cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

መንፈሳዊ ትምህርት | eotc theology

Eotc theology... ዘውትር ከሰኞ - አርብ በመርሐግብሩ #ተከታታይ ትምህርት በፅሁፍ #live ትምህርት #መዝሙር #ወቅታዊ ጉዳዮችን እንዳስሳለን

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
5 432
مشترکین
-224 ساعت
+107 روز
+9730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

___,__,_,___ 3ኛ-ኮርስ ክርስቲያናዊ ሕይወት እና ሥነ-ምግባር #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን🙏🌹🌹🌹 ◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆ ፩.፮.፬, #ትእዛዝ-❹-አባትህን እና እናትህን አክብር 🔷ይህች ትእዛዝ ከሌሎች በተለየ መልኩ የተነገረች ትእዛዝ ናት። 🔷በመጽሐፍ ቅዱሱ ቃል "አባትህን እና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር እድሜህ እንዲረዝም" ዘጸ 20፥12) በማለት ይገልጻል። 🔷ምንም እንኳን ሰውን የሚፈጥረው እግዚአብሔር ቢሆንም እናትና አባት በሰው ልጅ መፈጠር ሂደት ውስጥ ድርሻ እንዲኖራቸው አድርጎ ፈጥሮናል። 🔷ስለዚህ እናትና አባት የአንድ ቤተሰብ መሠረት ናቸው ቤተሰብ ከለለ ደግሞ ሕዝብ አይኖርም ሕዝብ ከሌለ አገር አገር አይኖርም። 🔷"እናትና አባትህን አክብር" የሚለው ቃል ወላጅ እናትህን እና ወላጅ አባትህን ብቻ ሳይሆን ሰጥተው ያሳደጉንን በሙሉ፣ የተነከባከቡንን፣ በመንፈሳዊ የወለዱንን፣ መምህሮቻችንን ፣ በእድሜ ሚበልጡንን...ማለቱ ነው። "እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደጠበቅሁ በፍቅርም እንደምኖር ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅር ትኖራላችሁ።" ዮሐ 15፥10) 🔷ማክበር ማለት ለእናቶቻችንና ለአባቶቻችን ሚያስፈልጋቸውን ማድረግና ማስቀደም እንዲሁም በትህትና መታዘዝ የመሳሰሉት ናቸው። ነገር ግን አምልኮተ እግዚአብሔርን በሚያስክድና ክፉ ድርጊት ውስጥ በሚያስገባ መሆን የለበትም። 🔷አባት ስንልም የአክብሮት አባቶቻችን ማለታችን እንጂ የሁሉ አስገኝ አባታችን እግዚአብሔር ብቻ ነው። "ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ አባታችሁ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነውና።" ማቴ 23፥9) 🔷"አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል" (መዝ.102፥13) እንዳለ የእግዚአብሔር አባትነት መተኪያ የሌለውና እርሱን አባት ብለን በምንጠራበት መልክ ማንንም ልንጠራ አይገባም። 🔷ከዚህ በተረፈ ግን ሰዎችን ማክበር እራሳችን ከምናገኘው ደስታ በተጨማሪ በእግዚአብሔር ፀጋ እንደሚጨመረን የታወቀ ትእዛዝ ነው። ◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆ #ቀጣይ_ትምህርታችን-->ትእዛዝ-➎-አትግደል #ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!! ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE ╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮ @dnzema @dnzema @dnzema ╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
نمایش همه...
#እየተከታተላችሁ ለነበራችሁ ቀጣይ ክፍል👇👇👇
نمایش همه...
ያሬድ ነጎድጓድን ..ከደመናት ተውሶ ዜማን ....ከመላዕክቱ ማዕድ ቆርሶ ብስራትን ...ከገብርኤል ቀንሶ የሚካኤልን ሰይፍ... ተንተርሶ ያሬድ በልሳኑ እያዜመ ...በልቡ እየተቀኘ የድጓውን ባህር ቀዝፎ...በቅኔው ማዕበል እየዋኘ ከላይ....ከመላዕክቱ ነጥቆ ምድርን ..በዜማ ሰንጥቆ በመወድሱ ጎርፍ ...አጥለቅልቆ በዝማሬው ሰረገላ ...አምጥቆ መሬት ላይ አንስቶ...ከሰማይ ያደረሰን ከመላዕክቱ ጋር አቁሙ...ግዕዝና ዕዝል ያዘመረን አራራይ ብሎ በርህራሔ...በዝማሬ ሲቃ ያስለቀሰን ያሬድ ዋይ ዜማ እያለ....ዋይታን አጥፍቶ ዋይታ ልቅሶአችን ቀይሮ...ዋይ ዜማ ዝማሬን ተክቶ እንደ መላእክቱ አርቅቆ እንደ ሰውም አድምቆ ሰማይና መሬት አስተባብሮ ከመላእክቱ ጋር ደምሮ "ሃሌ ሉያ" ብሎ አዘምሮ በዜማ ቁልፉ ከፍቶ...በቅኔው በትር ገልጦ አሳየን ከላይ እግዜርን...ከዜማ ወንበር ላይ አስቀምጦ ያሬድ ኢትዮጵያ ላይ... የቆመ የዜማ ብርሃን ሻማ ጥበብን ያገኘንበት ...የመስፈሪያው አውድማ ይህ ነው ብርሃን የአለሙ...ኢትዮጵያዊ ነው ቀለሙ ከያሬድ በተጨማሪ..."ምድራዊ መልአክ" ነው ስሙ Moges Hunyalew
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE ╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮ @dnzema @dnzema @dnzema ╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
نمایش همه...
#ግንቦት_11 #ቅዱስ_ያሬድ_ካህን_ወማኅሌታይ ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ያሬድ የተሰወረበት ነው። ይህም ቅድስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን ነው እርሱም በኢትዮጵያ አገር ከታነፁ አብያተ ክርስቲያን ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተሰበከና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት። ይህም አባ ጌዴዎን ትምህርትን ሊአስተምረው በጀመረ ጊዜ መቀበልም ማጥናትም እስከ ብዙ ዘመን ተሳነው። በአንዲት ዕለትም መምህሩ በእርሱ ላይ ተበሳጭቶ መትቶ አሳመመው። ያሬድም ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ ከዛፍ ሥር ተጠለለ። ወደ ዛፉ ላይም ትል ሲወጣ አየ ትሉም ከዛፉ እኩሌታ ደርሶ ይወድቅ ነበረ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ከአደረገ በኋላ በጭንቅ ከዛፉ ላይ ወጣ። ቅዱስ ያሬድም የትሉን ትጋት በአየ ጊዜ ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ተመልሶ አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝና እንደ ወደድክ አድርገኝ አለው መምህሩም ተቀበለው። ከዚህ በኋላ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት በአጭር ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን ተምሮ ፈጸመ ዲቁናም ተሾመ። በዚያም ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ። እግዚአብሔርም መታሰቢያ ሊአቆምለት በወደደ ጊዜ ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ላከለት እነርሱም በሰው አንደበት ተናግረውት ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእሳቸው ጋራ አወጡት በዚያም ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የሚያመሰግኑበትን ማኅሌታቸውን ተማረ። ወደ አነዋወሩ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ በአክሱም ዳር ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን በሦስት ሰዓት ገባ በታላቅም ቃል ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ የጽዮንም ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ። ዳግመኛም እንዴት እንደሚሠራት የድንኳንን አሠራር ለሙሴ አሳየው አስተማረው አለ። ይቺንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት። የቃሉንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ንጉሡም ንግሥቲቱም ጳጳሱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ የመንግሥት ታላቆችና ሕዝቡ ሁሉ ወደርሱ ሮጡ ሲሰሙትም ዋሉ። ከዚያም በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት በየክፈለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ በመጸውና በጸደይ በአጽዋማትና በበዓላት በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በዓል በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓል የሚሆን አድርጎ በሦስቱ ዜማው ሠራ ይኸውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው። የሰው ንግግር የአዕዋፍ የእንስሳትና የአራዊት ጩኸት ከዚህ ከሦስቱ ዜማው አይወጣም። በአንዲት ዕለትም ቅዱስ ያሬድ ከንጉሥ ገብረ መስቀል እግር በታች ቁሞ ሲዘምር ንጉሡም የያሬድን ድምፅ እያዳመጠ ልቡ ተመሥጦ የብረት ዘንጉን በያሬድ እግር ላይ ተከለው ከእርሱም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ያሬድም ማኅሌቱን እስከ ሚፈጽም አልተሰማውም። ንጉሡም አይቶ ደነገጠ በትሩንም ከእግሩ ላይ ነቀለ ስለ ፈሰሰው የደምህ ዋጋ የፈለግኸውን ለምነኝ ብሎ ለያሬድ ተናገረው ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ አለው። ንጉሥም በማለለት ጊዜ ወደገዳም ሔጄ እመነኲስ ዘንድ አሰናብተኝ አለው ንጉሡም ሰምቶ ከመኳንንቱ ጋራ እጅግ አዘነ ተከዘም እንዳይከለክለውም መሐላውን ፈራ እያዘነም አሰናበተው። ከዚህ በኋላም ቅዱስ ያሬድ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ፈጽሞ የከበረሽና የተመሰገንሽ ከፍ ከፍም ያልሽ የብርሃን መውጫ የሕይወት ማዕረግ የሆንሽ የሚለውን ምስጋና እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ከፍ አለ። ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ። እግዚአብሔር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቶታል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን ያሬድ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE ╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮ @dnzema @dnzema @dnzema ╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#እናቴ_ሆይ "ደስ ብሰኝ ባንቺ ደስ እሰኛለሁ፤ ባዝንም ባንቺ እፅናናለሁ፤ መከራና ችግርም ቢያገኘኝ ወዳንቺ እጮሃለሁ።" (#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ - በመጽሐፈ አርጋኖ)
نمایش همه...
4👍 2
⛪️ #ጻድቅስ ከመ በቀልት ይፈሪ #ወይበዝኀ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ ትኩላን #እሙንቱ ውሰተ ቤተ እግዚአብሔር  (መዝ/ዳዊት ፺፪ ፥፲፪) #እንኳን_አደረሳቹሁ_የእምየ_ተዋሕዶ_ልጆች     ⛪️አብነ ገብር መንፈስ ቅዱስ (፭🕯️) #አባታችን_አቡነ_ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐገራቸው ንሂሳ #ግብጽ ነው፡፡ አባታቸው #ስምዖን እናታቸው#አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ #እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ#ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች፡፡ በዚህ መሠረት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ #አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለ አባታችን ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ተነስተው #ስብሐት ለአብ #ስብሐት #ለወልድ #ስብሐት ለመንፈስ #ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል። #በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን ይመስላሉ፡፡ አባታችን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያ #262 ኖረው #በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል፡፡ #መላእክት በአክናፈ እሳት #ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል፡፡ #ለፅንሰትከ ፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በብሥራተ መልአክ #ለተፀነስነከው መፀነስና በወርኃ ታኀሣሥ ለተወለድከው ልደትህ ሰላም እላለሁ። #ክቡሩ አባት ሆይ ስለ ዓለሙ መድኃኒት ኢየሱስ #ክርስቶስ ስለ ጌትነቱ ልደት ተርሴስ ግብር እንደገበረ፤እኔም ፍጹም ልባዊ የእጅ መንሻ ወርቅ አቀርብልሃለሁ። #ለተኃፅኖትከ፥ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የቤተ ክርስቲያን መብራት የምትሆን የተመረጠች የክብርት እናትህን ጡት ባለመጥባት #በመንፈስ ቅዱስ እንክብካቤ ስለ አደግኸው አስተዳደግህ ሰላም እላለሁ።   ⛪️     #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ🕯 #ገብረ_መንፈስቅዱስ የመንፈስ ቅዱስ ሰራ ኃጢአተኛን ሁሉ ወደ ፅድቅ የምትጠራ በኃጢአት ተውጣ #ኢትዮጵያን ብታያት በባህር ውስጥ ተዘቅዝቀህ ፀለይክላት ካልማርካቸው ከአምላክ ሙግት አርባ መአልት አርባ ምሽት አጥንትህ እስኪጣበቅ ደም ያፈሰስክላት የቺ ደጓ #ምድር_ዛሬም ሀዘን ላይ ናት ዛሬም ኃጢአት ላይ ናት ከባህር ባትገባ ደግመህ ባትጋደል የተሰጠህ ኪዳነ ቃል #እናምናለን ዛሬም ይጠብቃል ጠብቀን በቃልህ እንማፀናለን አንፃን በበረከት እንዘክራለን አቡዬ አቡዬ  #እንጠራሀለን የአባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት #በረከትታቸው አይለየን       ወስብሓት #ለእግዚአብሔ    🤲           🤲           🤲 #አሜን......... 🧡 ......... #አሜን               ⊹ #አሜን        ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE ╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮ @dnzema @dnzema @dnzema ╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
نمایش همه...
5👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
"…አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።"1ኛ ቆሮ15፣20 • ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን • አሰሮ ለሰይጣን ~አግአዞ ለአዳም • ሰላም ~እምይእዜሰ • ኮነ ~ፍስሐ ወሰላም።
نمایش همه...
ዘማሪ ቴዎድሮስ ዮሴፍ ሰዉነቴ ባንተ ፍቅር ተጠምዳለች ዉለታህን እያሰበች ታለቅሳለች መከራዉ ተረሳ ትካዜ ቀረልኝ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፈጥነህ ደርሰህልኝ አዝ____ ደጅህን ለመርገጥ መንገድ ስጀምር ተፈቶ አየዋለዉ የልቤ ችግር ወዳጄና አባቴ ሚስጥሬ ተስፋዬ ቀና እድል አረከኝ በነፍስ በስጋዬ አዝ____ በሚመጥን ፊደል በሚያምሩ ቃላት ነፍሴ ትጠማለች ስምክን ለመጥራት እንባዬ ይፈሳል አንደበት ያጥረነኛል ዉለታህን ሳስብ ልቤ ቀልጥብኛል አዝ__ ልዩ ኮነክ ለኔ መተክያ የሌለክ ልጅህ ሳትሰለች ዛሬም ትሰማለክ ዚጊቲ ልገስግስ ከደጅህ ልዉደቅ ገብረሂወት እዳልኩ ዘመኔ ይለቅ አዝ_ ስለቴን ስትሰማ ሲጠብቀኝ ምልጃህ ሳጉረመርምብክ ትታገሰኛለክ የጭንቄ ማረፍያ የህመሜም ፈውስ ባርከህ እግዚአብሔር ገብረ መንፈስቅዱስ አዝ___ ልዩ ኮነክ ለኔ መተክያ የሌለክ ልጅህ ሳትሰለች ዛሬም ትሰማለክ ዝቋላ ልገስግስ ከደጅህ ልዉደቅ ገብረ ሂወት እንዳልኩ ዘመኔ ይለቅ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE ╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮ @qedusan qedusan ╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
نمایش همه...
😍 2👏 1
ዳግማይ ትንሳኤ ማለት ዳግም መነሳት (ሁለተኛ መነሳት) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ #ዳግማይ\ትንሳኤ ተብሏል። ሁለተኛ ለምን ተገለጠ? 👉 ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጉኔን ዳስስ ብሎታል። ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑ በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል ።ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው ።ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች (የዳሰሰች)እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች ።እስካሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ። 👉 ሰንበትን ሊያጸናልን የአይሁድ ሰንበት፣እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም(ቅዳሜ)ናት ።በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ከሙታን መካከል የተነሳባት፣አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት(ዳግማይ ትንሳኤ)፣መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች ።ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች ።ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት ።እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን)የምናሳልፈው ማለት አይደለም ።እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ 👉 ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል ።በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ። "ብጹዓን እለ እንዘ ኢይሬእዩ የአምኑ" (ዮሐ20:29) የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE ╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮ @dnzema @dnzema @dnzema ╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
نمایش همه...
🙏 4 3👍 2