cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

DW Amharic

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
42 412
مشترکین
+1124 ساعت
+1877 روز
+1 31030 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
የተወደዳችሁ የዶቹ ቬለ አድማጮች የሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ስርጭታችን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በፌስቡክ በቀጥታ ይደመጣል። ለዕለቱ ካጠናቀርናቸው ዘገባዎች መካከል፤ የኦሮሚያው ግጭት እና የሰላማዊ ሰዎች አበሳ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የምሥራቅ ሀረርጌ ሀገረ ስብከት በሐረር ከተማ የሚገኝ የቤተክርስትያኒቱ ይዞታ ከሕግ ውጭ እንዲፈርስ ተደርጓል ማለቱ፤ በትግራይ ክልል ከተደረገዉ ጦርነት በኋላ የሥራ አጥነት ችግር፣ ስደት እና የወጣቶች ለሱስና ሌሎች ችግሮች ተጋላጭነት እያሻቀበ መሆኑን የሚያስቃኙት ይገኙበታል። ኦቲዝም በነርቭ ከፍተኛ ህክምና ባለሙያ እንዴት ይገለጻል? ይህንን የሚመለከት መሰናዶም ይኖረናል። በሰዓቱ ተገንታችሁ እንድትከታተሉን ከወዲሁ የአክብሮት ግብዣችን ይድረሳችሁ።
نمایش همه...
የተከበራችሁ የዶቼ ቬለ አድማጭ ተከታታዮች፤ በየዕለቱ የዜና እና የዜና መጽሔት ጥንቅሮቻችንን ከዩቲዩብ ቻናላችን ማግኘት እንደምትችሉ እናስታውሳችሁ። ትክክለኛው የዶይቼ ቬለ የዩቲዩብ ቻናል ከታች ያለው ሲሆን እስከዛሬ ሰብስክራብ ያላደረጋችሁ በማድረግ በዩቲዩብም ቤተሰብ እንሁን። ለሌሎችም ማጋራት አትርሱ። እናመሰግናለን። https://www.youtube.com/@dwamharic/videos
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ፔን አሜሪካ የተሰኘው ሃሳብን በነጻነት ለመግለጽ መብት የሚሟገተው ተቋም የዘንድሮ ዓመታዊ የሽልማት መርሃግብሩን ሰረዘ። ተቋሙ መርሃግብሩን የሰረዘው ለሽልማት ከተመረጡት ግማሽ የሚሆኑት እጩ ጸሐፊዎች ጋዛ ላይ የሚካሄደው ጦርነት በመቃወም ራሳቸውን በማግለላቸው ነው። ፔን አሜሪካ በመጪው ሳምንት ሰኞ ዕለት ኒው ዮርክ ከተማ ላይ ሊያካሂድ አቅዶት የነበረውን የዘንድሮውን የሽልማት መርሃግብር መሰረዙን ትናንት ይፋ ማድረጉ ተሰምቷል። ለዚህ መርሃግብር በእጩነት ከተመረጡት ከ61 ጸሐፊዎችና ተርጓሚዎች፤ 28 የሚሆኑት ፔን አሜሪካ ለፍልስጤማውያን ጸሐፊዎች ድጋፍ አላደረገም ማለታቸው ነው የተገለጸው። ሥራዎቻቸውን ለግምገማ ካቀረቡት መካከልም ጽሑፎቻቸው እንዲመለሱላቸው የጠየቁም አሉ ነው የተባለው። የድርጅቱ የፕሮግራም ኃላፊ ክላሪስ ሮዛስ ሻሪፍ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ድርጅታቸው እጩዎቹ በቀረቡበት ዘርፍ ላለመሳተፍ መወሰናቸውን እንደሚያከብር ተናግረዋል። ለውድድር የቀረቡት ሥራዎች በተከበሩና እና በጠንካራ ዳኞች ከተመረጡ በኋላ ይህ ያልተጠበቀ ነገር ሂደቱ እንዲቋረጥ በማድረጉ እንደሚያዝኑም አመልክተዋል። ይህ የፔን አሜሪካ ዓመታዊ መርሃግብር ከጎርጎሪዮሳዊው 1963 ዓም ጀምሮ በተለያዩ የስነጽሁፍ ዘርፎች በልብ ወለድ፤ በግጥም፤ የልጆች ስነጽሑፍና ቴያትር ጭምር ለተዘጋጁ ግሩም ሥራዎች እውቅና ሲሰጥ ቆይቷል። የዘንድሮው የሽልማት እጩዎች ራሳቸውን ያገለሉት ጋዛ ላይ የሚደርሰውን ወታደራዊ ጥቃት እንዲቃወም ለቀረበለት ጥሪ ምላሽ ባለመስጠቱ እንደሆነ ተገልጿል። በየካቲት ወር ከ1,300 የሚበልጡ ጸሐፊዎች እና ገጣሚዎች ተቋሙ መጽሐፍት ሲታገዱ እንደሚያደርጉት ለፍልስጤማውያን የሰብአዊ መብትም ድምጽ እንዲሆን ተጠይቆ ነበር። እጩዎቹ ራሳቸውን ካገለሉ በኋላ ፔን አሜሪካ ለአሸናፊነት የተመረጡትን ሥራዎች ይፋ አድርጓል።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ከገዢው ፓርቲ ብልጽግና ጋር ድርድር እያካሄዱ ነው መባሉን ህወሃት አስተባበለ። ፓርቲው በፌስቡክ ማኅበራዊ መገናኛ ገጹ ዛሩ ባሰራጨው አጠር ያለ መግለጫ ህወሃት ከብልጽግና ጋር የሚያደርገው ድርድር ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ለማስፋትና ለማጠናከር ያለመ ነው ብሏል። ህወሃትና እና ብልጽግና መሠረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት እንዳላቸው ያመለከተው ፓርቲው ልዩነታቸው እንዳለ ሆኖ ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች እንዳሉም አመልክቷል። እንዲያም ሆኖ «ህወሃት ከብልጽግና ጋር ለመቀላቀል ንግግሮች ተጀምረዋል የሚባለው አባባል ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው» ሲል ይህን በተመለከተ የሚናፈሰውን መረጃ አስተባብሏል።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
በአማራ ክልል ሰሜን ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አስታወቀ። ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ ም ከምሽቱ ሦስት ሰዓት መንስኤው እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት በፓርኩ የተለያዩ አካባቢዎች የእሳት ቃጠሎ መነሳቱ ነው የተገለጸው። እሳቱ በአካባቢው ሕዝብ ርብርብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ የተናገሩት የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቢምረው ካሣ በድርጊቱ የተጠረጠሩ ሦስት ሰዎች መያዛቸውን አመልክተዋል። በተጠርጣሪዎቹ ላይ በሕግ አግባብ ምርመራ ተደርጎ ጉዳዩ የሚጣራ መሆኑን፤ ቃጠሎው ያደረሰው የጉዳት መጠንም ተጣርቶ ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል። የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኝበት አካባቢ ሦስት ዓይነት የአየር ጠባይ እንዳለና በየዓመቱም ተመሳሳይ የእሳት አደጋ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እንደሚከሰት ነው ባለሥልጣኑ የገለጹት። ከቀናት በፊት የተነሳው እሳት በፓርኩ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እንደነበር በማመልከትም ፓርኩ ጓሳ እንደመሆኑ የተዳፈነ እሳት ንፋስ አቀጣጥሎት እንዳይነሳ ክትትል የማድረግ ጥረት መኖሩንም ተናግረዋል። የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በጎርጎሪዮስ የዘመን ቀመር በ1978 በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ከጅቡቲ የባሕር ወደብ አቅራቢያ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ሰጥማ በደረሰው አደጋ 16 ተሰዳጆች መሞታቸው ተገለጸ። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት IOM ዛሬ እንዳስታወቀው 28ቱ የጀልባዋ ተሳፋሪዎች እስካሁን አልተገኙም። ጀልባዋ 77 ተሰዳጆችን አሳፍራ እንደነበር ነው IOM በኤክስ ገጹ ይፋ ባደረገው አጭር መረጃ ያመለከተው። ከተሳፋሪዎቹ ውስጥም ልጆች እንደሚገኙበትም አስታውቋል። የጅቡቲ መንግሥት የአደጋ ጊዜ ሕይወት አድን ሠራተኞች ባሕር ላይ በደረሰው አደጋ የተጎዱትን ለማዳን ጥረት እያደረጉ እንደሆነም ገልጸዋል። እንዲህ ያለ አደጋ በተሰዳጆች ላይ በተጠቀሰው አካባቢ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሲደርስ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። የዛሬ ሁለት ሳምንት በጅቡቲ የባሕር ጠረፍ አቅራቢያ በደረሰው ተመሳሳይ የጀልባ አደጋ ልጆች ጨምሮ 38 ስተደኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በተያያዘ ዜና ከፈረንሳይዋ ካሌ ደሴት ወደ ብሪታንያ ለመሻገር ሲሞክሩ አምስት ስደተኞች ባሕር ላይ በደረሰ አደጋ መሞታቸው ተሰምቷል። ሟቾቹን ጨምሮ ከመቶ በላይ ስደተኞችን ጭና የነበረች መርከብ የገጠማትን አደጋ ተከትሎ የፈረንሳይ የባሕር ኃይል መርከቦች በስፍራው ደርሰው ተሳፋሪዎቹን ለማውጣት መቻላቸው ነው የተገለጸው። ተሰዳጆቹ ወደ ብሪታንያ ለመሻገር በሞከሩበት ምሽቱን የብሪታኒያ መንግሥት በሀገሪቱ የሚገኙ ሕገወጥ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለማሻገር የሚያስችለውን ሕግ አጽድቋል።
نمایش همه...
የእስራኤል እና የኢራን ቁርቁስ ወዴት ያመራል? የኢራን እና የእስራኤልን ቁርቁስ በአንክሮ የሚከታተሉ ጉምቱ ዲፕሎማቶች እና ተንታኞች መካከለኛው ምሥራቅን የሚያዳርስ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ሰግተዋል። በደማስቆ የተፈጸመ ጥቃት የሁለቱን ሀገራት የበርካታ አስርት ዓመታት የእጅ አዙር ፍልሚያ ገሀድ ቢያወጣውም በመካከላቸው በቂ ቂም እና አለመተማመን አለ። https://p.dw.com/p/4f0oi ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 DW
نمایش همه...
የሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 22ኛ ሣምንቱን በያዘው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጨዋታ በሳምንቱ መጨረሻ የተገናኙት ኢትዮጵያ ቡናና መቻል 1 - 1 በመለያየት ነጥብ ተጋርተው ውጥተዋል። እንግሊዝ ፕሪምየርሊግ በሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታዎች ሊቨርፑል ኤቨርተን ክርስታል ፓላስ እናአስቶን ቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሽንፈዋል። ኤፍ ኤ ካፕ ማንችስተር ዪናትድና ማንችስተር ሲቲ ለዋንጫ ይፋለምሉ። https://p.dw.com/p/4f3GK?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 DW
نمایش همه...
በሃሰተኛ ሰነድ ገንዘብ በማዘዋወር የተጠረጠሩት የሃይማኖት አባት ጉዳይ ባለፈው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብና ከአፍሪካ ኅብረት የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም፣ ከአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል። https://p.dw.com/p/4f3tt?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
نمایش همه...
በኢትዮጵያ ጉዳይ የሰባት ሀገራት የጋራ ጥሪ ኢትዮጵያ ውስጥ የተወሳሰቡ የፖለቲካ እና የጸጥታ ቀውሶችን ለመፍታት ብሎም በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ውይይት ማድረግ መሆኑን በኢትዮጵያ የሚገኙ የ 7 ሀገራት ኤምባሲዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ ገለፁ። https://p.dw.com/p/4f2dQ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 DW
نمایش همه...
የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በጋምቤላ ያደረሱት ጥቃት በጋምቤላ ክልል አኙዋ ብሔረሰብ ዞን ጆር ወረዳ ውስጥ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎችና በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ጸረ ሰላም የተባሉ ሀይሎች በመተባበር ባደረሱት ጥቃት 738 ቤቶች መቃጠላቸው ተገለጸ፡፡ https://p.dw.com/p/4f3Gd?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
نمایش همه...
ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አቋም የገንዘብ ሚንሰትር አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት ሰሞኑን ከዓለም ባንክ (WB) እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF) ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በዩናይትድ ስቴትስ ተወያይተዋል። https://p.dw.com/p/4f3RI?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
نمایش همه...
ከራያ አላማጣና ሌሎች ወረዳዎች ብዙ ህዝብ እየተፈናቀለ ነው ሰሞኑን በራያ አላማጣና አካባቢው ከተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ጋር በተያያዘ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች አሁንም ህብረተሰቡ ከሚያደርግላቸው ድጋፍ ውጪ ድጋፍ እንዳላገኙ አመለከቱ። https://p.dw.com/p/4f2hb?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
نمایش همه...
የሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና https://p.dw.com/p/4f4AO?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 DW
نمایش همه...
https://p.dw.com/p/4edUZ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
نمایش همه...
ዛሬ በተካሄደው 41ኛው የቪየና ከተማ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው ጫላ ረጋሳ አንደኛ በመሆን አሸነፈ። ጫላ ውድድሩን ለመጨረስ 2፡06፡35 ፈጅቶበታል። ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ኬንያውያኑ በርናርድ ሙአ እና አልበርት ካንጎጎ ውድድሩን አጠናቀዋል። የ 26 ዓመቱ ጫላ ለዚህ ውድድር ራሱን በሚገባ አዘጋጅቶ እንደነበር እና ውድድሩን በማሸነፉ ደስተኛ እንደሆነ ለኦስትሪያ መገናኛ ብዙኃን ORF ገልጿል። ጫላ ከ 2 ሰዓት ከ 6 ደቂቃ ያነሰ ለመሮጥ እቅድ ቢኖረውም የአየር ፀባዩ ቀዝቃዛማ መሆኑ እና ከ 32ኛው ኪሎ ሜትር በኋላም ነፋሻማ መሆኑ በኬንያዊው ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ለማሻሻል ሳይችል መቅረቱን ገልጿል። በቪያና ማራቶን ከጎርጎሮሲያኑ 2015 ዓ ም በኋላ ኢትዮጵያዊ አትሌት ማራቶን ሲያሸንፍ ጫላ የመጀመሪያው ነው። በሴቶች ውድድር ኤርትራዊቷ ናዝሬት ወልዱ አንደኛ ስትወጣ ኬንያዊያኖቹ ፌዝ ቼብኮች እና ሬቤካ ታኑኢ 2ኛ እና 3ኛ ሆነው አጠናቀዋል። እንዲሁ ዛሬ በተካሄደው 44ኛው የለንደን ማራቶን ውድድርም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ 2ኛ ወጥተዋል። በወንዶች ምድብ የተሳተፈው ቀነኒሳ በቀለ በርቀቱ ከ40 ዓመት በላይ ዕድሜ የራሱን ሰዓት በመሻሻል 2ኛ ሲወጣ የገባበትም ሰዓት 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ 16 ሰከንድ ሆኗል። በሴቶች ምድብ ብርቱ የአሸናፊነት ግምት የተሰጣት እና የማራቶን የክብረ ወሰን ባለቤት በሴቶች ትዕግስት አሰፋ ተጠባቂውን ውድድር ሁለተኛ በመሆን አጠናቀዋል። በውድድሩ ኬንያዊው አሌክሳንደር ሙቲሶ ሙንያዎ በወንዶች ውድድር አንደኛ በመሆን አሸንፏል። የ 27 ዓመቱ ሙንያዎ ቀነኒሳን 14 ሰከንድ ቀድሞ በመግባት ሊያሸንፍ ችሏል። ብሪታኒያዊው ኢሚለ ቼረስ ሶስተኛ ሆኖ አጠናቋል። በለንደኑ የሴቶች የማራቶን ውድድር ኬንያዊቷ ፔሬስ ጄፕቺርቺር አንደኛ በመሆን ስታሸንፍ «በሴቶች ብቻ የተሮጠ » አዲስ ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ችላለች። ጄፕቺርቺር ውድድሩን ለማጠናቀቅ ሁለት ሰዓት ከ 16 ደቂቃ ከ 16 ሰከንድ ወስዶባታል። ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስትን ተከትላ ሌላዋ ኬንያዊት ጆሲሊነ ጄፕኮስጌ ሶስተኛ ሆና ውድድሩን አጠናቃለች።
نمایش همه...
https://p.dw.com/p/4f1vL?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
نمایش همه...
እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በምትገኘው ራፋህ ከተማ ሌሊቱን በሰነዘረችው ጥቃት 18 ሰዎች ተገደሉ ። በጥቃቱ ከሞቱት መካከል 14ቱ ህጻናት መሆናቸውን የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። የጋዛ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ የሰጠውን መግለጫን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው ባለፉት 24 ሰዓታት እስራኤል በጋዛ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች በድምሩ 48 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ 79 ቆስለዋል። በእስራኤልና ሐማስ መካከል እንደ ጎርጎሮሲያውያን አቆጣጠር ጥቅምት 7 ቀን 2023 ዓ.ም ጦርነት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የሞቱ ፍልስጤማውያን ቁጥር 34,097 ደርሷል። የቆሰሉት ደግሞ 77 ሺህ ተጠግቷል። የእስራኤል ጦር በበኩሉ ምንም አይነት የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሳያቀርብ ከ 13 ሺህ በላይ የሀማስ ተዋጊዎች ያላቸውን መግደሉን አሶሺየትድ ፕረስ ዘግቧል።
نمایش همه...
ዩክሬንን ለመርዳት ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተስማማበትን የርዳታ ጥቅል የውሳኔ ረቂቅ የጀርመን መንግሥት አወደሰ። የጀርመን መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ በ X የማኅበራዊ ትስስር ገፃቸዉ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት « የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሁኑ ጊዜ ለዩክሬን የሚያደርገው ድጋፍ ጠንካራ መልዕክት ያዘለ ነው» ብለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ሀቤክ በበኩላቸው « ራይኒሽ ፖስት» ለተባለው ጋዜጣ እንደተናገሩት የአሜሪካ ውሳኔ የአለም አቀፍ አጋሮችን ቁርጠኝነት የሚያመላክት ነው ብለዋል። የዩክሬይኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ ሌሊቱኑ ለየዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምስጋናቸውን በማቅረብ ውሳኔው ጦርነት እንዳይስፋፋ የሚከላከል እና በሺዎች የሚቆጠር ህዝብን ህይወት የሚታደግ ነው ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ያፀደቀው ረቂቅ በጠቅላላው 95 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህንንም ሴኔቱ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ያም ከሆነ በኋላ 61 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬይን ፤ 13 ቢሊዮን ዶላር ለእስራኤል ፣ ስምንት ቢሊዮን ለታይዋን እንደሚውል ተመልክቷል። በቢሊዮኖች የሚቆጠረውን የዩናይትድ ስቴትስን የርዳታ ጥቅል በተመለከተ ሩሲያ በትችት ምላሽ ሰጥታለች። የዩናይትድ ስቴትስ ይበልጥ የተቀላቀለ ጦርነት ውስጥ እየገባች እንደሆነ እና የቬትናም እና አፍጋኒስታን አይነት ውርደት ሊጠብቃት እንደሚችል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ዛሬ አስጠንቅቀዋል። ሃማስ ዩናይትድ ስቴትስ ለእስራኤል የምታደርገው ወታደራዊ እርዳታ ' ለጋዛ ጥቃት ፍቃድ እንደመስጠት ነው ' ሲል ነቅፏል።
نمایش همه...
https://p.dw.com/p/4ezUe?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
نمایش همه...
ዩናይትድ ስቴትስ ጦሯን ከሀገራቸው እንድታወጣ የሚጠይቁ በመቶችዎ የሚቆጠሩ ኒጀራዊያን ዛሬ ተቋውሟቸውን ለመግለፅ አደባባይ ወጡ። ኒጀራዊያኑ ለተቃውሞ የወጡት ዩናይትድ ስቴትስ በመቶ ሚሊዮን ዶላር ከገነባችው የሰው አልባ አውኖፕላን ጦር ሰፈር ወታደሮቿን ለማስወጣት ዝግጅት ላይ እንዳለች በተሰማ በሁለት ቀናት ልዩነት ነው። ዩናይትድ ስቴትስ ከ1,000 በላይ የሚሆኑ ወታደሮቿን ከኒጀር ለማስወጣት መስማማቷን ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣን አርብ ዕለት ለአዣንስ ፋራንስ ፕረስ ገልፀው ነበር። በዚህም መሠረት ጦሩ በስርዓት ኒጀርን ለቆ የሚወጣበትን መንገድ ለማመቻቸት በሚቀጥሉት ቀናት አንድ የዋሽንግተን ልዑካን ቡድን ወደ ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሀገር ያቀናል። የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ የተካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሰፈር የሚገኝበት አጋዴዝ ከተማ ሲሆን ሰልፉን ያዘጋጁትም ባለፈው አመት መፈንቅለ መንግሥት ያደረገውን ሁንታ አገዛዝ የሚደግፉ 24 የሲቪል ማህበራት ስብስቦች መሆናቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል።
نمایش همه...
በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ ባንጉይ የሚገኝ ወንዝ ውስጥ ሰምጠው የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 58 ደረሰ። የጀልባዋ መስመጥ መንስኤ ከአቅም በላይ ሰዎችን ማሳፈሯ ነበር። እንደ ዓይን እማኞች ገለፃ ከእንጨት የተሰራችው ጀልባ ዓርብ ዕለት በማፖኮ ወንዝ ውስጥ ስትሰምጥ ከ300 በላይ ሰዎችን አሳፍራ ነበር ። ከፊሎች ቆመው ሌሎች በእንጨት ጀልባዋ ላይ ተቀምጠው ተስተውለዋል። የጀልባዋ ተሳፋሪዎች ከባንጉይ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ማኮሎ መንደር የአንድ የመንደር አለቃ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ለመካፈል እያመሩ የነበረ ሲሆን ጉዞ እንደጀመሩ ብዙም ሳይቆይ ጀልባዋ መስመጥ መጀመሯ ተዘግቧል። አደጋው ከተከሰተ ከ 40 ደቂቃ በኋላ የነፍስ አድን ሰራተኞች ቦታው ደርሰዋል። በቁጥር ያልተገለፀ እና ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎችን በሞተር ጀልባ መታደግ መቻሉን እና ሰራተኞቹም እስካሁን 58 አስክሬኖችን ከባህር ማውጣት መቻላቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዋቢውን ጠቅሶ ዘግቧል። የሟቾች ቁጥር እስከ 70 ከፍ ሊል እንደሚችል ይገመታል።
نمایش همه...
ክፍል 5«እውነተኛ ማንነቴ የታለ?» https://p.dw.com/p/4dD5S ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 DW
نمایش همه...
አምስተኛው ዓለም አቀፍ የካካዎ ጉባኤ የደሐ ገበሬዎችን ሕይወት ይቀይር ይሆን? ለቸኮሌት ምርት ዋነኛ ግብአት የሆነው የካካዎ ምርት ባለፉት ጥቂት ወራት ዋጋው በዓለም ዙሪያ በሦስት እጥፍ ጨምሯል ። ገበሬዎች ከፍተኛ ክፍያ እንዲፈጸምላቸውን እና ከድህነት እንዲወጡ ይሻሉ ። ሲታይ ቀላል የሚመስለው ጉዳይ ግን የዚያን ያህል ቀላል አይመስልም ። https://p.dw.com/p/4ezMy?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
نمایش همه...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ምዕምናን ሰልፍ በፍራንክፈርት በጀርመን የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ምዕምናን ፍራንክፈርት ከተማ ሰልፍ አካሔዱ። በተለያዩ የጀርመን ከተሞች የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት አባቶች እና ምዕምናን መሳተፋቸውን በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካሕናት መራዊ ተበጀ ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል። https://p.dw.com/p/4f0Qt?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
نمایش همه...
የደቡብ አፍሪቃ ሃገራት በገዳይ የኮሌራ ወረርሺኝ ተመቱ በደቡብ አፍሪቃ ከዐሥር ዓመት ወዲህ የተስፋፋው የኮሌራ ወረርሺኝ በዋናነት ዛምቢያ፤ ዚምባብዌ እና ማላዊን አጥቅቷል ። ወረርሺኙን ለመቅለበስ የነበረው የክትባት ክምችትም እየተሟጠጠ ነው ። https://p.dw.com/p/4ezHt?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 dw.com
نمایش همه...
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ጥሪ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀርበ። በምክክሩ መድረኩ ለሚሳተፉ ለእነኝሁ አካላት ኮሚሽኑ ተገቢውን የጥበቃ ዋስትና እንደሚያመቻች አስታውቋል። የታጠቁ የሚባሉት ቡድኖች እስከአሁን በአገራዊ የምክክር ጉባዔው ሥለመሳተፍ አለመሳተፋቸው በይፋ ያሉት ነገር የለም። https://p.dw.com/p/4f0U5 ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 dw.com
نمایش همه...
https://p.dw.com/p/4f0kr?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾 dw.com
نمایش همه...
የሚያዝያ 12 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና https://p.dw.com/p/4f0k?maca=amh-RED-Telegram-dwcom አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ 👉🏾
نمایش همه...
01:42
Video unavailableShow in Telegram
የኮሚሽኑ የምክከር ጥሪ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀርበ ፡፡ ኮሚሽኑ በምክክር ጉባዔው የሚሳተፉ የኦሮሚያ ክልል ማህበረሰብ ተወካዮች የማጠቃለያ ልየታ መድረክ በሻሸመኔ ከተማ እካሂዷል ፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ የሥራ ሃላፊዎች የኮሚሽኑን የሥራ ሂደት አስመልከተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ “ ያሏቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡ በምክክሩ ለሚሳተፉት ለእነኝሁ አካላት ኮሚሽኑ ተገቢውን የጥበቃ ዋስትና እንደሚያመቻች ነው ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እና ምክትል ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ሒሩት ገብረስላሴ የገለጹት ፡፡ ዘገባ ፡ ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዶቼ ቬለ
نمایش همه...
نمایش همه...
نمایش همه...
نمایش همه...
نمایش همه...