የቀጠናው ተመልካች
رفتن به کانال در Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 295
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-217 روز
-9130 روز
آرشیو پست ها
4 292
🇮🇷⚡️🇺🇸 አሜሪካ ከኢራን ጋር ለ40 ቀናት በዘለቀው ጦርነት ቢያንስ 42 አውሮፕላኖችን አጥታለች - ኮንግረስ
ፔንታጎን እነዚህን የአቪዬሽን ንብረቶች እና የጦር መሳሪያዎች ለመተካት የሚያስፈልገው አጠቃላይ ወጪ በግምት 29 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ገምቷል።
4 292
🇷🇺 የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላደምር ፑቲን ለኦፊሴላዊ ጉብኝት በዚህ ሰዓት ቻይና ገብቷል።
ጉብኝቱ የትራምፕን የቻይና ጉብኝት ተከትሎ የመጣ ነው። ዩክሬን፣ ኢራን፣ ወታደራዊ ግንኙነት እና ኢኮኖሚ የጉብኝቱ ዋና አጀንዳ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
4 292
🇺🇸🇨🇺—አሜሪካ “የአሜሪካንን ብሔራዊ ደህንነት አደጋ ላይ ጥለዋል” ብላ በመክሰስ 11 የኩባ ባለስልጣናት እና 3 የመንግሥት አካላት ላይ ማዕቀብ ጥላለች።
**
በኩባ ላይ ላለፉት 50 ዓመታት ሙሉ የኢኮኖሚ ማዕቀብ አለ።
አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ሩቅ ምሥራቅ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ ኤስያ፣ መካከለኛው አሜሪካ፣ አፍሪካ፣ ላቲን አሜሪካ …አጠቃላዩ ዓለም የንግድም፣ የኢኮኖሚም፣ የፖለቲካም፣ የማሕበራዊ ግንኙነትም ከኩባ ጋር በዚህ ምክኒያት አያደርግም።
ኩባ የቀራት አንድ ወዳጅ ቬኔዝዌላ ነበር። ነፃ ነዳጅ ይሰጣቸዋል፣ በዚያ እያረሱ፣ እያመረቱ ይኖሩ ነበር። ከቬኔዝዌላ መወገድ በኋላ፣ የኩባ እንጀራ ተቆርጧል።
አሜሪካ ብቻዋን አውላላ ሜዳ ላይ አግኝታታለች።
ኩባ፣ በመጨረሻ ልትንበረከክ እና እጅ ልትሰጥ ጫፍ የደረሰች ይመስላል።
4 292
🇮🇱⚡🇱🇧 የእስራኤል የገንዘብ ሚንስቴር በዛሌል ስሞትሪች፡- "ሂዝቦላ እጅ የማይሰጥ ከሆነ ብዙ ብዙ ተጨማሪ የሊባኖስን መሬት መያዛችንን እንቀጥላለን።"
በትናንትናው ዕለት፣ የዓለም አቀፍ ወንጀለኛ ፍርድ ቤት፣ ሚስጥራዊ የእስራት ማዘዣ በሚንስትሩ ላይ 'በጋዛ ላይ ለፈፀመው ወንጀል' በሚል ክስ፣ እንዳወጣበት ተሰምቷል፣ እንደ ሮይተርስ ዘገባ።
ስሞትሪች በምልከታው እጅግ ቀኝ ዘመም ፖለቲከኛ ሲሆን የእስራኤል ድንበር ሙሉ ጋዛን ጨምሮ ደቡብ ሶሪያን እና ደቡብ ሊባኖስን እንዲሁም ጥንታዊ ይዞታዎቻችንን ማጠቃለል አለበት የሚል ነው።
4 292
— 🇺🇸/🇮🇷 የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ካዜም ጋሪባዲ፦
'አሜሪካ ለዲፕሎማሲ እድል እየሰጠች እንደሆነ ትናገራለች፣ ነገር ግን በተመሳሳይ ጊዜ በሌላ ጥቃት ታስፈራራለች።
እንድንሸነፍ ሊያደርጉን ይፈልጋሉ፣ ግን አይችሉም። መሸነፍ የለም።
ማጥቃት ይችላሉ፣ ያጥቁ። ወይ እኛ እናሸንፋለን፣ ወይም ሰማዕት እንሆናለን [ሁለቱም ድል ናቸው]።'
4 292
— 🇺🇸/🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ፦ 'ኢራን ስምምነት ለመፈጸም እየለመነችን ነው፣ ነገር ግን እንደገና አንድ ዙር ኃይለኛ ቅምሻ ማቅመስ ሊኖርብን ይችላል።'
4 292
🇺🇸'ሃይማኖት በአስደናቂ ሁኔታ ወደ ሀገራችን እየተመለሰ ነው' ትራምፕ
'ሃይማኖት ጥሩ ነገር ነው'
'ሀገራችን እያደገች እንዳለችው ሃይማኖትም እያደገ ነው'
'ሀገራችን የተመሠረተችው በሃይማኖት እና በሃይማኖተኞች ነው። በዚያ ኩራት ይሰማኛል። ሃይማኖት ሲኖር ወንጀል ይቀንሳል።
4 292
+1
—❗️🇦🇪/🇮🇶 ትኩስ፦ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ 6 ድሮኖችን በአየር መቃወሚያ መጣሉን አስታውቋል። ሁሉም ድሮኖች ከኢራቅ የተተኮሱ ናቸው፣ እሁድ በባራካ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ላይ የተተኮሱትን ጨምሮ።
የእስራኤሉ Jerusalem Post ጋዜጣ፣ እሁድ ዕለት በኤሜሬት የኒውክሊየር ማብላሊያ ግቢ መግቢያ በር አቅራቢያ፣ ከኢራቅ የተተኮሰ ነው በተባለ ድሮን፣ የደረሰውን ፍንዳታ "ከኢራን የተላከ የማስጠንቀቂያ መልዕክት" ነበር ብሎታል።
ኢራኖች በዚህ ጥቃት ማሳየት የፈለጉት፣ ኢራን ላይ ምንም ዓይነት ወታደራዊ ዘመቻ የሚከፈት ከሆነ፣ በምላሹ የአረቡን ዓለም የኒውክሊየር ጣቢያዎችን ከመምታት ወደ ኋላ እንደማይሉ ነው፣ እንደ ጋዜጣው ሪፖርት።
4 292
ጥቂት ስለዚህ ገጽ ማስታወሻ፡
ይህ ገጽ እንዲከፈት ትልቁን ሚና የተጫወተ እና በዚህ አጋጣሚ መመስገን አለበት ብዬ የምለው አንድ ሰው አለ። እርሱም መምህር ዘመድኩን በቀለ ነው።
ከዘመዴ ጋር ግንኙነታችን ወደ ኋላ ዓመታት ይሻገራል፣ በፌስ ቡክ ይጽፍ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ አውቀዋለሁ። በሳል ርዕሶችን ያነሳል፣ በዚያ ዙሪያ ረጃጅም ጽሑፎችን ይጽፋል። 'አያልቅበትም እንዴ ሐሳቡ' እል ነበር። ብዙ ጊዜ የፊደል እና የቃላት አሰበጣጠሩ ያስደንቀኛል። የጽሑፎቹ ይዘት እና ጥልቀት እንዲሁም የዓረፍተ ነገሮቹ ኳሊቲ በጣም ይስበኝ ነበር። መጣጥፎቹ ስለ ምንም ጉዳይ ይሁኑ፣ ብቻ ተደጋግመው እንዲነበቡ ኃይል ነበራቸው። በሂደትም መፃፍና ማንበብ፣ አማርኛን እንደ አዲስ፣ ከማውቀው በላይ፣ ተምሬበታለሁ ብል ማጋነን አይደለም።
በግሌ ዜናዎችን ከልጅነቴ ጀምሮ ማንበብና ማድመጥ፣ የየቀጠናውን ፖለቲካ ማወቅ፣ መከታተል እና በዚያ ዙሪያ መነጋገር በጣም የምወደው ነገር ነበር። በዚህም ምክኒያት ነው ከዘመዴ ጋር መደዋወል የጀመርነው።
ዘመዴ በመረጃ አሰባሰብ ጎበዝ ነው፣ ይጠይቃል ይቀበላል። ስለ መካከለኛው ምሥራቅ በሰፊው እናወራለን፣ ከሀገራችን ጋር በተያያዘም፣ ስለ ቀጠናው እንዲህ ነው፣ እንዲያ ነው እንባባላለን። በደንብ ነው የምንወያየው፣ እናም በእንዲህ ያለው በአንዱ ወቅት ላይ ነው፣ ዘመዴ 'ለምን ቴሌግራም ከፍተህ የምትነግረኝን ለሰፊው ሕብረተሰብ አታጋራውም' የሚል ሐሳብ ያመጣው። ከዚያም ይህ ፔጅ ተከፈተ።
እኔ በመጀመሪያ ደረጃ ሙስሊም ነኝ፣ በመቀጠል ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ከዚያም ነፍጠኛ ዐማራ ነኝ። ዘመዴ የመሠረተው የሠራዊተ-ጌድዮንም ከመጀመሪያዎቹ አባላት መካከል ነኝ። የምሥረታውን ዓላማ ስላመንኩበት እና ስለወደድኩት በደስታ የገባሁበት ማህበር ነው። ይሄ ሁሉ የማልለውጠው እኔነቴ እና መንገዶቼ ናቸው።
አረበኛ አነባለሁ፣ እንግሊዘኛውንም እንደዚያው እችላለሁ። በማቀርባቸው መረጃዎች በሙሉ ገለልተኛ ለመሆን እና ወገንተኝነት ላለመውሰድ እጥራለሁ። ምክኒያቱም መረጃ ለአንባቢያን ማቀበል ማለት፣ መረጃ ለአንባቢያን እንደወረደ ወይም ሳይነካካ ማድረስ ማለት ስለሆነ ነው ብዬ ስለ ማምን ነው። የግል አቋሞች፣ የግል ምልከታዎች ሊኖሩኝ ይችላሉ። እነዚያን አቋሞቼን ግን ዜና-ነክ በሆኑ መረጃዎች ላይ አላመጣም። ምናልባት ራሱን የቻለ ሌላ ገጽ በመክፈት ያንን ማንፀባረቅ ይቻል ይሆናል።
**
ሰብስክራይብ ስላደረጋችሁኝ ሁላችሁንም በጣም አመሰግናለሁ። መልካም ቆይታ እመኝላችኋለሁ።
4 292
Repost from ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…✍
ኬንያውያን አንድ ቀን ሳይሞላ ለአድማው ጥያቄ መልስ ተሰጥቷቸዋል።
ትናንት ረፋድ ላይ 15 ሺልንግ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተደረገብን ብለው፣ የመላው ኬንያ የትራንስፖርት ዘርፍ (የማታቱ አሽከርካሪዎችና የጭነት መኪና ማኅበራት) በጋራ ቆመው ሀገር አቀፍ የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ፣ መንገዶችን በመዝጋት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
ይህ ተቃውሞቸውም በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በኬንያ የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለሥልጣን (EPRA) ምላሽ ተሰጥቶታል።
4 292
🇺🇸🇮🇷⚡️ - ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ውስጥ ለነበራት ወታደራዊ ዘመቻ በ79 ቀን ውስጥ ከ$85 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አውጥታለች።
4 292
+1
🇺🇸🇮🇷 በኒው ዮርክ ታይምስ የተሰበሰበ የህዝብ አስተያየት እንደሚያመለክተው፣ 64% የሚሆኑት አሜሪካውያን ከኢራን ጋር ጦርነት መግጠም ስህተት ነበር ብለው እንደሚያስቡ ያሳያል።
የኢራን ጦርነት ለአሜሪካ መንግሥት፣ በተለይ ደግሞ ለትራምፕ ለራሱ፣ ያመጣው ጣጣ እጅግ ሰፊ እና ብዙ ነው።
ጦርነቱ የትራምፕን ስም በአክራሪ ደጋፊዎቹ ፊት ሳይቀር ያበላሸ ነው። ሪፐፕሊካንን ብሎም MAGAን ለሁለት የሰበረ ጦርነት ነው። ጦርነቱ፣ ትራምፕና ፓርቲው በዓመታቶች ልፋት ከተለያየ ስብጥር ወደ አንድ የሰበሰቡትን የሕብረተሰብ የድጋፍ መሠረት
የናደ ነው።
በአስተዳደሩ ልበ ሙሉ፣ ጠንካራና ቆፍጣና መስሎ የታየውን ትራምፕ፣ ጦርነቱ አኮስሶ አሳንሶታል። የሚዘውረው ሌላ የውጭ አካል እንዳለ፣ አዛዡና ሹፌሩ እሱ አለመሆኑን በአደባባይ ነው ጦርነቱ ያሰጣበት (ቢያንስ ብዙዎቹ የሚያስቡት እስራኤል ጠምዝዛው ነው፣ አስገድዳው ነው የሚለውን ትርክት ነው። እሱም ቢሆን፣ ይህን ትርክት በመካድና ፉርሽ በማድረግ ላይ ብዙ ርቀት ሄዷል።)
ትራምፕ በራሱ ቢሆን፣ ጦርነት አይኖርም ነበር። ከጅምሩ ትራምፕ ፀረ ጦርነት ነበር። የገፋው አካል ገፍቶ አስገብቶታል። በሌላ በኩል ደግሞ የቬኔዝዌላ በዚያ ሁኔታ መቅለል፣ለኢራን ሚሽኑ የልብ ልብ ሰጥቶትም ይሆናል፣ ኢራን ቬኔዝዌላ እንዳልሆነች ዘግይቶ ቢረዳውም።
በዚህም የተነሳ በሕዝቡ ዘንድ ያለው ቅቡልነት ዛሬ 30ዎቹ% አካባቢ ነው።
ወሳኝ የኮንግረስና ሴኔት ምርጫ በወራቶች ይጠብቁታል። ዲሞክራቶች እንደሚያሸንፉ ጥርጥር አይኖረውም። ቢሆንም ግን፣ ትራምፕ በማንኛውም መንገድ ከዚህ ጦርነት መውጫ መንገድ ፈልጎ በመውጣት ሊመጣበት ያለውን የፖለቲካ እና የስብዕና ክስረት ሱናሚ፣ በጥቂቱም ሊገድበው ይፈልጋል።
ዛሬ የወሰነው ውሳኔ ከዚህም ጋር የተያያዘ ነው።
4 292
🇷🇺 ፑቲን፦ "ሩሲያ እና ቻይና የዓለምን ባላንስ በማስጠበቅ ላይ፣ ወሳኝ የሆነ የማረጋጊያ ሚና ይጫወታሉ።
በተባበሩት መንግስታት፣ በSCO እና በBRICS ውስጥ በመተባበር፣ የዓለም አቀፍ ሕግን እና የተባበሩት መንግስታት ቻርተርን ያስጠብቃሉ።
በቅርቡ በቤጂንግ እንገናኝ።"
**
ፑቲን ከቻይና መንግሥት የቀረበለትን ግብዣ ተቀብሎ ነገ ማታ ቻይና ይገባል። ይህም፣ ከትራምፕ የቻይና ጉብኝት ጥቂት ቀናቶች በኋላ የመጣ ነው።
4 292
🇺🇸🇸🇦🇶🇦🇦🇪🇮🇷- AXIOS እንደዘገበው፣ ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔው ላይ ከመድረሱ አንድ ቀን በፊት፣ ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ከኳታር እና ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መሪዎች ጋር በስልክ ተነጋግሯል።
➡ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ከሦስቱ የባሕረ ሰላጤው ግዛቶች የተላከውን የጋራ መልእክት ገልጾታል። በአጭሩ፣ "ለድርድር ዕድል ስጡ ምክንያቱም ኢራንን ከመታችሁ ሁላችንም ዋጋውን እንከፍላለን" የሚል ነው።
➡️ ሁለተኛው ምንጭ ለAXIOS እንደጨመረው፣ ትራምፕ ለአንዳንድ ጦርነት አቀንቃኝ አጋሮቹ፣ ሦስቱ መሪዎች በኢራን ሊደርስ በሚችለው የበቀል እርምጃ “የነዳጅ እና የኃይል ተቋሞቻችን ሊፈነዱብን ይችላሉ” ብለው በግልጽ እንደተናገሩ ነግሯቸዋል።
በዚህም ምክኒያት ጦርነቱን ከማባባስ ታቅቧል።
4 292
🇺🇸❌🇨🇩🇺🇬🇸🇸— በኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት አሜሪካ ባለፉት 21 ቀናት ውስጥ በኮንጎ-ኪንሻሳ፣ በኡጋንዳ ወይም በደቡብ ሱዳን የነበሩ የውጭ ዜጎች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ እገዳ ጥላለች።
4 292
🇮🇱🇮🇷⚡️— የእስራኤል ቻናል 14 ዘጋቢ ሺሞን ሪክሊን፣ በኢራን ላይ ከሚደረገው ዘመቻ ጋር የተያያዙ ተግባራትን በተመለከተ ዛሬ በቀጥታ ስርጭት ላይ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ሳያወጣ እንዳልቀረ ተነገረ።
ሪክለን፣ በኢስፋሃን የኒውክሌር ጣቢያ ሊከናወን ስላለው የመሬት ላይ ወረራ ዝግጅቶች የሚገልጹ ዘገባዎችን ጨምሮ፣
የበለጸገ ዩራኒየምን ለማውጣት የኮማንዶ ኃይሎች ጣቢያውን በመውረር ልምምዶች ማካሄዳቸውን በዘገባው ተናግሯል።
እንዲሁም ሰማሁት ባለው መሠረት፣ በኢስፈሃን ውስጥ ዩራኒየም የያዙት ትቦዎች ሲባል እንደነበረው በጥልቀት ከመሬት በታች እንዳልተቀበሩ እና “ወደ ተቋሙ ከተገባ በኋላ እነዚህ ትቦዎች በቀላሉ ሊወጡ እንደሚችሉ እስራኤልና አሜሪካ ደርሰውበታል" ብሏል።
የእስራኤል ጦር ኃይሎች አዛዥ መረጃው ከሚዲያ ስርጭት ላይ በፍጥነት እንዲወገድ መጠየቃቸው ተሰምቷል።
የተቃዋሚ የሽ አቲድ ፖርቲ አባላትም የውጭ ጉዳይ እና የደህንነት ኮሚቴ ሊቀመንበሩ ቦዔዝ ቢስሙት፣ "በኢራን ውስጥ የዘመቻውን ስኬቶች ሊጎዱ የሚችሉ እና ለአገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ስትራቴጂካዊ ጉዳት የሚያስከትሉ እንዲህ ያሉ መረጃዎች አወጣጥን በተመለከተ፣ አስቸኳይ ውይይት እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ በተለይ ከኢራን ጦርነት ዋዜማ እና በኋላ፣ በእስራኤል የሚገኙ መገናኛ ብዙሃንና ሚዲያዎች "ከልክ ያለፈ ሳንሱር" እና "መታፈን" ያሉትን የሚዲያ ቁጥጥር ሲያወግዙ ይሰማሉ።
4 292
🇮🇷⚡️የኢራን መገናኛ ብዙሃን፡- የአሜሪካ በሀገሪቱ ላይ የጥቃት ስጋት እንደገና በተነሳበት ወቅት፣ ኢራናዊያን ሴቶች በጠመንጃ አያያዝ ዙሪያ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው።
አሜሪካውያን ኢራቅን ሲወሩ፣ ሴቶችን እና ሕፃናትን ጨምሮ ብዙ ሲቪሎች መገደላቸውን እና አስከፊ ጥቃቶች መፈጸሙን ማስታወስ ይገባል።
4 292
— 🇺🇸/🇮🇷 የቀጠናው ተንታኞች ትራምፕ ሰረዝኩት የሚለውን የኢራን ጥቃት በሦስት መንገድ ያዩታል፡-
1. ትራምፕ ዋሽቶ ነው፣ ለነገ ምንም የታቀደ ጥቃት አልነበረም፣ ይህ የግፊት ስልት ብቻ ነው።
2. ለነገ የታቀደ ጥቃት አለ፣ እና አላጠቃም በማለት ኢራንን ለማታለል እየሞከረ ነው (ማለትም ያጠቃል)።
3. የቀጠናው ሀገራት ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል እና ሁሉም የኢነርጂ መሠረተ ልማቶቻቸው እንዲወድሙ አልፈለጉም።
4 292
🇺🇸🦠 — ሪፖርተር፦ አሜሪካውያን ስለ ኢቦላ መጨነቅ አለባቸው?
ትራምፕ፦ እኔ ስለ ሁሉም ነገር እጨነቃለሁ።
አሁን በአፍሪካ ብቻ የተወሰነ ይመስለኛል።
