cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ለሩህ°ቅመም

پست‌های تبلیغاتی
1 304
مشترکین
+224 ساعت
+27 روز
+430 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ወንድ ልጅን እንዲያ እና እንዲህ እያሉ ከብዙ ነገር ሊያጥሩት ቢችሉም ፍቅር ዘንድ ሲሆን ግን ፈፅሞ አይችሉትም። የትኛውም ወንድ ስለፍቅር ወደደም ጠላ ዝቅ ይላል። ፍቅሩ ከልቡ እንደሆን ክብሬን ብሎ የሚገፋው ፍቅር አይኖርም። በታሪክ መዛግብት ብዙ የተባለላቸው ቀይስ (መጅኑን ለይላ) ፣ ሮሚዮ ለዚሁ ፍቅር የሚሉት አለም የከፈሉት መስዋዕትነት ወንድ ከመሆንም በላይ ነበር። ከሁሉ በላይ ደግም (ረሱሊ አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ለፍቅር የነበራቸው መተናነስ ና ቦታ የፍቅርን ማዕና በግልፅ የሚያሳየን ነው። ለኸዲጃ «እሷን መውደድ ተሰጠሁኝ» ያሉበት ንግግር ቃላቶቹ ጥልቅ ናቸው። ስለፍቅር የሆኑትና የተሆነላቸው ሁሉ የፍቅርን ከፍታ የሚያሳዩን ናቸው። ዘለቅ ስንል ደግሞ የአላህና የመልዕክተኛው ሙሀመድ (አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ፍቅር ከሁሉ ልቆ በቂ ማሳያችን ነው። በአላህ ቃል ላይ ለዩሱፍ «በእውነቱ ፍቅሩ ልቧን መቷታል» የተባለላት ዙለይካ ስለፍቅር የሆነችውን ሁሉ ታሪክ ቆሞ ይመሰክራል። የዐሊይ ና የፋጢማም ፍቅር ምሳሌያችን ነው። ስለፍቅር መተናነስና እጅ መስጠት ማለት ሲሩ ብዙ እንደሆነ ያመላክተናል። ፍቅር መንገዱን አይሳት እንጂ ከሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎቶች ውስጥ ወሳኙ ጉዳይ ነው። በቃ ከልብ የሆነ ፍቅር ከአላህ ከራሱ የሆነ ኒዕማ ነው። ታዲያ ግን በኛ ዘመን ስለቆሸሸውና ስረከሰው ፍቅር አላወራሁም። (አብድልቃድር ኑር)
نمایش همه...
5👍 1
ድንገት በሆነኛው ቀን አንዳንድ ገፆችን ከህይወትህ ላይ ትሰርዛቸዋለህ። ቀልብህ ይወደው የነበረውን ሁሉ ማሳደድ ታቆማለህ። አብሮህ ሳለ ከልብ ላልነበረው ጉዳይ ሁሉ ጀርባህን ትሰጣለህ። ፊትህንም ወደአላህ ብቻ ታዞራለህ። ከልብ የሆነው ብቸኛ ጉዳይህ ወደአንተ እስኪመጣ ልብህን አሳምነህ በትዕግስት ትቆያለህ። አላህም አይቶህ ለቀልብህም ለልብህም በሆነው ብስራት ያበስርሀል። አብሽርልኝ የኔ ጀግና☺️ ታጋሾች ሆይ ትንሽ ጨምሩ ፥ ጥቂት ብቻ ቀረ ብለዋልና ኢብኑል ቀይም። ትንሽ ብቻ ፥ ትንሽ ብቻ ጠብቅ🤍 (አብድልቃድር ኑር)
نمایش همه...
17🤗 8
በዛም አለ በዚህ በሰበሩን ሰዎች እና ጥለውን በሄዱ ልቦች አማካኝነት በሆነ መልኩ ተገንብተናል። ባላሰብነው መንገድ ጥንካሬንና ቆራጥ መሆንን ተምረናል። ባስቀሩልን ሐዘን ተረማምደን ጀግነናል። በአትችሉም ተነስተን ችለን ተገኝተናል። ክብራችን ላይ በተረማመዱት ልክ ስለክብር የበለጠ አውቀናል። የነሱ ፀያፍ ተግባር ለኛ ከፍታ መሰረት ሆኗል። የነሱ እኛን መጉዳት ማንነታችንን እንድናገኝ መንስኤ ሆኖናል። በነሱ ኩነኔ ተግባር የፅድቅ መንገዱ ገርቶልናል። እናም አንዳንዴ እነዚህ ሰዎች ሊመሰገኑ ይገባል ብዬ አስባለሁ። አላህ እነዚህን ሰዎች ያለምክንያት እንድናውቃቸው አላደረገም። ያለአንዳች ሰበብ እነሱን ገፊ እኛን ደግሞ ተገፊ እንድንሆን አልፈቀደም። ባይገፉን የዛሬውን ማንነታችን ባላገኘን ነበር። በሰአቱ የወደቅን መስሎ ቢሰማንም በጊዜ ውስጥ ግን የሆነው ሁሉ ለኸይር መሆኑን እንረዳለን። እናም እነዚህን ሰዎች ስለስራቸው ባይሆንም እኛ ላይ ስላደረጉት አስተዋጽኦ ግን እናመሰግናለን። እንኳንም አወቅናቹ ፣ እንኳንም ገፋችሁን እንላለን። ምንአልባት እንዲያ ባታደርጉ ዛሬ ላለንበት የመብሰል ደረጃ ባልደረስን ነበር። (አብድልቃድር ኑር)
نمایش همه...
16👍 8
ወዳጄ! እኚያ የአላህ ነብይ ጧኢፍ ላይ ያን ሁሉ በደልና ግፍ ባስተናገዱበት ክስተት የአላህን ቁጣ ጨምሮ የጧኢፍ ህዝቦች ላይ ያሻቸው እንዲሆንባቸው በመላኢካው ጅብሪል ቢጠየቁ ፥ አይሆንም ያሉበት ታሪክ አዕምሮህ ላይ የሆነ ጭላንጭል እሳቤን አልፈጠረብህም? በዳዮቻቸው ምንም እንዳይሆኑ ያደረጉበት ተአምር አጀብ አላስባለህም? ይልቅ የረሱሊን ምላሽ ወደሐያትህ ስታመጣው ለይቅርታ ዝግጁ ከመሆን በዘለለ የትኛውም ስልጣንና አቅም ቢኖርህ መሻታህን ብቻ ለማስፈፀም ስትል ልትጠቀመው እንደማይገባ የሚጠቁምህ ነው። ከሰው በላይ ነኝ ብለህ በማሰብ በአንደበት ና ተግባርህ ጨቋኝ እንድትሆን የሚያደርግህ ego በረሱሊና በጧኢፍ ክስተት ካልተገራ ሰዉ መሆንም መመራመርም ይጎድልሀልና ግድየለም ራስህን መርምር። ረሱሊ በዛ ሰአት ላይ ከአላህ እገዛ ጋር ያሻቸውን የማስፈፀም አቅሙ ነበራቸው። ነገር ግን ያ አቅም ከሰው በላይ ነኝ ብለው እንዲያስቡ አላደረጋቸውም ፥ ይልቅ ምንም አለማድረግንና ማለፍን እንዲሁም ከአላህ የሆነ ይቅርታን ነበር የጠየቁላቸው። ይህ የነብያቶች መገለጫ ቢሆንም በነሱ መገለጫ የሆነን ትምህርት ካልወሰድክና ካልተመራመርክ ግን ትልቅ ችግር አለና እስቲ ጉዳዩን እሰብበት። እየቻልክ ልታልፋቸው የሚገቡ ብዙ ጉዳዮች አሉ። መናገር እየቻልክ በዝምታ የምታልፋቸው ብዙ ቦታዎች አሉ። እውነቱን እያወቅክ ባለማወቅ የምታልፈው አጋጣሚ አለ። ለአፀፋ የሚበቃ አቅም አለህ ግና ዟሊሞችህን በይቅርታህ ታልፋቸዋለህ። መተላለፍ ነው የሚያቆየን ወዳጄ! በተለይ በኛ ዘመን ሚያኗኑረን ይኸው ነውና አንዳንዴም የመተላለፍን ጥበብ አክብር። (አብድልቃድር ኑር)
نمایش همه...
🔥 5👍 2 2
በብዙ ተከበዉ ያላዩት "አንድ" መጥቶ ስለሚሞላዉ ባዶነት ለሚናዉዙ ሥሥ ልቦች ...                        .... የማያዉቁት ጠረን ይናፍቃል። ©samuel_dereje
نمایش همه...
9👍 1🔥 1
በሐያትህ እንጥፍጣፊ ፍቅር የቀረህ ቢሆን እንኳ ለእርሱ ሰዋው🤍 ሂድ ወደፍቅር አክናፍ እንዳሻህ ብረር ግና መዳረሻህ አላህ ይሁን። ምን ሳይገድህ ያሻህን አፍቅር ግና ያልጎደለ ሙሉ ፍቅርህን በሱ ላይ አርጋ። በዚህ አዲስ አመት ወደአላህ ሂጅራ የምናደርግበት ና ከሱም ጋር የምንቆይበት ይሁን🤍 #1446 (አብድልቃድር ኑር)
نمایش همه...
19👍 1
Reminder6: Be careful with ur words¡ U never knw how many times it keep repeating in someone's mine. (አብድልቃድር ኑር)
نمایش همه...
9🔥 2👍 1
00:59
Video unavailableShow in Telegram
1446ኛውን የሒጅራ አዲስ አመት መግባት ተከትሎ እነሆ አዲስ ዜና🤍 እንኳን ለ1446ኛው የሒጅራ አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🤍 እስከዛሬ በማስታወቂያ ብቻ የቆየንበትን አዲስ ፕሮግራም የምንጀምርበትን ቀን ወስነን ከትመናል። ይኸውም የዛሬን ቅዳሜ ጨምሮ በአላህ ፍቃድ ከሶስት ቅዳሜዎች በኋላ የምዕራፍ ሁለት ከአንባቢያን ጋር ልዩ ቆይታችንን  °ለሩህ ቅመም ቡክ ካፌ° በሚል አርዕስት ከተለያዩ አንባቢያን ጋር የምንገናኝ ይሆናል። መልካም ቆይታ! #ለሩህ_ቅመም_ቡክ_ካፌ #episode_2 #ٱقۡرَأۡ_Generation #በአብድልቃድር_ኑር #ሐምሌ_20 #z_spicesoul
نمایش همه...
50.79 MB
🥰 5 1
00:59
Video unavailableShow in Telegram
1446ኛውን የሒጅራ አዲስ አመት መግባት ተከትሎ እነሆ አዲስ ዜና🤍 እንኳን ለ1446ኛው የሒጅራ አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🤍 እስከዛሬ በማስታወቂያ ብቻ የቆየንበትን አዲስ ፕሮግራም የምንጀምርበትን ቀን ወስነን ከትመናል። ይኸውም የዛሬን ቅዳሜ ጨምሮ በአላህ ፍቃድ ከሶስት ቅዳሜዎች በኋላ የምዕራፍ ሁለት ከአንባቢያን ጋር ልዩ ቆይታችንን  °ለሩህ ቅመም ቡክ ካፌ° በሚል አርዕስት ከተለያዩ አንባቢያን ጋር የምንገናኝ ይሆናል። መልካም ቆይታ! #ለሩህ_ቅመም_ቡክ_ካፌ #episode_2 #ٱقۡرَأۡ_Generation #በአብድልቃድር_ኑር #ሐምሌ_20 #z_spicesoul
نمایش همه...
50.79 MB
1446ኛውን የሒጅራ አዲስ አመት መግባት ምክንያት በማድረግ እነሆ አዲስ ዜና! በማስታወቂያ ብቻ የቆየንበትን አዲስ ፕሮግራም የምንጀምርበትን ቀን ወስነን ከትመናል። የዛሬን ቅዳሜ ጨምሮ በአላህ ፍቃድ ከሶስት ቅዳሜዎች በኋላ የምዕራፍ ሁለት ከአንባቢያን ጋር ቆይታችንን  °ለሩህ ቅመም ቡክ ካፌ° በሚል ርዕስ ላይ ከተለያዩ አንባቢያን ጋር የምንገናኝ ይሆናል። #ሐምሌ_20 #ለሩህ_ቅመም_ቡክ_ካፌ #episode_2 #ٱقۡرَأۡ_Generation #አብድልቃድር_ኑር
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.