የቀጠናው ተመልካች
Kanalga Telegram’da o‘tish
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
4 294
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-137 kun
-8030 kun
Postlar arxiv
4 296
🇺🇸🇮🇱❌🇮🇷- አክስዮስ እንደዘገበው፣ ዶናልድ ትራምፕ እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ትናንት፣ ረጅም እና "አስቸጋሪ" የተባለ የስልክ ጥሪ አድርገዋል፣ በዚህ ጊዜ ሁለቱ መሪዎች ከኢራን ጋር ወደፊት በሚወሰደው መንገድ ላይ አልተስማሙም።
➡️ ትራምፕ ለኔታንያሁ፣ አስታራቂዎች ጦርነቱን በመደበኛነት ለማቆም እና የኢራንን የኑውክሌር ፕሮግራምም ሆነ የሆርሙዝ ወሽመጥን መከፈት የሚሸፍን እና የ30 ቀናት የድርድር ጊዜን ለመጀመር የሚያስችል ሰነድ ላይ እየሰሩ እንደሆነ ነግሮታል።
➡️ አንድ ምንጭ ከጥሪው በኋላ ኔታንያሁ "በጣም ከመበሳጨቱ የተነሳ ፀጉሩ የሚጨስ ይመስል ነበር" ብሎ የገለጸው ሲሆን፣ በዋሽንግተን የሚገኘው የእስራኤል አምባሳደር የኔታንያሁን ስጋቶች ለአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ማሳወቁ ታውቋል።
➡️ በተጨማሪም ኔታንያሁ ከትራምፕ ጋር ፊት ለፊት ለመገናኘት በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ ዋሽንግተን ጉብኝት ማቀዱ ተገልጿል።
4 296
🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 'በኢራን ውጥረት ምክንያት የእስራኤል ጦር ሠራዊት ከፍተኛ የዝግጅት ደረጃ ላይ ይገኛል' የእስራኤል የጦር ሠራዊት አዛዥ ኢያል ዛሚር።
ከኢራን ግጭት ጋር በተያያዙ እየተባባሱ ለመጡ ስጋቶች ወታደሩ ከፍተኛው የዝግጅት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ማስጠንቀቂያው የተሰጠው፣ የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ሠራዊት፣ IRGC፣ በቀጠናው ውስጥ የግጭት መባባስ ሊኖር እንደሚችል ከዛተ በኋላ እና የሰላም ስምምነት ካልተደረሰ አሜሪካ እንደገና ጥቃት ልትሰነዝር እንደምትችል ምልክት ከሰጠች በኋላ ነው።
4 296
🇮🇷⚔️🇺🇸🏴☠️ የኢራን የፓርላማ አፈ ጉባኤ ሙሐመድ ባገር ጋሊባፍ፦ “የጠላት ግልጽ እና ስውር እንቅስቃሴዎች አዲስ የጦርነት ዙር እየፈለጉ መሆናቸውን ያሳያል። ሕዝባችን፣ ወታደራዊ ኃይሎቻችን አቅማቸውን እንደገና ለመገንባት የተኩስ አቁም ዕድሉን በተሻለ ሁኔታ እንደተጠቀሙበት እርግጠኞች መሆን ይችላሉ" ብሏል።
ይህን ያለው ዛሬ IRGC በመግለጫው ኢራን 'ምንም አይነት ጥቃት ከተፈፀመባት የቀጠናውን ሀገራት በጦርነት አዙሪት ውስጥ ትከታለች…ተያይዘን እናልቃለን እንጂ ብቻችንን አንሄድም' ካለ በኋላ ነው።
በሌላ በኩል፣ የእስራኤል መንግሥት በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ሆስፒታሎች በፍጥነት ወደ አደጋ ጊዜ አሠራር እንዲገቡ አሳስቧል።
በእስራኤል አሜሪካ ጦርነቱን በማንኛውም ሰዓት ልትጀምረው ትቸላለች የሚል ሰፊ ግምት አለ። የኔታንያሁ መንግሥት፣ እስራኤል ወደ ጦርነት ለመመለስ ሙሉ በሙሉ ዝግጅቷን ጨርሳ እየጠበቀች እንደሆነ ገልጿል።
4 296
— 🇮🇱/🇮🇷 ሂዝቦላ፣ ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ በሰሜን እስራኤል 2 የአይረን ዶም ማስወንጨፊያዎችን ሲመታ የሚያሳይ የድሮን ተንቀሳቃሽ ምስል ለቅቋል።
ጥቃቶቹ የተካሄዱት ከሁለት ሳምንታት በፊት በተሳካ ሁኔታ ዒላማ በተደረገበት በጃል አል-አላም ወታደራዊ ጣቢያ ላይ ነው።
ሥፍራው፣ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ጥቃት የደረሰበት ሆኖ ሳለ፣ እስራኤል ማስወንጨፊያዎቹን ወደ ሌላ ቦታ ለምን እንዳላንቀሳቀሰች ምንም ፍንጭ የለም።
ሂዝቦላ፣ ምንም እንኳን ከሌሎች አንፃር ወደ ድሮን ውጊያ የገባው ዘግይቶ ቢሆንም፣ አጠቃቀም ላይ ልምድ እያገኘ እና አሁን ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ዒላማዎች እየመታ ያለ ይመስላል።
በFBV ድሮን ዉጊያ ዩክሬን፣ ሩሲያ እና ኢራን ከማንኛውም ሀገራት በላይ በአሁኑ ሰዓት መጥቀውበት ይገኛል።
**
የ$100 ሚሊዮን ዶላር መሳሪያን በ $300 ዶላር ድሮን።
4 296
⚡️🇧🇭🇪🇬🇮🇷የባህሬን ባለስልጣናት "ለኢራን ርህራሄ በማሳየት" ክስ፣ 6 ግብፃዊያን ዜጎች ላይ የ10 ዓመት እስራት ፈርደዋል።
በባሕረ ሰላጤው ሀገሮች፣ በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ፣ ለኢራን ትንሽም የሐዘን ወይም የርህራሄ ስሜት ማሳየት ወይም ኢራን ሲባል ከንፈር መምጠጥ የሚያስከስስ ወንጀል ከሆነ ወራት ተቆጥሯል።
የፖኪስታን መንግሥት በእነዚህ ሀገሮች፣ በተለይ በUAE፣ የሚኖሩ በሺ የሚቆጠሩ ፓኪስታናውያን፣ በእንዲህ ያሉ አላግባብ ክሶች ምክኒያት ወደ ሀገራቸው ተጠርዘው መባረራቸውን ማውገዙ ይታወሳል።
4 296
⚡️🇬🇧 ፦ የዩናይትድ ኪንግደም ቻንስለር ራቼል ሪቭስ ከኢራን ጦርነት ጋር በተያያዘ እየጨመረ ባለው የነዳጅ ወጪ ላይ ጫና እየጨመረ ባለበት ወቅት፣ የነዳጅ ቀረጥን እንደማታሻሽል እና በሴፕቴምበር የሚከናወን የ1pc (የብሪትሽ አንድ ሳንቲም) በሊትር ጭማሪን እንደምታስቀር ይጠበቃል።
ዜናው እንደዘገበው፣ መንግሥት በሚቀጥሉት ወራት የታቀደውን ሰፋ ያለ በደረጃ የሚከናወን በሊትር የ7 ሳንቲም (5pc) ጭማሪን ለማስወገድም እያሰበ ነው።
ይህ እርምጃ የተወሰደው የጭነት እና የሎጂስቲክስ ቡድኖች እየጨመረ ያለው የነዳጅ ዋጋ የአሠራር ወጪዎችን በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደገ እንደሆነ እና በመላው የዩናይትድ ኪንግደም ኢኮኖሚ ላይ ሰፊ የዋጋ ግሽበትን የማስነሳት አደጋ እንዳለው ማስጠንቀቂያ በሰጡበት ወቅት ነው።
4 296
+2
🇺🇸🇮🇱📞👑❌🇮🇷— ኒው ዮርክ ታይምስ እንደዘገበው አሜሪካ እና እስራኤል የቀድሞውን የኢራን ፕሬዝዳንት ማህሙድ አህመዲነጃድን በጦርነቱ የመጀመሪያ ቀናቶች ላይ፣ ለመሾም አቅደው ነበር።
➡ ጦርነቱ በተጀመረበት ጊዜ በእስራኤል ጥቃቶች የኢራን አያቶላህ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከተገደሉ ከቀናት በኋላ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን “ውስጥ ያለ አንድ ሰው” ሀገሪቱን ቢቆጣጠር የተሻለ እንደሚሆን በይፋ ተናግረዋል።
➡️ አሜሪካ እና እስራኤል ወደ ግጭቱ የገቡት አንድን የተወሰነ እና በጣም አስገራሚ የሆነ ሰው በአእምሯቸው ይዘው እንደሆነ ታውቋል፣ ማህሙድ አህመዲነጃድን።
➡️ በጠንካራ አቋሙ፣ 'እስራኤልን ከምድረ ገፅ አጠፋለሁ' በሚለው ታዋቂ ንግግሩ፣ እና በአሜሪካ ተቃዋሚ አመለካከቶቹ የሚታወቀው የቀድሞው የኢራን ፕሬዝዳንትን፣ ስልጣን ላይ ሊያወጡት አሜሪካና እስራኤል ዝግጅታቸውን ጨርሰው ነበር።
➡ ነገር ግን በእስራኤላውያን የተዘጋጀው እና አህመዲነጃድ የተማከሩበት ደፋር እቅድ፣ "መንገዱን ስቶ ተበላሸ" እንደ ዋይት ሃውስ ከፍተኛ ባለስልጣን። በዚህም መሠረት ሳይሳካ ቀረ።
➡ አህመዲነጃድ በቴህራን በሚገኘው ቤቱ በቁም እስር ላይ ነበር። ከቤቱ እስር ነፃ ለማውጣት፣ በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ፣ በእስራኤል በተወሰደው የድብደባ እርምጃ ቤቱ በስህተት በመመታቱ ቆሰለ። በዚህም የተነሳ ሁሉም ነገር ተበላሸ።
➡️ የእስራኤልና የአሜሪካ ባለስልጣናት አህመዲነጃድ ከጥቃቱ በሕይወት መትረፉን ተናግረዋል፣ ነገር ግን ከአደጋ በኋላ በአገዛዙ ለውጥ እቅድ ተስፋ ቆርጧል።
📝 ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በይፋ አልታየም፣ አሁን የት እንዳለ እና ሁኔታውም አይታወቅም።
🔗 ምንጭ፦ The NewYork Times
4 296
🇮🇷 ኔቶ በሆርሙዝ ወሽመጥ ወታደራዊ "ተልዕኮ" ላይ እየተወያየሁ ነው አለ።
- የኔቶ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለብሉምበርግ እንደተናገሩት፣ የውሃ መተላለፊያው እስከ ሐምሌ መጀመሪያ ድረስ ካልተከፈተ፣ ኔቶ መርከቦች በታገደው የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲያልፉ በመርዳት ላይ አንድ እርምጃ ይወስዳል።
- ሀሳቡ የበርካታ ኔቶ አባል ሀገራትን ድጋፍ አግኝቷል፣ ነገር ግን አስፈላጊውን የጋራ ስምምነት እስካሁን አላገኘም።
- በሐምሌ 7-8 በአንካራ በሚደረገው የብሎኩ መሪዎች ስብሰባ ላይ፣ ውሳኔ ሊወሰን ይችላል ተብሏል።
4 296
🇺🇸- የዛሬ ምሽቱ የኬንተኪ ግዛት የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ተሸናፊ፣ ፀረ እስራኤሉ ሪፐብሊካን፣ ቶማስ ማሲ፣ መሸነፉን ባመነበት ንግግር ላይ፣ ሕዝቡ "2028 2028" እያለ መጮህ ከጀመረ በኋላ በ2028 ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደር ፍንጭ ሰጥቷል፣ እሱም "አሳማኝ ክርክር አቅርባችኋል" ብሏል።
4 296
🇮🇱 🇺🇸 በአሜሪካ የእስራኤል የድጋፍ ማህበር፣ AIPAC፣ በ X ላይ
"የአሜሪካ የባሕር ኃይል ልዩ ወታደር የነበረው Ed Gallrein፣ ፀረ-እስራኤል የሆነውን ተወዳዳሪ Thomas Massie ስላሸነፍክ እንኳን ደስ አለህ!" "እስራኤል-ወዳጅ አሜሪካውያን፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ጠንካራ ህብረትን የሚደግፉ እጩዎችን መደገፍ እና እሱን ለማዳከም የሚሰሩትን ማሸነፍ፣ በመቻላቸው ኩራት ይሰማቸዋል።" "የእስራኤል ደጋፊ መሆን ጥሩ ፖሊሲ እና ጥሩ ፖለቲካ ነው!"📎 AIPAC
4 296
+2
⚡️🇺🇸 ኤድ ጋለሬን (የእስራኤል ደጋፊ እና የኢራን ጦርነት ዋና አቀንቃኝ) በኬንታኪ 4ኛ ዲስትሪክት የመጀመሪያ ዙር ምርጫ፣ ቶማስ ማሲን (ፀረ ጦርነት-ፀረ እስራኤል)ን አሸንፎታል።
ቶማስ ማሲ ወንበሩን በማስጠበቅ ላይ ዳግም ለመመረጥ የሚሮጥ ከፍተኛ የሪፐብሊካን ተፅእኖ ፈጣሪ እጩ ነበር።
በመጀመሪያዎቹ አካባቢ የትራምፕ ወዳጅ የነበረው ማሲ፣ በሂደት የትራምፕን ፖሊሲዎቹን እየተቃወመ በመሄድ ከትራምፕ ጋር፣ በተለይ በኢራን ጦርነት እና በኤፕስቲን ፋይል፣ ሊጣላ ችሏል። በዚህም ምክኒያት ትራምፕ ለማሲ ተቀናቃኝ ድጋፉን በመስጠት ዛሬ ማታ እንዲሸነፍ አድርጎታል።
ቶማስ ማሲ እንዲሸነፍ የአይሁዳዊያን ገንዘብ ለጋሾች ሚና ከፍተኛ ነበር። በዚህ የተነሳ እሱም በፀረ እስራኤል አጀንዳ ላይ ሮጧል።
የእሱ ሽንፈት ለትራምፕ ትልቅ ድል ሆኖ ተመዝግቧል። በሌላ በኩል ከትራምፕ MAGA ለተገነጠሉት ሪፐብሊካኖች፣ ትልቅ ሽንፈት ነው።
በዛሬው ምሽት በመላ ሀገሪቱ ትራምፕ የደገፋቸው የሪፐብሊካን ዕጩዎች፣ ከሞላ ጎደል ሁሉም አሸንፈዋል።
በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ፣ አሁንም ቢሆን፣ ከእስራኤል በተቃራኒ መቆም ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍል ጉዳይ እንደሆነ ይህ ምርጫ አሳይቷል፣ ተጽኖአቸው ከበፊቱ የተሸረሸረና የቀነሰ እንኳ ቢሆንም። በሌላ በኩል፣ በሪፐብሊካኖች ዘንድ የትራምፕ ተደማጭነት ዛሬም ከፍተኛ እንደሆነ ታይቶበታል።
4 296
+2
🇺🇸🚫🇮🇷CBS NEWS የአሜሪካ ባለስልጣናትን በመጥቀስ፦ በቅርቡ የተደረገ የደኀንነት ግምገማ እንደሚያሳየው፣ የአሜሪካ ኃይሎች በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ ከ10 በላይ የባሕር ውስጥ ፈንጂዎች እንደተቀበሩ ያምናሉ።
በዚህም የተነሳ የአሜሪካ ጦር አቅዶ የነበረውን የመርከቦች እጀባ ለጊዜው እንደተወ ለመርከብ ኩባንያዎች አሳውቋል።
ኢራን 5000 የባሕር ውስጥ ፈንጂዎች አላት ተብሎ ይገመታል። እነዚህ ፈንጂዎች የተለያየ ዓይነት ይዘትና ባህሪ ያላቸው ሲሆን፣ በብዛት ኢራን የምትጠቀመው ባሕሩ ወለል ላይ የሚቸነከሩትንና የመርከቡን አፍንጫና እንቅስቃሴ አሽትተው የሚፈነዱትን ነው።
አንዳንዴም ከባሕሩ ጠለቅ ብለው የሚንሳፈፉትን እንደምትጠቀም ይነገራል።
የባሕር ፈንጂዎችን በተመለከተ ትልቁ ችግር፣ ወሬው ነው። ሳይኖር እንኳ አለ ከተባለ፣ በአካባቢው ዝር ሚል መርከብ አይገኝም።
የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት የዓለምን ኢኮኖሚ፣ በተለይ ደግሞ የባሕረ ሰላጤውን ሀገራት፣ እያላሸቀ ይገኛል። በዚህ ዓይነት ቅርቃር ውስጥ ከአሁን በኋላ ለተወሰነም ጊዜ ቢሆን መቀጠል፣ ለአካባቢው ትልቅ ችግር ያመጣል።
አሁን ላይ እነዚህ ሀገራት ምርታቸውን እያመረቱ እና እየሸጡ አይደለም። እየኖሩ ያሉት ያላቸውን saving እየበሉ ነው። ያ ደግሞ ይመናመናል።
4 296
🇺🇸🤝🇸🇾 🇸🇾🇺🇸⚡️ — ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሶሪያው ፕሬዝዳንት አህመድ አል-ሻራአ ሽቶ ልኮለታል። የሶሪያው ፕሬዝዳንት ስጦታውን አመስግኖ በX አካውንቱ ልባዊ ምስጋናውን አቅርቧል።
አንዳንድ ግንኙነቶች ትዝታን ይተዋሉ፤ የእኛ ግን የሚመስለው ጥዑም ሽታን የተወ ነው ። አቶ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ ስለ ልግስናዎ እና ይህንን ውድ ስጦታ ሰጥተው ስለዘከሩኝ አመሰግናለሁ። የዚያ ግንኙነታችን መንፈስ (ያለፈው የመጀመሪያው የዋይት ሃውስ ጉብኝቱ) በሶሪያ እና በአሜሪካ መካከል የበለጠ ጠንካራ ግንኙነት መቅረጹን ይቀጥል።
4 296
🇺🇦 በጣም ተወዳጅ በሆነው የዩክሬን የቴሌቪዥን ቻናል ላይ፣ የሞቱ የዩክሬን የጦር ኃይሎች አባላት ወደ ማዳበሪያነት እንዲቀየሩ እና በእነሱ ላይ ፓርኮች ወይም ሰብሎች እንዲበቅሉ ሀሳብ ቀርቧል።
ይህም በዩክሬን ከፍተኛን ትችት እያስተናገደ ነው።
"ለአስክሬኑ ጥላ ዛፍ እንተክላለን፣ ሰው እየሞተ የሞተበት ቦታ ችግኝ እንተክላለን ቢያንስ አስከሬኑ ጥላ እንዲኖረው።"
4 296
🇮🇷⚡️🇺🇸 አሜሪካ ከኢራን ጋር ለ40 ቀናት በዘለቀው ጦርነት ቢያንስ 42 አውሮፕላኖችን አጥታለች - ኮንግረስ
ፔንታጎን እነዚህን የአቪዬሽን ንብረቶች እና የጦር መሳሪያዎች ለመተካት የሚያስፈልገው አጠቃላይ ወጪ በግምት 29 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ገምቷል።
4 296
🇷🇺 የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላደምር ፑቲን ለኦፊሴላዊ ጉብኝት በዚህ ሰዓት ቻይና ገብቷል።
ጉብኝቱ የትራምፕን የቻይና ጉብኝት ተከትሎ የመጣ ነው። ዩክሬን፣ ኢራን፣ ወታደራዊ ግንኙነት እና ኢኮኖሚ የጉብኝቱ ዋና አጀንዳ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
4 296
🇺🇸🇨🇺—አሜሪካ “የአሜሪካንን ብሔራዊ ደህንነት አደጋ ላይ ጥለዋል” ብላ በመክሰስ 11 የኩባ ባለስልጣናት እና 3 የመንግሥት አካላት ላይ ማዕቀብ ጥላለች።
**
በኩባ ላይ ላለፉት 50 ዓመታት ሙሉ የኢኮኖሚ ማዕቀብ አለ።
አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ሩቅ ምሥራቅ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ ኤስያ፣ መካከለኛው አሜሪካ፣ አፍሪካ፣ ላቲን አሜሪካ …አጠቃላዩ ዓለም የንግድም፣ የኢኮኖሚም፣ የፖለቲካም፣ የማሕበራዊ ግንኙነትም ከኩባ ጋር በዚህ ምክኒያት አያደርግም።
ኩባ የቀራት አንድ ወዳጅ ቬኔዝዌላ ነበር። ነፃ ነዳጅ ይሰጣቸዋል፣ በዚያ እያረሱ፣ እያመረቱ ይኖሩ ነበር። ከቬኔዝዌላ መወገድ በኋላ፣ የኩባ እንጀራ ተቆርጧል።
አሜሪካ ብቻዋን አውላላ ሜዳ ላይ አግኝታታለች።
ኩባ፣ በመጨረሻ ልትንበረከክ እና እጅ ልትሰጥ ጫፍ የደረሰች ይመስላል።
4 296
🇮🇱⚡🇱🇧 የእስራኤል የገንዘብ ሚንስቴር በዛሌል ስሞትሪች፡- "ሂዝቦላ እጅ የማይሰጥ ከሆነ ብዙ ብዙ ተጨማሪ የሊባኖስን መሬት መያዛችንን እንቀጥላለን።"
በትናንትናው ዕለት፣ የዓለም አቀፍ ወንጀለኛ ፍርድ ቤት፣ ሚስጥራዊ የእስራት ማዘዣ በሚንስትሩ ላይ 'በጋዛ ላይ ለፈፀመው ወንጀል' በሚል ክስ፣ እንዳወጣበት ተሰምቷል፣ እንደ ሮይተርስ ዘገባ።
ስሞትሪች በምልከታው እጅግ ቀኝ ዘመም ፖለቲከኛ ሲሆን የእስራኤል ድንበር ሙሉ ጋዛን ጨምሮ ደቡብ ሶሪያን እና ደቡብ ሊባኖስን እንዲሁም ጥንታዊ ይዞታዎቻችንን ማጠቃለል አለበት የሚል ነው።
4 296
— 🇺🇸/🇮🇷 የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ካዜም ጋሪባዲ፦
'አሜሪካ ለዲፕሎማሲ እድል እየሰጠች እንደሆነ ትናገራለች፣ ነገር ግን በተመሳሳይ ጊዜ በሌላ ጥቃት ታስፈራራለች።
እንድንሸነፍ ሊያደርጉን ይፈልጋሉ፣ ግን አይችሉም። መሸነፍ የለም።
ማጥቃት ይችላሉ፣ ያጥቁ። ወይ እኛ እናሸንፋለን፣ ወይም ሰማዕት እንሆናለን [ሁለቱም ድል ናቸው]።'
