fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

رفتن به کانال در Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

کانال Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 15 948 مشترک است و جایگاه 5 316 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 234 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 15 948 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 21 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 408 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 1 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 25.79% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 10.92% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 113 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 742 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 29 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 22 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

15 948
مشترکین
+124 ساعت
+1627 روز
+40830 روز
آرشیو پست ها
መኳንንት፣ መሳፍንትና ነገሥታት የሰጡትን የገዳሙን ርስት ጉልት ማንም እንዳይነካ፤ **ሴቶች ወደ ገዳሙ እንዳይገቡ (የአባቶች መነኰሳትና የባሕታውያን ብቻ መኖሪያ እንዲኾንና እኅቶች እንዳይቀላቀሉ በማሰብ) **መነኰስ ያልኾነ ማንም በሐይቅ ገዳም ቤትን እንዳይሠራ፡፡ ፠ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በሃገራችን አንጋፋና ቀደምት በኾነው ደብረ ዳሞ መካነ አእምሮ (University) የተማሩ እንደመኾናቸው፤ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሲመለሱም በሃገራችን በትምህርት መካነ አእምሮነቱ ዋናና ግንባር ቀደምቱን፤ በርካታ ሊቃውንትን ቅዱሳንን ያፈለቀውን የሐይቅ እስጢፋኖስ መካነ አእምሮ መሠረቱ፤ በዚህም የኢትዮጵያን ወርቃማ ዘመን መሥራች ነው፤ ልጆቻቸውም ይህን ወርቃማ ዘመን አስቀጥለውታል፡፡ በቆብ የወለዷቸው ቅዱሳን ሊቃውንት ብዙ ቢኾኑም ለአብነት ያህል ዐበይቶቹ፤ ✤ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ዘደብረ ጎል (ምድረ ዐማራን፣ ሸዋንና ደቡብን፤ ምድረ ትግራይን ያስተማሩ፤ የአቡነ ተክለሃይማኖት የመጀመሪያ መምህር የኾኑ) ✤ አቡነ ተክለሃይማኖት (ሐዲስ ሐዋርያ ተብሎ የተሰየመ፤ በሐይቅ ከመመንኰሳቸው በፊት 7 ዓመታት፣ ከመነኰሱ በኋላ 3 ዓመታት ተቀምጠዋል) ✤ አባ ሕዝቅያስ (ከምድረ ወግዳ ይዞ እስከ ጎጃም ያስተማሩ) ✤ አባ ገብረ እንድርያስ ዘደብረ ቆዘት (በጸበላቸው የእንጨት ቅርፊትን እንደ ደንጊያ መቁጠሪያ የሚያደርጉ፣ በድንጋይ ሠረገላ የሚጓጓዙ) ✤ እጨጌ አባ አሮን ዘደብረ ዳሪት (ከምድረ ዋድላ አንስቶ እስከ ዳውንት፤ ከበጌምድር እስከ ደምቢያ የሰበከ) ✤ አባ ገብረ ናዝራዊ ዘበለሳ (ምድረ ትግሬን ያስተማረ) ✤ አባ ኂሩተ አምላክ ዘዳጋ (እንደ መምህሩ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በእስጢፋኖስ ስም በጣና ላይ የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳምን የመሠረተ፤ ምድረ ሳርክን ይዞ እስከ ጋዝጌ፤ መላዋን የአላፋና ጣቁሳ እና የአገው ምድርን ያስተማረ) ✤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ዘደብረ ባሕርይ) (የኢትዮጵያ መብራት)፤ አብዛኛዋን የኢትዮጵያ ምድር ያስተማረና ቤተ ክርስቲያንን ከ40 በላይ በሚደርሱ ድርሳናቱ ያስጌጠ፡፡ ✤ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ፡፡ ✤✤ እንዲሁም ንጉሡ ይኵኖ አምላክ (ከንግሥናው በፊት በልጅነቱ ያደገውና የተማረው ከጻድቁ ዘንድ ነው፡፡) ፠ ጻድቁ በአጠቃላይ 44 ዓመታትን ማለትም፤ * 20 ዓመት በይትባረክ ዘመነ መንግሥት * 15 ዓመት በይኵኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት * 9 ዓመት በአግብዓ ጽዮን ዘመነ መንግሥት የኖሩ ሲኾን፤ ለ44 ዓመታት በገዳም ቆይታቸው ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም፥ ለሰውነታቸውም(ለጎናቸውም) ምኝታን አላስለመዱትም፡፡ ‹‹እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ፤ መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ፡፡›› እንዲል፡፡ ጻድቁ በሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩም የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር፡፡ ** የማረፊያው እለት በደረሰ ጊዜ ደቀመዛሙርቱና ሰዎች ተሰባሰቡ፤ በደብረ ነጐድጓድ ያደገውን ተክለ ኢየሱስን መምህር አድርጎ ሾመላቸው እነርሱንም ባርኳቸው፤ ኅዳር 26 በ1286ዓ.ም. በእለተ እሑድ ጧት ፀሐይ ስትወጣ ዐረፈ፤ ደቀ መዛሙርቱም እንደሚገባ አድርገው በፍየል ሌጦ አድርገው ገንዘው በክብር ቀበሩት፡፡ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

#ኅዳር_26_ #አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ፤ #_ከደብረ_ዳሞ_ቀጥሎ_በሃገራችን_ሁለተኛውን_መካነ_አእምሮ(#University)#የመሠረተ፤ #_በሃገራችን_ወርቃማ_ዘመን_ተብሎ_የሚታወቀውን_ዘመን_ፋና_ወግቶ_የጀመረ_ #_መጻሕፍትን በእጁ በመጻፍ ለትውልድ የታሪክ አሻራን ያሳረፈ #_የሐይቅ_እስጢፋኖስ_ገዳምን_ዳግመኛ_ያቀናና_ያስፋፋ፥ #በደብረ ዳሞ አስኬማ ዘመላእክትን የተማረ #እንደ እስጢፋኖስ ጸጋን ጽድቅንና ሞገስን የተመላ፥ በሥራው ፍጹም የኾነ፥ #የመጀመሪያውን_የዐቃቤ_ሰዐት_ማዕርግ_ያገኘ፡፡ #_ለቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል ፥ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ ፥ #አቡነ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫና_ #ለሌሎችም_በርከካታ_ቅዱሳን_ወላዴ_አእላፍ_ቅዱሳን_የኾነ፡፡ * በበጌምድር ዳኅና(አሁን ስማዳ) ገብርኤል በተባለ ቦታ ከአባታቸው ዘክርስቶስና ከእናታቸው እግዚእ ክብራ ነሐሴ 26 ሰኞ ተጸንሰው፤ ግንቦት 26/1205 ዓ.ም. ረቡዕ በቅዱስ ነአኵቶ ለአብ ዘመነ መንግሥት ተወለዱ፡፡ ወንድሞቻቸው ገብረ ጽዮንና ስቡሕ አምላክ ይባላሉ፡፡ *እስከ 30 ዓመታቸው ድረስ በእናት አባታቸው ቤት እያገለገሉና ትምህርት እየቀሰሙ ቆዩ፤ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጾላቸው ወደ 5ኛው የደብረ ዳሞ አበምኔት ዳግማዊ አቡነ ዮሐኒ ዘንድ እንዲሄዱ በራዕይ ነገራቸው፤ በመንገድም ሲሄዱም የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን አግኝተው ይምጻአ ምሕረት የሚባል ዲያቆንን አስከትለው ወደ ደብረ ዳሞ እንዲሄዱ መልአኩ ባዘዛቸው መሠረት ወደ ገዳሙ አቀኑ፡፡ *በደብረ ዳሞ ቆይታቸውም እህልን በመፍጨትና ለገዳሙ ንግድን (ሩቅ መንገድንና አስጨናቂ ኹኔታዎችን በማለፍ ) ይነግዱ ነበር፡፡ እንዲሁም ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጻፍ (በመገልበጥም) ትጉህ ጸሓፊ ናቸው፤ ይህ ይታወቅ ዘንድ በቅርብ የደብረ ዳሞ ዕቃ ቤት እስከተቃጠለበት ድረስ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በእጃቸው የጻፉት ወንጌል ይገኝ ነበር፡፡ *37ዓመት ሲኾናቸው ከአባ ዮሐኒ ሥርዐተ አስኬማ ዘመላእክትን ከተቀበሉ በኋላ መልአኩ ወደ ሐይቅ እንዲሄዱ በገለጻላቸው መሠረት በ1237 ዓ.ም. ወደ ሐይቅ በመምጣት በሐይቁ ዳር በሚገኘው ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤ.ክ. ለ6ወራት አገለገሉ፤ በዚሁ ደብር የሚገኘው ‹‹#ሔር_አምላክ_›› የተባለ ካህንም የጻድቁን ታሪካቸውን ጠይቆ ከተረዳ በኋላ ወደ ደሴቱ አስገባቸው፤ የአካባቢው ሕዝብም አገልግሎታቸውንና መንፈሳዊ ተጋድሏቸውን አይተው ንጉሡ ይትባረክ ዘንድ በመሄድ የገዳሙ አበምኔት እንዲያደርገው ጠየቁት እርሱም ሾመው፡፡ ጻድቁም ይህን ገዳም በዮዲት ጉዲት ከጠፋ ከ300 ዓመታት በኋላ ዳግም አቅንቶታል፡፡ *እርሳቸውም ደሴቲቷም ስለወደዷት ከገዳሟ ላለመውጣት፤ የባሕሩን ወደብም ላለመርገጥ ብፅዓት ገብተው 20 ዓመታት ያህል እንደኖሩ፤ አፄ ይኵኖ አምላክ እንደነገሠ ጻድቁ ወደ ንጉሡ እንዲመጡ ላከበቸው፤ እርሳቸው ግን ከሐየቁ እንደማይወጡ ብፅዓት እንዳለባቸው፤ ንጉሡ ወደ እርሳቸው እንዲመጣ ላኩበት፤ ንጉሡም በበቅሎ እስከ ጉልበቱ ድረስ ወደ ባሕሩ ገብቶ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ኂሩተ አምላክና ኀረየነ ክርስቶስ ከሚባሉ ደቀመዛሙርቶቹ ጋር በታንኳ (በጀልባ) መጥተው ተጨዋወቱ፤ ንጉሡም ምን ላደርግልህ ትወዳለህ ሲላቸው፤ * ገዳሟ የወንዶች ገዳም እንድትኾን ነው አሉት፤ ንጉሡም በቦታው ያሉትን ሴቶች ይህ ቦታ የወንዶች ገዳም ብቻ እንዲኾን ስለወሰንኩ የፈቀዳችሁ ከእኔ ጋር በከተማዬ መኖር አሊያ በፈቀዳችሁትና በመረጣችሁት ቦታ መኖር ትችላላችሁ የምትፈልጉትንም ኹሉ እሰጣችኋለሁ በማለት ሥርዐት አበጁለት፡፡ ደሴቲቱን ለቀው እየሄዱ ካሉት ሴቶች መካከልም አንዲቷ ምጧ ደርሶ ነበረና በደሴቱ ጫፍ ወለደች ቦታውም ‹‹#ምጥ_ገበታ_›› ተባለ፡፡ ዛሬ ክብረ በዓል የሚከበረው በዚሁ ምጥ ገበታ በተባለው ቦታ ነው፡፡ (ከምጥ ገበታ በስተምዕራብ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ፤ በስተሰሜን ምዕራብ መካነ አእምሮ (University)፤ በስተሰሜን የሴቶች ገዳም ይገኛል) * በንግግራቸው ሳሉም እባብና አለቅት በንጉሡን በቅሎ እግር ላይ ተጠመጠሙ፤ ጻድቁም መርዛማነት ያላቸው እንስሳት በዚህ ገዳም ሰውን እንዳይጎዱ አወገዟቸው፤ የደወልም ድምፅ ተሰማ ንጉሡም አሁን ስንት ሰዐት ነው የደወል ድምፁስ ምንድን ነው ብሎ ጻድቁን ጠየቀ፤ ጻድቁም ፱ኝ ሰዐት በመኾኑ ደወሉ ከገዳሙ የተደወለ መኾኑን ነገሩት ንጉሡም ለጻድቁ #የዐቃቤ_ሰዐት_ ማዕርግን ሰጣቸው (በአሁኔ ሰዐት ዐቃቤ ሰዐት የጠቅላይ ሚንስትሩ ዋና አማካሪ ከሚለው ጋር የተካከለ ነው)፡፡ (ምንም እንኳን እርሳቸው በሹመቱ ለመጠቀም ባይፈልጉም)፤ ከተከታያቸው ከአባ ዘኢየሱስ አንስቶ እስከ 16ኛው መጀመሪያ አጋማሽ ድረስ በሐይቅ መምህራን እጅ ቆይቷል፤ ኋላ የንጉሦች መናገሻ ከሸዋ ወደ ጎንደር ሲዛወር በቦታ ርቀት ምክንያት ይህ ሹመት በገጽ የሚሰጥ ሹመት ሁኗል፡፡) ✤ንጉሡ ይኵኖ አምላክ ለገዳሟ የሚከተለውን ሥርዐት ሠርተው መደ መናገሻቸው፤ ጻድቁም ወደ ደሴታቸው ተመለሱ፤

#የአቡነ ሀብተ ማርያም ክብረ በዓል የሚከበርባቸው ቦታዎች፤ ** ብሔረ ብፁዓን ደብረ ይሰበይ አቡነ ሀብተማርያም፤ ደብረ ሊባኖስ አጠገብ፡፡ ቡልጋ አቡነ ሀብተ ማርያም፡፡ አዲስ አበባ ቃሌ ተራራ አቡነ
+2
#የአቡነ ሀብተ ማርያም ክብረ በዓል የሚከበርባቸው ቦታዎች፤ ** ብሔረ ብፁዓን ደብረ ይሰበይ አቡነ ሀብተማርያም፤ ደብረ ሊባኖስ አጠገብ፡፡ ቡልጋ አቡነ ሀብተ ማርያም፡፡ አዲስ አበባ ቃሌ ተራራ አቡነ ሀብተ ማርያም፤ አስኮ (ከዊንጌት አጠገብ) https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

#ኅዳር_26_ #_ኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_ሀብተማርያም፡፡ #Share ያድርጉ ፠ አቡነ_ሀብተማርያም በሽዋ (የራውዕይ /ቡልጋ/) ከአባታቸው ፍሬ ቡሩክ ከእናታቸው ቅድስት ዮስቴና ነው የተወለዱት፡፡ ፠ ወላጆቹ በተለይም እናቱ ከማግባቷ በፊት መናኝ ነበረች፡፡ ጻድቁን እንደምትወልድ በበቃ ባሕታዊ ተነግሯት ጻድቁን ወልዳ በጽድቅ ኑሮ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ በክብር አርፋለች፡፡ ፠ ጻድቁ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› ሲባል ይሰማሉ፤ ይህንንም በሕፃን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ ‹‹ማረን እባክህን›› እያሉ ይሰግዱ ነበር፡፡ ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ፡፡ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል፤ የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል፡፡ ፠ ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው ትምህርትን ከቀሰሙ በኋላ መንነዋል፤ በታላቁ አባት በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኰሱ በኋላም ብዙ ትርፋትንና ተጋድሎን ሠሩ፡፡ ለአብነትም፤ *ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ፤ *በየቀኑ 4ቱን ወንጌልንና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ፤ *በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ፤ *ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ነው፤ *በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ፤ *ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ፥ ክቡር ደሙን ይጠጣሉ፤ *በልባቸው ውስጥ በፍጹም ቂምን፥ መከፋትን አላሳደሩም፡፡ * ረአዬ ኅቡዓት በመባል ይታወቃሉ፡፡ * በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ቦታውን ሲባርኩት ሦስት አጋንንት በጸሎቱ ሥልጣን የታሠሩለት ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡ * ‹‹#ጽድቅና_ትሩፋት_እንደ_ሀብተ_ማርያም፠›› ፠ ጌታችን ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይሔዱ ነበር፡፡ ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በኋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ እንዲህ አላቸው፤ * ‹‹ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ፤ ስለ ምናኔህ፣ ስለ ተባረከ ምንኵስናህ፣ ስለ ንጹሕ ድንግልናህ፣ ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ፣ ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ፣ ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ፡፡›› * በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን፤ 500 የዕንቊ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ፡፡ በስምህ የሚለምኑ፤ በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ ‹አማንየ በርእስየ› ብዬሃለሁ›› አላቸው፡፡ * ቅዱሳን መላእክትም ‹‹ሀብተ ማርያም ወንድማችን›› ሲሉ አቀፏቸው፡፡ ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው፡፡ ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች፡፡ በዝማሬም ወሰዷት፡፡ ✤ ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ሥልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነርሱም፤ 1ኛ. #_መብረቅ፣ 2ኛ. #_ቸነፈር፣ 3ኛ. #_ረሃብ፣ 4ኛ. #_ወረርሽኝ፣ 5ኛ. #_የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡ ፠ በተሰጣቸው ቃል ኪዳንም ከላይ ያሉትን 5ት መቅሰፍቶች የሚያርቁ በመሆናቸው፤ ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን በደብረ ሊባኖስ ገዳም እነዚህ 5ቱ መቅሰፍቶች እንዳይቀርቡ የሀብተማርያም ካህናት ከኅዳር 1-7(10) ማዕጠንት ያጥናሉ፤ ደብረ ሊባኖስ ገዳምም ለደብረ ይሰበይ አቡነ ሀብተማርያም ገዳም 1ድ በሬ ስጦታን ያበረክታሉ፡፡ ፠ በዛሬው ዕለት በኅዳር 26 ባረፈ ጊዜ፤ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው፤ በዝማሬ ፥ በማኅሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በጻድቁ መቃብር ቀበሩት፡፡ (ከወርቅ ንፁህ ፥ ከብርም የጠራ ፥ ከሁሉ የሚበልጥ ፥ የተመረጠ ፥ ሀብተማርያም መልአክ ዘበምድር ነው መልካሙ ዜናው እስከ አጽናፍ ተሰማ፡፡) #_በዛሬዋ ዕለት #በናግራን ያሉ ክርስቲያኖች በ6ኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕታት የኾኑበት ዕለትም ነው፡፡ #Share ያድርጉ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

#በሃገራችን_ከሚገኙ_የቅዱስ_መርቆሬዎስ_ክብረ_በዓል_ከሚከብርባቸው_ዋነኞቹ_፡፡ ✥1. ደብረ ጽባሕ ጸዶየ መርቆሬዎስ፤ በአጼ ይኵኖ አምላክ ዘመን የተመሠረተ፡፡ ✥2.ደረስጌ ደብረ ጽዮን ማርያም፤ ‹‹ደ
+6
#በሃገራችን_ከሚገኙ_የቅዱስ_መርቆሬዎስ_ክብረ_በዓል_ከሚከብርባቸው_ዋነኞቹ_፡፡ ✥1. ደብረ ጽባሕ ጸዶየ መርቆሬዎስ፤ በአጼ ይኵኖ አምላክ ዘመን የተመሠረተ፡፡ ✥2.ደረስጌ ደብረ ጽዮን ማርያም፤ ‹‹ደጃች ውቤ ደረስጌ ደብረ ጽዮንን በወርቅና በዕንቊ ከመሥራታቸውም በላይ ታቦተ መርቆሬዎስን ማምጣታቸው ተብሎ የሚነገርለት›› ተዓምር አድራጊ ስዕል የሚገኝበት ቤ.ክ (ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የነገሠበት)፤ ራስ ደጀን አጠገብ፤ ጃናሞራ (መካነ ሰላም ከተማ) ✥3. ጎንደር ደብረ ፀሐይ ቊስቋም ማርያም፤ የቅዱስ መርቆሬዎስ ታቦት ከጥንት ጀምሮ በድርብነት አለ ✥4. ጋሹ አምባ አርማንያ ቅዱስ መርቆሬዎስ (ሰሜን ሸዋ፤ ደብረ ሲና)፤ ስዕሉ በበዓለ መርቆሬዎስ ቀን የሚያሸበሽበው፡፡ ✥5. ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኡል (አ.አ)፤ የቅዱስ መርቆሬዎስ ታቦት ከጥንት ጀምሮ በድርብነት አለ ✥6. ደብረ ሲና ቅ.እግዚአብሔር አብ(አ.አ)፤ የቅዱስ መርቆሬዎስ ታቦት ከጥንት ጀምሮ በድርብነት አለ ✥7. አዲስ አበባ ጎፋ ደብረ መዊዕ ቅዱስ መርቆሬዎስ ወዮሐንስ መጥምቅ ቤ.ክ (በአዲስ አበባ በመርቆሬዎስ ስም የጠሰየመ ብቸኛው ቤ.ክ.) https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

#ኅዳር _25_በዓለ_ዕረፍቱ_ለሰማዕት_ቅዱስ_መርቆሬዎስ(#ፒሉፓዴር)፤ #Share ያድርጉ *አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት፡፡ አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡ ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡ *የወላጆቹ (አባቱን ኖህ እናቱን ታቦት) አገር አስሊጥ የምትባል ስትኾን እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ፒሉፓዴር ነው፡፡ * ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሯቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሯቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡ መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብረውት ነበሩ፡፡ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሯቸውን እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡ **በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በጦሩ መሀል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ›› አለው፡፡ መልአኩም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና ‹‹ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው›› አለው፡፡ ጦርነቱን ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት ‹‹ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት እረሳህ?›› አለው፡፡ ከጦርነቱም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በዚያ ስላልተገኘ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረጉ እንዳልተባበረ ንጉሡ ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስመጣው፡፡ ንጉሡም ‹‹ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?›› ባለው ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ ‹‹ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፣ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም›› አለው፡፡ ንጉሡም ተናዶ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡ ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የአገሩ ሰዎች እንዳይነሱበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጰዶቅያና የእስያ ክፍል ወደሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡ እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡ ✤ከብዙ ተአምራቱም አንዱ የቂሳርያውን ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስን እንዲሁም ጎርጎርዮስን ረድቶ ከሃዲውን ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡ ዑልያኖስ ነግሦ የክብር ባለቤት ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሠቃየት ጀመረ፡፡ የቂሳርያው ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም አስተምሮ ሊመልሰው ወደ ንጉሡ ቢመጣ ክብር ይግባውና ዑልያኖስ ጌታችንን ሰድቦ ባስልዮስንም አሰረው፡፡ ባስልዮስም በእሥር ቤት ሳለ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ጸለየ፡፡ ሥዕሉም ወዲያው ተሰወረው፡፡ ያንጊዜም ወደ ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘንድ ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለውና ወዲያው ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ በስዕሉ ላይ ያለው የቅዱስ መርቆሬዎስ ይዞ ከተሳለው ጦር ጫፍ ላይም ደም ይንጠፋጠፍ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ከሃዲውን ንጉሥ እንደገደለው ዐውቆ ‹‹የክርስቶስ ምስክር ጌታዬ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?›› አለው፡፡ ሥዕሉም ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አደረገ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡ ✤ሌላው ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በተአምሩ ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ እስላም ሰው አለ፡፡ ይኸውም የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራችበት በምስር አገር የሚኖር ከመሳፍንት ወገን የሆነ ወጣት ነበረ፡፡ ከብዙ ሰዎችም ጋር ሆኖ ወደ መሐመድ መቃብር ለመሄድ እንዳሰበ ለአባቱ ሲነግረው ስንቅ ሰንቀው በሰላም ወደ መካ መዲና ሸኙት፡፡ መካ ደርሰውም ሥራቸውም ፈጽመው ወደቤታቸው እየተመለሱ ሰባት ቀን ተጓዙ፡፡ በሌሊትም ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጁ ያ እስላም ወጣት ከግመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ፡፡ እነርሱም አብሯቸው የሚጓዝ መስሏቸው ስለነበር ባልንጀሮቹም በበረሃው ውስጥ ትተውት ሄዱ፡፡ እርሱም ወዴት እንደሚሄድ ስላላወቀ አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ እጅግ ደነገጠ፡፡ በዚያም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ ቅዱስ መርቆሬዎስን እንዲያድነው በመለመን ተሳለ፡፡ ወዲያውም ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈረሱ ተቀምጦ ወደ እርሱ መጣና ‹‹ከወዴት ነህ? ከዚህ በረሃ ውስጥስ እንዴት ጠፋህ?›› አለው፡፡ ወጣቱ እስላምም የሆነውን ነገረው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም ‹‹ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ›› አለውና በአየር ላይ እየበረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች በውስጧ አስገባውና ከእርሱ ተሰወረ፡፡ ይህም ወጣት በኋላ አምኖ ተጠምቆ ብዙ ሰማዕትነት ተቀብሏል፡፡ ገዳምም ገብቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ እንደገና ወደ አገሩ ተመልሶ ብዙዎችን ወደ ክርስትና አምጥቷል፡፡ በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ አበ ምኔትም ሆኖ ብዙ መነኰሳትን አፍርቷል፡፡ /ምንጭ፤ ከገድላት አንደበት/ #Share ያድርጉ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

ኅዳር 24 እንኳን ለ #የ24ቱ_ካህናተ_ሰማይ_በዓል እና በቆብ አያትና የልጅ ልጅ የኾኑት #አቡነ_ተክለሃይማኖትና_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_ከካህናተ ሰማይ ጋር #የሥላሴን መንበር ላጠኑበት ዕለት በሰላም አደረሳቹህ ፡፡ #Share ያድርጉ ※እግዚአብሔር ከሠራዊተ #ሩፋኤል (ሊቃናት) #ሃያአራት ሊቃናት መርጦ በምንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙርያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል፡፡ ሕዝ 1 ፥11-12 ※ስማቸውን #ካህናተ_ሰማይ አላቸው የእሳትና የወርቅ ጽና አስያዛቸው ፤ የብርሃን አክለሊል ጳዝዮን ከሚባል የብርሃን ዘውድ ደፋላቸው የብርሃን ዘንግ ማኀተሙ መስቀል የሆነ አስያዛቸው ፤ የብርሃን ላንቃ ኀብሩ መብረቅ የመሰለ አለበሳቸው ፡፡ ‹‹በዙፋኑ ዙርያ ሀያአራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሀያ አራት ሽማግሌዋች ተቀምጠው ነበር›› ዮሐ ራዕ 4፥-5 ※እነዚህም በአንድ ላይ በአጠኑ ጊዜ ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ #መብረቅ ፤ ድምጹ ነጎድጓድ ፣ መዓዛው መልካም የሆነ ነው ፡፡ ‹‹ ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምርው ብዙ ዕጣን ተሰጠው ፤ የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ወጣ››ዮሐ ራዕ 8 ፥3-5 ※የሚያጥኑት ምንድን ነው ቢሉ የጻድቃን ጸሎት ፤ የሰማዕታት ገድል ፣ የደጋግ ሰዎች ምግባር ነው ፡፡ በእናንተ እየጣጠነ ወደ እኔ ያርግ ( ይድርስ ) ብሏቸዋልና ፡፡ ያለ እነርሱም አቅራቢነት ጽድቅና ምጽዋት ወደ እግዚአብሔር አይቀርብም፡፡ ※ኣቋቋማቸውም እንዲህ ነው ፤ ኪሩቤል በቀኝ እንደ ቀሳውስት ሱራፌል በግራ እንደ ዲያቆናት ከፍ ብለው ፤ካህናተ ሰማይ ዝቅ ብለው ክንፍ ለክንፍ ገጥመው ቁመው ይኖራሉ ፡፡ እንዲሁም ሌሎችም ቅዱሳን መንበረ ሥላሴን ያጠኑ አሉ፡፡ ለምሳሌም፤ በቆብ አያትና የልጅ ልጅ የኾኑት #አቡነ_ተክለሃይማኖትና_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር አጥነዋል ፨ አቡነ ዮሴፍ ዘጂፋት፣ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንዲሁ አጥነዋል ፡፡ #Share ያድርጉ ፨ካህናተ ሰማይ የዐውዶ ሡራሄ፤ ሎቱ ለባህቲቱ ይደሉ ስባሔ፨ /ሰዐታት/ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ፡፡ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem ምልጃቸው አይለየን በረከታቸው ይደርብን አሜን!

፨፨፨ #በጽዮን_ስም_የተመሠረቱና_ዐቢይ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓላቸው_ኅዳር_21_የኾኑ፤ ✣ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም (ከክርስቶስ ልደት 980 ዓመታት በፊት በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን ታቦቷ የመጣው) ✣ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አዲስ ዓለም ደብረ ጽዮን ማርያም (በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ተመሠረተች) ✣ዝዋይ ደብረ ጽዮን ማርያም (ደቡብ ሸዋ) ✣ሳዶቅ አምባ ማርያም (በ1670 ዓ.ም. በአባ ሳዶቅ የተመሠረተች ፥ ሰሜን ተራሮች) ✣እንፍራንዝ ደብረ ጽዮን ማርያም (ጥንታዊዋ ደብር) ✣ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደረስጌ ደብረ ጽዮን ማርያም (በወርቅና በዕንቊ ተደርጋ በራስ ውቤ የታነጸች፤ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የነገሠባት፤ ስሜን፣ ራስ ደጀን አጠገብ) ✣ ደብረ ጽዮን ማርያም (ነቀምት) ✣ ደብረ ጽዮን ሰላም አድርጊው ቅድስት ማርያም (ባሕርዳር) ✣ አርባ ምንጭ ደብረ ጽዮን ማርያም ✣ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ማርያም (እንግሊዝ ፥ ለንደን) የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem