HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
رفتن به کانال در Telegram
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239
نمایش بیشتر2 273
مشترکین
+424 ساعت
+127 روز
+2530 روز
آرشیو پست ها
«የሚፈውስ እንባ»
- ሰውን የምታድን ክርስቶስ ሆይ! ከአንተ በቀር ማን ያድነኛል? የድኅነት ምንጭ ከኾንከው ከአንተ በቀር የታመመችውን ነፍሴን ማን ይፈውሳታል? አቤቱ ሆይ! እንኪያስ የታመመችውን ችግረኛ ሴት እንደፈወስካት እኔንም ከጥፋት ከምረረ ገሃነም አድነኝ፡፡ ምሕረት ቸርነትኅ በእኔ ላይ ትኹን፡፡ ጠላቴን ድል አደርገው ዘንድ እርዳኝ፡፡ ብርቱ በምትኾን ክንድኅ ደካማ የምኾን እኔን አበርታኝ፡፡ አበርታኝና ለተጋድሎ የተዘጋጀኹ እንደኾንኩ ዐይቶ ጠላቴ ይራድ፤ ይንቀጥቀጥ፤ ይፈርም፡፡ አበርታኝና ጠላቴ የተዋረደ ይኹን፡፡ አበርታኝና ጠላቴ (ዲያብሎስ) በሐፍሬት ከፊቴ ይመለስ፡፡ አበርታኝና እኔም ስምኽን ከፍ ከፍ ላድርገው፡፡
- አቤቱ ሆይ! ጐስቋላ የምኾን እንባዬን ተቀበልልኝ፤ ዕዳዬንም ፋቅልኝ፡፡ ፍቅርኅ የእኔን የበደለኛውን የክፉ ምግባሬ ፍሬ ይደምስስልኝ፤ ምረረ ገሃነምም አያግኘኝ፡፡ ቸርና ሰው ወዳጅ ሆይ! ዕዳዬን ደምስስልኝና ጠላቴ ይፈር፡፡ ፈተናውን ድል አደርግ ዘንድ፥ ድል አድርጌም ዘወትር ከአንተ ጋር እኖር ዘንድ ምሕረት ቸርነትኅ ከእኔ ጋር ትኹን፡፡
- አቤቱ ሆይ! አልቅሳ ሰምታኻታልና፥ በሚፈውስ እንባ አጥባኻታልና፥ ፍጥረትን ኹሉ ለፈጠርከው ለአንተም ቤተ መቅደስህ አድርጋኻታልና በደለኛ የምትኾን ሰውነቴ፥ ከባሕርይ አባትኅ ከአብ ከባሕርይ ሕይወትኅ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ታከብርኻለች፡፡ አሜን!!!
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.facebook.com/hailegebrieltube2021
https://www.tiktok.com/@walkinaddistv
መንፈሳዊ ምግባርና ሕይወት ምን ምን ከማድረግ ይነሣል ወይም ይጀምራል? ንስሐ ገብታችሁ በካህን ያልተፈታችሁ ይኼንን አስተውሉ! ንስሐ ገብተን በቀጥታ መቁረብ ለምን አቃተን?
https://youtu.be/Vji_Jl2DfkU?si=A6WtEVjY-c9No9_4
አጋንንትን ለማውጣትና ለመሸኘት ይኼንን ወሳኝ ምስጥር ማወቅ ይገባል!! ሴቶች በቅዳሴ ወቅት የወር አበባ ብከሰት ምን ማድረግ አለባቸው?? #አጋንንት #ጸሎት https://youtu.be/iRUR_Od-Wak
የኔታ ይባቤን ማጣት እጅግ መራራ ሐዘን፣ ከሐዘንም በላይ ነው። 😭😭
ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ ወንበር ተክለው በማስተማር በርካታ ሊቃውንትን ወልደዋል። ገዳሙን በማስተዳደርም ጭምር ብዙ አልምተዋል። አሁን ሁሉንም ጥለውት ሔዱ። ናዳ ማርያም ገዳም ላይ ታላቅ ሐዘን ወደቀ።
ከዚህ ቀጥሎ ያለው ጽሑፍ የመልአከ ምሕረት ግሩም አለነ ነው። 👇
......................
ለካ ገዳሙን የሚመራ መሪ - በጉባኤ ቤቱ የሚያስተምር መምህር ፈልጉ! ያሉን የስንብት ቃል ነበርን⁉️ እርሳቸው የተናገሩት እኛም በማስታወሻችን ላይ የጻፍንበት የብርዕ ቀለም ሳይደርቅ ዜና እረፍታቸውን ከመስማት በላይ ምን የሚገርምና የሚከብድ ነገር አለ⁉️ የኔታ ባደረባቸው ፅኑእ ህማም ምክንያት ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
▮ሥርዓተ ቀብራቸው ነገ በ23 የሚፈፀም ይሆናል▮
ጸሎተ አርጋኖን በአጋንንትና በመናፍስት ላይ ያለው የበላይነት! https://youtu.be/Fmho3nzvnfE?si=nZfgp6pbK18ybm86
በትዳር ውስጥ ኩርፊያ የሚያስከትለው መዘዝና ኦርቶዶክሳዊ መፍትሔዎቹ! ድምጽ አልባው መሳሪያ ብዙ ትዳሮችን ያበላሸው!
https://youtu.be/Ct7TClWophI?si=2Wjv_KsMlKnm14kw
10 መሠረታዊ ነገሮች አሁኑኑ ማድረግ ከቻላችሁ እመኑኝ ትለወጣላችሁ! https://youtu.be/d4s7vZjm5rQ?si=XOsIlWwMmnT_v_2e
የቡዳ አይን የሚባለው የሳይኮሎጂ ችግር እንጂ የአጋንንት ሥራ አይደለም!! ዮሐንስ ሽፈራውና ሌሎችም እንዲሁ ያስባሉ! ቡዳና አይነጥላ የሚባል አጋንንት የለም!
https://youtu.be/9dPYeXHCO6M?si=NS8_VijYCq6Rmltv
መተት ያደረጉብንን ሰዎች እንዴት ማወቅና መለየት እንችላለን? ከግለወሲብ አጋንንታዊ ሥራ ለመላቀቅ መፍትሔው ይኼው!! በገዛ ጓደኛዋ ባል የተደፈረችው ሴት! https://www.youtube.com/watch?v=JR4G0cD4hc8
መተት ያደረጉብንን ሰዎች እንዴት ማወቅና መለየት እንችላለን?? ከግለወሲብ አጋንንታዊ ሥራ ለመላቀቅ መፍትሔው ይኼው!! በገዛ ጓደኛዋ ባል የተደፈረችው ሴት!! https://youtu.be/JR4G0cD4hc8
ፍቅር ሲመነምን ውጤቱ የበዙ ጥፋቶችን ማስከተል ይሆናል!!
የፍቅር እጦት ቂም እና ጥላቻን ይፈጥራል። ይህ ደግሞ በኃጢአት ሐሴት ማድረግን ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ በመሰናከሉም ልብህ ሐሴት አያድርግ" ምሳ 24፥17
ሌላው የፍቅር እጦት ውጤት ቁጣ እና ክፋት ነው። እንዲህ ያለው ሁኔታ ስድብን፣ ጠብን፣ ግድያን፣ ነቀፋን፣ ማዋረድንና ስም ማጥፋት ማስፋፋትን ያስከትላል። ከዚህ በተጨማሪ የፍቅር እጦት ወይም ጉድለት ወደ ቅንዓት፣ ወደ አላዋቂነት፣ ወደ ኩራት፣ ወደ ጽናትን ማጣትና ወደ ጭካኔ ይመራል።
ለእግዚአብሔር የሚሆን ፍቅርን ማጣት በብዙ ጉዳዮች ውስጥ ሊገለጥ ይችላል፤ ከእርሱም መካከል ጸሎትን፣ መጽሐፍ ቅዱስንና ቤተ ክርስቲያንን መርሳት ጥቂቶቹ ናቸው። በእግዚአብሔር ፊት መቆምን ማጣት እና በእግዚአብሔር መንግሥት ፈጽሞ ሐሴት አለማድረግ ሌሎቹ ጉድለቶች ናቸው።
#ብጹዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
=> ገብርኤል ሆይ፣ ከሰው ወገን ከቶ ጧትና ማታ እንደኔ ኀዘንና ትካዜ የሚበዛበት የለም፡፡ ከመላእክትም ወገን እንዳንተ ያዘኑትን የሚያረጋጋ የለም ገብርኤል ሆይ ስለዚህ እኔም አውቄና አንተን አምኜ ይህንን ያቀረብኩልህን ጸሎት እንደ ትልቅ ዋጋ ቆጥረህ የማረጋጋት ቃልህን አሰማኝ🙏
መልክአ ገብርኤል
በግል ሕይወታችን መንበርከክ ስንጀምር ማስተዋል ይጨመርልናል!! ዝነኛ መሆን ሳይሆን አሁን የሚያስፈልገን መቀ'ደስ ነው! የቅድስት አርሴማ አስገራሚ ውተዓምር!! https://youtu.be/zRTTXSUGZ0s
👉ንስሓን የሰበክህ ክቡር አባት ሆይ! ለቅድስናህ በማይገባ ሁኔታ የፈጸምኩትን በደል ሁሉ በይቅርታህ ጥልቅ ውስጥ ጣልልኝ፤ ተነሳሒውን እኔን ይቅር በለኝ፡፡ ወደሚወዱህ ልጆችህ ተመለስ፣ ወደ እኛ በመምጣትህም ደስ ይበለን፡፡ ትመጣ ዘንድ አላዝዝህም፣ ሁለተኛ እንዳላፍር ትመጣ ዘንድ በትሕትና እማጸንሃለሁ እንጂ፡፡ እጅግ የተወደድክና የተከበርክ አባት ሆይ፣ እባክህ በፈቃድህ ወደ እኛ ና፣ በፍጹም ደስታና ፍቅር እንቀበልህ ዘንድ፡፡
(ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ➛ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.facebook.com/hailegebrieltube2021
https://www.tiktok.com/@walkinaddistv
መዝሙረ ዳዊትን ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በኋላ መጸለይ ለምን ተከለከለ?? ከሀጥያት ለመከልከል ብሎ ይኼንን የሚያደርጉ ብጹዕ ናቸው!! #ጸሎት #ስግደት #ንስሐ https://youtu.be/JA5rurkHNP4
#ምክረ_አበው
ከወድሞች አንዱ ወደ አረጋዊ መጣና "አባ፣ ደካማ ነኝና ጸልዩልኝ" አለው፡፡ አረጋዊም እንዲህ አለው "በሸተኛን ይቀባ ዘንድ በእጁ ቅባት የሚይዝና ሌላውን የሚቀባ ሰው እርሱም ደኀና ሆኖ ይቀባል፡፡ እንዲሁም እኛም ለሌላው ስንጸልይ ለራሳችን መድኃኒትና ፍስሐ ይሆነናል፡፡ ስለዚህ ወንድሜ ሆይ፣ አንዳችን ለሌላችን ልንጸልይና እርስ በርሳችን በጸሎት ልንተሳሰብ ይገባናል፤ ሐዋርያው "ትድኑ ዘንድ ለወንድሞቻችሁ ጸልዩ" ብሎ እንዳዘዘን፡፡
#ከበረሐውያን_ሕይወትና_አንደበት
=> አፈ ወርቅ
=> አፈ በረከት
=> ጥዑመ ቃል
=> ሐዋርያዊ
=> መምህር ወመገሥጽ
=> ዘኢያደሉ ለገጽ
=> በላዔ መጻሕፍት
=> ጽኑዕ ሰማዕት
=> ሊቅነት በብቃት
=> የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ
❖ የሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በረከት ትድረሰን።
ይኼንን ጸሎት እሳካሁን መጸለይ ካልጀመራችሁ ብዙ ተሸውዳችኋል!! የዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ጸሎትና በረከቱ! ለቅዱሳን ምልጃ ማቅረብና መንፈሳዊ አንድምታ!
https://youtu.be/uCb241E3qtw?si=Rz2kV85Skl0tkJif
+3
#ይኼንን_አገልግሎት_ተሳተፉ!
- የብዙዎች ሕይወት እየተቀየረበት ያለው የፍኖተ ሕይወት ጉባኤ ተካሄደ! የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የቅዱሳን ወዳጆች በ44ቱ ጸበል ቅድስት ሥላሴና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ህዳር 14 እሁድ የፍኖተ ሕይወት ጉባኤያችን የተወደዱ ክርስቲያኖች በተገኙበት በእግዚአብሔር ፈቃድ ከቅዳሴ በኋላ በጸበል፣በወንጌል፣በዝማሬ በቅብዐ ቅዱስ በበረከት በደስታና በፈውስ በደስታ አሳልፈናል።
- በእግዚአብሔር ኃይል ጠላታችን የተደመሰሰበት የቅድስት ሥላሴ ክብር ያየንበት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋና ፈውስን የተካፈልንበት ብዙዎች ሕይወታቸው የተቀየረበት ብዙ ድንቅ ተአምራትና በረከትን ያገኘንበት ምስክርነት የተሰጠበት ድንቅ ጉባኤ ነበር።
- ቀጣዩ ጉባኤያችን፦ የፊታችን ህዳር 20 እና 21 ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል። አድራሻ፦ ከጎተራ ወደ ወሎ ሰፈር መሄጃ ወንጌላዊት ሕንጻ ጀርባ ወይንም ዘንባባ ሆስፒታል ጀርባ 44ቱ ጸበል ፈለገ ዮርዳኖስ ቅድስት ሥላሴ እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ጸበሉ ስፍራ።
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.facebook.com/hailegebrieltube2021
https://www.tiktok.com/@walkinaddistv
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
