fa
Feedback
هداية القلوب (የልቦች መሪ)

هداية القلوب (የልቦች መሪ)

رفتن به کانال در Telegram

https://t.me/httpYelbochMeriQuran

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
228
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+177 روز
+1530 روز
آرشیو پست ها
📲በጅምዓ ቀን ዱአ ተቀባይነት ያለበት ሰዓት !! ☑️ ከአቡ ሁረይራ ተይዞ ቡኻሪና ሙስሊም እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፦ 【ጅሙአ ቀን ውስጥ ዱአ ተቀባይነት ያለባት አንዲት ሰአት አለች። አንድ ሙስሊም ያንን ሰአት እየሰገደ ወይም ጌታውን መልካም ነገር እየጠየቀ አያገኘውም፦ አላህ የለመነውን ሁሉ የሰጠው ቢሆን እንጂ።】 ▪️ይህንን ወቅት በተመለከተ መቼ ነው በሚለው ጉዳይ በኡለማዎች መካከል ብዙ አስተያየቶች ቢሰነዘሩም ከመረጃ አንፃር ግን ይበልጥ ተስፋ የሚደረግባቸው ሁለት ሰዓታቶች እንዳለ ጠቁመዋል። እነሱም፦ ①) ኢማሙ ኹጥባ ለማድረግ ሚንበር ላይ ከወጣበት ሰአት ጀምሮ ሶላቱ እስኪጠናቀቅ ድረስና ②) ከአስር ሶላት በኋላ ፀሀይ እስክትጠልቅ ብለዋል ☑️በነዚህ ሁለት ሰዓቶች ላይ ዱአ ልናበዛ ይገባል። https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk

የቁርአን ግብዣ በቃሪዕ ሰዐድ አል-ጋምዲ   የቴሌግራም ቻናል https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk

ዜና እና ፖለቲካዊ ትንታኔ ላይ ምኞትን ማቀላቀል ራስን መሸወድ ነው ~ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከሃምሳ ዓመታት በላይ ያስተማረ ዴቪድ ቻፕል የሚባል በሙያው አንጋፋ የሆነ የታሪክ መምህር ነበር። ነበር ያልኩት አሁን ይኑር አይኑር መረጃ ስለሌለኝ ነው። አንዴ ስለ ታዋቂው የፈረንሳይ መሪ ናፖሊዮን ቦናፓርቴ እያስተማረ ወደ ሩሲያ የላከው ጦር የገጠመውን ሁኔታ ያነሳል። ናፖሊዮን የሩሲያን ጦር በቅጡ ያልተደራጀ፣ በቂ ወታደራዊ አቅምና ልምድ የሌለው ልፍስፍስ አድርጎ ነበር የሳለው። በርግጥ የሩሲያ ጦር እንደዚያ አልነበረም። ነገር ግን ናፖሊዮን እንደዚያ እንዲሆን ፍላጎቱ ስለነበር ነው በዚያ መልኩ የተረዳው፣ አለ ቻፕል። የማይረሳኝ ንግግር። ምኞትና እውነታ ይለያያልና አውሮፓን ያንቀጠቀጠው የናፖሊዮን ጦር ሩሲያ ገብቶ እንደ ጨው ቀለጠ። በታሪክ እጅግ አሰቃቂ ከሚባሉ ሽንፈቶች ውስጥ አንዱ ሆኖ ተመዘገበ። የናፖሊዮን ውድቀት ሀ ብሎ የጀመረበት ወሳኝ የታሪክ እጥፋት ነበር። የዚህ ሁሉ ውድቀት መነሻ መሬት ላይ ያለን እውነታ ከግላዊ ምኞት ጋር ማቀላቀል ነበር፣ እንደ ቻፕል ገለፃ። አሁን ይህንን ያስታወሰኝ ወቅታዊውን የአሜሪካ፣ እ $ራeል እና ኢራን ጦርነት ጋር ተያይዞ ጉዳዩን የሚዘግቡና የሚተነትኑ እንደ አሸን የፈሉ "ተንታኞችን" ሁኔታ ሳስብ ነው። በአብዛኛው መሬት ላይ ያለውን እውነታ ሳይሆን ምኞትና ፍላጎታቸውን አደባልቀው ነው የሚተነትኑት። የሚገርመው ካለፉ ክስተቶች አለመማራቸው ነው። የሐማስ እና እ $ራeልን ጦርነት አስመልክቶ ልክ እንዳሁኑ ምርቃና የተጫጫነው ትንታኔ ሲያቀርቡ ነበር። አገር እየወደመ፣ አእላፍ ነፍስ እየረገፈ ዋናውን ምስል ጥለው ጥቃቅን ነጠላ ጀብዱዎችን ተራራ አሳክለው ይዘግቡ ነበር። ፍፃሜው ያው የምናውቀው ነው። በምርቃና የተሞላው ትንታኔ መጨረሻው ያው እንደተለመደው የዐረብ ሃገራት መሪዎችን በመሳደብና በመራገም ይጠናቀቃል። አሁንም ተመሳሳይ አካሄድ እየሄዱ ነው። ኢራን በከፍተኛ ሁኔታ እየፈራረሰች ነው። መሪዎቿ በጥቂት ቀናት ውስጥ ታድነው ተመተዋል። የምርቃና ዘጋቢዎች እንደሚዘግቡት ባደባባይ በጀግንነት እየተዋጉ አይደለም ያለቁት። የደህንነት መዋቅራቸው በጠላት እጅ ስለ ወደቀ፣ መገናኛ መንገዶቻቸው ስለተጠለፉ ነው በቀላሉ የታደኑት። ይሄው አሁን የተረፉት ከመሬት በታች ስለተደበቁ ለፈላጊ እንኳ ማግኘት አስቸጋሪ ሆነዋል እየተባለ ነው። እስካሁን ከተኮሰቻቸው ሚሳኤሎችና ድሮኖች ውስጥ ወደ እ $ራeል የተኮሰችው 15% ብቻ ነው። ቀሪው 85% ወደ አሜሪካ የጦር ሰፈሮች ከተኮሰችው ውጭ እንዳለ በዐረብ ሃገራት ላይ ነው የዘነበው። ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው ቁጥር ወደ ኢማራት ነው የተተኮሰው። ሆኖም ግን ኢራን ካስወነጨፈችው አጠቃላይ መጠን ውስጥ ከ85% እስከ 96% ኢላማውን ሳይመታ ወይም መሬት ላይ ሳይደርስ ከሽፏል። ከፋርስ / ዐረብ ባህረ ሰላጤ ማዶና ማዶ የደረሰው የንብረትም ሆነ ሰብአዊ ኪሳራ ለንፅፅር የሚቀርብ አይደለም። የአየር ክልሏ ሙሉ በሙሉ በጠላት ቁጥጥር ስር ሆኖ እንደሳቸው እየፈነጩበት፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ እያረሱት ነው። የባህር ኃይሏ እንዳለ ወድሟል። የኢነርጂ ማዕከላት ላይ ከባባድ ጥቃቶች ተፈፅመዋል። የመሳሪያ ማምረቻዎችና ማከማቻዎች ኢላማ ተደርገዋል። የምታስወነጭፋቸው ሚሳኤሎችና ድሮኖች መጠን በጣም እያነሰ እያነሰ መጥቷል። ማስተዋል ለፈለገ ይሄ የሚናገረው ሐቅ አለ። ይህ ሁሉ ከመሆኑም ጋር አሁንም ኢራን እያሸነፈች እንደሆነ የሚተነትን አለ። ምኞት ወ ፍላጎት። እውነታው ግን ሌላ ነው። ለኢራን ወግኖ ከደቡብ ሊባኖስ የሚናኩሰውን ሒዝበላህን ለማደን ሊባኖስ እንደ ሃገር ከባድ ድብደባ እየደረሰባት ነው። ከዚህም አልፎ የእ$ራeል ጦር ወደ ሌባኖስ ዘልቆ የገባ ሲሆን የያዘውን ሰፊ ክልል በቁጥጥር ስር አድርጌ እቆያለሁ ብሏል። የምርቃና ተንታኞች ግን ሒዝበላህ አልተቻለም እያሉ ነው። ካጠቃላዩ ውጤት ይልቅ አልፎ አልፎ በሚታዩ ነጠላ ክስተቶች ነው የሚፈነድቁት። የሃገሪቱን ከ8% እስከ 10% የሚደርስ ግዛት አሳልፎ ሰጥቶ ከዚያ ሒዝበላህ አልተቻለም ይባላል። የማይካደው ሐቅ ጦርነቱ እነ እ $ራeል እና አሜሪካ አቅደውት እንደገቡት የቀለለ አይደለም፣ ህልማቸውንም በቀላሉ ያሳኩታል ተብሎም አይጠበቅም። ወይ አላማቸውን እስከሚያሳኩ ድረስ ብዙ ዋጋ ይከፍላሉ። አለያ ደግሞ ረጅሙን ህልማቸውን ሳይወዱ በግድ ሰብስበው ያሳጥራሉ። በቀጠናው አልፎም በዓለም አቀፍ ደረጃ የጦርነቱ ትኩሳት ከተገመተው በላይ እንደሆነ እየታየ ነው። ወላፈኑ እኛም ጋር ደርሶ እየሞቅነው ነው። ጦርነትን ማጠናቀቁ እንደ መጀመሩ አይቀልም። ሩሲያ በአጭር ጊዜ አጠናቀዋለሁ ብሎ በኡክሬን ላይ የጀመረችው "ልዩ ዘመቻ" ይሄው አራት ዓመታትን ደፈነ። የኢራኑንም ፍፃሜ ዛሬ ላይ ማንም ፍጡር እርግጠኛ ሆኖ አያውቀውም። የፅሁፌ ዋና ጭብጥ ምኞትና ፍላጎታቸውን አደባልቀው በሚተነትኑ የምረቃና ተንታኞች አትሸወዱ የሚል ነው። እውነት እና ምኞ ይለያያሉ። ክስተቶችንና ወሳኝ ምክንያቶችን (factors) ተመርኩዞ የቢሆን ትንታኔ መስራት፣ ታሪክ መፃፍ እና ዜና መዘገብ፣ የተከሰተን ጉዳይ እና ምሁራዊ ግምቶችን ሳያዛንፉ ማቅረብ እንጂ ስሜትና ምኞትን እያደባለቁ እራስን ማስደሰት አይደለም። በጋዛ ጦርነት ጊዜ ዋናው ቁሳዊ ውድመት አይደለም እያሉ የሃገር ውድመትንና ሰብኣዊ እልቂትን እያቃለሉ ሐማስ አሸንፏል እያሉ ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል። ዛሬም እንደ ብዙዎቹ ትንታኔ ኢራን እያሸነፈች ነው። እንዳ'ፋችሁ ያድርገው እላለሁ። ለኢራን አላህ የሐማስ አይነት፣ የጋዛ አይነት "ድል" ያጎናፅፋት። ትልቁን ሰY^ ጣን እ $ራeልንም ከነ ምግዚቷ እስከ ወዲያኛው አከርካሪያቸውን ይስበራቸው እላለሁ። ፅሁፌ ከብዙዎች ፍላጎት እና ከተጋቱት ፕሮፖጋንዳ ጋር እንደማይገጥም ይገባኛል። ግን ብዙ መጠበቅ በከባዱ ቅስምን ይሰብራልና በስሱም ቢሆን መርምሩ፣ ከሰመሆናችሁ ውጡ ሁኑ እላለሁ። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

🔥የሃራም ፍቅር ምሳሌው ከረሚላ ውስጥ እንዳለ ምላጭ ነው።! ውስጣችንን እያጨለመው፣ ከአላህ እያራቀን ነው ሚሄደው፣ ማስመሰልም የተሞላበት የውሸት ፍቅር ነው።‼️
🔥የሃራም ፍቅር ምሳሌው ከረሚላ ውስጥ እንዳለ ምላጭ ነው።! ውስጣችንን እያጨለመው፣ ከአላህ እያራቀን ነው ሚሄደው፣ ማስመሰልም የተሞላበት የውሸት ፍቅር ነው።‼️

የቁርአን ግብዣ በቃሪዕ ያሲር አድ-ዶሳሪ       የቴሌግራም ቻናል https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk

እኔ ከሞትኩ በኋላ .... ◃◃◃◃◃◃◃◃◂◂◂◂◂◂◃◃◃◃◃◃ ይህች ዱንያ እኔ ካለፍኩ በኋላ ምን ትመስል ይሆን የሚለው ነገር ካሳሰበህ አንድ አንተ የምታውቀው ሰው ከሞተ በኋላ ምን እንደምትመስል አስተዉል። የምትወደው ወዳጅህ ሞተ። ብዙም ሳይቆይ ተረሳ። ዱንያ በሱ ሞት ምክንያት አልሞተችም፤ አልከሰመችም። ሰዎችም በተለመደው መደበኛ እንቅስቃሴያቸው ላይ ናቸው። ሥራህ ላይ አተኩር። ሥራህ ያስወሳሃል አልያም ያስረሳሃል። 🎒https://t.me/alruqyehsheriyeh 🎒https://t.me/alruqyehsheriyeh

Repost from N/a
(رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ.) አሁን ያላችሁበት ጥሩ ሁኔታ ወደ አላህ ፈላጊ ከመሆን አያግዳችሁ።ሁሌም ዱዓእ አድርጉ። በበራፉ ላይ ብዙ ቁሙ፣እስኪከፈትላችሁ ድረስ አንኳኩ። አላህ ሆይ ወደእኔ ለምታወርደው መልካም ነገር ሁሉ ፈላጊ ነኝ። #ማስታወሻ

ሸር አድርጓት ቻናላችን እናሳድጋት በእኛ ሰበብ አንድ ሰው ወደ ኸይር ቢመራ ያሰው በሚማረው ልክ አጅሩ ሳይቀነስ ይሰጣቾኋል አሏህ ሁሌም ወደ መልካም ነገር ተጣሪወች አመላካቾች ያድርገን

🌸 ከሴቶች ሁሉ ቆንጆ ማለት ነጭዋ ጠቆር ያለችው  ረጅሟ  አጭሯ ሰማያዊ ወይም የማር ቀለም ዓይን ያላት ረጅም ወይም አጭር ጸጉር ያላት ወይም ደግሞ ጉንጯ ላይ ጉድጓድ (Dimples) ያላት አይደለችም። ​🌸 ከሴቶች ሁሉ ቆንጆ ማለት እራሷን የጠበቀችና ለእሷ ብሎ የደከመውን አባቷን (ወይም ባሏን) ሽበት የምታከብር ናት። ​🌸 ከሴቶች ሁሉ ቆንጆ ማለት ጌታዋን የምትፈራ በስነ-ምግባሯና በስኬቷ የቤተሰቧን ስም ከፍ የምታደርግ ናት በልብሷ ወይም በውጫዊ ውበቷ ሳይሆን ውበቷ ስነ-ምግባሯና ሀያዕ (እፍረት) የሆነላት ናት። ​🌸 ከሴቶች ሁሉ ቆንጆ ማለት በንፅህናዋ በሀያዕዋና በቅንነቷ እህቶቿን የምትጠብቅ ናት። ከሴቶች ሁሉ ቆንጆ ማለት ​ተኳኩላ ተቀባብታና ተሸሽላ በሰው ፊት የምትታይ አይደለችም። ቆንጆ የምትባለው ውበት ማለት በአስተዳደግ በመልካም ስነ-ምግባር፣ በንጹህ ልብና በኢስላም እውቀት ላይ ነው። ​እውነተኛዋ ቆንጆ፣ ደግ፣ ውድና እንደ እንቁ የምትታየው ሴት ይችው ናት https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk

ربي لا تذرني فردا وانت خير الوارثين ጌታየ ብቻየን አትተወኝ አንተ ከወራሾች ሁሉ መልካሙ ነህ 💧ህመም ከባድ ነው ፈውስ ይፈልጋል  ያአሏህ  ብለን ጉዳያችንን መዘርዘር የሚቅተን በብዙ ነገር የታመምን ሰወች አለን ያረብ ...ያረብ ...ያረብ.. የልመናየን ተዓምር  በቅርቡ አሳየኝ አሏህየ ያረሂም https://t.me/ani_saa_as_selefya6025

#ክፍል 2 የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር አጫጭር ምክሮች ማውጫ። ⓵⓪⓵ የኢማን ወንድማማችነት ⓵⓪⓶ የዘመናችን ኸዋሪጆች ⓵⓪⓷ ግብይት ላይ ናታለል ⓵⓪⓸ ዒልምን ከማን እንማር ⓵⓪⓹ ሰውን በትናንቱ ማንነት ⓵⓪⓺ መውቀስ ⓵⓪⓻ የሰው ሀቅ ⓵⓪⓼ ብድር ⓵⓪⓽ መውሊድና ኢብኑ ⓵⓵⓪ ተይሚያህ ⓵⓵⓵ በእሳት መቅጣት ⓵⓵⓶ አራጣ ⓵⓵⓷ ሪያዕ ⓵⓵⓸ ሰው በርከት ሲል ዒባዳ ⓵⓵⓹ ላይ መነሸት ⓵⓵⓺ የወለድ ብር ተቀብሎ ⓵⓵⓻ ለሚስኪን መስጠት ⓵⓵⓼ አጉል ይሉኝታ ⓵⓵⓽ ፀጉርን ማበላለጥ ⓵⓶⓪ ዝሙት ⓵⓶⓵ የዳዕዋ አካሄድ ⓵⓶⓶ ፀጉርን መላጨት ⓵⓶⓷ ኩፋሮችን መኻለፍ ⓵⓶⓸ ሴቶች ⓵⓶⓹ ተሸቡህ ⓵⓶⓺ ታዋቂ ሰዎች ⓵⓶⓻ በመጥፎ ሰዎች ⓵⓶⓼ ⓵⓶⓽ መመሳሰል ⓵⓷⓪ ወንድ ሆኖ የሴት ሆርሞን ያለው ⓵⓷⓵ ያለ እውቀት መናገር ⓵⓷⓶ ሙሾ ማውረድ ⓵⓷⓷ የሸሪዓ ህግ ⓵⓷⓸ ጠንቋይ ⓵⓷⓹ ወንጀልን በዝርዝር መናገር ⓵⓷⓺ መጥፎ ገድ ⓵⓷⓻ በሽታ ⓵⓷⓼ ለሰዎች ተስፋ መስጠት ⓵⓷⓽ ቃልቻ ማለት ጠንቋይ ማለት ነውን? ⓵⓸⓪ ኮከብ ቆጣሪ ⓵⓸⓵ በቪድዮ ማሰተማር ⓵⓸⓶ ቀብርን እኩኩል ማድረግ ⓵⓸⓷ ውሻን መያዝ ⓵⓸⓸ በፎቶ ዙሪያ ዘርዘር ያለ ዳሰሳ ⓵⓸⓹ ኹጥባ ላይ አቀማመጥ ⓵⓸⓺ ሰይዲ ብሎ መጥራት ⓵⓸⓻ በግብይት ላይ መማል ⓵⓸⓼ መሀላን መጠበቅ ⓵⓸⓽ በፍጡር መማል ⓵⓹⓪ መሀላ ⓵⓹⓵ ኸጢቦች ⓵⓹⓶ በሙአዚን መበሳጨት ⓵⓹⓷ ተብዲዕና ተክፊር ⓵⓹⓸ ንግግርን ለማሳመር መጣር ⓵⓹⓹ ልክን ማወቅ ⓵⓹⓺ ምክር ለተማሪዎች ⓵⓹⓻ የተወሰኑ ጥያቄዎችና መልሶች ⓵⓹⓼ ኢስላም የጥፋት በሮችን ዘግቷል ⓵⓹⓽ ህመም ⓵⓺⓪ ባርነት በኢስላም ⓵⓺⓵ በቆመ ውሃ ላይ መሽናት ⓵⓺⓶ አቡ ሱፍያንና አር-ሪሳላ ፊልም ⓵⓺⓷ ባሏ የሞተባት ሴት ⓵⓺⓸ በወንድም ላይ ማጨት ⓵⓺⓹ በሸሪዓ ቅጣት ላይ ማማለድ ⓵⓺⓺ ቀብር ላይ መገንባት ⓵⓺⓻ ሰርግ ላይ መሳሪያ መተኮስ ⓵⓺⓼ ሽቶ በስጦታ የተሰጠው ሰው ⓵⓺⓽ ሚዲያ ⓵⓻⓪ ወረርሽኝ ⓵⓻⓵ ዑመር ⓵⓻⓶ ሰውን ከፊቱ ማደናነቅ ⓵⓻⓷ ስለ ረመዳን ⓵⓻⓸ ወሊይ ⓵⓻⓹ ትንሹ ሺርክ ⓵⓻⓺ የማይመሽበት ሀገር ላይ ሶላት ⓵⓻⓻ የሩቅ ሚስጥራት ⓵⓻⓼ የተቀበረ ብር ፍለጋ ⓵⓻⓽ ስስታምነት ⓵⓼⓪ የዑለሞች ሞት ⓵⓼⓵ ኸምር ⓵⓼⓶ የረመዳን ባሪያ ⓵⓼⓷ በፈተና ግዜ ⓵⓼⓸ በረካ ⓵⓼⓹ የደጃል ፈተና ⓵⓼⓺ የአላህ ሲፋ ⓵⓼⓻ ስለ ተውሒድ ሲወራ ⓵⓼⓼ ከልም የወጣ አለባበስ ⓵⓼⓽ ረመዳንን እንዴት  እናሳልፍ ⓵⓽⓪ እንግዳ ነገር ⓵⓽⓵ ፆም ማለት ⓵⓽⓶ ኒያ ⓵⓽⓷ ምቀኝነት ⓵⓽⓸ ራስን በራስ ማርካት ⓵⓽⓹ ትዳር፣ፍቺና ልጅ ማሳደግ ⓵⓽⓺ የሰለፎች መንገድ ⓵⓽⓻ ብልትን መንካት ⓵⓽⓼ መልካም ስነ ምግባር ⓵⓽⓽ የዲንና የአቅል ጎዶሎ ⓶⓪⓪ ውለታን መካድ ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!!

وَتَوَكَّلْ عَلَى الْعَزِيزِ الرَّحِيم አሸናፊ አዛኝ በኾነው (ጌታህ) ላይም ተጠጋ፡፡ ኢላሂ! በኔ ጉዳዬች ላይ አደራህን!* ኢላሂ! ሙሉ የሆነ ውክልና ላንተ ብቻ የተገባ ነው! https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk

انتَبه أنتَ مُراقَب.pdf16.45 MB

+5
ክፍል 1 በሙሐመድሲራጅ ሙሐመድኑር https://t.me/MerkezulimamiAhmed

አዲስ የሕይወት ስንቅ፦🫀 ቀልቡን ሰሊም 🕊 አላህ (ﷻ) እንዲህ ይላል፦ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ "ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረጋጋሉ።" https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk

አዳእ ወደዋእ ክፍል 1⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/649 ክፍል 2 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/673 ክፍል 3⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/691 ክፍል 4 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/717 ክፍል 5 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/729 ክፍል 6 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/749 ክፍል 7⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/765 ክፍል 8⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/788 ክፍል 9⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/809 ክፍል 10⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/827 ክፍል 11⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/848 ክፍል 12⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/860 ክፍል 13⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/886 ክፍል 14⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/901 ክፍል 15⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/931 ክፍል 16⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/974 ክፍል 17⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/994 ክፍል 18⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/1019 ክፍል 19⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/1032 ክፍል 20⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/1058 ክፍል 21 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/1113 ክፍል 22 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/1137 ክፍል 23 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/1155 ክፍል 24 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/1183 ክፍል 25 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/1220 ክፍል 26 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/1239 ክፍል 27 ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/1268 ክፍል 28 የመጨረሻው ⤵️ https://t.me/Sle_qelbachn1/1288

Repost from Amru Islamic App
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」 ╭┄┈┈⟢ ┊❏ አድ-ዳእ ወድ-ደዋእ ( ሙኽተሶር ) ╰───────────────╯     ╭🎙የደርሱ አቅራቢ:- ╎────⟢ ╎🎧 ኡስታዝ አቡ ሱፍያን ╰────────────── ┍📎 የዳውንሎድ ሊንክ: │ │https://t.me/AmruislamicApp/10 ├⎙  አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ! └─────────── ╭╼────────⟢ ┆📘 መሰል ጠቃሚ 📞 አፖችን ማሰራት ┆የምትፈልጉ በ 🔖 @Amuse6 ┆የቴሌግራም አድራሻችን ይንገሩን! ╰┈┈ ╭  ለመሰል ስራዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉን ┆ ┆ @AmruIslamicApp ╰╼──────────────╯ 🔖 T.ME/MULTEQA_SELEFIYIN 🔖 T.ME/MULTEQA_SELEFIYIN

يَا مُقَلِّبَ الْقُلُوبِ ثَبِّتْ قَلْبِي عَلَى دِينِكَ" ያ ሙቀሊበል ቁሉብ ሰቢት ቀልቢ ዐላ ዲኒክ 🫀ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታ ሆይ! ልቤን በዲንህ (በእምነትህ) ላይ አጽናልኝ። https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk

ሂወታችንን ከፖስታችን ጋር  አታያይዙት አህባቢ     ሰው  እውቀቱ እንደሚፖስተው ፕሮፋይል እንደሚቀያይረው ቢሆን ኑሮ   የት በደረሰ     ሁሉም ሰው     የየራሱ ተሰጥኦ አለው ግን ደግሞ ቁርአን ስንፖስት ይችእኮ ሀፊዝ ናት ባገባት ኑሮ         የሆነ ነገር ስንፖስት ይች እኮ ጀግናናት     የኔ በሆነች   አትበሉ    ወሬና ተግባር ይለያያል ለማለት ነው ሲቀጥል ደግሞ  እስቶሪ በሚለቀቅ ስአት    ስለሂወቷ የለቀቀች እየመሰላችሁ   እከሊት  ዛሬ ለቃለች  ከባሏ ተፋታለች ከእከልዬ ተጣልታለች አትበሉ      ሂወት እኮ ሚስጥር ነው    እንደት  ስለሂወቷ እስቶሪ ትፖስታለች ብላችሁ ታስባላችሁ      አንዳንዶቻችን የተሸወድንበት ስለሆነ ብዬ ነው  የነገርኳችሁ 🙌 ቻናል https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk