cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Book Store

ጠቀሚ የሆኑ ጹሑፍ( ከቁርአን , ከሀዲስ , የንፅፅር ሐይማኖት ..... ) ና መፅሐፍት በዚህ ቸነል ይገኛሉ ለጓደኛዎ ይጋብዙ ኪታቦችን በድምፅ እናም በሶፍት ኮፒ ( አብዛኛው በአማረኛ የተዘገጁ ነቸዉ ) እንልካለን በራካ አለሁ ፊኩም ወጀዛኩም አለሁ ከይራን ከሲራን ። ሼር የድርጉ

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
389
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

1 @mishary_rashid_al_afasi 2 @Yassen_Al_Jazairi 3 @Sheikh_Abu_Bakr_Al_Shatri 4 @Sheikh_Muhammad_Al_Luhaidan 5 @Abdulbasit_Abdussamed1 6 @Sheikh_Abdul_Rahman_Al_Sudais 7 @Ali_Al_Huzaifi 8 @Khalifah_At_Tonaeijy 9 @Ahmad_Al_Ajmy 10 @Sheikh_Saad_Al_Gamidi 11 @Emad_Al_Mansary 12 @Abdullah_ibn_Al_Basfar 13 @Sheikh_Nasser_Al_Qatami 14 @Abdulhadi_Kanakeri 15 @Sheikh_Maher_Al_Muaiqly 16 @Sheikh_Adel_Rayan 17 @Khalil_Al_Hussary 18 @Sheikh_Muhammad_Ayyub 19 @Abdullah_Awad_Al_Juhany 20 @Abdul_Rashid_Ali_Sufi 21 @Mohamed_Siddiq_El_Minshawi 22 @Abdul_Rahman_Al_Ossi 23 @Sheikh_Saud_Al_Shuraim 24 @Yasser_Al_Dosarii 25 @Muhammad_Al_Kurdi1 26 @Fares_Abbad1 27 @Sheikh_Salah_Bukhatir 28 @Imad_Zuhair_Hafez 29 @Muhammad_AbdulKareem 30 @Ahmad_Misbahi 31 @Abdulaziz_Az_Zahrani 32 @Ibrahim_Al_Asirii 33 @Abdulbosit_Qobilov1 34 @Abdullah_al_Matrood1 35 @Afzal_Rafiqov1 36 @Hani_Ar_Rifai 37 @Abdullah_Ali_Jaber 38 @Sheikh_Muhammad_Jibril 39 @Jazza_Alswaileh 40 @Bandar_Balila 41 @Mohammad_Al_Tablawi 42 @Wadee_Al_Yamani 43 @Ghassan_Al_Shorbajyi 44 @Zaki_Dagistan 45 @Ahmad_Al_Lahdan 46 @Abdullah_Xalif 47 @Yasser_Al_Qureshi 48 @Nabil_Al_Rifai 49 @Salah_Al_Hashem 50 @Shirazad_Taher 51 @Tawfeeq_As_Sayeghh 52 @Rashid_Al_Arkani 53 @Sheikh_Mustafa_Ismail 54 @Ali_Yakupovv 55 @Abdullah_Kamel 56 @Mahmud_Ali_Albanna 57 @Sheikh_Idris_Abkar 58 @Hassen_Saleh 59 @Moeedh_Al_Harthi 60 @Ahmed_Naina 61 @Waleed_Al_Naehi 62 @Saber_AbdulHakam 63 @Mohammad_Saleh_Shah 64 @AbdulMuhsin_Qasim 65 @Salah_Al_Budair 66 @Akram_Alalaqimy 67 @Jamaan_Alosaimii 68 @Abdulmohsen_Harty 69 @Abdul_Wadood_Haneef 70 @Mohammad_Al_Abdullah 71 @Yahya_Hawwa 72 @Hasanxon_Yahyo_Abdulmajid 73 @Khalid_Al_Jaleel 74 @Noreen_Muhammad_Siddique 75 @Ahmad_Al_Shalabii 76 @Alzain_Muhammad_Ahmad 77 @Abdulmohsin_Al_Obeikan © @Quran_Mp3_Collection
نمایش همه...
👍 1
ለመስዋዕትነት የቀረበው ማን ነው? بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ እንደምን ከረማችሁ? ውድ ሙስሊም ወንድም እህቶቼ፡ እንዲሁም ክርስትያን ወገኖች! ዘፈን በከበሮ ነገር በቀጠሮ ነውና! ሰሞኑን አንድ ርዕስ አስተዋውቄያችሁ ነበር፣ እርሱም ለእርድ የቀረበው ማን ነው? ዒስማኢል ወይስ ይስሐቅ (ዐ.ሠ)? የሚል ርዕስ ነበር፣ ታዲያ በዚህ ሀሳብ ዙርያ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለመስዋዕትነት የቀረበው ኢስማዒል ነው ሲል፡ አይሁድና ክርስቲያኖች በተቃራኒው አይ! አይ! ለመስዋዕትነት ይስሐቅ ነው የቀረበው ይሉናል። እስቲ በዚህ ሀተታ የዚህን ውብ ታሪክ ሚስጥር ቁርዓን በተዓምራዊ መንገድ እንዴት እንደገለፀው እናያለን። በቁርዓን ላይ አምላካችን አላህ ለዕርድ የቀረበው የኢብራሂም (ዐ.ሠ) የመጀመሪያ ልጅ የሆነው ዒስማዒል (ዐ.ሠ) እንደሆነ ቁርዓን ላይ ይነግረናል። (ሱረቱል ሶፋት 100-107) ከዚያም በዚህ የኢብራሂም (ዐ.ሠ) ፍፁም ታዛኝነትና ታጋሽነት ምክንያት በሁለተኛ ልጁ በኢስሐቅ አብስሮታል።(ሱረቱል ሶፋት 112-113) እስቲ በስፋት እንዳስሰው ኢብራሂም (ዐ.ሠ) ልጅ ሳይወልድ የእርጅና ዕድሜ ላይ ደርሶ ነበር፣ እድሜውም ሲገፋ አምላኩን እንዲህ ብሎ ተማፀነ፦ رَبِّ هَبْ لِي مِنَ الصَّالِحِينَ (ሱረቱ አልሷፍፋት - 100) ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡ ከዚያም አምላካችን አላህ ፀሎትን ሰሚ ነውና ፀሎቱን ተቀበለው፦ فَبَشَّرْنَاهُ بِغُلَامٍ حَلِيمٍ (ሱረቱ አልሷፍፋት - 101) ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡ አምላካችን አላህ ኢስማዔል (ዐ.ሠ) ከተወለደ በኋላ ኢብራሂምን (ዐ.ሠ) ሊፈትነው ፈለገ፤ አብርሃም (ዐ.ሠ) ኢስማዔልንም ከመሰጠቱ በፊትም ይሁን ከዚያም በኋላ በጣም አመስጋኝ ባሪያ ነበር። በዚህ የእምነት ጥንካሬው ምክንያት ፈተናው ቀጠለ እናም በስንት ፀሎት ያገኘውን አንድያ ልጁን እንዲያርድ መለኮተዊ ትዕዛዝ በህልሙ ተመለከተ። ከዚያም ያየውን ሁሉ ለልጁ እንዲህ ነገረው፦ فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ السَّعْيَ قَالَ يَا بُنَيَّ إِنِّي أَرَىٰ فِي الْمَنَامِ أَنِّي أَذْبَحُكَ فَانظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَا أَبَتِ افْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِي إِن شَاءَ اللَّهُ مِنَ الصَّابِرِينَ (ሱረቱ አልሷፍፋት - 102) ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ አባቱ ለልጁ ያየውን በነገረውና ምን ትላለህ? ብሎ በጠየቀው ጊዜ፣ የልጁ መልስ አስደናቂ ነበር፤ አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ስራ አላህ ከፈቀደ ታጋሽ ሆኜ ታገኘኛለህ አለው። ኢብራሂም (ዐ.ሠ) እና ልጁ ዒስማዔል (ዐ.ሠ) የታዘዙትን ለመፈፀም ወደ ታዘዙበት ስፍራ አመሩ። ከዚያም ፈጣሪያችን አላህ ባዘዛቸው መልኩ ልጁ ለመታረድ አባትየው ለማረድ በተዘጋጁበት ጊዜ አምላካችን አላህ በትልቅ በግ ዕርዱን ቀየረለት። As-Saffat 37:103-107 (103) فَلَمَّآ أَسْلَمَا وَتَلَّهُۥ لِلْجَبِينِ (104) وَنَٰدَيْنَٰهُ أَن يَٰٓإِبْرَٰهِيمُ (105) قَدْ صَدَّقْتَ ٱلرُّءْيَآۚ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُحْسِنِينَ (106) إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْبَلَٰٓؤُا۟ ٱلْمُبِينُ (107) وَفَدَيْنَٰهُ بِذِبْحٍ عَظِيمٍ (103) ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡ (104) ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ! (105) ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ (106) ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ (107) በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡ ውድ አንባቢያን! እንግዲህ ይስሐቅ ከዚህ በኋላ ነው የተወለደው፣ በዚህ ሰዓት ኢስሐቅ ገና አልተወለደም ነበር። በዚህ ትልቅ ፈተና በስተኋል ያገኘውን ብቸኛ ልጁን እንዲያርድ ተጠየቀ ታጋሽ ሆኖም ተገኘ። በዚህ በትዕግስቱም ምክንያት አምላካችን አላህ በሁለተኛ ልጅ በኢስሐቅ አበሰረው። As-Saffat 37:108-114 (108) وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِى ٱلْءَاخِرِينَ (109) سَلَٰمٌ عَلَىٰٓ إِبْرَٰهِيمَ (110) كَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُحْسِنِينَ (111) إِنَّهُۥ مِنْ عِبَادِنَا ٱلْمُؤْمِنِينَ (112) وَبَشَّرْنَٰهُ بِإِسْحَٰقَ نَبِيًّا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ (108) በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡ (109) ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡ (110) እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ (111) እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡ (112) በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡ እዚህ አንቀፅ ላይ "አበሰርነው" የሚለው ቃል ላይ የገባችው "و" ሁሩፉል አጥፍ (coordinating conjunction) ብስራቱ ሁለተኛ ብስራት መሆኑን ቁልጭና ጥንፍፍ አድርጋ ታሳያለች። እስቲ ሌላ ማስረጃ እንመልከት፦ وَامْرَأَتُهُ قَائِمَةٌ فَضَحِكَتْ فَبَشَّرْنَاهَا بِإِسْحَاقَ وَمِن وَرَاءِ إِسْحَاقَ يَعْقُوبَ [ ሱረቱ ሁድ - 71 ] ሚስቱም የቆመች ስትኾን (አትፍራ አሉት) ሳቀችም፡፡ በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ (በልጁ) በያዕቁብ (አበሰርናት)፡፡ መላእክት ለሳራ በኢስሐቅ ሲያበስሯት በልጁም ጭምር ነው፤ ስለዚህ ሳራም ሆነች ኢብራሂም (ዐ.ሠ) ኢስሐቅ (ዐ.ሠ) ሳይወለድ በፊት ኢስሐቅ ያዕቆብ(ዐ.ሠ) የሚባል ልጅ እንደሚወልድ ያውቁ ነበር። ስለዚህ ኢስሐቅ ነው ለመስዋዕትነት የቀረበው ማለት ስሜት አይሰጥም ፈተናም አይባልም፣ ምክንያቱም ቀድመው እናቱም ሆነች አባቱ ገና ኢስሐቅ ሳይወለድ ያዕቆብ የተባለ ልጅ እንደሚወልድ ስለሚያውቁ ፈተናው ስሜት አይሰጥም ነበር። ግን ፈተናው ግልፅና ከባድ ፈተና የነበረው በስተርጅና አብረሃም የወለደውን ብቸኛ ልጁን ኢስማዔልን እረድ ስለተባለ ነው፤ አብረሃም የልጁ ህልውና ይቀጥል አይቀጥል አያውቅም ነበር ዘርም እንደሚኖረው ቃል አልተገባለትምና የሚያውቀው ነገር የለም። ሉዚያም ነው አምላካችን አሏህ ፈተናው ከባድ እንደነበረ እንዲህ የገለፀልን፦ إِنَّ هَـٰذَا لَهُوَ الْبَلَاءُ الْمُبِينُ (ሱረቱ አልሷፍፋት - 106) ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ ነግርና ገመድ አለውሉ አይፈታምና በተቀመጠው መሰረት መረዳት ግድ ነው፤ ቁርዓኑ ባስቀመጠው መልኩ ኢስሐቅ የተወለደው ከፈተናው በኋላ ነው። መቼም ለጠቢብ አንድ ቃል በቂው ነው!
نمایش همه...
አሁን እስቲ ጉዟችንን ወደ ባይብል እናድርግና መፅሐፍ ቅዱስ በዚህ ዙርያ ምን ይላል? የሚለውን እንመልከት። ከዚያ በፊት ግን ሹክ የምልህ ቢኖር የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል የሆነው ኦሪት አብዛኛው የባይብል ሙህራን የሚስማሙት ለሙሴ የተሰጠው አንድ መፅሀፍ ሲሆን በ1446 BCE. እንደሆነ ነው። ግን እነዚህ እጃችን ላይ ያሉትን አምስቱን ፔንታቶች አይደለም እነዚህስ? ከተባለ እነዚህማ ሙሴ ከሞተ ከ1000 አመታት በኋላ የተፃፉ መፅሃፍት ናቸው። እነዚህ አምስቱ መፅሃፍት የተፃፉት ከ600 እስከ 400 BCE. እንደሆነ ለዘብተኛም ሆኑ ፅንፈኛ ሙህራኖች ይስማማሉ። ስለዚህ አሁን እጃችን ላይ ያሉት አምስቱ ኦሪቶች አይደለም ኦሪጂናል ሊሆኑ ይቅርና የቅጂ ቅጂ ቅጂ እጃችን ላይ አይገኝም። ምንጭ፦ McDermott, John J. (2002). Reading the Pentateuch: a historical introduction. Pauline Press. p. 21. ISBN 978-0-8091-4082-4. Retrieved 2010-10-03 ነገር አንዛዛሁ መሰል ምን ለማለት መሰለህ ወዳጄ! መፅሃፍቶቹ የሙሴም ሆነ የፈጣሪ ቃል ናቸው ብለህ እንዳትጠብቅ እንዲሁም በኋላ ማሳይህ ነገር እንዲገባህና እንድትረዳው ስለፈለኩ ነው። ወደ ነጥቤ ስመለስልህ መፅሀፍ ቅዱስም ልክ እንደ ቁርዓኑ ሁሉ ዒስማዔል የመጀመሪያ ልጅ እንደሆነ ይናገራል። የአብራሃም ሚስት ሳራ መሐን ነበረች፣ ከዚያም መውለድ ስላልቻለች አገልጋይዋን ለአብረሀም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው፣ ከዚያም ሄዶ ከአጋር ጋር ተኛ አጋርም ፀንሳ ኢስማዔልን ወለደች። ዘፍጥረት 16 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ የአብራም ሚስት ሦራ፣ ልጆች አልወለደችለትም ነበር፤ እርሷም አጋር የምትባል ግብፃዊት አገልጋይ ነበረቻት። ² አብራምንም፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ልጅ እንዳልወልድ አድርጎኛል። ምናልባት በእርሷ በኩል ልጆች አገኝ እንደሆን ሄደህ ከአገልጋዬ ጋር ተኛ” አለችው። አብራምም ሦራ ባለችው ተስማማ። ³ አብራም በከነዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከኖረ በኋላ ሚስቱ ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋን #አጋርን_ሚስት_እንድትሆነው_ለባሏ_ሰጠችው። ⁴ አብራምም ከአጋር ጋር ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች። አጋርም ነፍሰ ጡር መሆኗን ባወቀች ጊዜ እመቤቷን መናቅ ጀመረች። ነገርን አድምጦ እህልን አላምጦ ነውና! እዚህጋ አስተውለህ አንብብ፣ አጋር ለአብረሃም ሚስት እንድትሆነው ነው የተሰጠችው ስለዚህ ሚስቱ ናት። ሳራ አጋርን ስታሰቃያት ኮበለለች ከዚያም የአብረሃም ሚስት አጋር ገና እርጉዝ ሆና ከሳራ ኮብልላ ሳለች መልአክ ለአጋር እግዚአብሄር ዘሯን የተባረከና ብዙ እንደሚሆን ቃል ገባላት። “ደግሞም መልአኩ፣ “ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፤ ከብዛቱም የተነሣ ሊቈጠር አይችልም” አላት።” — ዘፍጥረት 16፥10 (አዲሱ መ.ት) “የእግዚአብሔርም (ያህዌ) መልአክ በተጨማሪ እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ ፀንሰሻል፤ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ችግርሽን ተመልክቶአል፤ ስሙን እስማኤል ትዪዋለሽ።” — ዘፍጥረት 16፥11 (አዲሱ መ.ት) ኢስማዔል የሚለውን ስም ያወጣው ራሱ እግዚአብሄር መሆኑን ልብ ይሏል። ምክንያቱም አብርሃም የሚወርሰውን ልጅ መውለድ ይፈልግ ስለነበር ብዙ ጊዜ ወደ ፈጣሪው ፀልዩአል። ኢሽማኤል የሚለው ስም የእብራይስጥ ቃል ነው፣ "יִשְׁמָעֵ'' ኢሽማ ማለት ሰማኝ ማለት ሲሆን "אל" ኤል ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነው። በአንድ ላይ ሲነበብ ትርጉሙ፦ 《አምላክ ፀሎቴን ሰማኝ ማለት ነው》። ስለዚህ ኢስማኤል አብርሃም የሚወርሰውን ልጅ ፍለጋ ፀልዮ የተሰጠው ልጅ መሆኑን አትዘንጋ። አጋር ኢስማኤልን በወለደች ጊዜ አብራሃም 86 አመቱ ነበር፡፡ ፈጣሪው ባዘዘው መልኩ እስማዔል ብሎ ሰየመው፦ ዘፍጥረት 16 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵ አጋር ለአብራም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ አብራምም ስሙን እስማኤል ብሎ ጠራው። ¹⁶ አብራም፣ አጋር እስማኤልን በወለደች ጊዜ ዕድሜው ⁸⁶ ዓመት ነበር። እስማዔል 13 አመታት በሞላው ጊዜ እግዚአብሄር እንዲገረዝ አዘዘ አብረሃም ኢስማዔልንም ሆነ ራሱን እንዲሁም በቤት ሚኖሩትን አገልጋዮቹን ሁሉ አስገረዘ። ዘፍጥረት 17 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁴ አብርሃም ሲገረዝ ዕድሜው ⁹⁹ ዓመት ነበር። ²⁵ ልጁም እስማኤል ሲገረዝ ¹³ ዓመቱ ነበር። ልብ በል! አብርሃም 99 እንዲሁም እስማዔል 13 አመቱ ላይ እንዳለ ኢስሐቅ ገና አልተወለደም ነበር እንግዲህ እዚሁ ምዕራፍ ላይ ነው እግዚአብሄር ለአብርሃም ያበሰረው። ዘፍጥረት 17 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ሦራን ከእንግዲህ ሦራ ብለህ አትጠራትም፤ ስሟ ከዛሬ ጀምሮ ሣራ ይሁን። ¹⁶ እኔ እባርካታለሁ ከእርሷም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ የብዙም ሕዝቦች እናት ትሆን ዘንድ እባርካታለሁ፤ የሕዝቦችም ነገሥታት ከእርሷ ይወጣሉ።” ¹⁷ አብርሃምም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ ሣቀና በልቡ፣ “እንዲያው ምንስ ቢሆን የመቶ ዓመት ሽማግሌ የልጅ አባት መሆን ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመቷ ልጅ መውለድ ትችላለችን?” አለ። ወዳጄ አንዴ ማስተዋልህን ብቻ እነሆ በለኝማ! እንግዲህ እንደምታየው ከሣራ የሚወለደው ኢስሐቅ ገና ሳይወለድ ፍሬያማ እንደሚሆን እግዚአብሄር ለአብረሃም ተናግሯል፡ አብረህ ደሞ ምን አለው? ሳቀና እኔም ሚስቴም አርጅተን እንዴት ልጅ ይኖረናል? ይልቁንስ ኢስማዔልን ብቻ ባርከህ ባኖርክልኝ አለው። “አብርሃም እግዚአብሔርን (ኤሎሂም)፣ “እስማኤልን ብቻ ባርከህ ባኖርህልኝ” አለው።” — ዘፍጥረት 17፥18 (አዲሱ መ.ት) New International Version ራሱ እንዲህ አስቀምጦታል፦ “And Abraham said to God, "If #only_Ishmael_might_live_under_your_blessing!"” — Gen 17:18 (NIV) ከዚህ የምንረዳው አብረሃም ሁለተኛው ልጅ ባይሰጠው ራሱ ብቸኛው ልጁ ኢስማዔል ብቻ ከተባረከለት በቂው እንደሆነ ነው። ከዚያም በመቀጠል እግዚአብሄር እንዲህ አለው፦ “እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) እንዲህ አለ፤ “ይሁን እሺ፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ እኔም ከእርሱ በኋላ ለዘሩ ሁሉ የሚሆን የዘላለም ኪዳን ከእርሱ ጋር እገባለሁ።” — ዘፍጥረት 17፥19 (አዲሱ መ.ት)
نمایش همه...
እውነት ለሁሉ [truth for all]

ይህ ቻናል ዓላማው በማስረጃና በመረጃ በመታገዝ እውነትን ከውሸት በመለየት፣ በአላህ ፈቃድ በጨለማ የሚኖሩ ወገኖችን ብርሃን ወደሆነው ኢስላም መጣራት ነው። قُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ [ ሱረቱ ሰበእ - 49 ] «እውነቱ መጣ፡፡ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም (ተወገደ)» በላቸው፡፡

ስለዚህ በእነዚህ ህግጋቶችና ስርዓቶች ምክንያት አብረሃም ኢስማዔልን እንጂ ኢስሐቅን ለእርድ እንዳላቀረበ እንረዳለን። እንደዚሁም የዘፍጥረት ፀሃፊ ምን ያክል የማጭበርበር ሂደት እንዳካሄደ ልብ ይሏል። “እርሱም፣ “እጅህን በብላቴናው ላይ አታሳርፍ፤ ምንም ጒዳት አታድርስበት፤ እነሆ፤ እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) እንደምትፈራ ተረድቻለሁ፤ ልጅህን፣ ያውም አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሳሳህምና” አለው።” — ዘፍጥረት 22፥12 (አዲሱ መ.ት) “እንዲህም አለው፤ “እግዚአብሔርም (ያህዌ) በራሴ ማልሁ አለ፤ አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሳሳህምና፣” — ዘፍጥረት 22፥16 (አዲሱ መ.ት) ሀሰተኛና ቀጣፊ በቃሉ መንገደኛ ደግሞ በቅሉ ይታወቃልና! ማስተዋል ለሚችል ሰው እውነታው ግልፅ ነው። አይሁዶች የኢስሐቅ ዘር ነን ብለው ስለሚያምኑ ኢስሐቅ ብለው ቀይረውታል፣ አምላካችን አላህ የዚህን ድብቅ ሚስጥር እውነታ በማያወላውል መልኩ አስቀምጦልናል፤ አልሃምዱሊላህ! يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ ۚ قَدْ جَاءَكُم مِّنَ اللَّهِ نُورٌ وَكِتَابٌ مُّبِينٌ [ ሱረቱ አል-ማኢዳህ - 15 ] የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን (ሙሐመድ) በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ ክርስቲያን ወገኖች ሆይ! ኑ ስለሙ ሰላም ታገኛላችሁ እስከመቼ በውሸት ተደብቃችሁ? https://t.me/ewnet_lehulum
نمایش همه...
እውነት ለሁሉ [truth for all]

ይህ ቻናል ዓላማው በማስረጃና በመረጃ በመታገዝ እውነትን ከውሸት በመለየት፣ በአላህ ፈቃድ በጨለማ የሚኖሩ ወገኖችን ብርሃን ወደሆነው ኢስላም መጣራት ነው። قُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ [ ሱረቱ ሰበእ - 49 ] «እውነቱ መጣ፡፡ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም (ተወገደ)» በላቸው፡፡

እዚህጋ 《ኢስማዔልን ብቻ ባርክልኝ》ሲለው እግዚአብሄርም 《ይሁን እሺ》 በማለት ተቀበለው። ኢስሐቅን ደግሞ እንደሚወለድና የዘላለም ቃል ኪዳን ከኢስሐቅጋ እንደሚገባ ይናገራል። ወዳጄ እስቲ አስበው እግዚአብሄር እንደዚህ የሚለው ማንም ለእርድ ሳይቀርብ በፊት ነው። ወዳጄ! አብረሃም ልጁ ኢስሐቅ እንደማይሞትና ዘሩ እንደሚቀጥል ጠንቅቆ ያውቃል ምክንያቱም አስቀድሞ ቃል ኪዳን ስለተገባለት። ኧረ እንደውም ሀሳቡ እንደዚህ ይቀጥላል፦ “ስለ እስማኤልም ቢሆን ልመናህን ሰምቼሃለሁ፤ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ፤ የዐሥራ ሁለት አለቆች አባት ይሆናል፤ ታላቅም ሕዝብ አደርገዋለሁ።” — ዘፍጥረት 17፥20 (አዲሱ መ.ት) እንግዲህ ከዚህ አንቀፅ እንደምንረዳው ኢስማዔልም እንደማይሞትና የተባረከ፣ ፍሬያማ፣ ታላቅ ህዝብ እንደሚሆን ነው። ታዲያ የዘፍጥረት ፀሐፊ ምን ነክቶት ነው ታሪክ የሚያዛባው? ኢስማዔልም ሆነ ኢስሐቅ ሁለቱም ከተባረኩና ፍሬያማ እንደሚሆኑ ለአብረሃም ቀድሞ ከተነገረው በኋላ ልጅህን እረድ መባሉ ስሜት ይሰጣልን? በጭራሽ ምክንያቱም ፈተና እስከሆነ ድረስ ማንም ማወቅ የለበትም። ስለዚህ የዘፍጥረት ፀሃፊ ግልፅ የሆነ ስህተት ሰርቷል! አንቀፁ ሲቀጥል እንደዚህ ይላል፦ “ኪዳኔን ግን የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ልጅ፣ #ከይስሐቅ_ጋር_አደርጋለሁ።”” — ዘፍጥረት 17፥21 (አዲሱ መ.ት) እንግዲህ ወዳጄ! ይሄንን ግልፅ ማጭበርበር ሹፍልኝ እግዚአብሄር ለእርድ ከሚቀርበው ይስሃቅጋ አስቀድሞ ቃል ከገባ ነገሩ አልቆለታል ይሄ ፈተና አይባልም። ከእርዱ በኋላ ከሆነ እንደዚ የተባለው ያስኬዳል፣ ቅሉ ግን ኢስሐቅ ሳይወለድ ነው ይሄ ሁሉ ቃል ኪዳን የተገባለት። ከዚያም የሆነው ሆኖ ይስሃቅ ተወለደ፦ ዘፍጥረት 21 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ እግዚአብሔር (ያህዌ) በተናገረው መሠረት ሣራን አሰባት፤ የገባውንም ተስፋ ፈጸመላት። ² ሣራ ፀነሰች፤ ልክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ባለው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት። ³ አብርሃም፣ ሣራ የወለደችለትን ልጅ ስሙን ይስሐቅ አለው። ⁴ አብርሃም፣ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ባዘዘው መሠረት ልጁን ይስሐቅን በተወለደ በስምንተኛው ቀን ገረዘው። ⁵ አብርሃም፣ ልጁ ይስሐቅ ሲወለድለት፣ ዕድሜው መቶ ዓመት ነበረ። አብረሃም ኢስሐቅን ሲወልድ እድሜው መቶ ነበር ይለናል፤ እዚህጋ የዘፍጥረትን ፀሀፊ ስህተት ደግሜ ላሳያቹ ወዳለው ምዕራፍ 17 ላይ ገና እንደሚወለድ ብስራት ሲያበስረው አብረሃም እድሜው መቶ ነበር። ኢስሐቅ የዚያን ጊዜ አልተፀነሰም ነበር፤ መፀነሱን የሚናገረው ጥቅስ ዘፍጥረት ምዕራፍ 21 ላይ ነው። “ሣራ ፀነሰች፤ ልክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ባለው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት።” — ዘፍጥረት 21፥2 (አዲሱ መ.ት) ታዲያ የአብረሃም እድሜ መቁጠሩን አቁሞ ነበር እንዴ? ኢስሀቅ ገና ሳይፀነስ የአብረሀም እድሜ መቶ ኢስሀቅም ተወልዶ የአብረሃም እድሜው መቶ ነው። ቲንሽ ፈገግ ያስብላል! እዚያው ዘፍጥረት ምዕራፍ 17 ላይ ያለውን ስህተትም ተመልከቱልኝ። እግዚአብሄር ለአብረሃም ኢስሀቅ እንደሚወለድ ያበሰረው ጊዜ፣ እንዲሁም ኢስማዔልም መገረዝ እንዳለበት፣ በቤት ውስጥ ያሉት ሁሉ መገረዝ እንዳለባቸው ሲነግረው፤ አብረሃም እድሜው 100 ነበር ይለናል፦ ዘፍጥረት 17 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵ ከእንግዲህ ወዲያ ስምህ አብራም መባሉ ቀርቶ አብርሃም ይሆናል፤ የብዙ ሕዝቦች አባት አድርጌሃለሁና። ⁶ ዘርህን እጅግ አበዛለሁ፤ ብዙ ሕዝብም አደርግሃለሁ፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ። ⁷ በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ በዚህም የአንተና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ (ኤሎሂም) እሆናለሁ። … ¹¹ ስለዚህ ሁላችሁም ሸለፈታችሁን #ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ኪዳን ምልክት ይሆናል። … ¹⁷ አብርሃምም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ ሣቀና በልቡ፣ “እንዲያው ምንስ ቢሆን #የመቶ_ዓመት_ሽማግሌ የልጅ አባት መሆን ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመቷ ልጅ መውለድ ትችላለችን?” አለ። ወዳጄ ተከተለኝማ! ችግሩ ምን እንደሆነ ላሳይህ አብረሃም ገና ሳይገረዝ እንዲገረዝ ትዕዛዝ ሲመጣለት እድሜው መቶ ነበር ይላል። ዘፍጥረት ምዕራፍ 17:17 ቲንሽ ዝቅ ብሎ ደግሞ አንቀፅ 24 ላይ አብረሃም ሲገረዝ እድሜው ቀንሶ 99 ሆነ ይልሃል፦ ዘፍጥረት 17 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²³ በዚያችም ዕለት አብርሃም እግዚአብሔር (ያህዌ) ባዘዘው መሠረት ልጁን እስማኤልን፣ በቤቱ ውስጥ የተወለዱትንና ከውጭ በገንዘቡ የገዛቸውን ወንዶች በሙሉ ገረዛቸው። ²⁴ አብርሃም ሲገረዝ ዕድሜው ⁹⁹ ዓመት ነበር። ²⁵ ልጁም እስማኤል ሲገረዝ ¹³ ዓመቱ ነበር። ወዳጄ እንደምታየው ይሄ ትልቅ ስህተት ነው፣ ፀሀፊው የሚፅፈውን ሁላ ራሱ አያውቀውም፣ ለዚያም ነው መጀመሪያ ላይ ላንተው አስቤ፣ ይህ የፈጣሪ ቃል እንዲሁም የሙሴ ኦሪት ነው ብለህ አትጠብቅ ያልኩህ።በነገራችን ላይ ፀሃፊው ስህተት የሰራው እዚህ ላይ ብቻ አይደለም እህህህ! ብለህ ከሰማኸኝ ኢንሻ አሏህ በክፍል ሁለት ብቅ እላለሁ። https://t.me/ewnet_lehulum
نمایش همه...
እውነት ለሁሉ [truth for all]

ይህ ቻናል ዓላማው በማስረጃና በመረጃ በመታገዝ እውነትን ከውሸት በመለየት፣ በአላህ ፈቃድ በጨለማ የሚኖሩ ወገኖችን ብርሃን ወደሆነው ኢስላም መጣራት ነው። قُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ [ ሱረቱ ሰበእ - 49 ] «እውነቱ መጣ፡፡ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም (ተወገደ)» በላቸው፡፡

ለመስዋዕትነት የቀረበው ማን ነው? የቀጠለ! بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ እንደምን ነህ ወዳጄ? በክፍል አንድ ላይ የዘፍጥረት ፀሃፊ ምን ያክል ትላልቅ ስህተቶችን እንደሰራ አየህልኝ አይደል? አሁን በማስቀጠልም የፀሀፊውን ችግር እንዲሁም ስርዓቶቹና ህግጋቶችስ ምን ይላሉ? የሚለውን እናያለን ና ተከተልኝ! ለማስተዋስ ያክል ይቺን ልበልህ፣ ሁለቱም የአብረሃም ልጆች ኢስሐቅም ይሁን ኢስማዔል በፈጣሪ ዘንድ ተባርከዋል። እግዚአብሄር እነሱንም ሆነ ዘራቸውን የባረከው ማንም ለዕርድ ከመቅረቡ በፊት ስለሆነ ከተባረኩ በኋላ ለዕርድ መቅረባቸው ምንም ስሜት አይሰጥም፣ ፈተናም አይባልም። ምክንያቱም አብረሃም ይሄንን ነገር ጠንቅቆ ስለሚያውቅ! ዛሬ ደግሞ ወደ ዋናው ነጠብ ልውሰድህና አጃዒብ! ላስብልህ። ዘፍጥረት 22 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) አብርሃምን ፈተነው፤ “አብርሃም!” አለው። እርሱም “አቤቱ አለሁ” አለ። ² እግዚአብሔርም (ኤሎሂም)፣ “የምትወደውን አንዱን ልጅህን፣ ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እኔ በማመለክትህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው። በዚህ ጥቅስ መሰረት እግዚአብሄር አብረሃምን እንደፈተነው ይናገራል። ፈተናው ምንድን ነው? መጀመሪያ ለአብረሃም ቃል የተገባለትን ኢስሐቅን ራሱ አብረሃም ልጁን እንዲያርደው ትዕዛዝ ተሰጠው። ልብ በልልኝማ አንዴ! አብረሃም ልጁ ኢስሃቅ እንደማይሞት ቀድሞ ያውቃል ምክንያቱም ቀድሞ እንዲህ ተብሏል ኣ! “እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ስለ ልጁም ሆነ ስለ አገልጋይህ አሳብ አይግባህ፤ ዘር የሚጠራልህ በይስሐቅ በኩል ስለ ሆነ፣ ሣራ የምትልህን ሁሉ ስማ።” — ዘፍጥረት 21፥12 (አዲሱ መ.ት) ወዳጄ በጣም ይቅርታ! ደጋገምኩብህ መሰል፣ ያው ነገርን ከስሩ ውሃን ከጡሩ ይባል የለ!? ነገሩ መጀመሪያም እንደተበላሸ አስረግጠህና እረግጠህ እንድትይዝልኝ ስለፈለኩ ብቻ ነው። አሁንም ወደ ዋናው ነጥብ ስመልስህ ጥቅሱ እንዲህ ይላል፦ “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያም ምድር ሂድ፤ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ።” — ዘፍጥረት 22፥2 እግዚአብሄር አብረሃምን ሲያዘው የምትወደውን አንድ ልጅህን ኢስሐቅን ሰዋ ብሎ ነው። እስቲ በዚህ ጥቅስ ላይ አንድ አራት ጥያቄ እናንሳና ራሱ ባይብል ገላጋይ ይኹነን። 1ኛ: እንዴ!! ኢስሐቅ ሁለተኛ ልጅ አይደል እንዴ? አዎ ኢስሃቅ ሲወለድ ኢስማዔል የ14 አመት ልጅ ነበር። ዘፍጥረት 16፥16 አጋር እስማኤልን ለአብራም በወለደችለት ጊዜ አብራም የሰማንያ ስድስት ዓመት ሰው ነበረ። ዘፍጥረት 21፥5 አብርሃምም ልጁ ይስሐቅ በተወለደለት ጊዜ የመቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ። 2ኛ: ኢስማዔል ታዲያ ለአብራሃም ልጁ አይደለምን? አረ ነው ያውም የበኩር ልጁ! “አጋርም ለአብራም ወንድ ልጅን ወለደችለት፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው።” — ዘፍጥረት 16፥15 3ኛ: አብረሃም ስንት ልጅ ነው ያለው? ሁለት ልጆች አሉት ይሄም ተፅፏል። “አንዱ ከባሪያይቱ አንዱም ከጨዋይቱ የሆኑ ሁለት ልጆች ለአብርሃም እንደ ነበሩት ተጽፎአልና።” — ገላትያ 4፥22 4ኛ አብረሃም ኢስማዔልን አይወደውም እንዴ? ኧረ በጭራሽ! በጣም ነው የሚወደው ይስሃቅን ሲበሰር እንኳን "ኢስማዔልን ብቻ ባርከህ ባኖርክልኝ" ብሎ እንዴት እንደሚወደውና እርሱ ብቻ እንደሚበቃው ተናግሮ የለ እንዴ? “አብርሃም እግዚአብሔርን (ኤሎሂም)፣ “እስማኤልን ብቻ ባርከህ ባኖርህልኝ” አለው።” — ዘፍጥረት 17፥18 (አዲሱ መ.ት) አሁንም የዘፍጥረት ፀሃፊ ልክ እንደቀድሞው ሁላ ትላልቅ ስህተቶችን ሰርቷል። ምንድን ነው? ካልከኝ ፦ 1ኛ ኢስሃቅን የአብረሃም ብቸኛው ልጅ አስመስሎ ማቅረቡ! 2ኛ ኢስሃቅን የበኩር ልጅ አስመስሎ ማቅረቡ! 3ኛ አብረሃምን ህግና ስርዓት እንደጣሰ አይነት ሰው አድርጎ ማቅረቡ! 4ኛ አብረሃም ኢስማዔልን እንደሚጠላው አድርጎ ማቅረቡ! በሙሴ ህግ መሰረት የወንድ ልጆች በኩራት ሁሉ ለእግዚአብሄር የሚሰጡ ሲሆን በእነርሱ ፈንታ የእንስሳት በኩር ይታረዳል። ““መጀመሪያ የተወለደውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከእስራኤላውያን መካከል የእናቱ የበኵር ልጅ የሆነው ማሕፀን ከፋች ሰውም ሆነ እንስሳ የእኔ ነው።”” — ዘጸአት 13፥2 (አዲሱ መ.ት) ““የእህልህን ወይም የወይን ጠጅህን በኵራት ለእኔ ከማቅረብ ወደ ኋላ አትበል። “የወንድ ልጆችህን በኵር ለእኔ ስጠኝ።” — ዘጸአት 22፥29 (አዲሱ መ.ት) ዘኍልቁ 3 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹² “እነሆ፤ በኵር ሆኖ በሚወለደው ሁሉ ምትክ ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን ወስጃለሁ፤ ስለዚህ ሌዋውያን የእኔ ናቸው፤ ¹³ በኵር የሆነ ሁሉ የእኔ ነውና። በግብፅ ምድር በኵር የሆነውን ሁሉ በመታሁ ዕለት ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ማናቸውንም የእስራኤልን በኵር ለራሴ ለይቻለሁ፤ የእኔ ይሁን። እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።” ወዳጄ! የበኩር ልጅ ህግ ምን እንደሆነ ምታውቀው ነገር ይኖር ይሆን? ህጉ ይሄን ይመስላል፦ ዘዳግም 21 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵ ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፥ ለእርሱም የተወደደችው ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ፥ በኵሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ቢሆን፥ ¹⁶ ለልጆቹ ከብቱን በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኵሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኵር ያደርገው ዘንድ አይገባውም፤ በዚህ ህግ መሰረት እንዴትም ብሎ ኢስሐቅ ለእርድ ሊቀርብ አይችልም፣ ምክንያቱም የበኩር ልጅ ኢስማዔል እንጂ ኢስሃቅ ስላልሆነ። አንዳንድ የዋህ ክርስቲያኖች ምን እንደሚሉ ታውቃለህ? አጋርኮ ለአብረሃም ባሪያው እንጂ ሚስቱ አልነበረችም ይላሉ! ይህ ንግግራቸው ለማጭበርበር እንዲመቻቸው እንጂ አጋር ለአብረሃም ሚስቱ ነበረች። አጋር ለአብረሃም ምኑ ናት? ሚስቱ! ማስረጃም ካልከኝ እነሆ ጀባ ብያለሁ፦ “አብራምም የሦራን ቃል ሰማ። አብራምም በከነዓን ምድር አሥር ዓመት ከተቀመጠ በኋላ፥ የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባሪያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።” — ዘፍጥረት 16፥3 አብረሃም እነዚህን ህግጋቶችና ስርዓቶች አልጠበቀም እንዴ? ኧረ ጠብቋል! “አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን ሕጌንም ጠብቆአልና።” — ዘፍጥረት 26፥5
نمایش همه...
እውነት ለሁሉ [truth for all]

ይህ ቻናል ዓላማው በማስረጃና በመረጃ በመታገዝ እውነትን ከውሸት በመለየት፣ በአላህ ፈቃድ በጨለማ የሚኖሩ ወገኖችን ብርሃን ወደሆነው ኢስላም መጣራት ነው። قُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ [ ሱረቱ ሰበእ - 49 ] «እውነቱ መጣ፡፡ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም (ተወገደ)» በላቸው፡፡

1.4 ለምን ተፈጠርን? ኃያሉ አምላክ ህያውና ዘላለማዊ ሲሆን ከማንም ምንም የማያስፈልገው በራሱ የተብቃቃ ወደ ፍጡራን የማይከጀል ነው።《 እናንተ ሰዎች ሆይ!እናንተ(ሁል ጊዜ)ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ። አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው።》ቁርአን (35፥15)ታድያ አምላክ በራሱ ቋሚና ብቻውን ዘላለም መኖር ከቻሉ የሰው ልጆችን መፍጠር ለምን አስፈላገ? ይህ ጥያቄ ለዘመናት በርካቶች ጠይቀውት በቂ ምላሽ ያላገኘሉት ጥያቄ ከመሆኑም ባሻገር እጅግ መልስ የሚያሻው መፈጠራችንን ትርጉም የሚሰጠው ወሳኝ ጥያቄ ነው። ማርክስ የተባለው ታዋቂው ፈላስፋ ተፈጥሮን ከቃኘና የመፈጠራችን ሚስጥር አልገባ ሲለው“ አምላክ ተፈጥሮን ያስገኛት ሊያላግጥባት ነው። ፈጣሪ ፍጥረታትን አስገኘና ከዛም ረስቷታል“ ብሎ ድምዳሜውን ሰጠ። እውን ጥበበኛው አምላክ ይህን ግዙፍ ፍጥረተ - ዓለም እንዲሁም የሰው ልጆችን ያስገኘው እንዲሁ ለፌዝ ፣ ለቀልድና ለጨዋታ ነውን? 《የፈጠርናችሁ ለከንቱ መሆኑን እናንተም ውደኛ የማትመለሱ መሆናችሁን ጠረጠራችሁን?》ቁርአን(23፥115)አምላካችን አላህ ምንንም ነገር ያለ ምክንያት አላስገኘም።《ሰማያትንና ምድርንም በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ሆነን አልፈጠርንም፣ሁለቱንም በምር እንጂ አልረጠርናቸውም ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም》ቁርአን(44፥38-39) እስኪ ለአፍታ በዙሪያችን ያለውን ነገር እንቃኝ። እግራችን ስር ያለውን ምድር ካስተዋልን የተለያዩ አይነት ፍራፍሬዎችንና አዝርዕቶችን እያበቀለች የምትጠቅመው እኛን ነው ፤ ከበላያችን ያለው ሰማይም ዝናብን ሲጥል እንዲሁ ተጠቃሚዎቹ የሰው ልጆች ናቸው። ቀኑን እንሰራበታን ልቱን እናርፍበታለን እንስሳዎችንም ለተለያዩ አገልግሎቶች እንጠቀምባቸዎለን እንዲሁም በርካታ ነገሮችን በጥልቀት ካስተዋልን የሰው ልጆችን በማገልገል ተጠምደዋል። ታዲያ ፈጣሪ ይህን ሁሉ ነገር የኛ አገልጋይ አድርጎ እኛንስ ለምንድን ነው የፈለገን? ለዚህ ወሳኝና አንገብጋቢ ጥያቄ በቂና የተሟላ መልስ የሰጠ ብቸኛው መለኮታዊ መፅሃፍ ታዐምረኛው ቁርአን ብቻ ነው። ይህ ታላቅ መፅሃፍ የሰው ልጆች የተፈጠሩበትን ቀዳሚና ዋነኛ አላማ በአጭሩ ሲያስቀምጥ《ጋኔንና ሰውንም(እኔን)ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም》ቁርአን(51፥56)ሲል የመፈጠራችንን አላማ ‘ እኛን ጨምረ ፍጡራንን ሁሉ ያስገኘውን አላህን ማምለክ ’ መሆኑን ይነግረናል። የሰው ልጅ እራሱን ከስሜት ባርነት አላቆ የዓለማቱ ጌታ ባሪያ ሲሆን ፣ በእጁ የጠረበውን ጣኦት መገዛት አቁሞ ለፈጣሪው ሲያጎበድድ እንዲሁም በአጠቃላይ ፍጡራንን ትቶ ፈጣሪን በብቸኝነት ሲያመልከና የአንዱ አላህ አገልጋይ ሲሆን በምድራዊ ዓለም ላይ ያለው ቆይታ በነፃነት የተሞላ ከማድረጉም ባሻገር የተፈጠረበት አላማ ተገንዝቦ ተግባር ላይ ያዋለ የተከበረ ፍጡር ይሆናል። ይህ ነው እንግዲ የመፈጠራችን ዓላማና የመኖራችን ሚስጥር። የሰው ልጅ ይህንን ትልቅ ዓላማ ተገንዝቦ እርሱን በፈጣሪ ሲያስገዛ እንዲሁም እንዳሱ ፍጡር የሆኑ አካላትን ከማምለክ ይልቅ በጌታው አምልኮ ላይ ማንንም ሳያጋራ ነፍሱን ለአንድ አላህ ሲሰጥ በምድራዊ ህይወት ደህንነትን ሰላምን በቀጣዩ ዓለም ዳግም ዘላለማዊ የተድላ ህይወትን ይወርሳል። እርግጥ ነው ብዙዎች የፈጣሪን መኖር ይቀበላሉ፣ ‘አሃዱ አምላክ’ በማለትም ይህ ፈጣሪ አንድና ብቸኛ መሆኑን ይመስክራሉ። ነገር ግን ለዚህ ኃያል ፈጣሪ ያላቸው ምልከታ እጅግ ከእውነት የራቀ ሆኖ እናገኘዋለክ። አንዳንዶች ፈጣሪ ሃያል ስለሆነ እሱ ላይ የምንዳርሰው በአማልክቶቻችን ነው በማለት ለአላህ አምሳሎችን ያደርጋሉ ፣ አላህም እንዲህ ሲል ይኮንናቸዋል 《ምንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን(በአላህ) ላይ ያጋራሉን?》ቁርአን(7፥192)በሌለም ቦታ 《ለእርሱ (ለአላህ)ምክሼን (አምሳያ)ታወቃለህን?》ሲል ይጠይቃል ቁርአን(19፥65) ሌሎች ደሞ ታላቁን አምላክ ሁሉን ቻይ ነው በሚል ፈሊጥ ሰው እስከ ማድረግም ይደርሳሉ። አምላክ በህልውናው ሁሉን ፈጣሪ አምላክ ሆኖ ሳለ እንዴት በደካማውና በፍጡሩ የሰው ልጅ ይመስላል《 እርሱ (አላህ)የሰማያትና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው። ለርሱ ሞክሼን (አምሳ) ታውቃለህን?》ቁርአን(19፥65) በርካቶች እንዲሁ በመላ ምትና ባልተጨበጠ መረጃ ላይ ተንተርሰው ስለ ኃያሉ አምላክ ኢ-ምክኒያታዊ የሆኑና ለፈጣሪ ልዕቅና የማይመጥኑ ግምቶችን ሲሰገዝሩ ቆይተዋል አሁንም እየሰነዘሩ ነው《የሰማያትና የምድር ጌታ የዙፋኑ ጌታ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ》ቁርአን (43፥82) ይህንን ፍጥረተ-ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ እንዲሁም እኛን የሰው ልጆችንም ካልነበርንበት ያስገኘን አምላክ አንድና ብቸኛ ከሆነ አምልኮ የሚገባውም ለርሱ ብቻ ነው። 《እርሱም ያ በሰማያትና በምድር (ሊገዙት የሚገባው)አላህ ነው። ሚስጥራችሁንም ግልፃችሁንም ያውቃል የምትሰሩትንም ሁሉ ያውቃል።》ቁርአን(6፥3) እርሱ አላህ ሊያጎበድዱለት ፣ ሊያጎነብሱለት ፣ ሊሰግዱለት ፣ ድካ የደረሰ መተናነስን ሊተናነሱለት የሚገባ በሰማይም በምድርም አምሳያ የሌለው ኃያል አምላክ ነው በተከበረው መለኮታዊ ቃሉ እንዲህ ይለናል 《(እርሱ)ያ ለናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማያንም ጣራ ያደረገ ነው፣ ከሰማይም (ዳመና)ውሀን ያወረደ በርሱም ከፍሬዎች ለናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው። እናንተም(ፈጣሪነቱን)የምታወቁ ስትሆኑ ለአላህ ባላንጣዎች አታድርጉ》ቁርአን(2፥22)ያለምንም ረዳት ፍጥነታትን ያስተኘ አምላክ አምልኮ የሚገባውም ለርሱ ብቻ ነው። የሰው ልጆች ድሮም ዘንድሮም የተላያዩ ነገሮችን ከአላህ ውጪ ሲያመልኩ ቆይተዋል። አሁንም እያመለኩ የገኛሉ። ገሚሱ ራሱ የጠረበውን ድንጋይና እንጨት አማልክት ብሎ ሰይሞ ለነሱ ሲሰግድ ፤ ሌላኛው ደግሞ ለፀሀይና ለጨረቃ የሚያጎበድድም አለ! ኃያሉ አላህ እንዲህ ይላል 《ሌሊትና ቀንም ፀሀይና ጨረቃም ከምልክቶቹ(ተአምራቶቹ)ናቸው። ለፀሃይና ለጨረቃ አትስገዱ። ለእዚያም ለፈጠራችሁ አላህ ስገዱ እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደሆናችሁ(ለሌላ አትስገዱ)》ቁርአን(41፥37) አንዳንዶች ደግሞ እንደራሳቸው አምሳያ የሆኑትን የሰው ልጆችን ወይ ቅዱሳን ወይ ነብያት ስለሆኑ ብቻ ከተሰጣቸው ደረጃ በላይ ከፍ በማድረግ ለአላህ ብቻ የሚገባን አምልኮ አሳልፈው ለነሱ ይሰጣሉ። 《 “ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከሆነው አላህ እርሱ የሚመግብም ሲሆን ሌላን አምላክ እይዛለሁን?” በላቸው።》 ቁርአን(6፥14) ሰማያትና ምድርን ያለምሰሶ ያቆመ ፣ እነርሱን በመፍጠር ላይም ከማንም እርዳታ ያላስፈለገው አምላክ እንዲሁም እኛን የሰው ልጆች ድንቅ በሆነ አፈጣጠርና እጅግ ባማረ አቋም ላይ ያስገኘን ፈጣሪ ከርሱ በቀር እውነተኛ አምላክ አለመኖሩ እርገጥ እንደሆነው ሁሉ አምልኮ ፣ ስግደት ፣ ፆም ፀሎትም ሆነ ሌሎች አምልኮዎች የሚገቡት ለርሱ ብቻ ነው። 《ስግደቴ ፣ መገዛቴ ፣ ሕወቴም ፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው፤ በል ለርሱ ተጋሪ የለውም በዚህም ታዘዝኩ ‘በል’ 》ቁርአን(6፥162-163) https://t.me/usefullIslamicBookstore
نمایش همه...
Book Store

ጠቀሚ የሆኑ ጹሑፍ( ከቁርአን , ከሀዲስ , የንፅፅር ሐይማኖት ..... ) ና መፅሐፍት በዚህ ቸነል ይገኛሉ ለጓደኛዎ ይጋብዙ ኪታቦችን በድምፅ እናም በሶፍት ኮፒ ( አብዛኛው በአማረኛ የተዘገጁ ነቸዉ ) እንልካለን በራካ አለሁ ፊኩም ወጀዛኩም አለሁ ከይራን ከሲራን ። ሼር የድርጉ

አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ! እንኳን የዒዱል ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ! ተናፍቆ የሚመጣ እና ሳይጠገብ የሚሄድ ብቸኛው ወር የረመዷን ወር ነው። አሏህ ከእኛም ከእናንተ መልካም ሥራዎችን ይቀበል! አሚን። ዒድ ሙባረክ!
نمایش همه...
የረመዷን ስጦታ ረመዷን ሙባረክ ያ ሙሥሊሙን ወሙሥሊማት! በ 13 አርስት የተሰደረ መጣጥፍ በረመዷን ወር እንካችሁ ብለናል። ሊንኩን በማስፈንጠር ያግኙት! 1. ሶውም https://t.me/Wahidcom/3136 2. የጦም ትሩፋት https://t.me/Wahidcom/3470 3. ረመዷን https://t.me/Wahidcom/2727 4.. የረመዷን ወር https://t.me/Wahidcom/3107 5. የክርስትና ጦም https://t.me/Wahidcom/3176 6. የጨረቃ አቆጣጠር https://t.me/Wahidcom/2717 7. ጨረቃ እና ኮከብ https://t.me/Wahidcom/2360 8. የሚታሰሩ ሰይጣናት https://t.me/Wahidcom/2724 9. ሡሑር https://t.me/Wahidcom/2726 10. ተራዊህ https://t.me/Wahidcom/833 11. ኢዕቲካፍ https://t.me/Wahidcom/2286 12. ለይለቱል ቀድር https://t.me/Wahidcom/2289 13. መሓላ እና ማካካሻው https://t.me/Wahidcom/2336 ሁሉም ቦታ ለሁሉም ሰው እንዲዳረስ አሰራጩ! ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ!
نمایش همه...