قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
رفتن به کانال در Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
914
مشترکین
-324 ساعت
-177 روز
+5330 روز
آرشیو پست ها
ሳዳት ሆይ ኡስታዝ ብዬ ልጥራህ!?
ለኔ ፍቀድልኝ!?
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አህባሽና ኢኽዋን ሁሌ እየዛተብህ፡
ሱፍያና ተብሊግ ጫት እየቃመብህ፡
ይሙትልን ብለው እየፀለዩብህ፡
ይህን ሁሉ ጫና ጆሮ ዳባ ብለህ፡
በተውሒድ ስብከት ላይ ዛሬም ድረስ አለህ!?
ከማውቃቸው ጀግኖች አንተ ትለያለህ፡
ታዲያ__!!
ሰዎችን በመልካም-ዘውትር እያዘዝከን፡
ወንጀል እንዳንፈፅም እየከለከልከን፡
በአሏህ ውድ ቃል_ሁሌ እያሳመንከን፡
አሏህን ተገዙ አንዱን ጌታ እያልከን፡
ለተውሒድ ለሱና በቻልከው ከለፋህ፡
ባለህ ትርፍ ጊዜ ሽርክን እያጠፋህ፡
ፕሮግራም አውጥተህ ሱናውን ካስፋፋህ፡
በረድ አንበርክከህ ቢዲአን ከገፋህ፡
ዳዒያችን ነህ ብዬ መስክሬ በእውነቱ፡
ኡስታዝ ሳዳት ብልህ ምንድን ነው ጥፋቱ!?
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ኡስታዝ አትበሉኝ ካልክ እሽ ግድ የለኝም፡
ግን ፈቃድ ይሰጠኝ እኔ አያስችለኝም፡
በስምህ ስጠራህ አዎ ይጨንቀኛል፡
እደነግጣለሁ ፍርሀት ይሰማኛል፡
አንገት እደፋለሁ ይሰቀጥጠኛል፡
ስለዚህ ኡስታዜ ብልህ ይሻለኛል‼️
የኔ ዘመን ክስተት የወጣቱ ወኔ፡
ችግሬን ተረድተህ ፍቀድልኝ ለኔ፡
የተውሒድ ሰባኪው የሱናው ወገኔ፡
#ሳዳት_አንተ_ማለትኮ_!!
ሱናን ለመዘመር ይሉኝታ አይዝህም፡
የአድናቂህ ጫጫታ አያታልልህም፡
የወቃሽ ወቀሳ አላሸነፈህም፡
ጥቅምና ዝና አላማለለህም፡
#ሰለፍይ ወንድም ነህ #ኢኽዋን አይደለህም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አትፈልግም እንጂ ብዙ ብዙ ባልኩህ፡
የውስጤን እምቅ ሀይል ፅፌ በነገርኩህ፡
ግን አንተ አትፈልግም እንድህ አይነት ነገር፡
እንጂማ ጀግና ነህ እውነት ለመናገር፡
በእናትህ ልጅ ጨከንክ ድምፅህን ሰማሁት፡
አሳማኝ ምክርህን በጥልቀት አየሁት፡
ገረመኝ አቋምህ ደነቀኝ ድፍረትህ፡
ለሐቅ ያለህ ቦታ አመለካከትህ፡
ትላንት ሆነ ዛሬ ተውሒድ ነው ስብከትህ‼️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አሏህ በአንተ ሰበብ ብዙ ሰው አቅንቷል፡
ሳይሰለቹ መምከር ላንተም ፅናት ሰጥቷል፡
ብዙዎች መጥተናል ከሱፍያ ገዳም፡
ዛሬ ለሐቅ እንጂ ለሽርክ አንነዳም፡
ይህንን ሁሉ እውነት አንተ ባትረዳም፡
ለዚህ ነው ስምህን የምናነሳሳህ፡
ሰበብ ሆነኸናል አንችልም ልንረሳህ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እንጂማ ፈፅሞ ድንበር አላለፍንም፡
ያለ ቦታህ ቁጭ በል በፍፁም አላልንም፡
ነገር ግን ኡስታዝ ነህ እወቀው እውነቱን፡
ተጨባጩ ክስተት መረጃ ነው ፍቱን፡
ከፍ ከፍ አድርገን አናካብድህም፡
እውነት ሀቂቃን ግን እመን ግደለህም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ከኢኽዋን መንጋጋ ከጥርሳቸው መሀል፡
አሏህ ሰበብ አርጎ እኔን አውጥተሀል፡
እኔ ኡስታዝ ብልህ ላንተ ምን ያንስሀል⁉️
#በተቻለህ_አቅም፤
ባረፍክበት ሁሉ ሐቅ አስተላልፈሀል፡
#የሱና_ጠበቃ፤
የጥመት መብረቅ ነህ እኛ ወደንሀል፡
#አሏህ_ይጠብቅህ፤
በተውሒድ ስብከትህ ክብር ይገባሀል፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እንባ ተናነቀኝ ምክርህን ሰማሁት፡
ሀሳብ ምኞትህን አሻግሬ አየሁት፡
በኔ ቁንፅል ሀሳብ በትንሿ ማንኪያ፡
መስፈርት አሟልተሀል በኡስታዝ መለኪያ፡
በስምህህ አልጠራም ይህን እወቅልኝ፡
እባክህን ሳዳት ይቅርታ አድርግልኝ፡
ኡስታዜ ልበልህ ለኔ ፍቀድልኝ፡
ሀያዕ ይይዘኛል በስምህ ስጠራህ፡
ዑስታዝ ያስብልሀል የሰራኸው ስራህ፡
ይሔ ተማፅኖዬ ላንተ ይድረስልኝ፡
ዑስታዜ ልበልህ ለኔ ፍቀድልኝ⁉️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
#በኑረዲን_አል_አረቢ 02/04/1443
---------------------------------------
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
---------------------------------
Repost from አል ኢርሻድ የሠለፍዮች ስቱድዮ
የኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐዶራዎችን ለማግኘት
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin/2989
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin/2989
Repost from ሙርሰል ሰይድ ጨፌ ❨Official Channel❩
ከደርስ የተቆረጠ 📄
ውሀን እን ድንጋይ 🪨 ወይም ሶፍት በአንድ ላይ 📱 ለእስቲንጃ መጠቀም ✅
👉https://t.me/murselseid
#መጅኑኑ_ለይላ
መግቢያ፦
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ በሆነው። የሰውን ዘር ከአንዲት ነፍስ የፈጠረ ለተፈጣሪው ቀዳሚ ሰው አደም ሚስት ትሆነው ዘንድ እንስቷን ሐዋ ከአደም ጎድን የፈለቀቀ ሁለቱንም በትዳር ገመድ ያሰተሳሰረ ከነርሱም ምድር ላይ በፍቅርና በመተሳሰብ ተመጋግበው ይኖሩ ዘንድ በርካታ ወንዶችንና ሴቶችን ያስገኘ ሁሉም ይተዋወቁ ዘንድ ረቂቅ ጥበብ ያላበሰ፣ የመዋደድን ምርጥ ዘር በመካከላቸው የዘራ፤ ለርሱ ብለው የተዋደዱትን በምፅዐት ቀን በዐርሽ ጥላ ስር እንደሚያሰጠልል ቃል የገባ ሀያል አምላክ አላህ ምስጋና ይገባው።
ሰለዋትና ሰላም ለዓለማት እዝነት ተደርገው በተላኩት የፍቅር ተምሳሌት በሆኑትና በፍጥረተ ዓለሙ ከወደዱም ሆነ ከተወደዱ፤ ካፈቀሩም ሆነ ከተፈቀሩ ሁሉ በላቁት ፍቅርንና መውደድን አፍቅረውና ወደው በተግባር ባሳዩት በጓድ ባልደረቦቻቸው አምሳል አልባ ውዴታ ተወደው ምሳሌ በሆኑት ፊት ላለፈውም ኋላ ለሚመጣውም የሚበቃ የመድህን ዋስትና (ሸፋዐተል ዑዝማ) በተጎናፀፉት፣ ለእናት ለአባታቸው አንድ ሆነው ለመላው ዓለም አባትም እናትም ወንድምም እህትም በመሆን ፍቅርን ባነገሱት የአላህ መልዕክተኛና የነቢያት መቋጫ ነብዩ ሙሐመድ ላይ ይስፈን፡፡
ይህ መጅኑኑ ለይላ (እብዱ የፍቅር ሰማዕት) በሚል ርዕስ የተሰናዳውና በእጃችሁ ላይ የሚገኘው መፅሃፍ በአንድ በቀዳሚው ሂጅራዊ ክፍለ ዘመን ውስጥ በህይወት ኖሮ ባለፈ የፍቅር ሰማዕትና በውድ ፍቅረኛው መካከል ስለተከሰተ እውነተኛ የፍቅር ታሪክ የሚተርክ በህይወታቸው የገጠማቸውን ውጣ ውረድ የሚያስቃኝ ታሪካዊ መፅሃፍ ነው።
የአፍቃሪው ቀይስ ኢብኑል ሙለወሕ ታሪክና የፍቅረኛው ለይላ ቢንት መህዲ ሰም በበርካታ የስነ ፅሁፍ ውጤቶችና መንዙማዎች ውስጥ የፍቅር ተምሳሌት ተደርገው መቅረባቸው በራሴ ላይ ፍቅረኛሞቹ ምን ያህል ቢዋደዱና በፍቅር ዓለም የላቀ መሰዋዕትነት ቢከፍሉ ነው በዚህ ደረጃ የገነነ ሰም ባለቤት ሊሆኑ የቻሉት? የሚል ጥያቄ እንዲያስነሳብኝ ማድረጉ ለዚህ መፅሃፍ መፃፍ አንዱ መንስኤ ሆኗል።
በተጨማሪም በጊዜያችን በርካቶች ይህን የፍቅር ታሪክ ለማወቅ እየፈለጉ ታሪኩ በአማርኛ ቋንቋ ባለመሰነዱ ምክንያት ከፍላጎታቸው ሳይደርሱ መቅረታቸውን በመገንዘብ ይህን የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት ማሰቤ ሌላኛው አንደርዳሪ ነበር፡፡
የመጅኑኑ ለይላ ታሪክ በብዛት ከግጥሞቹ ጋር ተያይዞ ጨረፍ እየተደረገ ከመሰነዱ ውጪ ወጥ ሆኖ ያልተፃፈ መሆኑ እኔ ለመፃፍ ያቀድኩትን አይነት ምሉዕና ወጥ ታሪክ ለማዋቀር ከፍተኛ ጥናትና ፅናት የሚጠይቅ እንዲሆን አድርጎብኛል። ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃም ለተወሰኑ ወራት ጊዜዬን ለታሪኩ ብቻ እንድሰጥ አስገድዶኛል፡፡በተለይም ታሪኩ በተለያዩ መፃህፍቶች ተበታትኖ መቀመጡና በየመሃሉ ልብ ወለድ መሰግሰጉ ጥንቅሩን አድካሚ አድርጎታል።ልብ ወለዱን ከእውነተኛ ታሪኩ ለመለየት መዛግብትን የማገላበጥና የማመሳከሩ ሂደትም ሰፊ ጊዜ ወስዶብኛል፡፡
መፅሃፉን በሁለት ምዕራፎች ያዋቀርኩት ሲሆን በመጀመርያው ምዕራፍ አንድ አንባቢ የፍቅር ታሪኩን ከማወቁ በፊት ቢያውቃቸው መልካም ነው ብዬ ያሰኳቸውን መረጃዎች አካትቻለሁ፡፡ መረጃዎቹም በጥቅሉ ፍቅረኛሞቹ የኖሩበትን መልከዓ ምድርና አካባቢ፣ ባህልና እሴት፣ መንግሰትና ስርዐት እንዲሁም ታሪኩን በተመለከተ በምን መንገድ እኛ ድረስ ሲወርድ ሲወራረድ እንደመጣ የሚገልፁ ፅሁፎች ተጠናቅረውባቸዋል።በማስከተልም የታሪኩን ዝነኝነት፣ ከመንዙማ ጋር ያለውን ትስስርና የነብያዊ ፍቅር ተምሳሌትነት በተመለከተ ውስን ብያኔዎችን አስፍሬባቸዋለሁ፡፡
በዚህ መፅሃፍ ላይ የተበረዘውን የፍቅር ታሪክ በማበጠር ትክክለኛና የተረጋገጡትን ብቻ አካትቼ ከልብ ወለድ ነፃ ለማድረግ የተቻለኝን ሞክሬያለሁ።በየመዛግብቱ ተዘበራርቀው የተቀመጡ ታሪኮችንም በተቻለ መጠን ቅደም ተከተል ይዘው እንዲቀመጡ ከፍተኛ ጥረት አድርጌያለሁ። በመፅሃፉ የተካተቱትን የፍቅረኛሞቹ የዐረብኛ ግጥሞችም ቃል በቃል ባልተረጉማቸውም መልዕክትና መንፈሳቸውን ግን አቻ በሆነ የአማርኛ ግጥም አደራጅቻቸዋለሁ።
በመጨረሻም መላው አንባቢ ታሪኩን በሚያነብበት ሰዓት ከወዲሁ እንዲያውቀውና እንዲገነዘብ የምፈልገው ነገር ቢኖር ይህ የፍቅር ታሪክ በእስልምና ስርዐት በሚተዳደር ግዛትና ሃገር ውሰጥ የተከሰተ የሁለት ሙሰሊሞች ታሪክ እንጂ ሙሉ በሙሉ እስልምናን የሚወክልና የሚገልፅ አለመሆኑን ነው::ከዚህ በተረፈ የፍቅርን ሁለንተናዊ ገፅታ ወደ ኋላ መልሶ የሚያሳየውን ይህን እውነተኛ ታሪክ በአንክሮ ታነቡት ዘንድ በአክብሮት እጋብዛለሁ ፡፡
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
~ ሸይኹ አለቀሱ!
ምን ያስለቀሳቸው ይመስለሃል ሐቢቢ? ያንተና የኔ በፊትና ላይ መውደቅ ብሎም የእለት ከእለት ተግባራችን አመፅ መሆኑ ነው ያስለቀሳቸው። አንተና እኔ ግን ልባችን እጅጉን ከመቆሸሹ የተነሳ በወንጀላችን ማልቀስ ቀርቶ ሲራጥን ያለፍንና የጀነት ካርድ የተሰጠን ይመስል ጧት ማታ በሐራም ተዘፍቀን ሳለ መሳቅ ሁኗል ስራችን። አላህ ይዘንልን ብቻ። ወጣቱን ሁሉ አላህ ልቦናውን ይመልሰው።
√ ሸይኽ ዓብዱረዛቅ አል'በድር -ሐፊዘሁላህ- ባያያዝኩት የድምፅ ፋይል እንዲህ ይላሉ፦
«ዛሬ ላይ በወንጀል እየተሰቃዩ ያሉ የዘመናችን ወጣቶች ከዚህ በፊት ታይተው የማይታወቁ ብዙ የፊትና በሮች ተከፍተውባቸዋል። በጣም አደገኛ በሮች ተከፍተውባቸዋል። እነዚህ ወጣቶች የሚያዝንላቸውና የሚራራላቸው እንደዚሁም አላህ ተውበት እንዲሰጣቸው፣ ልቦናቸውን እንዲያቀናው፣ ከፊትናዎች እንዲያዞራቸው፣ ከነፍሳቸውና ከሸይጧን ተንኮል እንዲጠብቃቸው ዱዓእ የሚያደርግላቸው ሰው ያስፈልጋቸዋል። የሚያዝንላቸው፣ የሚራራላቸው፣ እዝነት በተሞላበት መልኩ ወደ ኸይር የሚጠራቸው ያስፈልጋቸዋል።»
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from • قناة فوائد مشايخ المدينة •
اللهم أصلح أحوال المسلمين في كل مكان.
وأصلح فساد قلوبنا ونياتنا وأعمالنا وألسنتنا.
واستر عوراتنا وعيوبنا.
واغفر بعفوك ورحمتك ذنوبنا.
عرفات المحمدي.
https://x.com/Arafatbinhassan/status/2106038970626818554
Repost from ስለ ቀልባችን
🎁አድስ የኪታብ ደርስ!
-
💍 ወጣቱን ከፈተና ታድጎ ወደ ሐላል ጎጆ የሚያመላክት፣ ከትዳር ማሰብ ጀምሮ እስከ ስኬታማ የትዳር ሕይወት መመሪያ የሚሰጥ ድንቅና አጭር የኪታብ ትምህርት፦
📚የኪታቡ ስም -
📖 «رسائل للمقبلين على الزواج»
❝ምክር ወደ ትዳር ዓለም ለመግባት ላሰቡ❞
🎙አቅራቢ፦ አቡ ሱፍያን
🗓የሚጀመረው፦ ጁሙዓ • መስከረም 29
⏰ሰዓት፦ ዘወትር ጁሙዓ እና እሁድ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ
➖የሚቀርበው፦ በ«ስለ ቀልባችን» የቴሌ ግራም ቻናል ቀጥታ ስርጭት(Live)-🫴
https://t.me/Sle_qelbachn1
https://t.me/Sle_qelbachn1
⭕️ ላላገባችሁትም በትዳር ውስጥ ላላችሁም እጅግ ወሳኝ የሆነ ኪታብ ነው!
Repost from Woldia University Muslim Students
"ኢሬቻ ባህል እንጂ ሃይማኖት አይደለም" የሚሉ ሙስሊሞችን ማየት በጣም ልብ የሚያደማ ነው።❗️
ከላይ ሃለውን ቪዲዮ ተመልከቱ ለዛፉ ሲሰግዱ! ተመልከቱ የሚሰሩትን።❗️
🩸ሙስሊም ወንድምና እህቶቸ ሆይ❗️ የብሄር አጀንዳ አቅላችንን አስቶ ጀሃነም እንዳይከተን እንጠንቀቅ። አላህን እንፍራ።!!
መስቀልን የምንቃወመው የአማራ ስለሆነ አይደለም።የኩፍር በአል ስለሆነ እንጂ።!
ኢሬቻ የኦሮሞ ስለሆነ በተለየ አይን አናየውም። የኩፍር ቡላና ዳለቻ የለውም። ሁሉም ኩፍር ነው። ሁሉም የጣኦት አምልኮ ነው። ሁሉም ተውሒድን በጥብቅ ከሚያስተምረው ኢስላም ጋር ፈፅሞ የሚፃረር ነው። ሁለቱም ከኢስላም ጠርጎ የሚያስወጣ የለየለት ክህደት ነው።
ዛሬ የብሄር አጀንዳ እራሱን የቻለ ጣኦት ሆኗል። ሰዎች ለብሄር ሲሉ ካፊርን ይወዳሉ። ሙስሊምን ይጠላሉ። ለብሄር ሲሉ ለመስቀል፣ ለኢሬቻ ወግነው ይሟገታሉ። የኩፍር በአል ያከብራሉ።
የሚያሳፍረው ሸይኾችና ዱዓቶች ጭምር በዘረኝነት መለከፋቸው ነው። እስኪ የመስጂድ ኢማም ሆኖ፣ ጥምጣም ጠምጥሞ የኦርቶዶክስ ሰልፍ የሚያደምቅ፣ በዘራቸው የተነሳ ሙስሊም ትግሬዎችን ጭምር የሚያጥላላ፣ ለኢሬቻ "የእንኳን አደረሳችሁ" መልእክት የሚያስተላልፍን ልክፍተኛ አስቡ። ዘረኝነት አደዛዥ እፅ ነው።❗️ በዚህ በሽታ የተለከፈ ሰው እይታው ጠባብ ነው። አርቆ ማሰብ አይችልም። ይህንን ሀሺሽ፣ ይህንን ጣኦት አጥብቀን ካልተዋጋነው ብዙ ነገር ያሳጣናል።❗️
ያ'ያያዝኩት ቪዲዮ ኢሬቻ የሚያከብሩ ሰዎችን ድርጊት ነው።
🩸ሁላችንም ሼር እናድርገው ሼር ሼር ሼር❗️
የተወሰደ
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ።
ከጀነት በሮች ውስጥ ፆመኞች ብቻ የሚገቡበት ልዩ በር ረያን ይባላል ።
🌹ለጀግናዋ ሰለፊይ እህቴ… በልብሽ ልትይዢያቸው የሚገቡ የሕይወት መልዕክቶች 🌷
🌸ጀግናዋ እህቴ ...ይህን መልዕክት ለአንቺ የምጽፈው፣ በሕይወትሽ ውስጥ ሁሌም ደስተኛ፣ ጠንካራ፣ የተከበርሽ እና ከአላህ ጋር የተቆራኘች ሴት እንድትሆኚ ካለኝ ከፍተኛ ምኞት የተነሳ ነው።
ዱንያሽ በሰላም፣ ልብሽ በኢማን፣ ሕይወትሽ በበረከት፣ አኺራሽም በጀነት እንድትዋብ እመኛለሁ።
ስለዚህ እህቴ፣ እነዚህን ቃላት በልብሽ ጠብቀሽ አስቀምጫቸው፦
🌿 ① በጭራሽ ዋጋሽን ከሰዎች አትፈልጊ፤ ከአላህ ጋር ያለሽን ግንኙነት አጠናክሪ
እህቴ፣ ውበትሽ፣ ክብርሽ እና እውነተኛ ዋጋሽ በሰዎች አስተያየት አይወሰንም።
አንዱ ሰው ቢያደንቅሽ፣ ሌላው ቢነቅፍሽ፤ ዋጋሽ አይጨምርም፣ አይቀንስም።
ሰዎች የሚያዩት ውጫዊ ገጽታሽን ነው፤ አላህ ግን ልብሽን እና ሥራሽን ያያል።
አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِنْدَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ﴾
“ከእናንተ በአላህ ዘንድ ከሁሉ የተከበረው አላህን በጣም የሚፈራው ነው።”📖 አል-ሑጁራት፡ 13
ስለዚህ እህቴ፣ የሰዎችን ድንቆት ለማግኘት ሳይሆን የአላህን ውዴታ ለማግኘት ብለሽ ኑሪ።
🌸 ② ማንነትሽን በምንም አይነት ዋ አትሸጪ፤ ለማንም ብለሽ ራስሽን አትቀይሪ
እህቴ፣ ሁሉም ሰው እንዲወድሽ ስትሞክሪ በመጨረሻ ራስሽን ልታጭ ትችያለሽ።
አንዳንድ ሰዎች ማንነትሽን አይረዱም።
አንዳንዶች የምትይዣቸውን እሴቶች አይወዱም።
አንዳንዶችም ለእነሱ እንድትሆኚ ሊፈልጉ ይችላሉ።
ነገር ግን ጀግናዬ፦
ማንነትሽን በአላህ ትዕዛዝ ላይ ከገነባሽው ቡሀላ፣ የሰዎች ፍላጎት እንዲያፈርሰው አትፍቀጂ።ሰዎችን አክብሪ፤ ግን ለእነሱ ለመመሳሰል ብለሽ ክብርሽን አትጣዪ።
🥀 ③ ጀግናዬ ሁሉም ሰው በሕይወትሽ ውስጥ ለዘላለም አይቆይም
እህቴ፣ አንዳንድ ሰዎች ለጊዜው ይመጣሉ።
አንዳንዶች ትምህርት ይሆኑልሻል።
አንዳንዶች ደግሞ ለውጥን ያስተምሩሻል።
ስለዚህ አንድ ሰው ከሕይወትሽ ሲወጣ ሁሉንም ነገር እንደጠፋ አትቁጠሪ።
አንዳንድ መለያየቶች ህመም ቢኖራቸውም፣ አላህ በኋላ የምታውቂውን ሌላ ምክንያት ሊኖራቸው ይችላል። ትቶሽ የሚሄድ ሰው እንዳትከተዪ፤ የሚቀርልሽን አላህ እንዲያስተካክልልሽ ጠይቂ።
🌱 ④ እህቴ ሕልምሽን ይዘሽ ተጓዢ፤ ግን አላህን አትርሺ
በውስጥሽ ያለውን ችሎታ አታቃልዪ።
አላህ ለእያንዳንዱ ሰው የራሱን ችሎታ፣ ተሰጥኦ እና የሕይወት ጉዞ ሰጥቶታል።
ስለዚህ ራስሽን ከሌሎች ጋር አታወዳድሪ።
የሌላ ሰው ጉዞ የአንቺ መለኪያ አይደለም።
አንዱ ቀድሞ ይደርሳል፤ ሌላው ዘግይቶ ይደርሳል።
አንዱ በአንድ መስክ ይበረታል፤ ሌላው በሌላ።
አንቺ የራስሽን መንገድ በኢማን፣ በሥራ እና በተወኩል ላይ ታግዘሽ ተጓዢ።
♦️ ⑤ ጀግናዬ ሰብር ማለት ደካማ መሆን አይደለም
እህቴ፣ አንዳንድ ቀናት በጣም ከባድ ይሆናሉ።
አንዳንድ ቃላት ልብሽን ይሰብራሉ።
አንዳንድ ሰዎች ያሳዝኑሻል።
አንዳንድ ምኞቶችሽም ሊዘገዩ ይችላሉ።
ግን እነዚህ ሁሉ የጉዞሽ መጨረሻ አይደሉም።
አላህ በቁረአኑ እንዲህ ይላል፦
﴿إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ﴾
“በእርግጥ አላህ ከታጋሾች ጋር ነው።”
📖 አል-በቀራህ፡ 153
ስለዚህ ሰብር አድርጊ።
ግን ሰብርሽ ተስፋ የሌለው መጠበቅ አይሁን።
ሰብርሽ ከአላህ ጋር የሚያቆራኝሽ የኢማን ጉዞ የህይወትሽ ጋሻ ይሁን።
📚 ⑥ ዕውቀትን መማርን በጭራሽ አትተዪ፤ ዕውቀት የሴትን ክብር ያሳድጋል
እህቴ፣ የሚያምር ፊት ይለወጣል፤ የውጭ ውበት ይደበዝዛል።
ዕውቀት ግን ሲጨምር ዋጋው ይጨምራል።
የዲን ዕውቀት ፈልጊ።
ቁርአን በደንብ ቅሪ ተማሪ።
ሱናን አጥብቀሽ ያዥ እወቂ።
ዐቂዳሽን በደንብ አጠናክሪ።
ሥነ-ምግባርሽን አሳምሪ።
አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሏልና፦
﴿قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الَّذِينَ يَعْلَمُونَ وَالَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ﴾
“እውቀት ያላቸውና እውቀት የሌላቸው እኩል ናቸውን?”📖 አዝ-ዙመር፡ 9
🌷 ⑦ ጀግናዬ ልብሽን ከሰዎች ጉዳት ጠብቂ፤ ግን ልብሽን ጨካኝ አታድርጊው
እህቴ፣ ሰዎች አንድ ጊዜ ስላሳዘኑሽ ሁሉንም ሰው አትጥሊ።
ሰውን መውደድ ይቻላል፤ ግን ጥበብ መሆነሰ ያስፈልጋል።
ሰውን ማመን ይቻላል፤ ግን በደንብ መተዋወቅ ያስፈልጋል።
ለሰው መልካም መሆን ይቻላል፤ ግን ድንበር ማወቅ ያስፈልጋል።
ልብሽ ንጹሕ ይሁን፤ አእምሮሽ ግን ንቁ ይሁን።
🌙 ⑧ በሰዎች ስትጎጂ ተስፋ አትቁረጭ ይልቁንም ወደ አላህ ተጠጊ
እህቴ፣ አንድ ቀን ሰዎች ሁሉ ቢርቁሽም፣ አላህ አይርቅሽም ካንች ጋር ነው።
በሌሊት ሰግጂ እጅሽን አንስተሽ ዱዓ አድርጊ።
ቁርአን አንብቢ በሱም ቀልብሽን አረጋጊ።
ላነሰችም ለእህት ለወንድሞችሽም ዱዓ አድርጊ ።
የልብሽን ሁሉ ለአላህ ንገሪው።
ሰዎች በራቸውን ሲዘጉብሽ የአላህ በር ክፍት መሆኑን ሁሌም እንዳትረሺ።
አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፦
﴿أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ﴾
“ንቁ! የልቦች መረጋጋት አላህን ማስታወስ ነው።”📖 አር-ረዕድ፡ 28
🌹 ⑨ ራስሽን አክብሪ፤ ለሚያዋርዱሽ ሰዎች ራስሽን ዝቅ አድርገሽ አትስጪ
እህቴ፣ ለሰው ያለሽን ፍቅር እንዳያዋርድሽ።
አንድ ሰው ካላከበረሽ ደጋግመሽ ክብር እንዲሰጥሽ አትለምኚው።
አንድ ሰው ዋጋሽን ካልተረዳ ዋጋሽን ለማሳየት ሕይወትሽን ጊዜሽን አታባክኚ።
የአንቺ ዋጋ አንድ ሰው በሚሰጥሽ ትኩረት አይወሰንም።
አላህ ካከበረሽ በቂ ነውና አላህ ዘንድ የተከበረች እንስት ለመሆን ጣሪ።
🌺 ⑩ እህቴ… ሁሉ ነገር በጊዜው ይመጣልና በትዕግስት ጠብቂ
የምትመኚው ሊዘገይ ይችላል።
የምትፈልጊው ካንች ሊርቅ ይችላል።
የምትጠብቂው ሰው ሊዘገይ ይችላል።
ግን በምንም ሁኔታ ላይ ሁነሽ አላህን አትርሺ።
የአላህ ጊዜ ከእኛ ጊዜ የተሻለ ነው።
አንዳንድ ጊዜ “አሁን” ብለን የምንፈልገው ነገር፣ አላህ በእውቀቱ “በኋላ” ይለዋል።
ስለዚህ አትቸኩዪ፤ በአላህ ተመኪ፣ ታገሺ፣ ዱዓ አድርጊ።
🌿 እናም ጀግናዬ አንድ ቀን…
አንድ ቀን ወደ ኋላ ተመልሰሽ ስታዪ፣ ያለፍሽባቸውን ብዙ ነገሮች ትረዳቸዋለሽ።
የያሳዘነሽን ሰው፣ ያስለቀሰሽን ቀን፣ የዘገየውን ምኞት፣ የተዘጋውን በር…
እና ምናልባት በዚያን ጊዜ እንዲህ ትያለሽ፦
“አላህ ያደረገው ሁሉ በእውነት ለኔ የተሻለ ነበር።” ብለሽ ፈገግ የምትይበት ጊዜ ይመጣል።
ስለዚህ ጀግናዋ እህቴ…
ራስሽን ጠብቂ።
ልብሽን ጠብቂ።
ከአላህ ጋር ያለሽን ግንኙነት አጠናክሪ።
ዕውቀትን በቅሰምን አትተዪ።
ሰብርን ማድረግን አትርሺ።
ማንነትሽን ለማንም ብለሽ አትቀይሪ።
እና የሰዎች አመለካከት የሕይወትሽ መሪ እንዲሆን በጭራሽ አትፍቀጂ።
🌷 አንቺ የነገ ተስፋ ብቻ አይደለሽም፤ ዛሬም በአላህ ፊት የምትጠበቅ አማኝ ነሽ።
አላህ ልብሽን በኢማን ያብራልሽ፣ በሰብር ያጠናልሽ፣ በዕውቀት ያሳድግልሽ፣ በመልካም ሥነ-ምግባር ያስውብልሽ፣ ከሚጎዱሽም ይጠብቅሽ።
ለልብሽ የሚሆኑ መልካም ሰዎችን ይስጥሽ፣ የሚጠቅሙሽን ዕውቀት ይስጥሽ፣ በዱንያ ሰላምንና በአኺራ ጀነተል-ፊርደውስን ይወፍቅልሽ። 🌿
✍️ ከወንድማችሁ አቡ ሒበቲላህ ሁሰይን
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiyየልባችሁ ደርሶ፣አላህኮ ያንን ነገር አሳካልኝ! የምትሉበትን የደስታ ጊዜ አላህ ያቅርብላችሁ፤ ምኞታችሁንም ሁሉ ይሙላላችሁ።
🕌ለደቡብ ወሎ 5 መስጅዶች 5 ኡስታዞችን እንፈልጋለን 🕌
መስፈርት
1ኛ👉 ቁርአንና ሃድስን በአዱኒያ እያሉ በጀነት በተመሰከረላቼው ደጋግ ቀደምቶች (በሰለፎች) አረዳድ የሚረዳ
2ኛ 👉 ከየትኛውም ጀመዓ አፍካር የፀዳ
3ኛ👉ኢጃዛ ማቅረብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል
4ኛ👉 ከአሁን በፊት ልምድ ያላቼው ቢሆን ቅድሚያ ይሰጣቼዋል
5ኛ 👉 ደመወዝ በስምምነት
0933519871
@Jemalendro33
https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/16523
አብዝተህ ስራ ግን አብዝተህ አታዉራ #ስለዚህ ወንድ ልጅ ጥገኝነትን እንጅ ብቸኝነትን አይፈራም።
🌿 ሌሎች ወንድም እህቶችህን ለማቆሸሽ ስትሞክር፣ ራስህን ታቆሽሻለህ
📍ሰውን ጭቃ ቀብተህ ለማቆሸሽ ጭቃ ስትቆነጥር፣ ምንም እንኳን ዓላማህ ሌላውን ማቆሸሽ ቢሆንም፣ መጀመሪያ የሚቆሽሸው የራስህ እጅ ነው።
ሕይወትም እንዲሁ ነው። ሌላን ሰው በሐሜት፣ በስድብ፣ በሐሰት፣ በማዋረድ ወይም በማጥላላት ለማሳነስ የሚሞክር ሰው፣ ሌላውን ከማሳነሱ በፊት የራሱን ልብ፣ ምላሱንና አክላቁን ያቆሽሻል።
አላህ سبحانه وتعالى የሐሜትን አስከፊነት ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦
﴿وَلَا يَغْتَبْ بَعْضُكُمْ بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَنْ يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ﴾እንዲሁም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ فَلْيَقُلْ خَيْرًا أَوْ لِيَصْمُتْ»📍ስለዚህ የሌላውን ጉድለት ለማውራት ምላስህን ከመክፈትህ በፊት፣ የራስህን ጉድለት አስብ። የሌላውን ክብር ለማፍረስ ከመሞከርህ በፊት፣ የራስህን የስራ መዝገብ አስብ። አንድ ሰው ስለ ሌላው መጥፎ ነገር ሲናገር፣ የሚያሳየው የሌላውን ብቻ ሳይሆን የራሱን የልብ ሁኔታም ነው። ስለዚህ የሙስሊም መንገድ ሌላውን ማዋረድ ሳይሆን መሸፈን፣ ማሳነስ ሳይሆን ማስተካከል፣ ማጥላላት ሳይሆን መምከር ነው። ሌላውን ለማቆሸሽ ጭቃ አትቆንጥር፤ እጅህን አንጻ። ሌላውን ለማሳነስ ቃል አትፈልግ፤ ምላስህን ጠብቅ። ሌላውን ለማዋረድ ምክንያት አትፈልግ፤ ራስህን ለማሻሻል ምክንያት ፈልግ። 🌿 የሌሎች ወንድሞችህን ክብር በመጠበቅህ የራስህን ክብር ትጠብቃለህ፤ ሌሎች ወንድሞችህን ከማቆሸሽ በመቆጠብህ ራስህን ታስከብራለህ። አላህ ልባችንን ከጥላቻና ከቂም፣ ምላሳችንን ከሐሜትና ከሐሰት፣ አክላቃችንንም ከክፋት ይጠብቅልን። አሚን። ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba
Repost from አል ፈላሕ ቢ-ተውሒድ (ቢንት ጀማል) ቻናል
💎በባህር ላይ እየሰመጠ ያለ ሰው ዱዓ ሲያደርግ አይተህ ታውቃላችሁ?!
ከአላህ ውጪ ሌላ ተስፋ ቀልቡ ውስጥ ሳይኖር! በእንዲህ አይነት ዱዓ ብቻ ለችግራችን መፍትሄ ለበሽታችን ፈውስ እናገኛለን!
ጌታችሁም አለ፡-
ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁ፡፡" (40፥60)📖
https://t.me/AlFalah_BiTawheed
https://t.me/AlFalah_BiTawheed
Repost from Abu Hayder Aliy
﴿ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَاأَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا (٥٦) ﴾[سورة الأحزاب - الآية ٥٦]
التفسير :
(٥٦) : إن الله يثني عند ملائكته على الرسول محمد صلى الله عليه وسلم، وملائكته يدعون له، يا أيها الذين آمنوا بالله وعملوا بما شرع لعباده، صلوا على الرسول وسلموا عليه تسليمًا.
https://t.me/abu_hayder_aliy
ሰለፊ የሆነ አካል ለሰዎች የሚያሰራጨውን ነገር ሊጠነቀቅ ይገባል። የቢድዓ ባለቤቶችን ቂርዓት፣ ትምህርት ወይም ቻነል ማስተዋወቅና ማሰራጨት ሰዎች ወደ እነርሱ እንዲገቡ፤የተሳሳተ አቂዳና መንሐጅ እንዲወስዱ በር ሊከፍት ይችላል።
ስለዚህ ሰለፊ የሆነ አካል ሰለፊ የሆኑ መሻይኾችን፣ኡስታዞችን ፣ዳዒዎችን ያስተዋውቃል። ሰዎችም ወደ ተሳሳተ መንገድ እንደይገቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ ሲገባ በየ ሚድያ አውታሮቹ የሙኻሊፎችን ፣ድምፅ፣ቪድዎ፣ኦዲዮ፣ቻነል በሆነ ባልሆነ ምክንያት ላይክ እና ሼር ሊያደርግ አይገባም። የሚያሰራጨው ነገር ለራሱም ሆነ ለሌሎች አካላት አማና መሆኑን ሊውቅና ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።
አንተ ሱና ላይ ደፋ ቀና የምትል ሱና ወዳድ ወንድሜ ሆይ “የምታሰራጨውን አረጋግጥ፤ ለሰዎች ሐቅን አስተላልፍ፣ ለራስህም ሆነ ለሌሎች ወደ ጥመት የሚያደርስን በር በሙሉ ዝጋው።
አንሷር ሙሐመድhttps://t.me/ansuar_muhammed_0088
እህቶቻችንን ለማነው የምንተዋቸው?
~
"ባለ ዲኗን ምረጥ" የተባለው እንዲተገበር እንጂ ወሬ ለማሳመር አይደለም። ነፍስያህን እያስቀደምክ በሰንካላ ምክንያቶች ለመሸፋፈን አትሞከር። ባለ ዲኗ እህትህን ለመጥፎ ምርጫ እየገፋህ፣ አልባሌ ቦታ ላይ ስትወድቅ ጠብቀህ ጭንቅላትህን ብትነቀንቅ ምን ትርጉም አለው?!
ወንድሜ ነብያዊው ምክር ዋጋ ይሰጠው። "ባለ ዲኗን ምረጥ።" ትርጉሙና ዋጋው ብዙ ነውና። ይህንን ስታደርግ ለራስህም፣ ለልጆችህም፣ ለምታገባት እህትህም፣ ለማህበረሰብህም ትልቅ ውለታ እየዋልክ እንደሆነ እወቅ።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 20/2012)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
