fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

رفتن به کانال در Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

کانال Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 16 045 مشترک است و جایگاه 5 280 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 240 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 16 045 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 29 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 518 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 1 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 25.50% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 10.35% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 090 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 660 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 33 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 30 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

16 045
مشترکین
+124 ساعت
+917 روز
+51830 روز
آرشیو پست ها
‹‹#ያለ_ሥርዐት_የሚሄዱትን_ገስጿቸው_፡፡›› 1ተሰ. 5፥14 የጳጳሱ፣ የመምህር ዘበነና የሌሎች ካህናትና ዲያቆናት፣ እንዲሁም የቤ.ክ. ቦርድ አባለት የተባሉት በግንቦት 14 በሚካሄደው በቅዱስ ሲኖዶስ አጀንዳ እንዲያዝ ቃላችንን እናሰማ፥ ቃላችሁን አሰሙ!!!!! መምህር ዘበነ በሚያስተዳድረው በሃገረ አሜሪካ ባለች ቤተ ክርስቲያናችን ላይ በቤተ መቅደሱ ሰውነትን በሚያሳይ፣ ሴቶቹ ሳይሸፋፈኑ፣ ባለሠርገኞቹ ሥርዐተ ቤ.ክ. ያልኾነ ልብስ ለብሰው፣ ሙሽሮቹ ከንፈር ለከፈንር እየተሳሳሙ ጋብቻ ተደረገ (ተባለ!!!) ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጳጳስ በተገኙበት ከሥርዐተ ቤተክርስቲያን ውጪ በሆነ መንገድ የሠርግ ሥነ ሥርዓት እየተደረገ ነው (ተባለ!!!) ለቀጣፊ ይገባል ጥፊ! ነው ያሉት አበው፡፡ የአባቶቻችን አምላክ መድኀኔ ዓለም ይህንን ድርጊት በተለይም እያወቁ ያደረጉና ያስደረጉትን መገሰጽን ይገስጽልን፡፡ ወይ ቤተ ክርስቲያናችንን መልሱ፤ ወይም በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ተመላለሱ!!!፡፡

#እንኳን_ለ657ኛ_የአቡነ_ተክለሃይማኖት_ፍልሰተ_አጽም_ክብረ_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ፨ *አባታችን ባረፉ በ54ኛ ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም በአፄ ሰይፈ አርዕድ ዘመን ለ4ኛው እጨጌ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡ ‹‹አባቴ ተክለ ሃይማኖት የሚለኝ ሁሉ፤ በፍልሰቴ ቀን በገዳሜ ይገኝ እኔም ልጄ እለዋለው ከቅዱስ ሚካኤልና ከልጄ ፊልጶስ ጋር እባርከዋለው።›› /ገድለ ተክለ ሃይማኖት/ ግንቦት 12 በደብረ ሊባኖስ ትልቁ በዓል ነው፡፡ ጥንተ መሠረቱም፤ 12ቱ እጨጌዎች ከያሉበት ቦታ እየመጡ 1ድ 1ድ ወር ሙሉ በፈረቃ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ቅዱስ አጽም ተራ ገብተው ያጥኑ ነበር፡፡ ግንቦት 12 ግን ሁሉም ከያሉበት ተሰባስበው በአንድነት ያከብራሉ፡፡ #የጻድቁ_ዋና_ዋና_የታሪክ_ሂደቶች፤ ፠ከአባታቸው ከቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከቅድስት እግዚዕ ኀረያ፤ መጋቢት 24 ቀን ተጸንሰው፤ በታኅሣሥ 24 ቀን በ1190 ዓ.ም. በእቲሣ ተወለዱ፡፡ ፠በተወለዱ በ3ኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመሠገኑ፡፡ ፠በተወለዱ በ40ኛው በደብረ አጋዓዚት ማርያም ፍስሐ ጽዮን “የጽዮን ደስታ” ተበለው ተጠሩ፡፡ ፠እስከ 7 ዓመታቸው ድረስ ከአባታቸው ከጸጋዘአብ ዘንድ እየተማሩ ፠በ15 ዓመታቸው ዲቁናን ከጌርሎስ ዘንድ ተቀበሉ፡፡ ፠በ22 ዓመታቸው ከአቡነ ጌርሎስ ዘንድ ቅስናን ተቀበሉ፡፡ ፠በከተታ አውራጃ 3 ዓመት ወንጌልን እያስተማሩ ብዙ ድንቅ ነገርን አደረጉ፡፡ ፠በኅዳር 24 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ወደ ላይ ነጠቃቸው ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር 25ኛ ካህን ሆነው የሥላሴን መንበርን አጠኑ ፠በሐይቅ እስጢፋኖስ 10 ዓመት፥ በደብረዳሞ 12 ዓመት ኖረዋል፡፡ ፠በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች እየተዘዋወቱ አስተምረዋል፤ በአኵሱም ጽዮን፣ በዋልድባና በዙሪያቸው ባሉ ገዳማት እየዞሩ ተሳልመዋል፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም በመውረድም ተሳልመው ተመልሰዋል፤ ሲመለሱም ብዙ ቅዱሳን አብረዋቸው ተመልሰዋል፡፡ /እነ እጨ ዮሐንስ ዘጎንድ (ዘጠገሮን) ልብ ይሏል፡፡ ፠በ1267 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስን በአት አድርገው ኖሩ፡፡ ለ22 ዓመት ቆመው በመጸለይ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡ በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመት በጸሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በጸሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን 1290 ዓ.ም አረፉ፡፡ ፠፠፠አባታችን ባረፉ በ54ኛ ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም በአፄ ሰይፈ አርዕድ ዘመን ለ4ኛው እጨጌ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡ ፠የደብረ ሊባኖስንም ቦታ የሰጠው ሐኖ (ተክለ ሃይማኖት) /የግራርያ ሰው/፤ ሲሆን ዓፄ ልብነ ድንግል በነገሠ በ8ኛው ዓመት ‹መርሕ› ከምትባል ስፋራ ታቦቱ ከነዋየ ቅድሳቱ ጋር ‹ከምድኃሬ› ተዛውሯል፡፡ ይህንንም ያደረገው እጨጌው አባ ጴጥሮስ ነበር፡፡ #***ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ፨ እስመ በውስቴታ ተገብረ ፍልሰተ ሥጋሁ ወአፅሙ፤ እምነ አድባራት ኩሎን ዘተለዓለት በስሙ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ እንተ ቀደሳ በደሙ፤ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ፨ #ክብረ_በዓላቶቻቸው፤ #ኅዳር 24፤ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑበት #ታኅሣሥ 24፤ የአባታችን ልደት #ጥር 24፤ የአባታችን ስባረ አጽም #መጋቢት 24፤ የአባታችን ጽንሠት #ግንቦት 12፤ የአባታችን ፍልሰተ አጽም #ነሐሴ 24፤ የአባታችን በዓለ እረፍት ናቸው፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

በቅዱስ ያሬድ ወንበር ተተክተው እያስተማሩ ያሉ ሦስት ዐበይት የምስክር ጕኤ መምህራን፡፡ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ የቅዱስ ያሬድን ዜማውን ከነይትበሃሉ የሚያስተምሩ ዐበይት መምህራን እነዚህ ናቸው፡፡ አምላከ ቅዱስ ያሬድ በረድኤት፥ በበረከት፥ በጤና፥ በመግቦት ይጠብቅልን፡፡

#፭#የቅዱስ_ያሬድ_ድርሰቶች፤#የዜማው_ይዘት_የዜማው_ጠባያት_ከሌሎች_ዓለማዊ_ዜማዎች_የሚለይበት_ጠባይና_የዜማው_ጥቅም #ሀ_የቅዱስ_ያሬድ_የዜማው_ይዘት ፠ቅዱስ ያሬድ ዜማውን ያዘጋጀው ከብሉያት፣ ከሐዲሳት፣ ከሊቃውንት መጻሕፍት እየመረጠ ለምስጋናና ለጸሎት እንዲኾኑ አድርጎ ነው፡፡ ፠ዜማው ምስጢሩ የማይጠገብ፥ቃሉ የሚያረካ፥ አነጋገሩ የተሳካ፥ ጣዕመ ቃሉና ኀይለ ቃሉ ደስ የሚያሰኝ፥ ልብን የሚነካ ነው፡፡ ፠በይዘቱም የሥነ ፍጥረት ውበትን በማድነቅና የሥነ ፍጥረት አስገኝ የኾነውን እግዚአብሔርን በማመስገን ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ፠በአጠቃላይ የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ጌታ ለሰው ልጆች ሲል በዚህ ዓለም የፈጸመውን የማዳን ሥራ ሁሉ ገልጦ የሚያስረዳ ነው፤ የቅድስት ድንግል ማርያምን፣ የቅዱሳን መላእክትን፣ የነቢያትን፣ የሐዋርያትን፣ የጻድቃንና የሰማዕታትን ክብርና ቅድስና በማውሳት በስማቸው መማፀንና መጸለይ የሚያስገኘውን ጥቅም የሚያስረዳ ታላቅ ዜማዊ ሀብት ነው፡፡ ፠ከእርሱ በፊት የነበሩና በእርሱ ዘመን የተጻፉ የቅዱሳን ገድላትና ድርሳናትን እንዲሁም የበዓላትን ጥንታዊ አመሠራረት ውስጠ ምሥጢር በማስረዳት በዜማ ድርሰቱ አካቷል፡፡ ፠ምስጋናውንም ለአራቱ ክፍላተ ዘመን ለክረምት፣ ለመፀው (ለጥቢ)፣ ለሐጋይ (ለበጋ)፣ ለጸደይ (ለበልግ) እንዲኾን አዘጋጅቶታል፡፡ #ለ_የዜማው_ጠባያት ፨የቅዱስ ያሬድ ዜማ ሰማያዊ በመኾኑ ኅሊናን የመመሠጥ፣ ሥጋዊ ደስታንና ኀጢአትን ከማሰብ የመጠበቅ፣ ሰማያዊውን ድንቅ የምስጋና ምስጢር የማሳወቅ ኀይል አለው፡፡ ፨ከእግዚአብሔር የተገኘ ስጦታም በመኾኑ ብልየት (እርጅና)፣ ውላጤ (መለወጥ) የማይታይበት ዘወትር ሕያው የኾነ ብቸኛ ዜማ ነው፡፡ ፨የመንፈስ ቅዱስ ስጦታም በመኾኑ ዘወትር አዲስና የማያልቅ ጥልቅ ምንጭ ያለው ሕይወትን የሚያለመልም ነው፡፡ ፨ዜማውም ሰማያዊና መንፈሳዊ፣ ከእግዚአብሔር የተገኘ ለመኾኑ ማስረጃ የሚኾነን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ውጪ ያሉ ሰዎች ዜማውን ለተለያየ ዐላማ ይመኙታል፤ ነገር ግን ለመያዝም ኾነ ለመወሰን አይችሉም፡፡ ምክንያቱም በምድራዊ ጥበብና ፍልስፍና የሚያዝ የሚወሰን ሳይኾን ታላቅ መሥዋዕትነትን የሚጠይቅ፣ ሌት ተቀን ልቡናን ለሥላሴ ሰጥተው ከእግዚአብሔር የሚያገኙት በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሚያጸኑት፣ የሚማሩትና የሚያዜሙት እንጂ በገንዘብ የማይገዛ ታላቅ ጸጋ መኾኑ ነው፡፡ #ሐ.#የቅዱስ_ያሬድ_ዜማ_ከሌሎች _ዓለማዊ_ዜማዎች_የሚለይበት_ጠባይ፤  ዜማው አሳብን የሚገዛ፣ ከሥጋ ይልቅ በመንፈስ መመላለስን የሚያስተምር በመኾኑ፤  በአቀራረቡም የተወሰነ የዜማ ስልትና ቀመር ያለው በመኾኑ፤  ዜማው በአዝማናት ተለይቶ በወቅት ተከፋፍሎ የሚዜም መኾኑ፤  ማንኛውም ሰው ከተወሰነ የዜማ ስልትና ቀመር ውጪ በራሱ ፍላጎት የድምፅ ቅላጼውን ለማሳመር ስለፈለገ የሚያሻሽለው ወይም የሚለውጠው አለመኾኑ፤  ዜማው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌና ምሥጢር የተሞላ መኾኑና  የዜማው ምልክቶችና ዐይነቶች ጥልቅ ምሳሌና ምስጢር ያላቸው መኾናቸው ነው፡፡ #መ_የቅዱስ_ያሬድ_ዜማ_ጥቅም ሀ. የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በመጠበቅ፤ በየትኛውም አካባቢ የምትኖር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አንድ ዓይነት መዝሙር፣ አንድ ዓይነት ቅዳሴ፣ አንድ ዓይነት ማኅሌት፣ አንድ ዐይነት ሥርዐት በአንድ ዓይነት ጊዜ በአንድ ቀን ማቅረብና መፈጸም እንድትችል አስችሏታል፡፡ ለ. በነገረ መለኮት ትምህርት፤ ሊቁ የትርጓሜ መምህር ስለሆነ ከብዙ መጻሕፍት ስለሚጠቅስና የሃይማኖት ትምህርቱትንም በዜማ አቀነባብሮ መድረሱ በጣም ተወዳጅ ትምህርት እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ሐ. በሥርዓተ ጸሎት፤ ከዓመት እስከ ዓመት ለሚከናወኑ (የዘመናትና የሳምንታትን ጨምሮ) ማንኛውም ሥርዐተ ጸሎት ዋና መሪው የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ነው፡፡ ማኅሌቱ፣ ቅዳሴው፣ ፍትሐቱ፣ ጥምቀተ ክርስትናው ሁሉ በዜማው መሪነት የሚከናወኑ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ መ. ለቱሪዝም ሀብት (መስህብነት)፤ ክርስቲያናችን በየወሩና በየዓመቱ ከምታከብራቸው በዓላት ላይ ከሚቀርቡት ዝግጅቶች አብዛኛውን ክፍል የሚይዘው በቅዱስ ያሬድ ዜማ የሚቀርበው የዝማሬና የቅዳሴ አገልግሎት ነው፡፡

#፬#የቅዱስ_ያሬድ_ድርሰቶች፤ #1ኛ) ምዕራፍ (ውዳሴ ማርያም በዜማን፣ መስተጋብዕ፣ አርባዕት፣ አርያም፣ ሠለስት፣ ክስተተ አርያምን) ያጠቃልላል፡፡ ፠የውዳሴ ማርያም ዜማ ቅዱስ ኤፍሬም ሦርያዊ የደረሰውን ለቅዱስ ያሬድ እየነገረው ልብን የሚመስጥ ዜማ ደርሶለታል፡፡ ፠መስተጋብዕ፤ ስብስብ ማለት ሲኾን፡፡ ከዳዊት መዝሙር (ከ180ው የመስተጋብእ ድርሰት 1ድ ድርሰት በስተቀር) ለጸሎትና ለዝማሬ ተስማሚ የኾነው እየተውጣጣ ለመዝሙር ተስማሚ የኾነው የተቀመረ ነው፡፡ መስተጋብዕ ሲጀምር ‹‹ወለቡ ጽራኅየ (ጩኸቴን ልብ አድርግ›› ብሎ ነው፡፡ በዐቢይ ጾም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ጠዋት ይዘመራል፤ የቀድሞ መምህራን በፍልሠታም ይዘምሩት ነበር፤ ዜማው በዋነኛነት በግዕዝና በዕዝል ሲኾን በአራራይ ከሐሙስ ‹‹አንተሰ እግዚኦ ለዓለም›› የሚለውና ከቅማዴ ‹‹መንግሠትከሰ መንግሥት›› የሚለው ይገኙበታል፡፡ በየእለቱ እንዲደርስ (ከእሑድ በስተቀር) አድርጎ የደረሰው ነው፤ ፠አርባዕት፤ አራት አራተኛ ማለት ሲን በዳዊት መዝሙር በአራተኛው መሥመር ውስጥ እየገባ የሚዘመር ነው፤ ‹‹ቃልየ አጽምእ እግዚኦ ወለቡ ጽራኅየ፤ ወአጽምአኒ ቃለ ስእለትየ፤ ንጉሥየኒ ወአምላኪየኒ፡፡ ከፈጸመ በኋላ አርባዕት ይገባል፡፡ አርባዕት ሲጀመር ‹‹ቃልየ፤ ከመ ያፈቅርለ ጐሥዓ፤ ዐቢይ፤ ተሣሃለኒ›› ብሎ ነው (በዳዊት መዝሙር ጀምሮ ቀጥሎ በቅዱስ ያሬድ ድርሠት በኾነው በአርባዕት ያጠናቅቃል፡፡አብዛኛው በግጥም መልክ የተቀመረ ሲኾን አልፎ አልፎም በስድ ንባብ መልክ ይገኛል፡፡ ግእዝ ዕዝልና አራራይ ዜማ አለው፡፡ አርያም፤ አርያም ልዑል፥ ከፍተኛ ማለት ሲኾን፤ ቅዱስ ያሬድ ከአርያም ሰምቶ ‹‹ቀዳሚ ዜማ፤ አንድም ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ›› ስላመጣው ነው፡፡ ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብሎ የግጥም መል ባለው አእያም በተባለው ይጀምራል፡፡ በግጥም መልክና በስድ ንባብ ሲገኝ የግጠም አገጣጠሙ ከፍ ያለ የግጥም አገጣጠምን የተከተለነው፡፡ የሚባልበት ጊዜ በጾም ጊዜ በጾመ ድጓው እየገባ፣ በተለይ ደግሞ በክብረ በዓል ክሥተተ አርያም ሲደርስ ይዘመራል፡፡ ሠለስት፤ ስምዐኒ ብሎ የሚጀምር ባለ ብዙ ሃሌታ ያለው፤ በዳዊት መዝሙር በሦስተኛው መሥመር እየገባ የሚዘመር፤ አንድም 3 መዝሙሮች ብቻ የሚዘመሩለት ብዙውን ጊዜ በግጥም የሚቀርብ ሲኾን፤ ይኽ ዜማ የሚደርሰው በክብረ በዓላት ዋይዜማ፤ በስብሐተ ነግህ፣ በአርያም፣ በጾመ ድጓ ውሎ፣ በአርያም፣ በሰንበት፣ በፍትሐት ጊዜ ነው፡፡ ክስተተ አርያም፤ የሰማይ መከፈት ማለት ሲኾን በታላላቅ በዓል ቀን እንዲሁም ታላላቅ? ሰዎች ሲሞቱ የሚዘመር ነው፤ ክስተትን ቅዱስ ያሬድ ያዘጋጀው ከዳዊት መዝሙራት፥ ከጸሎተ ነቢያትና ከራሱም ጭምር ኀይለ ቃል ያላቸውን ባለሁለት መስመሮች ሐረግ በመውሰድ ሲኾን ዜማው እጅጉን ነፍስና ሥጋን፥ ልብንና ኅሊናን የሚመስጥ ነው፡፡ 2ኛ) ጾመ ድጓ፤ በዐቢይ ጾም የሚባል ነው፡፡ 3ኛ) ድጓ፤ በ4ት ክፍላተ ዘመናት የተቀመረ ነው፡፡ 4ኛ) ዝማሬ፤ ቅዱስ ቊርባን ድርገት ሲወርድ ለቅዱስ ቊርባን ክብር የሚዘመር ነው፡፡ 5ኛ) መዋሥዕት፤ ሰው ሥጋው ከነፍ ስትለይ ፍትሐት የሚደረግበት ጸሎት ነው፡፡ 6ኛ) የ14ቱን ቅዳሴያት ዜማ፤ 14ቱን ቅዳሴያት 14ት አባቶች የደረሷቸው ቢሆንም ዜማ የደረሰላቸው ግን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ 7ኛ) አንቀጸ ብርሃንን፤ ድርሰቱ ነው፡፡ /ይቀጥላል……/ በተጨማሪም ደግሞ፤ የቅዱስ ያሬድ የዜማ ዐይነቶች ግእዝ፣ ዕዝልና ዓራራይ በመባል ይታወቃል፡፡እነዚህ የዜማ ዐይነቶች የአንዱ ድምፅ ከሌላኛው ድምፅ ያልተደባለቀ፣ ወጥ የሆነ ድምፅ አላቸው፡፡ በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌና ትርጉም ያላቸው በሆኑ የዜማ ምልክቶች (ድፋት፤ ሂደት፤ ቅናት፤ ይዘት፤ ቁርጥ፤ ጭረት፤ ርክርክና ደረት) ደርሷል፡፡ የቅኔ ጀማሪም ነው፡፡ ‹‹ሕንፄሃ …›› የሚለውን ቤት መምቻ ያለውን ቅኔ ልብ ይሏል፤ አንድ ባለቅኔ ግን ይህን ሳይረዳ ‹‹ተትሕተ ያሬድ …›› የሚል ቅኔን ተቀኝቷል፡፡

#፫)#ሥርዐተ_ማኅሌት_ዘግንቦት_11ና_የቅዱስ_ያሬድ_ሌሎች_መጠሪያ_ስሞች #ማሕሌቱን_ለማሕሌት_አባት፤_እናቅርብለት:: ፠ (#ቅዱስ_ያሬድን_ያልዘከረ_ኢትዮጵያዊ_ምኑን_ኢትዮጵያዊ_ኾነ!?) ፠ (#ቅዱስ_ያሬድን_ያልዘከረ_ካህን_ምኑን_ካህን_ኾነ!?) ፠ (#ቅዱስ_ያሬድን_ያልዘከረ_ሰንበት_ተማሪ_ምኑን_ሰንበት_ተማሪ_ኾነ!?) ፠ ጥዑመ ልሳን፤ ፠ የሱራፌል አምሳያ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን እንዚራ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን፤ ፠ መዓርዒረ ዜማ፤ ፠ ካህን (ካህነ ስብሐት) ፠ ማኅሌታይ፤ ፠ መዘምር ዘበድርሳን፤ ፠ ሊቅ (ርእሰ ሊቃውንት) ፠ ዓርከ ሊቃውንት፤ ፠ ደራሲ፤ ፠ የመጽሐፍ መምህር፤ (ብሉያትንና ሐዲሳትን የሊቃውንትንም መጻሕፍት አስማምቶ የተረጐመ) ፠ ባለቅኔ (የቅኔ ጀማሪ)፤ ፠ የቤተክርስቲያን ጌጧና መሠረቷ ሕይወቷና እስትንፋሷ ፠ ልዑለ ስብከት፤ ፠ ሰማዕት፤ ፠ ባሕታዊ፤ ፠ መናኝ ፠ የዜማ አባት፤ ፠ የኢትዮጵያ ብርሃን፡፡ ፠ አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም) የኾነ:: ፠ እግሮቹ በመልካም መንገድ የሚጓዙና ወደ መልካም መንገድ የሚያስጕዙ ፠ ልቡናው የቅድስና ማኅደር የኾነ:: ፠ ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ የኾነ:: ፠ አእምሮው የመጠቀ፤ ፠ ድርሰቱ የተራቀቀ፤ ፠ እስከ አርያም ተነጥቆ ዕፁብ ድንቅ ምሥጢራትን የተመገበ ማን እንደርሱ:: …... /ማኅሌቱን በአ.አ ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ/ክ የምትቆሙ በደብረ ይባቤ የሚለውንና በሰማየዊ ቀለም የተቀባውን እየመረጣችሁ መጠቀም ስትችሉ፤ በሌሎች አድባራት ግን ሰማያዊ ቀለም የሌለበትን (በቢጫና እንዲሁ ያለቀለም የተቀመጠውን) እየመረጣችሁ መጠቀም ትችላላችሁ፡፡/ ፨*፨(ሥርዐተ ማኅሌቱን ስናዘጋጅ የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያንን ይትበሃል በመስጠት ለተባበራችሁን ለሊቀ ጠበብት አባ ኤርምያስና አርድዕቶቻቸው በተለይም ለዲ.ን አውራሪስ አምላከ ቅዱስ ያሬድ መድኀኔ ዓለም ይስጥልን፡፡) /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

#፪)#የቅዱስ_ያሬድ_አስደናቂ_ነገሮች #፠ከጌዴዎን ዘንድ ትምህርቱን አቋርጦ ሄደ ስንል፤ በአንድ ሾላ ዛፍ ላይ በትል አማካይነት ትዕግስትንና ማስተዋልን ቀስሞ፤ ወደ አጎቱ ተመልሶ ተምሮና ትምህርትን አምላክ ገልጾለት መምህረ መምህራን ሁኖ እንገኘዋለን፤ /እግዚአብሔር አምላክ ለቅዱስ ያሬድ ያንን ኹሉ ጥበብ ቶሎ ያልገለጸለት በቀላሉ ቢያገኘው ኋላ እንዳይታበይ ብሎ ነው፤ የሐዊራ ብስድር እስክንድራን ታሪክ ልብ ይሏል) #፠መምህር ነው ስንል፤ መናኝ ባሕታዊ ኾኖ እናገኘዋለን፤ /በደብረ ሐዊ ለ22ዓመታት መመኑን ልብ ይሏል/ #፠መናኝ ነው ስንል የተለያዩ የሃገራችንን ክፍሎች ገዳማትና አድባራት ሲጎበኝ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ሲጓዝ እንገኘዋለን፤ /ጣና ቂርቆስ፤ ዙር አባ አቡነ አረጋዊ፣ …. ሌላውንም ልብ ይሏል) #፠ወደ ገዳማትና አድባራት ይጓዛል ስንል፤ ወደ ደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ በደመና ተጭኖ ሂዶ ምሽቱን ወደ በዓቱ ሲመለስ እንገኘዋለን፡፡ #፠በሃገራችን በዋና ከተማ አኵሱም ተወልዶ ያደገ ነው ስንል፤ ሰው ሊኖርበት በማይችለው፥ በረድ በሚፈላበት፥ የነፋስ እሩምታ በሚያይልበት፥ ቅዝቃዜው አጥንት በሚሰነጥቅበት፥ ውርጩ እጅጉን በሚቀዘቅዝበት፥ ደመና በሚፈስስበት በራስ ደጀን ተራራ አጠገብ በደብረ ሐዊ መንኖ እናገኘዋለን፡፡ #፠ከሰዎች ጋር አብሮ ኑሯል ስንል፤ ከሰው የማይቀርቡና በዐለማችን ላይ ብርቅዬ ኾነው በሃገራችን የሚገኙ ከሃገራችን ኢትዮጵያም በሰሜን ተራሮች በአብዛኛው ከሚገኙት ዋልያ ጋር አብሮ ሲኖር፤ ዋልያዎችንም እንደ መጓጓዣና እንደ መጫኛ ሲያገለግሉት እንገኛለን፡፡ #፠በሙራደ ቃል የመላእክት ዜማ ተገልጾለት ተማረ ስንል፤ የግእዝ ቋንቋ ምሁርና ጠበብት ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ (ለተሰዓቱ ቅዱሳን መምህር መሆኑን ልብ ይሏል) #፠የዜማ ጀማሪ አባት ነው ስንል ባለቅኔ ኾኖ እንገኘዋለን (ሕንፄሃ ወሡራሬሃ …. የሚለው ቅኔውን ልብ ይሏል)፤ #፠ባለቅኔ ነው ስንል መተርጕም ኾኖ እንገኘዋለን፤ (ድጓው የብሉይና የሐዲስ ትርጓሜ መሆኑን ልብ ይሏል) #፠መተርጕም ነው ስንል ባለታሪክ፥ የታሪክ ምሁር ኹኖ እናገኘዋለን፤ #፠የታሪክ ምሁር ነው ስንል፤ የመርሐ አዝማን ሊቅ ኹኖ እናገኘዋለን፤ (ዓመቱን በሚገርም ሁኔታ ከወቅታቱ ጋራ አገናዝቦ መሠየሙን ልብ ይሏል) #፠የመርሐ አዝማን ሊቅ ነው ስንል ቅዱስ ኾኖ እንገኘዋለን፤ የቅዱሳንም ጓደኛ ኹኖ እንገኘዋለን፡፡ /የአቡነ አረጋዊ፣ የአጼ ገብረ መስቀልን ታሪክ ልብ ይሏል፡፡/ #፠ነቢይ ነው ሰንል ሐዋርያ ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ (ስለ ዳግም ምጽአት፣ ስለ መንግሥተ ሰማያትና …. ሌሎችንም ልብ ይሏል) #፠ሐዋርያ ነው ስንል ሰማዕት ኹኖ እናገኘዋለን፡፡ (እግሩን በጦር መወጋቱን ልብ ይሏል)፤ ሌላም ሌላም …. ፠#፠በአጠቃላይ ምድራዊ ነው ስንል ሰማያዊ፤ ሰማያዊ ነው ስንል ምድራዊ (ብእሲ ሰማያዊ ወመልአክ ምድራዊ) ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ #ዜማውን በግዕዝ ዕዝል አራራይ የዜማ ስልት የደረሰ፤ #በዓለም ደረጃ የዜማ ምልክቶች ባልታወቁበት ጊዜ ዜማዎቹን በምልክት የቀመረ፤ #የዜማ ሥርዓትን በመንደፍ የዓመቱን ቀለም ያዘጋጀ፤ #ዜማውን በ4ት ዘመናት ከፋፍሎ፤ ዘመናቱን በንዑሳን ዘመናት ከፋፍሎ ለወራቱና ለሰሙኑ ለእለቱ የሚገባውን ቀምሮ የደረሰ፤ #እንኳን በእርሱ ዘመን ዛሬ እንኳን ብዙ ነገሮች ተሰባስበዋል በተባለበት ዘመን ሊሠራ አይደለም ሊታሠብ በማይችሉ መልኩ መጽሕፍትን እንደ ንብ እየቀሰመ፤ እንደ ወይን እየጨመቀ፤ እንደ አረቂ እያጣራ፤ እየተረጐመ ላሰበው ድርሠት ያዋለ፤ … ስለ ቅዱሱ ምኑን ተናግረን እንጨርሰዋለን፡፡ … ##.. ይኼማ ኢትዮጵያዊ ሊኾን አይችልም ብለው ብዙ የውጭ ሃገራት ወደ ራሳቸው ለመውሰድ የሚዳዳቸው፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

#፩)#የቅዱስ_ያሬድ_ልደትና_የስሙ_ትርጓሜ ꔰ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ ሚያዚያ 5 ቀን በ505 ዓ.ም. ከአባቱ ይስሐቅ(አብድዩ) ከእናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) በአኵሱም ከተማ ተወለደ፡፡ (አንዳንዶች ልደቱን 493 ዓ.ም. ነው ይላሉ፤ እንዲሁም አባቱ ኖኅ ነው ይሉና መሪጌታ ይስሐቅ የቀለም አባቱ /መመህሩ/ ነው ይላሉ፡፡) ꔰ የስሙም ትርጓሜም ያሬድ ማለት እንዚራ፣ በገና፣ መሰንቆ ማለት ነው ፡፡ እነዚህ መሣሪያዎች በስልት በስልት ሲመቱ ለሚሰማቸው ደስ እንዲያሰኙ የያሬድም ዜማ በንጉሠ ነገሥቱ ክርስቶስ አደባባይ በቤተ ክርስቲያን ሲሰማ መላእክትን፥ ሰውንና እንስሳትን ደስ ያሰኛልና፡፡  አንድም ያሬድ ርደት፣ ወሪድ፤ መውረድ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ሰማያዊውን ልዩ ጣዕመ ዜማ ወደ ኢትዮጵያ አውርዷልና፡፡  አንድም ያሬድ ማለት ንብ ማለት ነው፤ ንብ የማይቀስመው አበባ እንደሌለ ሁሉ ቅዱስ ያሬድም ከመጻሕፍት የማይጠቅሰው የማይቀሰመው የለም፤  አንድም ያሬድ ማለት ረአዬ ምሥጢር፥ ነጻሬ ኅቡአት ማለት ነው፤ የመላእክት ምሥጢራት የነበሩትን ጸዋትወ ዜማ አምልቶ አስፍቶ ተናግሯልና፣ ነጻሬ ኅቡአት አለ፥ ኅቡእ (ስውር) የሆነ የጻድቃን፣ የሰማዕታት የነቢያት የሐዋርያትን ገድል አምልቶ አስፍቶም ይናገራልና፡፡ -ዐፄ ካሌብ ቤተ እስራኤል፣ ገብረክርስቶስና ገብረ መስቀል የሚባሉ ልጆች ነበሩት፤ ቅዱስ ያሬድ የተነሳው ከእነዚህ ውስጥ በዓፄ ገብረመስቀል ዘመን ነው፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

ዝከረ ቅዱስ ያሬድ በሃገራችንና በዓለማችን ደረጃ የሚዘከርባቸውን መርሐ ግብሮች እናስተዋውቃችሁ፡፡ ፠#በቀጨኔ_ደብረ_ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት፡፡ (በየወሩ ዝክረ ቅዱስ ያሬድ) ይደረጋል፡፡ ፠#በደብረ_ይባቤ _ቅዱስ_ያሬድ_ ቤ/ክ፤ ከግንቦት 9-11 ልዩ የሠርክ ጕባኤ ከ10፡30 ጀምሮ ተዘጋጅቷል ፠#በመካኒሳ_ምዕራፈ_ጻድቃን_አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_ቤ_ኆኅተ_ጽድቅ_ሰ/ት/ቤት፡፡#ዐውደ_ርዕይ_በእንተ_ቅዱስ_ያሬድ_ወቤተ_ክርስቲያን፤ ከግንቦት 7-11፤ ከቀኑ 10-12 ሰዐት፤ ፠#በጀርመን_ክሮምበርግ_ቅዱስ_ዑራኤልና_ቅዱስ_ያሬድ_ቤተ_ክርስቲያን (ለ3ት ቀናት፤ ከግንቦት 9 - 11 / 2011ዓ.ም. ጥናታዊ ጽሑፎች፣ ስብከተ ወንጌል፣ ያሬዳዊ ዝማሬ፣ ቅኔ፣ ሥነ ጽሑፍና ሌሎችም፡፡) ፠#በማኅበረ_ቅዱሳን (አዲስ አበባ፤ 3ኛ ፎቅ)፤ ግንቦት 11/2011ዓ.ም. ከቀኑ በ7፡30 የቅዱስ ያሬድ ድንቅ ዜማዎችን፣ ቅኔንና ትርጓሜውን ሌሎቹንም በተመለከተ ይቀርባል፡፡ ፠#ዝክረ_ቅዱስ_ያሬድ_ወአብነት_ትምህርት፤ #በአፍሪካ_ኅብረት_ደብረ_ምሕረት_ቅዱስ_ሚካኤል_ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት፤ ግንቦት 11 ከቀኑ 7-11 ሰዐት፡፡ ትምህርተ ወንጌል፣ ወረብና ዝማሬ፣ ቆይታ ከየኔታ ጋር፣ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች፣ ከእንግዳ ጋር ቃለ መጠይቅ ይኖራል፡፡ ፠#በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት አዳራሽ፤ ኀሙስ ግንቦት 15/2011ዓ.ም. ከቀኑ በ11 ሰዐት፤ ‹‹ምሴተ ጥበብ ዘቅዱስ ያሬድ›› በሚል የሥነ ጽሑፍ ምሽት (ሥነ ጽሑፍ፣ ዲስኩር፣ ያዳዊ ወረብ፣ ተውኔትና ሌሎችም ተጋባዥ መምህራን በተገኙበት) ይካሄዳል፡፡

#የዐርብ_ጕባኤ_፻፳፱ኛ_ሳምንት #ዐርብ_ግንቦት_፱/፳፻፲፩ዓ.ም. ከ፲፪-፪ ሰዓት፤ ጸሎቱ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል:: ትምህርት ይሰጣል፡፡