fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

رفتن به کانال در Telegram

💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።

نمایش بیشتر
8 797
مشترکین
-424 ساعت
-247 روز
-1430 روز
آرشیو پست ها
የምትረሳ ሳይሆን ሁሌም የምትታወስ ደግ ሠው ሁን! ~
የምትረሳ ሳይሆን ሁሌም የምትታወስ ደግ ሠው ሁን! ~

የክረምት ኮርስ ሱረቱ አል-ፋቲሃ ትርጉም https://t.me/SadatKemalAbuMeryem

🔖ዚክር እና ዱዓ  ማብዛት የኸይር  ሁሉ መክፈቻ ነው. አቡል ዓባስ ኢብኑ ተይሚያህ 📚 مجموع الفتاوى (٦٦١/١٠) =

የወንድማችን ጦለሀ አህመድ & የእህታችን ነጃት አብዱረህማን የኒካህ  ፕሮግራም በማስመልከት የተዘጋጀው የሙሀደራ ፕሮግራም 🌹ተ     🌹ጀ         🌹ም             🌹ሯ                  🌹ል ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም ተከታተሉ ሼር አድርጉት: 👇👇👇👇 https://t.me/tolehaahmed?livestream https://t.me/tolehaahmed?livestream

🔖 የአሹራ ቀን መጾም ጥበቡ ...! =
🔖 የአሹራ ቀን መጾም ጥበቡ ...! =

✈️ ቀጥታ ስርጭት ሙሃደራ 🎙 قصة نجاة موسى وغرق فرعون የሙሣ መዳንና የፊርአውን መስመጥ ታሪክ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 እሁድ ማታ ⏱ ከምሽቱ 3:30 🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም የስርጭት ሊንክ t.me/abu_reyyis_arreyyis?livestream t.me/abu_reyyis_arreyyis?livestream

فضل صيام يوم عاشوراء...

هل يجوز صيام عاشوراء فقط ؟!!

صيام عاشوراء ثلاثة أقسام...

👉አንድ ሴት ሰለፍይ ወይም ሷሊህ ደግ ናት ማለት ወንጀል የማትሰራ የማትሳሳት ጥቡቅ ናት ማለት አይደለም። ነገር ግን፦ ☞ሲያስታውሷት ትነቃለች ☞ሲመክሯት ትቀበላለች ☞ከስህተቷ ትመለሳለች ☞ለወንጀሏ እስቲግፋር ትጠይቃለች። ~ ممقول t.me/https_Asselfya

الأسبوع القادم .. إن شاءالله .. الإثنين ٩ محرم : تاسوعاء + سُنّة الإثنين الثلاثاء ١٠ محرم : عاشوراء " كفارة سنة " الأربعاء ١١
الأسبوع القادم .. إن شاءالله  .. الإثنين ٩ محرم :  تاسوعاء + سُنّة الإثنين الثلاثاء ١٠ محرم :  عاشوراء " كفارة سنة " الأربعاء ١١ محرم :   يلي عاشوراء الخميس ١٢ محرم  : سُنّة الخميس الجمعة ١٣ محرم :  أول الأيام البيض السبت ١٤ محرم :   ثاني الأيام البيض الأحد ١٥ محرم : ثالث الأيام البيض

❝የሴትነት ሞራል ...! በነገ ተስፋ ላይ እቅዷን ሰንቃ፤ ሁሉን እየቻለች ችግሮቿን ንቃ፤ ሰለፍያዋ እንስት ትታያለች ደምቃ፤ በስደት አለም ላይ ህይወቷን ገብራ፤ ዉስጧ እየታመመ ዉጯ የሚያበራ፤ ዉድ
❝የሴትነት ሞራል ...! በነገ ተስፋ ላይ  እቅዷን ሰንቃ፤ ሁሉን እየቻለች ችግሮቿን ንቃ፤ ሰለፍያዋ እንስት ትታያለች ደምቃ፤ በስደት  አለም ላይ ህይወቷን ገብራ፤ ዉስጧ  እየታመመ ዉጯ  የሚያበራ፤ ዉድ የአላህ ባሪያ ያች ሰለፍያ ትታያለች አምራ ..!   አንድ ጊዜ ስትቆርጥ  ሺ ጊዜ ስትለካ ፤ እንደነ ኸድጃ ደግሞ እንደበረካ፤ በዱኒያዊ ወረት በጌጥ ሳትረካ፤ ሴትነት እንዲህ ነዉ  ታዕምር ነዉ ለካ፤    ~        http://t.me/asselfya

የአሰሪዋ ስልክ ቁጥር 👇👇👇 mama jo Mobile 07 8506 9345
የአሰሪዋ ስልክ ቁጥር 👇👇👇 mama jo Mobile 07 8506 9345

🔖ትንሽ ስለትዳር --------- ትዳር ላወቀበት ምርጥ ህይ ወትህ ነው። እንዳውም በምርጥ ትዳር ላይ ያሉ ሰዎች ዘግይቼ ነው ያገባሁት በማለት ይቆጫሉ። የነብዩን (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለምን) ትዕዛዝ አክብረው በሸሪዓው መስፈርት የመረጡና አላህን የሚፈሩ ምርጥ ህይወት ውስጥ ናቸው። ይሁን እንጅ ቻሌንጅ የለም ማለት አይደለም። ቻሌንጆቹ እንደ ብልጠታችን ሊቀሉና ሊከብዱ ይችላሉ። ትዳር ትልቅ ት/ ት ቤት ነው። እንደፈለጉ መውጣት መግባት የለም። ሁሉም በሰአት ነው። ከትዳር በፊት እንደፈለጉ ማምሸት የሚቀናቸው ሰዎች ትዳር ውስጥም ይፈታተናቸዋል። አንዳንዶች እስር ቤት ነው ሲሉም ይሰማሉ። መንዘላዘል ለለመደ በርግጥም እስር  ቤት ነው። ምርጥ እስር ቤት ።# ዝርክርኮችን አንቆ የሚይዝ። እንጅማ:- ትዳር እስር ቤት ነው ማለት ~አንደኛ:- ከአማኝ ይህ ቆሻሻ ንግግር አይጠበቅም። ~ሁለተኛ:- ነብያቶች እስር ቤት ውስጥ ነበር የኖሩት ማለት ነው። ~ሶስተኛ:- መልካም ቀደምቶችም እንዲሁ እስር ቤት ውስጥ ነበሩ የኖሩት ማለት ነው። ~አራተኛ:- ይህ ሁሉ ባለትዳር እስር ቤት ውስጥ ነው ያለው ማለት ነው?  👉ለዚህ መጥፎ አስተሳሰብ ያነሳሳቸው አንድም ከመጥፎ ስነ ምግባራቸው የተነሳ አለያም በሚያጋጥማቸው መጥፎ አጋር ሊሆን ይችላል። እንጅ ያለ ትዳር መኖር በጣም ከባድ! ነው። ይህን አማኝ ሁሉ ያውቀዋል። ይህን  አስተሳሰብ የሚያስቡ ሰዎች ለሀራም የማይጨነቁ ዋልጌዎች አስተሳሰብ ስር የወደቁ ናቸው። በትዳር ውስጥ ትልቅ ደስታ አለ። አሏህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል።   وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَٰجًا لِّتَسْكُنُوٓا۟ إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَءَايَٰتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ «ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡»  አልሩም 21 👉ስለዚህ ትዳር ነፍሶቻችን የምትረካበት ፍቅርና እዝነት ያለበት ህይወት ነው። ስለዚህ ያላገባን  እናግባ ። ልጅ ያለንም "ዲኑንና ስነ ምግባሩን የምትወዱት ከመጣ ዳሩት " ብለዋልና ነብዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እና ልጆቻችን እንዳራቸው ። በጊዜ መዳር ለልጆቻችን እዝነት ነው። በተለይ ሀብታሞች ለልጃችሁ የመጣውን ባል ደሀ ነው ብላችሁ አትመልሱ። ከቻላችሁ አቋቁሙት። መቼም ብር ከልጃችን በላይ አይደለም። ሴቶችም አደራ አቅም የቻለውን ጠይቁ ከአቅም በላይ አትጠይቁ አላህን ፍሩ። አላህን ከፈራን ከማናስብበት አላህ ይሰጠናል። ትዳር ዛሬ ገብተንበት  ነገ የምንተወው እቃ እቃ ጨዋታ አይደለም!። ስለዚህ ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል። መልካም ከሆንን አሏህ መልካሟን ይሰጠናል። አትጠራጠሩ "መልካም ሴቶች ለመልካም ወንዶች ናቸው" ብሏል አሏህ። መምረጥ ያለብን ማንን እንደሆነ ማወቅ አለብን። አንዳንዶች ሚስት ፈልግልኝ የሚሉህ አይተህና ሰምተህ የማታውቃት አይነት ሴት ነው። ወንዶች ቁንጂና ላይ ያላችሁን መስፈርት አስተካክሉ። ቁንጅና ከዲንና ከጥሩ ስነ ምግባር ጋር ከተገኘ …… ነገር ግን ስታያት ደስ የምትልህ በቂ ናት። አንዳንዱ ደግሞ ምን አይነት ነው የምትፈልገው ስትለው ዲን ያላት ይልሀል። ዲን ሲልህ  በጣም ቆንጆ ማለቱ  ነው። ይህንን የምታውቀው ሲያገባ ነው። ጠንካራ ያልከው ወጣት ጅልባብ እንኳን መልበስ ያቃታትን ያገባና አስተካክላታለሁ ይልሀል። ኋላ ግን እሱ ሳይሆን እሷ ታስተካክለዋለች። ስራ እንደ ኒያ አይደል የሚገኘው ። ስለዚህ ኒያህን እስተካክል። ትዳር ውስጥ ከገባን በኋላ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በቀላሉ መፍታት ይጠበቅብሀል። ለዚህም የመጀመሪያው:- አላህን መፍራት ነው። ሁለተኛ:- ባህሪዋን ጠንቅቆ ማወቅ  በተለይ  በጣም የምትጠላውን ነገር በተቻለ መጠን መራቅ። ይህ ማለት አንዳንዴ ሴቶች ሸሪዓ የማይከለክለው ነገር ቢሆን እንኳን ሊጠሉ ይችላሉ ። የዚህን ጊዜ አንተ ሀራም አይደለ እያልክ አንጀቷን እንዳታሳርረው ተጠንቀቅ። ሶስተኛ:- ሁሌም ስህተትህን ማመን የበላይ መሆንን ብቻ አታስብ። በነገራችን ላይ ትዳር የመጀመሪያ አካባቢ ስንደዋወል እንደነበረን ስሜት አይደለም። ይሞቃል ይበርዳል። በበረደ ጊዜ ይህ መሆኑን ባውቅ ኖሮ እያልክ አታማር። አራተኛ:- ስሜቷን የሚጎዱ ነገሮችን መጠንቀቅ። ለምሳሌ ስለ ሁለተኛ ሚስት ማውራት። አንዳንዱማ ይገርማል እንዲትለማመደው እኮ ነው ይላል። ይህ ሞኝነት ነው። ምክንያቱም የሚለመድ ነገር ስላልሆነ። እንኳን ያንተ ሚስት የነብዪም ባለቤቶች አልለመዱትም። አልሰማህም እንዴ አንዷ ባለቤታቸው ምግብ ሰርታ ወደ ነብዩ ልካ ያችኛዋ ባለቤታቸው ምግብ የመጣበትን እቃ ስትሰብረው። ግዴለህም ልምከርህ መለፍለፍ ይቅርብህ። ጀግንነት አይደለም። ጀግንነት ማለት የያዝካትን በዲንም በዱንያም በመንከባከብ ማስደሰትና (አቅምህ ከፈቀደም ስሜቷን  ሳትጎዳት ሸሪዐው በፈቀደው መልክ የሷንም ሀቅ ጠብቀህ ሌላ ደርበህ ማግባት) ነው። ግን ስንቶቻችን ነን ለሁለተኛ ሚስት ተቅዋችን ስነ ምግባራችንና አቅማችን የሚፈቅደው። ብዙ ወንዶችኮ ገና ሁለተኛ እንዳገቡ የመጀመሪያዋን እንደ ሙዝ ልጣጭ አሽቀንጥረው ነው የሚጥሏት። ምክንያቱም ተቅዋ የለማ ይህ የሚያደርግ የቂያማ ቀን ጎኑ ተንሻፎ ይቀሰቀሳል።  ስለዚህ ስናገባም አሏህ እንፍራ በትዳርም ውስጥ ሆነን አሏህን እንፍራ ። አላህን የሚፈራ መውጫ ያደርግለታልና።   منقول t.me/https_Asselfya