
የክርስቶስ አድራጎት ሁሌም ልብን ይነካል፡፡ አምላክ እንዴት ትሁት ነው! ሥጋ ለብሶ መጥቶ ትህትናውን አየነው፡፡ የክርስቶስን አድራጎት ስመለከት እኔ ብዙ የሚቀረኝ ሰው እንደሆንኩ እገነዘባለሁ፡፡
ዮሐንስ ወዳለበት መምጣቱ ሲያስገርም ደግሞ ሌላው የሚገርመው ነገር ክርስቶስ ልጠመቅ አለ፡፡ ሥጋ ይልበስ እንጂ አምላክ ነው፡፡ አምላክን ማን ያጠምቃል? እርሱን ለማጥመቅ ክብር ማን የበቃ አለ? አይሁድ መጥምቁ ዮሐንስ ሲያጠምቅ አይተውት ከጠየቁት ጥያቄ አንዱ፡- ክርስቶስ ( መሢሕ ) ነህን ? ነበር፡፡ እርሱ ግን ሲመልስ፡- እኔ ክርስቶስ አይደለሁም አለ፡፡ እንዲያውም ያለው፡- የጫማውን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ ነኝ ነበር ( ዮሐ 1 ÷ 19 - 27 ) ፡፡ የጫማውን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ ያለለት ( ክርስቶስ ) አጥምቀኝ አለው ፡፡
ዮሐንስ ለክርስቶስ፡- ወደ አንተ መምጣት ሲገባኝ አንተ ወደኔ ትመጣለህን? በማለት ተናገረ፡፡ ክርስቶስ መምጣቱን ዮሐንስ ወዳለበት ድረስ መጣ፤ ስለዚህ መምጣቱን በተመለከተ ፡- አንተ ወደኔ ትመጣለህን? ከማለት ውጪ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ብዙ ሰዎችን ለንስሐ ሲያጠምቅ የነበረው ዮሐንስ አጥምቀኝ ለተባለው ነገር፡- እኔ ባንተ ልጠመቅ ይገባኛል በማለት መለሰ፡፡ ማጥመቅ ሳይሆን የታየው መጠመቅ ነው፡፡
አጥምቀኝ መባሉን ግን መከልከል ጀመረ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የከለከለውን ዮሐንስን ፡- ፍቀድልኝ አለው፡፡ ፍቀድልኝ የሚለው አነጋገሩ የሚያስገርም አባባል ነው፡፡ በእርሱም መጠመቁ ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም እንደሆነ ለዮሐንስ ነገረው፡፡ ከአእምሮው በላይ ሆኖበት ሲከለክል የነበረው ዮሐንስ ፈቀደለት፡፡
እስራኤላውያን እንዲሻገሩ የዮርዳኖስን ወንዝ እንደ ክምር ያቆመው አምላክ ( ኢያሱ 3 ÷ 14 - 17 ) በዛው ወንዝ ሊጠመቅ ገባ፡፡ እርሱ በፈጠረው ሰው ተጠመቀ፡፡ አቤት ትህትና ! እንደምን ያለ ትህትና ነው! አምላኬ ያኮራኛል፡፡ ክርስቲያን መሆኔ ያስደስተኛል፡፡ አምላኬ ትሁት ነው፡፡ ሰውን ለማዳን የመጣው አምላክ ሊያድነው በመጣለት ሊያውም በበደለው ሰው ተጠመቀ፡፡
በክርስቶስ ጥምቀት የእግዚአብሔር ሦስትነት ተገለጠ፡፡
አብ፡- በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።
ወልድ ራሱ ተጠማቂው ነው
መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ እንደ ርግብ ወርዶ ታየ፤ በክርስቶስም ላይ ኖረ፡፡
ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፡፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ አሜን፡፡
ምስጋና ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ መቼም መች ለዘላለሙ አሜን፡፡
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
እስቲ አስቡት ! ከኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልኩ ብሎ የተናገራቸው ቃል ገና ሳይርቅና ግልባጩም በዕላቱ ተጽፎ እስኪሰጣቸው ሳይይጠብቁ ቸኩለው ጣዖት ያመለኩትን ሕዝቦች ሙሴ ሲጸልይ መልሶ ይቅር ያለ አምላክ በድላችሁት፡- ይቅር በለን ያላችሁት አምላክ መልሶ እንዴት ይቅር አይላችሁም? ይቅር ያላቸው ሕዝቦች እኮ ይቅር በለን ሳይሉ እጃቸውን አጣጥፈው የተቀመጡ ነበሩ፡፡
እውነተኛ መንፈሳዊ እረኛ ( መሪ ) ስለ ሕዝቡ ሸክም ስላለው ምዕመናን (ት ) እግዚአብሔርን ሲበድሉ ፡- ማራቸው ራራላቸው የሚል ነው፡፡ እውነተኛ መንፈሳዊ እረኛ ( መሪ ) ሕዝቡን ሳይሰለች ደከመኝም ሳይል በቃለ እግዚአብሔር የሚመግብ ነው፡፡ ምዕመናን ( ት ) ከዛሬው ቃለ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ሕዝቡ የእግዚአብሔር ምሕረት ብዙ መሆኑን አትዘንጉ፡፡
መንፈሳዊ እረኛ ( መሪ ) የሆንን ደግሞ እንደ ሙሴ ዓይነት መሪ ( እረኛ ) መሆን እንደሚገባን እናስተውል፡፡ የአገር መሪዎችም ሳይቀሩ ሙሴን ቢመለከቱ ሕዝባቸውን እንዴት መውደድና ስለ ሕዝባቸው እንዴት ሸክም ሊሰማቸው እንደሚገባቸው ትልቅ ትምህርት ያገኛሉ፡፡
ማጠቃለያ
እውነተኛ መንፈሳዊ እረኛ ( መሪ) ስለ ሕዝቡ ያለውን ሸክም ሳይከብደው ተሸክሞ የሚኖር እንጂ ሸክም ሆኖበት በፈለገው ጊዜ የሚያወርደው ዓይነት ሸክም የተሸከ ሰው አይደለም፡፡ ሁላችንን እግዚአብሔር ይባርከን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን!
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
እውነተኛ መንፈሳዊ መሪ ( እረኛ ) ስለ ምዕመናን ያለው ሸክምና የእግዚአብሔር ይቅርባይነት ፡፡
ሕዝቡም ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰብስበው ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አናውቅምና ተነሥተህ በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን አሉት። አሮንም፡- በሚስቶቻችሁ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁም ጆሮ ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብራችሁ አምጡልኝ አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ በጆሮቻቸው ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብረው ወደ አሮን አመጡለት።
ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤ እርሱም፡- እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አላቸው። አሮንም ባየው ጊዜ መሠዊያን በፊቱ ሠራ፤ አሮንም፡- ነገ የእግዚአብሔር በዓል ነው ሲል አወጀ። በነጋውም ማልደው ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዉ፥ የደኅነትም መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሕዝቡም ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፥ ሊዘፍኑም ተነሡ።
እግዚአብሔርም ሙሴን፡- ከግብፅ ምድር ያወጣኸው ሕዝብህ ኃጢአት ሠርተዋልና ሂድ፥ ውረድ። ካዘዝኋቸው መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ፤ ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ለራሳቸው አደረጉ፥ ሰገዱለትም፥ ሠዉለትም። እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አሉ ሲል ተናገረው።
እግዚአብሔርም ሙሴን፡- እኔ ይህን ሕዝብ አየሁት፥ እነሆም አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነው። አሁንም ቍጣዬ እንዲቃጠልባቸው እንዳጠፋቸውም ተወኝ፤ አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ አለው። ሙሴም በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ጸለየ፥ አለም፡- አቤቱ፥ ቍጣህ በታላቅ ኃይልና በጽኑ እጅ ከግብፅ ምድር ባወጣኸው በሕዝብህ ላይ ስለ ምን ተቃጠለ? ግብፃውያንስ፡- በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ ከምድርም ፊት ሊያጠፋቸው ለክፋት አወጣቸው ብለው ስለ ምን ይናገራሉ? ከመዓትህ ተመለስ፥ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ።
ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም አስብ። እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው ክፋት ራራ፡፡
..በነጋውም ሙሴ ለሕዝቡ፡- እናንተ ታላቅ ኃጢአት ሠርታችኋል፤ አሁንም ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ፤ ምናልባት ኃጢአታችሁን አስተሰርይላችኋለሁ አላቸው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ፡- ወዮ! እኒህ ሕዝብ ታላቅ ኃጢአት ሠርተዋል፥ ለራሳቸውም የወርቅ አማልክት አድርገዋል፤ አሁን ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ አለ ( ዘጸ 32 )።
ማብራሪያ
ሙሴ በሲና ተራራ ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በመቆየቱ እስራኤላውያን እንደ ዘገየባቸው ባዩ ጊዜ ማለት ሙሴን ለአርባ ቀንና ሌሊት በዓይናቸው ስላላዩት ወንድሙ አሮንን ፡- ከግብፅ ያወጣን ሙሴ ምን እንደ ሆነ አናውቅም፡፡ አማልክት ( ጣዖት ) ሥራልን አሉት፡፡ አሮን ያሉትን ሰምቶ፡- ተዉ ፤ አይበጃችሁም፡፡ ሙሴን እንጠብቀው ፤ ከኔ በቀር ሌላ አማልክት አታምልኩ የተባለውን ከአሥሩ ትእዛዝ የመጀመሪያውን ለምን ትረሳላችሁ? ብሎ ሳይመክራቸው በመቅረት ይልቅስ አማልክትን እንዲያመልኩ፡- እሺ አላቸው፡፡
የፈለጉትን አማልክት እንዲሠራላቸው ስለ ፈለጉ አሮን የወንዶችንና የሴቶችን የጆሮ ወርቆች አምጡልኝ ስላላቸው ያመጡለትን ወርቆች ተቀብሎ በመቀረጫ ቀርጾ ቀልጦ የተሠራ ጥጃ አደረገው፡፡ አሮን እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብፅ እንዳወጣ እያወቀ ደግሞም የገዛ በትሩን እባብ አድርጎ ያሳየውን አምላክ ቸል ብሎና ለሕዝቡ ይባስ ብሎ ደግሞ ፡- ጥጃውን እስራኤል ሆይ ከግብፅ ያወጡህ አማልክት እነዚህ ናቸው ብሎ አረፈው፡፡
ከግብፅ ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮ ሳለና የኤርትራን ባሕር ከፍሎ እንዳሻገራቸው ሳይቀር እያወቀ አሮን ግን፡- እነዚህ ናቸው ከግብፅ ምድር ያወጡህ ብሎ ስለ ጣዖቱ የተናገረው፡፡ አሮን ማስተዋሉ ይደፈንበት እንጂ ሕዝቡ ራሳቸው፡- ከግብፅ ያወጣን ሙሴ ባሉት ጊዜ እንኳን ሕዝቡ ራሱ እግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት እንዳወጣቸው ቢጠቁሙትም ሊገባው አልቻለም፡፡ እንዲያውም ለሠራውም ጥጃ መሠዊያ በመሥራት ሕዝቡ መሥዋዕት እንዲያቀርቡ አዘዛቸው፡፡ ሕዝቡም በሉ፤ ጠጡ ዘፈኑም፡፡
ከሙሴ ጋር በተራራው ላይ የሚነጋገረው እግዚአብሔር አሮንና ሕዝቡ ያደረጉትን ነገር ስላየ ለሚያናግረው ለሙሴ ትልቅ መርዶ አረዳው፡፡ መርዶው ደግሞ አማልክት አታምልኩ ተብለው የተነገረላቸው ሕዝቡ ጣዖት እንደሠሩ፣ እንደ ሰገዱለት ፣ እንደ ሠዉለት፤ ጣዖቱንም ከግብፅም ያወጣን ይህ ነው እንዳሉ ነበር፡፡ እስራኤላውያኑ ላደረጉት ጥፋት ደግሞ ተመጣጣኝ ቅጣት ሊፈጽምባቸውም ስለሳበ እግዚአብሔር ሙሴን፡- ቁጣዬ እንዲቃጠልባቸው እንዳጠፋቸው ተወኝ ፡፡ አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ አለው፡፡
እነርሱ ቢጠፉ መሪነቱ ግን እንደማይቀርበት የተነገረውና ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ የተባለው ሙሴ ግን ሕዝቡ እንዳይጠፉበት በማሰብ ግን በእግዚአብሔር ፊት ጸለየ፡፡ እስራኤላውያኑ በመቀላመድ አማልክት ( ጣዖት ) እንዳወጣቸው የተናገሩትን በማስተካከል ፡- ከግብፅም ባወጣኸው ሕዝብህ ላይ ቁጣህ ስለምን ተቃጠለ አለው፤ ግብፃውያን ሲሰሙ ሕዝቡን መልሶ አጠፋቸው ስለምን ይበሉ፣ ከመዓትህ (ከቁጣህ ) ተመለስ፤ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ አለው፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ፡- ያወጣኸው ሕዝብህ ቢለውም ሙሴ ደግሞ ለእግዚአብሔር ሲናገር ፡- ሕዝብህ ፣ ሕዝብህ በማለት ቢበድሉትህም ሕዝቡ እንደሆነ አስረዳ፡፡ ልጆቻቸው ቁጣው እንዲቃጠል ቢያደርጉትም አባቶቻቸውን አብሃርምን ፣ ይስሐቅን ፣ እስራእልን ( ያዕቆብን ) እንዲያስብ ለመነው፡፡
ቁጣው የተቃጠለበት አምላክ በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ያሰበውን መዓት በመተው ራራላቸው፡፡
እግዚአብሔር እንዳለው ከተራራው ላይ ሙሴ ሲወርድ የሚያመልኩትን ጥጃ አይቶ ሙሴ እግዚአብሔርን፡- ተው፤ አትቆጣ ብሎ ሲያበቃ የእርሱ ቁጣ በተራው ተቃጠለ ፡፡ በነጋው ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ፡- ታላቅ ኃጢአት ሠርተዋል ይቅር በላቸው፤ ያለበለዚያ ከጻፍኸው መጽሐፍህ ደምስሰኝ አለው፡፡ እግዚአብሔር ግን ሙሴን ከሕይወት መጽሐፍ መደምሰስ ባለመፈለጉ ዓመፀኞቹን እስራኤላውያኑን ማረለት ( ዘዳ 10 ÷ 10፡11 ) ፡፡
እውነተኛ መንፈሳዊ እረኛ ( መሪ ) ስለ ሕዝቡ ግድ የሚለው ነው፡፡ ሕዝቡ ቢበድሉ ስለ ምዕመናኑ እግዚአብሔርን የሚለምን ነው፡፡ እነርሱን ከምታጠፋ እኔን አጥፋ የሚልም ነው፡፡ ምዕመናን፡- እናንተ እግዚአብሔር ብትበድሉ ስለ እናንተ የሚለምን ሰው እንዳለ እርግጠኛ ሆኜ እነግራችኋለሁ፡፡ ደግሞስ እናንተ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ( ት ) እግዚአብሔርን ትታችሁ ጣዖትን ያመለካችሁበት ቦታ የት አለ? እስራኤላውያን እኮ እግዚአብሔር ከዚህ በኋላ አምላካችን አይደለም ብለውት ሳይቀር እርሱ ግን ምሮአቸው አምላክ ሆነላቸው፡፡
አሮን ደግሞ ምን እንደ ሠራ ነግሬአችኋለሁ፡፡ እግዚአብሔር ግን ያንኑ አሮንን ነበር ካህን ሆኖ እንዲሾም ያደረገው፡፡ አቤት የእግዚአብሔር ቸርነት እንዴት ይደንቃል! የማረንን ልጆቹን መልሶ እንድናገለግለውና አመስጋኞች እንድንሆን የሚያደርግ አባት ነው ያለን፡፡
975
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
ወንጌል እንማር ::
ክፍል 6 ( ፮ ) ::
የመጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት ::
በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ፡- መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ። በነቢዩ በኢሳይያስ፡- የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ የተባለለት ይህ ነውና።
ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ።
ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤ ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።
ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው። እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?
እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ በልባችሁም፡- አብርሃም አባት አለን እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና። ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።
አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።
እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤
መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል ( ማቴ 3 ÷ 1 - 12 ) ።
ማብራሪያ
መጥምቁ የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማጥመቁ ነው፡፡
መጥምቁ ዮሐንስ ሲናገር፡- ከእኔ በኋላም የሚመጣው ግን ከኔ ይልቅ ይበረታል ( የሚከብር ) ያለው ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፡፡
መጥምቁ ዮሐንስ ለክርስቶስ አገልግሎት አስቀድሞ መንገድ የሚያዘጋጅ ነበረ፡፡ ንስሐ ግቡ በማለት ሰዎች ልባቸውን ወደ እግዚአብሔር እንዲመልሱ የሚሰብክ ሰባኪ ነበር፡፡
መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያከብር ፡-
ጫማውን መሸከም የማይገባኝ ነኝ በማለት ነው፡፡
ዮሐንስ በማኅፀን ውስጥ ገና የ6 ወር ፅንስ እያለ በደስታ የዘለለ ነው ( ሉቃ 1 ÷ 41 ፡ 45 ) ፡፡ ይህ ዮሐንስ ግን ጫማውን መሸከም አይገባኝም በማለት የክርስቶስ ክብር እንዴት ትልቅ እንደሆነ ይነግረናል፡፡
በነቢዩ ኢሳይያስ ከ700 ዓመት በፊት ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ትንቢት ተነግሮ ነበር፡፡
በነቢዩ በኢሳይያስ፡- የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ የተባለለት ይህ ነውና ( ኢሳ 40 ÷ 3 ) ።
ከክርስቶስ የማስተማር አገልግሎት በፊት ዮሐንስ፡- ንስሐ ግቡ እያለ ሕዝቡን ቀድሞ እንደሚያዘጋጅ ትንቢት ተነግሮ ነበር፡፡ ከ700 ዓመት በፊት ስለ እርሱ ትንቢት የተነገረለት ቢሆንም ስለ ክርስቶስ ሲናገር ግን ፡- ጫማውን መሸከም አይገባኝም ይለናል፡፡
ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ ። አ‘‘ሩ የቅድስና ሕይወት የተንጸባረቀበት ነው፡፡ ይህ በጽድቅ ሕይወት የሚመላለሰው ዮሐንስ ስለ ክርስቶስ ሲናገር ፡- ጫማውን ለመሸከም የማይገባኝ ነኝ በማለት የክርስቶስን ክብር ከፍ አድርጎ ያሳየናል፡፡
ዮሐንስ እንደሚወለድ የተነገረው በመልአክ ነው፡፡ ዮሐንስም ለእግዚአብሔር የተለየ በመሆኑ ገና ሳይወለድ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ እንዳይጠጣ ተከልክሏል ( ሉቃ 1 ÷ 13 - 17 ) ፡፡ ይህ ዮሐንስ ነው እንግዲህ ስለ ክርስቶስ ሲናገር ፡- ጫማውን መሸከም የማይገባኝ ነኝ የለው፡፡
ስለ ዮሐንስ ጠቅለል ስናደርገው እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፡-
እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም ( ማቴ 11 ÷ 11 ) ፡፡
ጥቅሱ የሚነግረን ከሴት ከተወለዱት መካከል እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ያለ እንዳልተነሣ ነው፡፡
እንዲህ ተብሎ የተመሰከረለት መጥምቁ ዮሐንስ ስለ ክርስቶስ ሲናገር ፡- የእግሩን ጫማ ለመሸከም የተገባሁ አይደለሁም ማለቱ ክርሰቶስን ከማንም በላይ ፣ ሁሌም ከፍ ማድረግ እንዳለብን ያመላክተናል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው፡፡ ዮሐንስ እንዴት አድርጎ እንዳከበረው አይተናል፡፡ የኛን ሥጋ ለብሶ ቢመጣም እንደ ዮሐንስ ደግሞ በአምላክነቱ ክብር ልናከብረው ይገባል፡፡
ልጆቹ ብንሆን የማይገባን ሆነን ሳለን ነው የሚገባን ያደረገን፡፡ ብንጸልይ ወደርሱ የማይገባን ሆነን ነው የሚገባን ያደረገን፡፡ ምንም ነገር የሚገባን አይደለንም የሚገባን ግን አደረገን፡፡
ለአብ፣ ለወልድ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ፤ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን፡፡
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
የታዘዝነውን ሁሉ አድርገን “ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን ” ልንል ነው የሚገባን ፡፡
ከእናንተም የሚያርስ ወይም ከብትን የሚጠብቅ ባሪያ ያለው፥ ከእርሻ ሲመለስ ፡- ወዲያው ቅረብና በማዕድ ተቀመጥ የሚለው ማን ነው?
የምበላውን እራቴን አሰናዳልኝ፥ እስክበላና እስክጠጣ ድረስ ታጥቀህ አገልግለኝ፥ በኋላም አንተ ብላና ጠጣ የሚለው አይደለምን? ያንን ባሪያ ያዘዘውን ስላደረገ ያመሰግነዋልን?
እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፡- የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ ( ሉቃ 17 ÷ 7 - 10 ) ።
ማብራሪያ
ከበላይ ያለውን ቃል የተናገረው ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ነው ፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስተምር በዘመኑ ካለው ነገር በመነሣት ያስተምር ነበር ፡፡ በጌታና በባሪያ በመመሰል ፣ ለገበሬዎች በእርሻ ወይም በዘር ፣ ለነጋዴዎችም በሚገባቸው መልኩ በምሳሌ ይመስል ነበር ፡፡
በዚያን ዘመን ባሪያ ያላቸው ጌቶችም ነበሩ ፡፡ በምሳሌ ማስተማሩ ሰዎች ትምህርቱን በቀላሉ እንዲረዱት ያደርጋል ፡፡
በጌታና በባሪያ መስሎ ካስተማረው ትምህርት የምንቀስመውን እንይ ፡፡
ባሪያ ያለው ጌታ ቢኖር ባሪያው አርሶ ወይም ከብትን ጠብቆ ሲመለስ መድከሙ አይቀርም ፡፡ ባሪያው ደክሞም ቢመጣ ገና ሳያርፍ ጌታው ወዲያው ፡- የምበላውን እራቴን አሰናዳልኝ ፤ በልቼ እስክጨርስ አገልግለኝ ፡፡ እኔ ከበላሁ በኋላ አንተ ትበላለህ ፤ ትጠጣለህ ይለዋል እንጂ ከእርሻው እንደ ተመለሰ በማዕዴ ተቀመጥና አብረን እንብላ አይለውም ፡፡
ባሪያው ከብት ጠብቆ ወይም አርሶ ቢመለስ ደግሞም የሚበላውን ለጌታው ስላቀራረበ ጌታው የሚያመሰግነው አይደለም ፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ እንድናደርግ የታዘዝናቸው ብዙ ትእዛዛት አሉ ፡፡ ከበላይ ያለው ታሪክ የሚያስተምረን የታዘዝነውን ሁሉ ባደረግን ጊዜ፡- የማንጠቅም ባሪያዎች ነን ፤ ልናደርገው የሚገባንን አደረግን እንድንል ነው እንጂ በሥራችን እንድንመካ አይደለም ፡፡
ለማጠቃለል የታዘዝነውን ትእዛዛት ሁሉ መፈጸም አለብን ፡፡ የታዘዝነውን ትእዛዛት ስንፈጽም በሠራነው ሥራ ልንመካ አይገባም ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን !
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
ወንጌል እንማር ፡፡
ክፍል 5 ( ፭ ) ፡፡
የክርስቶስ መሰደድ ፡፡
የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፡- ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው። እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ፡- ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።
ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ። ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ።
ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፡- የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ። እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ። በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ፤
በነቢያት፡- ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ ( ማቴ 2 ÷ 13 - 23 ) ።
ማብራሪያ
ሰብአ ሰገል፡- የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ልንሰግድለት መጥተናል ያሉትን ሰምቶ ሄሮድስ ተደናገጠ፡፡ ክርስቶስ መድኃኒት እንጂ ለሄሮድስ የስጋት ምንጭ አልነበረም፡፡ ሄሮድስን በመግደል ዙፋኑን የሚወርስ አልነበረም፡፡ ሕፃኑን ኢየሱስን ለመግደል በማሰቡም የጌታ መልአክ ለዮሴፍ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ግብፅ እንዲሸሽ ነገረው፡፡ ሊገድለው የሚፈልገው ሕፃኑ ኢየሱስ የሚሞተው ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት በቀራንዮ ተሰቅሎ እንደ ሆነ አላወቀም፡፡ ዮሴፍ ሊገደል የተፈለገውን ሕፃኑ ኢየሱስን ከእናቱ ጋር ይዞ ወደ ግብፅ ሸሸ፡፡
ሄሮድስ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ኢየሱስን አገኘዋለሁ በማለት ብዙ ሕፃናትን ገደለ፡፡ ሄሮድስ እርሱም ብዙ ላይኖርና ካስገደላቸው ሕፃናት መካከል ንጉሥ የሚሆን ቢገኝ እንኳን ንጉሥ ለመሆን ጭራሽ ዕድሜአቸው ሳይደርስ ብዙ ሕፃናትን አስገደለ
እናቶች ስለ ልጆቻቸው አለቀሱ፡፡ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ። ራሔል የያዕቆብ ሚስት ናት፡፡ ራሔል አለቀሰች ሲባል የእስራኤል ( የብዙዎች ) እናት ተደርጋ ተቆጥራ ነው፡፡ ሕፃናት የሞቱባቸውን እናቶች ሁሉ ወክላ በመቅረቧ ነው፡፡
ገዳይ ሄሮድስ ሲሞት ተገዳይ ሕፃኑ ኢየሱስ ሳይሞት ቀረ፡፡ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው ተፈፀመና ዮሴፍ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ተመለሰ፡፡
ልጄን ከግብፅ ጠራሁት ተብሎ ስለ እርሱ የተነገረው ትንቢት የሚነግረን ክርስቶስ ተሰዶ በግብፅ ሰለ ነበር ከግብፅ ወደ እስራኤል መመለሱን ነው፡፡
በነቢያት፡- ናዝራዊ ይባላል የተባለው ቃል በቃል በነቢያት መጽሐፍ ተጽፎ አናገኘውም፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰዶ መከራን ከተቀበለ እኛም በዓለም ሳለን መከራ እንዳለብንና መከራን መቀበል እንደሚገባን የሚያስተምረን ነው፡፡ ራሱም ጌታችን በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዞአችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ እንዳለ ( ዮሐ 16 ÷ 33) በዓለም ሳለን መከራ ይኖራል፡፡ መከራ ቢመጣብንም ግን አይዞአችሁ ተብለናል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከኛ ጋር ስላለ ያሸንፍልናል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን!
ይቀጥላል፡፡
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እግዚአብሔር አባታችንም ይራራልናል ፡፡
ወበከመ ይምህር አብ ውሉዶ ፡፡
ከማሁ ይምህሮሙ እግዚአብሔር ለእለ ይፈርህዎ ፡፡
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ
እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል ( መዝ 102 ( 103 ) ÷ 13 ) ፡፡
ማብራሪያ
የግዕዙን ትርጉም ከስሩ ስላስቀመጥሁ እዚህ ጋር መተርጎም አላስፈለገኝም ፡፡
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው በትእዛዙ ይመላለሳል ፡፡ እንደዚሁም በድሎ፡- ይቅር በለኝ የሚል ሰውም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው መገለጫ ነው ፡፡
እግዚአብሔር ፡- አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ብለን የምንጠራው አባታችን ነው ፡፡ እኛ ደግሞ ልጆቹ ነን ፡፡
አባት ሆኖ ለልጆቹ የማይራራ ማነው ? አባት ለልጆቹ ይራራል ፡፡ እንደዚሁ እግዚአብሔር አባታችንም ለእኛ ለልጆቹ ይራራልናል ፡፡
ልጆች ሆነን ስንቱን ጥፋት አጥፍተን አባቶቻችን እንዴት እንደ ራሩልን እናውቃለን ፡፡ አንዳንዶችን ስንቱን ዕቃ ሰብረን፣ ሰብረን የማይገልጸው ጊዜ አለ ፡፡ ስንቱን ድራሹን አጥፍተን አባታችን ራርቶልናል ፡፡
እግዚአብሔርም በቤቱ ስንመለስ ስንቱን ጥፋት አጥፍተን፡- ይቅር በለን ደግሞ ስንለው ስንቱን አረ ስንቱን በድል ራርቶልን ይቅር አለን ?
ቦርቀን ባደግንበት በአባታችን ቤት ሳናጠፋ ቀርተን አይደለም አንደዛ የቦረቅነው ፡፡ ብዙ ተራርቶልን እንጂ ፡፡ እግዚአብሔርም እየራራልን በቤቱ እንደሚቦርቁ ልጆች እንድንኖር የሚያደርግ ነው ፡፡
እግዚአብሔር ከምድራዊ አባት ለልጆቹ ይራራል ከምንለው በላይ ነው ፡፡ ምድራዊ አባት የበደለው ልጁን ይቅር ብሎ እንኳን ወዲያው አንደ ቀድሞው ጊዜ ፊቱን እንደ ወገግታ ላያበራለት ይችላል ፡፡ ሰማያዊው አባት ግን ይቅር በለን ባልነው ቅጽበት ፊቱን እንደ ወገግታ ያበራልናል ፡፡
ምድራዊ አባት ራርቶ ለልጁ ይቅር ቢልም፣ የሚያሳየን ፊት ልክ ሌሊቱ ሲነጋ ቀስ ብሎ ጨለማው በሚሸሽበት ዓይነት መልኩ የሚሆንበት ጊዜ አለ ፡፡ እግዚአብሔር፡- ይቅር በለን ብለን ሲራራልን የሚያሳየን ፊት ያጠፋነውን መብራት ወዲያው ባበራነው ቅጽበት ቦግ ብሎ እንደሚታየን ዓይነት ነው ፡፡
አኩርፈንም ይሁን በሌላ ምክንያት ከቤቱ ወጥተን ተመልሰን ስንመጣና፡- ይቅር በለን ስንለው ራርቶልን በእንዴት ያለ ፍቅር እንደ ተቀበለን እናስተውል ፡፡
ከቤቱ ወጥተን ፣ ተመልሰን መጥተን ፣ ይቅርታ ተደርጎልን መልሰን ስንበድለውና፡- ይቅር በለን ስንለውም አንዴ አይደለም ብዙ ጊዜ የራራልን እውነተኛ አባት ነው ፡፡
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር እስከ ዛሬ ድረስ እንደ ራራልን ወደፊትም በቤቱ በምንኖርበት ዘመን ሁሉ ይራራልናል ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን !
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
975
✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ
▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል ማግኘት ትችላላችሁ
https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w
▶️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMaweq
▶️ ፌስቡክ
fb.me/yeglie
