قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
رفتن به کانال در Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
914
مشترکین
-324 ساعت
-177 روز
+5330 روز
آرشیو پست ها
Repost from قَناةُ وفَوا ئِد أبي فَوزان الْحَبَشِيِّ
........"ታሳዝነኛለች".......
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
በኑሮ ስንክ ሳር በህይወት አዙሪት፡
በንጋት በምሽት ምድረ-ሽክርክሪት፡
በይሆናል ተስፋ ስትነድ እንደ ክብሪት፡
መልካም ጥሩ አሳቧ ሲወልድባት እብሪት፡
ፅኑና ብርቱዋ ዝንጉ ትሆናለች፡
ይህች አይነት እህቴ ታሳዝነኛለች፡
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
ትዳርን ስታስብ ኑሮን ለመጋራት፡
ከቢጤዋ ጋራ አብራ ለመዳራት፡
ሀሳብ ስትመገብ ህይወትን ለመምራት፡
ጧት ቁርስ ሳትበላ ማታ ሳትቀምስ እራት፡
የምታማክረው የምታወያየው ሰው እየቸገራት፡
ወስና እንዳትገባ አቋሙ እያስፈራት፡
ለሷ እንደማይሆናት ውስጧ እየነገራት፡
አለች እስከ ዛሬ በውዝግብ ስሜት፡
በለቅሶና በሳቅ በስላቅ በሀሜት፡
ውዝግብግብ ብላ ዛሬም ድረስ አለች፡
ምንም ባላግዛት ታሳዝነኛለች፡
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
ወስና እንዳቶወው ፍቅር ይይዛታል፡
በወደደች ቁጥር ደስታ ይሰማታል፡
ስትጠጋው ደግም በጣም ይጎዳታል፡
ፕላንና እቅዱ ያደናግራታል፡
ብቸኛ እንዳትሆን ልጅ መውለድ ያምራታል፡
ደግሞ ባንድ በኩል እድሜዋን ስታስብ፡
እየቆጠረ ነው ሞትን ለሷ ሊስብ፡
በቁጭት በንዴት ትላለች እንግብግብ፡
የህይወቷ ጣዕም ሲጠፋት የርሷ ግብ፡
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
ልቧ እየዋለለ በመሄድ በመቅረት፡
ሀዘን ያሳብቃል የልቧ ላይ ንዝረት፡
ትርጉሙ ጠፍቶባት የመንጋት የመምሸት፡
ሰላም ነኝ እያለች አለች በውሻሸት፡
ከደስታ ተኳርፋ ህይወት ትገፋለች፡
ይቺ አይነቷ እህቴ ታሳዝነኛለች፡
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
.......በኑረዲን_አልአረቢ....2015
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
ታዋቂ የነበሩ የጃሒልያ ዘመን ገጣሚያን
❶ ➛♦️ኢምሩዑል-ቀይስ
❷➛ጦርፈቱ ኢብኑ አብድ
❸➛ዘህረቱ ኢብኑ አቢ ሱለሚ
❹➛ለቢድ ኢብኑ ረቢዓህ(ሙኸድረም)
❺➛♦️አንተራ ኢብኑ ሸዳድ
❻➛ዓምር ኢብኑል ኩልሱም
❼➛ሐሪስ ሒ'ሊዘህ
❽➛ናቢዘቱ ዙብያንይ
❾➛አዕሸል አክበር
❿➛አብድ ኢብኑል አብረስ
⓫➛ሙሐልሐል ኢብኑ ረቢዓህ
⓬➛አውስ ኢብኑ ሐጀር
⓭➛አልቀመቱል ፈህል
⓮➛አዲይ ኢብኑ ዘይድ አል-ዒባድ
⓯➛አ'ሸንፈሪይ
⓰ ➛ተአ'በ'ጦ ሸ'ራ
⓱➛ዑርወት ኢብኑ ወርድ
⓲➛ሰመውአት ኢብኑ ዓዲያዕ
⓳➛ሐሪስ ኢብኑ ዑባድ
⓴➛♦️ሐቲም አጧዒይ
ከሞላ ጎደል ታዋቂወቹ የጃሒልያ ዘመን ገጣሚዎች እነዚህን ይመስላሉ...ግጥሞቻቸው በታሪክ ተሰንደው በአረቡ አለም ብሎም በአለም ላይ ተፅኖ ፈጣሪ ናቸው አንዳንዶቹ በቋንቋ መፀሀፎች ላይ የሰፈሩ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ በሸሪዓ ኪታቦች ላይም እንደ ምሳሌ ይቀርባሉ።
በተለይ ሶስቱ
❶♦️አንተራ ኢብኑ ሸዳድ
❷♦️ሐቲም አጧዒና
❸♦️ኢምሩዑል ቀይስ በሙስሊሙ ዘንድም እጂግ ታዋቂዎች ናቸው።
✅......በቀጣይ የሙስሊም ኢምፓየር ገጣሚወችን እንጠቅሳለን ኢንሻ አሏህ።
...በኑረዲን አል-አረብ
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from አቡ ዓብደሏህ(أبو عبد الله الولوي)🇸🇦
🔥 የዒልም ሲልሲላ | አዲስ ደርስ 📚
🌟 ኡስታዝ ሙሐመድ አሕመድ حفظه الله
ከየመን መርከዝ የመጡ፣ በዒልም አቅማቸውና በሱና ላይ ባላቸው ሂማ የሚገለጹ ኡስታዝ። 💎
📖 القواعد الأربع | ቀዋዒዱል አርበዓ
ከእንዲህ ያለ ኡስታዝ ጋር መማር፣ የአቂዳን መሠረቶች በጥልቀት ለመረዳትና የተማርነውን በትክክል ለመተግበር ውድ እድል ነው። 🌱📚
🚨 ነገ ጧት ይጀምራል! ⏰
🔥 የዒልም ፍላጎት ካለህ — እድሉን አታሳልፍ!
📌 መስፈርቶች:
❤️ የዒልም ፍላጎት
⏰ በሰዓቱ መገኘት
📝 ፈተና መፈተን
📍 መስጅደል አዝሀር | ወሎ ዩኒቨርሲቲ
📚 የዒልም ጉዞ… በሲልሲላ
ይቀጥላል! 🌿
📢❤️ ይህንን የዒልም መልእክት ለሌሎች የእውቀት ፈላጊዎችም SHARE አድርጉ!
🤲 አላህ ከእውቀት የሚጠቅመን ያድርገን።
بارك الله فيكم ونفع بكم 🌿
📲🔥 የTelegram ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
👉 https://t.me/abuabdelah123 👈
📢 JOIN • SHARE • ለሌሎችም አስተላልፉ! 🌿
ድካምህ ምንም ያህል ቢበዛና ቢበረታብህም፤ በዚች በዱንያ እረፍትን መፈለግ የማይቻል ነገር መሆኑን አስታውስ። የዚህም ማስረጃ የፍጥረታት ሁሉ ሁኔታ በመሆኑ ተጨማሪ ንግግር አያስፈልገውም። በሕይወት ታሪክ ውስጥ፣ አእምሮ ከሌለው «እብድ» ሰው በቀር አንድም እረፍት ያገኘ ሰውን ማግኘት ከባድ ነው። ስለዚህ ችግሩና መከራው ምንም ያህል ቢጠናብህ ታገስ፣ ተጋደል፤ የስሜትህና የምኞትህ ባሪያ እንዳትሆን! በትዕግስት የሚገኝ ሕይወት ፍሬው ያማረ፣ ስሩም የጸና የበረታነውና።
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
~ ወሰን አትለፍ!
ሸይኽ ረስላን -ሐፊዘሁላህ- እንዲህ ይላሉ፦
"የዘመኑ ሰዎች ስነ-ምግባር ብልሹነት ተፅዕኖ ፈጥሮብህ እንደነሱ ከመበላሸት አስጠነቅቅሃለሁ። የነሱ ስነ-ምግባር ፈር ቢለቅም አንተ በራስህ ትክክለኛ ባህሪ ላይ ፅና። ቢሰድቡህ አትስደባቸው። ቢከዱህም አትክዳቸው። ረሱልﷺ እንዳሉት "የከዳህን ሰው አትክዳው"። አንዳንዴ አንድ አካል የተከራካሪውን ወይም የባላንጣውን ብልግና እና ወንጀል እንደዚሁም ነውሮቹን ጠንቅቆ ሊያውቅ ይችላል። ነገር ግን ዲኑ ስለማይፈቅድለት በምንም አይነት መልኩ የዚያን ሰው ነውር አይናገርበትም። ይህን ማድረጉ ደካማ ሊያስመስለው ይችላል። ነገር ግን ይህ የትክክለኛ ስብዕና ባለቤት እምቅ ሃይል የሚረጋገጥበት ቦታ ነው። ይህም ልክ ረሱልﷺ ባልደረቦቻቸውን በዚህ እንደኮተኮቱት ሁሉ ማንኛውም ሙስሊም ሊላበሰው የሚገባ ስብዕና ነው።"
ከዚህ በመነሳት አንድን የጥመት ተጣሪ በተለያዩ ጥፋቶች ላይ ልታየውና ብዙ ጉዳጉዶችንና እጅ በአፍ የሚያስጭኑ ከእርሱ የማይጠበቁ ብልግናወችን ልታውቅ ትችላለህ። ነገር ግን ይህን ነውሩን እንድትሰትርለት ዲንህ ያዛል። ነውሩን ከማጋለጥ ሸሪዓ ይከለክልሃል። ይህን ብታደርግ ወንጀል ፈፀምክ እንጅ ዲንን ረዳህ አይደለም የሚባለው። የጥመት ተጣሪ ላይ መልስ ሲሰጥ በግልፅ የተሳሳተበትን ነጥብ አንስተህ በማስረጃ ረድ ታደርጋለህ እንጅ ገና መንሃጁ ልክ አይደለም በሚል የግል ሚስጥርና ነውሮችን መበተን ነውር ነው። ይልቁንም ልትደብቅለት ነው የሚገባህ።
አላህ እንዲህ ይላል፦
{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ كُونُوا۟ قَوَّ ٰمِینَ لِلَّهِ شُهَدَاۤءَ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَلَا یَجۡرِمَنَّكُمۡ شَنَـَٔانُ قَوۡمٍ عَلَىٰۤ أَلَّا تَعۡدِلُوا۟ۚ ٱعۡدِلُوا۟ هُوَ أَقۡرَبُ لِلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِیرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ } [سُورَةُ المَائـِدَةِ: ٨]
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡"
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
ሸሪዓዊ እውቀትን ለማሰራጨት ቪዲዮን የመጠቀም ብይኑ ወይም ሁክሙ፦
ጥያቄ፦ በቅርብ ጊዜያት ሰለፊይ መሻይኾች በቪዲዮ አማካኝነት ትምህርቶችን እና ሙሓደራዎችን መስጠት ጀምረዋል፣ ይህ ጉዳይ ለአንዳንድ ወንድሞቻችን ግርታን ፈጥሮባቸዋል።
መልስ፦
ይህ የቅርብ ጊዜ ክስተት አይደለም፤ የጥንት ዑለማዎችም ሲሰሩት የነበረ ተግባር ነው። ሸይኽ ኢብኑ ባዝ በህይወት የነበሩት መቼ ነበር? አላህ ይዘንላቸውና ከሞቱ ስንት ዓመት ሆናቸው? ከ25 ዓመታት በላይ፣ በ1420 ሂ. በሙሐረም ወር ነበር አላህ ይዘንላቸውና የሞቱት። እሳቸው በቪዲዮ ይቀረጹ ነበር፤ ይህም እውቀትን በማሰራጨት ረገድ ጠቀሜታ (መስለሀ) እንዳለው ያምኑ ነበር። ከእሳቸው በሁለት ዓመት ልዩነት የሞቱት ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚንም እንደዚሁ ነበሩ። ሸይኽ አል-አልባኒ እራሳቸው እና ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ምስል/ቪዲዮ መቅረጽን አጥብቀው ሀራም ከሚያደርጉ ዑለማዎች መካከል ነበሩ፤ ነገር ግን ጠቀሜታ ባለበት ቦታ ፈቅደውታል።
ሸይኽ አል-አልባኒ በተጠየቁ ጊዜ እንዲህ ብለዋል፦ "እነዚህ ቪዲዮዎች ወይም ቴሌቪዥኖች፤ አንድ ሰው በእነሱ ላይ ወጥቶ ለሰዎች የሶላትን አሰጋገድ ቢያስተምር፣ የሐጅ ጊዜ ሲመጣም የሐጅን አፈጻጸም ቢያስተምር፣ ይሄ ነው ጥቅሙ፤ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ያለው ፈሳድ ግን ያለ ጥርጥር ሀራም ነው።" ይህ የታወቀ ነገር ነው፤ ስለዚህ አብዛኛዎቹ ዑለማዎች በተስማሙበት ጉዳይ ላይ አትቃወም።
ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፣ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ሸይኽ አል-ፈውዛን፣ ሸይኽ አል-ሉሐይዳን፣ ሸይኽ ዘይድ፣ እና ሸይኽ ዑበይድ፤ እነዚህ ከፊል ዑለማዎች ናቸው፤ ብዙዎቹ በዚህ ውስጥ ያለውን ጠቀሜታ ወይም መስለሀ ይመለከታሉ። እንዲያውም ሸይኽ ኢብኑ ባዝ በግልጽ ሲናገሩ፦ "እኔ ክልክል ወይም ሀራም ነው ብዬ አምን ነበር፣ ነገር ግን በውስጡ ያለውን ጥቅም አየሁ" ብለዋል። እኔም በመጽሐፎቻቸው ላይ በተለያዩ ቦታዎች ዱዓቶች በእነዚህ ቻናሎች ላይ እንዲወጡ ሲመክሩ ተመልክቻለሁ። ሰዎችን ለማስተማር እና ሱናን ለማሰራጨት በቪዲዮ መቅረጽ ምንም ችግር የለውም፤ ይህ ካልሆነ ግን እነዚያን የባጢል ሰዎች፣ ሴኩላሪስቶችን፣ የቢድዓ እና የጥመት ሰዎችን መርዛቸውን በሰዎች መካከል እንዲረጩ መተው ይሆናል ብለዋል። በእነዚህ ቪዲዮዎች የበለጠ የተጎዱት አላዋቂ የሆኑ ሰዎች እና ሌሎችም ናቸው፤ የጥመት ሰዎችን በመከታተል ተጎድተዋል እንዲሁም አስመስለዋል፤ እንዲያውም እነዚህን ቻናሎች በመከታተል ምክንያት በአንዳንድ ቦታዎች ኢልሀድነት ተስፋፍቷል። ስለዚህ ኢንሻአላህ ምንም ችግር የለውም፤ በውስጡ ጥቅም ስላለው አትቃወም (አታውግዝ)፤ አትቃወም፣ ዑለማዎች ተናግረውበታልና አትቃወም።
📌 ይህ ሸይኽ ዐረፋት "አት-ተዝኪራህ ፊል-ፊቅሂ አሽ-ሻፊዒይ" (በአል-ሓፊዝ ኢብኑ አል-ሙለቂን፣ አላህ ይዘንላቸው) ለተሰኘው ኪታብ፣ የሽያጭን ምዕራፍ ሲያብራሩ ከሰጡት መልሶች የተቀነጨበ ነው።
በ3ኛው የኢንዶኔዥያ ሰለፊያ የኢማም አል-ሙዘኒ ኮርስ፣ 1446 ሂ.
Repost from • قناة فوائد مشايخ المدينة •
[حكم الفيديو لنشر العلم]
• يقول في الآونة الأخيرة بدأ المشايخ السلفيون يلقون الدروس والمحاضرات بوسيلة الفيديو وبعض إخواننا يستشكلون ذلك..
• الجواب:
هو ليس من قريب هذا فعل العلماء من زمان، متى كان الشيخ ابن باز حيًّا؛ قبل كم سنة توفي رحمه الله؟ أكثر من خمسة وعشرين سنة 1420هـ في شهر محرم توفي رحمه الله، كان يتصور في الفيديو ويرى أن ذلك مصلحة في نشر العلم، ومثله الشيخ ابن عثيمين الذي توفي بعده بسنتين والشيخ الألباني نفسه والشيخ ابن باز كذلك من أشد الناس تحريمًا للتصوير لكنهما أجازى ذلك فيما فيه منفعة. الشيخ الألباني لما سُئل قال هذه الفيديوهات أو التلفزيونات لو أن رجلًا يطلع فيها يعلم الناس صفة الصلاة، إذا جاء الحج علمهم صفة الحج؛ قال هذه هي الفائدة أما وهذا الفساد الموجود لاشك أنه حرام، وهذا معروف فلا تنكر في أمر أكثر العلماء عليه، الشيخ ابن باز والشيخ ابن عثيمين والشيخ الفوزان والشيخ الحيدان والشيخ زيد والشيخ عبيد وهؤلاء بعض العلماء، وكثير منهم يَرون المصلحة في ذلك بل الشيخ ابن باز صرح قال كنت أرى التحريم لكن رأيت المصلحة في ذلك، وأنا وقفت له في عدة مواضع من كتبه يوصي أو يقول على الدعاة أن يظهروا في هذه القنوات لا بأس من التصوير بالفيديو لتعليم الناس ونشر السنة، وعدم ترك هؤلاء من أهل الباطل العلمانيين وأهل البدع والضلال ينشرون سمومهم بين الناس، أكثر من تأثر في هذه الفيديوهات الجهال من الناس وغيرهم تأثروا وقلدوا هؤلاء من أهل الضلال؛ بل انتشر في بعض الأماكن الإلحاد لمتابعة هذه القنوات، فلا بأس إن شاء الله، ولا تنكر فيه مصلحة؛ لا تنكر قال به علماء لا تنكر. اهـ
📌 مقتطف من أجوبة الشيخ عرفات في شرحه على كتاب البيع من «التذكرة في الفقه الشافعي» للحافظ ابن الملقن رحمه الله
في دورة الإمام المُزَنِي السلفية الإندونيسية الثالثة ١٤٤٦ ه ✿
Repost from ዳእዋ ብቻ الدعوة فقط
ስለ ዑዙር ቢል ጀህል የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት ማዳመጥ ይችላሉዑዙር ቢል ጀህል ዑዙር ቢል ጀህል መስጠት ዑዙር ቢል ጀህልን ፋሽን አድርገው የያዙት አሉ ዑዙር ቢል ጀህል በአጭሩ ዑዙር ቢል ጀህል ኢጅቲሀድይ ነወ ዑዙር ቢል ጀህል አለ በዑዙር ቢል ጀህል ዙሪያ ጥያቄዎች እና መልሶች ተከታታይ ከከፍል ❶-❺
በኡስታዝኸድር አህመድ አል ኬሚሴ ሀፊዘሁሏህክፍል ❶ ክፍል ❷ ክፍል ❸ ክፍል ➍ ክፍል ❺ ዑዙር ቢል ጀህል በሚል ወሳኝ በጣም አስፈላጊ ነጥቦች ተነስተዋል ተከታታይ ዳእዋ ከከፍል ❶-➓
በኡስታዝ አቡ ኢምራን ሀፊዘሁሏህክፍል ❶ ክፍል ❷ ክፍል ❸ ክፍል ➍ ክፍል ❺ ክፍል ❻ ክፍል ❼ ክፍል ❽ ክፍል ❾ ክፍል ➓ ዑዙር ቢል ጀህል በሚል ተከታታይ ዳእዋ ከከፍል ❶-❺
በኡስታዝ አብዱ ሽኩር ሀፊዘሁሏህክፍል ❶ ክፍል ❷ ክፍል ❸ ክፍል ➍ ክፍል ❺
Repost from 6Kilo Jemea Qira'at Channel
~
የሸሪዐ እውቀት (ዒልም) ማለት ዲናችን ነው። ከዒልም መራቅ ከኸይር መራቅ ነው። እምነታችንን ለመማር፣ ዒልም ለመቅሰም ምን ያህል ትኩረት እንሰጣለን? ምን ያህልስ መስዋእትነት እንከፍላለን?
ሶሐቢዩ ጃቢር ብኑ ዐብዲላህ - አላህ ይውደድላቸው - አንድ የአላህ መልእክተኛን ሐዲሥ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለመስማት ሲሉ መጓጓዣ ግመል ገዝተው ወደ ሶሪያ የአንድ ወር መንገድ ተጉዘዋል። [ሙስነድ አህመድ፡ 16042] ሱብሓነላህ!! እኛስ በቅራቢያ ያለ መስጂድ ውስጥ የሚስሰጥ ትምህርት እንከታተላለን? እሱ ከሌለ ቁም ነገር የሚሰራጭባቸውን የማህበራዊ መገናኛ ፕላት ፎርሞች ትኩረት ሰጥተን እንከታተላለን?
ዲናችንን ለመማር ጊዜ እንስጥ። ቀላል የሚመስለን ነገር ሲጠራቀም ዋጋው በጣም ትልቅ ነው። መቼስ ዒልም ሳይለፉ እንዲሁ አይገኝም። ኢብኑ መስዑድ - አላህ ይውደድላቸው - እንዲህ ብለዋል፦
"ማናችሁም ቢሆን አዋቂ ሆኖ አይወለድም። እውቀት የሚገኘው በመማር ነው።" [አልኣዳቡ ሸርዒየህ፣ ኢብኑ ሙፍሊሕ፡ 1/35]
© IbnuMunewor
+1
ጋሽ ባህሩ ተካ ¡¡ በሀራ እና በሀላባ ሰለፊይ ቢሎ በገለፃቸው የለተሞ መንጋዎች መካከል አለመግባባት እንዳለ ገልፇል!!
ግን በእርሱ እና በመንጋው አውራዎች መካከል ያለውን አለበግባባት አልተናገረም!!
እኔ እምለው!! የለተሞ መንጋ እርስ በራሱ መቼ ተማምኖ ያውቃል??
አንዱ አንዱን በድብቅ ሪከርድ እያደረገ አንዱ አንዱን በድብቅ ካሜራ እየቀረፀ የእርስ በራሱን ምስጥር በአደባባይ በሚድያ የሚያሰጣ የሞኞች ስብስብማ አይደል??
መቼ መከባበር ያውቃል??
ደሞም የሚገርመኝ እርስበእርሱ ይባላና! እንትና እንትና ታረቁ በሚል ምትክ እንትና ተውበት አድርጎ ተመለሰ ይባላል¡
እሺ የለተሞ መንጋ ተከባብሮ ያውቃል ወይ??
የለተሞ መንጋ አንድ ሆኖ ያውቃል ወይ?
ልንገራችሁ ተከባብራችሁ፣ተዋዳችሁ፣ተሸፋፍናችሁ፣ተመካክራችሁ አታውቁም!!! ወደፊትም ችግርን ተነጋግሮ የመፍታት ባህል ታዳብራችሁ ብዬ አልጠብቅም!!!
ባህሪ ጎረምሳ ሁሉ እንዴት አድርጎ ነው በመነጋገር ችግሩን የሚፈታው??
ለማስመሰል እና ነውራችሁን ለመደበቅ ትሞክራላችሁ ግን አትችሉም በሚድያ ወጥታችሁ በሚላስ መለባለብ ትጀምራላችሁ!!
አሁንስ ማነው የግብፅ ተላላኪ የሆነው?
~
ሙርሲ ስልጣን የያዘ ሰሞን ነው። መካ ውስጥ ከአንድ ወዳጄ ጋር ታክሲ እየጠበቅን አንድ ግብፃዊ መጣ። በስልኩ የያዘውን ወሬ ሳያቋርጥ ወደየት እንደሆንን ጠየቀን። የሐጁ ግርግር ብዙም ስላላለፈ ከፍ ያለ ዋጋ ነገረን። ጓደኛዬ "20 ሪያል ይሆንሃል?" አለው። ወሬውን እንደቀጠለ እንድንገባ በእጁ ጠቆመን። ትንሽ እንደሄድን ስልኩን ሲጨርስ ደጋግሞ እየማለ እንደማያዋጣው ነገረን። ጓደኛዬ እላፊ ነገር መናገር ያዘ። "እናንተ ግብፆች ሌቦች ናችሁ" አለው። "ሌባው ሙርሲ ነው። ከናንተ መንግስት ጋር ተስማምቶ ናይልን እንድትገድቡ አደረጋችሁ" አለ። ገረመኝ። የሙርሲ እጅ ባይኖርበትም ምናልባት ባለማሰናከሉ እየወቀሰ መሰለኝ። ግብፃውያን ጋር ተገናኝታችሁ ኢትዮጵያውያን መሆናችሁን ካወቁ የናይል ጉዳይ መነሳቱ የሚጠበቅ ነው። የፖለቲካ መስመራቸው ቢለያይ እንኳ በብሄራዊ ጥቅማቸው አይደራደሩም።
ለነሱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ ግድብ እንደ ሃገር ስጋታቸው ነው። በየጊዜው "ሁሉም አማራጭ ጠረጴዛ ላይ ነው" እያሉ በኃይል አማራጭ ሲያስፈራሩ ማየትና መስማት የተለመደ ነው። እንደ ህዝብ ያለንን መከፋፈል ጠንቅቀው ስለሚያውቁ በተደጋጋሚ ከታዋቂ ሰዎች እስከ ተርታው የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ የኢትዮጵያ አማፂ ሃይሎችን በማገዝ ሃገሪቱን መበታተን ይገባል እያሉ ሃሳብ ይሰጣሉ። የሰሞኑ ጦርነትም ለነሱ ሰርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል። ስለ ጦርነቱ የሚዘግቡና የሚተነትኑ የዐረብኛ ስራዎች ማህበራዊ ሚዲያውን አጥለቅልቀውታል። ጦርነቱ አዲስ አበባ እንደተቃረበ ሁሉ ሲፅፉ አይቻለሁ። ትንታኔያቸው እንዳለ መሬት ላይ ያለውን ሳይሆን ምኞታቸውን የሚያንፀባርቅ ነው።
አብዛኞቹ በዚህ ጉዳይ ላይ የተጠመዱ የዓረብ ሚዲያዎች የተሳሳቱ ዘገባዎችንና ትንታኔዎችን ደጋግመው ቢያቀርቡም ምናልባት የስማቸው ጉዳይ አያሳስባቸው ይሆናል። የአልጀዚራ ተደጋጋሚ መዋሸት ግን ገርሞኛል። አልጀዚራ ትልቅ ስም እንዳለው የሚታወቅ ነው። ይህንን ስሙን በዋናነት ያገኘው በምዕራባውያን የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች ለዓለም እንዳይደርሱ የታፈኑ ድምፆችን በማስተጋባቱ ነው። ከመሆኑም ጋር እንደማንኛውም ሚዲያ የቆመለት ፖለቲካዊ ዝንባሌ አለውና መሳሳት ሳይሆን የታቀደባቸው ውሸቶችን ይዋሻል። ከጀርባ በምዕራባውያን ስውር እጆች ሲዘወር የነበረው እና "የዐረብ ፀደይ" (Arab Spring) የሚል የዳቦ ስም የተሰጠው ዓረቡን ዓለም በገዛ ልጆቹ የማፍረስ ሴራ በማቀጣጠል የጠላት መጠቀሚያ ሆኖ በግንባር ቀደምትነት ያገለገለው አልጀዚራ ነው። በዚያን ጊዜ ቤንዚን ነበር ሲያርከፈክፍ የነበረው። ተቃውሞዎችን ለማቀጣጠል ሀሰተኛ ዘገባዎችን ጭምር ያቀርብ፣ በሃሳብ የተለዩ ድምፆችን ደግሞ live ጭምር እያቋረጠ ያፍን ነበር። አንዴ ግብፅ ራቢዐተል ዐደዊያ አደባባይ ላይ በመንግስት የተጨፈ ^ ጨፉ ሰዎች በማለት በህይወት ያሉ ሰዎችን በከፈን ተጠቅልለው የሞቱ መስለው እንዲቀርቡ ያደረገበት አይረሳኝም። ብዙም ሳይቆይ ቪዲዮው እውነተኛ እንዳልሆነና ይልቁንም ሰዎቹ ለትወና ሲዘጋጁ እየተቀረፁ የሚያሳይ ምስል ወጥቶ ነበር፡፡
ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የአልጀዚራ የተለያዩ ድረ ገፆች ላይ የሚወጡ ዜናዎችም የተጋነኑ ብቻ ሳይሆኑ በቅጥፈት የታጨቁ ጭምር ናቸው። እንዳጠቃላይ የዐረብ ሚዲያዎች ሁኔታ የግብፅን የገዘፈ ተፅእኖ የሚያሳይ ነው። ግብፆች ከነ ፖለቲካ ልዩነታቸው ለሀገራቸው ጥቅም ያላቸው መዋደቅ የሚያደምም ቢሆንም የሚሄዱበት መንገድ ግን እኛን እንደ ህዝብም እንደ ሃገርም በሚጎዳን መልኩ መሆኑ ያሳምማል። በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ነው ጥቅማቸውን ማስከበር የሚፈልጉት። ተንታኞቻቸውና አክቲቪስቶቻቸው ይህንን በግላጭ ነው የሚያወሩት።
ለፖለቲካ ጉጉት የለኝም። ፖለቲከኛም አልወድም። ነገር ግን የሃገር መፍረስ ለኛ የሚያመጣብን ጣጣ በጣም ያስጨንቀኛል። አላህ ይጠብቀን እንጂ ቢከሰት ብዙ የድንበርና የብሄር ግጭቶች ይከተላሉ። ዛሬ ካለው የባሰ እልቂትና መፈናቀል ያሰጋል። ያለንበትን ተጨባጭ እና የፖለቲካ ሃይሎችን ዓላማ ያጤነ ሰው ይህንን መረዳት አይከብደውም። በተወጠረች ሃገር ውስጥ ከዚህ ስጋት እሩቅ ነን የሚለው አያሳምነኝም። በተቃውሞው ጎራ ያሉ አካላት እና ደጋፊዎቻቸው የሚቃወማቸውን ለማሸማቀቅና ለማምታታት ቢሞክሩም ይሄ የብልፅግና ወይም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳይ አይደለም። "በሃገር ላይ ያሉ ውጥንቅጦችን በማጣቀስ "ከዚህ በላይ ምን ሊኖር?" በማለት አፍ ሊያስይዙ ይሞክራሉ። ከዚህ የባሰ ብዙ ነገር አለ። ማሰብ ያልፈለገ አይታየውም። ወይም ባ'ፉ እየደለለ ለራሱ ቡድናዊ ጥቅም በመታገል ሃገር በላያችን ላይ ሊያፈርስብን የሚታገል አካል ለአላማው እየሰራ ስለሆነ ምንም ቢል አይደንቅም።
የሆነ ሆኖ ትናንት ሙስሊሙን "የግብፅ ተላላኪ" እያለ አፉን ሲከፍት የነበረ አካል፣ አፄ ዮሐንስ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የወሎ ሙስሊሞችን የፈጀው ለግብፃውያን በህቡእ እየሰሩ ስለ ነበረ ነው እያለ መርዘኛ ትንታኔ የሚሰጥ አካል እንዲሁም ከኛ ውጭ ለሃገር ታማኝ ላሳር እያለ የሚፎክረው አካል ዛሬ ላይ ሃገሪቱ መበታተን አለባት የሚሉ ሃይሎችን እቅድ ሊያሳካ እየተጋ ነው። እና ማነው የግብፅ ተላላኪ የሆነው?
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 19/2019)
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from 🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ሰለፍይ ወሰለፍያት እህት ወንድሞች ኢንሻአሏህ ነገ ረቡዕ ምሽት ሙሀደራ ፕሮግራም ይኖረናል ፡፡
⏰"በዕለቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን
➊ ኡስታዝ አቡ ሀሳን
🔖"ርዕስ በሰአቱ ይነገራል
➋ ኡስታዝ አቡ ሻኪራ
🔖ርዕስ "በሰዓቱ
❸ ኡስታዝ አቡ ኡባይዳ
🔖"ርዕስ በሰአቱ ይነገራል
❹ ወንድም አቡ ሂበቱላህ
🔖ርዕስ "በሰዓቱ
❺ ኡስታዝ አቡ አመቲ ረህማን
🔖ርዕስ በሰዓቱ
❻ ወንድም አቡ ሹራ
🔖ርዕስ በሰአቱ ይነገራል
❼ ወንድም ኑረድን አቡ ፋሩቅ
🔖ርዕስ "በሰአቱ ይነገራል
❽ ወንድም አቡ ኢምራን
🔖ርዕስ "በሰአቱ ይነገራል
📖ቲላዋ የሚጋብዙ ወንድሞች
🎤ወንድም አቡ ኢምራን
🎤ወንድም አቡ ሀይደር
🎙 የፕሮግራሙ መሪ ወንድም አቡ ማሂ
🗓ቀን እለት ረብዑ ምሽት
⏰ ሰአት
🇪🇹በኢቶ 3:00
🇸🇦በሳዑዲ 9:00
🇵🇸በዱባይ 10:00
ፕሮግራሙ የሚካሄድበት ሊንክ👇
👇👇👇👇👇
https://t.me/Asselefiyah_Channel
https://t.me/Asselefiyah_Channel
