cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Ethiopian Orthodoxs Daily

በቤተ ክርስቲያናችን በየቀኑ የሚታሰብ ቅዱሳን፤ የመፅሐፍ ቅዱስ ምንባባት ፤ ብሂለ አበው እና አስተማሪ የሆኑ መንፈሳዊ ፅሁፎች ያገኙበታል::Share https://t.me/ethiopianorthodoxs //like page on facebook fb.me/ethiopianorthodxs ለሀሳብ አስተያየትዎ @Yakob520

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
6 348
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-97 روز
-3730 روز
توزیع زمان ارسال

در حال بارگیری داده...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تجزیه و تحلیل انتشار
پست هابازدید ها
به اشتراک گذاشته شده
ديناميک بازديد ها
01
አቡነ ሀብተማርያም፦ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሃያ ስድስት በዚህች ቀን ኢትዮጵያዊው ኮከብ አቡነ ሀብተ ማርያም ተወለደ። በዚህችም ሀገር ፍሬ ብሩክ የሚባል አንድ ሰው ነበር፡፡ ይኸውም ከከበሩም ሰዎች ተለይቶ ብዙ ገንዘብ ያለው ባለ ጸጋ ነበር፡፡ በህጋዊ ጋብቻ ስሟ ዮስቴና የምትባል ሴት አገባ ይህችውም ሴት በደግ ሥራ ሁሉ የተሸለመች ያጌጠች ነበረች፡፡ እነዲህ ባለ ሥራ ሳለች መንፈሳዊ ሀሳብ እንዲህ ሲል ተነሳባት። ሃሳቧም "ለአንቺ በዚህ ዓለም መኖር ምን ይረባሻል ዛሬ የሚያልፍ የሚጠፋ ነውና የሚመሰገንበት ለዘለዓለም የሚኖር የማያልፍ ሌላ ዓለም ይገለጣልና  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ቢነዳ በነፍሱ ከተጎዳ ምን ይጠቅመዋል እንዳለ” ማቴ. 16÷26፣ ማር. 10÷36፡፡ ለአንቺ ግን በሰማይ ፀንቶ መኖርን ሁለተኛዋን ሀገር መያዝ ይሻላል" የሚል ሃሳብ መጣባት፡፡ ይህን ካሰበች በኋላ ፈጥና ተነስታ በሌሊት ከቤት በመውጣት በሀገሯ አንፃር ትይዩ ወደ ሆነው ከጅቦች፣ ከነብሮች፣ ከዓሳማዎች፣ ከጦጦችና ከዝንጀሮዎች በስተቀር ምንም ምን ወደ ማይኖርበት በረሀ ደረሰች፡፡ በዚያም ደጃፏ ያልተዘጋ ትንሽ ዋሻ አገኘች፡፡ በዋሻው ውስጥም መዝሙረ ዳዊትን በአንክሮ የሚደግም ክቡር ባህታዊ አየች ባየችውም ጊዜ ደነገጠች እርሱም ሴቲቱን ባያት ጊዜ ፍርሀት መንቀጥቀጥ በላዩ ላይ ወረደበት፡፡ መጀመሪያ ስትገባ የጋኔን ምትሀት መስላው ነበርና ሰው መሆኗን ባወቀና በተረዳ ጊዜ ተቆጣት፡፡ እሷም ቤቴን ንብረቴን ያለኝን ሁሉ ትቼ መጥቻለሁ በዓለም ውስጥ ያለውን ሁሉ ንቄ እመንን ዘንድ እወዳለሁና ስለዚህም ወደዚህ ምድረ በዳ መጣሁ አለችው፡፡ ይህም ባህታዊ በትህትናና በፈሪሀ እግዚአብሔር ይህን የሚያስደንቅ መልካም መልስ በመለሰችለት ጊዜ አንድ ሰዓት ያህል በመንፈስ ቅዱስ ረዳትነት መንፈሳዊ ሃሳብ አሰበ። እንዲህም አላት ምንኩስናስ የለሽም ነገር ግን በፍቅር በአንድነት ወደ ቤትሽ ወደ ህጋዊ ባልሽ በሰላም ተመለሽ አላት። ዳግመኛም አላት የተፈቀደልሽን እነግርሻለሁ ከህጋዊ ባለቤትሽ ወንድ ልጅን ትወልጃለሽ እርሱም ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ይሆናል የገድሉና የትሩፋቱ ዜና እስከ ዓለም ዳርቻ ይደርሳል አለት። ይህም ብቻ አይደለም በህይወተ ስጋ ሳለ በፈጣሪው እግዚአብሔር ፍቃድ የብዙዎችን ሰዎች ነፍሳት ከሲኦል ያወጣል። ልጄ ይህም ቅዱስ እንደ መላእክትም ክንፈ ፀጋ ተሰጥቶታል፤ በሰው አካል ከስጋ ሆኖ ሳለ በተመስጦ ወደ ሰማይ የሥላሴን የአንድነትን የሦስትነትን ምስጢር ያያል አላት፡፡ ቅድስት ዮስቴናም ከአረጋዊ ባህታዊው ይህን ነገር ሰምታ አደነቀች የፈጣሪዬ ፈቃድ ከሆነ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ አለች፡፡ ቡራኬም ፀሎትም ተቀብላ እግዚአብሔርን እያመሰገነች ወደ ቤቷ ተመለሰች። ጥቂት ወራት ከቆየችም በኋላ መልኩ እንደ በረዶ ነጭ እንደ ፅጌረዳም ብሩህ ቀይ የሆነ መልከ መልካም ገፁ ብሩህ የሆነ ልጅ በዛሬው ዕለት በግንቦት በ26 ቀን ተወለደ በዚህ ግዜ በአባቱና በእናቱ ቤት ታላቅ ደስታ ሆነ፡፡ ይህ ቅዱስ ህፃንም 40 ቀን በሞላው ጊዜ በኦሪትና በሉቃስ ወንጌል እንደተፃፈ በእግዚአብሔር ፊት ያቆሙት ዘንድ ወደ ካህን አቀረቡት፡፡ ካህኑም ለክርስትና አባቱ አሳልፎ ሰጠው ስሙንም ሀብተ ማርያም ብሎ ሰየመው ከዚህም በኋላ እናት አባቱም ተመለሱ፡፡ ይህ ቅዱስ ህፃን እግዚአብሔርን በመፍራት አደገ ከዕለታት አንድ ቀን ካህናቱ በቤተክርስቲያን ምህላ ሲያደርሱ እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ እያሉ ሲፀልዩ ሰምቶ በልቡ ይህች ፀሎት በጣም ጥሩ መልካም ፀሎት ናት አለ። እኔ ይህችን ፀሎት መርጫታለሁ በዚህ ዓለም ከአሳች ህሊና በሚመጣውም ዓለም ከገሀነም እሳት እንድንድንባት አውቃለሁ አለ ስግደትንም እንደፈጣን ፈረስ ሩጫ ብዙ እስኪያልበው ድረስ ይሰግድ ጀመር፡፡ አባታችን በሕፃናት ጊዜያቸው በግ ጠባቂ ሳሉ ጎደኞቻቸው የተሠረቀ እሸት ሠርቀም እንብላ ቢሉት አልበላም አላቸው እነርሱም ተሳለቁበት። በዚህም ሌሊት ቃል ከሰማይ ሶስት ጊዜ ሀብተ ማርያም  ሀብተ ማርያም ሲል ጠራው ይህም ህፃን አባቱ በአጠገቡ ተኝቶ ነበርና አባቱ የጠራው መስሎት አባቴ ሆይ አለሁ ሲል መለሰ፡፡ ይህንንም ማለቱ ቀድሞ በኤሊ ሊቀ ካህናት ጊዜ እንደተፈፀመ ሆኖበት ነው። ሳሙ. 3÷3፡፡ እንደዚህም ሁሉ እግዚአብሔር ይህንን ህፃን ሀብተ ማርያም እያለ ሶስት ጊዜ ጠራው፡፡ ህፃኑም ሀብተማርያም ተነስቶ ታጥቆ እጅ ነስቶ እንደ ሳሙኤል ጌታዬ ባርያህ ይሰማል በል ተናገር አለው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከአሁን ጀምሮ ግን በግ ጠባቂዎች ከእርሻቸው ያልሆነውን ከሌላ እርሻ የሆነውን እሸት አምጥተው ብላ ቢሉህ አልበላም በላቸው፡፡ እናንተ ግን ብትወዱ ሄዳችሁ ብሉ በኋላ ግን ገሀነም ትገባላችሁ በእሳት ትቃጠላላችሁ በላቸው እንተን ግን ለሚሰሙ ለመረጥካቸው ቃሉን ትነግራቸው ዘንድ ከእኔ ጋር በሚስጢር ትነጋገር ዘንድ መርጬሃለሁ አለ፡፡ አቡነ ሀብተ ማርያምም ለቃልህ እታዘዝ ዘንድ እሺ ብያለሁ አለው የጠራውም ቃል ስሜንም በኋላ እነግርሃለሁ ነገር ግን የምልህን ቃልና ትዕዛዝ ጠብቅ አለው ዮሐ. 15÷10፡፡ ከጥቂት ቀን በኋላ ዳግመኛ በጎቹን እየጠበቀ ሳለ ብዙም የበጎች እረኞች አብረውት ሳሉ አንድ የበግ ጠባቂ መጥቶ የአቡነ ሀብተ ማርያምን በትር በጉልበቱ ነጥቆት ሄደ፡፡ አቡነ ሀብተ ማርያምም ተከትሎ ያን በግ ጠባቂ በትሬን ለምን ትቀማኛለህ ቢለው ያም በግ ጠባቂ በጉልበቴ ነጥቄሃለሁ አለው፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያምም በጎቼን የምጠንቅበት በትሬን እንዳትወስድብኝ በህያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ ዳግመኛም አላምልህ​​ም እቋቋምህም ዘንድ ሀይል የለኝምና አለው፡፡ ያም በግ ጠባቂ በትእቢት እንቢ አልኩህ አለው አቡነ ሀብተማርያምም ከእንግዲህ ወዲህ አምልህ ዘንድ አልደግምም ነገር ግን በአንተ ላይ የሚደረገውን ሀይልና ተዓምር አንተው ታያለህና ብሎ ዝም አለ፡፡ ያም በግ ጠባቂ በህዋው በተሰቀለ ጊዜ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሀብተ ማርያም ሆይ ማረኝ እያለ ይጮህ ጀመር፡፡ ስመ እግዚአብሔርንና የፃድቁ ሀብተ ማርያምን ክብር ንቆ አቃሏልና ላዩ ታች ታቹ ላይ ቀኙ ግራው ግራው ቀኙ ሆኖ በአየር ተሰቅሎ ዋለ፡፡ በዚ የነበሩ የበግ ጠባቂዎችም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው በጣም አደነቁ፡፡ እነርሱም አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያምን ያደረጉትን ተአምር አይተዋልና እረኛውን እንዲምረው አሁንም አምላክን ስለወለደች ንዕድ ክብርት ስለምትሆን ስለ እመቤታችን ብለህ ማርልን አሉት ቅዱስ አባታችንም የሰቀልኩት እኔ ነኝን ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም አማልኩት እንጂ የሃይሉንም ፅናት ያሳየው ዘንድ የሰቀለው እግዚአብሔር ነውና እርሱ ሁሉን ቻይና ይቅርባይ አምላክ ከተሰቀለበት ያውርደው አላቸው፡፡ አባታችንም ይህን ቃል በተናገረ ጊዜ የበግ ጠባቂው ከተሰቀለበት ወርዶ በእግሩ ቆመ በግ ጠባቂዎችም ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ለዘመዶቻቸውና ለወገኖቻቸው ያዩትን ተአምር ከመጀመሪያው  እስከመጨረሻው ተናገሩ፡፡ ይህንንም ተአምር የሀገሩ ሰዎች ሰምተው አደነቁ ይህ ታላቅ ፃድቅ ልጅ ነው በፊትም ቢሆን እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ እያለ ሲፀልይና  እንደፈጣን ፈረስ ኮቴ ፍጥነት ሲሰግድ ፊቱንም በድንጋይ እየመታ የክርስቶስን ህማማት አስቦ ሲጋደል አይተውም አደነቁ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የአባታችን አቡን ሀብተ ማርያም ትጉአዊ፤ስጫ መንፈሳዊ በረከትና ቃል ኪዳናቸው ከኛ ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን።
5756Loading...
02
Media files
6920Loading...
03
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሃያ አንድ በዚህች ታላቅ ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ:: እርሷም በልጇዋ የመለኮት ብርሃን የተጎናጸፈች ናት። የመላእክት ሠራዊት በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው በፊቷ ይቆማሉ:: ሱራፊል ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥዋ እየሰገዱ እንዲ ይላሉ:- አብ በሰማይ ሆኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ:: ሰማዕታትም በየማዕረጋቸው መጥተው ይሰግዱላታል:: ጻድቃንም እንደተሰጣቸው ክብር ተሰልፈው ይሰግዳሉ:: ሄሮድስ ያስገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል:: የለመኗትን የማትነሳ የጠየቋትን የማትረሳ ቅድስት ድንግል ይህን አድርጊ አስደርጊ ሲሏት በማያልቀው በረከቷ አትረፍርፋ ትባርካቸዋለች:: እንዲህም 5ቀን ሁሉ ክርስቲያኖችም የማያምኑትም በግልጽ ተገልጣ ያይዋታል:: ወደ ቤታቸው ሲሄዱ ሰግደው ይሰናበቷታል ትባርካቸዋለች:: በዚህ ቀን በኃጢአት የወደቁ አስነሽን ይሏታል:: የጠፋም መልሽን ይሏታል:: የረከሱም ቀድሽን ይሏታል። ተምኔታቸውም ተፈጽሞ ሰግደው ይሄዳሉ:: ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ዘወትር በረከቷ ይጎብኘን:: አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን። በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ በእውነት አሜን:: 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
1 0484Loading...
04
ፃድቅ  አቡነ ዐቢየ እግዚእ:- አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት አሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን ኢትዮጵያዊው ፃድቅ  አቡነ ዐቢየ እግዚእ አረፉ። አባታቸው አፍቅረን እግዚእ እናታቸው ፅርሐ ቅዱሳን ይባላሉ። ሁለቱም ሃይማኖታቸው የቀና ምግባራቸው ያማረ በእግዚአብሔር የተወደዱ ናቸው። በወርቅ በብር የከበሩ ቢሆኑም ልጅ ግን አልነበራቸውም። በእመቤታችን ስም ለተቸገሩ ምፅዋትን በመስጠት ዘወትር ይማፀኑ ነበር። አንድ ቀን ድንቅ የሆነ ራእይ ተመለከቱና ፈቃደ እግዚአብሔርን ሲጠባበቁ ነሐሴ 7 ቀን ፅርሐ ቅዱሳን ፀነሰችና ግንቦት አንድ ቀን እንደ ፀሐይ የሚያበራ ልጅ ወለደችና በ40 ቀኑ ሲጠመቅ ስሙን ዓቢየ እግዚእ አሉት። ያጠመቁት የአክሱም ሊቀ ጳጳስ ወመተርጉም ሰላማ ሲሆኑ በሚያጠምቁበት ሰዓት ሊቀ መላእክ ቅዱስ ሚካኤል "ይህ ሕፃን ድውይ የሚፈውስ ሙታንን የሚያስነሣ ቅዱስ ይሆናል" ብሎ ትንቢት ተናገረለት። ወላጆቹ ባደገ ጊዜ ለመምህር ዘርዓ ሚካኤል ሰጡትና ብሉያትና ሐዲሳት መፃህፍትን ሌሎችምንም አስተማሩት። ከቡነ ሰላማ እጅም ዲቁናና ቅስና ተቀበሉ። ከቡዙ አገልግሎት በኋላ የሃሌ ሉያው አባ ሳሙኤል ቆብና አስኬማን ሰጠው። አባታችን እንስሳትን በቋንቋቸው ያናግሯቸዋል። የማይስማሙ አብረው ሊሆኑ የማይችሉ እንስሳትን አስማምተው አንድ ያደርጋሉ። አባታችን የጌታን 40ፆም በሚፆሙ ሰዓት በዋልድባ ባሉ ስውራን ቤተ ክርስቲያን ገብተው ሥርዓትን ይፈፅማሉ። እንደ መላእክትም ክንፍ አላቸው ብሔረ ሕያዋን ደርሰው ከቅዱሳን ተባርከው ይመጣሉ። የተለያዩ አስደናቂ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እየሰበኩ በብዙ ድካምና ፈተና ብዙሃንን አሳመኑ። እንደተራራ የገዘፈ ሰይጣን ሊፈትናቸው በመጣ ጊዜ ስመ ሥላሴ ጠርተው አማትበው ለሁለት ሰንጥቀውታል። በተሰጣቸው ታላቅ ፀጋም ሙት ያስነሳሉ ድውይ ይፈውሳሉ። የሚደንቁ ተአምራትን በእዝባቸው መካከል አደረጉ። አባታችን አንድ ቀን ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብቶ ሳለ ገዳማውያኑ "አንድ መነኮስ ብናገኝ ሥጋ ወደሙ በተቀበልን…" ብለው ሲነጋገሩ ባረካቸውና "ዛሬ የተዘጋጀ ቁርባን አለን?…" አላቸው። እነርሱም "አዎን" ባሉት ጊዜ አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ አዘዛቸው እነሱም አመጡለት። ባርርኩኝ አላቸው "እንደ መልኬ ፄዴቅ እንደ አቤል መዋትእን ይቀበልልህ" ባሉት ጊዜ "ሚ መጠን አለ።" ይህን ባለ ጊዜ ኅብስትንና ፅዋዕ ከፃሕል ጋር ተዘጋጅቶ ከላይ ከሰማይ ወረደ። ይህንንም ከእርሱ ጋር የነበሩ ሁሉ ይህ ኅብስትና ፅዋ ከየት መጣ እያሉ አደነቁ። አባታችንም የሐዋርያትን ቅዳሴ ቀድሶ አቆረባቸው። ቅዳሴውንም እንደጨረሰ ደመና ጠቅሶ በደመና ተጭኖ ጉዞ ሊጀምር ሲል እንዲህ አሉት፦ "አቤቱ ስለ እግዚአብሔር ብለህ ስምህን ንገረን አሉት?" "ስሜ ዓቢይ እግዚእ ይባላል የምንኲስና ስሜ የመረታ አገር እንጦንስ ነኝ አላቸውና" ባርኳቸው ሔደ። ለአባታችንም የወረደላቸው ያም ፃሕልና ፅዋ ዛሬም ድረስ አለ። ቅዱስ አባታችን ወንጌልን በማስተማር አጋንንትን በመዋጋት ሕሙማንን በመፈወስ የተለያዩ ተአምራትን እየሠራ ወንጌልን በመስበክ እግዚአብሔርን ካገለገለ በኋላ ከፈጣሪው ታላቅ ቃል ኪዳን ተቀብሎ በዛሬው ዕለት አርፏል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የአባታችንም በረከትና ቃል ኪዳን ይጎብኘን ለዘላለሙ አሜን። 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
9954Loading...
05
Media files
1 3044Loading...
06
ኢትዮጵያ ከመላእክት ጋር የሚዘምር ማሕሌታዊ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሚያጥን ካህን የምታፈራ ሀገር ናት። ለሰማይ አገልጋዮችን ገና ሳይሞቱ የምትልክ፣ ከተዋጊዎች መካከል ወደ ድል ነሺዎች መልእክተኛ የምትልክ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ያለች ናት? ቅዱስ ያሬድ በትሕትናው ከትል ተማረ። ትሑታንን ከፍ የሚያደርግ ፈጣሪም ከፍ አደረገውና ከመላእክት ጋር ዘመረ። ትልዋን ከዛፍ አውርዶ ቢጨፈልቃት ኖሮ ለአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት ያልነጠፈው የምስጋና ጅረት በሀገራችን ባልፈሰሰ ነበር። ኃይል አለኝ ብለህ የምትጨፈልቃቸው ትሎች ሰማይ የሚያደርሱህ መምህራኖችህ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ ይላል የታሪኩ ተግሣፅ። ቅዱስ ያሬድ እግሩን በጦር እየተወጋ እንኩዋን ዝማሬው ሰማያት ወስዶት አልተሰማውም ነበር። የእኛው ሲላስ የእኛው ጳውሎስ ቅዱስ ያሬድ ሆይ በዘመርክባት ሀገርህ ዛሬ ብዙ ጦር ተሰክቶባታል። ከአንተ ዜማ በቀር ዛሬም መጽናኛ የለንምና በምልጃህ አስበን። ጥዑመ ልሳን ያሬድ: ሊቀ ጠበብት ያሬድ: ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ!! (Deacon Henok Haile)
1 3255Loading...
07
ዳግም ትንሣኤ፦ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በዚህች ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሤኤው ሳምንት ለሐዋርያው ቶማስ ተገለጠለት:: የዛሬው ቀን እንደ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት አጠራር ዳግም ትንሣኤ ይባላል። በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ በዛሬው ዕለት የክርስቶስን ዳግም ትንሣኤ በማየታችን የእግዚአብሔር ልጅ የመባልን ክብር ያገኘንበት ቀን ነውና በቤተ ክርስቲያን ተገኝተን ልንከብር ያስፈልጋል። አባት ሆይ! ከአባቶቻችን ምስጋናን እንደ ተማርን ስለ ምሥጢረ ሥላሴ በዳግም ትንሣኤ አወቅን ተረዳን፤ እንዲሁም እናምናለን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ሒዱ አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው እንዳለ የምናምንባት ሃይማኖት ይህች ናት ከእርስዋ በቀር ለዘላለሙ ሌላ አንሻም። ካህናት ሆይ እንኳን ደስ አለችሁ! በዛሬው ዕለት አምላካችሁ እኛን የማጥመቅ፣ የማሰርና የመፍታት ሥልጣን፣ ክህነት የመስጠትን ሥልጣን፣ የመባረክን ሥልጣን፣ የመሾም የመሻር ሥልጣን፣ የመቀደስ የመፈወስ ሥልጣን የተሰጣችሁ ቀን በዛሬዋ ዳግም ትንሣኤ ናት እና ኑ በቤተ መቅደስ ተሰባስበን ደስታ እናድርግባት። ምእመናን ሆይ! ሀብተ ወልድ እና ስመ ክርስትና የምናገኝበትን የምሥራች ጌታ ለሐዋርያት የሰጠበት ቀን በዳግም ትንሣኤ ነውና ኑ በመቅደሱ ተሰባስበን በደስታ በሐሴት እናመስግን። ሌላም በዛሬው ዕለት ለሐዋርያው ቶማስ በእጆቹና በእግሮቹ ውስጥ የችንካሮቹን ምልክት አሳየው የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጎኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የተወጋበትን ቦታ አሳየው ቶማስም ጌታዬና ፈጣሪዬ መነሣትህን አመነኩ አለ:: ጌታችንም ብታየኝ አመንክብኝ የሚመሰገንስ ሳያየኝ የሚአምንብኝ ነው ብሎ መለሰለት:: በትርጓሜ ወንጌል እንዲህ ይላል ቶማስ በመድኃኒታችን ጎን ውስጥ እጁን በአስገባ ጊዜ እጁ በመለኮት እሳት ተቃጠለ በመለኮቱም ደግሞ በታመነ ጊዜ እጁ ከመቃጠል ዳነች:: ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በሐዋርያቶች ጸሎት በታጋዮች ጻድቃንም በድል አድራጊዎች ሰማዕታት ጸሎት ይልቁንም አምላክን በወለደች  በክብርት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ይምረን ዘንድ ወደርሱ እንለምን ለዘላለሙ አሜን:: መልካም ዕለተ ሰንበት። 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸       🌸 የምሥራች 🌸 ⛪️ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን 🙏በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን ⛪️አሰሮ ለሰይጣን 🙏አግኣዞ ለአዳም ⛪️ሰላም 🙏እምይእዜሰ ⛪️ኮነ 🙏ፍሥሐ ወሰላም 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
1 57412Loading...
08
ግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች:: እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት:: ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ:: ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መባዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበር:: እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኀዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር:: ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ:: ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው:: በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት:: ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት:: የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርግ ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች:: ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ማለት ነው:: ደግሞም ሀብትና ሥጦታ ማለት ነው:: በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት:: ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነት ያገኘንባት:: እንግዲህ እዚህ ጋር ልብ ይሏል:: በዚህ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ የኛ ልጅነት የኛ የመዳንችንን መንገድ እግዚአብሔር እንዴት እንዳከናወነልን እንረዳለን:: እግዚአብሔር ሰውን ሲያድን ማዳኑን የፈጸመው እጅግ በጣም ልዩ በሆነ ሁኔታ ነው:: ይህም ገናናነቱን ከእኛ ታናሽነት ጋር አዋሕዶ፤ ከሃሊነቱን ከእኛ ነፃነት ጋር አስማምቶ በመሆኑ ነው:: ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ሊያድነን ሲነሣ እንዲሁ በማንኛውም መንገድ ቢያድነን ታላቅ ቸርነትና ደግነት ሆኖ ሳለ እርሱ ግን ከዚያም በላይ በሆነ መንገድ እኛን አሳትፎ ፈቃዳችንን ተቀበሎ አስፈቅዶ አስወድዶ ያዳነን:: እርሱ ሁሉን ማድረግ ስለሚችል ብቻ ያለ እኛ ፈቃድ ሱታፌ እንዲሁ አፍአዊ በሆነ ሁኔታ እና ያለ ፈቃዳቸው አላዳነንም:: ባሕርያችንን ሲዋሐድም ያለ እኛው ፈቃድና ሱታፌ አላደረገውም:: የሚጠቅመንን የመዳናችንን ነገር ሲፈጽም እኛን አስወድዶና አሳትፎ ነው:: አካላዊ የእግዚአብሔር ቃል እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት ሲወርድ መከራ ተቀብሎ እኛን የሚያድንበትን መሣሪያ የወሰደው ከእኛው መዳኑ ከሚያስፈልገንና ከሚደረግልን ከሰዎች ነበር:: ይህ እንዲሆን ደግሞ ሰዎችን የሚወክልና እኛን ሁሉ ወክሎ የሚሳተፍ አንድ ሰው ያስፈልግ ነበር:: በዚህም ያ የሚያስፈልግ አንድ ሰው በዛሬዋ ቀን የተወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት:: በእወነት ምስጋና ይድረሳትና። ከዚህ በኋላ ነው እንግዲ የነቢያት ትንቢታቸው ከተፈጻሚነት የደረሰው:: ታዲያ የዛሬውን በዓል ስናከብርና ተድላ ደስታ ስናደርግ ከመንፈሳዊነት ሳንወጣ ልንጠነቀቅ ይገባል:: ይህን በዓል ስናከብርም ሌሊት በቤተ ክርስቲያን በማኅሌት÷ በዝማሬ÷ ጠዋት በኪዳንና በቅዳሴ÷ ታምሯን በመስማት÷ ወንግል በመማር ነው:: ክርስቲያኖች ከዚህ የወጣ ባዓል የላቸውም:: ብዙዎች የእኛን መንፈሳዊ በዓል ይዘው የራሳቸውንና የቤታቸውን ጣጣ ይዘውና አስታከው መንፈሳዊ በዓላ ላይ ለጥፈው ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም ከመንፈሳዊነታችን ጋርም የሚፃረር ነገር ሲፈጽሙ ይታያል ይህ አግባብ አይደለም:: የበግና የፍየል ከለር እየመረጡ÷ ቄጣና ፈንዲሻ እየረጩ÷ የቡና አተላ እየገለበጡ የሚከበር መንፈሳዊ በዓል የለም:: አስፀያፊም የተወገዘም ግብር ነው። እስኪ አንድ በዓለም ያለ ሰው ልደቱን ሲያከብር ወይ ሲደግስ የበግ ከለር መርጦ የሚያርድ ማን አለ? ወይ ቡና እያንቃረረ ቂጣና ፈንዲሻ በየጥጋ ጥጉ የሚጥል ማን አለ? ታዲያ እንደዚህ ያለን ኮተታ ኮተት ከየት የመጣ ነው:: የኛ አይደለም እንዲህ ያለ ነገር እንዲህ የሚያደርጉ ካሉ ፈጥነው ንሰሐ ሊገቡና ከክርስቲያኖች ማኅበር ሊገቡ ይገባል:: የእመቤታችንን የልደቷን በዓል ግን የምናከብረው በዝማሬ÷ በማኅሌት÷ በኪዳን÷ በቅዳሴ ጊዜ ሥጋወ ደሙ እየተቀበልን÷ ወንጌልን እየተማርን÷ የተራበ እያበላንና የታረዘ እያለበስን እየዘመርን ነው:: ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን። 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
1 45610Loading...

نمایش همه...
08:16
Video unavailableShow in Telegram
80.57 MB

01:08
Video unavailableShow in Telegram
5.18 MB
Photo unavailableShow in Telegram

آرشیو پست ها