fa
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

رفتن به کانال در Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

کانال ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 19 219 مشترک است و جایگاه 1 193 را در دسته پزشکی و رتبه 1 780 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 19 219 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 27 اوت, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -412 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -4 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 25.37% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 7.88% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 878 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 516 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 9 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 28 اوت, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته پزشکی تبدیل کرده‌اند.

19 219
مشترکین
-424 ساعت
-1067 روز
-41230 روز
آرشیو پست ها
የሴቶች የወሲብ ፍላጎት መቀነስ እንደ ሆርሞን ለውጥ (ማረጥ፣ እርግዝና)፣ የጤና ችግሮች (ስኳር፣ የልብ ህመም)፣ የመድሃኒት ውጤቶች፣ ድካም እና ህመም ያሉ አካላዊ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላል። በተጨ
የሴቶች የወሲብ ፍላጎት መቀነስ እንደ ሆርሞን ለውጥ (ማረጥ፣ እርግዝና)፣ የጤና ችግሮች (ስኳር፣ የልብ ህመም)፣ የመድሃኒት ውጤቶች፣ ድካም እና ህመም ያሉ አካላዊ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላል። በተጨማሪም፣ እንደ ጭንቀት፣ ድብርት፣ የሰውነት ምስል ጉዳዮች፣ የቀድሞ ወሲባዊ ጉዳቶች እና ዝቅተኛ በራስ መተማመን ያሉ የስነ ልቦናዊ ምክንያቶችም ተፅዕኖ ያሳድራሉ። ከባልደረባ ጋር አለመግባባት፣ የመግባባት ችግሮች፣ የፍቅር እጦት እና የባልደረባ ወሲባዊ ችግሮች በግንኙነት ነክ ምክንያቶች ውስጥ ይካተታሉ። የአኗኗር ዘይቤ (እንቅልፍ ማጣት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማነስ)፣ እንዲሁም ማህበራዊ እና ባህላዊ ምክንያቶችም ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ። እነዚህ ምክንያቶች ውስብስብ ስለሆኑ እና ከአንድ በላይ መንስኤዎች በአንድ ጊዜ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ከባልደራባ ጋር በደንብ መወያየት እና የጤና ባለሙያ ማማከር አስፈላጊ ነው። አዲሱን የ Youtube ቻናል subscribers ያድርጉ https://linktw.in/tiRGPP

በወንድ አካል ላይ ያለው የፕሮስቴት እብጠት (BPH) በወሲብ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ የፕሮስቴት ሕክምናዎች የወንድ ብልት አለመቆም ችግርን (Erectile Dysfunction) ሊያስከትሉ ይችላሉ?
በወንድ አካል ላይ ያለው የፕሮስቴት እብጠት (BPH) በወሲብ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ   የፕሮስቴት ሕክምናዎች የወንድ ብልት አለመቆም ችግርን (Erectile Dysfunction) ሊያስከትሉ ይችላሉ? የፕሮስቴት እብጠት (Benign Prostatic Hyperplasia - BPH) ካንሰር ያልሆነ የፕሮስቴት እብጠት ሲሆን ከ50% በላይ በሚሆኑ እድሜያቸው ከ50 በላይ በሆኑ ወንዶች ላይ የሚከሰት ነው። የፕሮስቴት እብጠት ብቻውን አስጊ ባይሆንም ህክምናዎቹ በወሲብ ጤና ላይ ግን ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። አንዳንድ መድሃኒቶች፣ በተለይ 5-አልፋ ሪዳክታዝ እንደፊናስቴሪድ (Finasteride) ያሉ ምርቶች የወሲብ ፍላጎትን መቀነስ እና በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የወንድ ብልት አለመቆም ችግርን ሊያመጡ  ይችላሉ። እንዲሁም አንዳንድ ቀዶ ህክምናዎች፣ ለምሳሌ የሚታወቀው Transurethral Resection of the Prostate (TURP) በወንድ ዘር መርጨት ሥርዓት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ይህም የወንድ ዘር ወደ ብልት ከመሄድ ይልቅ ወደ ሽንት ማጠራቀሚያ እንዲሄድ ያደርገዋል(Retrograde Ejaculation)። አዳዲስ መመሪያዎች እነዚህን የጐንዮሽ ጉዳቶች ከሕክምናው በፊት ከታካሚው ጋር መወያየት እና የተሟላ ውሳኔ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ያስረዳሉ። **** በ ዶ/ር እሌኒ ሞላ መረጃ ምንጭ፣ European Association of Urology (EAU). አዲሱን የ Youtube ቻናል subscribers ያድርጉ https://linktw.in/tiRGPP

ጠቃሚ መረጃ አዲሱን የ Youtube ቻናል subscribers ያድርጉ https://linktw.in/tiRGPP

የሀሞት ጠጠር አዲሱን የ Youtube ቻናል subscribers ያድርጉ https://linktw.in/tiRGPP

ለስፐርም ጥራት ማሽቆልቆል ምክንያት የሆኑ 9 ዋና ዋና ነገሮች! የአንድ ወንድ የመውለድ ብቃት በቀጥታ ከሚያደርጋቸው የዕለት ተዕለት ልምዶች እና ለአንዳንድ ነገሮች ከሚጋለጥባቸው ሁኔታዎች ጋር የተያ
ለስፐርም ጥራት ማሽቆልቆል ምክንያት የሆኑ 9 ዋና ዋና ነገሮች! የአንድ ወንድ የመውለድ ብቃት በቀጥታ ከሚያደርጋቸው የዕለት ተዕለት ልምዶች እና ለአንዳንድ ነገሮች ከሚጋለጥባቸው ሁኔታዎች ጋር የተያያዘ ነው። 1. በወንድ የዘር ፍሬ ላይ የሚደርስ ከፍተኛ አደጋ ወይም ጉዳት የሰውነታችንን የበሽታ መከላከያ ሥርዓት በማነቃቃt ለወንዶች መካንነት ምክንያት ሊሆን ይችላል። በአንፃሩ፣ ቀለል ያሉ የወንድ ዘር ከረጢት መላላጦችና መጋጨቶች የተለመዱ ቢሆኑም አብዛኛውን ጊዜ በመውለድ ብቃት ላይ የሚያመጡት ተፅዕኖ የለም። 2. ሲጋራ ማጨስ; የትምባሆ ጭስ የዘር ፈሳሽ ትኩረትን ፣ ወደፊት የመንቀሳቀስ ብቃትን ፣ ውጫዊ ቅርጽን እና የህይወት ቆይታን ይቀንሳል። በተጨማሪም ስፐርም ወደ እንቁላል የመግባት ብቃቱን እንዲያጣ ያደርጋል። 3. ስቴሮይድስ: ለተለያዩ ዓላማዎች (ለምሳሌ ለሰውነት ማሳደጊያ) የሚወሰዱ ውጫዊ ሆርሞኖች በአንጎላችን ውስጥ የሚገኘውን ፒቱታሪ ግላንድ ሆርሞን እንዳያመርት ያግዱታል። ይህ ደግሞ በጠቅላላው የዘር ፍሬ ምርትን ሙሉ በሙሉ ያቆማል። 4. አንዳንድ መድኃኒቶች: በርካታ የታዘዙ መድኃኒቶች በወንድ ዘር ሴሎች ላይ መርዛማ ተፅዕኖ በማሳደር ወይም የመራቢያ ሥርዓት መዋቅርን በማስተጓጎል መካንነትን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ለአብነት ያህል፦ ኬቶኮናዞል ፣ ስፒሮኖላክቶን (spironolactone)፣ የደም ግፊት መድኃኒቶች ፣ ኤሪትሮማይሲን ፣ ኒትሮፉራንቶይን ፣ ጄንታማይሲን እና ቴትራሳይክሊን ይጠቀሳሉ። 5. ጥብቅ ልብሶች: ጥብቅ የሆኑ ሱሪዎችንና የውስጥ ሱሪዎችን መልበስ በታችኛው የሰውነት ክፍላችን ላይ ያለውን ሙቀት ይጨምራል። የወንድ የዘር ፍሬ ሙቀት በ 1°C ብቻ እንኳ ቢጨምር የስፐርም ክምችትን በ 40% ይቀንሳል። ለዚህ ነው በኢንፌክሽን (በከፍተኛ ትኩሳት) ወቅት የስፐርም ምርመራ ሲደረግ ምንም ዓይነት ስፐርም የማይገኘው። 6. ውፍረት: ከመጠን በላይ ክብደት ያላቸው ወንዶች፣ መደበኛ ክብደት ካላቸው ወንዶች ጋር ሲነፃፀሩ በመውለድ ችግር የመጠቃት ዕድላቸው በ 50% የላቀ ነው። ይህ የሚሆነው በስብ ሴሎች ውስጥ አንድሮጅን ሆርሞን ወደ ኢስትሮጅን ስለሚቀየርና ይህ ሂደት የወንድ ዘር ዕድገትን በአሉታዊ መልኩ ስለሚጎዳው ነው። 7. ፕታሌትስ: እነዚህ በፕላስቲኮች እና በመዋቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች ናቸው። በሽንታቸው ውስጥ ከፍተኛ የፕታሌትስ መጠን የሚገኝባቸው ወንዶች የቴስቶስትሮን ሆርሞን መጠናቸው ዝቅተኛ ሆኖ ይገኛል። ዝቅተኛ ቴስቶስትሮን ማለት ደግሞ የመውለድ ችግር ማለት ነው። 8. አልኮል: ከመጠን በላይ መጠጣት የመውለድ ብቃትን በሚከተሉት መንገዶች ይጎዳል፦ 👉🏿የቴስቶስትሮን ሆርሞንን በመቀነስ 👉🏿የፒቱታሪ ግላንድ ሆርሞኖችን በማሳነስ 👉🏿 የወንድ ዘር (ስፐርም) ምርትን እና ተግባርን በማስተጓጎል! 9. BPA (ቢፒኤ); ቢስፌኖል ኤ (Bisphenol A) በፕላስቲክ ዕቃዎች ውስጥ የሚገኝ ኬሚካል ሲሆን፣ የቴስቶስትሮን ሆርሞን መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል። እንወያይ፦ ከእነዚህ 9 ነጥቦች ውስጥ እናንተን ይበልጥ ያስገረማችሁ ወይም ቀደም ሲል የማታውቁት የትኛውን ነው? በተለይ ጥብቅ ልብስ መልበስና ውፍረት በዚህ ደረጃ ተፅዕኖ አላቸው ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? አስተያየታችሁን በኮሜንት አጋሩን! 👇 ወንድ ወንድሞቻችንና ጓደኞቻችን ራሳቸውን እንዲጠብቁ Share በማድረግ መረጃውን አብዙላቸው! #የወንዶችጤና #የጤናመረጃ #መካንነት #ጤና #Ethiopia @Drshemse

የመቀመጫ ላይ ኪንታሮት ያለባችሁ አዳምጡ አዲሱን የ Youtube ቻናል subscribers ያድርጉ https://linktw.in/tiRGPP

ጥንቃቄ ይሄንን ችላ እንዳትሉ ሙዝ ከመብላቶ በፊት ለበለጡ መረጃዎች ቴሌግራማችንን ይጎብኙ 🌎 https://t.me/Drshemse

የጨጓራ መድማት ለበለጡ መረጃዎች ቴሌግራማችንን ይጎብኙ 🌎 https://t.me/Drshemse

ፀጉር ለሚሳባበርባችሁ እና ለሚነቃቀልባችሁ መፍትሄ ለበለጡ መረጃዎች ቴሌግራማችንን ይጎብኙ 🌎 https://t.me/Drshemse

የስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) መድኃኒቶች! የስንፈተ ወሲብ ችግርን ለማከም በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉት የ PDE5 inhibitors በመባል የሚታወቁ መድኃኒቶች ናቸው። እነዚህ
የስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) መድኃኒቶች! የስንፈተ ወሲብ ችግርን ለማከም በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉት የ PDE5 inhibitors በመባል የሚታወቁ መድኃኒቶች ናቸው። እነዚህ መድኃኒቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ: Sildenafil (Viagra) Tadalafil (Cialis) Vardenafil (Levitra) Avanafil (Stendra) እንዴት ነው የሚሰሩት? እነዚህ መድሃኒቶች የሚሰሩት በብልት ውስጥ ያሉ የደም ስሮች እንዲከፈቱ እና የደም ዝውውር እንዲጨምር በማድረግ ነው። ይህ የሚሆነው PDE5 የሚባለውን ኢንዛይም (enzyme) በመከላከል ነው።       የ PDE5 ኢንዛይም የብልት ጡንቻዎች እንዲኮማተሩ እና የደም ፍሰት እንዲቀንስ ያደርጋል። ስለዚህ እነዚህ መድሃኒቶች የ PDE5 ኢንዛይምን ሲገቱት የብልት ጡንቻዎች ዘና እንዲሉ በማድረግ ደም በቀላሉ ወደ ብልቱ እንዲፈስ ያደርጋሉ፣ ይህም ለግንኙነት የሚያስችል ጥንካሬ ያለው ብልት እንዲቆም ይረዳል። ማን መውሰድ የለበትም? እነዚህን መድሃኒቶች ከመውሰድዎ በፊት የጤና ሁኔታዎን ለሀኪምዎ መንገር በጣም አስፈላጊ ነው። በተለይም የሚከተሉት የጤና ህመሞች ካሉዎት እነዚህን መድሃኒቶች መውሰድ የለብዎትም:   የልብ ህመም ካለብዎት: ለልብ ህመም ናይትሬት (nitrate) የያዙ መድኃኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ። እነዚህን መድሃኒቶች ከናይትሬት ጋር አብሮ መውሰድ ለሞት ሊዳርግ የሚችል ከባድ የደም ግፊት መቀነስ ሊያስከትል ይችላል።   የደም ግፊት ችግር ካለብዎት: ዝቅተኛም ሆነ ከፍተኛ የደም ግፊት ካለብዎ።   የጉበት ወይም የኩላሊት በሽታ ካለብዎት: የመድሃኒቱ ተጽእኖ በሰውነትዎ ውስጥ የሚቆይበት ጊዜ ሊራዘም ስለሚችል የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሊያባብስ ይችላል።   ከሀኪም ወይም ከሳይኮሎጂስት ጋር መነጋገር: የስንፈተ ወሲብ መንስኤ የአእምሮ ጭንቀት ወይም ስነልቦናዊ ከሆነ ከሙያተኛ ጋር መነጋገር ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።    እነዚህ ምክሮች ከመድኃኒቱ ጋር ተዳምረው የበለጠ ውጤታማነት እንዲያገኙ ይረዳዎታል። ለበለጡ መረጃዎች ቴሌግራማችንን ይጎብኙ 🌎 https://t.me/Drshemse

ከፊል አረንጓዴ የሆነ ድንች ያለው ጉዳት

✍️ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ ወይም ፖስት ፒል ደጋግሞ የመወሰድ ጉዳቶች 👉ድንገተኛ #የወሊድ #መከላከያ ወይም #ፖስት #ፒል በመባል የሚታወቀው ታስቦ የተሰራው ባልታቀደና ባልታሰበ ግንኙነት አማካይ
✍️ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ ወይም ፖስት ፒል ደጋግሞ የመወሰድ ጉዳቶች 👉ድንገተኛ #የወሊድ #መከላከያ ወይም #ፖስት #ፒል በመባል የሚታወቀው ታስቦ የተሰራው ባልታቀደና ባልታሰበ ግንኙነት አማካይነት እርግዝና እንዳይፈጠር ለመከላከል ቢሆንም ብዙ ወጣት ሴቶች ግን እንደ መደበኛ የወሊድ መከላከያነት ሲጠቀሙበት በስፋት ይስተዋላል ። 👉በወር እስከ ሁለት ጊዜ ቢወሰድ ብዙም ችግር የማይፈጥር ቢሆንም በተደጋጋሚ እና ለብዙ ጊዜ ሲወሰድ በርካታ ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል ።ከነዚህም መካከል :- #የወር #አበባ #መዛባት :-ጊዜውን ያልጠበቀ፣ከፍተኛ ደም ያለው ወይ ዝቅተኛ ደም ያለው የወር አበባ ሊያስከትል ይችላል ።በአብዛኛው ፔሬድ እስከ ሳምንት ሊያዘገይ ቢችልም ከዛ በላይ ከቆየ ግን እርግዝና ሊሆን ስለሚችል መመርመር ያስፈልጋል ። #ከማህፀን #ውጪ #እርግዝና :-እንደ አጠቃላይ ሲታይ ፖስት ፒል እርግዝናን እና ስለዚህም ከማህፀን ውጪ እርግዝናን የሚቀንስ መሆኑ ይታወቃል ።ነገር ግን አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከፖስት ፒል በኋላ የሚፈጠር እርግዝና ከማህፀን ውጪ የመፈጠር እድሉ ከፍ ይላል ።ከማህፀን ውጪ የተፈጠረ እርግዝና በጊዜ ታውቆ ካልታከመ ለህይወት አስጊ ችግር ነው። ✅ክብደት መጨመር :-ለረጅም ጊዜ ፖስት ፒል በተደጋጋሚ መውሰድ የሰውነት ክብደት እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል #የደም #መርጋት :-በተለይ እድሜ ከ35 በላይ ከሆነ፣ሚያጨሱ፣ወፍራም እና በቤተሰብ የደም መርጋት ችግር ባለባቸው ሴቶች የመከሰት እድሉ ይጨምራል። በመሆኑም ማንኛውም የወሊድ መቆጣጠሪያ ከመጠቀም በፊት ሐኪም ማማከር ተገቢ ነው። አዲሱን የ Youtube ቻናል subscribers ያድርጉ https://youtube.com/@4_doctors?si=8XUD1paB7Lmj6Z7