6 860
مشترکین
+524 ساعت
+1437 روز
+29430 روز
آرشیو پست ها
Ø የተማሩትን ትምህርቶች ፈተና የመፈተን መብት
Ø ሰብአዊ መብት የማግኘት መብት አለው/አላት/
Ø በሚደረስበት ተገቢ ያልሆነ ጥቃት በት/ቤቱ አስተዳደር ይሁን በሕግ የመጠየቅ
Ø ከአስተዳደሩ ጋር ቀርቦ የመወያት መብት
Ø በት/ቤቱ ውስጥ ተሰባስቦ ማጥናት ድጋፍ የመጠየቅ መብት አለው፡
Ø በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከት/ት ሰዓት ውጪ የማጥናት መብት
11.ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት
ለአንድ ዓመት ከትምህርት ቤት የሚያሳግድ ጥፋት
Ø በትምህርት ቤት ውስጥ የስርቆት ድርጊት ፈጽሞ መገኘት፣
Ø ሴት ተማሪዎችን መተንኮስ፣ ማስፈራራት፣
Ø ቁማር መጫወት እና ከመሳሰሉ ሕገወጥ ድርጊቶችና ጥፋቶች አለመራቅ፣
Ø ሲጋራ ማጨስ፣ ቬፒንግ/ኢ-ሲጋሬት/፤ ኢ-ሊኩዊድ፣/ መጠቀም የአልኮል መጠጥ ጠጥቶ መገኘት፣ሺሻ ተጠቅሞ መምጣት ጫት ቅሞ መምጣት ሌሎች አደንዛዥ ዕጾችን ተጠቅሞ መምጣት፣
Ø ት/ቤቱና ወላጅ ባላወቁት እና አሳማኝ ባላሆኑ ምክንያቶች ከት/ቤት በአመቱ የትምህርት ካላንደር 10%መቅረት
Ø የት/ቤቱን ንብረት ሆንብሎ መስበር፣ ማበላሸት ማጥፋት፣
Ø በፈተና ወቅት ሁከት መፍጠር ፣ የፈተና ሰርዓቱ እንዲደናቀፍ ማድረግ መኮረጅና ማስኮረጅ፣
Ø የት/ቤቱን መምህራን፤ ሠራተኞችና ኃላፊዎችን መሳደብና ማንጓጠጥ እና ለመደብደብ መሞከር፤
Ø ተማሪዎችን መደብደብ ንብረት መንጠቅ ማስፈራራት፣
12.ከትምህርት ቤት እስከ መጨረሻው የሚያሳግድ ጥፋት
§ አደገኛ የሆኑ ስለታማ እና የጦር መሳሪያዎችን በት/ቤት ቅጥር ግቢ ይዞ መገኘት፣
Ø ስልክ፣ታብሌት ይዞ መምጣት፤ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ መጠቀም ተገቢ ያልሆነ ተግባር ማከናወን፤ (ተማሪ የሚያወናብዱ መረጃዎች ማስተላለፍ፤ ወዘተ)
§ ሴት ተማሪዎችን መደባደብና ሰብአዊ መብታቸውን መጣስ፣
§ ማንኛውም ጾታዊ ወይም ወሲባዊ ግንኙነት መፈጸም
§ ትምህርት ሴኩላር በመሆኑ በት/ቤት ግቢ ውስጥ ሀይማኖታዊና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማካሄድ፣
§ በማንኛውም የቡድን ጸብ እና አምባጓሮ ተግባር ላይ መሳተፍ ፣
§ ከኢትዮጵያዊ እሴቶች ያፈነገጡ እና ህጋዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን እና በዓላትን ማክበር እና መፈጸም ለምሳሌ /ዋተርዴይ፤ክሬዚ ዴይ፤እራቁት ቀን ከለር ዴይ ወዘተ…/
§ በት/ቤቱ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም በአካልና በጤና ላይ ጉዳት የሚያደርስ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት፣
§ የት/ቤቱን ንብረት ሆን ብሎ ለጉዳት ማጋለጠ፣
§ በት/ቤት ውስጥና አካባቢ ሴት ተማሪዎችን መድፈር፣
§ በፈተና ወቅት ለሌላ ተማሪ መፈተን ወይም ለራስ ማስፈተን፣
§ የተጭበረበረ የትምህርት ማስረጃ አቅርቦ መገኘት፣
§ መምህራንና የትምህርት ቤቱን ሠራተኞች መደባደብ
የኮልፌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
መልካም የትምህርት ዘመን… 2019 ዓ.ም
ለኮልፌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የቀንና የማታ ተማሪዎች በሙሉ
የት/ቤቱ መልእክት
ውድ ተማሪዎች እንኳን ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!!
በ2019 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሂደቱ ውጤታማ በሆነ አግባብ እንዲከናወን ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት የተጠናከረ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤በመሆኑም ት/ቤት የነገ አገር ተረካቢ ትውልድ የሚቅረጽበት ትልቅ ተቋም ስለሆነ ቅርብ ክትትል ይፈልገዋል፤የት/ቤቱ ራዕይና ተልእኮ እንዲሳካ ለማድረግ የተማሪዎችን የት/ቤት ቆይታ የተከለከሉና የተፈቀዱ ጉዳዮች እንዲሁም መብትና ግዴታን ማሳወቅ ስለሚያስፈልግ ከዚህ በታች የተገለጹትን የት/ቤቱ መተዳደሪያ ደንብና ተቋማ መገለጫዎችን ማወቅና ሳይሸራረፉ መተግበር ያስፈልጋል፡፡
ለወላጆች፡-
የተከበራችሁ ወላጆች ማንኛውም ሰው ከልጁ በላይ የሚወደው ነገር የለም ይህን የሚወደውን ሰብዓዊ ፍጡር ትልቅ እምነት በማድረግ ያሰረከባችሁት ለት/ቤት ስለሆነ እኛም ትልቅ አደራ አለብን ፤ስለዚህ የተሰጡንን ውድ ሰብዓዊ ፍጡር ለነገ ትርጉም ባለው ሁኔታ ለመቅረጽ እንድንችል በት/ቤት ቆይታ ተማሪዎች መተግበር ያለባቸውንና የተከለከሉ ጉዳዮችን አውቃችሁ የቅርብ ክትትል በማድረግ እገዛ እንድታደርጉ በታላቅ አክብሮት ለመጠየቅና ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
የተማሪዎች ግዴታዎች
1. ፕላዝማ በተመለከተ
Ø ማንኛውም የት/ቤቱ ተማሪዎች ፕላዝማውን የመጠበቅ የመንከባከብ የፕላዝማ እቃዎቹ እንዳይሰርቁ ከተሰረቁ ሌባውን የመጠቆም ፕላዝማ ለታለመለት እንዲውል የማድረግ ግዴታ አለበት ፡፡ ይህ ባይሆን ግን የጠፋውን የፕላዝማ እቃ የመተካት ፓላዝማውን የማስጠገን ግዴታ አለበት፡፡
2. የክፍል አያያዝና ንብረት አጠባበቅ በተመለከተ
Ø ተማሪዎች የሚማሩበትን ንብረት፡- መጽሐፍ፣ ፕላዝማ፣ወንበር፣ጠረጴዛ፣ በሮች፣መስኮቶች፣ ግድግዳዎች አፀያፊ ፅሁፍ እንዳይፃፍባቸውና ጉዳት እንዳይደርሰባቸው ንብረቶችን እንደራስ የመጠበቅ የመንከባከብ ግዴታ አለበት፡፡ ጉዳት ያደረሱት ሰዎች ለህግ የማጋለጥ ግዴታ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ንብረቶችን የመተካት ግዴታ አለበት፡፡
3. የት/ት ሰዓት አከባበርን በተመለከተ
ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች ወደ ት/ቤቱ ሲመጡ የመግቢያ ሰዓቱን የማክበር ግዴታ አለባቸው፡፡
ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች የሙሉ ቀን ትምህርት የመከታተል ግዴታ አለባቸው፡፡
ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች ጠዋት ተገኝቶ ከሰዓት ቢቀር እንደሙሉ ቀን ቀሪ ተቆጥሮ ከት/ቤቱ ይሰናበታል፡፡
ማንኛውም ተማሪ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከቀረ ወላጅ ሳያቀርብ መግባት አይችልም፡፡
4. የደንብ ልብስንና የፀጉር አያያዝን በተመለከተ
Ø ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች የት/ቤቱን የደንብ ልብስ/ዩኒፎርም/ ት/ቤቱ በሚያወጣው ህግ መሰረት አሟልቶ የመልበስና የመማሪያ ቁሳቁስ የመያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡
Ø የት/ቤቱ ሴት ተማሪዎች ሚኒ፣ ታይት፣ ጥላ ቅድ ስፌት፣እጀ ሙሉ ሹራብ መልበስ ፤በዩኒፎርም ላይ ሌሎች አልባሳትን ከላይ መደራረብ ፣ ፀጉር በዊግ መሰራት ፣ በክር መስራት፣ ፀጉር ቀለም መቀባት፣የተከለከለ ነው፡፡
Ø ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች /ወንድ ተማሪዎች በት/ቤቱ የተሰጣቸውን ዩኒፎርም ሱሪ ጠባብ / ሲኪኒ/ ሱሪ ያለማድረግ፣ የጆሮና ሌሎች ጌጣጌጦችን፣ ሀይማኖታዊ ይዘት ያላቸውን ነገሮች ያለማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡
Ø ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች /ወንድ ተማሪዎች/ ፀጉር የማሳጠር፣ ፀጉሩን ከሚገባው በላይ አሳድጎና የተለየ አይነት ቀለም ተቀብቶና የጸጉር ስታይል ተቆርጦ መግባት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
Ø ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች በት/ቤት ሰዓት ውጪ የት/ቤቱን የደንብ ልብስ ለብሰው በግቢ ውጪ መዘዋወር የተከለከለ ነው/በትምህረት ስዓት በትምህርት ቀናት/
Ø ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች የት/ቤቱ መታወቂያ መያዝና ለግቢዎ ሰራተኛ በተጠየቀ ጊዜ ማሳየትና መስጠት ግደታ አለባቸው፡፡
Ø ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች የመማሪያ መጻህፍት በክፍል ውስጥ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለባቸው፡፡
Ø ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች የተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ የተቀየሰውን ስትራቴጂ/ የቅዳሜ ማጠናከሪያ ትምህርት የመማር እንዲሁም ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ጠዋት/ሰኛ እሮብ እና አርብ ከ1፡00 እስከ 2፡00 በጥናት ፕሮግራም መሳተፍ፤ ማክሰኞ እና ሐሙስ ከትምህርት ስዓት በኋላ ከ9፡00 እስከ 11፡00 በቡድን የማጥናት ግዴታ አለባቸው፡፡
የት/ቤቱ መታወቂያ መያዝና ለግቢዎ ሰራተኛ በተጠየቀ ጊዜ ማሳየትና መስጠት ግደታ አለባቸው፡፡
5. በዓላትን በተመለከተ
o ማንኛውም የት/ቤቱ ተማሪ በት/ቤቱ እንዲያከብሩ የሚፈቀዱ በዓላትን ብቻ የሚያከብሩ ይሆናሉ፡፡
o ማንኛውም የት/ቤቱ ተማሪ መጤና የባህል ወረርሽኝ የሆኑ እሴት የማይጨምሩ የሆኑ እንደ ከለር ደይ በዓላትም የውሃ ቀን፣ የስጦታ ቀን፣ ክሬዚ ደይ ወዘተ ሆነ ሌሎች ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸውን በአላት በትምህርት ቀንም ሆነ ከትምህርት ሰዓት ውጪ በት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ማክበር ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
6. የሰንደቅ ዓላማ አከባበርን በተመለከተ
Ø ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች በሰንደቅ ዓላማ ስነ - ስርዓት (2፡00) ላይ የመገኘት፣ ስርዓቱን የማክበር፣ የመዘመርና ሰንደቅ ዓላማው በሚወጣበት ጊዜ ባሉበት የመቆም ግዴታ አለበት፣
7. ሞባይልና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች በተመለከተ፣
Ø ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች ት/ቤት ግቢ ውስጥ ሲገቡ ሞባይል ይዞ መግባት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
Ø ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች በትምህርት ሰዓትም ይሁን ከትምህርት ሰዓት ውጭ በት/ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በግልም ይሁን በቡድን ስልክ ማውራት ጌም መጫወት፣ ሀይፓድ፣ ኤርፎን ወዘተ ይዞ ከተገኘ ንብረቱ ለት/ቤቱ ገቢ ሆኖ በተማሪዎች የዲስፕሊን መመሪያ መሰረት ተጠያቂ ይደረጋሉ፡፡
8. በአጥር መዝለልን በተመለከተ
Ø ማንኛውም የት/ቤቱ ተማሪ በትምህርት ሰዓትም ይሁን ከትምህርት ሰዓት ውጪ በአጥር የገባ/የወጣ ከሆነ ለት/ቤት ዲስፕሊን ኮሚቴ ቀርቦ ከት/ቤት ይሰናበታል በህግም ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
9. ኃይማኖት በተመለከተ
Ø ማናቸውም የት/ቤቱ ተማሪዎች ት/ቤት ከሀይማኖትና ከፖለቲካ እንዲሁም ብሔር ተኮር ከሆኑ ጉዳዮች ተጽእኖ የፀዳ መሆኑን የማወቅና የመተግበር ግዴታ አለባቸው፣ይህን ተላልፎ የተገኘ ተማሪ በት/ቤቱ የተማሪዎች የዲስፕሊን መመሪያ ከመጠየቅ ባሻገር ከት/ቤቱ ጋር በትስስር በሚሰሩ የህግ አካላት የሚጠየቅ ይሆናል፡፡
Ø ማንኛውም የት/ቤቱ ተማሪዎች ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ማንኛውም ኃይማኖታዊም ሆነ ፖለቲካዊ ስርዓት ማከናወን አይችልም፡፡ በዕረፍት፣ በምሳ ሰዓት- በት/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን በመሆን መሰበክ ቀስቃሽ ጉዳዮችን ማራመድ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
10. የተማሪዎች መብት
Ø በተገቢው የመማር መብት
Ø የመጠየቅ መብት
Ø የትምህርት ቤቱን ንብረት የመጠቀም/ Linratory, bayberry/ እና የመሳሰሉት/
Repost from Ministry of Education Ethiopia
ማስታወቂያ
በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስክ ምርጫ ማጠናቀቂያ ቀን እስከ መስከረም 5 ቀን የተራዘመ መሆኑን እንገልጻለን።
ስለሆነም በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን ምርጫችሁን ያላስገባችሁ ተማሪዎች በ https://student.ethernet.edu.et ድህረ ገጽ በመግባት የራሳችሁን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም ምርጫችሁን እንድታጠናቅቁ እናሳውቃለን።
Repost from Kolfe education official channel🇪🇹
#MoE
የ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ወስደው በመደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን ከነሐሴ 28 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ እንዲያስገቡ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ተማሪዎች ምርጫቸውን ትምህርት ቤት መሄድ ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ሆነው በኦንላይን ማስገባት ይችላሉ።
የምርጫ ማስገቢያ ድረ-ገጹ፦ student.ethernet.edu.et ነው።
- በሕክምና ምክንያት ልዩ ሁኔታ ያላቸው፣
- የአካል ጉዳተኛ የሆኑ፣
- ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች
- ከ6 ወር በታች ሕፃን የሚያጠቡ እናቶች ተገቢውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ እንደሚጠበቅባቸውም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
https://t.me/kolfekeranioeducationbureau
ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎች አጥጋቢ ውጤት አምጥተዋል – ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ የትምህርት ፕሮጀክቶችን እውን ማድረጉን የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው 33ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ፣ በመዲናዋ ያለፉትን የትምህርት ስትራቴጂዎችን በማሻሻል በአዲስ ስትራቴጂ የሚመራበት ዓመት መሆኑ የዘንድሮውን ጉባኤ ለየት ያደርገዋል ብለዋል።
ባለፉት ጊዜያት ተረባርበን በሰራንባቸው የትምህርት ዘርፎች ላይ ውጤት ተመዝግቧል ያሉት የቢሮ ኃላፊው ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) ፣ በዚህም የተማሪዎች ውጤት ላይ ፣ የትምህርት ቤቶች ደረጃ እና የአመራሩና የትምህርት ባለሙያው የጋራ ውህደት የተረጋገጠበት ሆኗል ብለዋል።
ከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ የትምህርት ፕሮጀክቶችን እውን ማድረጉን ገልጸው ፣ በዚህም በትምህርት ዘርፍ ውጤት እየመጣ ይገኛል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በመዲናዋ ቀደም ሲል በደረጃ 4 ምንም የመንግስት ትምህርት ቤት ባልነበረባቸው አካባቢዎች ጭምር አሁን ላይ 23 ትምህርት ቤቶች መድረሳቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ከቀዳማይ ልጅነት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ድረስ የሰጠው ትኩረትና እያከናወነው ያለው ተግባር ለዘርፉ ሰፊ የቤት ስራ የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ፤ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠልና የበለጠ ከፍ ለማድረግ የሁሉም አካል ርብርብ እንደሚጠይቅ አሳስበዋል።
ይህ ጉባኤ በቀጣይ በትምህርቱ ዘርፍ ለሚከናወኑ ተግባራት በርካታ መሰረት የሚጥል ስለመሆኑም ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር)አብራርተዋል።
Repost from INFO TECH CRYPTO
#ጥቆማ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ-ምረቃ መደበኛ መርሐግብር (በመንግሥት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሐግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።
መስፈርቶች
➻ በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ወይም ደረጃ 4 አጠናቀው (COC) ያለፉ
➻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (UAT) ይወስዳሉ
የምዝገባ ጊዜ 👇
እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ድረስ
ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://admission.aau.edu.et
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና (UAT) ከጳጉሜን 02-04/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ
===============================
በአገራችን እየተመዘገበ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠልና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የአገሪቱን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ለማሟላት በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡
ይህንንም እውን ለማድረግ ልዩ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የተደራጁትን የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ማዕከላት በማድረግ በዘርፉ ብቃት ያላቸውን ሙያተኞችን እያፈሩ ይገኛሉ፡፡
በመሆኑም በ2019 ዓ.ም የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና ኦንላይን (Online) በመስጠት መቀበል ይፈልጋሉ፡፡
የትምህርት መስኮች፡-
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
ኢንጂነሪንግ
- አርክቴክቸር
- ሲቪል ኢንጂነሪንግ
- ወተር ሪሶርስ ኢንጂነሪንግ
- ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
- ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ማቴሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሪካል ፓወር እና ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሮኒክስ እና ኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪንግ
- ኮምፒዩተር ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
- ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ
አፕላይድ ሳይንስ
- አፕላይድ ባዮሎጂ
- አፕላይድ ኬሚስትሪ
- ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
- ፋርማሲ
- አፕላይድ ፊዚክስ
- አፕላይድ ጂኦሎጂ
- አፕላይድ ማቲማቲክስ
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
ኢንጂነሪንግ
- አርክቴክቸር
- ሲቪል ኢንጂነሪንግ
- ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
- ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሮሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ
- ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ
አፕላይድ ሳይንስ
- ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
- ፉድ ሳይንስና አፕላይድ ኒዩትሪሽን
- ጂኦሎጂ
- ባዮቴክኖሎጂ
የምዝገባ ጊዜ፡-
- ከነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት ይሆናል፡፡
የምዝገባ ቦታ፡
- የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ https://stu.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et; www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡- በድህረ ገፃችን የምዝገባው ቀን ካበቃበት በኋላ እናሳውቃለን ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-
- በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
· የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ይህንኑ አውቃችሁ ቅድሚያ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
· በቂ አመላካቾች የሌሉባቻው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡
· ለፈተና የሚቀርቡት የአመልካቾች ስም ዝርዝራቸው እና የፈተና ጣቢያዎች በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡- www.aastu.edu.et ; www.astu.edu.et እንደአመቺነቱም በe-mail የሚገለፅ ይሆናል፡፡
· አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም (ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡
· ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡
· አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
· የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡
· በውጤታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከላይ በተጠቀሱት ድህረ-ገፆች ይገለፃል፡፡
· በመስፈርቱ መሰረት ያልተመረጡ አመልካቾች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ይሆናል፡፡
· በፈተናው ዕለት ማንኛውንም የሞባይል ስልኮችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
· በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ከታች የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች እና ቴሌግራም ቻናላችንን መጎብኘት ይቻላል፡፡
www.astu.edu.et; www.aastu.edu.et
Telegram:https://t.me/AdamaSTU_ASTU
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ-ምረቃ መደበኛ መርሐግብር (በመንግሥት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሐግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።
መስፈርቶች
➻ በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ወይም ደረጃ 4 አጠናቀው (COC) ያለፉ
➻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (UAT) ይወስዳሉ
የምዝገባ ጊዜ 👇
እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ድረስ
ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://admission.aau.edu.et
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና (UAT) ከጳጉሜን 02-04/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
ማስታወቂያ
ለ2018ዓ ም 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ለተፈተናችሁ ተማሪዎች
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በተመለከተ የባዮሎጂ እና አፕትቲውድ ውጤት 00 የሚል ካለ እንድታረጋግጡ እና መረጃውን በወቅቱ ለት/ቤቱ በአስቸኳይ እንድታሳውቂ እናሳስባለን ፡፡
