My youth age for christ GOSPEL MINISTRY! ወጣትነቴን ለክርስቶስ!!🇪🇹🇪🇹
رفتن به کانال در Telegram
ወጣትነቴን ለክርስቶስ የታዳጊዎችና የወጣቶች የወንጌል አገልግሎት 👉ወጣቶችንና ታዳጊ ወጣቶችን ስለወንጌል እውነት ያስተምራል!! እንዲሁም ለታዳጊ ወጣቶች ሁለንተናዊ የሆነ ስልጠና ይሰጣል!! 👉ከተማሪዎች ጋር በመሆን በትምህርት ቤቶች ወንጌልን እንሰራለን።
نمایش بیشتر678
مشترکین
+124 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+1130 روز
آرشیو پست ها
🩸ኃጢአትህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላህ/ሽ አያደርግህም…
👉ብዙዎቻችሁ እግዚአብሔር የሚወደው ወደፊት የምትሆኑትን ማንነታችሁን እንደሆነ ታምናላችሁ—ያንን ፈተና በመጨረሻ አሸንፎ ተደጋጋሚ ቃሉን ማጠፍ ያቆመውን ሰው።
ነገር ግን አሁን ስላላችሁበት ማንነታችሁስ ምን ይባላል? በውስጥ ለውስጥ እየታገለ ስላለው ማንነታችሁስ?
አንዳንዴ እግዚአብሔር ስለ እኛ ያለው ስሜት እኛ ስለራሳችን ከምናስበው ጋር አንድ እንደሆነ እንገምታለን። በራስህ/ሽ ተስፋ ስለቆረጥክ እግዚአብሔርም ተስፋ የቆረጠብህ ይመስልሃል። በመታገልህ ሰልችቶሃል፣ ስለዚህ እርሱም አንተን መስማት የሰለቸው ይመስልሃል።
የበደል ስሜት ወደ እፍረት የሚቀየረው እንደዚህ ነው። "ስህተት ሠርቻለሁ" የሚለው ሀሳብ ወደ "እኔው ራሴ ችግር አለብኝ" ይለወጣል።
የጴጥሮስ ታሪክ በምንወድቅበት ጊዜ የእግዚአብሔር ፍቅር ምን እንደሚመስል ያሳየናል። ኢየሱስ ጴጥሮስ እንደሚክደው ያውቅ ነበር፤ ሆኖም «እምነትህ እንዳይጠፋ እኔ ስለ አንተ ለመንሁ» አለው (ሉቃስ 22:32)። ጴጥሮስ እጅግ ድካም ወደሞላበት ቅጽበት ከመድረሱ በፊት፣ ኢየሱስ አስቀድሞ ይጸልይለት ነበር። ኢየሱስ የጴጥሮስን ክደት አልደገፈውም፣ ነገር ግን በክደቱ ምክንያት አልተወውም።
«በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና…» (ዮሐንስ 3:16)። የእግዚአብሔር ፍቅር ማዳን ወደሚያስፈልገው ዓለም ኢየሱስን እንዲልክ አነሳሳው። ፍቅሩን መቀበል ለመጀመር የግድ የተሻለ የራሳችሁ ምስል (version) መሆን አይጠበቅባችሁም። ከእግዚአብሔር ፍቅር ውጪ ያደረገኝ ብላችሁ ባሰባችሁት በዚያው መታገላችሁ/ውድቀታችሁ ወደ እርሱ መምጣት ትችላላችሁ።
የእግዚአብሔር ፍቅር ንስሐ መግባትን አያስቀርም። ይልቁንም ከመሸሸግ ይልቅ ወደ እርሱ እንድትመለሱ ምክንያት ይሆናችኋል። ከምህረቱ አቅም በላይ እንደሆናችሁ ሳታስቡ፣ ኃጢአታችሁን በቁም ነገር መመልከት ትችላላችሁ።
በኃጢአታችሁ ወይም በውድቀታችሁ ምክንያት መወደድ እንደማይገባችሁ ከተሰማችሁ፣ አሁን ስላላችሁበት ሁኔታ ለእየሱስ እውነቱን በመናገር ጀምሩ።
«ጌታ ሆይ፣ ወድቄአለሁ፤ እርዳታህም ያስፈልገኛል። ይህንን ደብቄ መኖር አልፈልግም።»
እግዚአብሔር የሚወደው ሁሉንም ነገር አስተካክሎ የጨረሰውን የነገ ማንነታችሁን ብቻ አይደለም። አሁንም ይወዳችኋል፤ እየለወጣችሁ አብራችሁት እንድትመላለሱ ይበጃችኋል። ሕይወታችሁ ውስጥ እጅግ የምታፍሩበትን ክፍል ወደ እርሱ አምጡት። ዛሬ ወደ እርሱ የምትመለሱበት ቀን ይሁን።
ደጁ እንዴት አስፈሪ ነው
በኃያሉ ክንድህ መታመን ላቃተው
ቀኖቹ እንዴት ክፉ ናቸው
በጥላህ ስር ላልተሸሸገው ሰው
አድነኝ🙏
📖እግዚአብሔር ያያል!
👉ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ በእናንተ ላይ የሚሆን ነገር ያለም ያያል ልባችሁን ያያል እንባችሁን ያያል ሀዘናችሁን ያያል የምታልፉበትን ያያል ሚደረግባችሁን ያያል ይመለከታል ጌታ።
👉ባይመስልም እራሱ እግዚአብሔር ያያል በእግዚአብሔር መስመር ትክክለኛ መንገድ ላይ ሁን እንጂ ጌታ ያያል ቆየ ማለት አላየም ማለት አይደለም እየመረ ነው! እየተዋበ ነው ብቻ ትክክለኛው አቅጣጫ ላይ መሆንህን እርግጠኛ ሁን እንጂ የማያይ መሰለህ እንጂ እግዚአብሔር ያያል!
👉በሰዎች ሁሉ ላይ ከደረሰው የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ስለዚህ ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አይተዋችሁም፤ ነገር ግን በምትፈተኑበት ጊዜ ፈተናውን መታገሥ እንድትችሉ፣ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።
1 ቆሮንቶስ 10:13
👉ምክንያቱም የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤
ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤
የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።
1 ጴጥሮስ 3:12
👉ምሕረት፣ ሰላምና ፍቅር ይብዛላችሁ።
ይሁዳ 1:2🙏
የተወደደው ፀሐፊ እና ቃለ እግዚአብሔር አስተማሪ የሆነው ወንድማችን አምሳሉ ዳንኤል(ወንዴ) እግዚአብሔር ረድቶት "ምስጢራዊ ስፍራ" የተሰኘ መንፈሳዊ መጽሐፍ የጻፈ ሲሆን፥ መጽሐፉ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በፍና ቃ/ሕ/ቤተ /ያን በጥዋት እና ከሰዓት መርሀ ግብር ይመረቃል
በምርቃቱ ዕለት ከወንድማችን ጋር መጽሐፉን በማስመረቅ ጌታን እንድታመሰግኑ ተጋብዛችኋል ።
#MistrawiSifra
#AmsaluDanielWonde
#BookInauguration
#MistrawiSifraBook
#EthiopianSpritualBook
#AmsaluDaniel
#MistrawiSifra2026
የተወደደው ፀሐፊ እና ቃለ እግዚአብሔር አስተማሪ የሆነው ወንድማችን አምሳሉ ዳንኤል(ወንዴ) እግዚአብሔር ረድቶት "ምስጢራዊ ስፍራ" የተሰኘ መንፈሳዊ መጽሐፍ የጻፈ ሲሆን፥ መጽሐፉ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በፍና ቃ/ሕ/ቤተ /ያን በጥዋት እና ከሰዓት መርሀ ግብር ይመረቃል
በምርቃቱ ዕለት ከወንድማችን ጋር መጽሐፉን በማስመረቅ ጌታን እንድታመሰግኑ ተጋብዛችኋል ።
#MistrawiSifra
#AmsaluDanielWonde
#BookInauguration
#MistrawiSifraBook
#EthiopianSpritualBook
#AmsaluDaniel
#MistrawiSifra2026
_መኖር_የማልችልው_ያላንተ_ነው_ዘማሪ_ሳሙኤል_SINGER_SAMUEL_@MARSILTVWORLDWIDE_@.m4a29.77 MB
ሊመጣ_ነው_ዘማሪት_ዘመናይ_ጎሳዬ_አዲስ_ዝማሬ_Limeta_New_Zemenay_Gosaye48k.mp35.39 MB
የተወደደው ፀሐፊ እና ቃለ እግዚአብሔር አስተማሪ የሆነው ወንድማችን አምሳሉ ዳንኤል(ወንዴ) እግዚአብሔር ረድቶት "ምስጢራዊ ስፍራ" የተሰኘ መንፈሳዊ መጽሐፍ የጻፈ ሲሆን፥ መጽሐፉ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ፋና አጥቢያ ቃለ-ህይወት ቤተ ክርስቲያን በይፋ ይመረቃል።
በዕለቱ ከወንድማችን ጋር ጌታን እያመሰገንን፤ መጽሐፉን በማስመረቅ፤ የየራሳችንን ኮፒ አስፈርመን እንድንወስድ ተጋብዛችኋል።
#MistrawiSifra
#AmsaluDanielWonde
#BookInauguration
#MistrawiSifraBook
#EthiopianSpritualBook
#AmsaluDaniel
#MistrawiSifra2026
አንተ ለብቻህን እንድትደመጥ
የስጋዬ ጩኸቱ እረጭ ይበል ፀጥ
አንተ ለብቻህን እንድትደመጥ
የምኞቴ ጩኸቱ እረጭ ይበል ፀጥ
ተናገር🙏
🎙ስጋህ/ሰውነትህ የዲያብሎስ ርስት አይደለም።
አጋንንት ከጥላ ስር ሆነው በሹክሹክታ ብቻ ለመናገር አይረኩም። እረፍት የሌላቸው፣ ረሃብተኞችና ጥገኛ ፍጥረታት ናቸው።
ልብ ወለዱ "ቨነም" እንደሚለው ሁሉ፣ እነርሱም፡ "መግበኝ። አካል ስጠኝ። ማደሪያ ሁነኝ" እያሉ ይጮኻሉ።
ኢየሱስ እንዲህ ሲል አስጠንቅቋል፡ "ርኩስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ፡ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፡ አያገኝምም።" (ማቴዎስ 12:43-45)
👉አጋንንት ድርቀትን/ውኃ አልባ ቦታን ይጠላሉ። ማደሪያ ያጡ መንፈሶች በመሆናቸው በሰው ውስጥ ለማደር ይጓጓሉ። ሰዎችን ለመያዝ የሚጠባበቁ "ቤቶች" አድርገው ያዩአቸዋል።
ያለ አሰፋሪ/ማደሪያ ሰውነት ይኮማተታሉ። ማደሪያ ሲያገኙ ግን ይለመልማሉ። ሰው ይቅርና የእሪያ መንጋ እንኳ ለማደር ያገኙትን ማንኛውንም ነገር ይወስዳሉ። (ማቴዎስ 8:31)
👉አጋንንት ገላጭ/አስመሳይ ቅጂዎች ናቸው። እግዚአብሔር ለማዳን የሚያደርገውን ነገር፣ እነርሱ ለማጥፋት ይገለብጡታል።
🙌እግዚአብሔር ለማደስ/ለመለወጥ ያድራል፤ አጋንንት ግን ለማበላሸት ያድራሉ።
እግዚአብሔር ሌሎችን እንድትባርክ ይሞላሃል፤ አጋንንት ግን ሌሎችን እንድትሰብራቸው ይሞሉሃል።
👹በጋኔን መያዝ ማለት በሰማይ የጥበብ ሥራ ላይ የሲኦል ግድግዳ ላይ የሚሳል ሕገ-ወጥ ስዕል (ግራፊቲ) ማለት ነው። እግዚአብሔርን ማበላሸት ስለማይችሉ የእርሱን መልክ ያዘዙትን ሰዎች ያበላሻሉ።
🥹አንተን ማሰቃየት ብቻ አይደለም የሚፈልጉት፤ ለሌሎችም የማሰቃያ መሣሪያ ሊያደርጉህ ይፈልጋሉ።
👿እኩይ አላማውን ለማስፈጸም አካል ስለሚያስፈልገው ሰይጣን ወደ ይሁዳ ገባ። (ሉቃስ 22:3)
⚡️ነፃ መውጣት (Deliverance) ማለት ከአንድ ቤት ማባረር ማለት ነው። አጋንንትን ቤት አልባ ያደርጋቸዋል። ኢየሱስ ወደ መቅደሶች በመግባት የማይገባውን ነገር ሁሉ አውጥቶ ይጥላል። (ማቴዎስ 21:12-13)
አንተ የጨለማ ጉድጓድ እንድትሆን አልተፈጠርክም። የእግዚአብሔር ማደሪያ እንድትሆን ተፈጥረሃል።
🕊ነፃ መውጣት ቤቱን ባዶ ያደርገዋል፤ ደቀ መዝሙርነት/ትምህርት ግን ተሞልቶ እንዲኖር ያደርገዋል።
👉ኢየሱስ ማደሪያውን እንዲይዝ ፍቀድለት። አጋንንትን ቤት አልባ አድርጋቸው። ሕይወትህም እንደገና የጸሎት ቤት ይሁን።
ራስን መግዛት!
ራስን መግዛት (Self-Restraint) ማለት ፍላጎቶቻችንን፣ ስሜቶቻችንን፣ ምርጫዎቻችንን እና ድርጊቶቻችንን መቆጣጠር ነው፤ ይህም ለጊዜያዊ ደስታዎች ወይም ለድንገተኛ ፍላጎቶች ባሪያ እንዳንሆን ይረዳናል።
ራስን መግዛት መጥፎ ነገሮችን ብቻ መራቅ አይደለም፤ ይልቁንም ዓላማችንን፣ እሴቶቻችንን እና ወደፊት ያለንን ሕይወት የሚጠብቁ ምርጫዎችን በአስተዋይነት መምረጥ ነው።
1. መሄድ የሌለባችሁ ቦታ አትሂዱ
ብዙ ሰዎች የሚወድቁት ለመውደቅ አስበው ሳይሆን፣ ራሳቸውን ወደ የተሳሳተ አካባቢ በመውሰድና ተጋላጭ በመሆን ነው፡፡
2. መገናኘት የሌለባችሁን ሰው አታግኙ
ሁሉም ሰው ከእናነተ አመለካከት፣ እሴትና የሕይወት ልህቀት ጋር የሚመጥን ስላልሆነ መሰናክል ሊሆንባችሁ ይችላልና የምታገኙትን ሰው ምረጡ፡፡
3. የሚሰማችሁን ሁሉ አትናገሩ
ራሱን መግዛት የለመደ ሰው የሚናገረው ነገር መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል ስለሚያውቅ አንደበቱንም መቆጣጠር የሚችል ሰው ነው። የመጣለትንና ያሰበውን ሁሉ አይናገርም፡፡
4. ፍላጎታችሁን ሁሉ ወደ ውሳኔ ደረጃ አትውሰዱት
ፍላጎት ስሜት ነው፤ ውሳኔ ግን ሊታሰብብት የሚገባ እርምጃ ነው፡፡ ራሱን የሚገዛ ሰው አንድን የፈለግነውን ነገር ወደ ውሳኔ ከመውሰዱ በፊት በሚገባ ያስብበታል፡፡
5. ወደ ሕይወታችሁ የሚገቡትን ተቆጣጠሩ
የመጣ ሰው ሁሉ እና ያገኛችሁት እድል ሁሉ ወደ ሕወታችሁ መግባትና ስፍራ ማግኘት የለባቸውም፡፡ የግል ድንበርና መስመር ይኑራችሁ፡፡
Dr. Eyob Mamo🎙
መዳፉ ላይ ቁስል ካያችሁ
የህማም ሰው ካስተዋላችሁ
ውዴ እርሱ ነው ነፍሴን የያዛት
በእንቁ ሳይሆን በደም የገዛት
ጌታ ኢየሱስ ❤🙏
+1
"የእግዚአብሔር ኪዳን ምስጢር" በሚል ርዕስ በምህረቱ እንድርያስ የተጻፈው መጽሐፍ በውስጡ በርካታ መንፈሳዊ ዕውቀት የያዘ ስለሆነ መጽሐፉን አንብባችሁ እንድትጠቀሙበትና ጸሐፊውንም በርታ ቀጥል በማለት ከጎኑ እንድትቆሙለት እጠይቃችኋለሁ።
🎙መጋቡ ኤልያስ መና
የሶዶ ከተማ ቃ/ሕ/አ/ቤ/ሕብረት ዋና ጸሐፊ
"እግዚአብሔር ምትሃታዊን ሳይሆን
ልምምዳዊ ቅድስና ይፈልጋል።"
እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥7
Tsegawu Endrias🎙
📖 “የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል።” ምሳሌ 14፥15
👉ምርጫው ያንተ ነው ወዳጄ፣ ንግግሩን አሳምሮና መንፈሳዊ አስመስሎ በልብህ ትልቅ ስፍራ ያለውን ሰው ነው እየተከተልክ ያለሄው ወይስ
👉አካሄዱ፣ የነገሩ ጅማሬና መካከል በእግዚአብሔር ፊትና በቃሉ ውስጥ ትክክል የሆነን ሰው የምትመለከተው ❓
🔥እግዚአብሔር ውጤትን ሳይሆን መንገድን ነው የሚመለከተው🙏
MYAFC✝
ፀጋውን እንጂ ጽድቄን አልቆጥር
ከሰጠኝ በላይ ምንም አልጨምር
የማልጠቅም ባሪያ ታሪክ የሌለው
አንድ ነገር ግን አውቃለው.......
ኢየሱስ እንዳዳነኝ!!!😇
ፍቅርህ_ብዙ_ነው_የኔ_ጌታ_ዘማሪ_እዝራ_ንጉሴ_FIKREH_BIZU_NEW_YENE_GETA_EZRA_NIGUSSE256k.mp37.85 MB
ዝም በሉ!
ሁለት ሰዎች መግባባት እንዲችሉ ሁለቱ እኩል አያወሩም አንዱ ዝም ብሎ ሌላውን ማዳመጥ አለበት። እኛም ዛሬ ለእግዚአብሔር ምናወራው በዝቶብን ምናልባት ከእግዚአብሔር መስማትን ትተን እንዳይሆን የኛን ነገር ብቻ ነግረነው የእርሱን ሳንሰማ እንዳንቀር አሁን ዝም እንበልና እርሱን እንስማ። በዝምታ ውስጥ እግዚአብሔርን መስማት አለ እግዚአብሔርን በመስማት ውስጥ ዕረፍት፣ሰላም፣ደስታ አለ።
ምሳሌ1:33የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።
