cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

💖የኔ ፍቅር 😘

🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ❓ ❤ ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤ ❤ HBD ለማለት፤ 🎂 ❤ ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶‍♀ ❤ ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦‍♂ 🤩 የፈለጉትን የፍቅር ቃል ለኛ @yenefekirbot ላይ ይላኩልን 📬 በፍጥነት እናደርሳለን። ⚠️ የሚልኩለት ሰው member ካልሆነ መጀመሪያ ሊንኩን @yenefekir ይላኩለት።

نمایش بیشتر
أثيوبيا2 010زبان مشخص نشده استدین و مذهبی8 642
پست‌های تبلیغاتی
10 568
مشترکین
+224 ساعت
-257 روز
-14030 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ኤጭ! ...ይኼ እሁድ መጣ ደ'ሞ! °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° "አንተ!" "የፈጣሪ ያለኽ! ...ምን ያስጮኽሻል? ...አስደነገጥሽኝ እኮ!" "ይኼ ምንድን ነው?" "ምኑ እናቴ?" "ይኼ!" "እስኪ መነጽሬን አቀብዪኝ፤ ምንድን ነው?" "አታሹፍ!" "ኣ? ...ምን? ...ምኑ? ...የቱ? ...የማን ነው?" "ከምትንተባተብ ራስኽ ንገረኝ እንጂ!" "በ ለ ው! ...እነዚኽ ከይሲ ልጆች ከየት አግኝተው አምጥተውት ነው!? ...ትናንት ከቤት ወጥተው ነበር እንዴ?" "ዝጋ! ...ልጆቼን ያለ ኀጢአታቸው አትስደባቸው! ...የተገኘው ትናንት ለብሰኸው የዋልኸው ጃኬት ውስጥ ነው!" "ተረጋጊ እናቴ! ...ተረጋጊ! ...መቸም በዚኽ ትዳር የማይቀናብኝ የለም። አንዷ ምቀኛ! ...ኦ! ይቅርታ! አንዱ ምቀኛ መስክሬን ዐይቶ ኪሴ ውስጥ ከትቶብኝ ይኾናል እንጂ፣ እኔም ይኸው ካንቺ እኩል ማየቴ ነው!" "ዝ..ም በል እኮ ነው የምልኽ!" "እንዴ! ...እንዴ! ጥፊው ታዲያ ምንድን ነው? ...አበድሽ እንዴ?" "ማበድ ይነሰኝ!? በዚኽ ልክስክስ አመልኽ ጨርቄን መጣል ይነሰኝ!?" "ግዴለም እናቴ! ተረጋጊ! ...ትዳር መቼም እንደዚኽ ነው። አንዳችን እሳት ስንኾን አንዳችን ውኃ መኾን አለብን! ...ተረጋጊ! ...የሚጠጣ ውኃ ላምጣልሽ?" "ቆይ እሺ ምን ልኹን!? ...ትዳሬን ባልኹ! ልጆቼን ባልኹ! ኑሬዬን ባልኹ! እድሜ ልክ ያንተ መጫወቻ ኾኜ ልቅር!?" "ቀስ! ኧረ ቀስ! ...ልቅሶውን ምን አመጣው ታዲያ!? ...ልጆቹም ይተኙበት!" "የራሳቸው ጉዳይ!" "ቀስስስስ... ! ይኸውልሽ እናቴ! ...ነገሩን በማስተዋል ብታዪው እኮ ይኼን ያኽል የሚያበሳጭ አይደለም!" "ተው እንጂ! ...እ!" "ጤናዬን ለመጠበቅ! ...ያንቺን የሚስቴን፣ የልጆቼን እናት ጤና ለመጠበቅ እንደምጠቀም፣ ኦ! ይቅርታ! ማለቴ እንደገዛኹት ብታስቢው ጥሩ ነው!" "እስከ ዛሬስ በሽታ ላይ እንዳልጣልኸኝ በምን አውቃለኹ!?" "በስማም በዪ አንቺ! ...የሰይጣን ጆሮ ይደፈን! ...ሆ!" "በቃኝ! በቃኝ! በቃኝ!" "ምኑ?" "ይኼ ኑሮ! ...ካንተ ጋር የምኖረው የተልከሰከሰ ሕይወት! ...ከዚኽ በላይ በደል የምሸከምበት ጫንቃ የለኝም!" "ኮንዶም ባሌ ኪስ ተገኘ ብሎ ይኽን ያኽል ምሬት!? ...ኧረ ተዪ! ፈጣሪን በጦር አትውጊ!?" "ዝ...ም በል አንተ ልክስክስ ሴሰኛ! ...ዝም በል!" "እሺ! ...እሺ! ...በዪኝ ግዴለም! ...አጋጭኝ! ...እችለዋለኹ! ...እጅሽ ደግሞ ማቃጠሉ!" "ቆይ ከእኔ ምን አጥተኽ ነው? ...ምን አጎደልኹብኽ!?" "ያገኘሽው ኮንዶም እኮ ዐዲስ ነው። አገልግሎት ላይ አልዋለም!' "ኡኡይ! ዝ...ም በል እኮ ነው የምልኽ! ...ሰይጣኔን አታምጣው!" "የምን አታምጣው ነው? ...መጥቷል እኮ! ...መጥተዋል። አብራችኹ ናችኹ እኮ! ...ጥፊውን ብቻ አስቀሪልኝ! ...ሌላውን እችለዋለኹ።" "ውሻ ነኽ እሺ!" "ነኝ! ...ለዛሬ ነኝ! ...ይኹን! ብቻ አንቺ ተረጋጊ!" እ ፎ ይ! ኼደች። "ኧረ ቀስ በሩን! ...ያን የጸሎት መጽሐፍ የት ነው ያደረግሽው? ...በ ለ ው! ደኅና የኼደችልኝን እጠራታለኹ እንዴ! ...እውነት የት ነው ያደረግኹት!? ...ወይኔ! በእኩለ ጾም እንዲኽ ልነጀስ!? ...አይ አንተ ሰይጣን ለዛሬ ተሳኽቶልኻል። ...ቆይ ግዴለም! ...አኹን ጸሎቴ ላይ ድፍት ስል የቤቱ ሰላም ይመለሳል። ...ኤጭ! ይኼ መጽሐፍ የት ኼደ ደ'ሞ!? © በኃይሉ ገብረእግዚአብሔር ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️ 😘😍@Yenefekir😘😍 💝@Yenefekir💝
نمایش همه...
👍 4
ለቅሶ ቤት ሄድ ሄድኩና... እንባዬ ደርቆብኝ  : ለማልቀስ ስቸገር በድንገት ትዝ አለኝ  : ያደረግሺኝ ነገር ትውስ ያለኝ ጊዜ : የሰራሺኝ ስራ አልቅሼ አላለቀስኩ : ሳለዝን በሟቹ ድሮም ያንቺ ፍቅር : ለሀዘን ነው ምቹ       ላይክ  ማንን ገደለ....😂😂😂😂😂 ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️ 😘😍@Yenefekir😘😍 💝@Yenefekir💝
نمایش همه...
17👍 12😁 9
‍ ​​.             💗ፍቅሬን በምን ቋንቋ💗         ---------------------     ለአይኔ እንኳን ለአፍታ እንዳላጣሽ፤😏       እፈልግ ነበረ ፍቅሬ እንዲገባሽ።😞    ግን እንዴት ልናገር እንዴት ስ ላውራ፤🗣   ወደ ሌላ እንዳትሄድ እያለ ልቤ ሲፈራ።☹️      ስሜቱ ከባድ ህመሙ አይቻልም፤🤧 ፍቅርሽ ከብዶኛል ያዢልኝ አልቻልኩም።🙏    እንዴትስ ልናገር እንዴት ላውጣው፤😤      እያሰቃየኝ ነው ፍቅርሽ በእጣው።😐    ፍቅር ሠው ይገላል ሲሉ እሰማለሁ፤😇   እኔ ግን ስላንቺ ስንቴ ሞቼ ተነስቻለሁ።😘            ቃል ሲሰማ ከአንደበትሽ፤🥺       በውበት ፍክትክት ይላል ፊትሽ።😊   በምንስ ልግለፀው ፍቅርሽን በቃላት፤😅      እኔ ግን እፈራለሁ አይንሽን ለማየት።🫣         ♥️ሁሌም እወድሻለሁ!♥️ ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️ 😘😍@Yenefekir😘😍 💝@Yenefekir💝
نمایش همه...
👍 11🔥 2🥰 2
የሴቶች ቴክስት ትርጉም ሴቶች ትክክል ከሆነ 👍 ካልሆና 👎 በማረግ አረጋግጡልኝ🙏🙏 1.ችግር የለውም 👉በአቀረብከው ሀሳብ ላይ 100% አልተስማማችም ግን  ሀሳብም መስጠት አትፈልግም። 2.ላስብበት አሳውቅሀለው 👉በግልጽ አልፈልግም እያለችህ ነው ወዳንተም አትመለስም። 3.ቴከስትህን ውይ አላየሁትም ካለች 👉ስትሰክስህ ነው ይሉቁንም የላከውን ቴክስት አይተዋለች መመለስ ስላልፈለገች ነው። 4.እደፈለክ 👉ባወራከው ነገር ደስተኛ አደለችም እና ወሬውንም እድታቆም ትፈልጋለች። 5.ስትጣሉ ላናግርህ አልፈልግም ካለች 👉ማውራት ትፈልጋለች ግን ላጠፋሀው ጥፋት መጀመሪያ ይቅርታ እድትጠይቃት ትፈልጋለች። የትኛው ተመቻቹ ትክክል ያልሆነ የሚመስላቹ የቱ ነው comment ,አድርጉ ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️ 😘😍@Yenefekir😘😍 💝@Yenefekir💝
نمایش همه...
👍 36
✝ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን ! መልካም በዓል! ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️ 😘😍@Yenefekir😘😍 💝@Yenefekir💝
نمایش همه...
🙏 9
Ewnet anadjekalew gn eko felge aydelem betam ykrta🙏 ykrta adrglgn endebefitu enhun
نمایش همه...
😢 5😁 4👍 1
❤️❤️ እስኪ ስለ ጀዝቦች ትንሽ ልበላቹ😉😉     🤔እኔ ምላቹ ወንዶችዬ ቆንጆ ሴት ስታዩ ልፈርጡ ምደርሡት ነገር ነው ሚገርመኝ ካልሞትኩልሽ የምትሉት ነገርስ😁ደሞ በተቃራኒው የሆነችን ሴት ስታዩ አይንሽን ላፈር ምትሉት ነገርስ🤣እናውራ ከተባለማ ጉዳቹ አያልቅም ሴትን ልጅ ከወገብዋ በታች ባለው ዳሌዋ🙆አቅዋሙዋ በአለባበስዋ😂 በውበትዋ የምትለኩ ወንዶች ግን ጌታን ጀዠባ ናቹ ቂል🙈ሴት ልጅ እኮ ስሜት ናት ውሀ ናት የጠማው ይጠጣታል☺️ግን የያዛችዋት ቆንጆም ሆነች አስቀያሚ ጠበቅ አርጋት ወዳጄ አንተ ስፈዝ ብልጡ እንዳይቀማ ሴቶችም ብትሆኑ ወንድን ልጅ በአቅዋሙ በገንዘብ አትለኪው ጅል አትሁኚ😁ወንድ ልጅ ከወደደሽ ከልቡ ነው❤️ ጠበቅ አርጊው በእጅ የያዙት ወርቅ እንደመዳብ ይቆጠራል አይደል ሚባለው🤗 ደሞ እኮ ፍቅር በውበት በአቁዋም😌በገንዘብ በአለባበስ አትለኩ🙅የምትለኩ ግን ከምር ሰው ሣትሆኑ ትንሽ ናቹ😏 እና እላችዋለው ወንዶችዬ😝ግን ለምንድን ነው 123456 ሴት ካልያዛቹ የሚያማቹ🤔🤔ይድፋቹ ሙቱ እናንተ ጀዝቦች🙄🙄 እና ደሞ  ሴቶችም ብትሆኑ ለቆርቆሮ አትሙቱ🚗አሁንም ልድገምላቹ ወንዶች የያዛችዋትን ጠበቅ በውበትዋ እና በአካልዋ ሳይሆን በጭንቅላትዋ ለክዋት ያኔ እናንተ ከማንም በላይ አራዳ ናችው👍👍ግን ደሞ አሉ ልክ  ለሴት ልጅ ክብር ሚያስቡ ሴትን ልጅ በገላዋ በ ዳሌዋ😞የማይገምቱ ምርጥ አራዳ ወንዶች አሉ👍እነሡ ብቻ ይኑሩልን😍😍😍 ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️ 😘😍@Yenefekir😘😍 💝@Yenefekir💝
نمایش همه...
8👍 4😁 1
✒️የተከዳው የወፍጮ ቤት ሰራተኛ የጻፈው ደብዳቤ✉️ አንቺ ከረጢት ቢገባሽ አንድ መቶ ኪሎ ብልሹ ባህሪሽን ችዬ ነበር ያኖርኩሽ የሰጠሽኝ ፍቅር አምስት ኪሎ አይሞላም ነበር ፡ልቤን ዱቄት አድርገሽው ስትሄጂ ትንሽ አታፍሪም?? ፡ የሰራሁልሽን ሁሉ ውለታ ፍጭት ታደርጊዋለሽ?? ጥፋተኛው እኔ ነኝ ልመዝንሽ ይገባ ነበር፡ ፍቅርሽ ሽርክት መሆኑን ማወቅ ነበረብኝ በበርበሬ ወፍጮ ከተሽ አነደድሽኝ ፡ ሰፌዱ ልቤ አመልሽን ማበጠር ነበረበት አንቺ ወንፊት አድርገሽኝ ብትሄጂም የምታበረታኝ ሴት አላጣም፡ እመኚኝ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ጓያ እሆናለው እጠነክራለሁ ፡ እንደ ጤፍ የበዛ ብዙ ኩንታል ፍቅር እንደማገኝ አትዘንጊ ፡ ደሞ ገብስ ገብሱን ነዉ የፃፍኩልሽ ፡ አንቺ ሽንብራ 😂😂😂😂 ከተመቻቹ ÷ 𝐋𝐢𝐤𝐞 𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭 ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️ 😘😍@Yenefekir😘😍 💝@Yenefekir💝
نمایش همه...
😁 18👍 11
የማባልጋት ባለትዳር ነበረች ። ዋና ተግባራችን ወሲብ ነው ። የምንቀጣጠረው ለወሲብ ብቻ ነው ። የምናወራው ስለ ወሲብ ነው ። አንዳችን አንዳችንን የምንፈልገው ወሲብ ሲያምረን ነው ። አጠገቤ ሆና ባሏ ደውሎ ያውቃል: "ሰውዬሽ ደወለ" ብዬ ስልኳን አቀብያት አቃለሁ ። ምንም እንዳልተፈጠረ ስታወራው እርቃኗን አትመስልም ነበር። ይገርመኛል ድድብናችን ። ነውራችን ስለተደጋገመ ተግባራችን ብልግና መሆኑ ተሰወረብን ። ቢሮዋ እሄዳለሁ፣ ቢሮዬ ትመጣለች ። ጓደኛዬ ቤት፣ እኔ ቤት፣ የሆነ ኮስመን ያለ ሰዋራ ቦታ ፣የሆነ ድብቅ ፅድት ያለ ስፍራ ፣ መኪና ውስጥ ... ብዙ ብዙ ቦታ ትመጣለች እንዋሰባለን ። የታሪካችን መነሻ እና መድረሻው ወሲብ ነው ። አንድ ቀን በደነገጠ: ተስፋ በቆረጠ ድምፅ "ባሌ አወቀብን" አለችኝ .....ደነገጥኩ ። ጠፋሁኝ ...ጠፋች ከአስራ ሰባት ቀን በኋላ ጓደኞቼ "ገኒ ሃዘን ላይ ነች፣ ሙሉ ከላይ እሰከታች ጥቁር ለብሳለች፣ ከስታለች" አሉኝ "ምን ሆነች?" አልኩ "ባሏ ሞቶባት ነው፤ ራሱን አጥፍቶ ነው የሞተው" አሉ። ስደነግጥ፣ ፊቴ ሲቀያየር ፣ እምባዬ ሲያመልጠኝ አዝኜለት ነው የመሰላቸው ። እኔ እንደገደልኩት አልጠረጠሩም ። የጥፋተኝነት ስሜት ሊገለኝ ሲል ማምለጫ መፅሃፍ ቅዱስ ገለጥኩ። "ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል " የሚለው ከሁሉም ጎልቶ ተነበበኝ ። .. ሰው ይዞ መውደቅ ፤ ማስተካከል የማይቻል አወዳደቅ ፣ ሲያስታውሱት የሚያስነክስ አይነት አወዳደቅ፣ እነሳለሁ የማይሉት አወዳደቅ ፣ ወድቄ ነበር የማይሉት አወዳደቅ። በግዜ ምክንያት የማይደበዘዝ አወዳደቅ ... እንደዚህ አይነት መውደቅ ሲ..ያ...ስ..ጠ..ላ !! ! © አድኃኖም
نمایش همه...
😢 19👍 8 3
Walk እየበላን በመኃል "ነገን አዉቃለሁ ብዬ ፈጣሪን አልጋፋም። ዛሬን ግን በህይወቴ ስላለሽ ሁሌም ደስ ይለኛል" ብያት እምባ በእምባ ሆነች ትስቃለችኮ ግን እያለቀሰች ነዉ 🥹 የኔ አልቃሻ እንዴ ምን ሆነሽ ነዉ ብላት ደስ ብሎኝ ብላ ሳቀች ድጋሚ 😊 በቃ ይህቺዉ ነች የሴት ልጅ ልብ? 😳 ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️ 😘😍@Yenefekir😘😍 💝@Yenefekir💝
نمایش همه...
17👍 3🥰 2