cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Gospel Singer Zelalem Tesfaye

" ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 1:1-2) የእግዚአብሔር ወንጌል ስለ ክርስቶስ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ወንጌል ካለ የሰው ወንጌልም አለ፡፡ የሰው ወንጌል ወንጀል ነው፡፡ የእግ/ር ወንጌል ደግሞ ህይወት ነው፡፡ በዚህ ገጽም ህይወት የሆነው ወንጌል ብቻ ይሰበካል፡፡

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 706
مشترکین
-124 ساعت
-17 روز
-1830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

አንድ ዓመት ሞላው ክብር ለጌታ ይሁን! #ደማቅ_ሕይወት የመጀመርያ መፅሐፍ ከተመረቀ ዓመት ሞላለው ሀሌሉያ!! ጌታ ይመስገን አሁን ደግሞ #የደማቅ_ሕይወት አገልግሎት ከተጀመረ #4ተኛ_ዓመት_ክብረበዓሉን #በሆሳዕና እናከብራለን። በዚህም ክብረበዓል ጌታን የምናመሰግንበት እንዲሁም የቀደሙ የወንጌል አርበኞችን የምናከብርበት እውቅና የምንሰጥበት ታላቅ ጊዜ ይኖረናል። በፀሎታቹ በገንዘባቹ ከዚህ አገልግሎት ጎን እንድትቆሙ በጌታ ፍቅር እጠይቃለው። 251916624398 BL TV
نمایش همه...
ዛሬ ልደቴ ነው! መልካም ልደት ለኔ🎂🎂🎂
نمایش همه...
#በሆሳዕና_ከተማ_ይከበራል ሰላም ቅዱሳን የጌታ ፀጋ እና ሰላም ይብዛላቹ የዘንድሮ የደማቅ ሕይወት አገልግሎት 4ተኛው ዓመት ክብረበዓል #በሆሳዕና ከተማ ይከበራል በዚህ ቀን እንደሚታወቀው ረዥም አመታት ወንጌልን ላገለገሉ ለወንጌል አርበኞች የክብር አዋርድ እንዲሁም የምስጋናና የአክብሮት ዝግጅቶች ይኖራል። እንዲሁም ወንጌል ይሰበካል ጌታ በዝማሬ ይመለካል ከሐገር እና ከሐገር የውጭ ታላላቅ የወንጌል አገልጋዮች በመገኘትም ይባርኩናል ያገለግሉናል ። ቦታውን እና ቀኑን በቅርብ ቀን አሰናሳውቃለን #በሆሳዕና እና አካባቢዋ ያላቹ የጌታ ልጆች በዚህ ቀን በአንድነት ጌታን እንድናመልክ ለአርበኞች አክብሮታችንን እንድንገልፅ ተጋብዛቹኋል። አብሮ ለማገልገል ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከስር ባስቀመጥኩት ስልክ በመደወል አገልግሉ። 251916624398
نمایش همه...
نمایش همه...
#የበሻሻ_ሙሉ_ወንጌል ቤተክርስትያን አደጋ ላይናት እንድረስላት😭😭 በሻሻ ሄጄ የገጠመኝ 😭😭 አስደንጋጭ ክስተት #zelalemtesfaye

#protestant_mezmur #ደማቅ_ሕይወት_አገልግሎት #protestant_song

#ለበሻሻው_አገልግሎት_ጅማ_በሰላም_ገብተናል በጌታ ፀጋ እና ምህረት ከአዲስ አበባ ተነስተን እጅግ ከምወደው ከማከብረው ጌታ በሁለንተናዊ ፀጋ ከባረከው ከጆሲ ጋር ፕሮግራሙን ለመስራት ለበሻሻው ታላቁ ተልዕኮ ጅማ #አባጅፋር በሰላም ገብተናል ክብር ለኢየሱስ ይሁን። ጉዙዋችን እንደጌታ ፈቃድ በሻሻ እናደርጋለን በዛም ጌታ ሊሰራ የወደደው ታላቅ ተልዕኮ አለብን ሙሉ ሀሳቡን እና አላማውን እዛ ስደርስ አሳውቃቹኋለው። በዚህም ተልዕኮ ላይ የጅማ #አብያተክርስትያናት መሪዎች ታላላቅ የወንጌል ልብ ያላቸው የተወደዱ መጋቢዎች አብረውኝ ይጓዛሉ። የተወደዳቹ ቅዱሳን በሩቅም በቅርም ያላቹ በፀሎታቹ ከጎናችን ከወትሮ ይልቅ ትሆኑ ዘንድ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን ወንጌላችን ይቀጥላል ። #ደማቅ_ሕይወት_አገልግሎት BL TV 251916624398
نمایش همه...
#ይቅርታ_አድርጉልኝ_አጥፍቻለው🥺🥺 ዛሬ ዘማሪ አብነትን #ቶክቻውን አጊንቼው በወቅታዊ ጉዳይ በተፈጠረው ነገር ላይ አውርተናል #ኢንተርቪውም አድርጌዋለው ። ወንድማችንም አብነት ለተፈጠረው ነገር #ይቅርታ እንዲሁም ምላሽ ሰቱኋል ሙሉ ፕሮግራሙን #በzelalem_tesfaye_ዩትዩብ ቻናል ይጠብቁ 👉 https://youtube.com/@zelalemtesfaye-official8856?si=5M4a5lqXMaFuiUof
نمایش همه...
#በአገልግሎት_እንዴት_እንፅና? በአገልግሎት ጎዳና የተለያዩ እምነትን ፅናትን ትግስትን የሚጠይቁ ፈተናዎች እና ስኬቶች ይመጣሉ ደግሞም ያልፋሉ ነገር ግን በሕይወታችን ለሚመጡ መከራዎች በመፅናት ከፊት ጌታ ያየልንን ታላቅ ክብር ለማግኘት እንፅና! #በአካላዊ_ፅናት_እንፅና ጳውሎስ በአገልግሎት ጎዳና አካላዊ ፈተና ወይም ተግዳሮት ደርሶበታል ነገር ግን #ጳውሎስ በዚህ ሁሉ ለተጠራው እውነት ሲል #በፅናት በትዕግስት ከጌታ ጋር ሰራተኛ በመሆን ሁሉን በመታገስ በጌታው በመታመን ከፊት ያለውን ደስታ ተካፍሉኋል። #በውስጣዊ_ፅናት_እንፅና ሐዋርያው ጳውሎስ በሕይወቱ በሚገጥሙት ፈተናዎች ውስጣዊ ፅናት ነበረው በጌታ ፊት #ይፀልይ እና #ይታመን ነበር ውስጣችን በሚያደክሙ #ለአገልግሎት ያለን ፍቅር እምነት የሚያቀዘቅዙ ብዙ ተግዳሮቶች አሉ በዚህ ሁሉ ግን በፀሎት በፀፆም ቃሉን በማንበብ ከፀናን ወደታየልን በክብር እንደርሳለን። የተወደዳቹ #የአገልግሎት ጥሪ ያላቹ ወንድም እህቶቼ በአገልግሎት ጎዳና ያላሰባቹት ፈተና እና ተግዳሮት ሲፈራረቅባቹ #እንደጳውሎስ እንደ #አባቶቻችን በመፅናት #በመፀለይ በመታገስ ከፊትታችን ያለውን #ክርስቶስን በመልከት #የዲያቢሎስን ሽንገላ እና ሀሳቡን ባለመሳት እንድንበረታ ለታላቁ #ተልዕኮ ይበልጥ እንድንዘረጋ እንድንበረታ ጌታ ፀጋውን ያብዛልን! መልካም ቀን!
نمایش همه...
ምነው በዚህ ደረጃ ጭካኔ😭😭 ያለንበት ዘመን እጅግ ክፋት እና አመፃ ጎልቶ የሚታይበት ከቀድሞ ይልቅ አሁን የመጨረሻው ዘመን ይመስለኛል!! ይሄን ከላይ የምትመለከቱ ወንድማችን ብሩክ ይባላል የሚኖረው #በደቡብ አፍሪካ ነው ይሄ ወንድማችን ታታሪ ሰራተኛ እና ጌታን የሚወድ ወንድማችን ነው ። ነገር ግን በገዛ ወገኖቹ #አሲድ ደፍተውበት ከፍተኛ አደጋ ደርሶበታል🥺😭😭 ለማመን ለመስማት የሚከብዱ አስፈሪ ክፋቶች በአለም እየተሰሙ ነው ጌታ ኢየሱስ በደሙ ይሸፍነን ይጠብቀን !! የተወደዳቹ ወዳጆቼ ለዚህ #ለወንድማችን_ብሩክ እንፀልይለት የጌታ የምህረት እጁ በእርሱ ላይ እንድትሆን ጌታ እንዲፈውሰው ሁላችንም በፀሎት ከጎኑ እንቁም። በመጨረሻ በዚህ ወንድማችን ላይ ይሄን የከፋ ድርጊት ከፈፀሙ መካከል አንደኛው መያዙን ሰምተናል ሌላኛው ሀገር ቤት እንደተሰወረ እና የቪድዮ መልክት በመልቀቅ የግሉን ሀሳብ በራሱ ቋንቋ መናገሩ ብዙዎቻችን ማየታችን በማህበራዊ ሚዲያ ይታወቃል። የተወዳቹ ቅዱሳን ወንድሞቼ ጌታ ከድንገተኛ አደጋ ሞት ይጠብቃቹ እያልኩ ለዚህ ወንድማችን በሚያስፈልገው ለህክምና የሚሆነው የገንዘብ ድጋፍ እና ከሁሉ በላይ በሆነው በፀሎታችን እንድናስበው ስል በብዙ ትህትና እጠንቃለው።
نمایش همه...