fa
Feedback
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

رفتن به کانال در Telegram

የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ። ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን። We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com

نمایش بیشتر
1 720
مشترکین
-224 ساعت
-47 روز
-930 روز
آرشیو پست ها
Book your spot!!!
Book your spot!!!

ወደ ማይደርሱበት ህልም ።።።።።።።።።።።።።።። ነገ ተስፋን አዝሎ ልባችን ላይ በብሩህ ፊደላት ደምቆ ታተመ ህልማችን በሰዎች መዳፍ ተይዞ ወደ ማንደርስበት አዘገመ በቀቢፅ እይታ ፅልመትን ለመርታት በችኮላ አረማመድ ተመልከቱት ሰውን ወደ ማይደርስበት ህልም ተያይዟል መንገድ @Dagifa

እውነት ስለ እውነት እውነት እልሀለሁ እውነት በመናገር የምታጣው ነገር በምድር ላይ ያለ ሀሰተኛን ፍጡር አትበይኝ አትበይኝ እስኪ አንችው ንገሪኝ የእውነት በዝች ምድር ስለ እውነት ኑሮ ስለ እውነት የሞተ ንገሪኝ ማን ነበር?? ከ ፈጣሪ በቀር

ከጠበቅነው በላይ እስከ አሁን 26 ተወዳዳሪዎች በማግኘታችን እየተወዳደራችሁ ያላችሁትን እና ውድድሩን እየተከታተላችሁ ድምጽ እየሰጣችሁ ያላችሁትን ሁሉ እናመሰግናለን! የቤተሰባችን ቁጥርም 1000ን በመሻገሩ ደስታችን ግዙፍ ነው!!! ይህንንም በማስመልከት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ለሚወጡ ግጥሞችም የመጽሐፍት ሽልማት እንደምናበረክት እወቁልን!

አይ ሰው ከስር ከስራቸው እየተከተልን ሲጠሩን ስንመጣ ሲላቸው ሲያባሩን እኔ ነኝ ያለውን እነሱን ሊነካ ነክሰን እየያዝን ጥበቃው ቢሳካ የኖሩ ኖሩና ተምሳሌትን ቢያጡ ግብሩን እየሰሩ ስሙን ለኛ ሰጡ እጅጉንም ሳኩኝ ሆዴን አሻሽቼ ውሻ ብሎ ስድብ ከሰዎች ሰምቼ @sarinamard

"ህይወት....🤔 ጢባ ጢቤ..." ከፍታ ላይ 'ምታወጣ አንዲት ቅጠል ጥላ ትታ! አልያም ደ'ሞ የምትጥል ትንሽ ድልን አስገኝታ!! ወይም ደሞ..የለገመች... ከፍ ላትል ላትረታ ለሞከሯት.. ጠዋት ማታ!!! @ZionismT

መልካም ዜና ለሱ ሀዘኔን ላልካሰኝ ሳላለቅስ የቻልኩት ለ"ምነው?" ሆድባሰኝ ስወጣ ጠንካራ ተደብቆ አልቃሻ (ተብረክርኮም መቆም፤ቢዝልም ትከሻ) ሲፈሩት ይደፍራል ሃዘን እና ውሻ! @Guadyeee

ወዲህም ካየሽ ፈሶ ደም ወዲያም ካየሽ ፈሶ ደም ሌላው ሌላው ቢቀር "እኔን"ንን ለማለት ፤ አፍሽ አይሎገም ።።።።።።።።።።።።።።።፡።።። ✍ሳሙኤል አለሙ @Samuelalemuu

መንታ ፍልስፍና.... የሚንከራተተው ያ'ዳም ዘር በሙሉ: ሲዳፋ ሲቃና ሲዋትት መዋሉ: የመፈጠሩን ቅድ ሊደፍን ነው አሉ። @NikoTheGreat

.......የሞኝ ኑዛዜ...... ፈውስማ አለፈኝ፣ ምክኒያት ደንታን አልፎ ተቅበዝባዥ አረገኝ፣ ከፍርሃት እብደት ተርፎ ሃሳቤ ራስ ስቶ፣ ንግግሬ በዝቶ ይገላምጠኛል፣ እውነቴ ተብቶ . ውብ ብያለሁና፣ ደማቋ ደመራ ጭልም የሆንሽውን፣ የግሃነም ጮራ። -ኖኔም

ትናንት ትዝ እንዳይለኝ- ከራሴ ጋ ማልኩኝ ትናንትን ስረሳ- ለዛሬም አልኖርኩኝ ካላየሁዋት የነገ ፀሐይ ተወዳጀሁ እምነትን ይዤ ለተስፋ ደገስሁ ከዛማ... በተከራየሁት የጊዜ ሰሌዳ እኔ ሆንኩኝና የራሴ አለቃ፣ ቀጠሮን ቀጠርኩኝ ነገ ዛሬ ሲሆን ደሞ ላባርረው አዲስ ቅዠት ልቃዥ፣ የፈረደበትን መልሼ ልቀጥረው @Mtesfaye7

ለመደስኮሩማ ስብከት ለመስበኩ በወርች ሱባኤ ፍቅርን ለማምለኩ መምህር መች ሽቶኝ ለወሬ ሽንገላው እኔው መቼ አነስኩ የቸገረኝ ቢኖር የጠፋኝ ያጠረኝ መፍትሄ ብልሀቱ የአክስቴን ገዳይ ቆስሎ ከተኛበት ደግፎ ማንሳቱ በቆሎ ተዘርቶ ኩርንችት ማፍራቱ @Mahlet_Be

የእሽቅድድም ህይወት ግራን አስቀድሞ ቀኝን ለማስቀረት አንድ አካልን ጥሎ በአንዱ መንኳተት ሙሉነቱን ጥሎ በግማሽ እየለፋ በግማሽ አካሉ ሰውን እየገፋ ቀኙን ማዶ ጥሎ ግራውን እየሣበ በአንድ አካሉ ማራቶን ያሰበ @blessedloner

ከትርምስ መሀል ከኖረ ፀጥታ በክፉ ቀን መሀል ከበዛ ዝምታ ያንን ነዉ መተርጎም አንድም ለአንድምታ። ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ @Tizita21

ቤት የለኝም ያም ሰፈር የነሱ ይሄም የእነንትና የትጋ ቤቴን ልስራ ከማን ልጠጋና ዘር አልቆጥር ነገር የፈጣሪ ልጅ ነኝ እንግዲ እኔ አልሰራም ቤቴን ራሱ ይስጠኝ🙏 ያሬድ.የ @Yjaredy

......የዘመኔ ምስል....... ጉልበት ሳይዝል፤ ልብ ደከመ ስጋ አብቦ ፤ ነፍስ ቆዘመ በምጥ መሀል፤ ባለች ፈገግታ ስንቱ ታለለ ፤ ህይወት ተረት'ታ. ..!! (ነብዩ.ብ)

መሪ ቃል ባይሆን እሮጣለሁ፥ በዘመን ሜዳ ላይ፥ በሰው የመሆን መም፤ ባይሆን አሸንፌ፥ አውለበልባለሁ፥ የልቤን ባንዲራ፥ የ'ኔነቴን ቀለም። ካልሆነ ግን... ለመሮጥ የሚሆን፥ ቢያንሰኝ እንኳ አቅም፤ ሯጩን ላለመጥለፍ፥ መሙ ላይ አልወድቅም።

ኑ !ወደ ነፃነት እንንጎድ እፍ እያልን በጭስ እንባ ሳናባክን ኑ !ለነገ እንንደድ ኑ። (ኤደን ሙሉነህ) @Oritethe

፠ሰመመን፠ ሲቃ በሚንጠው በጠቆረ ሰማይ በዋይታ እርይታ በስቃይ ላይ ስቃይ በትዝታ ጭሰት ጭስ በሌለው ንዳድ በብቸኝነት ውስጥ በባይተዋር ጉድጓድ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ፋቅርን ተሸክሜ በቀቢፀ ተስፋ ላይቀለኝ ደክሜ አለሁ!! አለሁ እንዳለሁኝ ሞቼም አገግሜ፡፡ ✍️መሊኩ [ MAJNUN ] @Bufal

ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem - آمار و تحلیل کانال تلگرام @gitemsitem