fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

ምክር ለወጣቶች

ምክር ለወጣቶች

رفتن به کانال در Telegram

"አላማችን ወጣቱ ያለበትን የዲን ክፍተት እንዲስተካከል ማድረግ ነው"

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
7 405
مشترکین
+4524 ساعت
+1107 روز
+77230 روز
آرشیو پست ها
የሙስሊም ሴት ዋና መኖሪያዋ የት ነው❓ 🎙ኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን🎙 🌹እህቶች ስሙት ባረከሏህ ፊኩም Comment @Mujahid_Selefi https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab

ያሰላም ድምፅ 🌸እያስተነተናቹ ስሙት በዛው ለአሏህ ብላቹ ለምትወዱት ሳሂባቹ ላኩለት🙌 Comment @Mujahid_Selefi https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/Abu_Umer1

ለተከታዮቹ አድርሱለት👆👆

ሙስጠፋ አብደላ ሙብተዲዕ ነው ተጠንቀቁት 🍃በሼይኽ አብዱል ሃሚድ ቢን ያሲን አለተሚ (ሀፊዘሁላህ) https://t.me/katebabimide https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab

✅اسلام عليكم وراحمة الله و بركاته✅ ቁርአን ከቃኢዳ ጀምሮ መቅራት  ምፈልጉ ብቻ  በዚህ አናግሩኝ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @Mujahid_Selefi  የምንቀበለው ተማሪ ብዛት ቃኢዳ 5  ነዘር 5 ሂፍዝ 5  ተማሪ ብቻ ነው

በዚህ ጊዜ ህይወት ጣፋጭ ነበር እነ Samsumg I PHONE መጥተው በጠበጡንጂ https://t.me/Abu_Umer1
በዚህ ጊዜ ህይወት ጣፋጭ ነበር እነ Samsumg I PHONE መጥተው በጠበጡንጂ https://t.me/Abu_Umer1

ህይወቴ ያለ አንቺ ባዶ ነው❌ ህይወቴ ያለ አላህ ባዶ ነው✅ https://t.me/NasihaLishebab

ባረከሏህ ፊኩም በትእግስት አንብቡ👆👆🤙🤙

የሙመይዐህ ዋሻ የሆነውን የሙነወርን ልጅ ማጋለጥ፣ ሴራውንና ማምታቻውን ግልፅ ማድረግ!! ————— ክፍል 1⃣ ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:- “በእርግጥም የሙነወር ልጅ የሆነን ንግግር አንብቤያለሁ፣ ከንግግሩም ውስጥ "…እዚህጋ በቢድዓ ላይ የወደቀን ሁሉ በሙብተዲዕነት የሚፈርጅም አለ…" የሚል አለበት፣ ለእርሱም "ማን ነው በቢድዐህ ላይ የወደቀን ሁሉ በሙብተዲዕነት የሚፈርጀው?!" ይባላል፣ ሙብተዲዕ የተባሉትን አትጠቅሳቸውም ነበር? ግልፅ በሆነ ማስረጃ አትከላከልላቸውም ነበር? ሙብተዲዕ ያስባለቻቸው የሆነችውን የወደቁባትን የቢድዐህ አይነትስ ምን አይነት ናት ለምን አትጠቅሳትም? ለምንድነው ይህ ሁሉ ውሸት፣ማምታታትና ነገር አክብዶ የተለየ ክስተት በማስመሰል ማስፈራራት? እርግጥ ነው ሸይኽ ሐሰን ገላውና ሸይኽ ዐብዱልሀሚድ የተምይዕ ተጣሪ የሆኑ ጥቂት ሰዎችን ግልፅ በሆነ ማስረጃ ላይ ሆነው ሙብተዲዕ በመሆናቸው ብይን ሰጥተዋል፣ አንተ ግን (እነዚህን መሻይኾች) ከሀዳዲይነት ትቆጥራቸዋለህ፣ ታላግጥባቸዋለህ፣ ያለ አግባብ ትተቻቸዋለህ። በእርግጥ በሐበሻ ምድር በጀርህና ተዕዲል ላይ የሚቆም የለም ብለህ ሞግተህም ነበር፣ ከዚያም በኋላ ያለ እውቀት፣ በሱንና ዑለማእ ዘንድ ተቀምጠህ የተማርከው ነገር ሳይኖር፣ የተማርከበት ሞያህ አካዳሚና ታሪክ ሆኖ እያለ ሠለፊዮችን ጀርህ ስታደርግ ተመለከትነህ። በጀርህና ተዕዲል እውቀት ላይ አንዳች ድርሻ የሌለህ ስትሆን በዘርፉ ላይ ምንኛ የተዳፈርክና ድምበር ያለፍክ ብትሆን ነው ከሰለፊዮች ሆነው መልካም የሆኑ ሰዎችን የምትወርፈውና የምትተቸው?! በእርግጥ አላህ የተምይዕ ተጣሪዎችን እውነተኛ ማንነት አጋልጧል፣ የሁለት መመልከቻ ዓይኖች ባለቤት ለሆኑ ሁሉ ጉዳያቸው ግልፅ እንዲሆን አድርጓል፣ ሚዛናዊ ለሆነና ሰለፎች ለነበሩበት ነገር ጥልቅ እውቀት ላለው የአዕምሮ ባለቤት ለሆነ ሁሉ አደገኝነታቸው ግልፅ ሆኗል። በእርግጥ አንተም ከመገልበጥህና በስሜትህ ከመስመጥህ በፊት ይህን ታውቅ ነበር። ከከባባዱ የንግግር መጣረስና የመጋጨት ምክንያቶች እውቀትን ያለ አስተማሪ ከጋዜጣዎችና ከመፅሃፎች መያዝ፣ እንዲሁም ለመበቀልና ነፍሲያን ለመርዳት የበላይ ለማድረግ መነሳሳት (መታገል) ነው። ከተምይዕ ዋሻው አላዋቂነት የሚከተለውን የኢብኑ ተይሚያን ንግግር ማጣቀሱ ነው:- "ከቀደምትና ከኋለኛው ዘመን ሙጅተሂዶች ውስጥ ብዙዎቹ ቢድዐህ የሆነን ነገር ተናግረዋል ወይም ፈፅመዋል፣ ይሁን እንጂ ቢድዐ መሆኑን አላወቁም። ይህ የሆነው ወይ ትክክለኛ በመሰሏቸው ደካማ ሀዲሶች ምክንያት ነው፣ ወይም ደግሞ ከቁርኣን አንቀፆች ውስጥ ያልተፈለገበትን የተሳሳተ ፍቺ በመረዳታቸው ነው፣ ወይ ደግሞ ያልደረሷቸው ግልፅ ማስረጃዎች እያሉ በራሳቸው እይታ በመጓዛቸው ነው።" እኔም አልኩኝ:- የሀለቢይ ሙመይዓዎችና ኢልያስ አህመድ በ30 ማታለያዎቹ ላይ፣ ኸድር ከሚሴ፣ የተምይዑ ዋሻ ለቢድዐህና ለስሜት ባለቤቶች ሊከላከሉበት ይህን የኢብኑ ተይሚያን ንግግር በማጣቀስ ተከታትለዋል። ምንኛ የተራራቀ ሆነ! የኢብኑ ተይሚያ ንግግር የሙመይዐህ ሸይኾች ከሚፈልጉበት አውድ ከማመላከት ምንኛ ሩቅ ነው!። ሸይኹል ኢስላም የሚናገሩት ያለ እውቀት በቢድዐህ ላይ ስለ ቀደቀ ሰው ነው፣ "ቢድዐህ መሆኑን ባለማወቅ…" ብሎ ተናግሯል፣ ከዚያም በቢድዐህ ለመውደቃቸው ምክንያት ሊሆናቸው የሚችልን ነገር ጠቅሷል፣ "…ይህ የሆነው፣ ወይ ትክክለኛ በመሰሏቸው ደካማ ሀዲሶች ምክንያት ነው፣ ወይም ደግሞ ከቁርኣን አንቀፆች ውስጥ ያልተፈለገበትን የተሳሳተ ፍቺ በመረዳታቸው ነው፣ ወይ ደግሞ ያልደረሷቸው ግልፅ ማስረጃዎች እያሉ በራሳቸው እይታ በመጓዛቸው ነው።"ብሏል: ነገር ግን አላህ ሙመይዓዎችን በመጥፎ ግንዛቤና እሳቤ ቀጥቷቸዋል፣ ይህ ቀድሞ ለሱናን ሲከላከል ኖሮ መልሶ ሱናን ችላ ላለ ሰው የገጠመ ምንዳ ነው። ነገሮች ይገለባበጡበታል፣ የአዕምሮ ባለቤቶች እስከሚስቁበት ድረስ በነገሮች ላይ ይንቦጫረቃል። ከዚያም ለዚህ የተምይዕ ዋሻ "ማን ነው በሐበሻ ምድር ያለ እውቀት በቢድዐህ ላይ የወደቀው?፣ ይባላል፣ ኢኽዋኑል ሙፍሊሲንና የነርሱ ጭራ የሆኑትን የመሰብሰብ ተጣሪዎችን ነው ምትፈልግበት?፣ ታዲያ ከእውነተኛ ከሆንክ ለምን በእነሱ ላይ ማስረጃ ልታቆምባቸው አትሯሯጥም? ወይስ ከነገሩ ጀርባ ያለ ነገረ አለ ነው? (እያስመሰልክ ግልፅ ማድረግ ያልፈለግከው ድብቅ አጀንዳ)። በተምይዕና በተጅሚዕ ባለቤቶች ሰፍ ቆመህ እነርሱ እንዲወዱህ ሠለፊዮችን ለማስቆጨት ብለህ የማትጨበጥን ብዥታ ስትሰበስብላቸው አላህን አታፍረውም?! በውስጡ የምትደበቁበት ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ እንዲህ ነበር?! ስለ ሂዝቢዮች በተለይ ስለ ተምይዕና ተጅሚዕ ባለቤቶች በጥልቀት እውቀት ያለው ሸይኽ ረቢዕ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አለ:- "ሐቅን በማጥራት የሚታወቅ ከሱንና ሰው የነበረ ሆኖ ድብቅ በሆነች ቢድዐህ ከወደቀና ከሞተ ይህን በሙብተዲዕነት መፈረጅ አይፈቀድም፣ ይልቁንም በመልካም ይወሳል፣ በህይወት ካለ ግን ይመከራል ሐቁ ግልፅ ይደረግለታል፣ ሙብተዲዕ በመባል አይቸኮልበትም፣ በዚያው ካዘውተረና በግልፅ ከቀጠለ ግን ሙብተዲዕ ተብሎ ብይን ይሰጥበታል።" ከዚያም ሸይኽ ረቢዕ የሸይኹ'ል ኢስላምን ከላይ የተቀመጠውን "ከቀደምትና ከኋለኛው ዘመን ሙጅተሂዶች ውስጥ…" የሚለውን ንግግር ጠቀሰ። አሁን የሸይኹል ኢስላምን ንግግር ከሸይኽ ረቢዕና ከሙመይዐህ ሸይኾች ግንዛቤ ጋር አነፃፅር፣ የእውቀታቸውን ደካማነትና በሰለፎች መንገድ ላይ ያላቸውን የተደራረበ መሀይምነት ታውቃለህ። ከዚያም የተምይዑ ዋሻ በድጋሚ የኢብኑ ተይሚያን ንግግር ጠቅሷል፣ "የነዚህ አምሳያ የሆነው የፈጠሩትን ነገር በሱ ሳቢያ የሚወዳጁበትና የሚጠሉበት፣ ከሙስሊሞች ጀመዐህ የሚገነጠሉበት ንግግር ካላደረጉት እንደ ስህተት ነው የሚቆጠረው፣ የጠራውና የላቀው አላህ በዚህ አመሳያ ላይ ያሉ ስህተቶችን ለአማኞች ይምራል። ለዚህም ነው ከመልካም ቀደምቶችና ሊቃውንት ውስጥ ብዙዎች ይህን በሚመስሉ ጥፋቶች ላይ የወደቁት፣ በኢጅቲሃድ የተናገሯቸው ከቁርኣንና ከሱንና ጋር የሚፃረሩ ንግግሮች አሏቸው።" እኔም አልኩኝ:- በድጋሚ ይህንም የሸይኹ'ል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያን ንግግር በማንሳት የተምይዕ ሸይኾች ሀለቢይ፣ ኢልያስ አህመድና ኸድር ከሚሴ ተከታትለውበታል፣ ግባቸው ደግሞ ከቢድዐህና ከጥመት ባለቤቶች መከላከል ነው። ምክንያቱም ኢብኑ ተይሚየህ እዚህጋ የሆነን ቢድዐህ ቃል አምጥቶ በዚያች የቢድዐህ ቃል ምክንያት ከሰዎች ወዳጅነትና ጠላትነትን ያልመሰረተ ሰው ተግባሩ ከስህተት አይነቶች እንደሚያዝ አረጋግጧል። ያለ እውቀት በቢድዐህ ላይ በወደቀ ሰው ያለው ንግግሩ ግልፅ ነው። ይቀጥላል… ✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) #Join ↘️↘️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/Abu_Umer1

photo content

"ሩኩዕንና ሱጁድን አርዝም፤ ወንጀሎችህ እንዲረግፉ።" قال رسول الله ﷺ: "إن العبد إذا قام إلى الصلاة أُتي بذنوبه كلها فوضعت على عاتقيه، فكلما ركع
"ሩኩዕንና ሱጁድን አርዝም፤ ወንጀሎችህ እንዲረግፉ።" قال رسول الله ﷺ: "إن العبد إذا قام إلى الصلاة أُتي بذنوبه كلها فوضعت على عاتقيه، فكلما ركع أو سجد تساقطت عنه." የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ "ባሪያው ወደ ሶላት ሲቆም፣ ወንጀሎቹ ሁሉ መጥተው በትከሻዎቹ ላይ ይቀመጣሉ፤ ሩኩዕ ወይም ሱጁድ በሚያደርግ ቁጥር ከእርሱ ላይ ይረግፋሉ።" 🌷 📚 "ሶሒሕ አልባኒ"

"አንዱ ምን አለ መሰላቹህ....? ዱንያ ሁሉን ነገር ልትሰጥህ ትችላለች፤ ግን የልብ ሰላምን አትሰጥህም። የልብ ሰላም ያለው አላህን በማስታወስ ብቻ ነው።" 🌹 https://t.me/Abu_Umer1

👇በቅርቡ ከሱና የተንሸራተተው ሸይክ #አብዱልከሪም አህመድ ሱናን በመገዝገዝ ከሚታወቀው #ጀይላን ከድር ጋ በዘንድሮው (1447 ኛው) ሂ የሀጅ ስነስርዓት ወቅት። ✍️ያአላህ ልብን ገለባበጭ የሆንከው
👇በቅርቡ ከሱና የተንሸራተተው ሸይክ #አብዱልከሪም አህመድ ሱናን በመገዝገዝ ከሚታወቀው #ጀይላን ከድር ጋ በዘንድሮው (1447 ኛው) ሂ የሀጅ ስነስርዓት ወቅት። ✍️ያአላህ ልብን ገለባበጭ የሆንከው፣ልባችንን በሱና/በሰለፊያ ላይ አፅናልን። https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/Abu_Umer1

🚫 የሂጅሪያ አዲስ አመት ማክበር ክልክል ነው ‼ ነብዩ ከመካ ወደ መዲና የተሰደዱበትን ጊዜ በማሰብ የሂጅሪያ አዲስ አመትን ማክበር ወንጀል ነው ። ይህ ተግባር አላህ አላዘዘበትም ። ነብዩም አልሰሩ
🚫 የሂጅሪያ አዲስ አመት ማክበር ክልክል ነው ‼      ነብዩ ከመካ ወደ መዲና የተሰደዱበትን ጊዜ በማሰብ የሂጅሪያ አዲስ አመትን ማክበር ወንጀል ነው ። ይህ ተግባር አላህ አላዘዘበትም ። ነብዩም አልሰሩትም ስሩትም አላሉም ። ሶሓቦችም አላከበሩትም ። ታቢዒኖችም በከንቱ አልዘነጉትም ከዛ በኋላ የመጡ የኢስላም ሊቃውንቶችም ዲን ነው ብለው አልያዙትም ።    በመሆኑም በእነርሱ ዘመን ዲን ያልነበረ ዛሬ ዲን መሆን አይችልም ። የሂጅሪያን አዲስ አመት የሚያከብር ሰው በነሷራዎች ወይም በፋጢሚ ራፊዲዮች የሚመሳሰል ነው ። ስለዚህ ከዚህ ተግባር በመውጣት የራስንና የዲንን ክብር መጠበቅ ግድ ይላል ።     አላህ ወደ ቅኑ መንገድ ይምራን ! ። http://t.me/bahruteka https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab

እንደ ሀራም Relation ሴት ልጅን የሚሰብር ነገር የለም ተው ይቅርባቹ እህቶች ቀጥታ ወደ ሀላል ካልተገባ ገና ለገና ነገ ያገባኛል በሚል ባዶ ተስፋ የወንድ መጫወቻ ሆናቹ እንዳትቀሩ https://
እንደ ሀራም Relation ሴት ልጅን የሚሰብር ነገር የለም ተው ይቅርባቹ እህቶች ቀጥታ ወደ ሀላል ካልተገባ ገና ለገና ነገ ያገባኛል በሚል ባዶ ተስፋ የወንድ መጫወቻ ሆናቹ እንዳትቀሩ https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab

አላህ ﷻ በሐዲስ ቁድሲ ላይ እንዲህ ይላል፦ «يَا ابْنَ آدَمَ، إِنَّكَ مَا دَعَوْتَنِي وَرَجَوْتَنِي غَفَرْتُ لَكَ عَلَى مَا كَانَ مِنْكَ وَلَ
አላህ ﷻ በሐዲስ ቁድሲ ላይ እንዲህ ይላል፦ «يَا ابْنَ آدَمَ، إِنَّكَ مَا دَعَوْتَنِي وَرَجَوْتَنِي غَفَرْتُ لَكَ عَلَى مَا كَانَ مِنْكَ وَلَا أُبَالِي» "የአደም ልጅ ሆይ! እኔን እስከጠራኸኝ እና እስከተስፋ አደረግህብኝ ድረስ፣ ያለፈውን ሁሉ ወንጀልህን እምርልሃለሁ፤ ምንም ግድ አይሰጠኝም።" ከዚያ ደግሞ እንዲህ ብሎ አረጋገጠው፦ «يَا ابْنَ آدَمَ، لَوْ بَلَغَتْ ذُنُوبُكَ عَنَانَ السَّمَاءِ، ثُمَّ اسْتَغْفَرْتَنِي غَفَرْتُ لَكَ وَلَا أُبَالِي» "የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀሎችህ የሰማይን ጣራ ቢደርሱም፣ ከዚያም ምህረትን ብትለምነኝ፣ እምርልሃለሁ፤ ምንም ግድ አይሰጠኝም።" ከዚያም ደግሞ እንዲህ ይላል፦ «يَا ابْنَ آدَمَ، إِنَّكَ لَوْ أَتَيْتَنِي بِقُرَابِ الْأَرْضِ خَطَايَا، ثُمَّ لَقِيتَنِي لَا تُشْرِكُ بِي شَيْئًا، لَأَتَيْتُكَ بِقُرَابِهَا مَغْفِرَةً» "የአደም ልጅ ሆይ! ምድርን ያህል ወንጀል ይዘህ ብትመጣ፣ ከዚያም ከእኔ ጋር ምንም ሳታጋራ (በተውሒድ ላይ ሆነህ) ብትገናኘኝ፣ እኔም ምድርን ያህል ምህረት ይዤ ወደ አንተ እመጣለሁ።" መስፈርቱ ግን «لَا تُشْرِكُ بِي شَيْئًا» ማለትም በአላህ ምንም ነገር አለማጋራት ነው። ﴿ذَٰلِكَ فَضْلُ اللَّهِ يُؤْتِيهِ مَن يَشَاءُ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ﴾ "ይህ የአላህ ችሮታ ነው፤ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል። አላህም ታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው።" ሀቂቃ እሄ ሀዲስ ትልቅ ተስፋ ከሚሰጠን ሀዲስ አንዱ ነው አሁን ጊዜ አለን እና ለ ተውበት እንቸኩል አላህ አዛኝ ጌታ ነው

|| ሰበር ኸበር በዛሬው እለት የሙሐረም ጨረቃ መታየቱዋን ተከትሎ ነገ (ማክሰኞ) የሙሐረምና የ1448ኛ አመተ ሒጅራ የመጀመራያው ቀን ይሆናል። እንዲሁም የፊታችን ረቡዕ እና ሐሙስ ሳምንት ታሱዓዕና ዓሹራዕ ይሆናል። t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab

💐ኡኽታህ💐መሞትሽ ክፍተት መፍጠር መቻል አለበት። "መሞትሽ በሰዎች መሃል ምንም ዓይነት ክፍተት የማይፈጥር ከሆነ; መኖርሽ በሰዎች መሃል ምንም ዓይነት ጥቅም አልነበረውም ማለት ነው።     ይህ እንዳይሆን ከፈለክሽ   እስልምና ላይ ሸክም ሆነሽ ሳይሆን መኖር ያለብሽ; እስልምናን በምትችይው ያህል መሸከም አለብሽ። •━════✿🍃🌺🍃✿════━• 👇👇👇👇👇 https://t.me/AbuMerwanAselefy https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab

🔷 አለማዊ ጉዳዮች ሳያዘናጉን ቁርአንን እንሐፍዝ ፣ በዲናችን ላይ እንጽና ዶ/ር አብዱረዛቅ አል-በድር - ሀፊዞሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :-   "በዚህ ትኩረት በሚያሳጡ ፣ አዘናጊ ነገሮችና ታላላቅ ፈተናዎች በሞሉበት ወቅት ቁርአንን እንድትሸመድድና መላልሰህ እንድትመለከት አሏህ ካከበረህ ፣ ይህ በእርሱ አሏህ ከበርካታ ሰዎች መካከል የለየበት ነው .. በመሆኑም በዚህ አንተን ለይቶ ስለመረጠህ  አመስግነው ፤ በአቋምህ ላይ ጽና ፤ እውነተኛነትህን አሏህ ሊመለከት ዘንድ ለወደፊት እንደምትፈተንም እወቅ ..."  https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة  https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab

🇪🇹የኢትዮጵያ ሰለፊዮችን ትክክለኛ ቻናል በቀላሉ ለማግኘት👉OPEN👈 ምትለዋን ብቻ ይጫኑ