الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
رفتن به کانال در Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
2 203
مشترکین
+1824 ساعت
+617 روز
+46430 روز
آرشیو پست ها
Repost from قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚
+1
🧷
ቁስልን ማከም እንጂ "ማከክ አያድንም "
ኢላሂ ሰላም ካንተ ነዉ እና ሰላም አድርገን" ያረብ💧
https://t.me/https_Aselefyaإِنَّمَا الْأَعْمَالُ بِالنِّيَّاتِ، وَإِنَّمَا لِكُلِّ امْرِئٍ مَا نَوَى، فَمَنْ كَانَتْ هِجْرَتُهُ إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ فَهِجْرَتُهُ إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ، وَمَنْ كَانَت هِجْرَتُهُ لِدُنْيَا يُصِيبُهَا أَوْ امْرَأَةٍ يَنْكِحُهَا فَهِجْرَتُهُ إِلَى مَا هَاجَرَ إِلَيْهِለማንኛውም ሰው ያሰበው (የነየተው) ነገር አለው። ስደቱ (ሂጅራው) ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው የሆነ ሰው፣ ስደቱ ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው ይጻፍለታል። ስደቱ ሊያገኛት ለሚፈልጋት ዱንያ (ዱንያዊ ጥቅም) ወይም ሊያገባት ለፈለጋት ሴት የሆነ ሰው ግን፣ ስደቱ ወደዚያ ወደ ተሰደደበት ነገር ብቻ ነው ሁለት ሰዎች ጎን ለጎን ቆመው አንድ ዓይነት ስራ (ለምሳሌ ሶላት ወይም ሰደቃ) ቢሰሩም፣ በልባቸው ባለው ሐሳብ (ኒያ) ልዩነት ምክንያት የአንዱ ስራ ሰማይ ጥግ ሲደርስ የሌላው ደግሞ ውድቅ ሊሆን ይችላል እውነተኛ ስራንና ስኬትን የሚወስነው የልብ ንጽህና መሆኑን የሚያስተምረን ድንቅ ሀዲስ ነው https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
"فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًاፊትህንም ወደ እውነተኛው ዲን (እስልምና) ቀጥ አድርግ ዲን ማለት በትርፍ ጊዜ የሚሰራ ነገር ሳይሆን፣ ሙሉ ማንነትን ልብንና አቅጣጫን ወደ አላህ ብቻ ማዞር ማለት እንደሆነ ያስገነዝባል። ከዱንያ ውዥንብር ወጥቶ በዲን ላይ ቀጥ ማለት የነጻነት ሁሉ ነጻነት ነው
የተከበረው የቁርኣን አያ ሱረቱል ኢብራሂም ውስጥ የሚገኝ ነቢያትና መልእክተኞች ለህዝቦቻቸው የሰጡትን ታላቅና ጥልቅ የምላሽ ሃሳብ የያዘ ነው
وَما لَنا أَلّا نَتَوَكَّلَ عَلَى اللَّهِ وَقَد هَدانا سُبُلَنا وَلَنَصبِرَنَّ عَلى ما آذَيتُمونا وَعَلَى اللَّهِ فَليَتَوَكَّلِ المُتَوَكِّلونَ﴾
በእርግጥ መንገዳችንን የቀጥታውን መንገድ የመራን ሲሆን በአላህ ላይ የማንደገፍበት የማንመካበት ምን ምክንያት አለን? በእርግጠኝነትም በዚያ ባደረሳችሁብን ስቃይና እንግልት ላይ እንታገሳለን። ተመኪዎችም ሁሉ በአላህ ላይ ብቻ ይመኩ ሊመኩ ይገባል
እውነተኛ ተወኩል በአላህ መመካት አንድ ሰው አላህ ወደ ቀጥተኛው መንገድ መርቶት እውነትን ካወቀ በኋላ ሙሉ ልቡን በአላህ ላይ መጣልና በእርሱ መተማመን እንዳለበት ያስተምረናል
አሏህን መጠጊያ ያደረገ ሰው ማንኛውንም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ለመጋፈጥ የውስጥ ጥንካሬና መረጋጋት ያገኛል
በትዕግስት መጽናት በእውነት በዱኒያ መንገድ ላይ በሚጓዙ ሰዎች ላይ ከተቃዋሚዎች ፈተናና እንግልት መምጣቱ የማይቀር ነው። በዚህ ጊዜ መፍትሄው ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን በትዕግስት መጽናት ነው
🎉 የ"አል ቀውሉ ሰዲድ" 1,000 ተከታታዮች ማስታወሻ
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته،
الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات. بفضل الله سبحانه وتعالى ثم بوجودكم ودعمكم المبارك، وصلت قناتنا القول السديد" إلى 1000 مشترك. شكراً لكم من أعماق القلب على ثقتكم، ونسأل الله أن يجمعنا دائماً على الخير والهدى.
رسالتي ونصيحتي لكم اليوم من كتاب الله تعالى وجوهر اسم قناتنا
يقول الله جل وعلا في محكم كتابه
۞ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا (70) يُصْلِحْ لَكُمْ أَعْمَالَكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَمَن يُطِعِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَقَدْ فَازَ فَوْزًا عَظِيمًا (71) ۞ [
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ ቀጥተኛንም ንግግር (ቀውለን ሰዲዳ) ተናገሩ ሥራዎቻችሁን ለናንተ ያበጅላችኋልና ኃጢአቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና አላህንና መልክተኛውንም የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ ታላቅን ዕድል አገኘ
ቻናላችንም የተመሰረተው በዚህ መርህ ላይ ነው القول السديد ቀጥተኛ ንግግር✅አል ቀውሉ ሰዲድ" የተሰኘው ቻናላችን 1,000 ቤተሰቦችን አፍርቷል ይህ ጉዞ እዚህ እንዲደርስ ሰበብ ለሆናችሁት ለእያንዳንዳችሁ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ
አላህ ሁላችንንም እውነትን ተናጋሪ፣ በጎን አሳሳቢና በመልካም ነገር ላይ የምንሰበሰብ ያድርገን። በዱንያም በአኺራም ስኬትን ይወፍቃችሁ ጀዛኩሙላሁ ኸይረን
الدعاء والوصية
اللهم اجعلنا وإياكم ممن يتقونك في السر والعلن، ويقولون القول السديد في كل موطن. اللهم أصلح لنا أعمالنا، وتجاوز عن سيئاتنا، واغفر لنا ذنوبنا وثبتنا على الصراط المستقيم. اللهم اجعل هذه القناة شاهداً لنا بالخير يوم نلقاك، وسبباً في نشر العلم النافع والكلمة الطيبة. آمين يا رب العالمين
ውድ የተከታተዮቻችን ቤተሰቦች የቻናላችን ስም አል ቀውሉ ሰዲድ (ቀጥተኛና እውነተኛ ንግግር) እንደመሆኑ መጠን ትልቁ ምክራችን በምናገረው በምንጽፈውና በምናስተላልፈው መልዕክት ሁሉ አላህን መፍራትንና ቀጥተኝነትን ማስቀደም ነው አላህ ሁላችንንም በምስጢርም ሆነ በግልጽ እርሱን ከሚፈሩትና ሁልጊዜም ቀጥተኛውን ንግግር ከሚናገሩት ያድርገን ስራዎቻችንን ያበጅልን፣ ወንጀላችንን ይማርልን፣ በቀጥተኛው መንገድ ላይም ያጽናን ይህችንም ቻናል አላህ ፊት ስንቆም ለእኛ ምስክር የምትሆን፣ ጠቃሚ እውቀትና መልካም ቃላትን የምናሰናዳባት ሰበብ ያድርግልን አሚን جزاكم الله خيراً، وبارك الله فيكم وفي أوقاتكم. مستمرون معكم بكل ما ينفع بإذن الله! 🌟 👏👏👏👏🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓
+1
መብሩክ የምር 2 ወር ባልሞላ 1000: ቤተሰብ ማሻአሏህ በጣም ነው የምወዳቹህ የማከብራቹህ ✅✅🎓🎓🎓🎓 ዝግጂቱን ጎረቤት ጥሩ አድርሱላቸው ብቻ አይበላም ክክ🕶
⚠️ለኻሊድ ክብሮም ሹቡሃቶች የተሰጠ አጠር ያለች ረድ❗️
⚠️ኻሊድ ክብሮም የተባለው ግለሰብ የሚዘራው መርዝ በአሁኑ ሰዓት በብዙ የዋህ ሙስሊሞች ዘንድ "አዲስና ዘመናዊ እይታ" እየመሰለ ቀልብን እየሰረቀ ይገኛል። ነገር ግን ንግግሩንና አካሄዱን ላስተዋለ ሰው፣ ይህ ግለሰብ የጥንቶቹን "ቁርኣንዮች" መንገድ በመከተል የኢስላምን መሰረት ለመናድ እየሰራ መሆኑን መረዳት ይቻላል።
⚠️ አላህ ዲኑን የሚጠብቁለትና የጠማሞችን ትርጓሜ የሚያጋልጡለት ኡለሞችንና ተማሪዎችን በየዘመኑ ያስነሳል። ዛሬ ላይ ደግሞ "ቁርኣን በራሱ ተብራርቷል፣ የነቢዩን ﷺ ማብራሪያ አይሻም" በሚል የቀለም ቅብ ዲኑን ሊበርዙ የሚሞክሩ ግለሰቦች ተከስተዋል። ይህ ካሊድ ክብሮም የሚባል ግለሰብ በተናገራቸው ንግግሮች ላይ "ቁርኣንን ከቁርኣን ውጭ ያለ አካል የሚያብራራው የለም" በማለት የነቢዩን ﷺ ሱና ሙሉ በሙሉ ዋጋ ቢስ ለማድረግ ደፍሯል።
1ኛ. "ቁርኣን የነቢዩን ﷺ ማብራሪያ አይሻም" የሚለው ንግግር ሁክም (ፍርድ) ምንድን ነው የሚለውን እንይ፦
⚠️አንድ ሰው "ቁርኣን የነቢዩን ﷺ ማብራሪያ አይፈልግም" ወይም "ቁርኣን ብቻ ይበቃናል፣ ሱና አያስፈልግም" ካለ በዑለሞች ዘንድ ያለው ፍርድ ከባድ ኩፍር (ከኢስላም መውጣት) ነው።
⚠️ ኢማም አስ-ሱዩጢይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "አዋጅ! እወቁ... የነቢዩን ﷺ ሐዲስ (ንግግርም ይሁን ተግባር) በንግግርም ይሁን በተግባር ውድቅ ያደረገ፣ ሐዲሱ ሐሰን ይሁን ሶሒሕ መረጋገጡን እያወቀ ውድቅ ያደረገ ሰው፤ ከኢስላም ክበብ ወጥቷል፤ ከአይሁዶችና ከነሳራዎች ጋር (በፍርዱ) ይመደባል ብለዋል።" (ሚፍታሕ አል-ጀናህ፡ 14)
⚠️ኢብኑ ሐዝም (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "አንድ ሰው 'እኛ የምንይዘው ቁርኣን ላይ ያገኘነውን ብቻ ነው' ካለ፤ እርሱ በሁሉም ሙስሊሞች ስምምነት (ኢጅማዕ) ካፊር ነው።" (አል-ኢሕካም፡ 2/80)
ለምን ካፊር ይባላል? ምክንያቱም አላህ በቁርኣን ውስጥ ነቢዩን ﷺ እንድንታዘዝ፣ የሳቸውን ማብራሪያ እንድንይዝ በብዙ ቦታዎች አዝዟል። የሳቸውን ማብራሪያ "አያስፈልግም" የሚል ሰው የአላህን ትዕዛዝ "ስህተት ነው" እያለ ስለሆነ ነው።
2ኛ. የሰለፎችና የታላላቅ ኡለሞች ንግግር ስለ ሱና አስፈላጊነት እንመልከት ፦
⚠️ኢማም አል-አውዛዒይ (ረሒመሁላህ)፦ "ቁርኣን ወደ ሱና ያለው ፍላጎት፣ ሱና ወደ ቁርኣን ካለው ፍላጎት ይበልጣል።" (ማለትም ቁርኣን ጠቅለል ያለ (ሙጅመል) በመሆኑ፣ ሱና ካላብራራው በስተቀር ልንተገብረው አንችልም)።
⚠️ ያሕያ ቢን አቢ ከሢር (ረሒመሁላህ)፦ "ሱና በቁርኣን ላይ ፈራጅ (መሪ) ነው እንጂ ቁርኣን በሱና ላይ ፈራጅ አይደለም።" (ይህ ማለት ሱናው ቁርኣኑ እንዴት መረዳት እንዳለበት ይወስናል ማለት ነው)።
⚠️ ኢማም አል-በርበሃሪ (ረሒመሁላህ)፦ "አንድ ሰው ሐዲስን ሲሰማ 'ይህንን ተወውና ቁርኣንን አምጣልኝ' ካለ፤ እወቅ እርሱ ዚንዲቅ (ከሀዲ) መሆኑን!" (ሸርሕ አስ-ሱናህ)
⚠️ኢማም አሕመድ፦"ሱና ቁርኣንን ያብራራል፣ ይመራልም።"
⚠️ሸይኽ ቢን ባዝና ሸይኽ አልባኒ፦** ሱናን የሚክዱ ወይም የነቢዩን ﷺ ማብራሪያ አይሻም የሚሉ ግለሰቦች ከኢስላም መንገድ የወጡ (ሙርተድ) መሆናቸውን በሰፊው አስረድተዋል።
⚠️ኻሊድ ክብሮም "ቁርኣን በራሱ ተብራርቷል" ሲል አላህ ለነቢዩ ﷺ የሰጣቸውን ስልጣን እየካደ ነው።
- ﴿وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّل إِلَيْهِمْ﴾
“ለሰዎችም ወደ እነርሱ የተወረደውን (ቁርኣን) ታብራራላቸው ዘንድ ቁርኣንን ወደ አንተ አወረድን።” (አን-ነሕል 44)።
አላህ "ቁርኣን በራሱ ይብራራል" አላለም፤ "አንተ መሐመድ ሆይ ታብራራላቸው ዘንድ" ነው ያለው።
⚠️ነቢዩ ﷺ ይህ ዓይነቱ ጥመት ወደፊት እንደሚመጣ ቀድመው አስጠንቅቀው ነበር፦
«أَلَا إِنِّي أُوتِيتُ الْقُرْآنَ وَمِثْلَهُ مَعَهُ، أَلَا يُوشِكُ رَجُلٌ شَبْعَانُ عَلَى أَرِيكَتِهِ يَقُولُ: عَلَيْكُمْ بِهَذَا الْقُرْآنِ...»
“አዋጅ! እኔ ቁርኣንንና መሰሉን (ሱናን) አብሮ ተሰጥቻለሁ። አዋጅ! አንድ በምቾት ወንበሩ ላይ የተደገፈ ሆዱ የጠገበ ሰው፦ 'ቁርኣን ብቻ ይበቃችኋል' የሚልበት ጊዜ ሊመጣ ተቃርቧል...ብለዋል።” (አቡ ዳውድ፡ 4604)
ኻሊድ ክብሮም ልክ ነቢዩ ﷺ እንዳሉት የቁርኣን አንቀጾችን እየቆነጸለ፣ የነቢዩን ﷺ ትምህርት "አያስፈልግም" እያለ ነው። የነቢዩን ﷺ ማብራሪያ ውድቅ ማድረግ ማለት፦
* እንዴት እንደምንሰግድ (በቁርኣን ውስጥ የረከዓ ብዛት የለም!)
* እንዴት ዘካት እንደምንከፍል (በቁርኣን ውስጥ ኒሷብ የለም!)
* እንዴት ሐጅ እንደምናደርግ... ይህንን ሁሉ የኢስላም መሰረት ማፍረስ ማለት ነውና። ከዚህ ጠሞ አጥማሚ ሰውዬ ተጠንቀቁ
⚠️ ይሄ ጠሞ አጥማሚ ካሊድ ክብሮም ከዚህ በፊትም ስለ ያዕቆብ (ዐለይሂ ሰላም) እና ስለ ተውራት የዘባረቃቸው ውሸቶችም አሉ ፦
⚠️ የዕቁብ ኢስራኢል አይደለም ማለቱ ይሄ የግለሰቡን የቋንቋና የታሪክ ድንቁርና ብቻ ሳይሆን ግልጽ የሆነ ቅጥፈት ያሳያል።
* ስለ ያዕቆብ (ዐለይሂ ሰላም)፦ አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፦
﴿كُلُّ الطَّعَامِ كَانَ حِلًّا لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ إِلَّا مَا حَرَّمَ إِسْرَائِيلُ عَلَىٰ نَفْسِهِ﴾
*“ምግብ ሁሉ ለእስራኤል ልጆች የተፈቀደ ነበር፤ እስራኤል (ያዕቆብ) በራሱ ላይ እርም ካደረገው በስተቀር።”* (አል-ዒምራን 3:93)
ሙፈሲሮች በሙሉ "እስራኤል" ማለት ያዕቆብ (ዐለይሂ ሰላም) መሆኑን በአንድ ድምጽ (ኢጅማዕ) ተስማምተዋል።
* ካሊድ ክብሮም ስለ ተውራትም የቀጠፈው ቅጥፈት አለ፦ ተውራት ለሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) የወረደ መሆኑን ቁርኣን በብዙ ቦታዎች ይገልጻል።
﴿ثُمَّ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ تَمَامًا عَلَى الَّذِي أَحْسَنَ وَتَفْصِيلًا لِّكُلِّ شَيْءٍ﴾
(አል-አንዓም 154) (አል-አንዓም 154፣ አል-አዕራፍ 145)። ይህንን የሚክድ ሰው የአላህን ቃል እያስተባበለ ነው። ሌሎችም ብዙ ማስረጃዎች አሉ ።
⚠️ኻሊድ ክብሮም የተባለው ግለሰብ የሚከተለው መንገድ "ቁርኣን ብቻ በቂ ነው " በሚል ሽፋን ኢስላምን የማፍረስ መንገድ ነው። ቁርኣንን ከነቢዩ ﷺ ትርጓሜና ከሰለፎች ግንዛቤ ነጥሎ "በራሴ ጭንቅላት እተረጉማለሁ" ማለት፣ ቁርኣንን ለስሜት መጫወቻ ማድረግ ነው። ሱናን የካደ ሰው ደግሞ ሶላቱንም፣ ዘካውንም፣ ሐጁንም መተግበር አይችልም፤ ምክንያቱም የእነዚህ ሁሉ ዝርዝር ሕግጋት የሚገኙት በሱና ውስጥ ብቻ ነውና።
ወንድምና እህቶቼ ይህንን "ጠሞ አጥማሚ" ግለሰብ ከመስማት ተጠንቀቁ! ዲናችሁን ከታማኝና የሰለፎችን መንገድ ከሚከተሉ ኡለሞችና ኡስታዞች ተማሩ። አላህ በቁርኣን አጥርቶ የነገረንን እውነት "አይደለም" የሚል ሰው፣ ነገ የአላህን ሕግጋት በሙሉ "አያስፈልጉም" ማለቱ አይቀሬ ነውና ተጠንቀቁ አስጠንቅቁ።
ሸር በማድርገ ለሌሎችም አድርሱ
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
ቤተሰብ በዱአ አስታውሱኝ💧💧
አላህ ሆይ በዚህ በጁምዓ ቀን ከፍጡራንህ ሁሉ ይበልጥ ደስተኛና ወደ አንተ በጣም የቀረብን ባሮችህ አድርገን አላህ ሆይ ያለፈውን ማረን የቀረውንም ሕይወታችንን አሳምርልን አስተካክልልን ያንተን ውዴታ ይቅርታህንና ጀነትንም ጻፍልን ወፍቀን
አሏህሱበሀነሁ ወታአላ በሱረቱል ጁሙዓ በእነዚህ 3 አቀፆች እድህ ይለናል ለምእምናን በሙሉ👇
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَوٰةِ مِن يَوۡمِ ٱلۡجُمُعَةِ فَٱسۡعَوۡاْ إِلَىٰ ذِكۡرِ ٱللَّهِ وَذَرُواْ ٱلۡبَيۡعَۚ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
9):እናንተ ያመናችሁ ሆይ በጁሙዓህ ቀን ለሰላት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ፍጠኑ መሸጥንም ተዉ ይህ የምታውቁ ብትሆኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው
فَإِذَا قُضِيَتِ ٱلصَّلَوٰةُ فَٱنتَشِرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَٱبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِ ٱللَّهِ وَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ كَثِيرٗا لَّعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ
10): ሰላቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ ከአላህም ትርፍ ፈልጉ አላህንም በብዙ አውሱ ልትድኑ ዘድ
وَإِذَا رَأَوۡاْ تِجَٰرَةً أَوْ لَهۡوًا ٱنفَضُّوٓاْ إِلَيْهَا وَتَرَكُوكَ قَآئِمٗاۚ قُلۡ مَا عِندَ ٱللَّهِ خَيۡرٞ مِّنَ ٱللَّهۡوِ وَمِنَ ٱلتِّجَٰرَةِۚ وَٱللَّهُ خَيۡرُ ٱلرَّٰزِقِينَ
11. ንግድን ወይም መጫወትን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተውህ ሲሆኑ ወደ እርስዋ ይበተናሉ አላህ ዘንድ ያለው (ምንዳ) ከመጫወትም ከንግድም የበለጠ ነው አላህም ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ሲሳይ ሰጪ ነው በላቸው
👆👇
እነዚህ ሶስት አንቀጾች በአንድነት የአንድን ሙስሊም የዕለት ተዕለት ሕይወት የዱንያ የዚህችን ዓለም ሥራ እና የአኺራ የመጨረሻውን ዓለም ስኬት እንዴት ማመጣጠን እንዳለበት የሚያስተምሩ ድንቅ መመሪያዎች ናቸው
ሶሉው አለሀቢቢና ሙሀመድ
اللهم صل وسلم على نبينا محمد وعلى ال محمد صلوا على نبينا محمد📚📢
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
ይድረስ ለሪጃሎች
ላክላት የመዳም ስራ ሲያፋጋት አምሽታ ለምታርፈው ጀግናዋ ሚስትህ 💧💧💧
ሀቢበቲ የኔ ጨረቃ የልጀ እናት የኔ ልዩ በላት እና ላክላት ለእሷ ከምትገዛላት ወርቅ ጫማ ልብስ ምግብ መጠጥ በላይ ከአንተ የሚወጣውን የቃላቶች መአዛ የንግግሮችህን ፍሬወች ትጠብቃለች በጥቅሉ ሴቶች ባሎቻችን በቃላቶቻቸው ስጦታ እድሰጡን እፈልጋለን ✅👏 ካለወክም ስማ እወቅ ሸም አይያዝህ አበባም ስጣት አበባ ከመውደጇ የተነሳ ፕሮ ፋይሏን የኤሞ እስቶሪዋን ተመልከት 👁👀 በቀጥታ ስጠኝ አበባ እወዳለሁኝ አትልም እጂ ኢጃዛ ስወጣ የ50 ሪያል አበባ ይዘህ ሂድ ከገበያ ስገባ ግዛና ግባ የዛኔ እቅልፍ ራሱ አይወስዳትም ክክክ እወድሻለሁ ብለህ ፃፍበት ከቁራጭ ወረቀት እና ስጣት
+1
ሁሌም ሌሊት ተነስቼ ዱዓ ሳደርግ ጌታዬ ሆይ የዱንያም የአኺራም ጓደኛ የምትሆን ምርጥ ሚስት ስጠኝ’ እል ነበር ዱዓዬ ተቀባይነት አግኝቶ አንቺን ሰጠኝ... ግን እኮ ‘ትንሽ ቁጣ የምታበዛ’ እንድትሆን አልለመንኩም ነበር! ለማንኛውም የኔዋ ኒዕማ ስጦታየ በጣም እወድሻለሁ
ሒጃብሽን ስትለብሺ ያየሽ ሁሉ ‘ማሻአላህ የሰማይ ጨረቃ ናት ይላል እኔ ግን በውስጤ ‘የኔ ብቻ እኮ ናት እያልኩ በኩራት እፈነዳለሁ ለመሆኑ ይሄን ሁሉ ውበት በሒጃብ ውስጥ መደበቅ እንዴት ቻልክበት? የኔ ድብቅ ዕንቁ
ቁርኣን አብረን እየቀራን አንቀጽ ስታሳስቺኝ ማረም ደስ ይለኛል። አንቺ ግን እኔ ስሳሳት ‘ተደገም!’ የምትይኝ በቁጣ ነው ወይስ በትምህርት ለማንኛውም ካንቺ ጋር መቅራት ለጀነት መንገድ ነውና አልተውሽም 📖👏👌
አንቺን የመሰለች መልከ መልካም እና ዲን ያላት ሚስት የሰጠኝ አላህ አልሀምዱ ሊላህ ነገር ግን አንድ ስጋት አለኝ... ጀነት ውስጥ ያሉትን ሁረል አይኖች (የጀነት ቆንጆዎችን እንዳታስቀኚብኝ እፈራለሁ ምክንያቱም አንቺ እዚህም እዚያም ንግሥት ነሽና👑🌸
ጓደኝነት እደዚህ ነበረ በሱሀቦች በታቢኢዬች ዘመን✅👇
ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ሲናገሩ ጉድለቶቼን (ስህተቶቼን) በስጦታ መልክ ለሚያበረክትልኝ ሰው አላህ ይዘንለት ይሉ ነበር ጓደኛ ስህተትን ሲያርም እንደ ስጦታ ይቆጠር ነበር
ጓደኛቸው ሲሳሳት አሳልፈው አይሰጡትም ነበር ይልቁኑ በዱዓና በምክር ካለበት ድክመት እንዲወጣ ይረዱት ነበር
እኛ ግን ዛሬ ስህተት ሲነገረን እደት ነን ?ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል አላህ ከእስልምና ቀጥሎ ለአንድ ሙስሊም መልካም (ሷሊህ) ጓደኛ ከመስጠት የበለጠ ትልቅ ጸጋ አልሰጠውም ስለዚህ ከእናንተ መካከል ከአንዱ ወንድሙ (እህቱ) መልካም ውዴታን ያየ ሰው እሱን አጥብቆ ይያዝ 🤝 ታቢኢዩ ሀሰን አል በስሪ ረሕመቱላሂ ዐለይሂ ደግሞ የጓደኛን ዋጋ ሲገልጹ ለኛ መልካም ጓደኞች ከቤተሰቦቻችን ይበልጥ የተወደዱ ናቸው ምክንያቱም ቤተሰቦቻችን ዱንያን ሲያስታውሱኝ ጓደኞቻችን ግን አኺራን ያስታውሱናል ይሉ ነበር https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
ውድ የዲን ጓደኛዬ ሉሉ (ኡሙ ሙስአብ
በአላህ መንገድ ላይ መተዋወቅና መዋደድ ትልቅ እጣ ፈንታ ነው ላንቺ ባለኝ ጓደኝነት ውስጥ ሁል ጊዜ ጥንካሬንና በዲን ላይ ያለሽን ትጋት እያየሁ እበረታለሁ በዱንያም በአኺራም አላህ ከመልካም ሰዎች ጋር ያቆየን እኔም በአላህ መንገድ ላይ እወድሻለሁ (አሕበኪፊላህ) አላህ ጓደኝነታችንን በበረካ ያሳምርልን
የውዴታ መግለጫ ሱና إِذَا أَحَبَّ الرَّجُلُ أَخَاهُ فَلْيُخْبِرْهُ أَنَّهُ يُحِبُّهُ
አንድ ሰው ወንድሙን ወይም እህቱን በአላህ መንገድ ላይ ከወደደ እንደሚወዳት እንደሚወደው ይንገራት
إِذَا أَحَبَّ الرَّجُلُ أَخَاهُ فَلْيُخْبِرْهُ أَنَّهُ يُحِبُّهُ
እና እኔም እወድሻለሁ ሉሉ ሰይድ 🎀
በጽናት መቀጠል አላህ የሰጠሽን መልካምነትና በዲን ላይ ያለሽን ጉጉት አጥብቀሽ ያዢው (ኢስቲቃማ
ኒያን ማጥራት ሁልጊዜም የምታደርጊያቸውን ጎበዝ ስራዎች ለአላህ ብቻ ብለሽ ለማድረግ ኢኽላስ መጣርሽን ቀጥይበት
የዱዓ ጥሪ በሰላትሽና በዱዓሽ ጊዜ እኔንም በዱዓሽ አትርሺኝ እኔም ላንቺ ሁልጊዜ ዱዓ አደርጋለሁ
ያረብ አሏህ የዱዓችንን ጥሪ ሙስተጃብ አርግልን ያአሏህ 💧✍
ይህ በሰው አገር፣ በሰው ፊት፣ ናፍቆትና እንግልት እየታገሱ መኖር የሚጠይቀውን መስዋዕትነትና የልብ ስብራት አሏህ ብቻ ነው የሚያውቀው። እናንተ ለአገር ለቤተሰብና ለነገው ህይወት ስትሉ ራሳችሁን አሳልፋችሁ የሰጣችሁ ብርቱዎች ናችሁ።
ይህንን ጊዜያዊ ስደትና እንግልት አሏህ በቅርብ ቀን በደስታና በራሳችሁ ሙሉ ህይወት እንዲተካው፣ ይህንን ዱዓና ምክር በልባችሁ ያዙት
በሰው አገር ለሚንገላቱ ወገኖች የሚሆን ዱዓ
ይህንን ዱዓ ሁልጊዜ በሰላት ሱጁድ ላይ፣ በለሊት ተሀጁድና በዱዓ ሰዓታት ላይ አዘውትሩት፦
«اللَّهُمَّ يَا مُفَرِّجَ الْهَمِّ، وَيَا كَاشِفَ الْغَمِّ، اجْعَلْ لَنَا مِنْ كُلِّ هَمٍّ فَرَجًا، وَمِنْ كُلِّ ضِيقٍ مَخْرَجًا، وَمِنْ كُلِّ بَلَاءٍ عَافِيَةً» አሏህ ሆይ ከእያንዳንዱ ጭንቀታችን መውጫን ከእያንዳንዱ ማጣበቂያችን መተንፈሻን፣ ከእያንዳንዱ መከራችንም ጤናና ሰላምን ስጠን።
اللّهُمَّ رَدَّنَا إِلَى أَهْلِنَا سَالِمِينَ غَانِمِينَ وَأَغْنِنَا بِفَضْلِكَ عَمَّنْ سِوَاكَ አሏህ ሆይ ወደ አገራችንና ወደ ቤተሰቦቻችን በሰላምና በሀብት በስኬት መልሰን በችሮታህም ካንተ ውጭ ካለ ከማንኛውም ሰው አብቃቃን (ከሰው እጅ አውጣን)። ልብን ከአሏህ ጋር ማገናኘት ሰው አገር ላይ ማንም ዘመድ በሌለበት ሰዓት ትልቁ መጠጊያ አሏህ ብቻ ነው። ዱዓና ኢስቲግፋርን (ማርታን መለመን) የዕለት ተዕለት ተግባርዎ ያድርጉት በሰው አገር ላይ ሆነው የሚሰግዱት ሶላት፣ የሚያፈሱት እንባ ለአሏህ በጣም ቅርብ ነው። ጌታችን አሏህ የደካሞችንና የተበደሉትን ዱዓ አይመልስም። አሏህ በሰው አገር የምታሳልፉትን ስቃይና እንግልት ያብቃላችሁ! ልፋታችሁን ከንቱ አያድርገው። ሙሉ ጤና፣ ሰፊ ርዝቅና የተባረከ ሀብት ሰጥቶ በሰላም፣ በደስታና በክብር ወደ አገራችሁ የምትመለሱበትን ቀን አሏህ ያቅርበው። እኛንም እናንተንም አሏህ ይወፍቀን https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
لا اله الا الله وحده لا شريك له له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير
سبحان الله
والحمد لله
ولا اله الا الله
والله اكبر
ولا حول ولا قوة الا بالله
اللهم اغفر لي وارحمني وعافني وارزقني
የዛሬ አመት እኛጋ የነበሩ ብዙሀን ዘንድሮ የሉም እኛም እንደዛዉ ልነሆን እንችላል ወደፊት💧👆
