fa
Feedback
​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

​🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹

رفتن به کانال در Telegram

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
1 383
مشترکین
+624 ساعت
+3437 روز
+63530 روز
آرشیو پست ها
​قَدْ جَاءَتْكُمُ الْجُمُعَةُ فَأَكْثِرُوا مِنَ الصَّلَاةِ عَلَى النَّبِيِّ ﷺ (የጁመዓ ቀን መጥቷልና በነቢዩ ﷺ ላይ ሰላዋት ማውረድ አብዙ ​اللَّهُ
+1
​قَدْ جَاءَتْكُمُ الْجُمُعَةُ فَأَكْثِرُوا مِنَ الصَّلَاةِ عَلَى النَّبِيِّ ﷺ (የጁመዓ ቀን መጥቷልና በነቢዩ ﷺ ላይ ሰላዋት ማውረድ አብዙ
​اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ ​በዚህ የተቀደሰ ቀን በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰላዋት ማውረድን አንርሳ። በዛሬው ዕለት ወደ አላህ በዱዓ እንቃረብ፣ አላህም ዱዓችንን ይቀበለን። አሚን
የነቢዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ከተማ የሰላም ምንጭ ናት።
ለሁላችሁም መልካም የጁመዓ ቀን ይሁን ​#Jummah #Madina #MasjidAlNabawi #Islam #EthiopianMuslims #ጁመዓ #መዲና #ሰላዋት

📜ኪታቡ በ PDF ❝ለደስተኛ ሕይወት ጠቃሚ መንገዶች❞ الوسائل المفيدة للحياة السعيدة የሸይኽ ዐብዱረሕማን ብኑ ናሲር አሲዕዲ 1376 ሂ

❝ለደስተኛ ሕይወት ጠቃሚ መንገዶች❞ الوسائل المفيدة للحياة السعيدة ➠ ክፍል 11 የ መጨረሻ ክፍል

❝ለደስተኛ ሕይወት ጠቃሚ መንገዶች❞ الوسائل المفيدة للحياة السعيدة ➠ ክፍል 10

❝ለደስተኛ ሕይወት ጠቃሚ መንገዶች❞ الوسائل المفيدة للحياة السعيدة ➠ ክፍል 9

❝ለደስተኛ ሕይወት ጠቃሚ መንገዶች❞ الوسائل المفيدة للحياة السعيدة ➠ ክፍል 8

❝ለደስተኛ ሕይወት ጠቃሚ መንገዶች❞ الوسائل المفيدة للحياة السعيدة ➠ ክፍል 6

❝ለደስተኛ ሕይወት ጠቃሚ መንገዶች❞ الوسائل المفيدة للحياة السعيدة ➠ ክፍል 6

❝ለደስተኛ ሕይወት ጠቃሚ መንገዶች❞ الوسائل المفيدة للحياة السعيدة ➠ ክፍል 5

❝ለደስተኛ ሕይወት ጠቃሚ መንገዶች❞ الوسائل المفيدة للحياة السعيدة ➠ ክፍል 4

❝ለደስተኛ ሕይወት ጠቃሚ መንገዶች❞ الوسائل المفيدة للحياة السعيدة ➠ ክፍል 3

❝ለደስተኛ ሕይወት ጠቃሚ መንገዶች❞ الوسائل المفيدة للحياة السعيدة ➠ ክፍል 2

❝ለደስተኛ ሕይወት ጠቃሚ መንገዶች❞ الوسائل المفيدة للحياة السعيدة ➠ ክፍል 1

✍ እናቱን ለሚወድ ብቻ 🎂ደርሰሽ ለጡረታ የዘጠኝ ወር ቤቴ ኑሪልኝ እናቴ የደስታ ማጀቴ ውስጤ ነሽ አንጀቴ 🍢 እማየ🍢 ችግር አይቅረብሽ ኑሪ በደስታ ተፈጥሮሽ ልዩ ነው የጀሊል ስጦታ ሀቅ፣ሽን መጠበቅ ዛሬ ላይ ብረታ በእጀ ላንከባክብሽ ደርሰሽ ለጡረታ ⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤ 🎤 በወንድም አቡ ሹራ አህመድ ካሳየ ቻናሏን እናሳድጋት👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Sobabilalmesjid/4645 https://t.me/Sobabilalmesjid/4645

የቂረዓት ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት ☎️ በኡስታዝ አደም ኢብራሂም ሀፊዘሁሏህ ተ         ጀ                   መ                              ረ ገባ ገባ በሉ ሸር ሸር አድርጉ ለእህቶች ብቻ https://t.me/Asslfyaa https://t.me/Asslfyaa

⚠️ተውሒ! ተውሒድ! ተውሒድ!❗️ "ሙስሊም ዘንድ ያለው ውድ ነገር ተውሂድ ነው። የሰው ልጆች ዓይናቸውን ከሚጠብቁት በላይ፣ ውድ ሀብቴ የሚሉትን ነገር ከሚጠብቁት በላይ፤ ተውሂዳቸውን ሊጠብቁ ይገባል። ሀብትና ስልጣንን ከሚፈልጉት በላይ ተውሂድን ሊፈልጉ ይገባል። ⚠️ በዱንያም በሰላም የሚኖረው፣ የውስጥ ሰላምንና መረጋጋትን ማግኘት የሚቻለው በተውሂድ ስለሆነ ነው። ከሞት በኋላ ባለው ሕይወትም በሰላም መኖር የሚቻለው፣ የጀነት ደረጃዎች ላይ መውጣት የሚቻለው በተውሂድ ስለሆነ ነው። ⚠️ ሰዎች ድህነትን፣ የዱንያ እሳትን፣ አውሬንና ጠላትን ከሚፈሩት በላይ፤ የተውሂድ ተቃራኒ የሆነውን ሽርክ ሊፈሩና ሊጠነቀቁ ይገባል። በአላህ ያሻረከ፣ ከአላህ ውጭ ባለ አካል በማረድ ሊሆን ይችላል፤ ለቀብር ጠዋፍ በማድረግ ሊሆን ይችላል፤ ከአላህ ውጭ ያለ የሞተንና የበሰበሰን አካል 'ድረስልኝ፣ ከጭንቅ አውጣኝ' በማለት ሊሆን ይችላል፤ ለጂኒ በማረድ ሊሆን ይችላል፤ ጠንቋይን 'የሩቁን ያውቃል' ብሎ አምኖ በመቀበል ሊሆን ይችላል። የሽርክ ዓይነቶች ብዙ ናቸው። ⚠️ በአላህ ያሻረከ የተውሂድን ብርሃን ያጣል። የሠራውን ያህል መልካም ሥራ ቢሠራ፣ አንድ ሰው እሱ ጋር ሽርክ ካለ፣ ተውሂድ ከሌለው ሥራው ተቀባይነት አያገኝም። ከዚያ በፊትም የሠሯቸው መልካም ሥራዎች ካሉ፤ ሽርክ ከተተገበረ፣ ሽርክ ላይ ከወደቀ፣ ሽርክ ከሠራ አንድ ሰው የሠራው መልካም ሥራ ሁሉ ዋጋ ያጣል። የበተነ አቧራ ይሆናል፤ የፈሰሰ ውኃ ይሆናል። ⚠️ ስለዚህ ሙስሊም የሆነ፣ የጀነትና የጀሃነም ምንነት የገባው በሙሉ ከሽርክ ሊጠነቀቅ፣ ተውሂድን ነቅቶ ሊያውቅና ሊጠብቅ ይገባል። የተውሂድን ሙሉነት ከሚያሳጡ ነገሮችና ተውሂድን ከሚጎድሉ ነገሮች ሊርቅና ሊጠነቀቅ ይገባል።" t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

#እህቴ__ሆይ! ተግባርሽ ካላማረ + ከነበርሽበት እስካልተቆጠብሽ አው ርግፍ አድርገሽ እስካላቆምሽ ድረስ! 👉መሸፈንሽ (ኒቃብ መልበስሽ) ብቻ! መቶበትሽን (ከመጥፎ ነገር መራቅሽን) አያመለክትም! �
#እህቴ__ሆይ! ተግባርሽ ካላማረ + ከነበርሽበት እስካልተቆጠብሽ አው ርግፍ አድርገሽ እስካላቆምሽ ድረስ! 👉መሸፈንሽ (ኒቃብ መልበስሽ) ብቻ! መቶበትሽን (ከመጥፎ ነገር መራቅሽን) አያመለክትም! 👉ለብሰው ያለበሱ እኔ የማላያቸው የሳት ማቀጣጠያ የሆኑ ሴቶች አሉ! መባሉን አስታውሽ! ምን መሰላችሁ? #አላህ ካዘነላቸው ውጭ! አንዳንድ እህቶች! እንዲህ ይላሉ:- 👉አሁንማ ቶብቸ ተሸፍኜ (ኒቃብ) ለብሻለሁ! ከወንዶች ጋ አላወራም + አልቀራረብ + አልፈትንም ይላሉ! 👉ላኪን! በአካልም ሆነ በስልክ ሲያወሩ ሲፈፅሙት/ሲተገብሩት ይታያል! ሌላው 👉ሙዚቃ + ፊልም ተከፍቶ ያያሉ + ይሰማሉ አብው ያንጎራጉራሉ! 👉ደግሞም ይላሉ ትውስታ ነው ያኔ ከመቶበቴ /ከመሸፈኔ በፊት ከነ ፉላን ጋ ስንት life ቀጭተንበታል መሰላችሁ ይላሉ!! ወንጀል እንደ ዝና ይወራልን?? አላሁመስታዓን!!! እህቴ! 👉ከቶበትሽ የቶበትን ሸርጡ አውቀሽ ቶብች! ስትሰሪው/ስተገብሪው ከነበርሽበት መጥፎ ተግባር ተቆጠቢ! 👉አላህን ፈርተሽ ወንጀልሽን አስታውሰሽ አልቅሰሽ ዱዓ አድርጊ እንጂ! ☞ ስንት life ቀጭቸበታለሁ እያልሽ ወንጀልሽን እንደ ደህና ነገር ዝና መስሎሽ አታውሪ!! 👉ከላይ ጂስምሽን እንደ ሸፈንሽው ኒቃብ + ሂጃብ… … ልብሽንም + ንግግርሽንም በመልካም ነገር በቁርዓን + በሀድስ ከመጥፎ ነገር ሸፍኒው! So… ……………… ገብቶሻል! 👉ተሸፍነሽ /ቶብቻለሁ ብለሽ! በድብቅም ሆነ በግልፅ ፊልምን በማየት + ሙዚቃ በማዳመጥ + አጂ ነብይ ጋ በማውራት… ……… አላህን አትመጭ!! ወላሁ ተዓላ አዕለም!!

📩 ለእኛ... ለሁላችንም የተላከ መልእክት     ሁላችንም በውስጣችን መልካም ቤተሰብ የመመሥረት ትልቅ ሕልም አለን። ሁላችንም ልባችን በተመሳሳይ ምኞት ይረታል፤ ነገ መልካም ልጆች እንዲኖሩን፣ መልካም ባል ወይም መልካም ሚስት እንድንታደል እንመኛለን። ነገር ግን... ለአንድ አፍታ ቆም ብለን ራሳችንን እንጠይቅ! አሁን እኛ ማን ነን? በምንስ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው??? እኛ ወንዶች... ዓይናችንን ከባዕድ ሴቶች (ለእኛ ካልተፈቀዱ) እየከለከልን ነው? ሰላታችንን በወቅቱ እና በጀማዓ በመስጊድ እየሰገድን ነው?እኛ ሴቶች... ከሸሪዓዊ ሂጃብ ጋር ያለን ቁርኝት የት ላይ ነው? ከሰላታችን... በተለይም ከፈጅር ሰላት ጋር ያለን ጥንካሬ ምን ያህል ነው? ከሰዎች ጋር ያለን ሙዓመላ (ግንኙነት)፣ ታማኝነታችን እና ፈተናዎችን የመቋቋም ትዕግሥታችንስ? እስከ መቼ ነው አላህ የማይወደውን የሐራም ግንኙነት እና ንግግሮች ውስጥ የምንጣደው? እኛ በውስጣችን የምንደብቀውን ምስጢር አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው። አዎ! ሁላችንም መልካም ቤተሰብ የመመሥረት ሕልም አለን፤ ነገር ግን ለውጡን መጀመሪያ ከራሳችን መጀመር እንዳለብን ለምን ይዘነጋናል?እኛ ሴቶች... ባላችን ወደ ሌላ ሴት እንዳያይ እንመኛለን፤ ነገር ግን እኛ ራሳችን ለሌሎች ወንዶች መፈተኛና የስሜት መነሻ እየሆንን ከሆነ እንዴት ይሆናል? "ምንዳ (ዋጋ) ከሥራው ዓይነት ጋር ተመሳሳይነው" (የዘራነውን ነው የምናጭደው)። እኛ ወንዶች...ልጆቻችን መልካም እና ሳሊህ እንዲሆኑ እንመኛለን፤ ነገር ግን እኛ ራሳችን ለእነሱ የሚከተሉት ቀጥተኛ አርአያና ምሳሌ ሳንሆንላቸው እንዴት መልካምነታቸውን እንጠብቃለን? ስለዚህ ወንድሜ ሆይ ፣ እህቴ ሆይ ...እኛ ሁላችንም የተሻለውን የዲን ቤተሰብ ለመገንባት የለውጡ መጀመሪያ (ዋናው ዘር) እንሁን። ጅማሬው እኛው ራሳችን ነን...። https://t.me/+SpJHRe6JfQQ0NGI0