الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
رفتن به کانال در Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
2 192
مشترکین
+2824 ساعت
+447 روز
+45130 روز
آرشیو پست ها
+3
"አሏህ ሆይ! ይህንን አዲስ ዓመት የሰላም የጤና የደስታና የብልጽግና ዓመት አድርግልን። ልባችንን በደስታ ሙላው ከጭንቀትና ከከባድ ፈተናዎችም ጠብቀን። ያሰብናቸውን መልካም ምኞቶች ሁሉ አሳካልን በሲሳያችንና በሕይወታችን ላይ በረከትህን አውርድልን። ፈጣሪ ሆይ! ካለፈው ዓመት ስህተቶቻችን ተምረን የተሻሉ ሰዎች የምንሆንበት ብሩህ ዓመት አድርግልን። አሚን🤲🤲🤲
እጥን ምጥን ያለች ምክር 👌👌👌 ቤተሰብ ይቺቻናል ትደግ ገና ከጅምሯ የሚጣፍጡ ቁም ነገር አዘል ምክሮች አሏት ሀቂቃ ሸር በማድረግ እናግዛት አሙቲንም እናበረታታት✅👆
ቻናል ያላቹህ እደዚህ አለም አቀፍ ምክር ሲኖር ሸር አርጉት አይክበዳቹህ ሀቂቃ የግድ ታዋቂ መሆን የለባትም 👍👍
አሰላም ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድና የተወደዳቹህ የቻናላችን ቤተሰቦች አሏህ ይጠብቃቹህ በመቀጠል✍👇
እድታነቧት እፈልጋለሁኝ ለሌሎችም ሸር እድታደርጉት 👇 የፃፍኩት ሁሉንም ነው የሚል ማጠቃለያ ሳይሆን አዳድ ልጆች ስላሉ ለማስታወስ ነው 👌👌
ይህ በጣም ጠቃሚ እና በርካታ እህቶችን ሊያነቃቃ የሚገባው ትዝብት ነው። በአረብ ሀገር ያሉ እህቶቻችን ጠንካሮች የሰው ቤት ለማፅዳትና ለማስዋብ ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉ መሆናቸውን ማንም አይክደውም። ነገር ግን የራሳቸውን ክፍል እና መታጠቢያ ቤት (ሽንት ቤት) ችላ ማለት ትልቅ ስህተት ነው።
ይህንን አስገዳጅና /እህታዊ ምክር በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች እንመልከታቸው ?!
1. ራስን መውደድ እና ክብር ከራስ ክፍል ይጀምራል
የሰው ቤት አብረቅርቆ የራስን ማደሪያ በቆሻሻ መሙላት የራስን ክብር ዝቅ ማድረግ ነው። “የራሴ ክፍል ነው ማንም አይገባበትም” የሚለው አስተሳሰብ ፈጽሞ ስህተት ነው።
ሰው ባያየው እንኳን ፈጣሪ ያየዋል መላእክት ንፅህና በሌለበት ቦታ አይጠጉም።
እራስሽን የምታከብሪ ከሆነ ለአካልሽ ብቻ ሳይሆን ለሚያድርበት ክፍልሽም ክብርና ንፅህና መስጠት አለብሽ
2. ጤና እና የአእምሮ እረፍት
የበሽታ መፈልፈያ ሽንት ቤትና ክፍል ካልተፈገፈገ እና ካልተፀዳ ባክቴሪያ ፈንገስ እና ተላላፊ በሽታዎች ይቀፈቀፉበታል። በቀን አስራ ሁለት ሰአት የሰው ቤት ስታፀጂ ውለሽ ማታ ቆሻሻ ክፍል ውስጥ መተኛት ለጤና እጅግ አደገኛ ነው።
የአእምሮ ውጥረት የተዝረከረከ እና የቆሸሸ ክፍል ጭንቀትንና ድብርትን ይጋብዛል። ንፁህ ክፍል ግን ከስራ ብዛት ለደከመ አእምሮ ትልቅ እረፍትና ሰላም ይሰጣል
3. "ነገ" የሚባል ነገር አለ (ባንክሺን አታበላሺ!)
በአረብ ሀገር ስራ መቀያየር የተለመደ ነው። አንቺ ስራ ቀይረሽ ስትወጪ ሌላ እህትሽ ያንን ክፍል ትረከበዋለች
ዝባላ (ቆሻሻ) ጥለሽ ስትሄጂ የሚቀጥለው ሰው የሚረግምሽና የሚታዘብሽ መሆኑን አትርሺ። በሄድሽበት ቦታ ሁሉ መልካም ስምሽንና ታሪክሽን እንጂ ቆሻሻሽን አትተዊ።
አንቺስ ብትሆኚ ስራ ቀይረሽ ስትገቢ የሌላ ሰው ሽንት ቤት ቆሽሾና ክፍሉ ዝባላ ሆኖ ብታገኚው ምን ይሰማሻል? ለራስሽ የማይመችሽን ለሌላው እህትሽ አትመኚ
4. ለአረቦቹ የምንሰጠው ምስል
አረቦቹ ክፍላችንን በድንገት ቢያዩት ወይም ስራ ስንቀይር ገብተው ቢታዘቡት “ውጭዋ እሸት ውስጧ ሽልጥ” ማለታቸው አይቀርም። “እኛን ፈርታ ነው እንጂ ንፅህና ባህሪዋ አይደለም” የሚል ታዝቦት ውስጥ ይከተናል። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያውያንን መልካም ስም ያጠፋል።
✍👇 ጥብቅ ማጠቃለያ ምክር ለአህቶቻችን ውድ እህቴ! የሰው ቤት የምታሳምሪው በደሞዝሽ ምክንያት ነው። የራስሽን ክፍልና ሽንት ቤት የምታፀጂው ግን ለራስሽ ስትይ ለጤናሽ ስትይ እና ለክብርሽ ስትይ ነው። በቀን 15 ደቂቃ ብቻ ለራስሽ ክፍል ስጪ። አልጋሽን አንጥፊ ሽንት ቤትሽን በክሎረክስ ፈግፍጊ ቆሻሻሽን በየቀኑ ጣዪ። የትም ቦታ ስራ ስትቀይሪ ክፍሉን ያስረከብሽው ሰው “የእውነት ንፁህ እና የተባረከች ልጅ ነበረች!” ብሎ እንዲመርቅሽ እንጂ እንዲረግምሽ አታድርጊ። ንፅህና የኢማን (የእምነት) አካል ነውና እራስሽን ጠብቂአሏህ የእርፈት እንጀራ ለሁላችንም ይስጠን ስደት በቃቹህ ይበለን
አሰላም ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድና የተወደዳቹህ የቻናላችን ቤተሰቦች አሏህ ይጠብቃቹህ በመቀጠል✍👇
እድታነቧት እፈልጋለሁኝ ለሌሎችም ሸር እድታደርጉት 👇 የፃፍኩት ሁሉንም ነው የሚል ማጠቃለያ ሳይሆን አዳድ ልጆች ስላሉ ለማስታወስ ነው 👌👌
ይህ በጣም ጠቃሚ እና በርካታ እህቶችን ሊያነቃቃ የሚገባው ትዝብት ነው። በአረብ ሀገር ያሉ እህቶቻችን ጠንካሮች የሰው ቤት ለማፅዳትና ለማስዋብ ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉ መሆናቸውን ማንም አይክደውም። ነገር ግን የራሳቸውን ክፍል እና መታጠቢያ ቤት (ሽንት ቤት) ችላ ማለት ትልቅ ስህተት ነው።
ይህንን አስገዳጅና ወንድማዊ/እህታዊ ምክር በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች እንግለጻቸው
1. ራስን መውደድ እና ክብር ከራስ ክፍል ይጀምራል
የሰው ቤት አብረቅርቆ የራስን ማደሪያ በቆሻሻ መሙላት የራስን ክብር ዝቅ ማድረግ ነው። “የራሴ ክፍል ነው ማንም አይገባበትም” የሚለው አስተሳሰብ ፈጽሞ ስህተት ነው።
ሰው ባያየው እንኳን ፈጣሪ ያየዋል መላእክት ንፅህና በሌለበት ቦታ አይጠጉም።
እራስሽን የምታከብሪ ከሆነ ለአካልሽ ብቻ ሳይሆን ለሚያድርበት ክፍልሽም ክብርና ንፅህና መስጠት አለብሽ
2. ጤና እና የአእምሮ እረፍት
የበሽታ መፈልፈያ ሽንት ቤትና ክፍል ካልተፈገፈገ እና ካልተፀዳ ባክቴሪያ ፈንገስ እና ተላላፊ በሽታዎች ይቀፈቀፉበታል። በቀን አስራ ሁለት ሰአት የሰው ቤት ስታፀጂ ውለሽ ማታ ቆሻሻ ክፍል ውስጥ መተኛት ለጤና እጅግ አደገኛ ነው።
የአእምሮ ውጥረት የተዝረከረከ እና የቆሸሸ ክፍል ጭንቀትንና ድብርትን ይጋብዛል። ንፁህ ክፍል ግን ከስራ ብዛት ለደከመ አእምሮ ትልቅ እረፍትና ሰላም ይሰጣል
3. "ነገ" የሚባል ነገር አለ (ባንክሺን አታበላሺ!)
በአረብ ሀገር ስራ መቀያየር የተለመደ ነው። አንቺ ስራ ቀይረሽ ስትወጪ ሌላ እህትሽ ያንን ክፍል ትረከበዋለች
ዝባላ (ቆሻሻ) ጥለሽ ስትሄጂ የሚቀጥለው ሰው የሚረግምሽና የሚታዘብሽ መሆኑን አትርሺ። በሄድሽበት ቦታ ሁሉ መልካም ስምሽንና ታሪክሽን እንጂ ቆሻሻሽን አትተዊ።
አንቺስ ብትሆኚ ስራ ቀይረሽ ስትገቢ የሌላ ሰው ሽንት ቤት ቆሽሾና ክፍሉ ዝባላ ሆኖ ብታገኚው ምን ይሰማሻል? ለራስሽ የማይመችሽን ለሌላው እህትሽ አትመኚ
4. ለአረቦቹ የምንሰጠው ምስል
አረቦቹ ክፍላችንን በድንገት ቢያዩት ወይም ስራ ስንቀይር ገብተው ቢታዘቡት “ውጭዋ እሸት ውስጧ ሽልጥ” ማለታቸው አይቀርም። “እኛን ፈርታ ነው እንጂ ንፅህና ባህሪዋ አይደለም” የሚል ታዝቦት ውስጥ ይከተናል። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያውያንን መልካም ስም ያጠፋል።
✍👇 ጥብቅ ማጠቃለያ ምክር ለአህቶቻችን ውድ እህቴ! የሰው ቤት የምታሳምሪው በደሞዝሽ ምክንያት ነው። የራስሽን ክፍልና ሽንት ቤት የምታፀጂው ግን ለራስሽ ስትይ ለጤናሽ ስትይ እና ለክብርሽ ስትይ ነው። በቀን 15 ደቂቃ ብቻ ለራስሽ ክፍል ስጪ። አልጋሽን አንጥፊ ሽንት ቤትሽን በክሎረክስ ፈግፍጊ ቆሻሻሽን በየቀኑ ጣዪ። የትም ቦታ ስራ ስትቀይሪ ክፍሉን ያስረከብሽው ሰው “የእውነት ንፁህ እና የተባረከች ልጅ ነበረች!” ብሎ እንዲመርቅሽ እንጂ እንዲረግምሽ አታድርጊ። ንፅህና የኢማን (የእምነት) አካል ነውና እራስሽን ጠብቂአሏህ የእርፈት እንጀራ ለሁላችንም ይስጠን ስደት በቃቹህ ይበለን
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
👉 የእስላማዊ ትላልቅ ቻናል መግዛት የምትፈልጉ ዋጋቸው 💵
👉5k subscribers 3000 birr
👉6k subscribers 3500 birr
👉7k subscribers 4000 birr
👉8k subscribers 4500 birr
👉9k subscribers 5000 birr
👉10k subscribers 6000 birr
🫰መግዛት የሚፈልግ ብቻ ያናግረን ✨
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
''የብዙ ሟች ቤተሰቦችን ማግኘት አልተቻለም'' 🚨
⚠️ አስቸኳይ መልዕክት፡ #ሸር ይደረግ! ⚠️ የሟቾች ቤተሰቦችን ማግኘት ባለመቻሉ አስቸኳይ እገዛ ይፈለጋል። 🚨''
ዛሬ ማለዳ ሰኔ 08/2018 ዓ.ም በደሴ እና ኮምቦልቻ መካከል በሚገኘው ''ሀረጎ'' መንገድ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ የ31 ሰዎች ሕይወት ማለፉ የሚታወስ ነው።
የሟቾች አስክሬን ደሴና ከምቦልቻ ሆስፒታሎች የሚገኝ ሲሆን ''በዚህ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ብዙ ሰዎች መታወቂያ እና ማንነታቸውን የሚገልፅ መረጃ ባለመኖሩ'' አስከሬን ለማስረከብም ሆነ ሁኔታውን ለማሳወቅና የቤተሰቦቻቸውን አድራሻ ማግኘት ከባድ ሆኗል ተብሏል።
አደጋ የደረሰበት ''አውቶቡስ ሰኔ 07/2018 ዓ.ዓ መነሻው ከቦረና መካነ-ሰላም ከተማ እንደሆነም የተገለፀ ሲሆን'' ይህ መልዕክት ለሚመለከታቸው ቤተሰቦች በፍጥነት እንዲደርስ ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ።
በተለይ ከመካነ-ሰላም ወደ አድስ አበባ የተጓዘ የቤተሰብ አካል ካለና አድራሻው የጠፋባችሁ ወይም የምታውቁት ሰው ካለ መረጃዎችን በማመሳከር እንድትተባበሩና መረጃው ለሌላቸው ደግሞ ይህንን ፅሁፍ በየግሩፑ እና በየገጻችሁ #Share በማድረግ አግዙ።
የአንድ ሰው ''ሼር'' ማድረግ ለአንድ ቤተሰብ መጽናኛና መረጃ ሊሆን ይችላል።
ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለተጎጅ ቤተሰቦችም መጽናናትን እንመኛለን!
+5
ውድና የተከበርሽ እህቴ ሆይ! ይህች አጭር መልዕክት ለአንቺ የተዘጋጀች የልብ ስጦታ ናት በጥንቃቄ አድምጪኝ፡✉️🎀
ውበትሽ ያለው በሀያእሽ (በሀፍረትሽ) ውስጥ ነው የሙስሊም ሴት ትልቁ ጌጧና ክብሯ ጥንካሬዋና ውጫዊ ውበቷ ሳይሆን ለአላህ ያላት ፍርሃትና የምትከናነበው ውብ ሀያእ ነው። ሂጃብሽ ፋሽን ሳይሆን የአላህ ትእዛዝ! የአንቺም መለያ መሆኑን አትዘንጊ።
ልብሽን በቁርአን አርጥቢው የዚህ ዲንያ ሩጫና ጭንቀት ልብሽን እንዳያደክመው! ሁልጊዜም ወደ ጌታሽ ተመለሺ። በቀን ጥቂት ገጾችንም ቢሆን ከቁርአን ጋር የመኖር ልምድ ይኑርሽ።
መልካም ጓደኞችን ምረጪ ወደ አላህ የምታቀርብሽን✉️ ዲንሽን እንድታውቂ የምታበረታታሽንና በክፉ ቀን ከአጠገብሽ የማትጠፋውን እውነተኛ እህት በጥብቅ ያዢ
ጊዜሽን በአግባቡ ተጠቀሚበት በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ (ሶሻል ሚዲያ) ላይ የምታሳልፊው ጊዜ ለአንቺ ምስክር የሚሆን እንጂ በአንቺ ላይ የሚመሰክር እንዳይሆን ተጠንቀቂ። የሚጠቅምሽንና ለአኺራሽ የሚበጀውን ብቻ ተከታተዪ አጋሪም።
💎 አንቺ የኡማው መሰረት ነሽ! አንቺ መልካም ስትሆኚ ትውልድ ይስተካከላል። አላህ በፅናት ላይ ያቆይሽ🦋 በዱንያም በአኺራም ስኬታማ ያድርግሽ🎀🎀
Repost from ስለ ቀልባችን
🎉አልሐምዱ ሊላህ!
በቅርብ ጊዜ የጀመርነው የ«ስለ ቀልባችን» የቲክቶክ ገፃችን በአጭር ጊዜ ውስጥ 10,000 ተከታዮችን አፍርቷል። ከልብ ለምትወዱን፣ ለምትከታተሉንና ለምታበረታቱን ሁሉ ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን!
⭐️በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮቻችንም አብራችሁን እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን፤ ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ፡👍🫴👇
📹 ዩቱብ (YouTube):
t.ly/sle_qelbachn_yt
🆔 ኢንስታግራም (Instagram):
t.ly/sle_qelbachn_ig
🌐 ቲክቶክ (TikTok):
t.ly/sle_qelbachn_tt
📖ፌስቡክ (Facebook):
t.ly/sle_qelbachn_fb
✅
ስለ ቀልባችን🩵 ኑኑኑ ደርሱ እንደቀጠለ ነው🎙🎙
⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇
https://t.me/Multeka_Selefiyin?videochat=590bda823f316bcd6c
🟠 አሁን ቀጥታ ስርጭት ቂራአት
~~
📖 የቁርአን ተፍሲ ሱረቱል አእራፍ (
🎙 በኡስታዝ አቡ ሐኒፋ ሑሰይን ኢድሪስ ሰዒድ ሐፊዘሁሏህ
ተ
ጀ
መ
ረ
👉 ሸር አድርጉት. ተቀላቀሉ አድም አድርጉ
ግቡ ተከታተሉ 📢
https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris?videochat=59dc0e0734fd48907f
ኢብኑ ሙነወር ወረባቦ ነውደ የሚል ጪቅጪቅ ተነስቷል ክክክ አወን ነው
ድብን ያለ የወረባቦ ሰው ያውም ከአረባቲ በታች የጭፍቱ ሰው ነው 👌👌 የ015 ✅✅👏👏 ነው ጥማቹሁን አውጡ ክክክክ
ሆ ዞሮ ትምርቱ ለሁላችንም ተደራሽ ነው በቃ አትጫጩ
-------ውቧ ወረባቦ ቦከክሳና ጪፍቱ-------
የወረባቦ ምድር ተውሂድ የሞላባት
በሱናዋ ማዕረግ ፀሐይ የወጣባት
ያቺ ውቧ አገር ጀግና ያፈራችበት
ሀቅ የተንቀሳቀሰላት ውበት የሞላባት
ክፉ አታይም እዛስ አንበሳ ያለባት።
ወደ ቦከክሳ ሰማይ ከፍ ብለን ስናይ
ከጫሊ በላይ ነው ከነደመናው በታይ
እሸቱ የበቀለበት የሱናው ፋና ወጊ
አቡ ሻኪራ ጀግናው ተውሂድን አስፋፊ
አቡ ሱፍያንም አለ የዲን መጠጊያ
በቦከክሳ ምድር የሀቅ መኖሪያ።
እነዚህ ሁለት ጀግኖች የሱና መብራቶች
የወረባቦ መብራት የተውሂድ አርበኞች
ቢድዓን ሊያጠፉ የታጠቁ ጀግኖች።
-------የተውሂድ ሰንደቆች-------
የወረባቦ ፍሬዎች የሱናው መብራቶች
የተውሂድ ባንዲራን ያነገሱ ጀግኖች
በሀቅ ጎዳና ላይ የቆሙ አርበኞች
እናንተን ማወደስ ያኮራል ልቦችን
በሩቅ ለምንሰማ ለኛ ለስደተኞች።
አቡ ሻኪራ ጀግናው የቁርጥ ቀን መብራት
በቦከክሳ ምድር የበቀለው ኩራት
ተውሂድን ሲያስተምር ይታያል ፅናቱ
ለሰለፍያ መንገድ የለፋው በዕውነቱ
አላህ ይጠብቀው ይባረክ ህይወቱ።
አቡ ሱፍያንም አለ ሌላኛው አንበሳ
በሱናው ጎዳና ታሪኩ የማይረሳ
የቢድዓን ጨለማ በትግሉ የገፈፈ
ከእነ አቡ ሻኪራ ጋር ሀቅን ያሰረፈ
ለዲኑ መቆሙ ዓለም ያወቀው ነው
በወረባቦ ምድር ስሙ የገነነው።
ምቀኛ ቢቆጣ ሀቅ ግን አይሸሸግ
የእናንተ ስም ሁሌም በሱና ሲያደግ
ድምፃችሁን ሰምተን በስልካችን ስክሪን
ከስደት ሀገር ሆነን ይደሰታል ልባችን
ዕውቀትን እንጋታለን በየቤታችን።
-------ታድላለች ወረባቦ-------
ወረባቦ አገሬ ታድላለች በጣም
በማር በወተቱ በተፈጥሮው ጣዕም
ለምለም ነው አገሯ የለውም አምሳያ
አረንጓዴ ለብሳ ለዓይን ማረፊያ።
ግን ከማር ወተቱ ይበልጣል ውበቷ
በውስጧ በቀሉ የዲችን መብራቷ
በሸይኾቿ ስምና በኡስታዞቿ ጥራት
ዛሬማ በተለይ ለብሳለች ኩራት
ታሪክ ይዘክረው ይውጣና ዛሬ ወሬው
የቦከክሳን ልጆች ዓለም ይወቅልኝ አገሩ የት እንደው!
ከጫሊ በላይ ነው ማደሪያው መንደሩ
ቦከክሳ ነው ይኸው የጀግኖች አገሩ።
የወረባቦ ፍሬው እሸቱ አስገራሚ ነው
አቡ ሻኪራና አቡ ሱፍያንን አቅፎየያዘነው
በሰለፍያ መንገድ ተውሂድን የዘሩት
ለዲናቸው ክብር ሌት ተቀን የለፉት።
ምቀኛም ይቃጠል ወዳጅም ይደስት
ዛሬ እጅግ ደስታ አለ ከወረባቦ ደሴት
=ኢ==ብ===ኑ===ሙ==ነ==ወ==ር==✍
ወረባቦ ብለህ ግጠምለት አቦ
ስለዚህ ገጣሚው ስንኝህን አስተካክል
ከአረባቲ በታች ጪፍቱ ብለህ ተክል!
ካረባቲ በታች ቁልቁል ስንወርድበት
ጪፍቱ ትታያለች ዕውቀት የናኘበት
የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ያ የተወለደበት
የሱናው ጉብል ነው ዓለም ያወቀበት
በሀቅ ንግግሩ የጪፍቱው መብራት
ወረባቦን በሙሉ ያደመቃት ኩራት።
አቤት መጣፈጡ የነሱ ምክርና ትምህርት
የሱናው ጉብል ነው በዕውቀቱ የረቀቀ
በሀቅ ንግግሩ ሰለፍያን ያደመቀ
ካረባቲ በታች ስሙ ይናፈሳል
በጪፍቱ የበቀለው ፍሬ ለዲን ይደርሳል።
አቤት መጣፈጡ የእናንተ ምክሮች
ልብን የሚነኩ የሀቅ ምስክሮች
አላህ ያርዝመው ዕድሜና ጤናችሁን ባላችሁበት ቦታ ይጠብቅ ህይወታችሁን
✉️✉️✉️✉️
ጥበብ ባይኖረኝም ቃላት ለመደርደር
የልቤን አድናቆት ፈለግኩት መናገር
ለሦስቱ ኡስታዞች ይድረስልኝ በክብር
📝📝
✍ام عفيفة بنت محمد🍃
አድስ ሙሐደራ ደሴ አረብ ገንዳ መስጅድ
💉ስለ ሽርክና ተያያዥ ርዕሶች ምረጥ ምክር
🎙በኡስታዝ አቡ ሒዛም (ሀፊዘሁሏህ)
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
ዛሬ ከአሱር ቡሀላ ደሴ ሸዋበር መስጅድ ኡስታዝ አቡ ሒዛም ደዕዋ ያደርጋል ደሴዎች ተዘጋጅታችሁ ጠብቁን
በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው ኡስታዝ አቡ ሒዛም ገብቷል
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy?livestream=1b4b207b81c6744f49
አቦ ዳእዋውን የሙነወር ልጅ ያድርገው አይ ጥበብ የባቦው ንጉስ አሏህ ይጠብቅህ📢
✍الأستاذ ابن منوّر على منهج السلفية الصافية، وكلامه في نصح الناس وتوجيههم كالعسل في حلاوته وطيب أثره. نسأل الله أن يحفظه ويثبته على الحق، وأن ينفع به العباد والبلاد.👏✅