cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
29 273
مشترکین
+8424 ساعت
+4067 روز
+81730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ: #የማርያም_ሐዘን (#ዓርብ_በሦስት_ስዓት_የሚነበብ አባ፡ ሕርያቆስ፡ የደረሰው፡ ድርሳን፡ ይህ፡ ነው።) ወዳጆቼ ሆይ የአባቶች አለቃ የያዕቆብ ልቅሶ፤ ዛሬ ታደሰ አለ። በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ለወለደችው ለተወዳጅ ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስም። መከራ ስለተቀበለችበት ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስም። የድንግልና ጡቷን ለእጠባችው ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። በቤተልሔም በበረት ስለወለደችው ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። በማኅፀንዋ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ለተሸከመችው ተወዳጅ ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቶ ወልዳ ላልሳመቻቸው ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ፤ እንደ ሰው ሁሉ በብብቷ ለተሸከመችው ልጇ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቦታ ወደቦታ ይዛ ላልተሰደደችባቸው ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ። ከሀገር ወደ ሀገር አዝላ ለተሰደደችበት ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቶ መቃብራቸውን ላላአየች ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ። በአንድ ልጅዋ መቃብር ደጃፍ ላይ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። የባለ መልካም ጽሕም ሽማግሌ የያዕቆብ ልቅሶ በብላቴናይቱ ድንግል ዘንድ ዛሬ ታደሰ። ወንድሞቹ ባሰሩት ጊዜ ያዕቆብ ወደ ዮሴፍ አልተመለከተም። ድንግል ግን ልጅዋን በዕንጨት መስቀል ላይ ተቸንክሮ አየችው። ዮሴፍ በሰፊ ጉድጓድ ውስጥ ሳለ ያዕቆብ በላዩ፡ ያለቅስ ዘንድ ወደ ዮሴፍ አላየም። ድንግል ግን በአይሁድ ጉባዔ መካከል ተሰቅሎ ልጅዋን አየችው። ዮሴፍን ወንድሞቹ ልብሱን ገፈው ሲያራቁቱት ያዕቆብ አላየም። ድንግል ግን በጎ ምክር በሌላት በአይሁድ መካከል ልብሱን ተገፎ ራቁቱን ሁኖ አየችው። ወንድሞቹ ዮሴፍን በሃያ ብር ሲሸጡት ያዕቆብ አላየም። ድንግል ግን ይሁዳ ልጅዋን በሠላሳ ብር ሲሸጠው አየች። አራዊት ባልቀደዱት ልብስና በሌላ ደም ላይ ያዕቆብ አለቀሰ። አምላካዊ ደም ግን ድንግል ማርያም ስለእርሱ በላዩ የምታለቅስበት በቀራንዮ አለት ላይ የፈሰሰው ነው። ድንግል ግን ዛሬ ያየችው ልጅዋን ያለበሱትን ሌላ ልብስ ነበረ፤ የራሱን ልብስ ግን እርስ በርሳቸው ተካፈሉት። የዮሴፍ ወንድሞች ወንድማቸው ዮሴፍን በሸጡት ጊዜ አለቀሱ ተጸጸቱ። የእስራኤል ልጆች ግን ጌታቸውን በሸጡት ጊዜ አላለቀሱም፤ አልተጸጸቱም። የያዕቆብ ልጆች ወንድማቸው በነገሠ ጊዜ ተደሰቱ። አይሁድ ግን ጌታቸው ከሙታን ተለይቶ በተነሣ ጊዜ ደስ አላላቸውም። ድንግል ሆይ፤ በእውነት በልጅሽ መቃብር ላይ ልቅሶሽ ጣዕም ያለው አሳዛኝ ነበረ ማርያም ሆይ ለምን ተቀምጠሻል? ምን ታደርጊያለሽ? ብለው የልጅሽን መሰቀሉን በነገሩሽ ጊዜ በመላእክት መካከልም ቃልሽ ያማረ ነበር። እነሆ ልጅሽን በመኰንኑ ፊት አቁመውታል፤ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትም ያሰቃዩታል፣ ያቃልሉታል፣ ማርያም ሆይ ምን ታደርጊያለሽ? እነሆ ልጅሽን በፍርድ አደባባይ መካከል ልብሱን ገፈው እያራቆቱት ነው። የኢያቄም ልጅ ማርያም ሆይ ለምን ተቀምጠሻል? ምንስ ታደርጊያለሽ? እነሆ በኢየሩሳሌም ሜዳ የሚሰቀልበትን ግንድ ብቻውን ተሸክሞአል፤ አንድ እንኳ ወደ እርሱ የሚቀርብ የለም። የሐና ርግብ ሆይ ለምን ተቀመጥሽ? የምትሰሪውስ ምንድን ነው? እነሆ ልጅሽን ሰቅለውት በቀራንዮ ቦታ ቁሞአል። የዳዊት ዘር ሆይ ልጅሽን በመስቀል ላይ ለምን ከፍ ከፍ አደረጉት? እመቤት ድንግል ሆይ በዮሐንስ ቤት ዛሬ ልቅሶሽ በእውነት ጣዕም ያለው ነበረ እንዲህ ስትዪ። ወዮ ለዚህ መራራ ወሬ ነጋሪ ለኢዮብና እስራኤል ለተባለ ያዕቆብ ከአረዷቸው መርዶ የመረረ ነው። ዛሬ ወደእኔ ለሚመጣ ለዚህ ለክፉ ወሬ ወዮ። ልጄ ሆይ አገሩን በኢቃጠሉ ጊዜ ለሎጥ ከአረዱት መርዶ ያስጨንቃል። በእኔ ላይ ለደረሰው ለዚህ አስጨናቂ ስብከት ወዮ። ልጄ ሆይ ስለ ኃያላነ እስራኤል ሞት ከአረዱአቸው መርዶ ይበልጣል። በዚህ በክፉ ወሬ ወደእኔ ለመጣው ለዚህ ወሬ ነጋሪ ወዮ። ልጄ ሆይ እነሆ ስታረጋጋኝ ሠላሳ ዓመት ይሆናል፤ ልገሥጽህም አልተቻለኝም። ዛሬ ወደ እኔ ወሬህ እስከመጣ ድረስ ወጥተህ እስከምትገባ አንዲት ሰዓት እንኳ አላመንኩህም። ልጄ ሆይ ለሐዘኔ ሁሉ ጥንቱ ሰሎሜ ናት፤ እኔ ዳኛውን አየው ዘንድ ከቤቴ አልወጣም፤ በፈራጁም ፊት አልቆምም። ሌባውን ራሱን ሲቆርጡት ሽፍታውንም ይገድሉት ዘንድ ሲፈርዱበት አላየሁም። ከቶ ቀራንዮን አላየሁትም፤ የጎልጎታንም ቦታ አላውቅም፤ ሁል ጊዜም በሚጣሉበት ቦታ አልቆምኩም። ልጄ ሆይ ክፉ የሆነ ፍርድ አላየሁም፤ በፍርድ አደባባይም ከቶ ለዘላለሙ አልቆምኩም። ልጄ ሆይ ያደረኩብህን ግፍ አላውቅም እኔም በዮሐንስ ቤት ነበርኩ። ልጄ ወዳጄ ሆይ በሊቀ ካህናቱ በሐና ግቢ የተቀበልከው ግፍ ወሬው መራራ ነው። ልጄ ወዳጄ ሆይ ዛሬ ከእኔ ላይ ነጻነቴን አስወገድክ፤ ስለልደትህ በናዝሬት መልካም የምስራች ነገሩኝ። ዛሬ ግን በኢየሩሳሌም ይህችን ክፉ መርዶ አረዱኝ። በዮሴፍ ቤት መልካም ዜና በዮሐንስ ቤት ግን የሞት ዜና መጣልኝ ። ልጄ ወዳጄ ሆይ እኔ በልቤ ደስ እያለኝ ተቀምጨ ነበር። በየዕለቱ ፋሲካ ደርሶአል በዓሉን እናከብር ዘንድ ወደሀገራችንም እንመለሳለን እያልኩ ነበር፤ የዚህ ዓይነት ፋሲካም ደረሰኝ። ልጄ ወዳጄ ሆይ በእንባና በሐዘን በዓሌ ወደ ልቅሶ ተመለሰ፤ ፋሲካየም ወደልብ ሐዘን። በዮሐንስ ቤት ሳለች ስለ ልጅዋ የመከራ ወሬ በመጣበት ጊዜ ድንግል እመቤታችን ይኸንን ልቅሶ ታለቅስ ነበር። ከእርስዋ ጋራ ይሔድ ዘንድ ከንጹሐን ሐዋርያት አንድ ፈለገች አላገኘችም፤ አይሁድን ከመፍራት የተነሳ ሁሉም ትተውት ሸሽተዋልና። ከእርስዋ ጋራ ይሔድ ዘንድ ስለ ጴጥሮስ መረመረች፤ እርሱማ የካህናት አለቆችን ከመፍራቱ የተነሳ ልጅሽን ከቶ አላውቀውም አለ፤ ሒዶም ተሸሽጓል አልዋት። ዳግመኛም ስለ ጌታችን ወንድም ስለ ያዕቆብ መረመረች፤ ለያዙት ሰዎች በተራራ ላይ ልብሱን ትቶ እንደ ሸሸ ነገርዋት። እንድርያስንም ፈለገችው፤ እርሱስ ወደ ከተማ አብሮት አልመጣም አልዋት፤ እንደዚሁ ቶማስም ሽሽቶ ሔደ። ስለ በርተሎሜዎስም ጠየቀች፤ እርሱም ከወንድሞቹ አስቀድሞ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ፊልጶስም ጠየቀች፤ እርሱም የፋናዎችን ውጋገንና መብራቶችን ባየ ጊዜ ፈርቶ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ዮሐንስ ወንድም ስለ ያዕቆብ መረመረች፤ አንድ ጊዜ ስንኳ እንዳልቆመ ነገርዋት። ስለ ማቴዎስም መረመረች፤ እርሱም ግብር ስለሚቀበላቸው አይሁድንና የካህናት አለቆችን እጅግ ስለፈራ እነርሱም ስለሚጠሉት በሌሊት ጨለማ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ሁሉም መረመረች፤ አብሮ ወደ ቀራንዮና ወደጎልጎታ ከሔደው ዮሐንስ በቀር አንድም አላገኘችም። ድንግልም ከልጅዋ ደቀ መዛሙርቶች ከዮሐንስ በቀር አንድ እንኳ ባለማግኘቷ እንደገና ዳግም ወደ ጽኑ ልቅሶና ሐዘን ተመለሰች። እንዲህ እያለችም አለቀሰች፦ ልጄ ወዳጄ ሆይ ወዮልኝ ወንድሞችህ ሸሹ ትተውህም ተሸሸጉ። አባቴ ጴጥሮስ ሆይ ጌታህን እንዳትክድ ሁልቀን እጠራጠርህ ነበር፤ ስለ እርሱ ወርቅ ብር አልሰጠህ ለምን ጌታህን ፈጥነህ ካድከው? ስለርሱ መርከብ ወይም ቀዛፊ አልሰጠህም፤ መምህርህንና ጌታህን ዛሬ ለምን ካድከው? ስለርሱ ምንም አልሰጠህም ወንድ ልጅም ቢሆን ወይም ሴት ልጅ። ጴጥሮስ ሆይ ስለ እርሱ ወንድምን ወይም ወዳጅን አልሰጠህም። ልጄን ለምን ካድከው? በዚህ ሁሉ ልብህ ለምን ቀላል ሆነ?
نمایش همه...
ጴጥሮስ ሆይ እስከ ፈራህና ፈጥነህ እስከ ካድክ ድረስ ለእኔ ነው ትል ዘንድ በድጋሚ ሌላ መስቀል አላየህ፣ እንደ ብረትም የተሳለ አንደበት ሰጥቶህ ነበር። ጴጥሮስ ሆይ አንተስ ያለ እሳትና ያለእንጥረኛም ፈጽመህ አቀለጥከው። ጴጥሮስ ሆይ ከሰው ሁሉ ለገጽህ ግርማ ሰጥቶህ ነበር፤ ብርሃናቸው የማይጠፋ ዓይኖችን የሰጠህ ሲሆን ስለጌታህ አንዲት ጥፊ ትቀበል ዘንድ ዛሬ አልታገሥክም። ጴጥሮስ ሆይ የመንግሥት ሰማያትን መክፈቻ የሰጠህን ልጄን በካድከው ጊዜ አልፈራህም፤ በሊቀ  ካህናቱም ግቢ አልታገሥክም፤ በእርሱ ፈንታም ለዓለሙ ሁሉ የታመነ ጠባቂ አድርጎ ሾመህ። ጴጥሮስ ሆይ ስለ ጌታህ አንድ ጊዜ እንኳ ጥቂት መከራ አልተቀበልክም። ጴጥሮስ ሆይ ለዓለሙ ሁሉ አባት ትሆን ዘንድ ሾመህ፤ አንተ ግን ለልጄ የወንድማማችነት ፍቅርን አላደረግህም። ጴጥሮስ ሆይ አምላካዊ እጁን በራስህ ላይ ጫነ፤ አንተ ግን ከመካድህ በፊት ዛሬ በራስህ ላይ የእሾህ አክሊል ይጭኑብህ ዘንድ አልፈቀድክም። ጴጥሮስ ሆይ ልጄ ለአንተ ወዳጅህ እንጅ እንደ ጌታህ እንዳልሆነ አስብ። ልጄን እንደዚህ ትክደው ዘንድ ለአንተ አግባብ ኣይደለም። ጴጥሮስ ሆይ ከእኛ ጋራ ይህ ሁሉ ድካም እንዳገኘው እንደ አባቴ ዮሴፍ ብትሆን ኖሮ። ጴጥሮስ ሆይ እንደ እርሱ ወደ ኄሮድስ ቢጎትቱህ በግብጽ ምድርም ከእኛ ጋራ መከራ ተቀባይ ብትሆን እንደ እርሱ መታገሥ ባልቻልክም ነበር እንጃ። አባቴ ጸድቁ ዮሴፍ ሆይ በአጥንቶችህ ላይ የሰማይ ጠል ይውረድ። ነፍስህም ዕፀ ሕይወትን ትመገብ፤ ከእኛ ጋራ ታግሠህ መከራ፡ ስትቀበል እንደ ጴጥሮስ ልጄን አልካድከውምና። ጴጥሮስ ሆይ ወደ ፍርድ አደባባይ አልወሰዱህ በባለ ሥልጣኖችም ፊት አላቆሙህ ፈጥነህ ጌታህን ካድከው። ድንግል በዮሐንስ ቤት እንደዚህ ስታለቅስ ሳለ ዮሐንስ እያለቀሰ መጣ እርሷንም እያለቀሰች አገኛት። ድንግል እመቤታችንና ዮሐንስም ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርስ በርሳቸው እየተላቀሱ ሁለቱም አብረው ነበሩ። ዮሐንስም ድንግልን እናቴ ሆይ ጌታችንን ጴጥሮስ ስለካደው አታልቅሺ አላት፣ አሳልፎ እንደ ሰጠው እንደ ይሁዳ ነውር የለበትምና። በእራት ጊዜ ጴጥሮስ ሆይ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ሲለው መምህሬን ሰምቻለሁና። ጴጥሮስም እንደዚህ በአንተ ላይ ይደረግ ዘንድ አይገባም፤ ጌታዬ ፈጣሪዬም እስከ ዘላለሙ ድረስ እልክድህም መሞት ይሻለኛል፤ እንደዚህም በእኔ ላይ አይሆንም፤ ስለ አንተ ነፍሴን አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ። ከዚህ ቀደምም መምህራችን ጌታ መምህሬ ጴጥሮስን ሦስት ጊዜ ሲገሥፀው ሰምቻለሁ። ሰይጣን ባለጋራዬ ወግድ ከኋላዬ ዕንቅፋት ሁነህብኛልና ሰው ሰውኛውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና አለው። አሁንም እመቤቴ እናቴ ሆይ ስለ አባቴ ጴጥሮስ መካድ አታልቅሽ ለኃጢአተኞች ሁሉ ለንስሐ ምሳሌ ነውና። በቃሉ ያመነውን የጌታችንን ቃል አስተባብሎ ነበርና። በሐዘኗ የሚገኝ በረከት ከዐይንዋ የፈሰሰ የዕንባ ውኃ ጸጋ ለዘላለሙ ከእኛ ጋራ ይኑር አሜን። (#ግብረ_ሕማማት_ዘዓርብ_ሦስት_ሰዓት)
نمایش همه...
3👍 1
#የሰሙነ_ሕማማት_ዓርብ ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያን ልዩ ቀን ነው፡፡ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁ ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሳ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ ግብር ነፃ የሚያወጣ ሲገረፍ የዋለበት፣ ወልደ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ድኅነት በመስዋዕትነት ሙሽራ የሆነበት የደስታ ቀን፤ አሳዳጅ አሳሪያችን ዲያብሎስ ከነወጥመዱ ድል የተነሳበት ቀን ነው። ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን የተለያየ ምስጢራዊ ስያሜዎች ተሰጥቶታል፡፡ #የስቅለት_ዓርብ ይባላል የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለ ድኅነት መስዋዕት ሆኖ የዋለበት ዕለት በመሆኑ የስቅለት ዓርብ ተብሏል።  (ማቴ 27፡35) #መልካሙ_ዓርብ ይባላል ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት ማንም ሰው ሲያጠፋ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት ይደረግ ነበር፡፡ በተለይ በሮማውያንና በፈሪሳውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ነበረ። በዚህ ዕለት ግን ታሪክን የሚቀይር ነገርን የሚገለብጠው አምላክ የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምህረት ምልክት፣ የሕይወት አርአያ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ፣ የቤተክርስቲያን ጌጥ፣ የገዳማት ዘውድ ስላደረገውና በዕለተ ዓርብ በሞቱ ሕይወትን ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡ በዚህ ዕለትም ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱ ፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ ተአምራት አሳይቷል፦ 1. ፀሐይ ጨልማለች 2. ጨረቃ ደም ሆናለች 3. ከዋክብት ረግፈዋል 4. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዷል 5. ምድር ተናወጣለች (ተንቀጥቅጣለች) 6. መቃብሮች ተከፍተዋል 7. ሙታን ተነስተዋል በዓመት አንድ ጊዜ የምናገኘው ይህ ዕለት ቀራንዮን የምናስብበት ነገረ መስቀሉን የምናስተውልበት እንጂ ስለምድራዊ ኑሮአችን ስንባክን የምንውልበትና በዋዛ ፈዛዛ ልናሳልፈው አይገባም፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
نمایش همه...
50👍 25🙏 6
#የሰሙነ_ህማማት_ሐሙስ #ጸሎተ_ሐሙስ በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡  የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ (ማቴ. 26፥36-46 ዮሐ.17) #ሕፅበተ_ሐሙስ_ይባላል፡- ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፤ «በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ እኛም የአንተን አርአያ አንዘነጋም የሌላውን እግር እናጥባለን፤» ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡ #የምስጢር_ቀን_ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡ #የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡- ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ «ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱ ጠጡ» በማለቱ ይታወቃል (ሉቃ. 22፥20) ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለሆነ የሐዲስ ኪዳስ ሐሙስ ተባለ፡፡ #የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት (ዮሐ. 15፥15)፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
نمایش همه...
13👍 4
#በእንተ_ጸሎት_ሐሙስ "ተራሮችን በኃይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፡፡ የባሕርን ውኃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በቀላያትም መዝገቦች የሚሾማቸው ርሱ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውኃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ  ኩስኩስት አፈሰሰ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሚታጠቡበት ገንዘብ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በደብተራ ኦሪት ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውኃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ዠመረ፡፡ የተረከዞቻቸውንም እድፍ በታጠቀው ማበሻ ጨርቅ አሸ፡፡"  (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ) "በወገቡ የታጠቀውን ማድረቂያ አይተው መላእክት አደነቁ፤ ስሙ ከፀሓይና ከጨረቃ በፊት የነበረ ርሱ አገልጋይ ኾነ፤ ሕያው ጌታን ሱራፌል ያመሰግኑታል፤ ቦታውን ግን አያውቁም፤ ሱራፌልን የፈጠረ ርሱ በራት ጊዜ ወገቡን ዘርፍ ባለው ዝናር ታጠቀ፤ እንዳያቃጥል በመፍራት የማይታይ እሳት ለሐዋርያት አገልጋይ ኾኖ አብነት ይኾናቸው ዘንድ የትሕትና ሥራን የሚሠራበትን ውሃ በኩስኩስት ቀዳ የደቀ መዛሙርቱን አለቃ ጴጥሮስንም እግሩን ሊያጥበው ጠራው" (ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘሥሩግ) @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
نمایش همه...
87👍 14🙏 7😍 5
🙏 41 23👍 6
#የሰሙነ_ሕማማት_ረቡዕ #ምክረ_አይሁድ_ይባላል ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ. 26÷1-14፣ ማር. 14÷1-2፣ ሉቃ. 22÷1-6) የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡ #የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቱዋ ማርያም) "ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ" ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ረቡዕ የመዓዛ ቀን ይባላል፡፡ #የእንባ_ቀንም_ይባላል ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና። (ማቴ. 26÷6-13፣ ማር. 14÷9፣ ዮሐ. 12÷8) ኃጢአትን በማሰብ ማልቀስና ራስን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ከምታስተምረን ማርያም እንተ እፍረት እንባን ለንስሐ ሕይወት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
نمایش همه...
35👍 12🙏 5
ንጹሕ ሆነን የረከሰ ምራቅን አለመጠየፍ እንዴት ይቻለናል? ያለ በደል የሚደረግ ውንጀላ እና ግፍንስ "በቃ" አለማለት እንዴት ይሆናልናል? ያለ ጥፋት የሚመጣብንን ምን ያህል ጥፊዎች እንታገሳለን? ስንት ጅራፎችንስ እንቀበላለን? ስንት ውርደቶችንስ እንሸከማለን? መድኃኔዓለም ይህን ሁሉ ነገር የተቀበለው ስለ እኛ መዳን ነው። እኔ ግን ስለ ራሴ መዳን በጀርባህ ላይ ካረፉት ጅራፎች የአንዲቱን ሰንበር ያህል እንኳን መከራ ለመቀበል ትዕግስቱ የለኝም። "ተሰሃለኒ እግዚኦ በከመ ዕበየ ሳህልከ" - "አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ" መዝ 50፥1 ዲያቆን አቤል ካሳሁን
نمایش همه...
88🙏 13👍 3
ዐቢይ ጦም ሊጠናቀቅ ሲል የተሰጠ ምዕዳን እነሆ የተቀደሰውን ወርኃ ጦም ወደ ማጠናቀቅ ተቃርበናል፤ የጦሙን ጉዞ ወደ ማገባደድ ደርሰናል፤ እግዚአብሔር ረድቶንም ወደ ወደቡ ልንደርስ ተጠግተናል፡፡ ነገር ግን እንዲህ በመኾኑ ልል ዘሊላን ልንኾን አይገባንም፤ ይህን ምክንያት አድርገን ከከዚህ በፊቱ ላይ ትጋታችንንና ንቃታችንን እጅጉን እንጨምር እንጂ፡፡ የመርከብ አለቆች ብዙ ባሕረኞችንና ዕቃ ጭነው ረጅም የባሕር ላይ ጉዞ ካደረጉ በኋላ ወደ ወደቡ ሊደርሱ ሲሉ መርከባቸው ከዓለት ጋር እንዳትጋጭና ድካማቸውን ኹሉ ከንቱ ላለማድረግ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡ ሯጮችም እንደዚሁ ወደ መጨረሻው መስመር ሊቃረቡ ሲሉ ኃይላቸውን ኹሉ አሟጥጠው ተጠቅመው ሽልማቱን ለመውሰድ ይጥራሉ፡፡ ትግለኞችም ምንም እንኳን ስፍር ቊጥር የሌለው ቡጢ ቢደርስባቸውም፣ ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ተመትተው ቢወድቁም ሽል ማቱን ይወስዱ ዘንድ የመጨረሻውን ዙር ትግል እጅግ ከፍ ባለ ጉልበ ት ይታገላሉ፡፡ ስለዚህ የመርከብ አለቆች፣ ሯጮችና ትግለኞች ድል ወደ ማድረግ ሲቃረቡ እጅግ ከፍ ያለ ትጋትና ጥንቃቄ ኃይልም እንደሚጠቀሙ፥ እኛም ወደ ታላቁ ሳምንት ደርሰናልና እግዚአብሔር ስለረዳን እያመሰገንን ጸሎታችንን፣ ተአምኖ ኃጢአታችንን፣ በጎ ምግባራችንን፣ ምጽዋ ታችንን፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለን መስተጋብራችንን፣ ራስን የመግዛት ጠባያችንን፣ እንደዚሁም ይህን የመሰለው ሌላው ምግባራችንን ከፍ ባለ ትጋትና ጥንቃቄ ልንፈጽም ይገባናል፡፡ እነዚህን በጎ በጎ ነገሮችን ወደ ጌታ ቀን (ወደ በዓለ ትንሣኤ) የምንደርስ ከኾነ ከጌታችን ዘንድ ባለሟልነትን እናገኛለን፤ ከማዕዱ ዘንድ መሳተፍ ይቻለናል፡፡  (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አምስቱ የንስሐ መንገዶች፣ ገጽ 148)     @beteafework  @beteafework 
نمایش همه...
56👍 16🙏 6🏆 2