የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
رفتن به کانال در Telegram
ኢዜማ ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጎች መብት የተከበረባት፣ ማኅበራዊ ፍትህ የሰፈነባት ሰላማዊ እና የበለፀገች ሀገር እንድትሆን የሚሠራ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ነው።
نمایش بیشتر2 946
مشترکین
+324 ساعت
+27 روز
-1830 روز
آرشیو پست ها
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( #ኢዜማ )
እንኳን ለ 2019 ዓ.ም አደረሳችሁ!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
#ኢዜማ #ezema
#ኢትዮጵያ #Ethiopia
#አዲስ_ዓመት
የኢዜማ ሊቀመንበር ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ የአዲስ ዓመት መልዕክት
#ኢዜማ #ezema
#ኢትዮጵያ #Ethiopia
#አዲስ_ዓመት
የኢዜማ መሪ ኢዮብ መሳፍንት የአዲስ ዓመት መልዕክት
#ኢዜማ #ezema
#ኢትዮጵያ #Ethiopia
#አዲስ_ዓመት
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው የነብዩ መሀመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ።
መልካም በዓል!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
#ኢዜማ #ezema
#ኢትዮጵያ #Ethiopia
በ #ኢዜማ ዕይታ፤
«ያለን አንድ ሀገር ነው፤ በዚህ ሀገር ውሰጥ የሚኖር ሕዝብ አንድ ሕዝብ ነው» ይኽ ማለት ይህ ሕዝብ አንድ ቋንቋ፣ አንድ እምነት እና አንድ ባህል ብቻ ያለው ሕዝብ ነው ማለት አይደለም።
#ኢዜማ #ezema
#ኢትዮጵያ #Ethiopia
+1
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ምርጫ ክልል የ #ኢዜማ አባል የሆኑት ደምስ ገብሬ በኃላፊነት የሚመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በድጋሚ ስኬታማ ዓመትን አሳለፈ።
በክልሉ ሳይንስ፣ ኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ በተካሔደው የ 2018 ዓ.ም. የአፈፃፀም ምዘና የዞኑ መምሪያ 97.4 % እንዲሁም በኮደርስ አፈፃፀም 98.3 በማምጣት ክክልሉ 1ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ የዕውቅና እና የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶለታል።
ከዚህ ቀደም ይኸው መምሪያ በአባላችን እየተመራ ባለፈው 2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2018 እቅድ መድረክ ላይ በአጠቃላይ አፈፃፀም 1ኛ በመውጣት ሽልማት እንደተበረከተለት ይታወሳል።
ኢዜማ እሴቶቼ ናቸው ሲል ካስቀመጣቸው መካከል አንደኛው ልኅቀት (Excellence) ሲሆን የሀገራችን በርካታ ችግሮች መፍትሔ ማግኘት የሚችሉት ልኅቀትን መመዘኛ ባደረገ የሥራ ውጤት መለኪያ ብቻ ነው የሚል ጠንካራ እምነት ያለው ሲሆን ይህንን ልህቀት ለሚያሳዩ አባላት እንዲሁም የፓርቲው ልዩ ልዩ አሀዶች ዕውቅናን እንደሚሠጥም በግልጽ አስቀምጧል።
በዚሁ መሠረት የፓርቲያችን አባል ደምስ ገብሬ በአመራርነት ለተቋሙ ስኬታማነት ከሌሎች ሠራተኞች ጋር በመሆን ለዚህ ውጤት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና እያቀረበ በተጨማሪም ከፍ ያለ ኩራት እንደተሠማው ለመግለጽ ይወዳል።
#ኢዜማ #ezema
#ኢትዮጵያ #Ethiopia
ከሐምሌ 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሔደ ባለው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ፤ በተለዩት አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት ከተደረገው ምደባ ጋር በተያያዘ የነበረውን ቅሬታ እንዲሁም እንዴት ተፈታ የሚለውን አሰመልክቶ የኢዜማ ተወካይ ዮሐንስ መኮንን ከebs television ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይከታተሉ።
#ኢዜማ #ezema
#ኢትዮጵያ #Ethiopia
#ሀገራዊ_ምክክር #National_Dialogue
https://youtu.be/z8ezXkhL7mk?si=P41o2cRfQ32Sbt93
ለሰላም የቀረበውን ጥሪ አስመልክቶ ከኢዜማ የተሠጠ የድጋፍ መግለጫ!!
በ 8 ፓርቲዎችና 11 ሲቪክ ማሕበራት የተቋቋመው የትግራይ ሰላምና ለውጥ ፈላጊዎች እንቅስቃሴ ሕጋዊ አካልነቱን ባጣው ሕወሓት አማካኝነት በትግራይ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለው አፈና፣ ስቃይ እና እንግልት እንዲቆም እና ጦርነት እንዲቀር ጫና ለማድረግ ያለመ የሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እንደጠራ መረጃ ደርሶናል፤ የለውጥ እንቅስቃሴው ሁሉም ይህን ሰላማዊ ዓላማ የሚደግፉ ኢትዮጵያውያን በሰልፉ ድጋፋቸውን እንዲሰጡም ጥሪ አቅርቧል።
ፓርቲያችን ኢዜማ የትግራይን ህዝብ ከዳግም ጦርነት እና ስቃይ ለማዳን የሚደረጉ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ እንደሚደግፍ በተደጋጋሚ በገለፀው መሠረት ለዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ይፋዊ ድጋፉን እየገለፀ የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎችም በሰልፉ በመገኘት እምቢ ለጦርነት የሚል ድጋፋቸውን እንዲያሳዩ ጥሪውን ያቀርባል።
እምቢ ለጦርነት!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
የኢዜማ ም/መሪ ንጋቱ ወልዴ ሀገራዊ ምክክሩን አስመልክቶ ከ NBC Ethiopia ጋር ያደረጉትን ቆይታ ነገ ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም ከምሽት 3:00 ሰዓት ጀምሮ ይከታተሉ።
#ኢዜማ #ezema
#ኢትዮጵያ #Ethiopia
+8
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) አመራሮች እና የቋሚ ኮሚቴ አባላት በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ለመወያያነት የቀረቡ አጀንዳዎችን ፓርቲው ለሃገራዊ ምክክር ካዘጋጃቸው አጀንዳዎች አንፃር ፈተሹ።
ውይይቱን የፓርቲው መሪ ኢዮብ መሣፍንት እና ሊቀመንበሩ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ ባቀረቡት መነሻ ሐሣብ የተጀመረ ሲሆን ተሳታፊዎች ተጨማሪ ሐሣቦችን አቅርበው ተወያይተዋል።
የውይይቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ምክትል ሊ/መንበር ማዕረጉ ግርማ ሀገራዊ ምክክር የኢዜማ ጉዳይ ብቻ እስኪመስል የተከታተልነው ዓበይት ጉዳይ መሆኑን ገልፀው በጉባኤውም ፓርቲውን ወክለው የሚሣተፉ አመራሮች ምን ያህል እንደተዘጋጀንበት እንደሚያሣዩ ጥርጥር የለኝም ሲሉ ገልፀዋል፤ መድረኩን የፓርቲው ም/መሪ ንጋቱ ወልዴ መርተውታል።
#ኢዜማ #ezema
#ኢትዮጵያ #Ethiopia
የኢዜማ አመራር የሆኑት ዮሐንስ መኮንን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በአሐዱ ራዲዮ አሐዱ መድረክ ላይ ያደረጉትን ቆይታ ይከታተሉ።
https://youtu.be/496wrQ6xdH0?si=NGx1sSS4thuzDufF
#ኢዜማ #ezema
#ኢትዮጵያ #Ethiopia
በትግራይ የሚገኙ ዜጎቻችን ወደጦርነት ላለመግባት በሚያደርጉት ጥረት ሁሉ ከጎናቸው እንደምንቆም እንገልፃለን!!
እምቢ ለጦርነት!!
ኣብ ትግራይ ዝርከቡ ዜጋታትና ናብ ጦርነት ንዘይምእታይ ኣብ ዝገብርዎለው ፃዕሪ ኹሉ ኣብ ጎኖም ጠጠው ከም እንብል ክንገልፅ ንፎቱ!!
እምቢ ንጦርነት!!
We reaffirm our unwavering commitment to stand with our citizens in Tigray in all their efforts to prevent war and safeguard peace.
No to war!!
#ኢዜማ #Ezema
#ኢትዮጵያ #Ethiopia
#እምቢ_ለጦርነት #NoToWar
ዛሬ ምሽት 3:00 ሰዓት
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) መሪ ኢዮብ መሳፍንት በ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) አንድ ዕድል ፕሮግራም ላይ ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ።
#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
የኢዜማ መሪ ኢዮብ መሳፍንት በተለያዩ ጉዳዮች በ EBC ወቅታዊ ፕሮግራም ላይ ያደረጉትን ቆይታ ይከታተሉ
https://youtu.be/ULHkENupbs8?si=TIiPX99y0jmZbYDu
የሀገር አቀፉ ምርጫ 2018 ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከኢዜማ የተሠጠ መግለጫ!!
ሀገር አቀፉ ምርጫ 2018 መጠናቀቁን በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ የምርጫ ውጤት በማሣወቅ አረጋግጧል፤ ምርጫው ከነእንከኖቹም ቢሆን በሰላም በመጠናቀቁ ፓርቲያችን እንኳን ደስ አለን ለማለት ይወዳል።
በተጨማሪም ፓርቲያችን ለውድድር በቀረበባቸው ቦታዎች 13 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና 73 የክልል እና የከተማ ምክር ቤት ወንበሮችን በድምሩ 86 መቀመጫዎችን በማግኘት በሀገር አቀፍ ደረጃ ቀዳሚው ተፎካካሪ ፓርቲ ሆኖ አጠናቋል። ይህንን ተጨባጭ ስኬት ላስመዘገቡ የፓርቲያችን ዕጩዎች፣ አባላት፣ ደጋፊዎች እና በሂደቱ በቅንነት ለተሳተፉ አካላት ሁሉ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል።
ፓርቲያችን ከቀጣዩ ምርጫ በፊት ባሉት ዓመታት ጠንካራ ጎኖቹን በማስቀጠል እንዲሁም የነበሩበትን ክፍተቶች በስትራቴጂ እና ሌሎች አስፈላጊ ተግባራት በመሙላት ተጨባጭ የተፎካካሪ ፓርቲነት ሚናውን ጊዜ ሳያባክን የሚጀምረው ዛሬ መሆኑን እየገለፅን፤ በነዚህ ዓመታት ከዚህ ቀደም ስናደርገው እንደነበረ ሁሉ ብሔራዊ ጥቅሞችን በሚያሣኩ ጉዳዮች ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃይል ጋር በመተባበር የምንንቀሳቀስበት መፎካከሪያ አጀንዳዎች ላይ ማኅበረሰባችንን በሚመጥን ጨዋነት ልዩነቶቻችንን እና ትችቶቻችንን እያቀረብን የጀመርነውን ጤናማና ዘመናዊ የፖለቲካ ባሕል የማዋለድ ተግባራችንን በተጠናከረ መልኩ የምንቀጥልበት እንዲሁም ለተጨማሪ ስኬት የምንንደረደርበት እንደሚሆን ቃል እንገባለን።
በመጨረሻም ገዢ ሆኖ እንዲቀጥል ለተመረጠው ብልጽግና ፓርቲ እንዲሁም በውድድሩ ተሳትፋችሁ የሕዝብ ውክልናን ላሳካችሁ ተፎካካሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን።
አሸናፊው ፓርቲ ከዛሬ ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለመገንባትና ፍትሐዊ የፖለቲካ ምህዳርን ለሁሉም እኩል ተደራሽ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንዲሠራ፤ ለሀገር እድገትና ለውጥ ጠቃሚ ሀሳቦች ከማንኛውም ወገን ሊገኙ እንደሚችሉ በመረዳት አማራጭ ሃሳቦችን እንዲሰማ፤ እንዲሁም ትችቶችን በሆደ ሰፊነት እያስተናገደ ሀገራችን የሚያስፈልጋትን ዴሞክራሲ በጋራ እንድንገነባ ጥሪ እናቀርባለን።
#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
#ምርጫ_2018
የኢዜማ መሪ ኢዮብ መሳፍንት ምርጫውን እና ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከ NBC ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉትን ቆይታ ዛሬ ምሽት 3:00 ሰዓት ይከታተሉ።
https://youtu.be/q4kVabVLsrI?si=-NmZ6E2AHaPrSibB
#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
የ #ኢዜማ አዲስ አበባ ምርጫ ክልል 19 አባል እና የሴቶች መምሪያ ቋሚ ኮሚቴ አባል የነበሩት ሊሊ ኃይሉ በትላንትናው ዕለት ሰኔ 11/ 2018 ዓ.ም. ባደረባቸው ሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ፓርቲያችን በአባላችን ሕልፈት የተሠማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው፣ ዘመድ እና ወዳጆቻቸው በቶሎ መጽናናትን ይመኛል።
ጦርነትን ሳይጀመር ማስቆም የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ የቤት ሥራ ሊሆን ይገባል!!ሀገራችን በታሪኳ እስከአሁን ድረስ በተለያዩ የኃይል አማራጮች ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁም የመንግሥት ሥልጣንን ለመቀየር ስትባዝን አለች፤ ሆኖም የረጅም ዓመት ሀገረ መንግሥት ታሪኳን በማይመጥን መልኩ እስከአሁን ኋላቀር ከሚባሉት ሀገራት ግንባር ቀደም ከመሆን የዘለለ አንዳች ነገር አላገኘችም። ላለፉት ከ 30 ዓመታት በላይ በሀገሪቱ ውስጥ ላሉ ችግሮች፣ ግጭቶች፣ ጥቃቶች እንዲሁም ሌሎች በርካታ ችግሮች በዋነኛነት ምክንያቱ ደግሞ ሕወሓት ሥልጣነ መንበሩን በኃይል ካረጋገጠ በኋላ ያሠፈነው የብሔር ፖለቲካ ነው። ይኽ የፖለቲካ ሥርዓት ከፍተኛ ችግር ያስከተለ ቢሆንም በሕወሓት ተንኳሽነት የተጀመረው እና ከሁለት ዓመታት በላይ የፈጀው የሰሜኑ ጦርነት ያስከተለውን የሰው ህይወትና የንብረት ውድመት በከፍተኛነቱ የሚስተካከለው የለም። ከዚህ ጥፋት መልስ በፕሪቶሪያ ስምምነት ከጦርነት መውጣት የተቻለ ቢሆንም ይህ በዘላቂነት እንዳይቀጥል በተለይ ሕጋዊ ማንነቱን ባጣው ሕወሓት በኩል እንደሥምምነቱ እንዳይፈፀም የታዩ ዳተኝነቶች እና እንደ አጠቃላይ የፖለቲካ ሥሪቱ ላይ ውጤት ሊያመጣ የሚችለውን ሀገራዊ ምክክር፣ የ2018 ዓ.ም ምርጫ በትግራይ ክልል እንዳይከናውን በማድረግ፣ በክልሉ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እንዳይመለሱ በታጋችነት በመያዝ በአጠቃላይ በክልሉ ያለው ችግር እንዳይፈታ በማድረግ ይኸው ችግር መልሶ ይፈጠር ይሆን የሚል ስጋትን እንደያዘ አለ። ለትግራይ ማኅበረሰብ እቆረቆራለሁ የሚለው ይህ ቡድን ከእሰጠዓገባ ውጪ መኖር የማይችል በሚመስል መልኩ የተለያዩ ችግሮችን ለመፍጠር እየሞከረ የከረመ ሲሆን ግንቦት 02/2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እና በክልሉ አፀደቀ በተባለው አዋጅ ግልጽ የጦርነት አዋጅን ለፍፏል። በተለይም በአዋጁ ያካተተው አስገዳጅ የወታደር ምልመላ፤ የተለዩ ድምፆች በትግራይ እንዳይሰሙ ያስቀመጠው ልጓም፤ ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር የሚመስለው የፕሮፖጋንዳ ልፈፋ ይኽንን ተፈጥሯዊ ጠበኛ ባሕርዩን እና ፍላጎቱ አሁንም የትግራይን እና አጠቃላይ የኢትዮጵያን ህዝብ በስንት ልፋት ወዳስቆመው ጦርነት እና እልቂት መክተት መሆኑን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። በመሰረቱ አዋጁን ማውጣቱ እና በተለይም ከወታደር ምልመላ እና ጦርነቱን ካለመደገፍ ጋር በተገናኘ የተካተቱት ቅጣቶች ማኅበረሰቡ በጦርነቱ ለመሣተፍ ፍላጎት እንደሌለው እና በዚህም ቡድኑ ስጋት ያደረበት መሆኑን በግልፅ የሚያሣይ ነው፤ ይህ ተስፋ የቆረጠ እድሜያቸው የገፋ የሥልጣን ጥመኞች ስብስብ አሁንም በግጭት ውስጥ አፍላ ወጣቶችን የመማገድ ዓላማ አድርጎ ከዚህ ቀደም ልጆቻቸውን ያጡትን እናቶች፤ በስለት ከጦርነቱ የተረፈ የቀረ ልጅ ያላቸውን ጧሪ ቀባሪያቸውን ሊነጥቃቸው አሰፍስፎ መምጣቱ ለትግራይ ህዝብም ሆነ ለሰው ልጆች ሁሉ እንጥፍጣፊ ርህራሄ እንደሌለው ያሳያል። ይህንን ኃይል በቃህ ማለት እና በትግራይ ያሉ ወገኖቻችንን ከማያባራ መከራ መታደግ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን የጋራ የቤት ሥራ ሊሆን ይገባል፤ ጦርነትን ሳይጀመር በፊት ማስቆም ይገባናል። ኢዜማ የትኛውም ፖለቲካዊ ችግር በውይይት መፈታት አለበት ብሎ በጽኑ የሚያምን ሲሆን ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆነን እንደ ሕወሓት ዓይነት ደም የማይጠረቃ አካል እና እሱን የሚዘውሩ ጥቂት ግለሰቦች በቃችሁ ብሎ ለማስቆም እና የትግራይ ህዝብን ካላስፈላጊ መከራ ለመታደግ በህዝብ ላይ ምንም አይነት መስዋዕትነት በማያስከትል መልኩ በሕገወጥ ቡድኑ ላይ ብቻ ያነጣጠረ አስፈላጊ ሕጋዊ እርምጃ በመንግሥት እና ከመንግሥት ጋር በጋራ በሚቆሙ ማንኛውም ለትግራይ ማኅበረሰብ በሚቆረቆር አካል ሊወሰድ እንደሚገባ ያምናል፤ ማኅበረሰቡም አሁን ለጦርነት ዕያሣየ ያለውን እምቢተኝነት በተጠናከረ መልኩ እንዲገፋበት ጥሪ እናቀርባለን። በመጨረሻም በዚህ ሒደት ውስጥ ፓርቲያችን ማኅበረሰቡ እያለፈበት ያለውን ጭንቀት እየኖረበት ያለውን አሰቃቂ ሁኔታ ለመቅረፍ ባለው አቅም ሁሉ በቀጥታ ለማገዝ ከማንኛውም ሀገራዊ ኃይል ጋር በጋራ ለመሥራትና የበኩሉን ለማበርከት ዝግጁ መሆኑን ያረጋግጣል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ግንቦት 04/ 2018 ዓ.ም.
