fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

رفتن به کانال در Telegram

ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
323
مشترکین
+124 ساعت
-77 روز
+5830 روز
آرشیو پست ها
What legacy will you leave for the next generation? ​We live on this earth for only a short span of time. Days pass by and years replace one another; in the end, however, our history is measured not by the length of time we lived, but by the good footprint we planted and the positive impact we left behind. ​Take a moment to stop and ask yourself: “If I were to depart from this world today, what did the generation gain because of me?” ​Every single minute you live today is the foundation of tomorrow's history. Even if your name fades from the face of the earth, the good work you have done will remain alive in the hearts of people. ​Therefore, arise today! Let your life be a launching pad for others, and your story a lesson for generations to come! http://t.me/eqrai_jemea

~ ሸይኹ አለቀሱ! ምን ያስለቀሳቸው ይመስለሃል ሐቢቢ? ያንተና የኔ በፊትና ላይ መውደቅ ብሎም የእለት ከእለት ተግባራችን አመፅ መሆኑ ነው ያስለቀሳቸው። አንተና እኔ ግን ልባችን እጅጉን ከመቆሸሹ የተነሳ በወንጀላችን ማልቀስ ቀርቶ ሲራጥን ያለፍንና የጀነት ካርድ የተሰጠን ይመስል ጧት ማታ በሐራም ተዘፍቀን ሳለ መሳቅ ሁኗል ስራችን። አላህ ይዘንልን ብቻ። ወጣቱን ሁሉ አላህ ልቦናውን ይመልሰው። √ ሸይኽ ዓብዱረዛቅ አል'በድር -ሐፊዘሁላህ- ባያያዝኩት የድምፅ ፋይል እንዲህ ይላሉ፦ «ዛሬ ላይ በወንጀል እየተሰቃዩ ያሉ የዘመናችን ወጣቶች ከዚህ በፊት ታይተው የማይታወቁ ብዙ የፊትና በሮች ተከፍተውባቸዋል። በጣም አደገኛ በሮች ተከፍተውባቸዋል። እነዚህ ወጣቶች የሚያዝንላቸውና የሚራራላቸው እንደዚሁም አላህ ተውበት እንዲሰጣቸው፣ ልቦናቸውን እንዲያቀናው፣ ከፊትናዎች እንዲያዞራቸው፣ ከነፍሳቸውና ከሸይጧን ተንኮል እንዲጠብቃቸው ዱዓእ የሚያደርግላቸው ሰው ያስፈልጋቸዋል። የሚያዝንላቸው፣ የሚራራላቸው፣ እዝነት በተሞላበት መልኩ ወደ ኸይር የሚጠራቸው ያስፈልጋቸዋል።» = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

🎁አድስ የኪታብ ደርስ! - 💍 ወጣቱን ከፈተና ታድጎ ወደ ሐላል ጎጆ የሚያመላክት፣ ከትዳር ማሰብ ጀምሮ እስከ ስኬታማ የትዳር ሕይወት መመሪያ የሚሰጥ ድንቅና አጭር የኪታብ ትምህርት፦ 📚የኪታቡ ስ
🎁አድስ የኪታብ ደርስ! - 💍 ወጣቱን ከፈተና ታድጎ ወደ ሐላል ጎጆ የሚያመላክት፣ ከትዳር ማሰብ ጀምሮ እስከ ስኬታማ የትዳር ሕይወት መመሪያ የሚሰጥ ድንቅና አጭር የኪታብ ትምህርት፦ 📚የኪታቡ ስም - 📖 «رسائل للمقبلين على الزواج» ❝ምክር ወደ ትዳር ዓለም ለመግባት ላሰቡ❞ 🎙አቅራቢ፦ አቡ ሱፍያን 🗓የሚጀመረው፦ ጁሙዓ • መስከረም 29 ⏰ሰዓት፦ ዘወትር ጁሙዓ እና እሁድ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ ➖የሚቀርበው፦ በ«ስለ ቀልባችን» የቴሌ ግራም ቻናል ቀጥታ ስርጭት(Live)-🫴 https://t.me/Sle_qelbachn1 https://t.me/Sle_qelbachn1 ⭕️ ላላገባችሁትም በትዳር ውስጥ ላላችሁም እጅግ ወሳኝ የሆነ ኪታብ ነው!

📚የኪታቡ PDF - ይህ ነው! 📖 «رسائل للمقبلين على الزواج» ❝ምክር ወደ ትዳር ዓለም ለመግባት ላሰቡ❞

"ኢሬቻ ባህል እንጂ ሃይማኖት አይደለም" የሚሉ ሙስሊሞችን ማየት በጣም ልብ የሚያደማ ነው።❗️ ከላይ ሃለውን ቪዲዮ ተመልከቱ ለዛፉ ሲሰግዱ!  ተመልከቱ የሚሰሩትን።❗️ 🩸ሙስሊም ወንድምና እህቶቸ ሆይ❗️ የብሄር አጀንዳ አቅላችንን አስቶ ጀሃነም እንዳይከተን እንጠንቀቅ። አላህን እንፍራ።!! መስቀልን የምንቃወመው የአማራ ስለሆነ አይደለም።የኩፍር በአል ስለሆነ እንጂ።! ኢሬቻ የኦሮሞ ስለሆነ በተለየ አይን አናየውም። የኩፍር ቡላና ዳለቻ የለውም። ሁሉም ኩፍር ነው። ሁሉም የጣኦት አምልኮ ነው። ሁሉም ተውሒድን በጥብቅ ከሚያስተምረው ኢስላም ጋር ፈፅሞ የሚፃረር ነው። ሁለቱም ከኢስላም ጠርጎ የሚያስወጣ የለየለት ክህደት ነው። ዛሬ የብሄር አጀንዳ እራሱን የቻለ ጣኦት ሆኗል። ሰዎች ለብሄር ሲሉ ካፊርን ይወዳሉ። ሙስሊምን ይጠላሉ። ለብሄር ሲሉ ለመስቀል፣ ለኢሬቻ ወግነው ይሟገታሉ። የኩፍር በአል ያከብራሉ። የሚያሳፍረው ሸይኾችና ዱዓቶች ጭምር በዘረኝነት መለከፋቸው ነው። እስኪ የመስጂድ ኢማም ሆኖ፣ ጥምጣም ጠምጥሞ የኦርቶዶክስ ሰልፍ የሚያደምቅ፣ በዘራቸው የተነሳ ሙስሊም ትግሬዎችን ጭምር የሚያጥላላ፣ ለኢሬቻ "የእንኳን አደረሳችሁ" መልእክት የሚያስተላልፍን ልክፍተኛ አስቡ። ዘረኝነት አደዛዥ እፅ ነው።❗️ በዚህ በሽታ የተለከፈ ሰው እይታው ጠባብ ነው። አርቆ ማሰብ አይችልም። ይህንን ሀሺሽ፣ ይህንን ጣኦት አጥብቀን ካልተዋጋነው ብዙ ነገር ያሳጣናል።❗️ ያ'ያያዝኩት ቪዲዮ ኢሬቻ የሚያከብሩ ሰዎችን ድርጊት ነው። 🩸ሁላችንም ሼር እናድርገው ሼር ሼር ሼር❗️ የተወሰደ

ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ። ከጀነት በሮች ውስጥ ፆመኞች ብቻ የሚገቡበት ልዩ በር ረያን ይባላል ።

°• 🌻
اترك همك لله 🎙 الشيخ عبد الرزاق البدر حفظه الله

እማዬ ግፉን ችለህ ተማር ብላሀለች እሽ!? "እንዲህም ይጠናል" ============== የኔ ቤት አንተ ነህ እኔ እቤት አልገባም፡ ተማር ያልፍልናል አጥና የኔ ልባም፡ እናትህ እያለሁ ልጄማ አታነባም፡
እማዬ ግፉን ችለህ ተማር ብላሀለች እሽ!? "እንዲህም ይጠናል" ============== የኔ ቤት አንተ ነህ እኔ እቤት አልገባም፡ ተማር ያልፍልናል አጥና የኔ ልባም፡ እናትህ እያለሁ ልጄማ አታነባም፡ በችግሮች መሃል፤ ፅኑና ታታሪ ጀግና እናት ስትኖርህ፡ ከቆራጥነት ጋር፤ ተስፋ እያሳየች ነው የምታስተምርህ፡ ህይወት ካዋሳት ህግ፤ የሆነችውን ነው ለልጇ እምትነግርህ!! ....ይህችን ጀግና አየሀት...!? ....ምክሯንስ ሰማሀት....!? ...አስተውለሀል ወይ ያላትን ብልሀት..!? ...ደርባባ እናትህን እንደት አገኘሀት..እ..!? ይህች ሚስኪን እናት፤ ጎዳና ዳር ሆና በቆሎ እየሸጠች፡ በሀሳብ ጥላ ስር፤ ኑሮን ለማሸነፍ እንደተቀመጠች፡ በጨለመ ጊዜ፤ በእጇ ትንሽ ባትሪ ይዛ እንደጨበጠች፡ በወኔ ተሞልታ፤ እማዬ ለልጇ ይህን ተስፋ ሰጠች፡ ስማማ የኔ ውድ፤ በርታ ብለህ ተማር ልጄ እንዳትከፋ፡ ፅና ልክ እንደኔ፤ ብቻ ለስኬትህ አንብብ አጥና ልፋ፡ በዚህች በኛ ሐገር... እንደያዝኩት መብራት ጭላንጭል ነው ተስፋ። ስለዚህ የኔ ልጅ፤ ችግሮችን አልፈህ ደምቀህ እንድታብብ፡ እኔም ባንተ ስኬት፤ እንባየን እንዳብስ ዛሬ በባትሪ አንብብ፡ ጠንክርልኝ ልጄ፤ በየጎዳናው ላይ መኪና አትመልከት፡ እኔን ብቻ ስማኝ፤ አታስተውል ሌላ አልባሌ ስብከት፡ ከእኩዮችህ ጋራ፤ አትራጭም ውሀ አታጋጭም ቆርኪ፡ ሳትከፋ ስማኝ፤ ከሀብታም ልጆች ጋር የለህም ንክኪ፡ አትራቅ ከጎኔ፤ እኔ ባትሪ ልያዝ አንተም አንብብ እስኪ፡ ይገባኛል ልጄ፤ የጓደኞችህ ድምፅ ያጓጓል ያስቀናል፡ እኔም ይቆጨኛል፤ አቅማችን ይችናት ታዲያ እንደት ይሆናል፡ አይዞህ ህልም ካለ፤ ከጎዳናው ዳር ላይ እንዲህም ያጠናል፡ 👉..በርታ ልጄ...አይዞህ...!! .....በኑረዲን አል-አረብ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

ሰላም ለእነዛ ለአይናችን እሩቅ ለልባችን_ግን_እጅግ ቅርብ ለሆኑት ለአላህ ብለን ለምንወዳቸው ለአላህ ብለው ለሚወዱን በተውሂድ መንገድ ላስተሳሰረን 💧    የሰው ልጅ ለአላህ ብሎ ከተዋደደ የአገር እሩቅ በጫራሽ የልብን ፍቅር አይቀንሰውም ብቻ እኛ ንያችንን እናስተካክል ። የአላህ ሰላምእና እዝነት አይለያችሁ http://t.me/Asselefya2

ማን እንደ እናት! ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: አንድ ሰው ወደ አላህ መልእክተኛ (ﷺ) ዘንድ መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ ﴿يا رَسولَ اللَّهِ، مَن أحَقُّ النّاسِ بحُسْنِ صَحابَتِي؟ قالَ: أُمُّكَ، قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أُمُّكَ، قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أُمُّكَ، قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أبُوكَ﴾ “አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ማነው ለኔ ከሰዎች ጥሩና እውነተኛ ወዳጅ አድርጌ ልይዘው የሚገባ?  “እናትህን” አሉት። ከዛስ በመቀጠል አላቸው: “እናትህን” አሉት። ከዛስ በመቀጠል አላቸው:  “እናትህን” አሉት። ከዛስ በመቀጠል አላቸው:  “አባትህን” አሉት።” 📚 ቡኻሪ (5971) ሙስሊም (2548) ዘግበውታል ©

ከአገር መፍረስ ባሻገር ~ አገር እንድትፈርስ የሚመኙ፣ አገር ለማፍረስ የሚጥሩ፣ ለአገር አፍራሾች ድጋፍ የሚሰጡ ብዙ ሰዎች አሉ። ወንድሜ ሆይ! እውነት በሃገር መፍረስ የምታተርፍ መስሎህ ነው? ለመሆኑ አገር ሲፈርስ ምን ምን ሊከሰት እንደሚችል አሻግረህ ተመልክተሃል? ወይስ በሆኑ አካላት ላይ ያለህ ጥላቻና ቁጭት በሩቅ እንዳትመለከት ሸፍኖብሃል? ወንድሜ አገር ዳቦ አይደለም ፤ እንደዋዛ ቆራርሰህ በመካፈል አትገላገልም። * ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ይፈናቀላሉ። እንኳን አገር ፈርሶ በብሄር ግጭትና ጥቃት ብቻ የሚሊዮኖች ህይወት ተመሰቃቅሏል። ምናልባት አንተ ከሚፈናቀሉት ባትሆን እንኳ ራስህን በነሱ ጫማ ላይ አድርገህ ተመልከት። * ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ትዳር ይፈርሳል። ከሌላ ብሄር ጋር የተጋቡ ወገኖቻችን እጅግ ብዙ ናቸው። ይሄ ዘር እየለየ የሚገድል ትውልድ የሚተዋቸው እንዳይመስልህ። ስንት ቤተሰብ እንደሚበተን ተመልከት። * ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ንብረት ይወረሳል። እንኳን አገር ፈርሶ ሰላም በመጥፋቱ ብቻ የስንቱ ምስኪን ንብረት በተለያዩ ክልሎች በጉልበተኛ ተነጥቋል! * ሃገር ሲፈርስ እዚያም እዚህም መቋጫ የሌለው የድንበር ግጭት ይነሳል። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው በሶማሊና በኦሮሞ የድንበር ግጭት ከሚሊየን በላይ ህዝብ የተፈናቀለው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው አፋርና ዒሳ በየጊዜው የሚጋደለው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው ዘጠኝ መቶ ሺ አካባቢ የጌዲዎ ህዝብ የተፈናቀለው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው የወሎ ኦሮሞና የሸዋ አማራ የሚጋጨው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው በደቡብ ክልል የተለያዩ ህዝቦች መካከል ግጭት የሚቀሰቀሰው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው "ወሎ ኦሮሞ ነው"፣ "ወልቃይት፣ ደራ፣ በረራ፣ መተከል አማራ ነው" የሚል ጩኸት የምንሰማው፡፡ ሃገር ከፈረሰ እነዚህ ጩኸቶች ዛሬ ከምናየው በላይ ሚሊዮኖችን የሚበላ እሳት ይቀሰቅሳሉ። * ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ነፍስ ይጠፋል። ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ መጨረሻቸው እልቂት ነው። * ምናልባት መልኩ ይቀየር ካልሆነ በስተቀር በሃገር መፍረስ ጭቆና የሚቀር፣ ለድሃ ቀን የሚወጣ እንዳይመስልህ። ወላሂ! ዘር እየለየ፣ ሃይማኖት እየመረጠ በሚገድል ቡድን፣ ከርሱን በሚያስቀድም ፖለቲከኛ መቼም ፍትህና ነፃነት አታገኝም። የሚሻለው በጋራ ለሰላምና ለፍትህ መጣር ነው። መፍትሄው እንደ ህዝብ ከገጠመን የስነ ምግባር ዝቅጠት ለመውጣት ተባብሮ መሥራት ነው። ችግራችን ስር የሰደደ ነው። ችግራችን በማህበረሰብ ደረጃ የተንሰራፋ ነው። ስለ መንግስት ችግር ጧት ማታ ማውራቱን እንደ ንቃት ቆጥረን እራሳችንን እየሸወድን እንጂ እንደ ህዝብ መተዛዘናችን ሳስቶ መጨካከን ነግሶብናልኮ። ~ በየገበያው የሚያጭበረብረው፣ በየተቋሙ ህዝብ የሚያጉላላው፣ ... ሁሉ ምንም ስቅ ሳይለው ስለ ፍትህ እየወሸከተ ነው። ~ ለብዙዎች ከትምህርት ገበታ መራቅ ሰበብ የሚሆነው፣ ዘርና ሃይማኖት እየለየ ተማሪዎቹን የሚያከላፍተው አስተማሪ ምንም ሳያፍር ስለ ፍትህና ርትእ እየጮኸ ነው። ~ ታካሚዎቹን ፊቱን አጨፍግጎ የሚያስተናግደው፣ በግዴለሽነት የሰው ነፍስ ላይ የሚቀልደው፣ ለርካሽ ጥቅም ሲል የማይገናኝ ምርመራ እያዘዘ ደካማ ወገኑ ላይ ጭካኔ የሚፈፅመው ሃኪም እኮ ነው ስለ ፍትህ የሚጮኸው! ~ የተበላሸ ምግብ፣ ጊዜው ያለፈበት መድሃኒት፣ ፎርጂድ እቃ፣ የተጭበረበረ ምርት፣ ... የሚሸጠው ነጋዴ እኮ ነው "መስራት አቃተን" እያለ የሚያለቅሰው። ~ ፍትህ በገንዘብ የሚሸጠው፣ ከሌባ ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራው፣ እምነትና ብሄር እየመረጠ ፍትህ የሚቀብረው ዳኛና ፖሊስ እኮ ነው ስለ ፍትህ የሚዘፍነው። ~ ሚሊዮኖች የወጡበትን መሬት ሶስት አራት ካርታ ሰርቶ የሚቸበችበው ሰራተኛ፣ የሚሊዮኖችን ውሃና መብራት እየቆረጠ ሺ ጊዜ ብር  እየተቀበለ የሚቀጥለው ሌባ እኮ ነው ስለ ፍትህና ስለ ነፃነት የሚለፍፈው። ~ መንገዶችንና ህዝባዊ ተቋማትን ከደረጃ በታች እየሰራ በሀገር በወገኑ ላይ የሚቆምረው እኮ ነው ለሀገር ለወገኑ ተቆርቋሪ መስሎ የሚፈተፈተው። ~ መኪናና ሞተር ሳይክል አዘጋጃቶ፣ አንድ ላምስት ተደራጅቶ የሚዘርፈው፣ ህፃናት እያፈነ የሚወስደውኮ ነው እኩል ስለ ፍትህ የሚያወራው! ~ የሁለት ቀን ጨቅላ፣ የ70 አመት አዛውንት፣ አቅመ ደካማ ሴቶችን ሳይቀር የሚገድለው እኮ ነው የነፃነት ታጋይ የሚባለው። እስኪ በየትኛው ዘርፍ ነው የሚነሳ ጥሩ ነገር ያለን? ፖለቲከኞቹ የኛው ነፀብራቆች ናቸው። እኛኑ ነው የሚመስሉት። ከኛው የወጡ እንጂ ከሌላ ፕላኔት የመጡ አይደሉም። ክፋታቸው ክፍታችን፣ ንቅዘታቸው ንቅዘታችን ነው። እንደ ህዝብ በዚህ ደረጃ መልካሞች የመነመኑ ከሆኑ እንዴት ነው ፍትህና እፎይታ የምናገኘው? በቅድሚያ በራሳችን ላይ ሰፊ ስራ መስራት ይጠበቅብናል። ወደተነሳሁበት ስመለስ፣ ስግብግብ ስሜታችን እየጋረደን፣ ቁንፅል አመልካከታችን እየሸወደን እንጂ በርግጠኝነት በሃገር መፍረስ እንደ ህዝብ ከሳሪዎች እንጂ አትራፊዎች አይደለንም። ስለዚህ ደግመን ደጋግመን ልንመለከት፣ ከጥፋት ልንርቅ፣ ለአጥፊዎች ጉልበት ከመሆንም ልንጠነቀቅ ይገባል። ጥፋትን ማስቆም ባንችል እንኳ ቢያንስ ተጋሪ ባለመሆን የራሳችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል። = https://t.me/IbnuMunewor

የማለዳ መልእክት (50) ~ በሞት የተለዩ ወላጆቻችሁን በዱዓችሁ አትርሱ። ከቻላችሁ በሶደቃ አስታውሷቸው፤ በተለይም አገልግሎቱ የሚቆይ የሆነ ሶደቃ ቢሆን ተመራጭ ነው። ለምሳሌ አጅሩን ለነሱ በማሰብ
የማለዳ መልእክት (50) ~ በሞት የተለዩ ወላጆቻችሁን በዱዓችሁ አትርሱ። ከቻላችሁ በሶደቃ አስታውሷቸው፤ በተለይም አገልግሎቱ የሚቆይ የሆነ ሶደቃ ቢሆን ተመራጭ ነው። ለምሳሌ አጅሩን ለነሱ በማሰብ የመስጂድ ግንባታ ላይ መሳተፍ፣ ውሃ ማውጣት፣ የደዕዋ ስራን ማገዝ፣ የወቅፍ አገልግሎት፣ ወዘተ. (ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 20/1448) = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

የሉምዐቱል ኢዕቲቃድ ደርስ ተጠናቋል፣ አልሐምዱሊላህ። ~ የኪታቡ ፒዲኤፍ ፋይል፦ https://t.me/IbnuMunewor/9934 ክፍል 1↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9938 ክፍል 2↓
የሉምዐቱል ኢዕቲቃድ ደርስ ተጠናቋል፣ አልሐምዱሊላህ። ~ የኪታቡ ፒዲኤፍ ፋይል፦ https://t.me/IbnuMunewor/9934 ክፍል 1↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9938 ክፍል 2↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9943 ክፍል 3↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9954 ክፍል 4 ↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9991 ክፍል 5↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10000 ክፍል 6↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10005 ክፍል 7 ↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10033 ክፍል 8↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10041 ክፍል 9 ↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10051 ክፍል 10↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10124 ክፍል 11↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/10134 ክፍል 12 https://t.me/IbnuMunewor/10164 ክፍል 13 https://t.me/IbnuMunewor/10176 ክፍል 14 https://t.me/IbnuMunewor/10177 ክፍል 15 https://t.me/IbnuMunewor/10181 ክፍል 16 https://t.me/IbnuMunewor/10217

~ከሳዳት ተማሩ የሀበሻው ንጉስ ኡስታዝ ሳዳት ከማል መርሁ ወጥ ነው እውነት ያስቀድማል በዲን መዋሸትን በጥብቅ ይቃወማል ወቀሳን ሳይፈራ፣ ለዲን ዘብ ይቆማል የሽርክን ወረርሽኝ፣ በጥበብ ያክማል የቢድዓን ተውሳክ፣ በድፍረት ያርማል ውለታህ ብዙ ነው የተውሒዱ ጀግና የሱናው ነፀብራቅ፣ ስምህ ነው ገናና ድምፅህ ያስተጋባል በሁሉም ቀጠና ጠላት ያ ደ ን ቅ ሃ ል ወዳጅ  ይቅርና የኛ ቆራጥ ጀግና፣ ግልፅ ነው ቀመሩ እውነት አትደብቁ ውሸት አትቀባጥሩ በዲን ስም አትዋሹ ያለዒልም አታውሩ ሰዎች መንገድ ለቀው ውሸትን ካወሩ መልስ ይሰጣቸዋል ሳዳት መምህሩ አ ያ ስ ጨ ን ቀ ው ም  ሀገር እና ዘሩ ለ "ፍ ት ህ" መቆምን ከሳዳት ተማሩ = t.me/Abu_lmran_Alaseriy

ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ። የጀሀነም በር ጠባቂ መላዒካ ማሊክ ይባላል፡፡

ለአስተውሎት ~ ፉዶይል ብኑ ዒያድ አንዱን ሰው “እድሜህ ስንት ነው” ብለው ጠየቁት። * "ስልሳ አመት" አለ። - "ስልሳ አመት ሙሉ ወደ ጌታህ እየተጓዝክ ነው፡፡ መድረሻህ ሳይቃረብ አይቀርም።" * "ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!" (እኛ ለአላህ ነን፡፡ ወደሱም ተመላሾች ነን) - “ 'ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን' የሚለውን ተፍሲሩን ታውቃለህ? ለአላህ ባሪያ እንደሆነ ወደሱም ተመላሽ እንደሆነ የሚያውቅ እንደሚቆም ይወቅ፡፡ እንደሚቆም ያወቀ እንደሚጠየቅ ይወቅ፡፡ እንደሚጠየቅ ያወቀ መልስ ያዘጋጅ፡፡” * "ምንድን ነው መፍትሄው?" - "ቀላል ነው!" * "ምንድን ነው እሱ?" - "በቀረህ እድሜ መልካም ስራ፡፡ ያለፈው ይማርልሃል፡፡ ቀሪው እድሜህን ካጠፋህ ግን ባለፈውም በቀሪውም ትያዛለህ፡፡" ምንጭ፦ [ሒልየቱል አውሊያህ፡ 8/113] አስተውል። ስልሳ ዓመት ከደረስክም አስተውል። ስልሳ ካልደረስክም ገና ነኝ ብለህ አትዘናጋ ነቃ በል። (ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 20/2005) = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ድካምህ ምንም ያህል ቢበዛና ቢበረታብህም፤ በዚች በዱንያ እረፍትን መፈለግ የማይቻል ነገር መሆኑን አስታውስ። የዚህም ማስረጃ የፍጥረታት ሁሉ ሁኔታ በመሆኑ ተጨማሪ ንግግር አያስፈልገውም። ​በሕይወት ታሪክ ውስጥ፣ አእምሮ ከሌለው «እብድ» ሰው በቀር አንድም እረፍት ያገኘ ሰውን ማግኘት ከባድ ነው። ​ስለዚህ ችግሩና መከራው ምንም ያህል ቢጠናብህ ታገስ፣ ተጋደል፤ የስሜትህና የምኞትህ ባሪያ እንዳትሆን! በትዕግስት የሚገኝ ሕይወት ፍሬው ያማረ፣ ስሩም የጸና የበረታነውና።

ድካምህ ምንም ያህል ቢበዛና ቢበረታብህም፤ በዚች በዱንያ እረፍትን መፈለግ የማይቻል ነገር መሆኑን አስታውስ። የዚህም ማስረጃ የፍጥረታት ሁሉ ሁኔታ በመሆኑ ተጨማሪ ንግግር አያስፈልገውም። ​በሕይወት ታሪክ ውስጥ፣ አእምሮ ከሌለው «እብድ» ሰው በቀር አንድም እረፍት ያገኘ ሰውን ማግኘት ከባድ ነው። ​ስለዚህ ችግሩና መከራው ምንም ያህል ቢጠናብህ ታገስ፣ ተጋደል፤ የስሜትህና የምኞትህ ባሪያ እንዳትሆን! በትዕግስት የሚገኝ ሕይወት ፍሬው ያማረ፣ ስሩም የጸና የበረታነውና።

አሁንስ ማነው የግብፅ ተላላኪ የሆነው? ~ ሙርሲ ስልጣን የያዘ ሰሞን ነው። መካ ውስጥ ከአንድ ወዳጄ ጋር ታክሲ እየጠበቅን አንድ ግብፃዊ መጣ። በስልኩ የያዘውን ወሬ ሳያቋርጥ ወደየት እንደሆንን ጠየቀን። የሐጁ ግርግር ብዙም ስላላለፈ ከፍ ያለ ዋጋ ነገረን። ጓደኛዬ "20 ሪያል ይሆንሃል?" አለው። ወሬውን እንደቀጠለ እንድንገባ በእጁ ጠቆመን። ትንሽ እንደሄድን ስልኩን ሲጨርስ ደጋግሞ እየማለ እንደማያዋጣው ነገረን። ጓደኛዬ እላፊ ነገር መናገር ያዘ። "እናንተ ግብፆች ሌቦች ናችሁ" አለው። "ሌባው ሙርሲ ነው። ከናንተ መንግስት ጋር ተስማምቶ ናይልን እንድትገድቡ አደረጋችሁ" አለ። ገረመኝ። የሙርሲ እጅ ባይኖርበትም ምናልባት ባለማሰናከሉ እየወቀሰ መሰለኝ። ግብፃውያን ጋር ተገናኝታችሁ ኢትዮጵያውያን መሆናችሁን ካወቁ የናይል ጉዳይ መነሳቱ የሚጠበቅ ነው። የፖለቲካ መስመራቸው ቢለያይ እንኳ በብሄራዊ ጥቅማቸው አይደራደሩም። ለነሱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ ግድብ እንደ ሃገር ስጋታቸው ነው። በየጊዜው "ሁሉም አማራጭ ጠረጴዛ ላይ ነው" እያሉ በኃይል አማራጭ ሲያስፈራሩ ማየትና መስማት የተለመደ ነው። እንደ ህዝብ ያለንን መከፋፈል ጠንቅቀው ስለሚያውቁ በተደጋጋሚ ከታዋቂ ሰዎች እስከ ተርታው የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ የኢትዮጵያ አማፂ ሃይሎችን በማገዝ ሃገሪቱን መበታተን ይገባል እያሉ ሃሳብ ይሰጣሉ። የሰሞኑ ጦርነትም ለነሱ ሰርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል። ስለ ጦርነቱ የሚዘግቡና የሚተነትኑ የዐረብኛ ስራዎች ማህበራዊ ሚዲያውን አጥለቅልቀውታል። ጦርነቱ አዲስ አበባ እንደተቃረበ ሁሉ ሲፅፉ አይቻለሁ። ትንታኔያቸው እንዳለ መሬት ላይ ያለውን ሳይሆን ምኞታቸውን የሚያንፀባርቅ ነው። አብዛኞቹ በዚህ ጉዳይ ላይ የተጠመዱ የዓረብ ሚዲያዎች የተሳሳቱ ዘገባዎችንና ትንታኔዎችን ደጋግመው ቢያቀርቡም ምናልባት የስማቸው ጉዳይ አያሳስባቸው ይሆናል። የአልጀዚራ ተደጋጋሚ መዋሸት ግን ገርሞኛል። አልጀዚራ ትልቅ ስም እንዳለው የሚታወቅ ነው። ይህንን ስሙን በዋናነት ያገኘው በምዕራባውያን የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች ለዓለም እንዳይደርሱ የታፈኑ ድምፆችን በማስተጋባቱ ነው። ከመሆኑም ጋር እንደማንኛውም ሚዲያ የቆመለት ፖለቲካዊ ዝንባሌ አለውና መሳሳት ሳይሆን የታቀደባቸው ውሸቶችን ይዋሻል። ከጀርባ በምዕራባውያን ስውር እጆች ሲዘወር የነበረው እና "የዐረብ ፀደይ" (Arab Spring) የሚል የዳቦ ስም የተሰጠው ዓረቡን ዓለም በገዛ ልጆቹ የማፍረስ ሴራ በማቀጣጠል የጠላት መጠቀሚያ ሆኖ በግንባር ቀደምትነት ያገለገለው አልጀዚራ ነው። በዚያን ጊዜ ቤንዚን ነበር ሲያርከፈክፍ የነበረው። ተቃውሞዎችን ለማቀጣጠል ሀሰተኛ ዘገባዎችን ጭምር ያቀርብ፣ በሃሳብ የተለዩ ድምፆችን ደግሞ live ጭምር እያቋረጠ ያፍን ነበር። አንዴ ግብፅ ራቢዐተል ዐደዊያ አደባባይ ላይ በመንግስት የተጨፈ ^ ጨፉ ሰዎች በማለት በህይወት ያሉ ሰዎችን በከፈን ተጠቅልለው የሞቱ መስለው እንዲቀርቡ ያደረገበት አይረሳኝም። ብዙም ሳይቆይ ቪዲዮው እውነተኛ እንዳልሆነና ይልቁንም ሰዎቹ ለትወና ሲዘጋጁ እየተቀረፁ የሚያሳይ ምስል ወጥቶ ነበር፡፡ ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የአልጀዚራ የተለያዩ ድረ ገፆች ላይ የሚወጡ ዜናዎችም የተጋነኑ ብቻ ሳይሆኑ በቅጥፈት የታጨቁ ጭምር ናቸው። እንዳጠቃላይ የዐረብ ሚዲያዎች ሁኔታ የግብፅን የገዘፈ ተፅእኖ የሚያሳይ ነው። ግብፆች ከነ ፖለቲካ ልዩነታቸው ለሀገራቸው ጥቅም ያላቸው መዋደቅ የሚያደምም ቢሆንም የሚሄዱበት መንገድ ግን እኛን እንደ ህዝብም እንደ ሃገርም በሚጎዳን መልኩ መሆኑ ያሳምማል። በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ነው ጥቅማቸውን ማስከበር የሚፈልጉት። ተንታኞቻቸውና አክቲቪስቶቻቸው ይህንን በግላጭ ነው የሚያወሩት። ለፖለቲካ ጉጉት የለኝም። ፖለቲከኛም አልወድም። ነገር ግን የሃገር መፍረስ ለኛ የሚያመጣብን ጣጣ በጣም ያስጨንቀኛል። አላህ ይጠብቀን እንጂ ቢከሰት ብዙ የድንበርና የብሄር ግጭቶች ይከተላሉ። ዛሬ ካለው የባሰ እልቂትና መፈናቀል ያሰጋል። ያለንበትን ተጨባጭ እና የፖለቲካ ሃይሎችን ዓላማ ያጤነ ሰው ይህንን መረዳት አይከብደውም። በተወጠረች ሃገር ውስጥ ከዚህ ስጋት እሩቅ ነን የሚለው አያሳምነኝም። በተቃውሞው ጎራ ያሉ አካላት እና ደጋፊዎቻቸው የሚቃወማቸውን ለማሸማቀቅና ለማምታታት ቢሞክሩም ይሄ የብልፅግና ወይም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳይ አይደለም። "በሃገር ላይ ያሉ ውጥንቅጦችን በማጣቀስ "ከዚህ በላይ ምን ሊኖር?" በማለት አፍ ሊያስይዙ ይሞክራሉ። ከዚህ የባሰ ብዙ ነገር አለ። ማሰብ ያልፈለገ አይታየውም። ወይም ባ'ፉ እየደለለ ለራሱ ቡድናዊ ጥቅም በመታገል ሃገር በላያችን ላይ ሊያፈርስብን የሚታገል አካል ለአላማው እየሰራ ስለሆነ ምንም ቢል አይደንቅም። የሆነ ሆኖ ትናንት ሙስሊሙን "የግብፅ ተላላኪ" እያለ አፉን ሲከፍት የነበረ አካል፣ አፄ ዮሐንስ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የወሎ ሙስሊሞችን የፈጀው ለግብፃውያን በህቡእ እየሰሩ ስለ ነበረ ነው እያለ መርዘኛ ትንታኔ የሚሰጥ አካል እንዲሁም ከኛ ውጭ ለሃገር ታማኝ ላሳር እያለ የሚፎክረው አካል ዛሬ ላይ ሃገሪቱ መበታተን አለባት የሚሉ ሃይሎችን እቅድ ሊያሳካ እየተጋ ነው። እና ማነው የግብፅ ተላላኪ የሆነው? (ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 19/2019) = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor