HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
رفتن به کانال در Telegram
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239
نمایش بیشتر2 280
مشترکین
+124 ساعت
+117 روز
+3230 روز
آرشیو پست ها
#አትሌትክሳችንና_ድብቁ_የአጋንንቱ_ሥራ_ሲገለጥ!! ለማዳም ቅሜሞች የተላለፈ ጥብቅ መልዕክት!! እህታችን እንዴት ከካንሰር ዳነች!! #ethiopia #ጸሎት 😱😭 https://www.youtube.com/watch?v=pSZVoIObUqw
በሕጻንነቱ በጸበል ተደግሞ የገባ መተት!! የሁላችንም ጥያቄ ዛሬ ተመለሰ!! 7ቱ የቅዱስ ቁርባን ወሳኝ ጥቅሞች!! ለዘርና ቋንቋ ጣኦት ሁላችንም ሰገድን!! 😱😭 https://youtu.be/EnIuWwh7UXs
መጋቢት ፩ /1/በዚችም ዕለት የሰማዕቱ የቅዱስ እለእስክንድሮስ መታሰቢያው ነው። ይህም ቅዱስ ሰማዕት የሮም ሀገር ሰው ነው ለእርሱ ባለመታዘዙና ለረከሱ ጣዖቶቹ ባለመሠዋቱ ከሀዲው መክስሚያኖስ ጽኑዕ ስቃይን አሠቃየው። እጅግ ከባድና ታላቅ የሆነ ደንጊያ በእጆቹና በእግሮቹ ላይ አሥሮ ሰቀለው። ብዙ ግርፋትንም ገረፈው ጐኖቹንም ቀደደ በፊቱም ላይ የእሳት መብራት ጨመሩ። ሥቃዩንም ባልፈራ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጀ። የፈጣሪው በረከት በእኛ ላይ ይደር ጸሎቱና በረከቱ ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር #Subscribe #Like #Share 👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239
#የምስጥር_መተትን_ድራሹን_የሚያጠፋው_ተዓምረኛው_ገዳም!! ሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም!! #መተት #መንፈስ #አጋንንት #ሽንቁሩ_ቅዱስ_ሚካኤል! #ethiopia https://youtu.be/AteNEW2COGs
የምስጥር_መተትን_ድራሹን_የሚያጠፋው_ተዓምረኛው_ገዳም!! ሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም!! #መተት #መንፈስ #አጋንንት #ሽንቁሩ_ቅዱስ_ሚካኤል! #ethiopia https://youtu.be/AteNEW2COGs
#ዘወትር_የሚሰገድ_የአምልኮት_ስግደት_በተግባር! በዐብይ ጾም ወቅት የሚሰገድ ስግደት!! እንዴት እንስገድ? የንስሐ እና የአምልኮት ስግደት በተግባር!! #ጸሎት https://youtu.be/OE7f3Mfj1ng
መቁጠሪያን ከሕሊና ጸሎት ጋር በተግባር እንዴት እንጠቀም! https://youtu.be/TAslYa1mUuQ?si=uJ8pBWgodl9aTuCO
መቁጠሪያን ከሕሊና ጸሎት ጋር በተግባር እንዴት እንጠቀም! https://youtu.be/TAslYa1mUuQ?si=uJ8pBWgodl9aTuCO
የካቲት ፳፱ /29/
በዚችም ዕለት የአርሞኒ ሀገር ኤጲስቆጶስ የከበረ ቢላካርዮስ በሰማዕትነት አረፈ።
ይህም አባት ፈጽሞ እስከ አረጀ ድረስ በተሾመበት ወንበር ብዙ ዘመናት ኖረ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትንም ደረሰ። ሕይወት በሆኑ ትምህርቶቹም ብዙ ነፍሳትን መሥዋዕትን አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ።
በክርስቲያንም ወገኖች ላይ የስደትና የመከራ ወራት በሆነ ጊዜ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ደሙን ሊያፈስ ወደደ ሕዝቡንም ሰብስቦ በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ አዘዛቸው። ስለ ጌታችን ኢየሱስ ደሙን ሊያፈስ ይሻልና እነርሱ እንግዲህ ፊቱን እንደማያዩት ነገራቸው።
ሰምተውም አለቀሱ ስለ መለየታቸውም እጅግ አዘኑ የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ ለምን ትተወናለህ አሉት ማስቀረትና ማስተውም ባልተቻላቸው ጊዜ ከእርሳቸው ዘንድ ወጥቶ ወደ መኰንኑ ሔደ በፊቱም ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ብዙ አሰቃየው። ሕዝቡም ብዙ ልመናን አብዝተው ለመኑት ራስህን አድን ከከተማም ውጣ አሉት እርሱም ልባቸውን ደስ ያሰኝ ዘንድ በሥውርእወጣለሁ አላቸው።
በዚያችም ሌሊት ሰማዕትን ትሆን ዘንድ የተመኘኸውን በጎ ምክር ለምን ረሳህ እንደሚለው ሰው ሁኖ ራእይን አየ። ከዚህም በኋላ ተመልሶ ለመኰንኑ ተገለጠለት በዚያንም ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ መኰንኑ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ ሥጋውንም ምእመናን አንሥተው ወሰዱት ለኤጲስቆጶሳትም እንደሚገባ አክብረው ገንዘው በመቃብር አኖሩት።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@Estifanos2239
#ቁጣ_ድል_አይንሣህ
=> ወንድምህን ከሚገባው ይልቅ ለማክበር ሰውነትህን አትጋት። ባገኘህውም ጊዜ እጁን እግሩን ሳመው፤ በጎ አድርግለት አክብረህ ወደህ እየው፡፡ ሥራው ባይደለ ሥራ አመስግነው፣ ከአንተም በተለየ ጊዜ የእሱን ነገር ተናገር፡፡ ከበጎ ሥራው ወገን መናገር በሚቻልህ ገንዘብ በጎ በጎ አድርግለት፡፡
=> በጎ ነገር በመናገርህ ወደ በጎ ሥራ ትስበዋለህ ታነቃቀዋለህ፡፡ አንተ ባመሰገንከው ምስጋና፣ አንተ ባከበርከው ክብር የተነሣ ያፍር ዘንድ እንዳመሰገንከው ያልሆነ እንደሆነ ያፍራል፤ እንዲህ የሆነ እንደሆነ ዘርአ ትሩፋትን ትዘራበታለህ፡፡
=> ነፍስህ ከለመደችው ባልንጀራህን ከማክበር የተነሣ በጎ ነገርን መውደድ በልቡናህ ይቀርጻል፡፡ ፍጹም ትሕትናን ገንዘብ ታደርጋለህ ሳትጥር ብዙ ሥራ ትሠራልህ፡፡ የምታከብረው በጎውን ሰው ብቻ አይደለም ነውር ያለበትም ቢሆን አክብረው እንጂ፡፡ እንዲህ የሆነ እንደሆነ አንተ ካከበርከው ክብር የተነሣ አፍሮ ካንተ ድኅነትን ያገኛል።
=> ገንዘብህ የምትሆን ይህችን ጥበብ ለሁሉ አድርጋት፤ ጥበብም የተባለች ሰውን ማክበር ለሰው ማዘን መራራት ናት። አንዱንስ እንኳን አትቈጣ፣ ተቈጥተህ አታሳዝነው፣ ቍጣ ድል አይንሳህ፡፡ ስለ ሃይማኖትም ቢሆን፣ ሥራው ክፉ ስለሆነም ቢሆን ሰው እንዳታማ ተጠበቅ እንጂ አትፍረድበት፡፡ በልዕልና ፊት አይቶ ሳያዳላ የሚፈርድ ዳኛ ክርስቶስ አለንና፡፡ ወደ በጎ ሥራም ልትመልሰውም ብትወድ እዘንለት፤ እያለቀስህ የለዘበ ነገር ንገረው፤ በቍጣ አትናደድበት፤ ጸብ ያለህ ይመስለዋል ፍቅር ውስጣዊ ቍጣን አይሻምና።
#ማር_ይስሀቅ
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@Estifanos2239
መወለድ 2: እግዚአብሔርን ልጅ ብቻ ስጠኝ ብለው የተወለዱ ልጆች! #abelbirhanuየወይኗ #ጸሎት #ebs #ethiopia #hailegebrieltube https://youtu.be/DDk8lu-velM
እናትና አባቱን የሚያስደበድበው ክፉው የዓይነጥላ መተት!! የአዕምሮ ታማሚ ነው ብዬ ሆስፒታል አስገባሁት!! 3ቱ እውነተኛ ክርስትናን የሚኖር ሰው ደረጃዎች!! https://youtu.be/MRULtt1xHWY
የካቲት ፳፰ /28/በዚች ዕለት በነገሥታት መክሲሞስና መክስምያኖስ ዘመን ሮማዊ ቅዱስ ቴዎድሮስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህንንም ቅዱስ ለጣዖቱ እንዲሰዋ ንጉሱ ሊደልለው ቢሞክር እንቢ አለው በመጨረሻም ንጉሱ ለመኮንኑ ሰጠው መኮንኑም ሊያሳምነው ባልቻለ ግዜ አንገቱን አነቀው እግዚአብሔርም ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ አዳነውና እየዞረ የሚያስተምርበትን መንፈሳዊ ፈረስ ሰጠውና ወደ እስያ ሔደ። ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ የከበረ ቴዎድሮስን ከነፈረሱ እንዲይዙት በትምህርቱም የአመኑትን ሁሉ እንዲገድሉ መቶ ፈረሰኞች ወታደሮቹን ላከ። ከሴቶችና ከልጆች በቀር ስድስት ሺህ አርባ ስምንት ሰውን ገደሉ። ሊይዙትም ወደ ቅዱስ ቴዎድሮስ በደረሱ ጊዜ ፈረሱ በላያቸው ተወረወረ ከአፉም እሳትን አውጥቶ አመድ እስኪሆኑ አቃጠላቸው ነገር ግን ሌሎች አግኝተው ያዙትና ወደ ንጉሥ ወሰዱት እርሱም ወደ እሥር ቤት እንዲአስገቡት እንዳይበላና እንዳይጠጣም ደጃፎችን እንዲዘጉበት አዘዘ። ጌታችንም ተገለጠለትና ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ዕድል ፈንታውን ከርሱ ጋር በመንግሥተ ሰማያት ያደርግ ዘንድ ቃል ኪዳንን ሰጠው። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ቴዎድሮስን ወደ ነደደ እሳት ወረወሩት ምስክርነቱንም ፈጸመ የመላእክት አለቆች ሚካኤልና ገብርኤል ነፍሱን ተቀበሉ በሦስት አክሊላትም አቀዳጁት ሥጋውንም አውሳብያ የተባለች የመኰንኑ ሚስት ወሰደች ዋጋው ብዙ በሆነ ሽቱም ገነዘችውና ወደ ገላትያ ወሰደችው በዕብነ በረድ ሣጥንም አድርጋ በዚያ ቀበረችው ቤተ ክርስቲያንም ሠራችለት ከሥጋውም ታላላቆች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጹ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር #Subscribe #Like #Share 👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239
መወለድ 1: እግዚአብሔርን የተባረከ ልጅ ስጠኝ ብለው የተወለዱ ልጆች! #ethiopia #abelbirhanuየወይኗ #ጸሎት #live #hailegebriel https://youtu.be/LrBozPgejfc
ወጣቱ ከእንስሳት ተምሮ እንዴት ሕይወቱ ልቀየር ቻለ? 450 ሽህ አጋንንት ከሰማይ እሳት አዝንበው ያቃጠሉ አባት!! በጋብቻችን ውስጥ ያለው የዲያብሎስ ውጊያ!! https://youtu.be/EUXur9jGJkc
የዲያብሎስ ውጊያ ካለባችሁ እመኑኝ ባለጸጋ ናችሁ!! የመርካቶ ገበያ በመናፍስት የመለካከፍ ዳፋ!! የንግድ ሱቅ ያላችሁ ቤተሰቦች ልታዳምጡት የሚገባ!! #ጸሎት
https://youtu.be/U5d7T7cD464
የካቲት ፳፮ /26/በዚች ዕለት ዖዝያ ይባል የነበረ ዕውነተኛ ነቢይ ሆሴዕ አረፈ። ዳግመኛም ይህ ነቢይ በአራቱ የይሁዳ ነገሥታት ዘመን ትንቢት ተናገረ። እሊህም ዖዝያን፡ ኢዮአታም፡ አካዝ፡ ሕዝቅያስ ናቸው። በትንቢቱም ድንቆች ሥራዎችን ተናገረ የእስራኤልንም ልጆች ገሠጻቸው የአመንዝራ ልጆች ብሎም ጠራቸው እግዚአብሔርም ቍጣውን ከእርሳቸው እንደማይመልስ አስረዳቸው። እንዲህም አለ የእስራኤል ልጆች ቍጥራቸው እንደማይሠፈርና እንደማይቈጠር የባሕር አሸዋ ቢሆን ከጥቂት በቀር አይተርፍም አለ። ስለ አሕዛብም በእግዚአብሔር ማመን ተናገረ እንዲህም አለ እኔ ወገኖቼ ያልሆኑትን እጠራቸዋለሁ እነርሱም ይሰሙኛል። ዳግመኛም ስለ መድኃኒታችን መከራ መቀበልና በከበረ ደሙ ስለ መዳናችን ስለ ትንሣኤውም እንዲህ ብሎ ተናገረ። እሱ በመከራ ገርፎ ያድነናል እርሱም በመከራ አቍስሎ ይቅር ይለናል ሲያድነንም በሁለተኛው ቀን ነው በሦስተኛውም ቀን ድነን በሱ ፊት እንነሣለን እግዚአብሔርንም አውቀን እንከተለው ዘንድ ስለ ሞት ሥልጣን መሻር ስለ መቃብርም መሸነፍ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ ሞት ይዘህ ማስቀረትህ መቃብርስ ድል መንሳትህ ወዴት ነው ትንቢትን እየተናገረ ሰባ ዓመት ያህል ኑሮ በበጎ ሽምግልና አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑርለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር #Subscribe #Like #Share 👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239
አብዛኛው ስንበት ተማሪ አይቆርብም ለምን ይሆን?? የሰንበት ትምህርት ቤቶች የመናፍስት ፈተና! ዛሬ ጸበል እንጠጣለን ነገ ደግሞ እንሰክራለን!! #ethiopia https://youtu.be/ZQeZJJPMjsc
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
